#ቅዱስ_ኡራኤል_እንኳን_አደረሳችሁ_አደረሰን
ኡራኤል ማለት ምን ማለት ነው ?
ኡራኤል ማለት ትርጉሙ #የብርሃን_ጌታ_የአምላክ_ብርሀን ማለት ነው ::
ቅዱስ ኡራኤል ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ ስትሰደድ መንገድ የመራ የረዳ መልአክ ነው ::ክርስቶስ ለአለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሀን ፅዋ ተቀብሎ በብርሀን በመነስነስ ለአለም የረጨ "ለነብዩ እዝራ ሱቱኤል ፅዋ ጥበብ ያጠጣ እርሱ ነው ::ይህ መልአክ ያፅናናናል ይታደገናል ይመግበናል ይመራናል ስሙ ከወጥመድ ከሰይጣን ከክፉ መናፍስት ውጊያ ሁሉ ይጠብቀናል ::
#ኡራኤል ፦ እግዚአብሔር ፍጹም ብረሃን ነው ፣የብረሃናት ጌታ ፣የብረሃናት አምላክ እራሱ የምያበራል የነፍሳችን ብረሃን ሲል ይተርጉመዋል።
ይህ ቅዱስ መላዕክ በመብርቅ ፣በነጉድጓድ ላይ ከፍጥረት ጅምሮ የተሾመ ቅዱስ መላዕክ ነው።
ለመቅስፍት ሳይሆን ለበረከት ለበዓት ሳይሆን ለይቅርታ የሚላክ መላዕክ ነው ።
የጌታችን መዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ደም በብርሃን #ጽዋ ቅድቶ ለአለም የረጨ ቅዱስ መላዕክ ነው። (#ሔኖክ28;13)
እንኳን አደረሰቹ አደረስን የመላኩ ጥበቃው አይለየን ።
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.

የተሰበረ ጽዋዕ
እዚኽ ፎቶ ውስጥ በአካል የማውቀው ዘማርያምን ብቻ ነው፡፡ ሌሎች ግን በማኅበራዊው ሚዲያ መልስ ሲሰጡና ሲጠይቁ አያቸዋለሁ እንጂ ፊት ለፊት ተገናኝተን አናውቅም፡፡በወንድሞቻችን ፊት ፕሮቴስታንት ሰባክያን ምላሳቸውን ሲተሳሰር ብዙ ጊዜ አይቻለኹ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ "ከኦርቶዶክስ ወንድሞች ጋር እንዳትከራከሩ" የሚል አዋጅ ሲያውጁ ሰምቻለኹ ጰንጤዎቹ፡፡
በአጭሩ፥ እኒኽ ወንድሞቻችን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳን መላእክትና ሰዎችን ታመልካለች የሚለውን ፕሮቴስታንታዊ የድር ምሽግ ሲበጣጥሱ ተመልክቻለኹ፡፡ ከዐይን ያውጣችኹ አልላችኹም፡፡ ዐይንም ጆሮም ውስጥ ናችኹና፡፡
ጽንዑ ወኀይሉ፡፡ ለማለት ነው አመጣጤ፡፡
ከእኒኽ ወንድሞች መኻል አንዱ ወይም ኹሉም ሊሳሳቱ የሚችሉ ናቸው፡፡ የቀለም ሠረገላ የማያሰናክለው የለምና፡፡
ደግሞም እኔ እንኳ የሰማኋቸው የሚታረሙ ስሕተቶች አሉ፡፡የሚታረም ነገር ተገኘ ማለት ግን፥ ሙሉ እርሻው አረም ነውና አያስፈልግም የሚል ቧልት መናገር ቅንነትና ወንድማዊ ፍቅር ይጎድለዋል፡፡
በአንድ ወቅት፦
አንድ እጅግ የተከበሩ ሊቅ ከአንዲት ሴት ጋር ድቀት አገኛቸው፡፡ እኒኽን ሊቅ ብዙ ሰው ያውቃቸዋል፡፡ በዚኽኛው ታሪክ ግን ሰፊው ሕዝብ ስለማያውቃቸው ስማቸውን ልለፈው፡፡
ይኽን ድቀታቸውን የሰማ ደብተራ አንድ ቀን ማሕሌት ውስጥ አገኛቸው ሊቁን፡፡"ደግሞ አንተ እዚኽ ምን ልታደርግ ገባኽ?"
ሲል በፍና ተሣልቆ አፌዘባቸው፡፡ እርሳቸውም "እኔኮ የተሰበርኩ ጽዋዕ ነኝ" ብለው አንጀት የሚበላ መልስ ሰጡት፡፡
የተሰበረ ጽዋዕ ሰባራ ስለኾነ አይጣልም፡፡ንዋይ ቅዱስ ነውና በክብር ከዕቃ ቤት ይቀመጣል እንጂ፡፡
እንደዚያ ደብተራ ለቤተክርስቲያን የቀናን እየመሰለን ጥቂት ሸራፋ ያገኘንባቸው ጽዋወችን ኹሉ አውጥተን እንጣል ማለት እጅግ የከፋ በደል ነው፡፡ክርስቶሳዊውን መንገድ የረሳ ነውና፡፡ "ድኅረ ተሰብረ አጽንዖ ለሰብእናነ ልሕኵት፥ ለብሓዊ ክርስቶስ በማየ ሐዲስ ጥምቀት" የምትል ድንቅ የንጉሥ ጉባኤ ቃና አለች፡፡ ግርድፍ ትርጉሟ፦ ገላ'ችን ከተሰበረ በኋላ ሸክላ ሠሪው ክርስቶስ በአዲስ የውኀ ጥምቀት እንደገና ሠራው፡፡ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ከጌታዋ የተማረችው የተሰበረን መጠገን ነው፡፡
ችግሩ፥ መጠገን እንደመስበር ቀላል አይደለም፡፡ ለመጠገን ዕውቀትና ቅንነት ያስፈልጋል፡፡ ለመስበር ግን ኦርቶዶክሳዊ የዘብነት ቀለም የተቀባች ምላስ በቂ ናት፡፡
ወንድሞች በጎ ሲሠሩ እናበርታ፡፡ሲስቱ እንክርዳድ ከስንዴ እየለየን በፍቅር እናርም፡፡አልታረምም የሚል ካለ ደግሞ የቤክርስቲያን ቱንቢ ያርመዋል፡፡እንደ ግለሰብእ እኔ ነኝ ቱንቢው ማለት ግን የስሕተት ስሕተት ነው፡፡
በየሚዲያው ሌሎች ጥሩ ወንድሞችም አሉ፡፡ ነገር ግን በልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎት የተገለጡ ናቸውና ተውኳቸው፡፡
መ/ር ስሙር

🌹
ጣ ዕ ም ፡ የ ሌ ለ ው ፡ ስ ብ ከ ት
ወደ ከተማችን አንድ ሰባኪ ሊሰብክ መጣ ፣ የመጣው ለመስበክ ፈልጎ አልነበረም እኛን ለማዳን ጉጉት አድሮበት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ሊያሰማን ጓጉቶ አልነበረም በግድ ተገፍትሮ ፣ ተተፍቶ ፣ ተወርውሮ የመጣ ዓይነት ሰው ነበር ፡፡
ወደ መሃል ከተማም አልገባም የከተማችን አንድ ሦስተኛውን ብቻ ከተጓዘ በኋላ ስብከቱን ጀመረ የሰበከው ስብከት ሰላምታ የለውም ፣ መግቢያ የለውም ፣ መውጫም የለውም ፣ ማጽናኛም የለውም ‹ ንስሓ ግቡ › የሚል አዋጅ የለውም በጩኸት የተናገረው አንድ አስደንጋጭ ዐረፍተ ነገር ብቻ ነበር ‹‹ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች !! ›› ከነነዌ ነዋሪዎች አንዱ የነነዌን ታሪክ ቢጽፈው የሚጽፈው እንዲህ ነበር ፡፡
የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ናቸው ዮናስ ደግሞ እነርሱ የማያውቁትን አምላክ የሚያመልክ ነቢይ ነው ዮናስ ወደ እነርሱ የመጣው የማዳን ተልዕኮ ይዞ አልነበረም ፡፡
ወደ አሕዛብ መላኩ አላስደሰተውም ዮናስ ወደ ነነዌ የመጣው እንደ ሌላ ሰባኪ በየትኛውም ትራንስፖርት ተጉዞ ሳይሆን በዓሣ አንበሪ ወደ ነነዌ ተተፍቶ ነው ፡፡
የተተፋ ሰባኪ እንዴት ደስ ብሎት ይሰብካል ? እንኳን ስብከት ይቅርና ማንኛውም ሥራ ያለ ፍላጎት እንዴት ሊሳካ ይችላል ? ዮናስ የነነዌ ሕዝብ እንዲድን ፍላጎትም አልነበረውም እንዲያውም ከመጀመሪያውም ፍርሃቱ ‹ ትጠፋላችሁ › ብሎ ተናግሮ ሳይጠፉ ቢቀሩስ የሚል ነበር ፡፡
ዮናስ ወደ ከተማይቱ ዘልቆ ሲገባም በፍላጎት አልሰበከም ፤ የሰበከው ስብከት ተስፋ የሚያስቆርጥ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ነበር የነነዌ ሰዎች የማያውቁትን አምላክ እንዲያውቁ ዕድል የሚሰጥ ትምህርት አልተሠጣቸውም ፡፡
ዮናስም እንደ ኖኅ ‹ ይኼንን ያህል ዘመን ተሠጥቷችኋል ተመለሱ › ብሎ አልሰበከም መርከብ ሠርቶ ግቡም አላላቸውም በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች › ብሎ ጮኸ ፡፡
የነነዌ ሰዎች ግን ( ማን ነው የሚገለብጣት ? › ለምን ትገለበጣለች ? › ‹ ለመሆኑ አንተ ማን ነህ ? › ( ዝም ብሎ ትገለበጣላችሁ ይባላል ? መጀመሪያ ትምህርት አይቀድምም ? › አላሉም ፡፡
ራሳቸውን እንጂ ሰባኪውንና ስብከቱን ለመገምገም ጊዜ አልነበራቸውም፡ ‹‹ እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ ››
አንድ ላይ ኃጢአት መሥራት ቀላል ነው ፤ አንድ ላይ ንስሓ መግባት ግን ይከብዳል በሀገር ደረጃ ንስሓ መግባት ግን እጅግ ያስደንቃል የነነዌ ሀገር ህዝቦች ሀገር የምትገለበጥ ከሆነ ሀገር እንቀይር › አላሉም ፤ ራሳቸውን መቀየር እንደሚሻል ተረድተው ነበር ሁሉም እኩል ልቡ ተሰበረ ፤ ሁሉም ማቅ ለበሰ ፡፡
የሰባኪው ስብከት ጣዕም የለውም ብለው አላማረሩም ፣ ‹ ተስፋ የሚሠጥ ስብከት መቼ ሰማን › አላሉም ሰባኪው እያዋዛ አላስተማራቸውም ፣ ምሳሌ አልነገራቸውም ፣ ቅኔ አልተቀኘላቸውም
ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ‹‹ የተላከላቸው ጨካኝ ሐኪም ነበር የያዘው መድኃኒትም የሚያቃጥል ነበር ፤ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ቃል ተናገራቸው ፤ እነርሱ ግን አቁስሏቸው ተፈወሱ ›› የነነዌ ሰዎች ንስሓ ከላይ እስከታች ነበር ነገሥታቱ ሳይቀር ማቅ ለበሱ ‹‹ ነነዌ ትገለበጣለች ›› ብሎ ሲናገር ንጉሡ ወታደሮች ልኮ ዮናስን ማሰር ይችል ነበር ፡፡ ‹‹ ምን በሀገራችን ላይ ታሟርታለህ ? ›› ብለው_አፉን አላፈኑትም ።
መፍትሔውን ንገረን ያለውም የለም ችግሩ እነርሱ ናቸውና መፍትሔውንም ያውቁታል ስለዚህ ራሳቸውን መውቀስ ወደዱ ሀገሪቱ በአንድ ልብ አለቀሰች።
ንጉሡ ፡- ሰዎችና እንስሶች አንዳች አይቅመሱ ! ብሎ አዋጅ አስነገረ ከቤተ መንግሥት ጾም የሚታወጅባት ነነዌ እንዴት የታደለች ናት ? ‹‹ መኳንንቶችሽ ማልደው የሚበሉ አገር ሆይ ወዮልሽ ›› ተብሎ ከተጻፈ መኳንንቶችዋ የሚጾሙላት ሀገር እንዴት የታደለች ትሆን ? ( መክ . 10 ፡ 16 )
መቼም ሕዝብ ብቻ መጾሙ ነገሥታት ቢበሉ የተለመደ ነው ነገር ግን እየበሉ የሚጾምን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል ? ሲጠጡ እያደሩስ ሲጸልይ የሚያድርን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል ?
ንጉሥሽ ላንቺ ማቅ ለብሶ ያለቀሰልሽ ፣ እንስሳት ሳይቀር የጾሙልሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ ? ሕዝብሽ ጾም ሲታወጅ የማያላግጡ ፣ ‹ እኔ በፈለግሁበት ጊዜ ነው የምጾመው › ብለው የማይመጻደቁ ፣ እንኳን ከቤተ ክህነት ይቅርና ከቤተ መንግሥት የታወጀን ጾም በትሕትና የሚጾሙብሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ ? የዋሐን ሕጻናትን ጡት ከልክለው የፈጣሪን ርኅሩኅ ልብ የሚያስጨንቁ ፣ እንስሳትን ከውኃ ከልክለው ለምህላ የታጠቁ የነነዌ ሰዎች ምንኛ ድንቅ ናቸው ፡፡
ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የቤተ መንግሥቱን ሁኔታ እንዲህ ይሥለዋል ፡፡
‹‹ የነነዌ ንጉሥ ወታደሮቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸውም ፡- ይህ ድል እንደተጎናጸፍንባቸው ውጊያዎቻችን አይደለም ፤ ከባዕድ ሀገር በተሰማው ዜና ኃያላኖቻችን ሳይቀሩ ተብረክርከዋል ፤ አንድ ዕብራዊ መጥቶ በቃሉ አብረከረከን የጀግኖች እናት ነነዌ አንድን ለብቻው የመጣ ደካማ ሰው ቃል ፈርታለች ፡፡ስለዚህ ወገኖቼ ፤ የማይፈርስ አጥር እንገንባ ፤ ይህች አጥር ንስሓ ናት ፤ ሥውር ጦርነት ታውጆብናልና ራሳችንን ሥውር መሣሪያ እናድርግ !! ››
ዮናስ በነነዌ መመለስ ደስ አልተሰኘም ትንቢቱ ስለማይፈጸምለት ብቻ አይደለም ‹‹ የእስራኤል ሽማግሌዎች በሚቀማጠሉባት ሰዓት የነነዌ ሽማግሌዎች ሲያለቅሱ አየ ።
ጽዮን በዝሙት እንደ ሰም ስትቀልጥ ነነዌ ታነባ ነበር ›› እስራኤል ከፈጣሪ በራቁበት ሰዓት አሕዛብ የንስሓ ዕንባ ሲታጠቡ ሲያይ ክብር ከእስራኤል መልቀቁን አይቶ ተከፋ ፡፡
ዮናስ እስከመጨረሻው ሰዓት የነነዌን መጥፋት ይጠባበቅ ነበር ዮናስ ነነዌ የምትገለበጥበትን ቀን ሲቆጥር ነነዌ ደግሞ ኃጢአትዋን ትቆጥር ነበር ፡፡
ዮናስ ስለ ነነዌ እንደ ሙሴ ‹ እነርሱን ከምታጠፋ እኔን አጥፋኝ › አላለም ፤ በተቃራኒው ‹ እነርሱን ካላጠፋህ እኔን አጥፋኝ › እስከማለት ደረሰ በእርግጥም ዮናስ በሽተኛ አክሞ ስለዳነለት የሚበሳጭ ሐኪም ሆነ ፡፡
የነነዌ ሰዎች ግን የሰባኪው ማንነት ፣ የስብከቱ ውበት አልባነት ፣ የአነጋገሩ ለዛ ምክንያት ሳይሆናቸው ተስፋ በማይሰጥ ስብከት ተሰብረው ራሳቸውን አዳኑ ፡፡
ብዙ ስብከት አልፈለጉም ፤ ክፋትን ለመተው እ.ና ይቅር በለን ለማለት የተሰበረ ልብ እንጂ በእውቀት መሞላት አያስፈልግም የኛ ኃጢአታችን ደግሞ ከነነዌ ሰዎች ከበለጠ ቆየ የጋራ ክፋታችንን በጋራ ንስሓ እንጠበው።
📖 የኤፍራጥስ ወንዝ መጽሐፍ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ጾመ ነነዌን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት "የዛሬዋ ነነዌ ኢትዮጵያ መሪዎች ልብ ገዝተው ወይም ራሳቸው ማቅ እስከለብሱና እስኪመለሱ ወይም ደንዳና ልባቸው ጎርፍ ሆኖ እንደ ፈርዖንና እንደ ሔሮድስ እንዲሁም ዲዮቅልጥያኖስ ይዟቸው እስኪሔድ ድረስ ተጋድሏችን ይቀጥላል። ተጋድሏችን ከሥጋና ከደም ጋር አይደለም።" ብለዋል።
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
Audio
✝ሰማንያ አራት ዓመት✝
ሉቃ 2÷37
Size:-29.4MB
Length:-2:08:31
አዲስ አበባ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ የካቲት 8/2014ዓ.ም የተሰጠ
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
ሉቃ 2÷37
Size:-29.4MB
Length:-2:08:31
አዲስ አበባ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ የካቲት 8/2014ዓ.ም የተሰጠ
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
📡 በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
ይ🀄️ላ🀄️ሉ
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
🔑 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘማሪዎች ውስጥ የማንን ዝማሬ ማግኘት ይፈልጋሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔴የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
⚫️የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
ዝ?የቀዳሜጸጋ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🔴የኪነጥበብ መዝሙር
⚫️የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🔴የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ እና ወ.ዘ.ተ......
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
ይ🀄️ላ🀄️ሉ
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
🛑እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን🛑
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲ █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

Forwarded from Now Button Bot
💰ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ❓
አዋ ከሆነ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
👇👇
አዋ ከሆነ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
👇👇