Telegram Web
ቴሌግራም እንደ ቲክቶክ ገንዘብ የምንሰራበትን Telegram Stars የተሰኘ Gift Coin አምጥቷል።

ቴሌግራም ይህን ነገር ለማስተዋወቅ Major በተሰኘ Airdrop መጥቷል። አሁን ላይ ሰው invite በማድረግ በቀላሉ የቴሌግራም Star Coin መስራት ትችላላቹህ።

አሁኑኑ ጀምሩት


https://www.tgoop.com/major/start?startapp=835671370
👍7🔥3
#AddisAbaba #NationalExam

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም ” - ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪ ወላጆችና ከተማሪዎች ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ስለተጠየቀበት የበየነ መረብ (ኦንላይን) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱን ጠይቋል።

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ምን አሉ ?

“ ፈተና በሁለት አይነት መልኩ (በኦንላይንና በወረቀት) ይሰጣል።

በኦን ላይን የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲ ላይ ተመድበው የነበሩ አብርሆት ላይብረሪና ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ይሆናሉ።

የተቀሩት ግን በሁሉም በግልም በመንግስም መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩ ት/ቤቶች ሆኖ በተመደቡበት (ድልድል የወጣላቸው ት/ቤቶች ያውቃሉ) መሠረት ፈተናውን በወረቀት ይወስዳሉ።

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱት፦
- በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ 
- በሲቪል ሰርቪስ
- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 
- በአዲስ አበባ ሳይንሰና ቴክኖሎጂ
- በጳውሎስ ሚሊኒየም የተመደቡ በዚያ ይወስዳሉ።


እንዲሁም፣ በአብርሆት ላይብረሪ ላይ የተመደቡ ተማሪዎች፣ የሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኦንላይን ይወስዳሉ።

የቀሩት ግን በሌላ መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩት ስለታጠፈ በወረቀት ይወስዳሉ።

በወረቀት የሚወስዱት ዩኒቨርሲቲ ነው የሚገኙት በባለፉት ሁለት አመታት እንደተሰጠው ማደሪያቸውም፣ መዋያቸውም፣ መፈተኛቸውም እዛው ይሆናል። አድረው ሲጨርሱ ነው የሚወጡት።

በኦንላይን የተመደቡት ግን ውሎ ገብ ነው። ተፈትነው ወደ ቤታቸው ሂደው አድረው ተመልሰው በጠዋት መጥተው ይፈተናሉ። ” ብለዋል።

የተፈጠረው ውዝግብ ምንድን ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፥ “ የተፈጠረ ነገር የለም። በድብልቅ መንገድ እንደምንጥ ታሳቦ ነበረ። እሱን ነበር ስንለማመድ የነበረው ” ነው ያሉት።

“ አሁን More እርግጠኛ በተኮነበት መፈተኛ ጣቢያ (ከላይ በተገለጹት) ብቻ ይሰጣል። ” ሲሉ አክለዋል።

ትምህርት ቤቶች “ ቀርቷል ” ሲሉ ተስተውለዋል፤ ታዲያ መረጃውን ከየት አግኝተውት ነው ? ቢሮው ትዕዛዝ አውርዶ ነበር ? ስንል ኃላፊውን ጠይቀናል።

ዶ/ር ዘላለም ፥ “ በዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ጣቢያቸዎች እንደሚሰጥ ነገር ግን ሌሎች ጣቢያዎች የነበሩት፣ በእነርሱ ላይ ካልሆነ በስተቀር ' ቀርቷል ' ተብሎ የተሰጠ መግለጫ አልነበረም ” ብለዋል።

አክለው፣ “ ለሙከራ ስንሞክርባቸው የነበሩ እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ተማሪዎችና ቤተሰብ ላይ እንግልት እንዳይሆን እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ቀንሰናል ” ያሉት ኃላፊው፣ “ በእርግጠኝነት ሊፈጸሙባቸው ተብሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ የተወሰኑት ላይ ግን ተወስኗል ” ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው እንደቀረ ያስተላለፈው መልዕክት ነበር ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ “ ትምህርት ሚኒስቴር እኮ በገጹ ላይ አስታውቋል እንዳልቀረ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም። በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ተይዘው የነበሩት በተለያዩ ምክንያቶች ተቀንሰዋል ” ብለዋል።

ቢሮዎ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ጻፈው ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው ደብዳቤ (ከላይ ተያይዟል) የቢሮ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ፥ “አዎ። ትክክል ነው !! ” ብለዋል።

“ አሁን ባልናቸው ጣቢያዎች ማለት ነው። በፊት በ153 ጣቢያዎች ብለን ነበር ይዘን የነበረው አሁን ግን በእርግጠኝነት ይሳካል የተባለበት ቦታ ከላይ የተጠቀሱት ጣቢያዎች ብቻ ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም በተቀመጠው መርሀ ግብር መሠረት ተማሪዎች ከምንም አይነት ውዢምብር ራሳቸውን ጠብቀው ከቢሮውና ከትምህርት ሚኒስቴር በሚወርዱ መመሪያዎች ብቻ ተረጋግተው እንዲፈተኑ አሳስበዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍253
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ከሚወስዱባቸዉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ ወደሆነው የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩት በመግባት ላይ ናቸው፡፡

በዛሬው እለት ወደ ፈተና ጣቢያዎቹ መግባት የጀመሩት ከሀምሌ 3 ጀምሮ ብሔራዊ ፈተናውን መውሰድ የሚጀምሩ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሲሆኑ ተማሪዎቹ ወደ ተቋማቱ ሲገቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በፌደራል የጸጥታ አካላት ተገቢው የፍተሻ ስራ መከናወኑን በየፈተና ጣቢያዎቹ ባደረግነው ምልከታ አረጋግጠናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ወደ ኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩት በመግባት ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን በማበረታታት የፍተሻና ሌሎች እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ተመልክተዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍26
#National_Exam

አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል፡፡

ፈተናው በሁለት ዙር ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ፈተና መርሐግብር የእንግሊዝኛ እና ሒሳብ ፈተናዎች ይሰጣሉ፡፡

ዘንድሮ 700,000 የሚሆኑ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍14🔥5
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀትና በኦላይን መሰጠት ጀምራል፡፡

በዛሬው እለት ፈተና መውስድ የጀመሩት የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ተማሪዎች ሲሆኑ ፈተናው በኦላይንና በወረቀት 23582 ተፈታኞች መሰጠት የጀመረ ሲሆን የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ አየለች እሸቴ ጋር በመሆን ፈተና እየተሰጠባቸው ከሚገኙ የፈተና መስጫ ጣቢያዎች መካከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎና በአብሮህት ቤተ መጻሕፍት በመገኘት መልከታ በማድረግ ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወቃል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍154
#Update

አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና #በድጋሜ የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች ውጤት ይፋ ተደርጓል፡፡

በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት ሲማሩበት ወደነበረው ተቋም መላኩንና  ተፈታኞችም ወዛው በመሔድ ማየት እንደሚችሉ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለቲክቫህ ተናግረዋል።

በተጨማሪም https://result.ethernet.edu.et/ ላይ በመግባት ውጤት ማየት ይቻላል።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ እንደሚችሉም ተጠቁሟል።

Via ቲክቫ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍38😁4
የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

(ሀምሌ 5/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ውጤቱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ አድርገዋል።

በዚሁ መሰረት የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው በቀጣይ ጥቂት ቀናት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተመሳሳይ ይፋ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ አስታውቀዋል።

ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ፡፡

https://aa.ministry.et/#/result


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍5010
የአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል !

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሠጡት ቃል ፦

“ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ተለቋል። የማለፊያ ውጤት ወስነን ቆርጠን ይፋ አድርገናል።

ወንድም ሴትም 50ና ከዚያ በላይ ያመጡ ናቸው ወደ ሚቀጥለው ክፍል የሚያልፉት። የአካል ጉዳተኞች ማለፊያ ነጥብ 45 እና ከዚያ በላይ ነው።

78 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞቻችን አልፈዋል።

የ6ኛ ክፍል ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል። ”


የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መመልከቻ : https://aa.ministry.et/account#/student-result
(መለያ ቁጥርና ስም ያስገቡ)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
👍4612
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ትራምፕ በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ በነበረው የምርጫ ቅስቀሳቸው ላይ በስናይፐር የግድያ ሙከራ ተፈጸምባቸው

የ2024ቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪ ዶናልድ ትራምፕ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል።

ትራምፕ በፔንሲልቫኒያ ግዛት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነው ቀኝ ጆሯቸው አካባቢ በጥይት የተመቱት።

የ78 አመቱ ፕሬዝዳንት የደረሰባቸውን ጉዳት ተቋቁመው ለደጋፊዎቻቸው ደጋግመው “ታገሉ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዶናልድ ትራምፕ የግድያ ሙከራ ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎችን ለማንበብ ቀጣዩን ሊንክ ይጫኑ፦ https://bit.ly/3S99jPc


@NATIONALEXAMSRESULT
👍26🔥10
"ባካሄድነው ጥናት 90 በመቶ ተማሪ ኮራጅ መሆኑን ደርሰንበታል"- አለማየሁ ተ/ማሪያም (ዶ/ር)
#FastMereja
በኢትዮጵያ የኩረጃ ደረጃ ምን ያህል ነው? ሀገርንስ ምን ያህል ይጎዳል? በሚል በ2004 በተደረገ ጥናት 90 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ኮራጅ መሆናቸው ተረጋግጧል ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ተ/ማሪያም (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

ተመራማሪው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዳጉ ፕሮግራም በነበራቸው ቆይታ፤ በቀደመው የትምህርት ሥርዓት የመመዘኛ ፈተናዎች የሚሰጡበት ሂደት ለኩረጃ ምቹ እንደነበሩ ተናገረዋል፡፡

ተማሪዎች በፈተና ወቅት የማያውቁትን ጥያቄ መልስ ከሌሎች ለመቅዳት ድሮም ይሞክሩ እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ሥር ሰዶ በዘመቻ መል የሚካሄድ ሆኗል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ተማሪዎች ከትምህርቱ በበለጠ የኩረጃ መንገዶችን ያጠናሉ የሚሉት ተመራማሪው፤ በጥናቱ 27 የሚሆኑ የኩረጃ ዘዴዎች እንዳሉ ደርሰንበታል ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያልፉ ከመፈለግ አንፃር እንዲሁም መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጭምር ለኩረጃው እገዛ እንደሚያደርጉ ይናገራሉ፡፡

ይህም ፈተናውን አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች የሥብዕና ጉድለት እንደሚታይባቸው እዲሁም መሰረታዊ የሆነው መፃፍ እና ማንበብ ሲቸግራቸው እንመለከታለን ይላሉ፡፡

በተለይም የተጀመረው የበይነ በረብ (ኦን ላይን) ፈተና አሰጣጥ ሲጠናከር የተንሰራፋውን የኩረጃ መጠን በመቀነስ እና ተማሪዎችን በማብቃት ረገድ ላቅ ያለ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT
😁48👍42
2025/07/13 02:45:04
Back to Top
HTML Embed Code: