Telegram Web
ሽሮም በላህ ስጋም በላህ እኩል ትጠግባለህ!
የተሰጠህን አሜን ብለህ ካልተቀበልክ ያለህን ትቀማለህ እና ባላቹ ነገር ተደሰቱ😘😍
በፀጉር ላይ ፀጉር እየደረብሽ በጠፍር ላይ ጠፍር እየደረብሽ ታዲያ እንዴት በእኔ ላይ ሌላ ወንድ አለመደረብሽን እርግጠኛ እሆናለው🤷‍♂
የሴት ልጅ የዋህነት የሚገባህ አንተን ለማስቀናት ብላ የማታውቀውን ወንድ ፎቶ Profile አድርጋ ስታያት ነው😜🤣
ዘንድሮ ፀባችን ለዘመድ ለመንገር እንኳን ያስፈራል እስኪ እንዴት ነው ፍቅረኛዬ ቂጥ ግዛልኝ ብላኝ ተጣላኋት ብዬ ለእናቴ የምነግራት🤔
ከዚህ ወድያ አልወድሽም

.
.
.
ከዚህ ወድያ አልወድሽም
የለም እወድሻለው ገና
ማፍቀር አጭር ቢሆንም
መርሳት ረጅም ነውና።

ከበዕዉቀቱ ስዩም

@Eliasshitahun
@Eliasshitahun
@Eliasshitahun
ብዙ ጊዜ ፍቅርን እንሰብካለን ግን አንኖረውም ትርጉሙ ሚገባን ግን ስንዘምርለት ሳይሆን ውስጡ ሆነን ስናጣጥመው ነው
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@yefkralem
ገፅ:- ፩
አርብ:- ሰው የተፈጠረበት ቀን፡፡
(ዘወትር አርብ ምሽት)
--------/////---------
ሰው አንድም ዛሬ
አንድም ነገ
አንድም ትናንት፡፡
አንድም አሁን በአካል
አንድም ነገ በተስፋ
አንድም ትናንት በትዝታ፡፡
"ትዝታህን ውሰድ ብለሽ የላክሽብኝ
አንቺው ጋር ይቀመጥ እኔም ያንቺ አለብኝ፡፡"
የትዝታ ባሪያዎች ነን፡፡ እወቀታችንም እምነታችንም ምን ቢገዝፍም የትዝታ ባሪያዎች ነን፡፡ በሳይኮሎጅስቶች ነገህን አስብ ትናንት አልፏል ብንባልም፡፡ ሰው የትዝታው ባሪያ ነው፡፡
በጊዜ ብዛት የስሜቱ መጠን ይቀንስ ወይ ይጨምር ይሆናል እንጂ፡፡ መርሳት አይቻለንም፡፡ እንርሳ ብለን ስንሟገት በዛው ቅፅበት ነገሩን እያሰብነው ነው፡፡ ይሄንን ፅሁፍ እንኳን እያነበብን ወደ ብዙ ትዝታ ተስበናል፡፡ በልብ የተኖረ በጭንቅላት መቀመጡ አይቀሬ ነው፡፡ ትዝታን ጠላቴ ብሎ መጥራት ራስን መካድ ነው፡፡ ለተኖረው ትናንት ራስን ማመስገን ትልቅነት ነው፡፡ ክፉም ይሁን በጎ፡፡
የብዙ የአእምሮ በሽታ ተጠቂዎች ፍላጎት ወደትዝታ ተመልሶ ማን እንደነበሩ ማስታወስ ሲሆን የብዙ ጤነኞች ፍላጎት ደሞ ማን እንደነበሩ መርሳት ነው፡፡ ያሳለፍነው ለመርሳት የምንታገለው የሆነውን ማመን መቀበል ስለማንፈልግ ነው፡፡ የትናንት የፍቅር ትዝታችንን ለማጥፋት የምንጥረው የፍቅር ወዳጃችን ስለጠፋ ነው፡፡ ከፍቅረኛ ስንለያይ ከትዝታ ጋር መኖር የጀመርን ይመስለናል፡፡ ግን ትዝታው መጀመሪያም ተቀመጦ ነበር፡፡ለማሰብ እንችል ዘንድ ግን አልቻልንም፡፡ ምክንያቱም የትዝታችን ባለቤት አጠገባችን ነበርና፡፡ ስንለያይ ግን የኖረንው ሁሉ መታሰብ ይጀምረናል፡፡
ትዝታ ህመም አይደለም፡፡ ትዝታ መርገም አይደለም፡፡ ትዝታ ከሰው በተለየን ጊዜ ሰውየውን እኛ ጋር የሚያስቀርልን ከሷ በተለየን ጊዜ እሷን እኛ ጋር የሚያስቀርልን በረከት ነው፡፡

* * * * * * * * * *
ገፅ- ፪
አርብ:- ሰው የተፈጠረበት ቀን፡፡
........./////..........
ስህተትን አለመቀበል ያህል ደዌ የለም፡፡ ስናጠፋ እንፈራለን ስንፈራ እንደበቃለን ስንደበቅ እንጋለጣለን ስንጋለጥ እንዋሻለን ስንዋሽ እንሳሳታለን ስንሳሳት እንፈራለን.....ተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ እንወድቃለን፡፡
ሰው መሆናችንን መቀበል የምንወደው በበጎ ጎኑ ብቻ ነው፡፡ ክፉ ማንነታችን ላይ ሰውነትን እናጣጥላለን እንነጥላለን፡፡
ልክ ስንሆን እኛ ነን ብለን ደረት እንነፋለን፡፡ ስንሳሳት ሌላ 'እኛ' እንፈጥራለን፡፡ ስህተታችንንን ለሰይጣን ወይ ለመጠጥ ወይ ለስሜታዊነት እንድረዋለን፡፡ የናንተ ነው ስንባል አንቀበለውም፡፡
በሰው እና በፈጣሪ መሐል ያለ እርቅ የሚጀመረው ስህተትን በመቀበል ነው፡፡ ያልተቀበልነው ስህተት ይቅርታን አያሰጠንም፡፡
ከፈጣሪም ከራሳችንም ጋር ያለንን እርቅ ስሕተታችንን በመቀበል እንጀምረው፡፡ ከደሙ ንፁህ ነኝ ማለት ብቻ ንፁህ አያረገንም፡፡ እጃችንን ስንታጠበው ብንውል አንነጻም፡፡
መቀበል፡፡
እንደሴተኛ አዳሪዋ ሴት ....እንጴጥሮስ .....እንደ.... እንደ.....መቀበል ነጻ ያወጣናል፡፡
ተባረክ ስሕተት
ተመስገን ስሕተት ብለን አሜን ካልን ንስሃም ቅርብ ነው፡፡ እንቅልፋችንን የምናጣው በስሕተት ቆጠራ ጊዜያችንን ስለምንገፋው ነው፡፡ ይቅር እንበለው እኛነታችንን፡፡
እንታረቀው፡፡ ከራሳችን እና ከሰዎች ስሕተት ጋር ማሪያም ጣት እንሰጣጥ፡፡

* * * * * * * * * *
እቀናለሁ አዎ
አጥንት ያነቅዛል ሲል ባይገባንም ውሉ
ቅናት ይሉት ነገር ተሰጥቷል ለሁሉ፡፡
አዎን እቀናለሁ
ያልቀኑበት ነገር ሲነጠቅ ስላየሁ፡፡
ብቻ ወድሽ የለ እኔ ምን አውቅና
ራሴን የማገኝ በሆንሽው ስቀና፡፡
ይኸውልሽ ጉዴ
ከከንፈርሽ በታች
ባለው ጥቁር ነጥብ ስቀና እያየሽኝ
እንደማላቅ ነገር ማርያም ስማኝ አልሽኝ፡፡
ለምን
ለምን ከንፈርሽ ጋር
ለምን አንቺን መርጣ
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን ሳመችሽ ስል ብዬ ደፋ ቀና
አትፍረጂ ፍቅሬ
አፍቃሪ አይመርጥም በፍቅሩ ሲቀና፡፡
(እኔ ምን አቃለሁ
ብቻ ወድሻለሁ!!)
እናቴ
"ፌስቡክ ክፈትልኝ"

ደገጥኩ ፡፡ የቀልዷን ቢሆንም ቢሆንም ክው አልኩ፡፡ "ለምንሽ?" ልላት ነበር ተውኩት፡፡

እናቴ ፌስቡክ የላትም!!! ስለዚህ ምርጥ እናት አለኝ፡፡

በውስጤ ስንቱን አወጣሁ አወረድሁ....
:
ታድለሻል አንቺስ ባለሽበት አለሽ፡፡
በነበርሽበት፡፡ ሽበት ጨመርሽ እንጂ፡፡ ንቀት አልጨመርሽም፡፡ ታድለሻል፡፡


የእናትነት በረከት ስለልጇ ምንም መረጃ አለመስማቷ መሰለኝ፡፡ ዘላለም የፍቅር ሀውልቷን የሚንድባት ምንም ነገር አታውቅም፡፡


ከሰው
ከሴት
ከመጠጥ ቤት ዳታ የላትም ስለልጇ፡፡ ምን እንደተባለ ምን እንደሚባል አታውቅም፡፡


እናቴ ፌስቡክ የላትም!!!
ያው ነች ለልጇ እንደነበረችው፡፡ እንደስላሴ ቁጥር፡፡ አልጨመረችም አልቀነሰችም፡፡

የልጇን ጉድ የስሙን ብዛት እንደመልዕክት ዩሀንስ ቃላት አንዴ የሚጣል አንዴ የሚነሳ ልጅ እንዳላት አታውቅም፡፡ ታድላ!!!

"ይቅርብሽ አልኳት" በደፈናው፡፡
:
ካህን ከነታቦቱ የሚታማበት ሰፈር ነው ፌስቡክ

አልኳት::

ገጣሚ ከነውርደት አጋጣሚው የሚዘረገፍበት

ማርያም ከነልጇ የምትሰደብበት

አንዳንዱ "እናትህ እንዲህ ትሁን" ብሎ ለእናት ያለውን ክብር የሚያስረዳበት ..የሚከራከርበት፡፡

ጁመዓ ከነሼኹ የሚዋረድበት

ጠቅላይ ሚንስትሩ ተከታይ ለማፍራት ከሀበሻ ሜም ጋር የሚፎካከሩበት

በሰባት ሥላሴ ናቸው ብሎ ሰባት ላይክ ለማግኘት ሰባቴ ጥቅስ የሚለጥፍ ሰው የሞላበት

ባለዜና
ባለዜማ
ባለሀገር
ባለሸገር
ባለ በሌለ ነገር ሁሉ የሚዘባረቅበት...

ኢንተርኔት አይደለም አምፖል ለሌላቸው ገበሬዎች በኢንተርኔት ትግል የሚካሄድበት የሆነ ነገር ነው ፌስቡክ፡፡
" ይቅርብሽ " አልኳት በደፈናው፡፡



እናቴ ፌስቡክ የላትም!!! ስለዚህ እናት አለኝ፡፡
አሸንፈናል....ግን ይርበናል?
(ሦስት ተከታታይ ክፍል ያለው ህመም)
ክፍል-፩
:
:
ዘመን የየራሱ 'ማይግሬን' አለበት፡፡ ትውልድ የየራሱ ሽባነት አለው፡፡ የሁሉም 'አሁን' ምንጭ 'ትናንት' ነው፡፡

ትናንታችን ውስብስብ ነው ለማለት አሁንን ማየት በቂ ነው፡፡ በየጦርነቱ በየምሽጉ ድል የሚቀናን ህዝቦች ለመሆናችን ምስክር አያሻንም፡፡

አድዋን ለማክበር በየአመቱ ወደ ፒያሳ ከሚወጡት ወገን ነኝ (ወይም ነበርኩኝ)::

ወደ እንጦጦ ወደንጉሱ ቤት እሄዳለሁ፡፡
በፀሀይ
በረሀብ
በድካም፡፡
(ልብ በሉልኝ የድል ቀን ነው)

የገጠር ቤት እያየሁ፡፡ ውሃ መብራት በቅጡ የሌለበት የሀገሬን ጎጆ እየታዘብኩ፡፡ ደግነት ያለው ያገሬው ሰው ልቡ ልተለወጠም፡፡ ኑሮውም አልተለወጠም፡፡ የአድዋ ጦርነት ጊዜ በነበረበት ድህነት አለ፡፡

ጥያቄ፡- ያሸነፍናቸው ይጠግባሉ
ያሸነፍናቸው በመኪና ነው የሚንደላቀቁት ያውም በነፍስ ወከፍ ገቢ፡፡ እኛስ?

ለዛ ነው ትውልዱ መንገድ ላይ ከነኮተቱ እንደቀረ ቤት ተከራይ ላጤ የተደናበረው፡፡ ዕቃ አለው ከትናንት የተረፈው ታሪክ ውርስ ግን ለሱም ለተረፈውም የሚሆን መጠጊያ የለውም፡፡ የተረፈው ነገር ከምን አዳነው?

ማሸነፋችን ከምን አዳነን?
ከምን?

ከማንነት ዝቅጠት?
ከእርስ በእርስ ጦርነት?
ከመናናቅ?
ከሙስና?
ከችግር ከችጋር?
በራስ ከማፈር?
ከምን?
:
:
በሀቅ መሞገት ያለብን የራሳችን የውስጣችን ጠብ ላይ ነን፡፡ (Inetrnal conflict ) ይሉታል፡፡

ኩራት ራት ሆኖብን ካልሆነ በየመንገዱ የወደቀው ነፍስ ብዛት
የአሮጊቶች እንባ
ዓለምን በመዳፉ የሰራ ፈጣሪ ማደሪያው ታቦቱ ቀኑ ለመለመኛ መዳፍ ሲጠሩ
የ13 አመት ጀምሮ ያሉ ሴቶች ሴተኛአዳሪ መሆናቸው
በሞራልም
በመንፈስም
በአካልም
ወድቀን ሳለን .....አሸንፈን የሚለው ቃል መፈክር ብቻ ይሆንበታል ለትውልዱ፡፡

ይመራል፡፡ ግን ሀቅ ነው፡፡

አሸንፈናል .....ግን ይርበናል::

ያሸነፍናቸው ....የት ናቸው?
አሸንፈናል .....ግን ይርበናል::
ህመም -፪

በጦብያ ሰማይ ስር ከተጻፉ ኦቶባዮግራፊ መጽሐፍ እንደ ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለማርያም የተሳካለት የለም፡፡ የርሳቸውን የዘመን ውጣ ውረድ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን፡፡ ለአሁን ግን ......

በኦቶባዮግራፊ መጽሐፋቸው ላይ ሰርክ ስለሚያስገርመኝ ነገር ላውራችሁ፡፡
ገጽ 69፡፡ የጦብያ ሌላኛው ገጽ፡፡

ከአድዋው ድል ማግስት ወደየቤቱ ወታደሩ ሲመለስ:- "....ወታደሮቻችን በሣጥን የተከተተውን ዕቃ እየበረበሩ ከውስጡ እያወጡ ሲሻሙ በሜዳው ሙሉ በየትም መነዛዘሩት፡፡ በሜዳው ላይ በየትም የተበታተነው ዕቃ ብዛቱ የአንድ የትልቅ ከተማ ዕቃ ያህላል፡፡
ተግዞ ተጭኖ የሚያልቅ አይመስልም፡፡ አይኖቼን አሰከራቸው፡፡ ስንቱ ተቆጥሮ ይዘለቃል፡፡ ጣልያኖችስ ይኸን ሁሉ ግሳንግስ በምን ጭነው አመጡት? ወይን ጠጅ -አረቄ-በያይነቱ ዱቄት-ማካሮኒ-ሱካር-ፎርማዥ-ሰርዲን-ኮንሴርቫበያይነቱ-ክብሪት-ሲጃራ-ሥዕል የተሳለበት ጋዜጣ-ብስኩት.....ይህን ሁሉ ጉድ አሞራው ወታደራችን ባንድ አፍታ አመሰቃቀለው፡፡ ይህ ሁኔታ ድል አድራጊዎቹን ፍጹም አስክሯቸዋል፡፡

ባንዲት ክብሪት ወይም ሴንጢ ወይም ብልቃጥ ጠርሙስ ወይም ሰዓት የተነሣ "እኔ ልውሰድ እኔ እብሳለሁ" በማለት እየተጣሉ ጎራዴ ይማዘዛሉ ይቋሰላሉ ይታኮሳሉ ይጋደላሉ፡፡ ባቢሎን እንደፈረሰች ጊዜ ሰዎች ቋንቋ ለቋንቋ ተሳሳቱ፡፡

ተቀምጬ ሳስተውል ብዙ ቆየሁ ከዛም መደባደቡ በረድ ሲል ጠበቅኩና እኔም የተራዬን ለመዝረፍ ተነሣሁ፡፡ ....." ይሉናል፡፡

*ከጦርነት ማግስት የተሸናፊውን ንብረት መውረስ ደንብ ቢሆንም የአድዋው ከዚህ የሚለው መጋደልም ጭምር መኖሩ ነው፡፡ (እንደፊታውራሪ አገላለፅ ከሆነ)

ከትውልድ ትውልድም የኛ መልክ ይኽው ነው፡፡ ድል በቀናን ማግስት መነጣጠቅ መዘረራረፍ፡፡ ያውም እርስበራሳችን፡፡

ድል አድርገናል በጦርነት፡፡ ድል አድርገውናል በድህነት፡፡ ችጋራችን ከዘመን ዘመን አለቀቀንም፡፡ መልካችን እስኪመስል ድረስ ተጣብቆናል፡፡ የወጣቱም ተስፋ የሽማግሌውም እርጅና የህፃናቱም መኮላተፍ ተዛንፏል፡፡

ተሰራርቀናል፡፡ ተቀማምተናል፡፡ ተነጣጥቀናል፡፡
ይሄም የኛ መልክ ነው እና እንቀበለዋለን፡፡

አሸንፈናል፡፡ ግን ይርበናል፡፡

* * * * * * * * *
Graphics:- simon
o shame! Where is the blush?
(ዊልያም ሼክስፒር:- ሐምሌት )

ህመም-፫

አምላኩን በመልክ ይመስለዋል ተብሎ የተሰራው ሰው በግብር የመምሰልም አደራ ተጥሎበታል፡፡ (ረስቶታል ወይም አቅቶታል እንጂ)

የሰው ድርሻ መኖር ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ማኖር ነው፡፡ ለዛም ነው ሌሎችን በስዕል በሙዚቃ በቃል በቅርፅ በህንፃ በመቃብር ጽሑፍ በምን በምን የምናኖራቸው፡፡ ከሁሉ በላይ ግን በአካል በመንፈስ በስጋ አብረውን ያሉትን ማኖር ነው መኖር፡፡

የዚህ ዘመን Individualism ፍለስፍና በየቤቱ ገብቶ እንደተበላሸ ወተት ተበጣጥሶ አስቀምጦናል፡፡ ከትናንትም የቀረን ጀብደኝነት ዛሬም ያኖረን ኩራት ለነገ የሰነቅነውም ተስፋ የጋራ አልሆን ብሎን እንፏቀቃለን፡፡

ሁሉ ወድቆ ተሰብሮ ተሰነካክሎ በስህተት መመጻደቅ መኩራራት ይዘናል፡፡ ይሄኔ ነው "ሐፍረት ሆይ ቅላትሽ ወዴት አለ?" የምንለው እንደ ሼክስፒር፡፡

ከአድዋም
ከማይጨውም
ከካራማራም
ከሌሎችም ድል ማግስት ያለን እኛ 'ትውልድ' የተባልን ለምንሆነው ለሆነው ነገር ሁሉ "ሐፍረት ሆይ ወዴት አለሽ?" ማለት ይገባናል፡፡


እንደጋራ ይዘነው ያለን ነገር ቢኖር መመጻጀቅን፡፡
በጎጣችን በሃይማኖታችን በአቋማችን በምንቀባጠረው ዲስኩራችን እንደትውልድ " victims of superiority complex" በሚባል ደዌ ከተኛን ሰንብተናል፡፡

ላላስቀጥለነው ስልጣኔያችን ዛሬም ለቀጠለው ጠኔያችን ማስታገሻችን ትንሽ ማፈር ነው፡፡ በአባቶቻችን የመኩራታችንን ያህል በራሳችንም ቀን መድበን አደባባይ ወጥተን ማፈራችንን መግለጽ አለብን(በየሕህሊና ደጃፋችን)፡፡

"በቤተክርቲያን ታሪክ ውስጥ እጅግ የሚያኮራው
የጳውሎስን ሙያ ብቻ አየደለም የሚያስተምረን፡፡ እጅግ ከሚያሳፍረው ከከሐዲው ይሁዳ ህይወትም ብዙ ነገር እንማራለን::"
(ብርሃኑ ድንቄ፡:- አልቦ ዘመድ)

ከአባቶች ልክነት ብቻ ሳይሆን ስህተትም መማር ብልህነት ነው፡፡ ከኛም የተወሳሰበ የብሽቅ አኗኗር 'የይሁዳ' ታሪካችን መመለስ ነቄነት ነው፡፡ ይሄም የኛ ማንነት ነው ብሎ መውሰደም ያስከብረናል ያሻግረናል፡፡

አሸንፈናል፡፡ ግን ይርበናል፡፡
ለምን?
ራሳችንን ክደናል::
2025/02/18 18:55:12
Back to Top
HTML Embed Code: