Forwarded from አርምሞ🧘🏽♂ (ሞገስ ዘአምድ Gυrυ🪽)
ሀሳዊ-ካፒታል እንደ ካርል ማርክስ፦
በአንዲት ትንሽና ደሃ የገጠር መንደር ውስጥ ሁሉም ሰው በብድር እዳ ተዘፍቆ ይኖራል። በድንገት አንድ ሀብታም ቱሪስት ወደ መንደሩ ይመጣል። ከዛ ወደ አንድ ሆቴል ይገባል። እንግዳ መቀበያ ላይ 100 ዶላር ያስቀምጣል። እና ምቹ ክፍል ለመምረጥ ወደ ላይ ይወጣል። በዚህ መሃል የሆቴሉ ባለቤት መቶ ዶላሩን በመውሰድ ስጋ ቤቱ ጋር ተሯሩጦ እዳውን ይከፍላል። ስጋ ቆራጩ በነዚህ ዶላር ተደስቶ ወደ ከብት ነጋዴው ተሯሩጦ የቀረውን ዋጋ ከፍሎ ያካክሳል። ከብት ነጋዴው በተራው መቶ ዶላሩን ወስዶ እዳውን ሊከፍል ወደ ምግብ ሚመገብበት ነጋዴ ጋር ይሄዳል።
የምግብ ነጋዴውም ከሩቅ ሀገር ምግብ ይዞ የሚመላለሰው የከባድ መኪና ሹፌር ጋር ይሄዳል። የከባድ መኪና ሹፌሩም መኖውን ለማድረስ በፍጥነት ወደ መንደሩ ያቀናል። በዚህም ከዚህ በፊት የበረበትን እዳ በማሰብ ለሆቴሉም ባለቤት መቶ ዶላር ይሰጠዋል። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ባለ ሀብቱ ቱሪስት ከመምጣቱ በፊት የሆቴሉ ባለቤት ተመልሶ መቶ ዶላሩን ቅድም በነበረበት የእንግዳ መቀበያ ቦታ ላይ ያስቀምጠዋል። የክፍሎቹ ስታንዳርድ ያልተመቸው ቱሪስት ወርዶ መቶ ዶላሩን ወስዶ ከተማውን ለቆ ለመውጣት ይወስናል።
ከከተማዋ ነዋሪዎች ውስጥ አንዳቸውም ያተረፉት ነገር የለም። ነገር ግን ሁሉም እዳውን ከፍሎ ጨርሷል!።
🤝🏼Forwarded from የስብዕና ልህቀት
በሌላው ጫማ መሆን
አንድን ሰው በትክክል ለመረዳት በሱ ቦታ ብሆን ኖሮ ምን ይሰማኝ ነበር ብለህ ማሰብ አለብህ። አንዳንድ ነገሮችን በሌሎች ጫማ ውስጥ ሆነህ እስካለየሀቸው ድረስ ልትረዳቸው አትችልም። እናም በሌሎች ጫማ ሆነህ የሰዎችን ስሜት ለመረዳት ሞክር። በሕይወት ውስጥ ባሉ ጠቃሚ ግንኙነቶችህ ውስጥ ሁሉ ተጠቀምበት፡፡ ከቤተሰቦችህ ጋር፣ ከሰራተኞችህ ጋር ወይም ከመራጮችህ ጋር ሊሆን ይችላል፡፡ የሚና መቀያየር (role reversa) የጋራ መግባባትን ለመፍጠር የሚሆን ቀላልና ፈጣን ስልት ነው። አንደ ለማኝ ለብሶ የሚያስተዳድረው ህዝብ ውስጥ በመግባት ችግራቸውን ለመረዳት እንደጣረው ንጉስ ሁን።
የስብዕና ልህቀት
#share
@Human_Intelligence

የሴትልጅ ቁንጅና ምንድነው?
_______
(ውበትና ደም-ግባትስ?)
"ቁንጅና ምንድነው ሰዎች አስረዱኝ
እኔ እሷን ወድጄ ታምሜያለሁኝ...
ውበትና ቁንጅናሺ፣ ይማርካል ለሚያይሺ.."
- ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ
በየዘመኑ "የሴት ልጅ ውበት" የሚባለውን አስተሳሰብና መስፈርት ማን ፈጠረው? "ቆንጆ" ሴት ከቆንጆ ሰው በምን ትለያለች? ሴቶች በ"ሽንጥና ዳሌሽ ሲታዩ..." ዓይነት መስፈርቶች እንዲለኩ የበየነላቸው ማነው?
ወንዶች ሴቶችን የሚስሉበት መንገድ ከስሜት ጋር የተያያዘ ለምን ሆነ? ከወሲባዊ መስህብ አሊያም ከመራባትና ከእናትነት አስተሳሰቦች ውጭ ሊታሰብ የሚችል የሴት ልጅ ሰብዓዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ከየማኅበረሰቡ አንጎል የተነነው በምን ምክንያት ነው?
ውበት ምንድነው? ደርባባነትን ከሴት ልጅ ለምን እንድንጠብቅ ሆንን? በዘመናት ውስጥ የተቸራቸውን ማኅበራዊ ተክለሰብዕናና የተሰጣቸውን ሚና ለመጫወት እምቢ ያሉ ሴቶች ዕጣፈንታ ምንድን ነበር? አሁንስ ምንድነው?
ወንዶች በጥቅሉ ለሴቶች ያለን ዝንባሌ በጎችንና ፍየሎችን ሽንጣቸውን ለክተን፣ ጥርሳቸውን ፈልቅቀን፣ ሸሆናቸውን መትረን ለመግዛት ከምንሄድበት መንገድ ብዙም ያልተለየ ሆኖ የሚገኘው በምን የተነሳ ነው? ተፈጥሯዊ ነው? ወይስ ማኅበራዊ?
የሴቶች ተፈጥሯዊ ሰዋዊ አገልግሎት ምንድነው? ብለን ነው የምናስበው? ለምን?
የሴትን ልጅ አካላት ዕርቃን እያወጡ የተሳሉ አያሌ ክላሲካልና ሞደርን የጥበብ ሥራዎች (ሥዕሎች፣ ቅርፃቅርፆች፣ ስነፅሑፎች፣ ሙዚቃዎች፣ ወዘተ.) ለምን በየዓለሙ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ሆኑ?
የሰውልጅ ሴትን ልጅ ከsensual pleasure ውጭ ለማሰብ ያልቻለበት አብይ ምክንያቱ ምንድነው? ሴቶችስ ራሳቸውን ከመኳኳልና ከማጊያጌጥ፣ ሽንጥና ዳሌያቸውን ከማጉላት፣ ፀጉራቸውን ከመሾረብና በአልባሳት ከመሸለም ውጭ ያለውን ጥልቅ የራስ ማንነታቸውን ለመፈለግ ብዙ ዝንባሌ የማያሳዩት ለምንድነው?
በሴትነት ውስጥ ከማኅበራዊው መስፈሪያ ሚዛን የማፈንገጥ ዋጋው ምን ያህል ነው? ይህች ዓለም የማን ዓለም ነች?
እውን It's a man's man's world እንደሚባለው.. ዓለማችን የወንዶች ብቻ ዓለም ነች? ከሆነች ሴቶች የተነጠቀ ሙሉ የሰውነት ክብራቸውንና ዋጋቸውን ለማስመለስ ምን ያድርጉ?
የፆታ አስተሳሰባችን በምን በምን ነገሮቻችን ውስጥ ሥር እንደሰደደ፣ እስከ ምን ከፍታ እንዳሻቀበና እንዴትስ ተብሎ እንደተድበሰበሰና እንደተሸነገለ ልብ ብለን አስተውለነዋል?
ሴትነት ምንድነው? ወንድነትስ? ውበትስ? የሴት ልጅ ውበት ምንድነው? ሴትን ልጅ ያለ ጭንና ባቷ ለማሰብ ፈቃደኝነቱ ያለው ወንድ ከመቶ ስንት ፐርሰንት ነው? ራሷን ከቀሚሷ ውጭ አድርጋ ማሰብ የምትችልስ ሴት ከመቶ መሐል ስንት ትገኛለች?
የነዳጅ ዘይትን የሚተኩ በርከት ያሉ የኃይል አማራጭ ቴክኖሎጂ ተገኝተዋል በዘመናዊዋ ዓለማችን። ግን የዔለም ኢንዱስትሪ ሁሉ ከነዳጅ ጋር የተያያዘ ነው። ዲዛይኑ፣ ሸቀጡ፣ ንግዱ፣ ኢኮኖሚው፣ ቴክኖሎጂው፣ መኪናው፣ መርከቡ፣ አውሮፕላኑ... ሁሉ ከነዳጅ ጋር የተሳሰረ ነው። በዚህ የተነሳ ዓለም የሚያውቀውንና ህልውናውን የመሠረተበትን ኋላቀሩን ነዳጅ ዘይት መተው አይፈልግም። የሴት ልጅ ውበትስ ተመሣሣይ ነገር ይኖረው ይሆን?
በዓለም ሁሉ "የሴቶችን ውበት" መሠረት አድርገው የሚመረቱ ምርቶች፣ ዲዛይኖች፣ ፅሑፎች፣ ሳይንሶች፣ ፊልሞች፣ ኢንደስትሪዎችና ማኅበራዊ አወቃቀሮች... ባንዴ ተንደው እውነተኛ የሴቶችን ሙሉ ሰውነትና ክብር ወዳረጋገጠ ዘመናዊ አስተሳሰብ መሻገር ይችላሉ? የሚቻል ነው? ሴቶች ቂጥና ፊታቸው እየታየ የሚመዘኑበት ዘመን እስኪያበቃስ ስንት ዓመት ይፈጃል?
ይህ የናዖሚ ዎልፍ መፅሐፍ ላለፉት 3ሺህ ዓመታት የተቀነቀኑ የስነውበት ፍልስፍናዎችን፣ ሳይንሶችንና አስተሳሰቦችን እጅግ ጥልቅ በሆነ መንገድ ይቃኛል። አጥብቆ ይሄሳል። እና የውበትን ትርጉም እንድንፈትሽ ያስገድዳል።
ሴቶች ከወንዶች የውበት መስፈርት ራሳቸውን ማላቀቅ አለባቸው፣ ነፃ መውጣት አለባቸው ትለናለች።
በምጥን ፈገግታዋና በመርገፍ ቀሚሷ ዓለምን የምታማልለው ሞናሊዛ የኋላቀሩ ዘመን ማስረጃ ሆና ተቀድዳ የምትጣልበት፣ የፒካሶና የሌሎች በዓለም የተደነቁ የእርቃን ሴቶች ሥዕሎችና ኃውልቶች ተጠራርገው ወደ ቆሻሻ ቅርጫት የሚጣሉበት፣ የሴት ልጅን ሉዓላዊነት ያከበረ፣ ኮርማዊውን የወንዶች ዓለም የገረሰሰ፣ አዲስ የሴቶች ነፃነት ዘመን መበሠር አለበት ትላለች።
ከዚህ በፊት "ዘ ሴክስ ኦፍ ቲንግስ" የሚል አስገራሚ መሠል ይዘት ያለው በአንዲት ጀርመናዊት-እንግሊዛዊት ሪሰርቸር ዶክተር የተፃፈ አንድ ዳጎስ ያለ መፅሐፍ አግኝቼ ስገረምና የያዝኳቸውን ሁሉ የሴትልጅ አስተሳሰቦች ስሞግት ቆይቼ ነበር።
ይህን መፅሐፍ ካነበብኩ በኋላ ደግሞ ብርቱካን ከንፈርሽ፣ ብርንዶ ትንፋሽሽ፣ የዘንባባ ማር ይመስላል ፍቅርሽ፣ ፅጌረዳ ስላንቺ ልጎዳ፣ ሐር ይመስላል ፀጉርሽ፣ ሎሚ ተረከዝሽ፣ ስልታዊ ውዝዋዜሽ፣ ዓይናፋርነትሽ፣ ችቦ አይሞላም ወገብሽ፣ ካንቺ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት፣ እና አንቺን ያለውን በቴስታ ጥርሱን🤩... የመሣሰሉትን የምወዳቸውን የሙዚቃ ስንኞች ከአዕምሮዬ ለማጥፋት ምን ዓይነት ላጲስ መጠቀም እንዳለብኝ በማሰላሰል ላይ ነኝ🤓!!!
ይህች ደራሲና ተመራማሪ፣ ሶስተኛው የፌሚኒዝም አብዮት ተብሎ የሚጠራውን አስተሳሰብ ያፈለቀችና ለዓለም ያስተዋወቀች ጉምቱ ምሁር ስለመሆኗ ከተለያዩ ዜና መወድሶች ለመረዳት ችዬአለሁ።
ለማንኛውም ሃሳቦቿ የያዝካቸውን የሴት ልጅ ውበት ኮተቶች ሁሉ ያስጥሉሃል። ግን ፍራቻዬ ያለንን አስጥላን... በምትኩ የምትሰጠን ውበት ምን ዓይነት እንደሆነ ደራሲዋም ራሷ በትክክል ያወቀችው አልመሠለኝም።
ሽንጥና ዳሌሽ ሲታዩን ትተን... ወደ ምን እንሻገር? ውብ የምንላትን ሴት ከየት እናግኛት? ከስንደዶ አፍንጫና ከማር ከንፈር ውጭ ያለችዋ ቆንጆ ሴት ማነች? ከወዴትስ ትገኛለች? እውን አለችስ ወይ በዓለም ላይ? ሴቶቹ ራሳቸውስ ይቀበሏታል?
ደራሲዋ የምትሰብከን ሴቶች ከሙክትነትና ከጌጥነት አሊያም ከስሜት ማስተንፈሻነት የወረደ የወንዶች አስተሳሰብ ነፃ የሚወጡባት ዓለምስ እውን በዚህ የቅርብ ዘመን ትውልድ እውን ሆና እናያት ይሆን? ...
የወንዶች አሽኮርማሚነት፣ እና የሴቶች ተሽኮርማሚነት አብቅቶ፣ ማንም ማንንም የማያሽኮረምምባትን ዓለም የምናየው መቼ ነው? መቼ ነው ያቺ የፍፃሜ (ዋንጫ) ቀን መምጫዋ? ምን ምልክትስ እንጠብቅ?
ወንድሜ (እና እህቴ🤩)... በበኩሌ ጥይቴን ጨርሼያለሁ!
አሰፋ ሀይሉ ✍

Forwarded from ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
እሱ፤ አንድ ሚልዮን ብር ብሰጥሽ ከኔ ጋር ትተኛለሽ?
እሷ፤ አንድ ሚልዮን ብር? ዋው! ይመስለኛል አዎ፡፡
እሱ፤ በመቶ ብርስ?
እሷ ፤ ጥፋ ከዚህ፡፡ ምን መስዬህ ነው? ሴተኛ አዳሪ?
እሱ፤ ሴት አዳሪነትሽን መጀመሪያውኑ ተስማምተናል፡፡ አሁን በገንዘቡ ላይ እንደራደር።
ልክነት መቼ እና እንዴት ነው
የሚኖረው? መቼ ነው ይህቺን ሴት ሴተኛ አዳሪ የምንላት? መቼ ነው ይህቺን ሴት ክብሯን የጠበቀችው? መቶ ብር ወይስ መቶ ሺ ብር ላይ? ወይስ አንድ ሚሊዮን ላይ? መቼ ነው ክብሯን ያጣችው?
የገነባነው ክብር እና ፅድቅ በየትኛው የብር መጠን ላይ እንሽረዋለን? ከሻርነውስ የእውነት መልካም ሰው ነን ማለት እንችላለን?
ምናልባት ምግባራችን እንደ ሴቷ በገንዘብ ስላልተፈተነ ይሁን ጥሩ ሰው የመሰልነው ?
@zephilosophy

ኤለን መስክ እንዲህ ይላል፦
“ከቀድሞዬ ፍቅረኛዬ አምበር ሄርድ ጋር በተለያየንበት ጊዜ ላደረኩላት ነገር ሁሉ ሒሳብ ጠየቅኳት እና ሁሉንም ነገር ሙሉ በሙሉ ከፍላለች:: በሴቶች ላይ በጣም ስስታመ ነኝ 💸::
አምበር ሄርድ የእኔ ገንዘብ እስከሆነ ድረስ በግዴለሽነት ገንዘብ ማውጣት ትወድ ነበር። በዚህም ለብዙ የበጎ አድራጎት ስራ የሚውል ገንዘብ እያለችኝ መቀበል ታዘወትር ነበር።
ትዊተርን የገዛሁት ለፖለቲካዊ ወይም ለንግድ ዓላማ ሳይሆን ለአምበር ነው። እንደ ቫለንታይን ቀን ስጦታ ልሰጣት ፈልጌ ነበር። ነገር ግን ከቫላንታይን አንድ ቀን በፊት በትዊተር ላይ አዲስ የወንድ ጓደኛ ስታገኝ ከእኔ ጋር ተለያየች።
ከእኔ ጋር ከተለያየች በኋላ ከትዊተር አገድኳትና ስሙን ወደ
X ቀየርኩት። ነገር ግን አዲሱ ፍቅረኛዋን በቴስላ ድርጅት ውስጥ ቀጠረችው። እና ከጥቂት ቆይታ በኋላ እኔ አለቃው ላይ እንዲህ ማድረግ ስላልፈለገ ተለያት።
ከዚያም በግንኙነታችን ወቅት ለምታጠፋው ለእያንዳንዱ ሳንቲም ደረሰኝ ሰጠኋት። እና ሙሉውን ገንዘብ መልሳ ከፈለችኝ። ምክንያቱም ግንኙነታችንን ከመጀመራችን በፊት አብረን ካልሆንን ትከፍለኛለች የሚል ሰነድ እንድትፈርም አድርጊያለሁ። በሴቶች ጋር በጣም ንፉግ ነኝ እና ለዚህም ይመስለኛል እስካሁን ያላገባሁት”
✌🏼😌Forwarded from ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
ተቀጣሪ ወይም ነጋዴ ሆነህ ቤት ብትገነባ
- ከገቢህ 35% የገቢ ግብር
- የመሬቱ ሊዝ
- የጣራና ግድግዳ ግብር
- ለግንባታው የባንክ ብድር ወለድ
- በምትከፍለው እያንዳንዱ ትራንዛክሽን ባንክ ቻርጅና ቫት
- አሁን የንብረት ግብር
- በሁሉም ክፍያ ላይ ቫት
- ከሆነ ባለሥልጣን ጋር ከተነጃጀስክ ውርስ
- 30% ግሽበት
- ያለምክንያት መዋጮ
- ያለዕድሜህ ሽበት
- የማይቆም ጦርነት
=> መፍትሔ:- ባገኘኸው የትኛውንም safe መንገድ ስደት
Via Abdulkadir Hajj Nureddin
@EliasMeseret
- ከገቢህ 35% የገቢ ግብር
- የመሬቱ ሊዝ
- የጣራና ግድግዳ ግብር
- ለግንባታው የባንክ ብድር ወለድ
- በምትከፍለው እያንዳንዱ ትራንዛክሽን ባንክ ቻርጅና ቫት
- አሁን የንብረት ግብር
- በሁሉም ክፍያ ላይ ቫት
- ከሆነ ባለሥልጣን ጋር ከተነጃጀስክ ውርስ
- 30% ግሽበት
- ያለምክንያት መዋጮ
- ያለዕድሜህ ሽበት
- የማይቆም ጦርነት
=> መፍትሔ:- ባገኘኸው የትኛውንም safe መንገድ ስደት
Via Abdulkadir Hajj Nureddin
@EliasMeseret
Forwarded from የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw
‹‹የጥምቀት ወግ››
++++++
እንደ ጥምቀት የምወደው በዓል የለም፡፡
ነፍሴ ነው፡፡
ገና ጥር ከመግባቱ ያቁነጠንጠኛል፤ ደረሰ ደረሰ እያልኩ፡፡
ዋነኛው መንፈሳዊና ሐይማኖታዊ ፋይዳው እንዳለ ሆኖ ጥምቀት ለእኔ ህዝባዊ ፌስቲቫል፣ ገፋ ሲልም የካርኒቫል ቀለምና ስሜት ያለው ወደር የለሽ የአደባባይ ነጻ የህዝብ በዓል ነው፡፡
ጥምቀት ባለህብረ ቀለም የባህል አውደ ርእይ፣
የውበት አውድማ፣
ግዙፍ የህዝብ ቡፌ ነው፡፡
ልብ ላለው፤ ከከተራ ጀምሮ ያለው መንፈሳዊ፣ ሐይማኖታዊ፣ ህዝባዊና ባህላዊ ትእይንት ልብን ይሰውራል፡፡
እንኳንም ኢትዮጵያዊ ያደረገኝ ያሰኛል፡፡
በደስታ ያፍነከንካል፡፡፡፡
‹‹እነሆ ጥምቀት ደረሰ
ነጭ ነጩን እየለበሰ
ህዝቡ ወደ ባሕር ገሰገሰ
ታቦቱን እያነገሰ››
እየተባለለት መምጣቱ የሚበሰርለት የጥምቀት በዓል ለወንዱም ለሴቱም፣ በተለይ ደግሞ ለአፍላዎቹ የመታያ፣ የመዋቢያና፣ የመፍኪያ ወቅት ነው፡፡
ወንዶች ሌላ ጊዜ ችላ የሚሉትን በመፈተል ብዛት የተቆጣጠረ ፀጉራቸውን ብን አድርገው ያበጥራሉ፣ እንደ ኪሳቸው ውዱን ይለብሳሉ፡፡
ሴቶች ሹሩባቸው በዘመኑ ፋሽን ይቆነደዳሉ፤ የቻሉ ሂውማን ሄራቸውን ልቅም ተደርገው ይሰፋሉ፣ ታጥበውና ታጥነው፣ እንሾሽላ ሞቀው፣ ሳውና ባዝ ውለው፣ ተቀሽረውና አስደንጋጭ ውበታቸውን ይዘው እንደ ኪሳቸው ባማረው ቀሚስ ተውበው ብቅ ብቅ ይላሉ፡፡
‹‹ይሄ ሁሉ ቆነጃጅት የት ተደብቆ ነው›› እስኪባል…
ቀይ ቢባል፣ ጠይም ቢባል፣ ጥቁር ቢባል…ውበት…ሃበሻዊ ውበት ሁሉም በየአይነቱ
… ከባለ ግቢ ትልቅ ብረት በር፣ ከቀበሌ ቤት ደጃፍ፣ ከየኮንዶሚኒየሙ ቤት ያለማቋረጥ ይፈሳል፡፡
ከብዛቱ የተነሳ ያፈዛል፣ ያደነዝዛል፡፡
እንደው ለመሆኑ ለጥምቀት የማያምርባት ሴት የትኛዋ ናት?
ከቤት ሰራተኛ እስከ የሃብታም ሚስት..
ከአጎጠጎጤ ኮረዳ እስከ ቀብራራ እመቤት..
ከቫዝሊን እስከ ውድ ሜክአፕ የተቀቡ ፊቶች እንደ ፀሃይ እያበሩ በጃንጥላ ተከልለው መንገዱን ሲያጥለቀልቁት ማየት እውነትም ጥምቀት የእኩልነት በአል ነው አያሰኝም?
በዓመት አንዴ የሚያገኙትን ብስኩት፣ ለስላሳና ሎሊፖፕ አከታትለውና ደራርበው የሚያላምጡና የሚጠጡ ከደሃና ባለጸጋ ማህጸን የወጡ ህጻናት በደስታ ሲቦርቁ ሰታይ ልብን ደስ አይልም?
ዶሮ ግዙልኝ፣ ሰንጋ እረዱልኝ፣ ዳቦ ድፉልኝ፣ ቶርታ ሸምቱልኝ ሳያስብል ሁሉንም እንዳቅሙ አስውቦና አስጊጦ በአደባባይ እኩል የሚያደርግ የሁሉም በዓል ነው ጥምቀት!
ታቦት አንግሶ ሲያበቃ፤
ለጥምቀት በዓል አደባባይ ወጥቶ ያልዘፈነ፣ ሆ ብሎ ያላስባለ ጎረምሳ፣
ግጥም ተቀብላ በስሜት ያልደገመች፣ ያላጨበጨበችና እስክስታ ያልወረደች ኮረዳ፣
በሃርሞኒካ ግጥምና ዜማው ስሜት የማይሰጥ ግን በስሜት የተሞላ ‹‹ሲሲ..ፓራራ›› ሙዚቃ ያልተናጠ ወጣት ምኑን ወጣት ሆነ?
ይሄ ሁሉ ሲሆን በክቡ ጥግ ቆመው ወጣቶቹን በግብረገብ ሚዛን ላይ የሚያስቀምጡ ተቆጪ አዛውንትና በአለፈብኝ ቁጭት የሚወዘወዙ ጎልማሶች ካልታዩበት ምኑን ጥምቀት ሆነ!
እንዲህ ያለውን ምስቅልቅል ግን ውብ ስእል እንካችሁ የሚል ሌላ በአል የለም፡፡
ጥምቀትን የሚመስል አንዳችም ነገር የለም፡፡
የሚገርመኝ ለወትሮው የሚያንገሸግሸኝ ጩኸትና ሁካታ፣ የድምፅ መጋጨትና መሳከር፣ የብዙ ነገር መደበላለቅ ለጥምቀት ሲሆን የሚጥመኝ ነገር ነው ፡፡ ጭራሽ ድምጽ ካልተማታብኝ፣ ነገር ካልተሳከረብኝ፣ ቀለም ካልተደባለቀብኝ ቅር ይለኛል፡፡
አለ አይደል…
እዚያ ማዶ ….
‹‹ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም ››
ወይ ደግሞ
‹‹እጣን እጣን ይሸታል መሬቱ
አባቴ ገብርኤል ያደረበቱ ››
እያሉ በመዝሙር የህዝቡን ስሜት የሚገዙ ዘማሪዎችን ስሰማ…
ከወዲህ ደግሞ
››አሞራ በሰማይ ሲያይሽ ዋለ
የአንገትሽ ንቅሳት ውበትሽን እያየ ››
እያሉ እየጨፈሩ ልጃገረዶችን የሚባብሉ ጎረምሶችን ዘፈን ስሰማ ደስ ይለኛል እንጂ አልረበሽም፡፡
ምድሪቱ ላይ ያለ ምግብን አንዱን ባንዱ ላይ እየደራረብኩ ስበላ አሁንም ደስ ይለኛል እንጂ አይጣላኝም፡፡
ጥምቀት ነዋ! ካልተደባለቀ ምኑን ጥምቀት ሆነው!
ስለዚህ ዛሬ በከተራ
ድብልቅልቅ፣ ሽብርቅ፣ ድምቅና ፍልቅልቅ ያለ የጥምቀት በዓል ስመኝላችሁ ከደስታ በቀር የሚሰማኝ አንዳችም ስሜት የለም፡፡

Forwarded from Dildiy - (ድልድይ) (Demis Seifu)
----
የሕላዌ ውበት … የኑባሬ አክሊል … የጥበባት ሁልቆ
ራስን መውለድ ነው … ከራስ ውስጥ ፈልቅቆ!!!
----
https://www.tgoop.com/bridgethoughts
የሕላዌ ውበት … የኑባሬ አክሊል … የጥበባት ሁልቆ
ራስን መውለድ ነው … ከራስ ውስጥ ፈልቅቆ!!!
----
https://www.tgoop.com/bridgethoughts
Forwarded from ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
"ብሔርተኛነት ጨቅላ ሕፃናትን እንደሚያጠቃ አደገኛ በሽታ ነው።"
በብሔርተኛነት ላይ ትችት በማቅረብ የሚታወቁት ኤሪክ ሆብስቦውንን /Eric Hobsbawn/፣ እና ፍራንዝ ፋነንን /Franz Fanon/ የመሳሰሉ ምሁራን እንደሚሉት “ብሔርተኛነት የተካረረ ልዩነትንና ቅራኔን በመፍጠር አንድን ሕዝብ በሌላ ሕዝብ ላይ አነሳስቶ ስልጣንና ሀብትን ለመቆጣጠር በመሳሪያነት ጥቅም ላይ የሚውል ርዕዮት ነው። የውጪ ጥራዝ- ነጠቅ ርዕዮት ሰለባ በመሆን ጤናማ የሆነውን የባሕልና የቋንቋ ወይም የብሔር ማንነታችንን አውዳሚ ወደሆነ የፖለቲካ መሳሪያነት በመቀየር አስተሳሳሪ ማንነታችንን በጣጥሰን ጥለነዋል። አሁን በእጃችን ላይ የቀረችው ስጋና ደሟ የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን ተነጥቃ በአፅመ-ቅሪቷ ብቻ በመኖርና ባለመኖር መካከል እየተንገዳገደች የምትገኘው አገረ-ኢትዮጵያ ነች። አገረ-ኢትዮጵያም የግንባታ ሂደቷ ከመቆምም አልፎ በመቀልበሱ ምክንያትም አሁን የምትገኝበት ደረጃ በከፍተኛ የህልውና የአደጋ ቋፍ ላይ ነው። ዓለም-አቀፍ እውቅና ኖሯት በስምና በካርታ ላይ ከመኖሯ በቀር ለህልውናዋ ዋስትና የሚሰጡ እጅግ ብዙ አስተሳሳሪ እሴቶቿን አጥታለች።
ብሔርተኛነትን በርዕዮትነት እንደማራመድ ለአገር አንድነትና ሰላም ብቻ ሳይሆን ለብሔር-ብሔረሰቦች የእኩልነት መብት መከበርም ፀር የሆነ የፖለቲካ አመለካከት የለም። አንድ ኃይል ራሱን በአንድ ብሔር ስም አደራጅቶ ለፖለቲካ ስልጣን ከታገለና ስልጣን ከያዘ በኋላ የሁሉንም የአገሪቱን ሕዝብ ጥቅምና ፍላጐት የሚያስጠብቅ የእኩልነት ስርዓት ሊመሰርት አይችልም። ብሔር የመሬት ወይም የግዛት ባለቤት ከሆነም ከዚያ ብሔር ውጪ ያሉ ዜጐች መጤና ሁለተኛ ዜጐች ተደርገው ከመታየት ሊድኑ አይችሉም።
በአገራችን በተግባር እየሆነ ያለውም ይኸው ነው። አልበርት አንስታይን /Albert Einstein/ በጥሩ አባባል እንደገለፀው ብሔርተኛነት “ጨቅላ ሕፃናትን እንደሚያጠቃ አደገኛ በሽታ” /Infantile Disease/ ነው።
የኢትዮጵያዊነትን መሸነፍ እንደ ጥሩ ውጤትና ድል በመቁጠር የሚኩራሩ የዘመናችን ብሔርተኞች ብዙዎች ሆነዋል። ይህ መኩራራታቸው የሚመነጨው ግን ብሔርተኛነት ሄዶ ሄዶ የአጥፍቶ-ጠፊነት ውጤት እንደሚያስከትል ካለመረዳት ነው። ጆን ግሬይ /John Gray/፣ በርትራንድ ረስል /Bertrand Russell/፣ ሃናህ አረንት /Hannah Arendt/ እና መሰል ፀሐፍት እንደሚሉት “የብሔርተኝነት ትግል ሲጀመር በፍጥነት የሚያድግና የሚጠናከር ሲሆን፣ በሒደት ግን በውስጡ በሚፈጥረው የጥላቻና የመከፋፈል አዙሪት ባልተቋረጠ ሁኔታ እየተበተነና እየተዳከመ የሚሄድ ነው። ብሔርተኛነት በቆየና የበለጠ በተጠናከረ ቁጥር ሁሉጊዜ የሚፈጥረው ሌላ ከሱ የባሰ ጠባብና አክራሪ ብሔርተኛነትን ነው። ከዚህ የተለየ ሌላ የእድገት ዑደት የለውም። እድገቱ ቁልቁል ነጓጅ /Degenerative/ ሒደት ነው።
አንድ ጊዜ የጋራ መተሳሰሪያችን ከሆነው ከኢትዮጵያዊነት ወይም ከዜግነት ማንነታችን መነቀል ከጀመርን በኋላ አሁን ላይ ንዑስ-ብሔርተኞች ሲሉ እንደሚሰማው ከብሔር ማንነታችን አውርዳችሁ አድዋና ተንቤን፣ ወለጋና አርሲ፣ ወይም ጎንደርና ጎጃም ወዘተ... ብላችሁ አትከፋፍሉን ብሎ ሌሎችን ማማረር ትርጉም የለውም። እንዲህ ዓይነቱ አባባል የብሔር ፖለቲካን መነሻ እንጂ መድረሻን አስቀድሞ ካለማወቅ የሚመነጭ ድክመት ነው። በዜግነት ደረጃ ያልጠበቅነውን መተሳሰር ወደ ብሔር ደረጃ ከወረድን በኋላ አስጠብቀን የማስቀጠል ዋስትና ሊኖረን አይችልም። አንድ ጊዜ የብሔርተኛነት ፖለቲካን የተለማመደ ሕዝብም የራሴ የሚለውን አገር ከመመስረት ባነሰ በሌላ ማናቸውም ዓይነት ውጤት የመርካት ዕድል የለውም። ሁልጊዜም ብሶተኛ፣ ነጭናጫና ጠባጫሪ ሆኖ የሚኖር ነው።
ተዋቂው ፀሀፊ ኤሪክ ሆፈር /Eric Hoffer/ እንደሚለው፣ “ማንኛውም የግለሰቦችን መብት ለቡድን ጥያቄ አሳልፎ የሚሰጥ የቡድን እንቅስቃሴ ሕዝብን ለጊዜው በብሶት፣ በስሜትና በጥላቻ ከማነሳሳት ባለፈ አገርንና ስርዓትን በጋራ የመገንባትና የማስቀጠል ሚና የለውም”። ባለፉት 33 ዓመታት በአገራችንም ሆነ በአካባቢያችን ሲሆን እንደታየው የብሔር “ነፃ አውጪ” ድርጅቶች ዕጣ-ፈንታ እየተበተኑ ከመሄድ የተለየ አልሆነም። የራሳቸውንም ሆነ “ነፃ እናወጣሀለን” የሚሉትን ሕዝብ ሕይወት ከመኖር ወደ አለመኖር ሲቀይሩት እንጂ ችግሩን ሲፈቱለት አልታዬም። የኦነግ፣ የብአዴን፣ የኦህዴድም ሆነ የ50 ዓመታቱ የሕወሓት የብሄርተኛነት ጉዞ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊያን ብሔርተኛነትን በአገር ደረጃ በፖለቲካ ርዕዮትነት ማራመድ ከጀመርን በኋላ በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ መጠን በሚሊየኖች ስንፈናቀልና በጭካኔ ስንጨፈጨፍ በገሃድ እያየንም ዛሬም በሚያሳዝን ሁኔታ የተለየና አዲስ መፍትሄ ማሰብ አልቻልንም። በመረረ ጥላቻ፣ በአጉል እልህና ፉክክር ሕሊናችን ስለተጋረደ “የጅል ዘዬ ሁሌ አበባዬ”እንዲሉ ዛሬም “ብሔርተኝነት ወይም ሞት!” በማለት የጥፋቱን መንገድ የበለጠ አጠናክረን ቀጥለንበታል።
ከልደቱ አያሌው ገፅ የተወሰደ

Forwarded from የስብዕና ልህቀት
በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ባህሪህን ይወስናል
ባህሪይህን ተመልከተውና በራስህ ላይ ያለህን አመለካከት በግለጽ ይጠቁምሃል፡፡ ከሰዎች ጋር ስትሆን የምትገልጠው ባህሪይ በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ነጸብራቅ ነው፡፡ ብቻህን ስትሆን፣ ስለራስህ ስታስብ፣ ራስህን በመስታወት ስትመለከተው ስለራስህ የምታስበውን ትክክለኛውን ሃሳብ አግኘውና ከሰዎች ጋር ስትሆን የምታንጸባርቀውን የባህሪህን ፍቺ ይነግርሃል፡፡
ለምሳሌ፣ ጤናማ የሆነ በራስ መተማመን አመለካከት ያለው ሰው የሚገልጠው ባህሪይና የዝቅተኝነት ስሜት ያለው የሚገልጠው ባህሪይ አንድ አይደለም፡፡
እንደተገፋና እንደተናቀ፣ ዝቅተኛ እንደሆነ የሚያስብ ሰው ማንም ሳይነካው ሰውን የሚነካና የሚተናኮስ ባህሪይ ያዳብራል፡፡ ማንም ገፋው አልገፋው ምንም ለውጥ እንደማያመጣበት የሚያስብ ሰው የተረጋጋና አላማው ላይ የሚያተኩር ባህሪይ ይታይበታል፡፡
ለምንም ነገር ያለመመጠን ስሜት ያለበት ሰው የፍርሃትና የአይን አፋርነት ባህሪ ይወርሰዋል፡፡ የሚመጥን ማንነትና አመለካከት እንዳለው የሚያስብ ሰው ደፋርነትና ተግባቢነት ይኖረዋል፡፡
ሰዎች አይፈልጉኝም የሚል ስሜት ያለበት ሰው ለሁሉም ሰውና ለሁሉም ነገር እሺ ባይነት ያጠቃዋል፡፡ ተፈለገም አልተፈለገም ተረጋግቶ የሚኖር ሰው ያመነበትንና ያላመነበትን በመለየት ሃሳቡን መግለጽ ችግር የለበትም፡፡
ተወዳድሮ ለማሸነፍ እንደማይበቃ የሚያስብ ሰው አታላይና አጭበርባሪ ባህሪይን ያዳብራል፡፡ ምንም ነገር ቢሆን ራሱን አሰልጥኖ መወዳደር እንደሚችል የሚያምን ሰው ደግሞ ቀጥተኛና እውነተኛ ይሆናል፡፡
በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ጤናማ ሲሆን ማሕበራዊ ግንኙነትህም እንደዚያው ጤናማ ይሆናል፡፡
ስለዚህ ማሕበራዊ ሕይወትህ እንዲስተካከል ከፈለክ በቅድሚያ በራስህ ላይ ያለህን ምልከታ አስተካክለው፡፡
ዶክተር ኢዮብ ማሞ

ኑሮ አያሻግርም!
እኮ ማነው!
የሰውነት ድልድይ እንዲህ እየፈረሰ፣
የሰውነት መንገድ እንዲህ እየሻከረ፣
መንገዱን ሊያስውብ እንዲህ ያሳመረ?
ይልቅ ንገሩልኝ!!
ለእንደኔ ዓይነቱ ሰው፤
በግርግር ደቦ ትልሙ ለፈረሰ፤
የአበባ ዘመኑን በነጠላ መንገድ ሲጓዝ ለጨረሰ፡፡
በቁስ መደራረብ፣
በዜና ጋጋታ ተስፋ አይሰፈርም፤
“አስፓልት” እግር እንጂ ኑሮ አያሻግርም!
በረከት በላይነህ
የመንፈስ ከፍታ
@Zephilosophy
እኮ ማነው!
የሰውነት ድልድይ እንዲህ እየፈረሰ፣
የሰውነት መንገድ እንዲህ እየሻከረ፣
መንገዱን ሊያስውብ እንዲህ ያሳመረ?
ይልቅ ንገሩልኝ!!
ለእንደኔ ዓይነቱ ሰው፤
በግርግር ደቦ ትልሙ ለፈረሰ፤
የአበባ ዘመኑን በነጠላ መንገድ ሲጓዝ ለጨረሰ፡፡
በቁስ መደራረብ፣
በዜና ጋጋታ ተስፋ አይሰፈርም፤
“አስፓልት” እግር እንጂ ኑሮ አያሻግርም!
በረከት በላይነህ
የመንፈስ ከፍታ
@Zephilosophy
Forwarded from የስብዕና ልህቀት
አንዳንዴ . . . ያለ ነው!
አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም!
አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም!
አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም!
አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም!
አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም!
አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም!
አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም!
አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም!
አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም!
አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም!

ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ መሪዎች ሰው መሆናቸውን እጠራጠራለሁ አሉ‼️
👉🏿 ከ50 ዓመታት የአህጉሪቷ የነጻነት ጉዞ በኋላ፣ ለህዝባችው አስፈላጊውን መሠረተ ልማት ካላሟላችው ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?
👉🏿በወርቅ፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ፣ በዩራኒየም፣ በብረት፣ በማዕድን፣ በብር፣ በማግኒዥየም፣ በነሐስ፣ በጋዝ የተፈጥሮ ሃብቶቻችው ላይ ተቀምጣችው፣ ህዝባችው በረሃብ፣ በትምህርት አለመዳረስ፣ በጤና አገልግሎት እጦት፣ ቢሞት፣ ሰው ነን ብላችው ታምናላችው?
👉🏿በስልጣን ላይ ቆይታችው፣የራሳችሁን ዜጎች ለመግደል ከውጭ የጦር መሣሪያዎችን ስታስገቡ፣ ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?
👉🏿የገዛ ዜጎቻችሁን እንደውሻ ስታንገላቱና ስትገድሉ፣ ማን ዜጎቻችሁን እንዲያከብር ትጠብቃላችው?
👉🏿በራሳችው አገር ላይ ቀማኛና ሌባ በመሆናችው ፣ የሃገራችሁን ሀብቶች ሁሉ በመስረቅ፣ አብዛኞቹ ዜጋዎቻችው በስደትና በድህነት ውስጥ እንዲያልፉ ስታረጉ፣ የሰው ልጆ ነን ብላችው ታስባላችው?
ትራምፕ ይሄን የተናገሩት ሰሞኑን በዋሽንግተን ዋይት ሀውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መሆኑን ተመልክቻለሁ።
[አዩዘሀበሻ]
===================

Forwarded from አርምሞ🧘🏽♂
-እንዲህም አለ፦
“I am not God. I am not a Deva. I am a Human… I am the Awakened one, who has seen the Truth of the world.” በሰውነቱ ውስጥ ያሉትን አተሞች ሁሉ ለመቁጠር በሚያስችል መልኩ ስለ አእምሮው ጥልቅ ትንታኔ አድርጓል።
-
“Noting in this world is solid” ለዚህ አባባሉ ዘመናዊ ትርጓሜውን ልተነትን ብነሳ ረጅም ነው። ነገር ግን አሳጥሬው እንዲህ ያለህ ነው፦ ሁሉም ነገር ባዶ ቦታ ባላቸው ጥቃቅን ቅንጣቶች ተከቧል። እና እነዚህ ቅንጣቶች በቋሚ እንቅስቃሴ እና ፍሰት ውስጥ ከሚገኙ ጥቃቅን የኃይል ኳሶች በስተቀር ምንም አይደሉም። የሰው ልጅን ጨምሮ ለትንሽ ነፍሳት የምንታየው ልክ እንዲህ ባለ ኤሌክትሮኒክስ ኃይል ተበታትነን ነው። እናም አንዲት ትንሽ ነፍሳት ስላየችው አንድ ሰው አቋም ብንጠይቃት፤ ጥቃቅን የኤሌትሪክ ኳሶች በአንድ ቦታ ተሰብስበው እንደተመለከተች ነው የምትነግረን።
-ይህ ሰው የሚያገኛቸውን ሰዎች በጠቅላላ ቋንቋቸውን በአንዴ የመልመድ ብቃት ነበረው። ነገር ግን ሁሌም ሲሰበሰቡ የሚናገረው ንግግር የፓሊ ቋንቋ ብቻ ነበር። በጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ ተመስጦ ሲያደርግ የትኛውም እንስሳ አይጎዳውም ነበር። እንስሳቱ እሱ ጋር ሲደርሱ ቦዲ ትራዛክሽናቸው እና ኬሚካል ሪአክሽናቸው ይዳከማል። በሜታ
“Amity benevolence” የተጠራቀመው ኃይሉ በእንስሳቱ ላይ እርጋታ ይለቅባቸዋል።
-“
Rebirth” የዳግም የመወለድን ጽንሰ ሐሳብ በሰፊው አጋርቷል። ራሱን በራሱ ተመልክቷል እናም በዚህ ህይወት ውስጥ “ቡድሃ:የበራለት” ለመሆን የበቃው ቀደም ባሉት ህይወቶች ሁሉ በሰራቸው መልካም ስራዎች ምክንያት እንደሆነ ደጋግሞ ተናግሯል።
-እንደ አንጉሊማላ ያለ የ999 ሰዎችን ነፍስ ያጠፋ፤ እንደ አምራፓሊ ያለች የከተማዋ ዝሙተኛ ሴት፤ እንደ ሳካካ ያሉ ፀባየ ጥፉ ተከራካሪ እና ቡድሃን በየቀኑ የሚያሽጓጥጠው ሁሉም በጠቅላላ ወደ ሀይማኖቱ ገብተው “አርሃንት” ሆኑ።
-ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ቀልድ የማይቀልድ፣ ሐሜት የማይወድ እና በሰው የማያሾፍ ነገር ግን ሁልጊዜ ፊቱ ላይ በሚበራው ፈገግታ ያገኙትን ሁሉ መማረክ የሚችል፤ ድንቁ አስተማሪ ሲድሃርታ ጓተማ ቡድሃ ነበር።
-ቡድሃ አንድ ቀን ለምጽዋት ሲሄድ አንድ ትንሽ ልጅ ከፊት ለፊቱ አንድ አቧራ የለበሰ ሳህን አነሳ። ቡድሃ በቀስታ ፈገግ አለና የምጽዋውን ሳህኑን ወደ ፊቱ አስጠጋው። ደቀመዝሙሩ አናንዳ የፈገግታውን ምክንያት ምን እንደሆነ ጠየቀው። ቡድሃም፦ “ይህ ልጅ በፓታሊፑታ ከተማ የኔፓሪኒባና ሞት በማስከተል ይሞታል። ከሁለት አመት ተኩል በኋላ እንደገና ይወለዳል። እና ቻካቫቲ
“wheel turning” ንጉሠ ነገሥት ይሆናል። እና ለቡድሂስት አገዛዝ ጥቅም 84,000 የብረት ቤተመቅደሶችን በመገንባት ታሪክ ይሰራል። ይሄም ልጅ በነሱ ዘንድ ታላቁ አሾካ የሚባለው ንጉስ ነበር። አሾካም በጣም ጥሩ መልክ የነበረው፣ የተመጠነ ቁመት፣ ሰፊ ትከሻዎች፣ ረጃጅም ጆሮዎች፣ ሰማያዊ አይኖች፣ ፀጉሩ ላይ መለስተኛ ጠባሳ እና በቸርነት እና ምህረት የተሞላ ንጉስ ነበር። ከአስደናቂው ገላው ውስጥ ማራኪ ጠረን እንደሚወጣው ተነግሯል።
-ከቡድሃ ብዙ ደቀ መዛሙርት መካከል አናንዳ የማስታወስ አቅሙ የጎላ እንደነበር ይነገራል። አብዛኞቹ የቀደሙት የቡድሂስት ሱታ ፒታካ ጽሑፎች በአንደኛው የቡድሂስት ምክር ቤት የቡድሃ ትምህርቶችን ጨምሮ አንድ ላይ ለአስተምህሮ ያበቃው አናንዳ ነው።
-ዛሬ የቡድሃ ሃይማኖት እጅግ በጣም ሳይንሳዊ አስምህሮ ተደርጎ ይወሰዳል። እና አንዳንድ ልዩነቶችም እንዳሉ መካድ አያስፈልግም። በጊዜ ሂደት የተከሰተ ነው። ቡድሃ የሰጠው የአዕምሮ እና የአካል እውቀት የልቡ እምነት እውነታ እንጂ ለየትኛውም የሃይማኖት ህግጋት የሚውል አስተምህሮ አልነበረም!።
-አናንዳ ከመነኩሴው ቡድሃ የህይወት ክህሎት በመነሳት፤ ሁል ጊዜ ቢሆን ይጾማል እናም እስከ ፓሪኒባና ድረስ በባዶ እግሩ ረጅም ርቀት በመጓዝ ያስተምርም ነበር። መገለጥን ካገኘ በኋላ ከቤተሰቡ ጋር ተገናኘና አባቱን፣ እናቱን፣ አሳዳጊ እናቱን፣ ሚስቱን እና ልጁን ወደ ኒባና መራቸው። የአገሩ ሰዎች ሲናገሩ እንደነሱ አይነት ደስተኛ ቤተሰብ አጋጥሞን አያውቅም ይላሉ። የዚህ ሁሉ ስነ መሠረት የሆነው መምህሩ ቡድሃ ታላቁ ሳይንቲስት ከ2600 ዓመታት በፊት የተወለደ ሲድሃርታ ጓተማ ነበር፤ የእሱን ፈለግ የተከተሉት ሰዎች በጠቅላላ የመገለል፣ የመረጋጋት አስተምህሮ እናም ደግሞ የተመስጦ ቴክኒኮችን አሁንም በመተግበር ላይ ይገኛሉ ይህም በዓለም ዙሪያ አድናቆት ያለው ስብስብ ነበር።
-በቡድሃ ውስጥ በጣም የሚያስደንቀው ነገር ከምቾት ቀጠና ወጥቶ እውነትን የፈለገ ብቸኛ ሰው መሆኑ ነው። ይህ ብሩህ አእምሮ ያለው ሰው አምላክም አይደለም፣ ነቢይም አይደለም፣ እሱ ተፈጥሮውን የተረዳ አንድ ሰው ነው። ታድያ እንደ ሰው ኖረና ሞተ። በሃይማኖቱ ውስጥ የገነት ተስፋ የለም፤ የገሃነም ስጋት አልተቀመጠም። ለመጸለይ አገልግሎት የተቀመጠ መፅሃፍ የለም። እሱንም መከተል ግዴታ አልተደረገም። ምንም አስገዳጅ የአምልኮ ሥርዓቶች አልተቀመጡም። ብቻ የቡድሃን ትምህርቶች መከተል አንድ ሰው የተሻለ ሰው ያደርገዋል። “ድሃማ” የሚባለው አስተምህሮቱን አንድ ሰው መማር ካልፈለገ አይጎዳውም፤ ነገር ግን እሱ ወይም እሷ የተሻለ ሰው የመሆን እድላቸውን ያጣሉ!።
Forwarded from ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
ቡድናዊነት በድናዊነት?
ብርሀን ደርበው
የምንከተለው ፋሽን፣ የሚያስቁን ቀልዶች የምንወዳቸው ሙዚቃዎች ወዘተ ወዘተ... እውን የወደድነው የምንወደውን ነው? የምናደርገው ሁሉ በራሳችን ውሳኔ እና ፍላጎት የተደረገ ወይስ ቀልብያችን የሚለን ሌላ ሆኖ አንዳች ኃይል አስገድዶን?
አንዳንዴ እራሴን እንዲህ ብዬ ጠይቃለሁ የምትከተለው ፋሽን የሚያስቁህ ቀልዶች የምትወዳቸው ሙዚቃዎች ወዘተ ወዘተ... ያንተ ምርጫ ወይስ አንዳች ኃይል አስገድዶህ ምትመርጠው? እውን የወደድከው ሁሉ የምትወደውን ነው? የምታደርጋቸው ውሳኔዎች ባንተ ፍላጎት በቀልብያህ ፍቃድ ወይስ ሌሎች ስለወደዱት ላለመነጠል በዓለም ውስጥ
መናኒ ላለመሆን?
Solomon Asch የተባለ ሳይኮሎጂስት Confirmity Line Experiment የምትባል የሰውን ልጅ ውሳኔ አሰጣጥ የምትገመግም አንዲት የምትገርም ጥናት አለችው። እነሆ ጥናቱ A,B,C ሲል የሰየማቸውን ሦስት የተለያየ ቁመት ያላቸው መስመሮች አዘጋጀ።
ተሳታፊዎች በተዘጋጀላቸው ክፍል ውስጥ ሁሉም በየተራ የትኛው መስመር ረዥም እንደሆነ ጮክ ብለው ይናገራሉ። ታድያ ይሄ ሁሉ ሲሆን ክፍሉ ውስጥ በየዙሩ ከሚገኙት ተሳታፊዎች ከአንዱ ወይ ከሁለቱ በቀር ሁሉም ተዋናያን(ሆን ብለው ስህተት የሆነውን እንዲመርጡ) ይሆኑና በመጨረሻ የተቀረው መልሱን እንዲመልስ ይደረጋል።
ታድያ ውጤቱም ከቅጥረኛ ተዋናያን ጋር ከነበሩት ውስጥ በአማካይ 75% ተሳታፊዎች ቢያንስ አንዴ ስህተት የሆነ መልስ ሰጥተዋል። በአንጻሩ ያላንዳች ተጽእኖ ለብቻቸውን (control group) የመለሱ ተሳታፊዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ትክክለኛውን መልስ መልሰዋል።
በጥቅሉ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው እውነታው ግልጽ እና እርግጥ ሆኖ ሳለ ከሌሎች ላለመነጠል ሲል እያወቀው አልያም ብዙ ሰው ካለውማ ልክ ነው (ሞት ከአገር ጋር እንቅልፍ ነው እንዲሉ አበው) በማለት ካለው እውነት የብዙኃኑን ስህተት ይቀላቀላል።
ግላዊነት በሚንቆለጳጰስበት በዚህ በዘመነ ሉላዊነት ምንበላውን ምግብ ፣የት መብላት እንዳለብን፣ ምንለብሰውን ልብስ፣ ማንን መጥላት፣ ማንን መደገፍ እንዳለብን ሁሉ ባንድም ይሁን በሌላ መንገድ የሚወስንልን ማህበራዊ ሚድያው ሆኗል። ፍቅራችን አድናቆታችን ጥላቻችን የኛ አይደለም። ከየትኛውም ጊዜ በላቀ የመንጋነት ስነልቡና በዓለም ላይ ተንሰራፍቷል። ሌሎችን ቀድሞ መከተል ሌሎችን እንደመምራት የሚቆጠርበት ዘመን ላይ ነን።
ቡድናዊ አስተሳሰብ የተለየ ሃሳብ ማመንጨትን ፣ በተለየ መንገድ ነገሮችን ተረድቶ የተለየ
መፍትሔ መስጠትን ፣ አዲስ እይታን፣ ልዩ ምልከታን በጥቅሉ በራስ መቆምን የሚገድል
ከቡድን ውጭ ያለን ሁሉ በድን የሚል ምልከታ ነው።
Hannah Arendt የተባለች ፖለቲካል ፊሎሶፊስት Adolf Eichman ስለሚባል የናዚ መኮነን የፍርድ ሂደት ላይ በጻፈችው Eichman in Jerusalem በተባለ መጽሐፏ እንዲህ ትለናለች ‘’The sad truth is that most evil is done by people who had never made up their minds to be good or evil. ‘’
የሚያሳዝነው ብዙ ክፋቶችና ጥፋቶች የተሠሩት ክፉና ደጉን ለይተው ክፋትን በሚፈጽሙ ክፉ ሰዎች እና አረመኔዎች ሳይሆን ኢየሱስ “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው።” እንዳለው የሚያደርጉትን ሁሉ አስበውበት ሳይሆን አሳስበዋቸው በፈጸሙ ፤ ስማ በለው በሚመራቸው ጆሯቸው የአእምሮዋቸውን ቦታ በተካባቸው ብኩኖች ነው።
ከሶቅራጥስ ግድያ እስከ ክርስቶስ ስቅላት፣ከጆርዳኖ ቡሩኖ ቃጠሎ እስከ ስልሣዎቹ መረሸን፤ ከናዚ የዘር ፍጅት እስከ አገራችን ፍጅት በፍራቻ በጥላቻ ና በስጋት
ቡድኖች በባህል በፖለቲካ እና በሃይማኖት ስም የመንጋ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ታላቅ ጥፋት
አድርሰዋል እያደረሱም ነው።
ብዙኃንን መከተል ለምን?
የሰው ልጅ ተፈጥሮ(Human natures need to belong) Aristotile(አርስጣጣሊስ) Man is by nature a social animal ሰው በተፈጥሮው ማህበራዊ እንስሣ ነው ይለናል።
በሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ውስጥ ለአደን ለመሄድም ሆነ ከአራዊት ጥቃት እራስን ለማዳን የሰው ልጅ ሕይወቱን ለማስቀጠል የሄደበት መንገድ በቡድን መሆንን ነው። ታድያ በስነ ተረክ እና በባህል ተጠቅሞ ኃይልን ለማንበር ፣ ሰላምን ለማስፈን እና ነውጥን ለመግራት የሚያደርገው ትግል በ DNAያችን እና በ ንቃት ህሊናችን ውስጥ ስለሚታተም ከመንጋው መነጠል ወደ ሞት መጓዝ ነው ብሎ እንዲያስብ እና እንዲደምድም ያደርዋል።
ታድያ እርግጠኛ ባለመሆን ፤ተቀባይነትን ለማግኘት፤ መጣልን/መገለልን ፍራቻ በጥቅሉ ክብርን ለማግዘፍና ህላዌን ለማስቀጠል ሲል ብዙኃኑን ይከተላል።
የማህበራዊ ሚዲያን መስፋፋት ተከትሎ የዲጂታል መንጋነትም ለመቆጣጠር በማያስችል ሁኔታ እየተስፋፋ ነው። ጭብጨባችን እንኳ የራሳችን አይደለም። የገደል ማሚቶዎች ሆነናል ፤ በቀቀናዊ ማንነትን ተላብሰናል። ነገሩን ተረዱትም አልተረዱትም ሃሳብን በሃሳብ ከመሞገት ይልቅ በስድብ፣በዛቻ እና በማስፈራራት የሚመልሱ ከልቡናቸው/በጣታቸው በኩልም ይሁን በአፋቸው/ ከጸያፍ ነገር በቀር የሌለ የሚመስል ባለማእረግ ተራጋሚዎችን እያፈራን ነው።
ዲጂታል መንጋዎች ተከታዮቻቸው እንዲነኩባቸው አስተያየት እንዲሰጥባቸው አንዳች ትችት እንዲደርስባቸው አይፈልጉም። የሚከተሉትን ሰዎች ከፈጣሪያችው እኩል አንዳንዴም በላይ እንከን የለሽ አድርገው ስለሳሏቸው እነሱን ለነካባቸው እንጦሮንጦስ ድረስ ወርደው በቀል የመሰላቸውን ነገር ለማድረግ ሁሌም ዝግጁ ናቸው።
ኒቼ Beyond Good and Evil መጽሐፉ ላይ እንዲህ ይላል “Insanity in individuals is something rare - but in groups, parties, nations and epochs, it is the rule.” ቡድኖች እብደታቸውን ሕግ ያደርጉታል።
በማህበር ሲታበድ፤ በጎራ ሲወፈፍ፣ በወል ሲነሆለል፤ ስሜት ይነግሣል ምክንያት ቦታ ያጣል። መቃወም ያስወግራል ፣ መለየት ያስቀጣል ፣መሞገት ያሠድዳል፣ መመርመር ያስቀስፋል ። ከኛ ወዲያ ክንደብርቱ ከኛ ወድያ ኃያል ርቱዕ ከኛ ወድያ ጎራሽ... ፣ ከኛ ወዲያ ላሳር ከኛ ወድያ... ። የሁሉ ነገር መለኪያ ፣ የሁሉ ነገር መተኪያ፣ እና ሁሉ ነገር በራሱ እኛ ነን የሚል የተደፈነ አስተሳሰብን ያጸናል።
እኛ ደሞ(የመተርጎም ነጻነቱን ላንባቢው ትተን) መኖርን የሚያክል ጥናት የለምና ኖረን ካየነው እንዲህ እንላለን Even a pacifist in a mob could become a warmonger.
ቡድናዊነት/የመንጋ እሳቤ በግለሰቦች ውስጥ ያለን እውነት፣ ለውጥ ፣ሂደትና ፈጠራ ወደ በድንነት በመለወጥ በራስ መቆምን የሚያሽመደምድ ነው። መንጋነት ሲነግሥ ሰውነት ይረክሳል፣ ፍትሕ ትንጋደዳለች፣ ስልጣኔ አፈር ይበላዋል።የወል እሳቤ ማጤን መመርመርን በጥቅሉ ሰው መሆንን የሚገድል ነቀርሳ ነው።
በጅምላ ማሰብ፤ የሰው ልጅ የመጀመርያው ሞቱ ነው። ቆም ብለህ አስብ።ከእሳቱ ከልለው ከጨለማው የዶሉህን ትተህ የራስህን ሻማ ለኩሰህ ብርሃንህን አብራ።ሰው ሆነህ ሳለህ እራስህን ስለምን ታሳንሳለህ? ራስህን ችለህ አስብ! በራስህ ተጠራ! ሰው ሁን!
ብዙኃን በመንጋ ፣በቡድን፣ በጎራ ሲያስቡና ሲወስኑ ብቻቸውን መቆም የቻሉ ምንኛ የታደሉ ናቸው። የሰውነት ምልአት የመሻገር ከፍታ እነርሱ ጋር ናትና።
ቸር ያቆየን!
Credit to ባይራ ዲጂታል መፅሄት
@Bayradigital