Forwarded from የኔ_እይታ 🧘🏽 Thoughts (ዘ ተ ሐ ር ዩ)
የምትወደው ሰው ላይ ስንት የማትወደው ነገር እንዳለ ረጋ ብለህ ስታስበው ሲጀመር በመውደድ ትገረማለህ. . .
ደግነቱ አብረኸው ስትሆን የምትወደው እንጂ የማትወደው አይታይህም
Forwarded from የኔ_እይታ 🧘🏽 Thoughts (ዘ ተ ሐ ር ዩ)
መኖርህ መጥፋትህ የሚያስጨንቃቸው፤
ማጣት መከፋትህ የሚያሳስባቸው፤
የሚጨነቅልህ ስላንተ ሚያስብ በዙሪያህ ከጠፋ፤
ማንም የለኝ ብለህ ከቶ እንዳትከፋ፤
መኖርክን ፈላጊ ጠዋት ማታ አሳቢ
እንዲኖር በተስፋ፤
በርከት ያለ ገንዘብ ተበድረህ ጥፋ
. . .🏃♂️
Forwarded from የኔ_እይታ 🧘🏽 Thoughts (ዘ ተ ሐ ር ዩ)
አነጋገር የፈጠርካት ዓለም በአእምሮ ውስጥ ያለው እምነት እና አመለካከት ውጤት ነች፡፡
አታካች እና ፈተናው የበዛ የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ከተዘፈቅክ መንስኤውን ለማወቅ ወደ ሌላ ማማተር አይኖርብህም፡፡
የገዛ አእምሮህ ላይ ጣትህን ቀስር፡፡
ወስጥህ በነውጥ ማዕበል ከፍ ዝቅ ባለ ቁጥር ውጪውም አብሮ ከፍ ዝቅ ይላል፡፡
ይህ የተራቀቀ ፍልስፍና አይደለም፡፡ ደረቅ ሀቅ እንጂ፡፡ በአአምሮህ ውስጠ ያለው እምነት ውጪውን አለም አጥለልህ ፍርድ እንድትሰጥ ይረዳሃል።
Forwarded from የኔ_እይታ 🧘🏽 Thoughts (ዘ ተ ሐ ር ዩ)
አለማወቁን የማያውቅ እሱ ሞኝ ነውና ተወው
አለማወቁን የሚያውቅ ብልህ ነው አስተምረው
ማወቁን የማያወቅ እሱ ያንቀላፋ ነውና አንቃው
ማወቁን የሚያውቅ እሱ ጠቢብ ነውና ተከተለው!
👉ሱፊዝም
📚ጥበብ - ከጲላጦስ
Forwarded from የኔ_እይታ 🧘🏽 Thoughts (ዘ ተ ሐ ር ዩ)
የሚገርሙኝ ዘመን ተሻጋሪ ቃላት
- ከእመጓ መፅሐፍ
- በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)
(ገፅ 162-163)
~በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተዉታላችሁ፡፡ ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፤ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፤ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፤ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ፡፡ ምኞታችሁ ልክ የለውም፤ አምሮታችሁ ብዙ ነው፡፡
~የአማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል፡፡ ተዉ የተባላችሁትን ትሽራላችሁ፤ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፤ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ፡፡ …
~ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ፤ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም፡፡ ሁሉ አላችሁ፤ ግን ባዷችሁን ናችሁ፡፡ ሃይማኖት እንጅ እምነት የላችሁም! …
~መቀመሚያውን ነግሬህ ማርከሻውን ሳልገልጥልህ መጀመሪያውን ብቻ ሞጭልፈህ ትተኸኝ ትሄዳለህ፡፡ ጥበብን ‹‹ሀ ግዕዝ›› ብዬ ላስተምርህ ብሞክር፣ መንደር ውስጥ በቃረምካት ዕውቀት ተመክተህ በመሰልቸት ‹‹ሆ ሳብዕ›› ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ፡፡
~የግል ታሪካችሁ ቢታይ ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተልከፈከፈ የተማሪ ኮፋዳ ውስጥ ያለ እህል ይመስላል፡፡
~ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ፣ ሰርታችሁ ሀብት ስታፈሩ፣ ከላይ የሆናችሁበትን ሃገር ለቃችሁ፣ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ፡፡ ትቀጥላላችሁ፣ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ፡፡ ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትጸጸታላችሁ፡፡ በጽኑ ታማችኋል!
~ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ፡፡ ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ፤ እናም ወደ ኋላ ስለታሪካችሁና ስለ ቅርሳችሁ ባሰባችሁ ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማችኋል፡፡
~ስለሆነም ከኋላ ታሪካችሁና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ። የአሸናፊነትንና የተሸናፊነትን ትርጉም በአንድ ላይ የያዙ ሃውልቶች ታቆማላችሁ፡፡ ለግልጽነትና ለነጻነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ ዕርቃን ወደ መሆን ወረዳችሁ፡፡
~ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ፡፡ በዚህ ዓለም ጥድፊያ ታማችኋል፡፡ ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፤ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ፤ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ አገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ፡፡
~በቁማችሁ የናቃችሁትን የሀገራችሁን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትናፍቃላችሁ፡፡ ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ፡፡
~ግብዝነታችሁ መጠን የለውም፡፡ ሁለት ሀገር እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ፤ አንዱን በደም ሌላኛውን በመታወቂያ ታስባላችሁ፡፡ ከአንዱም ግን በአግባቡ አትኖሩም፡፡ ዘመናችሁም በምልልስና በመዋተት ያልቃል፡፡
~ምን እንደምትፈልጉ አታውቁም እናም ፍለጋችሁ አያልቅም፡፡

ተስፋ!!
ይህቺን ምድር የሚያስተዳድር ... በስውር እጁ ዓለምን የሚገዛ ... የሰው ልጆችን በሙሉ የሚዘውር... ዓይን ተከድኖ እንዳይቀር እጅ ተሰብስቦ እንዳይቀመጥ ያደረገ...የሞተን ልብ የሚቀሰቅስ... የታጠፈን እግር የሚያዘረጋ ... የዓለማችን ሀያሉ ገዢ - ተስፋ!!
ህይወት ጋር ትግል እንድንገጥም የልብ ልብ እንዲሰማን ያደርገናል። የሄደውን ሸኝተን ለሚመጣው ደጃፋችንን የምንከፍተው እሱ ስላልሞተብን ነው። ሰው ትልቁ ስጦታው የመጠበቅ ተስፋው ነው። የአገኛለሁ ተስፋው ነው። ነገ የተሻለ ቀን ነው የሚለው ተስፋው ነው። ተስፋቸውን የገደሉት ናቸው ቀን የጨለመባቸው።
እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብህም ይጽና እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።
መዝ ፤ ፳፮ ፡ ፲፬

አንድ የ30 አመት ጎልማሳ ብዙ ከወላወለ በኋላ እድሜ ልኩን ሲመኘው የነበረን የምህንድስና ትምህርት ለመማር ለምዝገባ ወደ አንድ ኮሌጅ ሄደ፡፡ ቢሮ እንደገባ የተማሪዎች አማካሪ አገኘውና ሲያማክረው “በመማርና ባለመማር መካከል ብዙ ወላውያለው ” አለው፡፡
አማካሪው ምክንያቱን ሲጠይቀው፣ “አሁን 30 አመቴ ነው፡፡ ስመረቅ እኮ 35 ሊሆነኝ ነው” በማለት የመወላወሉን መነሻ ምክንያት ነገረው፡፡
አማካሪው የመለሰለት መልስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ትምህርት ገፋው፡፡ “የዛሬ አምስት አመት እኮ ብትማርም ሆነ ባትማር 35 አመት መሙላትህ አይቀርም፡፡ ሳትማር 35 አመት ከሚሞላህ፣ ተምረህ ቢሞላህ አይሻልም?”
እስቲ አንድ ጊዜ ጸጥ በሉና እድሜያቹ ስንት እንደሆነ አስቡት፡፡ ከዚያም በአሁኑ እድሜያቹ ላይ አምስት አመት ደምሩበት፡፡ ድምሩ ስንት መጣ?
ብትማሩም ባትማሩም እድሜያቹ መጨመሩ አይቀርም ሳትማሩ እድሜያቹ ከሚጨምር ተምራቹ እድሜያቹ ቢጨምር የተሻለ ነው ።
ሴት ልጅ ጌጥ ናት የሚሉትን ተዋቸው!
ምን መራራ ሀቅ አለ መሰለህ እዚህ ዓለም ላይ? አንተ የተስፋህና የመኖርህ ኢነርጂ ሴት ናት። አበቃ!!
ወንድ ልጅ ገና ወደ ምድር ሳይላክ ጀምሮ ዓይኑን የገለጠችለት ሴት ናት። በውበት ልቡን - በእውቀት አዕምሮውን የለኮሰችው እሷው ነበረች። ነገርግን የኋላ ኋላ አብዮት ልጇን እንደበላችው ማህበረሰብ ደግሞ የሴትን ልጅ ልዕልና ሸመጠጣት። በየጓዳው ግን ተደብቆ ያንሾካሹካል " እሷ ባትኖር እኮ- ህእ" ይላል ። አዎ! እሷ ባትኖር አንተ የመኖር ጉጉትህ ይንጠፈጠፋል።
አሰልጥንሀለች። ሚስት ሆና በከንፈሯ እናት ሆና በጡቶቿ እዚህ አድርስሀለች። ብዙዎቹን መገልገያ ፈጠራዎችህን ተመልከት በሷ ኢንስፓይሬሽን የተዘጋጁ ናቸው። የለበስከውን ሸሚዝ እንኳ ስትገዛ ትወደው ይሆን ብለህ በትንሹ አስበሀል😉 ስኬትህ ናት።
ደግሞ እስኪ እያት። አታምርም? በባዶ ሜዳው መሀል ለብቻዋ የበቀለች ቀይ አበባ አትመስልህም ተፈጥሮዋን ስታስብ? የሷ ድንቅ ተፈጥሮ አንተንም ግርማ ሞገስ ጨምራልሀለች ። እንጂ እውነቱን ስነግርህ ብቻህን ንፍጣም ነገር ነህ።
ሴት ልጅ ጌጥ ናት የሚሉትን ተዋቸው። እሷ የጌጡ ፈርጡን ናት!

ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ
እኔና እናንተ ከሚከተሉት ከሶስቱ አይነት ልምምድ ከአንዱ ነን፡፡
1. ወላዋዮች
አንዳንዶቻችን ወላዋዮች ነን፡፡ ይህንንም ያንንም ለመጀመር እናስብና በሃሳባችን በማውጣትና በማውረድ ከከረምን በኋላ አንዱንም ሳንጀምረው ከአመት አመት እናልፋለን፡፡ አንዳንዶች የማይጀምሩት ከፍርሃት የተነሳ ነው፡፡ ሌሎች ደግሞ እንዴት እንደሚጀመር ክህሎት ስለሚጎድላቸው መጀመር ያስቸግራቸዋል፡፡ የዝቅተኝነትና ያለመቻል ስሜትም እንዳይጀምሩ የሚያደርጋቸው ሰዎችም አሉ፡፡
2. ጀማሪዎች
አንዳዶቻችን ጀማሪዎች ነን፡፡ ከሃሳብ ባለፈ ሁኔታ የማንጀምረው ነገር የለም፡፡ ነገር ግን አንቀጥለውም፡፡ ብዙ ጀምረን ያልጨረስናቸው ነገሮች አሉን፡፡ አንዳንዶች በሚገባ ያላቀዱበትን ነገር በስሜት ስለሚጀምሩ ነው የሚያቆሙት፡፡ ሌሎች ደግሞ እንቅፋትን የመቋቋም አቅም ስለሌላቸው የመጀመሪያው እንቅፋት ያስቆማቸዋል፡፡ የጀመሩትን ነገር ሳይጨርሱ ሌላ የመጀመር አጉል ልማድ ያለባቸውም ሰዎች አሉ፡፡
3. ጀምሮ ጨራሾች
አንዳንዶቻችን እናስባለን፣ እናቅዳለን፣ እንጀምራን፣ የጀመርነውንም ሳንጨርስ አናቆምም፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚያስቡትን፣ የሚያቅዱትንና የሚጀምሩትን በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ትክክለኛውን ሂደት ተከትለው የጀመሩትን ሳይጨርሱ አያቆሙም፡፡ ብቸኛው የስኬት መንገድ ይህኛው ነው፡፡
አስቡ! አቅዱ! ተዘጋጁ! ጀምሩ! ቀጥሉ! ጨርሱ!
ዶክተር እዮብ ማሞ
Forwarded from የኔ_እይታ 🧘🏽 Thoughts (ዘ ተ ሐ ር ዩ)
14ቱ የህይወት ህግጋት ሊዮ ቶልስቶይ 🫀+🧠
1.ከጠዋቱ አስራ አንድ ሰዓት ላይ ተነሱ
2.ሁልጊዜ ከአራት ሰዓት በፊት ወደ መኝታ ሂዱ
3.በቀን ውስጥ ሁለት ሰዓት መተኛት ተፈቅዶላችኋል።
4.በልክ ብሉ
5.አልኮል መጠጥ እና ጣፋጭ ምግቦችን አስወግዱ
6.በየቀኑ ለአንድ ሰዓት ያህል የእግር ጉዞ አድርጉ
7.በምክንያት ላይ ያልተመሠረቱ ሁሉንም አጠቃላይ አስተያየቶች ችላ በሉ
8.በአንድ ጊዜ አንድ ነገር በማድረግ ትኩረታችሁን ሰብስቡ
9.የማይጠቅም ከሆነ እምቢ ማለት ልመዱ
10.ለሌሎች ለማሳየት መጨነቅ አይጠበቅባችሁም መልካም ነገርን አድርጉ።
11.ምኞታችሁን በስራ ተዋጉ
12.ያልቀናቸውን እርዱ
13.ስሜታችሁን አታሳዩ
14.ሌሎች ስለእናንተ ምን እንደሚያስቡ መጨነቅን አቁሙ
" አትጨነቁ "
ሳይገቡኝ የተጨነኩባቸው ነገሮች ሳልጨነቅ ካሳካዋቸው ይበልጣሉ......። ንዴት ፤ ቁጣ ፤ ጉጉት ፤ ችኮላ ፤ ብስጭት የሌለበት ተግባሬ በጣም ጥቂት ቢሆንም ስኬታማ ፍሬ ነበረው.... ጭራሽ የጓጓሁለት ነገር ሲሳካ አይቼ አላውቅም ። የቸኮልኩለትም ነገር በጥቂቱ ቢሳካም ትርጉሙ ሊገባኝ አልቻለም... "ለዚህ ነበር የተወዛገብኩት....."የመሳሰሉትን መብሰልሰል ከማስከተል ውጪ
ለጉጉታችሁን ወሰን አበጁለት....።የት እንደደረሳችሁ ግራ እስኪገባችሁ ድረስ የቆማችሁበት ይጠፋል አንዳንዴ...።
ያላችሁት ሁሉ አይሳካም ፤ የግባችሁ መስመር ስክነት ከሌለው... አሁን ላለሁበት ደረጃ ሰክኜ ካሰብኩት በላይ የተጨነከበት እጥፍ ነው ነገር ግን የተጨነኩበትን ነገር ፍሬውን ላየው አልቻልኩም...
# ተጨንቄ አንብቤ ያለፍኩት ፈተና አልነበረም..
# ስሜታዊ ሆኜ የሰራሁት ሁሉም ነገር ስህተት ነበር ውጤቱ...
#ደንግጬ የቀረብኩት ቃለ መጠይቅ (interview) ውጤት አልነበረውም.....
እራሴን ሳላዳምጥ ነገሮችን በጣም አጋንኜ ያደረኩት ሁሉ ውጤታማ አልነበረም።
እራስን ማዳመጥ እና መስከን is the best ምንም አዲስ ነገር የለም/ስትደርሱበት እርካታው ተኖ ሌላ ሃሳብ ብቅ ይላል
አጉል ጉጉት ሳታስቡት ስግብግብ ነው የሚያደርጋችሁ ወይ::

ራስን መውደድ ማለት ሌላውን ማንቋሸሽ ሳይሆን እራሳችንን በተገቢው መንገድ ማነፅ ነው social interaction ላይ ሰውን ዝቅ አርገን ራሳችንን የበላይ ማድረግ አምባገነንነት እንጂ ራስን መውደድ አደለም።
self-love ባለንና በራሳችን ባህሪ confident መሆን እና እራስን ጥሩ ደረጃ ለማድረስ መትጋት ነው ይህን ለማረግ ደሞ የምንተማመንበት personality ያስፈልገናል እና moral of the story make a personality which u,ur self could love it አምባገነን የሆኑ ሰዎች የself love ጉድለታቸውን ሰውን በመጨቆን ስለሚሞሉት ነው
Forwarded from የኔ_እይታ 🧘🏽 Thoughts (ዘ ተ ሐ ር ዩ)
ለአንድ ጥበበኛ:-
"እገሌ እኮ መብረር ይችላል" አሉት።
"ምኑ ይገርማል ታዲያ ከርሱ ያነሱት እን ዝንብ እና
ትንኝ ሁሉ ይበሩ የለም እንዴ!" በማለት አጣጣለባቸው።
"እንትና እኮ ውሃ ላይ መሄድ ይችላል ።" አሉት። " ምኑ ይገርማል ታዲያ ቁራጭ ጣውላም ባህር ውሃ ላይ ቢጥሉት አይሰጥምም ውሃ ላይ ይሄዳል እኮ" አላቸው።
"እንግዲያውስ ባንቱ እይታ ገራሚው ነገር ምንድነው? " አሏቸው። " እጅግ አስደናቂው ነገር ሰዎች የያዙትን ዓላማና መርህ ሳይለቁና ሳይስቱ በከባድ ፈተናዎች መሃል ከሰዎች ጋር መኖር ፣ አለመዋሸት፣ አለመስረቅ፣ አለማታለል፣ እምነት ለጣሉብህ መታመን ፣ የተማመኑብህን አለማሳፈር፣ ሰዎችን በየትኛውም መልኩ ልባቸውን አለመስበር. . .
እጅግ አስደናቂው ነገር ይህ ነው ብለው መለሱላቸው !!!
Forwarded from ው ል ብ ታ 🪔. . .
ከደቂቃዎች በኋላ ግርግር የማይታይበትን መንገድ ይዘን ስንሄድ ወደእኔ ዞር አለ እና...
"እናንተ ወጣቶች የዚህ የቁሳዊው ስልጣኔ ፍሬዎች ናችሁ"
ብሎ ጨዋታውን ቀጠለ...
.
"......እኛ ሽማግሌዎች ደግሞ የመንፈሳዊው ዓለም ፍሬዎች ነን።ስልጣኔያችንም መንፈሳዊ ነው...እናንተ ይሄንን አስተውሎት ያነሰውንና ሆሆታና ጭብጨባ የበዛበትን፣ልጓም የማያውቅ የእሽቅድምድም ዘመን ትወክላላችሁ።እኛ ደግሞ የረጋውን ጥንታዊውን ዘመን እንወክላለን...!በእናንተ ውስጥ እርጋታና ሰላም ጠፍቷል።ብዙ ትሮጣላችሁ እንጂ የእርካታን ደጃፍ አትረግጡም..:ቤት ለመስራት አልያም ለቤት ኪራይ የሚያስፈልጋችሁን ገንዘብ ለመሰብሰብ እድሜ ልካችሁን ስትቅበዘበዙ ትኖራላቹሁ።ይሄንን ገንዘብ ለማግኘት የህይወታችሁን አብላጫ ጊዜ የምታሳልፉት ግን ከቤት ውጭ በየአደባባዩና በየስርቻው ስር ስትጉላሉ ነው...
.....
የኑሮ ጭንቀታችሁ የምትይዙ የምትጨብጡትን አሳጥቷችኋል።ደስታና እርካታን የምትፈልጉበት መንገዳችሁ፣ሁሌም ሌላ ጥያቄ ይጭርባችኋል እንጂ መልስ ሰጥቷችሁ አያውቅም..እንዲህ እንደሆናችሁም ታልፋላችሁ"..።
ዮቶር(ኮብላይ ካህን)📖📓
@wlbta

እስቲ ዛሬ ደግሞ Feb 14 " Valentine's day" በመሆኑ ስለ በዓሉ እና ስላመጣጡ አንዳንድ ነገር ልበላችሁ🤌
💭
.
.ስንቶቻችን ይሆን የቫለንታይን ቀን(የፍቅረኞች ቀን ብለን የምናከብረው) የሚከበርበት ምክንያትና መነሻው የምናውቀው?
ወይስ ሰው ስለ አከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው?
ክርስቶስ ከመወለዱ ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት
አረማዊ ሮማውያን የካቲት 14 ማታና የካቲት 15 "የተኩላ አዳኙ"ለሚሉት ሉፐርኩስ(Lupercus) ክብር በማለት በጣኦት አምልኮ ያከብሩት ነበር።ሮማውያን ይህ በዓል ሉፐርካልያ
(Lupercalia) ይሉታል።ንጉሥ ቆንጠንጢኖስ ክርስትና የሮማውያን ይፋዊ ሃይማኖት መሆኑ በማወጁ ማነኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተወስኑ ሮማውያን ሰዎች ግን በዓሉን ማክበር አልተዉም።ይህንን አረማዊ በዓል
ማለትም ሉፐርካልያ የሮማው ጳጳስ ገላስዮስ ክርስትያናዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር አደረጉ።ጳጳስ ገላስዮስ ለካቲት 15 ሲከበር የነበረው በዓል የቅዱስ ቫለንታይን ቀን በሚል አዲስ ስያሜ
የካቲት 14 እንዲከበር አደረጉ።
እንዴት ይህ አረማዊ በዓል የቅዱስ ቫለንታይን ቀን የሚል ስያሜ ተሰጠው?
ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው። ቫላንታይን ጥንታዊው ታዋቂው ሉፐርኩስ ነው። ሉፐርኩስ በግሪካውያን ፓን(pan) ተብሎ ይጠራል። በጥንታውያን አይሁድ
ደግሞ ባል(Baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል።ባል
በመጽሓፍ ቅዱስ ዘፍጥረት 10-9 ላይ ታላቁ አዳኝ ተብሎ ለተገለጸው ኒምሮድ ሌላኛው መጠርያው ነው። ኒምሮድ የሮማውያን የተኩላ አዳኙ ሉፐርኩስ ነበር። በዚህ መሠረትም የቅዱስ ቫለንታይን ቀን የአረማውያን ለኒምሮድ ክብር የሚያከብሩት የጣኦት አምልኮ ነው።
ቫለንታይን የሚል ቃል ቫለንቲኑስ(valentinus) ቫለንስ ከሚል የላቲን ቃል የመጣ ነው።
ቀጥተኛ ትርጉሙ ጠንካራ፣ሃይለኛ ታላቅ ማለት ነው።ዘፍጥረት10-9 ላይ እንደምናነበው " እርሱም በእግዚአብሔር ፊት አዳኝ ነበረ ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር
ፊት ሃያል አዳኝ እንደ ኒምሮድ ተባለ።" ኒምሮድ የሮማውያን ጀግና ሃይለኛ ሰው ቫለንታይን ነበር።
ሌላኛው የኒምሮድ ስም ሳንክቱስ(Sancutus) ወይ ሳንታ (santa) ነው ሳይንት(saint) የሚል የእግሊዝኛ ትርጉምአለው ማለትም ቅዱስ። የሮማውያን ሉፐርካልያ በመጨረሻ ቅዱስ
ቫለንታይን የሚል ስያሜያዘ ማለት ነው።
ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን በቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቀማሉ። በባቢሎናውያን ባል(bal) ልብ የሚል ፍቺ ነው ያለው።በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት
ለቫለንታይን ቀን(የፍቅረኛሞች ቀንየምንለው) መገለጫ እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን የጣኦት ጌታ ነበር። በሌላ መንገድም ኒምሮድ ወይም ቅዱስ ቫለንታይን ሳተርን ተብሎ
ይጠራል።ሳተርን የሮማ-ባቢሎን ከአባራሮዎቹ ለመሸሽ በምስጥራዊ ቦታ የሚደበቅ ጣኦት ነው።ሳተርን የሚል የላቲን ቃል ሴመቲክ(አይሁድ) ቋንቋ ከሚናገሩ ባቢሎናውያን የተገኝ ነው። መደበቅ፣ራስን መደበቅ የሚል ፍቺ አለው።
በጥንታዊ እምነትም ኒምሮድ(ሳተርን) ከአባራሮዎቹ በመሸሽ ወደ ጣልያን እንደተጓዘይነገራል።የአፐኒን ተራራ ስያሜው ወደ ኔምብሮድ ወይም ኒምሮድ ተቀየረ። ይህ ተራራ ኒምሮድ በጣልያን የተሸሸገበት ቦታ ነበር። ሮማም በዚ ተራራ ላይ እንደ
ተመሰረተች ይታወቃል።ሮም ፈርሳ እንደገና ከመሰራትዋ 753 ዓ/ዓ በፊት ሳቹርንያ (ሳተርን፡ኒምሮድ የተደበቀባት ቦታ) የሚል ስያሜ ነበራት። ኒምሮድ በዚህ ቦታ ተይዞበፈጸመው ወንጀል
ተገደለ።በንጉሥ ቆንጠንጦኖስ ጊዜም ክርስትያናዊ ሰማዕት የሚል የውሸት ክብር ተሰጥቶት በሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መዘከር ጀመረ። ኒምሮድ፣ባል፣ቫለንታይን፣ታላቁ አዳኝ፣ፋውኑስና
ሉፐርክስ 31ኛ፣32ኛና 33ኛና ደረጃ (ዲግሪ) ላይ ያሉ ፍሪማሶኖሪዎች ከሚያመልኩት ባፎሜት(የሜንደዝ ፍየል) ጋር የሚስተካከል ነው።
እንግዲህ በሰላቢ እጆች (ኢሊሙናቲ) ሴራ ዘመናዊነት ተላብሶ ድብቅ ጣኦት የሚመለክበት የቅዱስ ቫለንታይን ቀን እኛ ደግሞ የፍቅረኛሞች ቀን በማለት እያከበርን ማለትም እያመለክንነው።
አንድ በአል የሚከበርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሊኖረው ግድ ነው። ሆኖም የምናከብረውን በአል የምናከብርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሳናውቅ ከሴረኞች ድብቅ አላማ ማስፈጸምያ ከመሆን መቆጠብ ይበጃል።
🫴ያዉ እድትገነዘቡ ስለፈለኩኝ ነዉ መቅረት ያለበት ነገር ነዉ ብዬ ስላሰብኩኝ!!!

አስተማሪ ታሪክ
አንድ ሌባ በተደጋጋሚ በጨለማ ወደ አንድ ግቢ ይገባል። አንድ ቀን የግቢው ባለቤት እግቢው ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ላይ ወጥቶ ሌባውን ይከታተለዋል ሌባው እሮጦ መጥቶ ዛፉ ስር ቆመ ከዛ ሌባው ዛፉ ስር እንደቆመ ቅኝት ይጀምራል ወደ ፊት፣ ወደ ኋላ፣ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተዟዟረ አየ...
ይሄኔ የቤቱ ባለቤት ዛፉ ላይ ሆኖ አንዲት የዛፍ ፍሬ ወደታች ለቀቀበትና ፍሬዋም የሌባውን አናት ዳብሳ ወደቀች ሌባው ቀና ብሎ ወደ ላይ አየ ከቤቱ ባለቤት ጋርም ተፋጠጠ የቤቱ ባለቤትም፦ “ይህን ያደረኩት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? ሁሌ ልትሰርቅ ባሰብክ ጊዜ ሰዉ እንዳያየኝ ብለህ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ብቻ ሳይሆን ወደ'ላይም ማየት እንዳለብህ ላስታውስህ ፈልጌ ነው” አለው።
moral of the story:-
ክፉ ነገር አንስራ፤ ሰው እንዳያየን ብለን ግራ እና ቀኝ ማየት ሳይሆን ያለብን የፈጠረን አምላክ እንዳያዝንብን እንጠንቀቅ፤ ከክፉ ነገር እንታቀብ ሰዉን ሳይሆን ፈጣሪን እንፍራ።
Forwarded from የኔ_እይታ 🧘🏽 Thoughts (ዘ ተ ሐ ር ዩ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🤌 አመዳም of the week😉
ብዙ ጊዜ ስለ እውነት ይወራል እውነት አንጻራዊ ነው እውነት አንድ ነው እየተባለ ይነሳል ለኔ ግን እውነት የሚባል ነገር የለም።ከጅምሩ እኔ እውነትን ግለጠው ብባል ለኔ እውነት ማለት የማይለወጥ ዘላላም ያው ቋሚ የሆነ ከየትኛውም አቅጣጫ ቢታይ አንድ አይነት የሆነ ነገር ነው የምለው።ለዚ ነው ይመስለኛል ክርስቶስም እውነት እኔ ነኝ ያለው ምክንያቱም እርሱ እንዴትም ቢታይ በሁለንታ አለም ውስጥ ዘላለም የማይለወጥ ማንነት እና የራሱ እኔነት ስላለው ነው ለኔም የሚዋጥልኝ እንዲ ነው እውነት እንዲ ነው ከየትኛውም ዙርያ ቢታይ ያው አንድ አይነት ነው።ጤፍ በአይን ሲታይ አንድ ቅንጣት ነው በማይክሮስኮፕ ሲያዩት ግን ግዙፍ ይሆናል ስለዚ እይታው ሲቀየር ማንነቱም ተቀየረ እውነነት ነው ከተባለ ግን በየትኛውም ሚዛን እና መስፈርት ያው አንድ መማንነቱ ያለመለወጥ እራሱ ነው የሚገለጠው በዚ አለም ክንውን ደግሞ እንዲ ያለ የማይለወጥ እውነታ የለም!! ለዚ ነው እውነት እግዚአብሄር የሆነው።ሰው ግን ሲኖር አንዳንዴ እውነታውን መቀየር አይቻልም ይላል የትኛውን እውነታ ነው የሚቀይረው??እንዳልኩት እውነት ያው የሆነ የማይለወጥ ነገር ከሆነ በዚ ህይወት ውስጥ የማይለወጥ ነገር ምን አለና ነው እውነታውን መቀየር አይቻልም የሚባለው??።
በዚ ኑረት ውስጥ ህይወት ለኔ ልክ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ባትሪ ይዞ እንደመጓዝ ነው አንድ ስንራመድ የማይታይ የነበረው ወገግ እንደሚል ሁሉ በህይወትም ነገ የምንለው ቀን የሚጀምረው ልክ ስንረግጠው ነው ለምሳሌ ነገ የምናደርገገውን ነገር ዛሬ ላይ በአእምሯችን ውስጥ አጠናቀነው ሊሆን ይችላል ነገር ግን ነገ ውስጥ የምናደርጋቸው ነገሮች ገና አለመኖር ውስጥ ናቸው የሉም እያንዳንዱ ነገር ወደመኖር የሚመጣው ከምናደርግበት ቅጽበት ጀምሮ ነው ለምሳሌ እኔ ከዚ ቀጥሎ የምጽፈውን ነገር ባውቅም እስካልጻፍኩት ድረስ ግን የለም ጭራሹኑ!! even አእምሮዬ ውስጥም ሀሳቡ እንጂ ነገሩ እራሱ የለም በሌላ አነጋገር እግዜር እራሱ አልፈጠረውም ማለቴ ነው ምን አለ መሰለህ እግዜር ለዚ ህይወት ያበረከተው ነገር ቢኖር ያኔ አለምን እና ፍጥረታትን ብረሀንን ፈጥሮ ህይወትን ከማስጀመር ውጪ ሌላውን ነገር በራሱ እንዲከናወን ነው የተወው ስለዚ ሁሉም ክንወናችን ወደ ፍጥረት የሚለወጠው ከምናደርገው ቅጽበት ጀምሮ ነው ሁሉም የሚሆነው እኛን ተከትሎ እኛው እንዳደረግነው ነው።እንግዲ ህይወት ቅጽበት ከሆነች የቱን የወደፊት እውነታ ነው የማንቀይረው ታድያ??

ለማወቅ አንስነፍ
አንዳንዴ ልክ ነን ብለን እናውቃለን ብለን ያሰብናቸው ነገሮች ፈፅሞ ያላወቅናቸው ገና ብዙ የሚቀሩን እና ልንሰራባቸው የሚገቡ ነገሮች ሆነው ሊገኙ ይችላሉ ስለዚህ ሁሌም ለመማር ለማወቅ ራሳችንን ክፍት አድርገን አንጠብቅ እውቀት ጥግ የለውም።