እግዚአብሔር አብ የኢየሱስ ክርሰቶስ አባት የሚባለው ሰው ሆኖ በተወለደበት የኋለኛው ልደቱ በኩል በተናጠል ሳይሆን ዘመን ከመቆጠሩ በፊት ከአብ በተወለደው ረቂቅ ልደቱ በኩል ነው ። ነገር ግን ቀድሞ ዘመን ሳይቆጠር ከአብ የተወለደውም በኋለኛው ዘመን ሰው ሆኖ ከድንግል ማርያም የተወለደውም አንድ ወልድ (ልጅ) ነው እንጂ ሁለት አይደለም። ሰው ሲሆን ከተፈጸመው ረቂቅ የተዋሕዶ ምሥጢር የተነሣ አብ አባት ሲባል ለወልድ መለኮት ብቻ አይደለም ፤ ድንግል ማርያምም እናት ስትባል ለወልድ ሰውነት ብቻ አይደለም ፤ ክርስቶስ ከዋሕዶ በኋላ አንድ እንጂ ሁለት አይደለም። (የልቦና ችሎት ገጽ-14 )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
👍8🙏3❤2
አርቲስት ማክዳ አፈወርቅ 👉 ከቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ!
...............
በነገረ መለኮት 2ኛ ድግሪ (Masters ) ተመራቂ ጀግኒት
ዛሬ የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት በማስተርስ ፕሮግራም ካስመረቃቸው ተማሪዎች አንዷ አርቲስት ማክዳ አፈወርቅ ናት።ይህ ለብዙዎች አርአያነት ያለው ትልቅ ነገር ነው።በተግባር የተገለጠ ሕይወት ማለትም ይኸው ነው። Congratulations እህታችን።እግዚአብሔር ቤትሽን ትዳርሽን ይባርክ። 🙏ልባም ሴት🙏
👉በቴሌግራም -ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://www.tgoop.com/edomiyas221
........💒.............

❤74👏9🥰3
+ የመከራ ጉዞ +
አምኖባት ለተሳፈረባት ሁሉ ሚቀርለት አይደለም አይነቱ ይለያይ እንደሆነ እንጂ ሁሉ በዛ ውስጥ እንዲያልፍ ይሆናል ላጡት የማስተዋል ዕውቀት ከሷ ይወለዳል ባተሌነት እንዲቀር እርሱ ብልህ መምህር ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው ፦" እንደ ብልህ አሰልጣኝ ኹሉንም ነገር እንዲያዩ እያደረገ ያለማምዳቸው ነበር ። መከራ ሲገጥማቸው እንዳይፈሩ ፈተናዎችን መቋቋም እንዲችሉ ክብር ሲያገኙ እንዳይመኩ "። ሰጥታ ባለባት መርክብ ሳይሆን እረፍት ባልሆነባት መርከብ እንዲጓዙ አደረጋቸው ሐዋርያቱን ።
ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። እነሆም፥ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ ። ማቴ 3፥23 ተከተሉት ወደ መስቀል በወጣ ጊዜ ሰማዕታት በመከራ መሰሉት መከተላቸው እስከሞት መታመናቸው ነውና ።
የእርሱ እስከሆነ መነኮስነቱ ከመከራ ሚያስመልጠው አይደለም መከራው ለዓለማዊው እንጂ ለእነርሱ እንደማይገባ አድርጎ መረዳት ሳይሆን ለሁሉም የሰው ልጆች የተገባ እንደሆነ ማሰብ መከተላቸው ከእርሱ መከራ ተሳትፈው ከክብሩ ይሳተፍ ዘንድ ፈቃዱ ሆኗልና ።
ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሰኔ 22 2017 ዓ.ም

❤22👍1🙏1
በብፁዓን ጳጳሳት ዙሪያ ‹‹ምን ትላለህ?›› ቢሉኝ
(ደብተራ በአማን ነጸረ ከfb ገጽ በከፊል የተወሰደ እንቅጯን )
--
3. ከተርእዮና ከእወደድ ባይነት ፆር ቢላቀቁልን እንወዳለን፡፡ የሥራቸው ፍሬ ቢናገር፡፡ በሀገረ ስብከት ልሳናትም በቤተ ክርስቲያናት ልሳናትም ደጋግሞ ምስል መደርደር ደስ አይልም፡፡ ሥራቸው ቢናገር፡፡ የቤተ ክርስቲያን ይፋዊ ልሳናትም የጳጳሳት ዲያሪ ወይም ዜና መዋዕል መጻፊያ ባይምሰሉ፡፡ የኤዲቶሪያል ፖሊሲያቸውን ተከትለው በአንጻራዊ ነጻነት ቤተ ክርስቲያን የተሰጠቻቸውን ተልዕኮ ሚዛን ጠብቀው ቢወጡ፣ ጳጳሳት ባይጓተቷቸው፡፡
--
4. በቤተ ክርስቲያን ላይ ፈተናዎች ሲመጡ ባይሸሸጉብን፡፡ ዝቋላን ያህል ገዳም መከራ ሲደርስበት በዚያ ልክ መሸሸግ ያስቀይማል፡፡ ሆድ ያስብሳል፡፡ በእንዲህ ዓይነት መከራዎች አጽናኝ ያስፈልጋል፡፡ በክርስቶስ አካል ነን፡፡ የአንዱ ሕዋስ ሞት በአናት ላይ ላሉት ካልተሰማ ያውካል፡፡ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠትና ጉዳዩን በባለቤትነት መያዝ ከብዙ ውስጣዊና ውጫዊ ችግር ይታደጋል፡፡ በተለይ ተደጋጋሚ የኦርቶዶክሳውያን ፈተና የሚበረታባቸው አህጉረ ስብከቶችና የሚመሯቸው ጳጳሳት ራስን መሸሸግ አንጀት ይቆርጣል፡፡
--
5. ሀገረ ስበከትን ትቶ አምስት ኪሎ መመሸግ ጥልቅ ቅሬታና ኀዘን የሚፈጥር ተግባር ነው፡፡ በእረኝነት እንዲጠብቃቸው የተሰጡትን የሀገረ ስብከቱን ምዕመናንና ካህናት ግድያ ዋሽግንተንና ለንደን ከሚኖሩ ምዕመናን በኋላ በፌስቡክ የሚሰማ ጳጳስ በእረኝነት ለመጥራት ይቸግራልኮ! ሕገ ቤት ክርስቲያንንና ቀኖናንም የጣሰ ተግባር ነው፡፡ ሀገረ ስብከታችሁን፣ መንበራችሁን ብትኖሩበት፣ ብትዳኙበት፣ ብታስተምሩበት፣ ብትቀድሱበት ክብሩና በረከቱ ለሁላችን ነው፡፡ ተደራራቢዎቹ ሀገረ ስብከቶችም እንደ ቀኖናው ከሆነ እኩል ጊዜ ተመድቦ በየተራ ቡራኬና ጉብኝታችሁን እንዲያገኙ ይጠበቃል። ታውቁታላችሁ፡፡ አምስት ኪሎ ላይ ተሰባስቦ የከተማዋን አጥቢያዎች ጥሪ፣ የመጽሐፍና ሲዲ ምርቃት፣ የሕንፃ ምርቃት፣ የሠርግ ሽምግልና፣ … በየጥሪው መወሰድ ከሀገረ ስብከታዊው ተልእኮ የሚመጣጠን አይመስለንም፡፡ በዛ!

❤8
እናት ከአንድ ጡቷ ደም እና ወተት ካለበት ሰውነቷ ለወለደችው ልጇ የሚሆን ወተት ተለይቶ እየፈሰሰላት የእግዚአብሔር መገለጫ ሁና በፍጹም ፍቅሯ ልጇን ትመግባለች ።
ሥላሴ በሴት አንቀጽ ቅድስት ፣ ውድሰት ተብለው መነገራቸው ለዚህ ነው ። እናት ከባሕርይዋ ልጅ ወልዳ አጥብታ እንደ ምታሳድግ ሦላሴም በከሀሊ ባሕርያቸው ይህንን ዓለም ፈጥረው መግበው ለመኖራቸው ምሳሌ ፣ የሕፃናት እናት የሥላሴ ምሳሌ ናት ። (ከመዝ ነአምን እንዲህ እናምናለን -223)

❤8👍2
በዘመናችን ከሰባኪው ተምረው ንስሐ ገብተው ቀድመው ክብረ መንግሥቱን እየወረሱ ያሉ ብዙዎች ናቸው ። አገልግሎት ሕይወት ሳይሆን የሙያ መስክ የሚመስለን አገልጋዮች መንጋውን ወደ በረት እያስገባን እኛ ግን ውጪ ላይ ከጨለማና ከጅብ ጋር ተፍጠን ለመኖር የወሰንን መሆናችን ምንኛ ያስቆጫል?! ቀራጮችና አመንዝሮች ከሩቅ ተነሥተው መጥተው ንሰሐ ገብተው ሲድኑ እያየን መሞታችን ምንኛ ያሳዝናል?! ከሩቅ ተነሥተው መጥተው ንስሐ ገብተው ሲድኑ በቤቱ እያለን መሞታችን ምንኛ ያሳዝናል ?! እያወቁ መሞትና ድኅነትን እንደገፍት እንደ አይሁድ መሆናችንስ ምንኛ ያሳፍራል?!
(ኦርቶዶክሳዊ ንስሐ ገጽ-368 ዲ/ን ባንተአምላክ አያሌው )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
(ኦርቶዶክሳዊ ንስሐ ገጽ-368 ዲ/ን ባንተአምላክ አያሌው )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
❤12
ወደማደርያው.aac
6.8 MB
+ የዓውደ ምህረት ዝማሬ +
(ዲያቆን ፍፁም ከበደ )
#ወደማደሪያው_ገብቼ
ወደማደሪያው ገብቸ ልስገድ
ለእግዚአብሔር(2)
ምስጋናንም ላቅርብ ስለስሙ ክብር(2)
አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ
በአጸደ መቅደሱ እሰግድለታለሁ
ስለስሙ ክብር ውድቄ እነሳለሁ(2)
በመከራየ ቀን ሁኖኛል መከታ
ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ
የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በዕልልታ(2)
አስር አውታር ባለው በበገና
በመላዕክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና
የአፌንም ነገር ሰምቶልኛልና(2)
ለስሙ ልንበርከክ ለዕርሱ እንደሚገባ
ስለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወዳደባባዩ በዕልልታ ልግባ(2)
አሸበሽባለሁ ድምጼን አሰምቼ
በቤተ መቅደሱ ለሊት ተገኝቸ
እንደካህናቱ እጆቸን ዘርግቼ(2)
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
(ዲያቆን ፍፁም ከበደ )
#ወደማደሪያው_ገብቼ
ወደማደሪያው ገብቸ ልስገድ
ለእግዚአብሔር(2)
ምስጋናንም ላቅርብ ስለስሙ ክብር(2)
አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ
በአጸደ መቅደሱ እሰግድለታለሁ
ስለስሙ ክብር ውድቄ እነሳለሁ(2)
በመከራየ ቀን ሁኖኛል መከታ
ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ
የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በዕልልታ(2)
አስር አውታር ባለው በበገና
በመላዕክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና
የአፌንም ነገር ሰምቶልኛልና(2)
ለስሙ ልንበርከክ ለዕርሱ እንደሚገባ
ስለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወዳደባባዩ በዕልልታ ልግባ(2)
አሸበሽባለሁ ድምጼን አሰምቼ
በቤተ መቅደሱ ለሊት ተገኝቸ
እንደካህናቱ እጆቸን ዘርግቼ(2)
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
❤13
ሙሴ በብሉይ ኪዳን የተመሰለ ሲሆን ኢያሱ ደግሞ በሐዲስ ኪዳን ይመሰላል ። ይህም ማለት በሙሴ የነበሩ ኪዳን የተሰጣቸው አብርሃም ፣ ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ ፣ ፳ኤል በኢያሱ የተሥፍው ወራሽና ተከፍይ ሁነዋል ። በጊዜው በአካለ ነፍስ የነበሩት ኪዳናውያን እለ አብርሃምጨ ፣ ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ ሌሎችም ልጆቻቸው ምድረ ርስትን ለመውረስ በተሥፍ የቀሩ ቢሆንም በኢያሱ ሐዲስ ኪዳን ምሳሌነት በተነገረ ምሥጢር መንግሥተ ሰማይ የገቡ በአካለ ነፍስ በኢያሱ ክርስቶስ ነውና ።
ሙሴ በብሉይ ኪዳን የተመሰለበትም ምክንያት ከግብጽ እስከ ከነዓን ድረስ መና እያወረደ ፣ ውኃ እያፈለቀ ዓርባ ዘመን ቢመግብ ቅሉ ምድረ ርስት መግባት አልቻለም ነበር ። በብሉይ ኪዳን የነበሩ ነፍሳት ጻድቃን ምሳሌ ነውና ። በኢያሱ በሐዲስ ኪዳን መመሰሉ ግን በነፍሳት የተመሰሉ ፳ኤል ዘሥጋን ምድራዊ ርስትን በማውረሱ በኋላ ዘመን ኢያሱ ክርስቶስ መንግሥተ ሰማያትን ለማውረሱ ምሳሌ ሆነው ። (ከምዝ ነአምን ገጽ 231)
ከሊቃውንት መጽሐፍ አስተማሪ ጹሑፎች ዘወትር ያገኛሉ ቤተሰብ ይሁኑ #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ ።

❤10
ዓምደ ሃይማኖት.apk
42.9 MB
+ ሁሉን በአንድ መተግበሪያ +
#መንፈሳዊ ትምህርት ጥያቄዎች መልሶች በአንድ መተግበርያ App አውርደው ይጠቀሙ ።
ከዓመታት በፊት፣ ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለሚነሱባቸው ጥያቄዎች በጥቂቱም ቢሆን ምላሽ እንዲያገኙ ታስቦ በተዘጋጀው መተግበሪያችን/App ዛሬ እጅግ ዘመናዊ ሆኖ ተሻሽሏል። አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ብዙ exclusive content አካቶ መጥቷል።
ለተጨማሪ ድጋፍ እና ቀጥተኛ ምላሾች በsupport channels (በዋናነት በEmail, በ WhatsApp እና በTelegram) እንሰጥ የነበረውን አገልግሎት በማሳደግ፣ (ከምዕመኑ የሚደርሰን የጥያቄዎች መጠን ማስተናገድ ከምንችለው በላይ ሁኗልና) የበለጠ የጥያቄዎችዎን ምንነት ተረድቶ በተሻለ ፍጥነት መልስ የሚሰጥ አጋዥ AI Chatbot አካቶ መጥቷል። ይህም በመጀመሪያ ደረጃ ሙከራ ላይ ያለ breakthrough ነው።
AI ስጋት እንደሆነ ሁሉ ትልቅ opportunityም ነው። ካልቀደምነው፣ ካላስተማርነው የሌላውን ተምሮ ይቀድመናል። ይህንን cutting edge ቴክኖሎጂ በእምነታችን አገልግሎት በማዋል፣ የእኛን እውቀትና እሴት እንዲያንጸባርቅ የማድረግ ኃላፊነት አለብን።
የዚህን መተግበሪያ ጥቅም ለብዙዎች ለማድረስ፣ እባክዎን Share ያድርጉ!
( ዮሴፍ ፍስሐ )

❤5👍3⚡1
ልዩ መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር እየተደረገ ነው እየገባችሁ ተሳተፉ🥰
👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/edomiyass21
https://www.tgoop.com/edomiyass21
👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/edomiyass21
https://www.tgoop.com/edomiyass21
+ አዲስ የዝማሬ አልበም ምረቃ +
በዘማሪ አዲስ "ክርስቶስ አይማልድም" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የዝማሬ አልበም ምረቃ መርሐ ግብር ሐምሌ 6 ቀን በዲላ ዋለሜ ደ/ስ/ቅ/ዑራኤል ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፅዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ይመረቃል ።

❤6👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤6👍4🙏2🥰1
ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
https://www.tgoop.com/edomiyass21?videochat
.......ሊንኩን በመጫን ቀጥታ ወደ ቮይስ ቻት ይወስዳችዋል
ነገረ መላእክት ተከታታይ ኮርስ ተጀምሯል🎙🎙🎙
ቮይስ ቻት ግቡ 📺📻
ነገረ መላእክት ተከታታይ ኮርስ ተጀምሯል🎙🎙🎙
ቮይስ ቻት ግቡ 📺📻