Telegram Web
💦ትንቢተ ዮናስ💦
ምዕራፍ 1
በህዝብዋ መካከል ዓመጽ ስለ ፀና
በጣም ተቆጥቼ አዝኛለሁና
ይህን ለነነዌ ንገራት በአዋጅ
አለና ለዮናስ ለአሚታይ ልጅ
እግዚአብሔር አዘዘው እንዲሄድ በቶሎ
ዮናስ እምቢተኛው አሰበ ኮብልሎ
ከአምላክ ተደብቆ አምልጦ ሊጠፋ
ወደ ተርሴ ሊጓዝ ፤ ሄደ ወደ ያፋ
ዋጋ ከፈለና በመርከብ ተሳፍሮ
አያጉረመረመ ባህሩን ተሻግሮ
ዮናስ ተደብቆ ሊሄድ በግስገሳ
ከእግዚአብሄር ተልኮ ማዕበል ተነሳ
ታላቅ ሞገድ ሆኖ ባህሩ ተቆጣ
መርከበኞች ፈሩ ትልቅ ሽብር መጣ
መርከቡ እንዲቀለው እናድርግ እያሉ
አንስተው ብዙ እቃ ወደ መርከብ ጣሉ
ባህሩም ባሰበት በጣም ተናወጠ
መርከከቡ መሰለ የተገለበጠ
ሰው ሁሉ ተነሳ ጸሎት ለማድረስ
ይህ ሁሉ ሲሆን ተኝቷል ዮናስ
ወደ ዮናስ ሄዶ የመርከቡ አለቃ
ቀሰቀሰው እና ከእንቅልፉ ሲነቃ
እግዜር እንዲያድነን ከዚህ ክፉ ጥፋት
ተነስ ፀልይ አለው ይብቃህ ማንቀላፋት
በመርከብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ተሰብስበው
ተመካከሩ እና በነገሩ አስበው
አለ ኃጢአት ሰርቶ ከእኛ ጋር የመጣ
ለይተን ለማወቅ እንጣጣል እጣ
አለዚያ አንድንም ስለተባባሉ
ተሰበሰቡ እና እጣ ሲጣጣሉ
እውነትም እንዳሉት አጥፊው ሰው ታወቀ
በእንቢተኛው ነብይ በዮናስ ወደቀ
ዮናስ ተረዳና እጁ እንደተያዘ
ያጠፋውን ጥፋት ገልፆ ተናዘዘ
ምነው ባትመጣ ተጣልተህ ከጌታ
እየው መርከባችን እንደሚንገላታ
ቁጣው እንዲታገስ ለማግኝት ጸጥታ
በል አንተው ፍረደን ምን ይበጃል ቢሉ
ዮናስ መለሰና እዚህ ያለህ ሁሉ
ስለምን ይጠፋል በኔ የተነሳ
ወደ ባህር ጣሉኝ አለብኝ አበሳ
ተመልከቱ እነሆ ስራውን አወቀ
ጥፋቱን ገለጠ ይህው መች ደበቀ
እሱ ከፈረደ መልሶ በራሱ
ምን እናድግ ብለው ሊጥሉት ተነሱ
ከደሙ አንፃን ሲሉ ለእግዜር አመልክተው
ወደ ባህር ጣሉት ዮናስን አንስተው
በዮናስ ላይ ኖሮ የመጣው ይህ መዓት
ባሕሩ ፀጥ አለ ልክ በዚያው ሰዓት

ምዕራፍ 2 ለማግኘት forward ይቀላቀሉን

ይቀጥላል

ይቀጥላል....
ዜማውን ለማግኘት ከላይ ያለውን forward በመንካት ቻናላችን ይቀላቀሉን

ታብሷል እንባዬ ሸሽቷል መከራዬ
ማርያም ማርያም እያልኩ
ኧረ ስንቱን አለፍኩ፪
።።።።።።።አዝ
እኔስ መስሎኝ ነበር ማይገፍ ቀኑ
ነብሴን ያስጨነቃት ያዘን ወላፈኑ
ማልቀስ ብቻ ሆኖ ዘወትር ስራዬ
አናግርሻለው ሆኜ ለብቻዬ
ድንግል ደረሽልኝ ህልሜን ፈታሽልኝ
አልኩኝ ቀና ቀና ያም ቀን አለፈና
።።።።።።።አዝ
መቆሸሼን አይቶ ከሳሼ ቢከሰኝ
እመአምላክ ግን ምልጃሽ አዲስ አደረገኝ
ነጩን አለበሽኝ ወርቃማውን መፍታ
እንዴት ዘነጋለው ያንችንስ ውለታ፪
።።።።።።አዝ
በቀኙ ባትቆሚ ፀሎቴን ባትሰሚ
አይሰምርም ጉዞዬ ፅልመት ነው ተስፍዬ
።።።።።።አዝ
እንደናት አባብለሽ አሳድገሽኛል
ኑሮዬ ሲጨልም ብርሃን ሆነሽኛል
የተማመንኩበት ሲሸሸኝ ወዳጄ
አንቺ ግን አገኘሽ በጓዳ በደጄ ፪
።።።።።አዝ
አፈራች በለሴ ተደሰተች ነብሴ
ለምን ላቀርቅርህ አሁን ልዘምርህ
።።።።።።አዝ
ትላንት ያዩኝ ሁሉ ዛሬ ይገረማሉ
እንዴት በእግሩ ቆመ እየተባባ
ለሰው የማይቻል ለልጅሽ ተችሏል
እንዳያልፉት የለም ለልጅሽ ተችሏል፪
።።።።።።አዝ
ከቤቴ ማጠፊ ችግሬን ምትቀርፊ
እንዳንቺ ማን አለ ጭንቀቴን የጣለ
ታብሷል እንባዬ...፪
ታላቅ በሆነው እምነትሽ

ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ
ካለሽበት ገስግሼ መጣሁኝ
እናቴ ክብርሽን አንግሼ
ሆንኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ
እናቴ ቅድስት አርሴማ
ዝናሽ ለዓለም ተሰማ
#-አዝ።።።።።።።።
ስመጣ ባልጋ ነበረ
ተስፋዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ሥራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት
#-አዝ።።።።።።።።።
ደምግባት ከንቱ ብለሽ
ለሰማይ ክብር ታጭተሽ
የእምነቴ አሰረ ፍኖት
በምልጃሽ አለሁ በህይወት
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል
#-አዝ።።።።።።።።።።።።
እርዳታሽ የደረሰለት
ያመጣል የልቡን ስለት
ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው
ባንቺ አፍሮ የሄደው ማነው
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
እነሆ ድንቅ ዝማሬ በእውነት

https://www.tgoop.com/ortodoksawimezmur
🌼 መልካም በዓል ይሁንላችሁ:: 🌼
+++ ጥንቃቄ ለመላው ኦርቶዶክሳዊ❗️
ሁሉም ኦርቶዶክስ-ሼር-ያድርግ!!!

+++ የቀበሌ መታወቂያ ጉዳይ❗️+++

+++ ታግዶ የቆየው የመታወቂያ እድሳት ከዚህ ከህዳር ወር ጀምሮ መሰጠት የተጀመረ መሆኑን ተከትሎ መታወቂያ ለማሳደስ የሚሄዱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከታች የምትመለከቱትን ፎርም አስቀድመው እንዲሞሉ በመደረግ ላይ ይገኛል።

+++ በሚሞላው ፎርም ላይ ከተካተቱት መጠይቆች አንደኛው " ሃይማኖት " የሚለው ነው። አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ ባለማስተዋልና ትኩረት ባለመስጠት በዚህ መጠይቅ ሥር "ክርስቲያን" የሚለውን መጠሪያ መጠቀም ልምድ አድርጎት ይታያል።

+++ ሆኖም በዚህ ወቅት እንደ ወል ስም እያገለገለ በሚገኘው ስም መጠቀም ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ምዕመናን/ት ቁጥር ጋር ተያይዞ በቀጣይ ትልቅ ፈተና ይዞ የሚመጣ መሆኑን በማስተዋል ሐይማኖት በሚለው መጠይቅ ሥር " ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ " የሚለውን የሃማኖታችንን መጠሪያ ለይቶ በአግባቡ መሙላት ይገባዋል።

+++ በክርስትና ስም የሚጠቀሙ ሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች በመኖራቸውና ይህም የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር የተዛባና የተሳሳተ እንዲሆን ያደርጋል።

+++ በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ እንዳለው ኦርቶዶክሳውያን ከሀገሪቱ ፖለቲካዊ ፤ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች እየተገፉና እየተገለሉ እንዲሄዱ በማድረግ ቁጥራቸውን በማዛባትና ዝቅ አድርጎ በማሳየት ፍላጎታቸውን ለማሳካት ለሚፈልጉ አካላት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አይገባም።

+++ በተለይም በዕድሜ የገፉና የቀለም ትምህርት ያልቆጠሩ ወገኖቻችንን በማሳወቅ "ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ" የሚለውን የሃይማኖታችንን መጠሪያ በአግባቡ እንዲሞሉ ማድረግ ከእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ የሚጠበቅ ተግባር ነው።
ቸሩ አምላካችን በተዋሕዶ ሃይማኖታችን ያጽናን!
ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
ኅዳር ፲፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም

ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡

ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡ እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡ በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡

ምንጭ፡-

ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡፡

ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ምንጭ:- ከማሕበረ ቅዱሳን ገፅ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

     ሥርዓተ ማህሌት ዘህዳር ጽዮን
  
🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር  ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
  🕯
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ፤ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት፤ እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት፡፡
🕯

ዘጣዕሙ ፦
ሰላም  ለዝክር ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ፤ለወልድኪ አምሳለ  ደሙ ፤መሠረት ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእም ቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

🕯
ዚቅ
ዘዘካርያስ ተቅዋም  ዘወርቅ፤ዘሕዝቅኤል  ነቢይ ዕፁት  ምሥራቅ ለመሠረትኪ  የኃቱ  ዕንቈ ሰአሊ ለነ ማርያም በአሚን ንጽደቅ፡፡
🕯
    ነግስ፦
ነቢያተ እሥራኤል ጸሐፉ በመጽሐፎሙ እሙነ፤ ነገረ ሰቆቃው ወላህ በዘመኖሙ ዘኮነ፤ ውስተ አፍላጋ አመ በጼዋዌ ነበርነ፤ውስተ ኵሃቲሃ እንዚራቲነ ሰቀልነ ፤ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን እምነ፡፡

🕯
ዚቅ
ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሃ ዚአነ፤
እንተ ረከበተነ በእንተ ጽዮን፤
ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ
🤲
ወረብ፦
ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሃ ዚአነ  እንተ ረከበተነ/2/
ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ/2/

🕯
  ማኅሌተ ጽጌ
ዘካርያስ ርእየ ለወርኃ ሳባጥ በሠርቁ፤ ተአምረኪ ለዘይት ማእከለ ክልኤ አዕጹቁ፤ማርያም ጽዮን ለብርሃን ተቅዋመ ወርቁ፤ ዕዝራኒ በገዳም አመ ወዓለ ዉዱቁ፤ለኅበረ ገጽኪ ጽጌ  ሐተወ መብረቁ፡፡
 
🕯
   ዚቅ፦
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፯ቱ መኃትዊሃ፤ ወ፯ቱ መሣውር  ዘዲቤሃ፤ ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ ዘኩለንታሃ ወርቅ  ወያክንት፤ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት
 
🤲
ወረብ፦
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ፯ቱ መኃትዊሃ/2/
ዕዝራኒ ርእያ በርእየት ብእሲት/2/
  🕯

ዚቅ(ዘበአታ)
ዕዝራኒ ርእያ በርእየተ ብእሲት፤ ወሶበ ርእያ ኢኮነት  ብእሲት አላ ሀገር ቅድስት ፤ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ዘኲለንታሃ ወርቅ ወያክንት
🕯
    መልክዓ ማርያም 
ሰላም ሰላም ለዝክረ  ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ  ከልበኒ  ወቍስጥ  ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል  ለባሲተ ዐቢይ ትዕዛዝ፤ይስቅየኒ ለለጽባሑ  ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ  ለሠናይ አርዝ፡፡

🕯
ዚቅ
ሃሌ ሉያ X3 እምነ ጽዮን በሀ፤
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርጉት በስብሐት፤ዓረፋቲሃ ዘመረግድ ሥርጉት በስብሐት፤ ወማኅፈዲሃ  ዘቢረሌ  ሥርጉት በስብሐት፤ እምስነ ገድሎሙ ለሰማዕት ሥርጉት በስብሐት፤ታቦተ ሕጉ  ለንጉሥ ዐቢይ ሥርጉት በስብሐት፤
እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፤ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ፡፡

🤲
ወረብ
እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ ፀሐየ ጽድቅ/2/
ለሰማዕትሥርጉት በስብሐት ሥርጉት በስብሐት/2/

🕯
መልክዓ ማርያም፦
ሰላም ለአስናንኪ ሐሊበ ዕጐልት ዘተዛወጋ፤ ወመራዕየ ቅሩፃት  እለ እምሕፃብ ዐርጋ፤ ማርያም ድንግል  ለደብተራ  ስምዕ  ታቦተ  ሕጋ ፤
አፍቅርኒ  እንበለ  ንትጋ ለብእሴ  ደም ወሥጋ፤ ዘየዐቢ  እምዝ ኢየኃሥሥ ጸጋ፡፡
   
🕯
  ዚቅ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት  ሕጽርት፤ ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት፤ንጉሥኪ  ጽዮን ኢይትመዋዕ በፀር ወኢየኀድጋ ለሀገር፡፡

🤲
   ወረብ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር  በካህናት ሕጽርት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት/2/
ንጉሥኪ ጽዮን ኢይትመዋዕ በፀር ወኢየኀድጋ ለሀገር/2/

🕯
   መልክዓ ማርያም፦
ሰላም ለከርሥኪ ዘአፈድፈደ ተበጽዖ፤እም ታቦተሙሴ ነቢይ ለጽሌ ትእዛዝ ዘየኀብኦ፤ማርያም ድንግል ጊዜ ጸዋዕኩኪ  በአስተብቍዖ፤ ለፀርየ ብእሴ አመጻ ኀይለ  ዚአኪ  ይጽበኦ፤እስከነ  ያሰቆቁ ጥቀድኅሪተ ገቢኦ፡፡

🕯
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት፤
ተመጠወ  ሙሴ ኦሪተ፤ ጽላተ አሥሮነ ቃላተ፡፡

🤲
ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት፤
ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ ጽላተ አሥሮነ ቃላተ፡፡

🕯
  መልክዓ ማርያም፦
ሰላም ለመከየድኪ እለ ረከቦን መከራ፤እምፍርሃተ ቀተልት ሐራ እንበለ አሣእን አመ ሖራ፤ማርያም ጽዮን ታቦተ ቃለ ጽድቅ መንፈቃ ዕሥራ፤ ዕጐላት እም ዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ፤ አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እም ይእዜ ለግሞራ።
🕯

  ዚቅ
ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ፤
ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ፤አእመርክዋ አፍቀርክዋ፤ከመ እኅትየ  ኀለይኩ፤እም ድኅረ ጉንዱይ መዋዕል፤
ወእምዝ እም ድኅረ ኅዳጥ ዓመታት፤ካዕበ ርኢክዋ ወትትሐፀብ በፈለገ ጤግሮስ
፡፡

🤲
ወረብ
ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ/2/
ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ አእመርክዋ አፍቀርክዋ ለቤተ ክርስቲያን/2/

🕯🕯🕯
   መልክዓ ማርያም፦
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ለዘይስእለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ማርያም ዕንቍየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤
ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ፡፡

🕯
ዚቅ
አብርሂ አብርሂ  ጽዮን፤ ዕንቍ ዘጳዝዮን፤
ዘኃረየኪ ሰሎሞን፡፡
🤲🤲

ወረብ
አብርሂ አብርሂ ጽዮን/2/
ዕንቍ ዘጳዝዮን ዘኃረየኪ ሰሎሞን ንጉስ/2/
🕯

  ምልጣን 
ዓይ ይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ እምርሑቅ፤ ከመ ማኅቶት ብርህት ከመ ፀሐይ፤ ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት ዕዝራኒ ተናገራ ዳዊት ዘመራ፡፡
🕯
አመላለስ፦
ዕዝራኒ ተናገራ /2/
ተናገራ ዳዊት  ዘመራ/4/

🤲🤲
ወረብ ዘምልጣን
ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት፤
ዕዝራኒ ተናገራ ተናገራ ዘመራ ዳዊት

🕯
እስመ ለዓለም
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ኩለንታሃ ወርቅ በየማና ወበጸጋማ አዕጹቀ ዘይት ፤ደብተራ ፍጽምት ሀገር ቅድስት፤ ነቢያት ይትፌሥሑ በውስቴታ፤ ሐዋርያት ይትኃሠዩ በውስቴታ፤ ወዳዊት ይዜምር በውስተ ማኅፈዲሃ፤ ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ በቃለ ዳዊት ይሴብሑ፤ወይብሉ ኵሎሙ ሃሌ ሉያ፡፡

🕯
   አመላለስ፦
ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ በቃለ ዳዊት ይሴብሑ/2/
ወይብሉ ኵሎሙ ሃሌ ሉያ(4)።

🤲
   ወረብ
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ኩለንታሃ ወርቅ በየማና ወበጸጋማ አዕጹቀ ዘይት፤
ነቢያት ይትፌስሑ ሐዋርያት ይትሐሰዩ በውስቴታ ወዳዊት ይዜምር በውስተ ማኅፈዲሃ፡፡

🕯🕯🕯
     ሰላም
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ገነተ ትፍስሕት መካነ ዕረፍት፤ እንተ ይእቲ ማኅደር ለካህናት፤ ለእለ የኃድሩ በፈሪሃ እግዚአብሔር፤ ይእቲኬ ቤተ ክርስቲያን፤በውስቴታ የዓርጉ ስብሐተ ካህናት በብዙኅ ትፍስሕት ወሰላም፡፡


👇👇👇👇👇
ለመቀላቀል
     @ortodoksawimezmur
@ortodoksawimezmur
    
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
አበቃልኝ አትበል !

በዚህ ደስ የሚል የሚያምር ጠዋት ነቅተሀል ፤ ማታ ስትተኛ ዛሬ እንደምትነቃ ማረጋገጫ አልነበረህም ነገር ግን ተስፋ ነበረህ ነገ ይሄን አደርጋለው ብለህ ያቀድኸው ነገር ነበር ! እናም ነቅተህ የማድረግ እድል ገጥሞሀል ስለዚህ ዛሬ ያነቃህ ዛሬ እድል የሰጠህ ፈጣሪ አብሮህ ነበር አሁንም አብሮህ አለ ከዚህም በኋላ አብሮህ ነው እስካለህ ድረስ እስከጠየቅኸው ድረስ እስከለፋህ ድረስ መቼም አይተውክም !
ደስስስ የሚል ቀን😍
የተባረከ ቀን ተመኘን🙏🙏
ስኬት ለሚገባው  የፈጣሪ ስጦታ ነው!

በጣም በሚገርም ሁኔታ በጣም ትልቅ ስኬት ላይ ያሉ ፣ የሚያስቡትን ትላልቅ ሀሳብ ያሳኩ የእውነት ደስተኛ የሆኑ ሰዎች የህይወታቸው ትልቁን ድርሻ የሚሰጡት ለፈጣሪ ነው ፤ እንዴት ተሳካልህ ሲሉት ፈጣሪ በመንገዴ ሁሉ ከእኔ ጋር ሆኖ ረዳኝ እኔ በብዙ ለፋው እርሱም እንደሚገባኝ አይቶ ካሰብኩት በላይ ሰጠኝ ብለው በልበ ሙሉነት ይናገራሉ ፤ የፈጣሪ ዋጋ የገባው ሁሌም አሸናፊ ነዉ!

😁ተመስገን ዛሬ ቀኑ ደስ ይላል😂

🤩ደስስስ የሚል ቀን😁 ፈገግ ያለ ውሎ😍
ፈጣሪ አለልን !🙏

ፈጣሪ አይተውም ቀን አለው እየሆነ ስላለው ስለሚሆነው ስለሆነውም ሁሉ የእርሱ መልካም ፍቃድ ከጎናችን ነው ትቶን የማያውቅ መቼም አይተወንም !

የተባረከ ቀን 😍
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 9 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሠላም አሸጋገራችሁ።

ከእርስዎ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሰጥ ልዩ የዓውደ ዓመት  ስጦታ።

ይህንን ምስል ለወዳጅ ዘመዶ በማጋራት
እርሶም ታሪክን ይጻፉ።

መልካም ዓውደ ዓመት
#ቆዳው_ለትውልድ
#ሐመረ_ብርሃን

https://linktr.ee/hamereberhan
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🌼🌼እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሠላም አሸጋገራችሁ። 🌼🌼

ከእርስዎ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሰጥ ልዩ የዓውደ ዓመት  ስጦታ።

ይህንን ተንቀሳቃሽ ምስል ለወዳጅ ዘመዶ በማጋራት
እርሶም ታሪክን ይጻፉ።

መልካም ዓውደ ዓመት

#1ቆዳ_ለሐመረ_ብርሃን


https://linktr.ee/hamereberhan
🔥🔥🔥BTC Miner is a bitcoin miner with a fully automated process. Earn money automatically by being active every day.
Click the link below to join automatic mining to make money
https://www.tgoop.com/BTC_Miner_aa_bot?start=891671269
2024/11/05 00:32:22
Back to Top
HTML Embed Code: