ጥያቄ፩
አንድ በምስል ማንሻ ወይም በCamera) የሚነሳ ምስል ላይ የምስል አስቀሪው ወይም የ(Photographer) ሚና ምንድን ነው? የተነሳውን ምስል የሚያየው ሰው የተነሳው ነገር ምን እንደሚመስል ማሳየት ብቻ ነው ወይስ ምን?
መልስ ፩
እኔ የምስሉን ውበት እና እውነት.... ኀሣብ አክዬበት ባስመለክት ደስ ይለኛል! መቼም እንደ ሀገሬ ሰው ደግሶ ሲበሉለት ሲጠጡለት ደስ እንደሚለው ኹሉ እኔም እዩልኝ ብዬ ያመጣሁትን አንድ ምስል ተመልካች በምን መስፈርት ያይልኝ ይኾን? ብዬም አስባለሁ። ዘዎትር ግን በዚህ ሙያ ውስጥ ከእውነት ጎን ብቆም ደስ ይለኛል።
''ምስል'' እውነት ነውና።
ሚኪያስ ልየው/Mikiyas liyew
ታኅሣሥ ፳፻፲፬

ልክ የህክምናውን አገልግሎት ጨርሼ ስወጣ ''እግዚአብሔር ይማርህ''
ነበረ ያለቺኝ!
አሜን! ''አሁን ተሽሎኛል''።
ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
አዲስ አበባ,ኢትዮጵያ
፳ ፡ ፬ ፡ ፳፻፲፬ዓ.ም
ወደ መንገደኞች |To Travlers
#Peoplesofaddis #ወደመንገደኞች #Totravlers #Selfproject
@Mykeyonthestreet

ከመንገዱ ምስሎች መካከል አንዱ ይኽ ነው።
አመሻሹ ላይ ይኽ ቦታ ቅልጥ ያለ ገበያ ነው። አትክልት የተባለ ከጥቂቶቹ በስተቀር እዚህ ይሸጣል። መንገደኛው ኹሉ ያማረውና ያሻውን በቻለው መጠን ይገዛል።
ይኽ የዕለት ተዕለት የመንገዱ ግብር ነው። ቀልቤን የገዛኝ ግን ይኽ ኹናቴ ነው ፤ ነጋዴዎቹ ጋሪ ላይ ዘርግተው ከሚሸጡት አትክልቶች መካከል አንዱ ''ሙዝ'' ነው። ደጋግሜ እንደተመለከትኩት አብዛኛው ወደ ቤቱ የሚገባ መንገደኛ የሚገዛው ይኽንኑ ሙዝ ነው። ነጋዴዎቹ የሚሸጡትን ሙዝ ጥራትና ጣዕም ለማሳየት እና ለማስቀመስ ወደ አጠገባቸው ጠጋ ላለው መንገደኛ ፈቃዱን እንኳን ሳይጠይቁ አገዳ የሚያክለውን ሙዝ ''ላጥ ላጥ'' አድርገው ( ይኸው ቅመሱት) ሲሉም ተመልክቻለሁ።
ይቺ የተላጠች አንድ ፍሬ ሙዝ ናት በአፅንኦት ቀልቤን የገዛችው። የብዙኀኑ ግብር ነውና ለውክልና የሚበቃው ፥ መንገደኛው ኹሉ የቀመሳትን የአንድ ፍሬ ሙዝ ልጣጭ ለሙዝ ሻጩ ነጋዴ መልሶ ይሰጠዋል። ይመስለኛል ነጋዴዎቹ ከጋሪዎቻቸው ግርጌ ላይ ልጣጭ የሚያስቀምጡበትን ጥቁር ፌስታል ተመልክተው ኖሯል ፤ እሱ ውስጥ እንዲከቱት ነው የሚሰጧቸው ብዬ ነው የገመትኩት። ይኽን ልምድ በዛ ያለ መንገደኛ ጋር አስተውዬዋለሁ። የማታው የተለመደ ዑደት ይኽ ነው።
ጠዋት ላይ ላይ እኔ ማታ ለማሳያነት ሲላጡ ካየኻቸው ጣፋጭ ሙዞች (መጣፈጡን በመገመት ነው) ገሚሱ በፌስታል ግማሹ ደግሞ መሐል አስፓልት ላይ ተከምሮ አየዋለኹ።
ይህን ስመለከት ታድያ የእኔ አዕምሮ የጠየቀው ጥያቄ ይኽ ነው ፥
''ማታ ሙዝ ከገዙት መንገደኞች መካከል ምን ያኽሉ ጣዕሙን ለመለየት ከቀመሱት አንድ ፍሬ ሙዝ ልጣጭ ጋር ጠዋት ላይ ተገናኝተው ይኾን?''
ሌላ ጥያቄ ፤ ''ወደ ሥራ ለመሄድ ሲጣደፉ ካጣጣሙት ሙዝ ልጣጭ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው የወደቁና ጉዳት የደረሰባቸው መንገደኞችስ ይኖሩ ይኾን?''
ይኽን የሚመልስልኝ እና ምስክርም ለመኾን የሚበቃው ትላንትና መንገደኞቹ ጣዕም ሲለኩበት የነበረው ዛሬ ደግሞ አስተውሎታቸው ሲለካ የነበረበት ራሱ ''መንገዱ'' ብቻ ነው።
የመንገዱ ምስል ይገርመኛል ፤ ይደንቀኛል።
ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
አዲስ አበባ,ኢትዮጵያ
፳፮፡ ፬ ፡ ፳፻፲፬ዓ.ም
#Ethiopia #Addisabeba #Totravlers #ወደመንገደኞች #Selfproject

የልጅነቴ ምስል ይመስለኛል ፤ ብቻ ሳስበው ጣዕሙ ከጎረቤታችን እስከ ቤተሰብ ድረስ ያለው የስነስርዓት ያዝ እና የ እረፍ ባህል ጣዕም ነበረው። ከባህል ፣ ከዕድሜ ፣ ከእምነት አንፃር የማደርጋቸው ነገሮች ተመዝነው ልክ ካልሆኑ ''ተው ፣ እረፍ ፣ስነስርዓት ያዝ''ያሉኛል። ዛሬም አለሁ። አድጌ..ዓለሁ ብል እንኳን ይኽን ልምድ እንደ ትውልድ አሳድጌዋለው ወይ?
አብርሆት ቤተ መፅሐፍት ደጃፍ ላይ የተነሳ ምስል ነው።
ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
አዲስ አበባ/Addisabeba
ጥር ፪ ፳፻፲፬ዓ.ም
#Ethiopia #Addisabeba #Totravlers #ወደመንገደኞች #Selfproject
አብርሆት ቤተ መፅሐፍት ደጃፍ ላይ የተነሳ ምስል ነው።
ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
አዲስ አበባ/Addisabeba
ጥር ፪ ፳፻፲፬ዓ.ም
#Ethiopia #Addisabeba #Totravlers #ወደመንገደኞች #Selfproject
PHOTO EXHIBITION AND EVENT ዘና•ነቃ•ስራ
PHOTO EXHIBITION
January 13-15/2022
EVENT
January 15/2022
ቅዳሜ 8:00 Local time
@Mykeyonthestreet
@Mykeyliyew
https://www.tgoop.com/tolobuna
PHOTO EXHIBITION
January 13-15/2022
EVENT
January 15/2022
ቅዳሜ 8:00 Local time
@Mykeyonthestreet
@Mykeyliyew
https://www.tgoop.com/tolobuna