tgoop.com/Optimisticbatch/3632
Last Update:
የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንዴት ይሰራል?
የዩኒቨርሲቲ ምደባ የሚሰራው እንደድሮው ጊዜ በቀጥታ በሰዎች ሳይሆን ዘመናዊ እና አለም አቀፋዊ ተቀባይነት ባለው ማሽን ነው። ታዲያ ምደባው ሲካሄድ በዋነኝነት የተማሪዎችን ውጤት መሰረት በማድረግ ነው፡፡
ይኸውም :- ምደባው በቅድሚያ ምደባውን ለሚያከናውነው ማሽን እነዚህ የመረጃ ግብዓቶች inpute ይሰጡታል። እነሱም
- ከመቁረጫ ነጥብ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ስም ዝርዝር
- የዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅም
- የመቁረጫ ነጥብ
- የተማሪዎች ውጤት
- PHASE (ምድብ)
PHASE ማለት ለምሳሌ እነሱ inpute ሲያስገቡ
PHASE 1 ከ አንደኛ ምርጫ እስከ አምስተኛ ምርጫ
PHASE 2 ከ አምስተኛ ምርጫ እስከ አስረኛ ምርጫ ወ.ዘ.ተ እያለ እንዲሰጥ አድርገው program ያደርጉታል ማለት ነው።
ከላይ ያሉት የመረጃ ግብዓቶች ከገቡለት በኋላ ማሽኑ
1 የተማሪውን ውጤት (ነጥብ)
2 የተማሪውን የምደባ ምርጫ አሞላል
3 የዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅምን
መሰረት በማድረግ ተማሪዎችን ይመድባል፡፡ በዚህ መልኩ ምደባ ሲሰራ እነሱ ብቻ በሚያውቁት scale መሰረት:
- በጣም ጥሩ ውጤት ያመጣ ተማሪ
PHASE = ONE , CHOICE = ONE
ይደርሰዋል ማለት ነው። ማለትም የመጀመሪያ ምድብ የመጀመሪያ ምርጫ ማለት ነው፡፡
- ከዚያ scale ቀጥሎ ያመጣ ተማሪ ደግሞ:
PHASE = 1 , CHOICE = 2
ይደርሰዋል ማለት ነው። ማለትም የመጀመሪያ ምድብ ሁለተኛ ምርጫ ማለት ነው።
የምደባ ውጤት በቅርብ ቀን ውስጥ ይፋ የሚደረግ ሲሆን ይፋ ሲሆንም የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER
BY Optimistic Batch
Share with your friend now:
tgoop.com/Optimisticbatch/3632