Telegram Web
እኔ እሆን.aac
4.5 MB
ሰላም የተዋህዶ ልጆች እንኳን :🌿ለሕፅበተ እግር🌿
በሰላም አደረሳችሁ/ረሰን🙏
..ዕለቱን በተመለከተ አጠር ያለ
ግጥም አዘጋጂቻለው ተጋበዙልኝ
🌿መልካም ዕለተ ሐሙስ🌿
@zosemas
ስቅለት.aac
6.7 MB
✤ስላም ተወዳጆች✤
✥እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶ የሰቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ/ን✥
✧ ይህችን ዘለግ ያለች ግጥም ዕለቱን አሰመልክቼ አዘጋጅቻለው ሁላችሁም ለወዳጆቾ በማጋራት ታዳምጡ ዘንድ እጋብዛለው✦
@zosemas
✤የትንሳኤ ፍሬ✤
ደረሰ ሊፈታ፣ሕማምህን ልረሳ
ዳግም የተውኳትን፣ሐጥያትን ላነሳ
ሞቴ ሊጀምር ነው፣ከሞት ሰትነሳ
ጌታ ሆይ! ዳግም አትሙት በልቤ
ትንሳኤህ ያድርገኝ እንጂ፣አንተን እንዳቅህ ቀርቤ
የልቤ መቃን ይከፈት፣መቃብሩ ሰውነቴን በትንሳኤ ብርሃን ይፍረስ
ሞቴ በአንተ እንደሞተ፣ሕማምህ በልቤ ይንገስ
እባክህ! የጋረደኝን ጨለማ፣ከዓይኔ ክበብ ላይ አውልቀው
ከትንሳኤህ ማዶ ያለውን አንተነትህን ልወቀው
እንደ ማርያም መግደላዊት፣ማንን ትሻለህ በለኝ
እንዳይገባይኝ ባውቀውም፣በቸርነትህ ጠይቀኝ
ትችላለህ አውቀዋለው በኤማሁስ ስታበራ
ላልተረዳሁ ላልገባኝ ምስጢርህን ስታብራራ
አይቻለው ከዚህ ቀደም፣በተዘጋ በር ስትገባ
እሻለሁኝ! ምን በዘጋውየልቤን በር፣ በጥበብህ እንድትገባ
አቤቱ ውስጤን አድሰው፣የፍቅር ማረሻ አንስተህ፣የልቤን ዙፍን እረሰው
ዳግም ሞቶ እንዳይቀር፣ ከትንሳኤህ ፍሬ አጉርሰው።

🌿እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ🌿
በዓሉን #የሰላም #የፍቅር #የአንድነት #የመተሳሰብ እንዲሁም #ሀገራችን የሰላም አየር ምተነፍስበት ያርግልን
🌿 መልካም በዓል🌿
//ፍፁም ገነነ//
ሚያዝያ/24/2013ዓ.ም
@zosemas
>>>>> የሰማዩ መንገደኛ <<<<

የአመነ ሰው ከክርስቶስ ዙፋን የሰማያዊውን ደጅ በንሰሃ ለመምታት የምትሄድባቸው አምስቱ የንሰሃ መንገዶች፦
(1) ሀጢያትን ማሰብ

የመጀመሪያው መንገድ የሰራነውን ሀጢያትን ማሰብ/ማሰላሰል/፡፡ ሀጥያተኛነትህን የምታስበው እና የምታሳስበው ከሆነ እግዚአብሔር ይቅር ሊልህ ታማኝ ነው። ሀጥያተኛነትህን ስታስበው ደግመህ አትበድልም። ህሊናህ ሲከስህ መንፈስ ቅዱስ ሲወቅስህ እንጂ በጌታ ዙፋን ፊት ሌላ አካል እስኪከስህ አትጠብቅ።

"እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።" (መዝሙር 51:3)

(2) የሌሎችን ጥፋት መርሳት

ሁለተኛው መንገድ ንሰሃ ከመግባትህ በፊት የሌሎችን በደል ይቅር በላቸው። ይህም ስሜትን መቆጣጠር እና ሌሎች ሰዎች በአንተ ላይ ያደረጉትን ሀጢያት ይቅር ማለት አለብህ። ሌሎችን ይቅር ስትል ጌታ ይቅር ይልሃል።

"ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅርብለናልና፤" (የሉቃስ ወንጌል 11:4  )

(3) ፀሎት

ፀሎት ሶስተኛው መንገድ ሲሆን። ይቅር ይለኛል ብለህ አምነህ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክከህ ስለሀጢያትህ ፀልይ እርሱንም እጠበኝ ቆሽሻለሁ፣ አንፃኝ ከበረዶ ይልቅ ነጭ እሆናለሁ በለው። መለወጥ እና በሰውና በአንተ ፊት ቅዱስ ሆኜ እንድኖር መንፈስህ ይቆጣጠረኝ በለው። ስትጨርስም ስለምህረቱ የምስጋናን ፀሎት አምጣ።

"በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ። ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል። ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ። አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ!" (መዝሙር 51:7-10)

(4) ደግነት

መንገድ አራት ምህረትና ፍቅሩን ለመለመን በፊቱ ስትቆም ከሚሰጥና ደግ በሆነ ልብ ይሁን። ደግነትህ ብዙ እንድትቀበል ያደርግሃል። መካስ ባትችልም እንደ ካሳ ግን የተቀበልከውን ፍቅር ለብዙ ስጠው።

(5) ትህትና

አምስተኛው መንገድ ትህትና ። በማስመሰል ሳይሆን በእውነት ትህትና የአንተ ክብር ምንም መልካምነት እንደሌለው እና ትከሻህ በሀጥያት ሸክም እንደጎበጠ በእግዚአብሔር ፊት ሁን። እግዚአብሔርም በምህረት ከባዱ ሸክምህን ከላይህ ላይ አራግፎ ሀጢያትህን በደሙ እያነፃ ፍቅሩን በልብህ ያሳዝልሃል።

"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" (ማቴዎስ 11:2)

# የሰማዩ መንገደኛ ሆይ በየእለት ኑሮህ ብትችል በሁሉም ካልቻልክ ከነዚህ በአንዱ መንገድ ላይ ተጓዝ! ነገር ግን እንዳልቆምክ እና በየእለቱ እየተጓዝክ መሆንህን እርግጠኛ ሁን!! እግዚአብሔር ይርዳህ!!
መልካም መንገድ!!!
​​አብዝቶ ማድነቅ

የአንድ ቀን ንጉሥ ሆኖ የሞተ አንድ ንጉሥ ነበር። ይህ የሆነው በከባድ ነገር አይደለም። ይልቁንም በተሾመ ዕለት ከበው እጅ ከሚነሱት ሕዝብ ብዛት የተነሣ እስትንፋስ አጥሮት ነው።

በእውነቱ ኀዘናችን ከሚጎዳን እኛው ደስታ የምንለው ያመጣብን እዳ ብዙ ነው። ረጋሚዎቻችን ካጠፉን ይልቅ አድናቂዎቻችን የገደሉን ይበዛል።

ሰዎችን በተቀመጡበት ቦታ እንዳይገኙ፥ ቃላቸውን እንዳይጠብቁ፤ ለሕዝብና ለእግዚአብሔር ለራሳቸውም እንዳይታመኑ የሚያደርጋቸው ጭፍን አድናቂ ነው።

እንደ ሰዎች ልክ ብንሆን እንደ እግዚአብሔር አናውቅሞ። አባ አጋቶን ሊያርፍ በተቃረበ ጊዜ ሦስት ቀን ያለ መንቀሳቀስ በአቱ ውስጥ ተኛ። ሦስተኛው ቀን ላይ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አንጻር በአንቃዕድዎ ሰቅሎ ዋለ። ደቀመዛሙርቱም አባታችን ምን ታያለህ? አሉት። እርሱም ወደ ክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እመለከታለሁ ሲል መለሰላቸው።

እነርሱም ምነው አባታችን አንተም ፍርድን ትፈራለህን ቢሉት፤ አይ ልጆቼ! እንደ እኔ ሠራሁ ብያለሁ እርሱ ገና ነህ አልሠራህም ቢለኝ የት እገባለሁ ብሎ አስተማራቸው።

እንደ እኛ የበሰለው በእግዚአብሔር በፊት ጥሬ ይሆናል። እንደ እኛ ያጸደቅነው በቅድመ እግዚአብሔር ኩኑን ይሆናል። እንደ እኛ ያከበርነው በፍትሐ እግዚአብሔር ኅሡር ይሆናል። ለወደፊት የሚረቡትን ሁሉ እንዲጠፉ ያደረግናቸው ያለመጠን እያደነቅን ስሕተታቸውን የሚያዩበት እድል ነስተናቸው ነው። እንደዚህም ስላደረግን ለሃይማኖትና ለሕዝብ ሳይሆን ለስማቸው የሚሞቱ ድልድሎችን አፍርተናል።

እናም ዝምታ የክርስቲያኖች ግርማ ነውና በሥራ እየተናገርን ማንንም ከማድነቅ ከመተቸት ብናርፍ እንዴት ማለፊያ ነው!

በዚህ ወቅት አብዝቶ ቢያደንቁት እውነት እየመሰለው ኩራት ጥፋት፤ አብዝቶ ቢተቹት ሽንፈት እየመሰለው ክፋት ነው የሚያበዛውና ሰውን በሥራ መዝለፍ። ጌታ ዝም ብሎ ሥራውን ሠርቶ ራሱን እንደገለጠ በሥራ እንገለጥ፤ በሥራ እናመስግን፤ በሥራ እንዝለፍ።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምሮ ሲጨርስ አብዝተው ላጨበጨቡለት ሕዝብ ለኔ ማጨብጨባችሁ ምን ያደርገልኛል። ይልቁንስ ያዘዝኳችሁንም ስትፈጽሙ ያን ጊዜ ነው ያጨበጨባችሁልኝ ነበር ያላቸው።

ሞኝ ሕዝብ የሚባለው ፈጥኖ የሚያምን ፈጥኖ የሚክድ፥ ፈጥኖ የሚወድ ፈጥኖ የሚጠላ፤ ቸኩሎ የሚያደንቅ ቸኩሎ የሚተች፤ ቸኩሎ የሚመርቅ ቸኩሎ የሚረግም ነው። ይህም ይህ ነው። የነገሩትን ሁሉ ሳይመረመር የሚቀበል ነው።

እንደ እባብ ሊገድል የሚያመሰግን አለ። እንደ ዮሐንስ መጥምቅ እናንተ የእፉኝት ልጆች እያለ ለድኅነት የሚዘልፍም አለ።

የምንወድውን ያደነቀ ሁሉ ወዳጅ ላይሆን ይችላል። የማይወዱንን ሁሉ የሚነቅፍም አሳቢ አይደለም።

አንጥያኮስ የሚባል የፅርዕ ንጉሥ ወደ እስራኤል ግዛት ለማስፋፋት ሲገባ እንዲህ ነበር ያደረገው። ይህ ሰው ጣኦት አምላኪ ሲሆን ወደ እስራኤል ሲመጣ ግን መልኩን ደብቆ፦ በኦሪት አምናለሁ፣ መሥዋዕተ በግዕ እሠዋለሁ፣ ለሥዕለ ኪሩብ እሰግዳለሁ፣ አነጥፋለሁ እጋርዳለሁ አላቸው። በዚህ ሕዝቡን መክፈል ቻለ።

ግማሹ ሕዝብ አንጥያኮስን ያህል ንጉሥ ይህን ሁሉ ሊፈጽም ቃል ሲገባ ለምን ወደ መቅደስ እናስገባውም አሉ። ነገሩም አልቀረ ሌሎቹም አመኑና ሰውየው መቅደስ ገባ። በደንብ ሥልጣኑን ካረጋገጠ በኋላ ግን ነገሩን አመጣ። መሥዋዕተ በግዕ በሚሠዋበት ቦታ እርያም ሠዋበት። የሊቀ ካህናቱንም ሚስት በጡቶቿ መቅደስ ውስጥ ሰቅሎ ገደላት። ሊቀ ካህናቱንም በሰም አቅልጦ በብረት ምጣድ ተኩሶ፣ ሌሎችንም በሰይፍ ፈጃቸው።

የሚወዱትን ሃይማኖታቸውን ከነሥርዓቱ ከማድነቅ በላይ ለሥርዓቱ ሊታዘዝ ቃል ገብቶ የመጣው በሐሰት ሰዎችን በሞት ሥርዓቱን በክህደት በመጣስ ፈጸመ።

በዚህ ዘመንም ወይ አንጥያኮሶች ሆነው የሚያደንቁን፥ ወይ እባብ ለብሰው የሚያወያዩን፥ ወይ የሚጠሉንን በመተቸት የእኛን ድክመት ተጠቅመው ክብር የሚሰበስቡ ፥ሌሎችን በመተቸት ብቻ ለራሳቸው ዝና ከማጠራቀም በቀር ለእኛ ቀዳዳዎች አንድ እንጨት የማይቆርጡ የገቢያ ግርግር ሽፍታዎች ናቸው የበዙት።

በሃይማኖትም ሰው ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በረት ወጥቶ የሚኮበልለው ሌላው እውነት ስለሆነ ሳይሆን ሌላው ውስጥ መወደስ እንጅ መገሠጽ ስለሌለ ነው። መብላት እንጅ መጾም፥ መቀማጠል እንጅ ትሕርምት የለም። ሰው እንደሚወደው እንጅ እግዚአብሔር እንደሚወደው ስለማይኖር ነው። ዓለም ደግሞ የራሱን ይወዳል ብሎናል መድኀኒታችን። እንደ ጌታ ፈቃድ ጽሙና ሳይሆን ዝላይ ወዳለበት፥ ሥርዓት ሳይሆን መረን መልቀቅ ወዳለበት የሚጎርፈውም ስለዚህ ነው።

እንደ ዮሐንስ መጥምቅ የሚገሥጹን ግን ለሕይውት መንገድ ለክርስቶስ ያደርሳሉ። ለዚህ ነው እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ ልጆቿን ከማመስገን ይልቅ የምትገሥጸው! አሁንም ንስሐ ለመግባት ልባችን ይስበርልን

አባ ገብረ ኪዳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ጾመ_ዮዲት
ከጷጉሜ1-5/6--የፈቃድ ጾም።
እንኳን አደረሳችሁ!!!

በናቡከደነጾር ዘመነ መንግሥት ንጉሡ ሥልጣኑን መከታ በማድረግ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በግድ እያስገደደ እጅ መንሻ ይቀበል ነበር፡፡ የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበለውንም እየገደለ፣ ጭፍሮቹ ኃያልነቱንና ገናናነቱን በዓዋጅ በጦር አዛዦች ጭምር እያሳወጀ፣ በርካታ የጦር ሠራዊቶችን አሰልፎ ከአይሁድ ከተማ ገባ፡፡ በዚያም ነዋሪዎችን በማስፈራራት የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበሉትን ሁሉ እያሳደደ ስላስጨነቃቸው ማቅ ለብሰው፣ አመድ ነስንሰውና ድንጋይ ተንተርሰው ወደ ፈጣሪያቸው በመጮህ መለመን ጀመሩ። በጭካኔ የተሞላው የጦር አበጋዙ ሆሎፎርኒስም ይበልጥ እጅግ እንዲሰቃዩ ውኃ የሚቀዱበትን ስፍራ ተቆጣጠረው፤ በግዴታ ማርኮም እጅ እንዲሰጡ እንዳደረጋቸው በመጽሐፈ ዮዲት ፪፥፪ ላይ ተጽፏል፡፡ በአካባቢው ይኖር የነበረ ዖዝያን የተባለ አንድ ሰው የአባቶቻቸው አምላክ ጸሎታቸውን እንዲሰማቸው ለአምስት ቀናት በትዕግሥት ይጾሙና ይጸልዩ ዘንድ ሕዝቡን መከራቸው፤ እነርሱም በትዕግሥት ሊጠብቁ ተስማሙ፡፡

የእስራኤል ልጆች የናቡከደነጾርን ጦር ብንችል ተዋግተን እንረታለን፤ ካልሆነም እጅ እንሰጣለን በማለት ይመካከሩ ጀመር። በዚያን ጊዜ ባሏ የሞተባትና በንጽሕና ተጠብቃ፣ በጸሎትና በሕገ እግዚአብሔር የምትኖር ዮዲት የተባለች ሴት ነበረች። (ዮዲት ፯፥፲) እግዚአብሔርን የምትፈራ ብቸኛዋ ሴት እርሷ ነበረችና ምክክራቸውን ስትሰማ ለምን «እግዚአብሔር ያድነናል አትሉም» ብላ ገሠጸቻቸው፡፡ ማቅ በመልበስ፣ አመድ በመነስነስና ድንጋይ በመንተራስም ሱባኤ ገባች። በሦስተኛው ቀንም እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቧን የምታድንበትን ጥበብ ገለጸላት፤ ዮዲትም እግዚአብሔር የሰጣትን ውበት ተጠቅማ ሕዝቧን ከጥፋት የምትታደግበትን ጥበብ ተረዳች።

የክት ልብሷን ለብሳ፣ ሽቱ ተቀብታና ተውባ የጠላት ሠራዊት ወዳሉበት የጦር ሰፈር በድፍረት አመራች፡፡ ሠራዊቱም ውበቷን አይተው እጅግ በመደነቅ «ይህችስ ለአለቃችን ትገባለች» ተባብለው ከጦር መሪያቸው ዘንድ ወሰዷት። እርሷም ቀድማ ማምለጫ መንገድ አዘጋጅታ ነበርና ወደ አዛዡ ከገባች በኋላ «ክቡር ጌታዬ ሆይ ርስት ተወስዶብኛል፤ እንድትመልስልኝ አስቀድሜ ደጅ ልጠና መጥቻለውና ርዳኝ፤ ትብብርህ አይለየኝ» አለችው፡፡ በስሜት ፈረስ ታውሮ የነበረው የሠራዊቶቹ አዛዥም የጠየቀችውን እንደሚፈጽምላት ቃል ገባላት። ባማረ ድንካን እንዲያስቀምጧት ሎሌዎቹን አዘዘ። ዮዲትም የተሰጣትን ጥበብ ተጠቅማ፣ መውጣት ስትፈልግ የምትወጣበትን እና የምትገባበትን ዕድል በእግዚአብሔር አጋዥነት ዐወቀች፡፡ ከቀናት በኃላ የጦር አበጋዙ ለሠራዊቱ የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ዮዲትን ከጎኑ አስቀመጣት፤ ከበሉና ከጠጡ በኋላም ሁሉን ሰው አስወጣ፤ እልፍኙን በመዝጋት ከእርሷ ጋር ብቻውን ሆነ፤ ነገር ግን እንቅልፍ ጣለው፡፡ (ዮዲት ፰፥፪) እርሷም ወደ አምላኳ ጸለየች፤ ፈጣሪዋ እንዲረዳትም አጥብቃ ለመነች። በኋላም ከራስጌው ሰይፍ አንስታ አንገቱን ቀላችው፤ በድኑንም ከመሬት ጣለችው። የሆሎፎርኒስን ሞት ሠራዊቱ ሲሰሙ አውራ እንደሌለው ንብ ተበተኑ፤ ከፊሎቹ ሞቱ። እስራኤላውያንም ከሞት ተርፈው በእግዚአብሔር ኃይል ድል አደረጉ፤ በደስታም ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ።

ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ የሚያስረዳን ዮዲት ጠላቶቿን ድል ያደረገችው በጾምና በጸሎት እንደሆነ ነው፡፡ ለእኛም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ምንም እንኳ ወርኃ ጳጉሜን የፈቃድ ጾም ቢሆንም በሀገራችን የተጋረጠውን ችግር እናልፍ ዘንድ በፈቃደኝነት እንጾማለን። እግዚአብሔር አምላካችን ለሁላችንም ጥበብ ሰጥቶናል። ይህም ችግሮችን ሁሉ የምንፈታበት መንገድ ነው። በዚህም የዓመተ መሸጋገሪያና የክረምቱ ወር ማብቂያ በመሆኑ ዕለተ ምጽአት ስለሚታሰብበት በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ከሌሊት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን ጠበል በመጠመቅ፣ በማስቀደስና በመጸለይ እንዲሁም ሥጋ ወደሙን በመቀበል ልናሳልፍ ይገባል። ዕለተ ምጽአትም ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው ዓለም መሸጋገሪያችን ነውና በቀኙ እንቆም ዘንድ እንጾማለን፡፡ የሚመጣውን አዲስ ዘመንም በንጽሕና ለመቀበል ስላለፈው ዓመት ኃጢአታችን ንስሓ የምንገባበት ጾምም ነው።

ከተጋረጠብን ችግር «እግዚአብሔር ያድነናል» በማለት ልክ እንደ ዮዲት ሱባኤ ገብተን፣ ማቅ ለብሰን፣ አመድ ነስንሰንና ድንጋይ ተንተርሰን አብዝተን ልንጾምና ልንጸልይ ይገባል፡፡ ሊለያየን፣ ሊነጣጥለን፣ ሊበታትነን እና ሊገድለን ካሰበው እንዲሁም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና አንድነትን ሊነፍገን ከቃጣው ጠላትና ሃይማኖታችንን ሊያስተወን ከሚመጣ ፀረ ሃይማኖት እንድናለን። ስለዚህ ከፊታችን ያለችውን ስድስቱን የጳጉሜን ቀን በፍቅር፣ በአንድነትና በሃይማኖት ጸንተን፣ ጾመን፣ ጸልየን ለዘመነ ማቴዎስ እንድንደርስ እግዚአብሔር አምላካችን ይርዳን፤ አሜን።

🌹 የእመብርሃን ፍቅሯ ይብዛልን 🌹
❖❖❖ፀጋ አብ ሂሩተ ዘወልድ ሱራፌል ዘመንፈስ ቅዱስ ይህድር በላዕሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡ (የአብ ፀጋ የወልድ ቸርነት የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ለዘለዓለም በላያችን ላይ ይደር አሜን፡፡ ❖❖❖
👉🏽
@SaintGebrielSundaySchool
Forwarded from ገብረ እግዚአብሔር ኪደ (ገብረእግዚአብሔር ኪደ)
+ ለምንድን ነው የምንጾመው? +

እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡ ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው? በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን? በየቀኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታወቀ የተረዳ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ [በመጾማችን - በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?

በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡ ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያት ነው፡፡

#አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች - ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ - አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡ በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡

#ኹለተኛው ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ አጥቶ የመራብ ትርጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡ በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድናስብ ያስፈልጋል፡፡
🌿ደሐራዊ ልደት🌿
.
.
.
ምድር ተደነቀች፣ባ'የችው ተገርማ
የአምላክን መወለድ፣ብስራቱን ብትሰማ
ይህ ነገር ድንቅ ነው፣እጅግ የረቀቀ
ፀሀይ ግርግም ወርዶል፣ሰው እየፈለገ
ይህ!
ከተፈጥሮ ርቀት፣(ጠብቆ ይነበበ)ከልማድ የላቀ
አሀዜ ዓለማት፣ገባሬ መንክራት፣ሳለ የረቀቀ
በፍቅር አሽክላ፣በመውደድ ተጠልፎ፣በሰው እጅ ወደቀ።
ኑ እንመልከተው፣ፀሀይ ተጠቅልሎ
በአምላክ መልክ ላይ፣የሰው ልጅ ተስሎ
ቢያድለኝ!
እንደ ሰባ ሰገል፣እንደ ተጓዦቹ
ከሜዳው በዋልኩኝ፣ልክ እንደ እረኞቹ
ምን እንኳን ብጎድል
ማግደው ባይኖረኝ፣ግብሬ ተበላሽቶ
እጅ መንሻ ባልይዝ፣ ሀብቴ ከእኔ ጠፍቶ
በሆንኩኝ መሬቱን፣የኤፍራታን ስፍራ
በአምላካዊው ብርሃን፣ልቤን እንዲያበራ

አዳም ሆይ! ከዘመኔ ማዶ
ከህቱም መሬት ላይ፣አካልህ ተገኝቶ
የተፈጥሮ ሕግጋት፣ በአምላክህ ተሰርቶ

አካልህ ሳይጎድል፣ሳይቆስል ሳይደማ
ሄዋን ተገኝታለች፣ ከአንተነትህ ማማ
ይገርማል!
በወንድነት ባህርይ፣ማህፀን አበጅቶ
ዘርን ሳያጣምር፣ሰያዋህድ ከቶ
ወንድ እናት ትሆን ዘንድ፣ሰርቶሀል አጥርቶ
እናም ና ታየው ዘንድ፣ካለህበት ሰፍራ
የፈጠረክ አምላክ፣ከድንግል ተገኝቷል፣
ከአንተነትህ ዳራ
ሄዋን ሆይ!መሻትሽ ሊፈፀም፣ምኞትሽ ተሳክቶ፣
አዳማ'ዊ አካልሽ፣
ከአምላክ ተዋህዶ
ባህሪይሽን ተላብሷል፣አምላክ ሰው ይባል ዘንድ
ሰው አምላክን ወልዶ
ይደንቃል!
ከመናገር በላይ፣ከማሰብ ይረቃል
ቀዳማዊ ሳለ፣በፍጡር አጠራር
ታናሽ ነው ተብሏል
እሱ!የዓለም ገዢ፣የፍጥረታት ጌታ
ተወልዷል ከድንግል፣ ማህተሟን ሳይፈታ
በግ ነው የሚታረድ፣ከበረት የዋለ ከክብቶቹ ጋታ
ህይወት ነው የሚያድን፣ የደሙ ጠብታ
ቀስ በቀስ ያደገ፣ የአዳም ዘር መከታ

ድንግል ሆይ!
የልጅሸን ልደት፣አብሬሽ እንዳከብር፣
ሰሙን እንድ ጠራ
ከበረቱ ደጃፍ፣መላዕክት ካሉበት
ከእረኞቹ ጋራ
እንድገኝ በሰዓቱ፣ "በጎል በጎል" ሲባል
ከዝማሬው ስፍራ
በአጠቡት ጡቶችሽ፣በአቀፉት አጆችሽ
እልሻለው አደራ
አውቃለው!

አደራዬ ከቶ፣ እንዳይነጥፍ አምናለው
ስላጣነው ሰላም፣ስለተነጠቅ ነው
በመላዕክት ልሳን፣ያኔ እንደ ተባለው

ዛሬም በ ልደቱ፣እንዲባል የጥንቱ
ሰላም ለሰው ልጆች፣ ለአዳም ዘር በብርቱ
እንዲሉን መላዕክት፣ሆነው በአንድነቱ
አንጥፋ ከበረት፣ እንኑር በቤቱ።

🌿 #እንኳን #ለጌታችን #ለመድሐኒታችን #ለኢየሱስ #ክርስቶስ #የልደት #በዓል #በሰላም #አደረሳችሁ🌿
🌿#መልካም #በዓል!🌿
#በድጋሚ የተፖሰተ

//#ፍፁም ገነነ//
@zosemas
ደሐራዊ ልደት(፪).aac
4.5 MB
ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች 🌿እንኳን ለጌታችን ለመዳሐኒታችን ለኢየሱሰ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ🌿
🌿መልካም በዓል🌿
@zosemas
አድዋ!

የነፃነት የድል አምባ
በዕምነት በርኖስ፣ በዕንባ መባ
ፈርሷል ባንቺ ፣ሀገር ሚንድ፣ ታላቅ ደባ
አድዋ
መናገሻሽ እውነት እንጂ፣መች አንግቦ የሀሰት ካባ
ማን ነው ከቶ የሚያፈርስሽ፤
ምን ሀይል ነው የሚንድሽ፤
ቅድስቲቱን የእግዜር አምባ
አድዋ!
የድል ነፀብራቅ እውነቷ
የፅናት ምሥጢር ሕይወቷ
መሰናስልሽ ሰውነት
ሰብሳቢ ያለ ልዪነት
የሰውነትሽ ልኬቱ
አጥንት ያለየው ስሌቱ
ዘውግ ያልናጠው ማንነቱ
በደም የተዋሀደን፣የማንነትሽ ስሪቱ
በዕትብትሽ መሀል ያለፈው፤
ኢትዮጵያዊነት ነው በብርቱ

አድዋ!
ሊቃውንትሽ በያሬድ ዜማ፤በቅኔ አለም ቢናኙ
የጦሩን ስፍራ ለውጠው፤ቅኔ ማህሌት ቢያሰኙ
የጠላት ልቡ ረበደ
ጉልበቱ አቅሉን በመሳት፤
ለኢትዮጵያውየን ሰገደ

ሀይ አድዋ!
ሼሆችሽ የማለሉልሽ፣በወኔ የታገሉልሽ
ኢማም ኡስታዙ በህብረት፣በዱአው በአንድ የቆሙልሽ
አንቺ የድል ተምሳሌት፣የኢትዮጵያዊነት ህብር ነሽ

አድዋ!
ካህንሽ ታቦት አክብሮ፣ፅና ማጥንቱን አብሮ
ቅድመ እግዚአብሔር የሚያሳርግ፤
የዕምነት ማህሌት ወድሮ
ከፊትሽ አስቀድሞታል፣እግዜር ሀያሉን በዕሮሮ

አድዋ! ያቺ የጥንቷ፣ዛሬም በኛ ትውልድ መጥታ
የመከፋፈል ዕብሪትን፣ከእኔነት ጎራ ለይታ
በእኛነት አንድ ታድርገን፣በኢትዮጵያዊነት ረታ።

23/06/2013
ፍፁም ገነነ
@zosemas
ጾም በአንተ ውስጥ የሆነ አንድ ነገር መለወጡን ተመልከት።

ከጾም የምታገኝው ነገር የምግብ ለውጥ መሆኑን ብቻ አትመልከት። ለተሻለ ህይወት የሚደረግ ለውጥ መሆኑን ተመልከት። ይህም ማለት በአንተ ውስጥ ያለ ጉድለትንና በውስጥህ እንዳለ የሚሰማህን ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር የሚሆን ድክመት ተመልከት ማለት ነው። ይህ ሳይሆን ከቀረ በሃምሳ አምስቱ የሁዳዴ ጾም ቀናት ውስጥ ራስህን አሸንፈህ ከቆየህ በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር የፍቅር ዝምድና እና የተረጋጋ ግንኙነት ሳትፈጥር ከጾሙ አስቀድሞ የነበረህን አቋም ሙሉ ለሙሉ ይዘህ ለመውጣት ከሆነ የነፍስህ ጥቅም ምን ሊሆን ነው? አንተ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳታመጣና አስቀድመህ በነበርህበት ሁኔታ ውስጥ እያለህ እስከ አሁን ድረስ ስንት አጽዋማት እንዳለፉህ አስብ!

በሁሉም አጽዋማት ውስጥ ፈቃድህ ደካማ ጎንህን ለማሸነፍ ስኬታማ እንድትሆን አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር እንድትታረቅ አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ወይም የእርሱን ፈቃድ ጣፋጭነት እንድትቀምስ አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ከእግዚአብሔር። ጋር የሚኖርህ ዝምድና እስከ አሁን ድረስ እንደምን የሰፋና የጠለቀ ይሆን ነበር!

ስለዚህ ንስሃ በመግባት ጾምህን ጀምር። ጾምህን በጸሎት በምጽዋት በስግደት በመንፈሳዊ ንባባት በቅዳሴ በኪዳን ጸሎቶች አጅበው። እነዚህን ሁሉ በማድረግህ ከእግዚአብሔር ጋር ትወዳጃለህ የሁዳዴ ጾም የያዛቸው በረከቶች ብዙ ናቸውና። እኒህን ካደረክ በመጨረሻ ላይ ውጤቱን ከአምላክህ ትቀበላለህ።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
2025/01/22 06:19:08
Back to Top
HTML Embed Code: