Telegram Web
لا تنسوا وِردَ الصلاة على الحبيب بعد عصر الجمعة
(اللهم صلِّ على محمد عبدِك
و نبيِّك و رسولِك النّبيِّ الأمّيِّ)
80 مرة . ثم تختم بالسلام عليه



#መልካሙን_ነቢይ❤️_በሕልም_ለማየት_ፍቱን_መሳሪያ!
"اللَّهُمَّ صَلِّ علَى مُحمَّدٍ النَّبِيِّ، وَأزواجِهِ أُمَّهاتِ المُؤمنينَ، وذُرِّيَّتِهِ وأهلِ بَيتِهِ، كما صَلَّيتَ علَى ءَالِ إبراهِيمَ، إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ" (100 مرّة).
هذه الصّيغة مجرّبةٌ لرؤيةِ الرّسولِ الأعظمِ صلّى اللهُ عليهِ وسلّمَ في المنامِ، نقولُها ُخلِصينَ_النِّيّةَ_للهِ_تعالَى_في الليلِ أو في أيّ ساعةٍ مِن النَّهارِ مائِةَ مرّةٍ على حسبِ النّشاط.
ከላይ ተጠቀሰዉ ሶለዋት ማለት ረሱላችን ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላምን #በመናም( #በሕልም)ለማየት የተጀረበና ዉጤታማነቱ የተረጋገጠ ነዉ፡፡ኒያችንን ለአሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ብለን በማጥራት ሌሊት ላይ ወይም በማንኛዉም ሰዓት ቀን ላይ በነሻጣ 100 ጊዜ በማለት የምንናፍቃቸዉን ዉድ #ነቢይ❤️ በዉስጣችን እያሰብን እንበለዉ

https://www.tgoop.com/joinchat-YGFauLVOp5hiODI8
📌ክፍል 1
የዒልሙ ባህር #ኢማም_አን_ነወዊይ

ሠዎች እነሡን ሸይኽ፥ዒማም፥ዐለም፥ዓላመህ፥ፈቂህ፥ዓቢድ፥ዛሂድ ብለው ይገልፆዋቸዋል!!(ይህ ሁሉ የሲፋ/ፀባይ/ መጠሪያ ግን ሲያንስባቸው ነው እንጂ መቼም አይመጥናቸውም) ሙሉ ስማቸው አቢ ዘከርያ ሙህዪዲን የህያ ብኑ ሸረፍ ቢን ሙሪ ቢን ሀሠን ቢን ሁሠይን ቢን ሙሀመድ ቢን ጁሙዓህ ቢን ሂዛም አል-ሂዛሚይ አን-ነወዊይ አድ-ዲሚሽቂይ ይባላል። በነገራችን ላይ #ሙህዪዲን የተባለው ስማቸው ቅፅል ነው። አሏህ በሳቸው ሠበብ ዲንን ህያው አድርጓልና ሠዎች 'ዲንን ህያው ያደረገ' ብለው ሠየሟቸው። ደግሞ #አቢ_ዘከርያ ያሏቸው ዘከርያ የሚባል ልጅ ስላላቸው ሳይሆን በዛ ግዜ ትልልቅ ዑለማዎችን ልጅ ባይኖራቸው እንኳን የአንድ ሠው አባት እንደሆኑ አድርገው ቅፅል ስም ይሰጧቸው ነበር። (እንጂማ ኢማሙ ነወዊይ መች ልጅ ወለዱ?!! እረ እንደድም ጭራሽ አላገቡም!! ) . አብዛህኛው ሠው ሚያውቃቸው ለቀብ(ቅፅል ስም) ደግሞ #ነወዊይ በሚለው ነው። ይህም በተወለዱበት መንደር ስም የተሠየመ ነው።(ልክ ለምሳሌ የሳሪስ ልጅ ከሆንክ አስ-ሳሪሲይ እንደምትባለው ማለት ነው😊)

የተወለዱት በወርሀ #ሙሀረም በ 631 ሒጅሪ አቆጣጠር ፥ ነዋ በምትባል የሻም መንደር ውስጥ ነው።(ነበር እያልኩ ማላወራው ሁሌም ህያው ስለሆኑና አሁንም ድረስ አብረውን ስላሉ ነው። አሏህስ 'ሞቱ ብለህ አታስብ' አይደል ያለው) እናም ወላጆቻቸው በእስልምና ስነ-ስርአት ኮትኩተውና አንፀው በአደብ በተዝኪያ እንዲያድጉ አረጓቸው። የአሏህንም መፅሀፍ ቁርአንን ገና በጨቅላ እድሜያቸው እንዲያነቡ አደረጓቸው።

ክፍል 2 ይቀጥላል....

https://www.tgoop.com/joinchat-YGFauLVOp5hiODI8
💚 የዱንያ ማማር
ከአላህ ጋር ባለ ግንኙነት ነውና
⇘ ዱንያህ እንድታምር ከፈለግክ
አንተ እንደምትፈልገው ሳይሆን
አላህዬ እንደሚፈልገው አድርጋት ።

                       https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
💚 ጭንቀትህ ሁሉ የአላህን ውዴታ
ማግኘት ሆኖ መኖር በጣም ደስ ይላል
⇘ ልብህ በአላህ ፍቅር እየመታ
ምላስህ አላህን ማውሳት ሲያዘወትር
ዱንያ ውስጥ ሆነህ ሌላ ዓለም ውስጥ
እንዳለህ ይሰማሃል ።

                       https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
💚 አዛንን ብዙ ጊዜ ችላ ብለህ ፣
ቁርአንን ርቀህ ፣ ብዙ ወንጀል ላይ
ወድቀህም እስካሁን እየተነፈስክ ነው
አላህዬ እዝነቱን አልነፈገህምና እባክህን
ወደ አላህ ተመለስ ።

                       https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
💜 ነፍስህ ቁርአን መሀፈዝ
በጣም ከባድ ነው አትችልም ስትልህ
እንዲህ ብላህ ቅራላት...

(وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِنْ مُدَّكِرٍ)
" ቁርአንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው
ተገንዛቢም አለን? "
[አል ቀመር 17]

ነፍስህ ባክህ ጊዜ የለህም ተወው ስትልህ
እንዲህ ብለህ ቅራላት...

( يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُلْهِكُمْ أَمْوَالُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ عَنْ ذِكْرِ اللَّهِ ۚ وَمَنْ يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ)
" እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ
አላህን ከማስታወስ አያታሉዋችሁ ፡፡
ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ
እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው ፡፡"
[አል ሙናፊቁን 9]

ነፍስህ ተኛ ብላ ስትጎተጉትህ
እንዲህ ብለህ ቅራላት...

( كَانُوا قَلِيلًا مِنَ اللَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ)
" ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ ፡፡"
[አዛሪያት 17]

๏ ትልቁ ጂሃድ ማለት
ከነፍስህ ጋር የምታደርገው ትግል ነው
ነፍስ በመጥፎ ነገር አዛዥ ናት
እንቢ ብለህ ካሸነፍካት
ትርፋማና ደስተኛ ትሆናለህ
ካሸነፈችህ ደግሞ ትከስራለህ
ከእድለቢሶችም ትሆናለህ ።
አላህ ይጠብቀን
https://www.tgoop.com/joinchat-TcSd56N1aJTYW5oA
💜 ‏﴿إِنَّ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانَ يَهْدِى لِلَّتِى هِىَ أَقْوَمُ﴾

"ይህ ቁርአን ወደዚያች
እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው
መንገድ ይመራል፡፡"

⇨ መስተካከልን የፈለገ
መመራትን የፈለገ
ህይወቱን ማሳመር የፈለገ
በመቅራት, በማስተንተንና
በመተግበር ከቁርአን ጋር ይኑር ።
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAE3Enec6U7Z6_8_TtQ
🍃 #ሱረቱ አል-ፋቲሀ..........የአላህን ቁጣ
ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ ያሲን .........ከቂያማ ቀን ጥማት
ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ አል-ዱኻን..........ከቂያማ ቀን ጭንቀት
ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ አል-ሙልክ..........ከቀብር ቅጣት
ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ አል-ካፊሩን..........በሞት ሰአት ከኩፍር
ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ አል ኢኽላስ..........ከኒፋቅነት
ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ አል-ፈለቅ..........ከምቀኝነት
ትከላከላለች::

⭐️ #አንድ #አይሁዳዊ ሙስሊሞችን ፊትና ውስጥ
ለማስገባት ይፈልግና ወደ ሙስሊሞች ሀገር ጉዞ
ይጀመራል፡፡ ልክ እንደደረሰም የከተማይቷ ጫፍ
ላይ አንድ እረኛ ወጣት ያገኛል አስ እስኪ ፈተናውን
#ከሱ ልጀምር ይላል ከብዙ ጫወታዎች በውሀላ

#ሙስሊም በመምሰል ጥያቄውን ይሰነዝርበታል:-

#አይሁዳዊው:-ይህ ቁርአን ግን የበዛ
አይመስልህም ለምን ግን ተመሳሳይ ተመሳሳይ
የሆኑትን ቦታዎች አጥፍተን ከ30 ጁዝ
አንቀንሰውም እንደገና 30 ጁዝ መሀፈዙ ራሱ
ይከብዳል...

#እረኛው #ወጣት :-አዎ ልክ ነህ ግን አንድ ጥያቄ
ልጠይቅህ ቁርአን ውስጥ እየተደጋገሙ
የሚመጡትን ከማጥፋታችን በፊት ከሰውነትህ
ውስጥ ተደጋጋሚ የሆኑትን አናጠፋም!! #ለምሳሌ
☞ከአይኖችህ ውስጥ አንዱን
☞ከጆሮዎችህ ወስጥም
አንዱን
☞ከእግሮችህ ውስጥም አንዱን......

#አይሁዳዊውም በጣም ይደናገጥና እንዲህ
ይላል:-
#እረኛዎቻቸው አንዲህ ከሆኑ ኡለማኦቻቸው ምን
ያህል ጠንካሮች ናቸው ሲል ይደነቃል ...
ወድያውም ከተማዋን ለቆ ይወጣል::
Like እና ሼር ያድርጉ!


══ •⊰✿💚✿⊱• ══

🎖SHARE🎖
Join👇👇
https://www.tgoop.com/joinchat-TcSd56N1aJTYW5oA
💜 ጀሀነምን ማየቱ ብቻ
ተመልሰህ በአላህ አምነህ ተቀብለህ
ጥሩ ጥሩ ነገር ለመስራት እንድትመኝ
ታደርግሃለች…
๏ ገብቶ በውስጧ መቀጣቱስ
እንዴት ቢሆን ነው በአላህ? !!!

﴿وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ وُقِفُوا عَلَى النَّارِ فَقَالُوا يَا لَيْتَنَا نُرَدُّ وَلَا نُكَذِّبَ بِآيَاتِ رَبِّنَا وَنَكُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَُّ﴾
" በእሳትም ላይ በተቆሙ ጊዜ
ምነው (ወደ ምድረ ዓለም) በተመለስን
በጌታችንም አንቀጾች ባላስተባበልን
ከምእምናንም በሆንን ዋ ምኞታችን !!!
ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያሰደነግጥን ነገር ባየህ ነበር) ፡፡"
[አንዓም 27]

እድሉ ተበላሽቶ የሞተው
ምነው በተመለስኩ ጥሩ በሰራሁ
ብሎ ሲመኝና ሲፀፀት
๏ አንተ በህይወት እስካለህ
ጥሩ ጥሩ እየሰራህ የአላህን እዝነትና
ጀነትን እየተመኘህ እደለኛ ሁን ።
https://www.tgoop.com/joinchat-TcSd56N1aJTYW5oA
💜 ብዙ አይነት መፅሀፍቶች
ብዙ አይነት ስህተት በርግጠኝነት
ይኖራቸዋል በየጊዜም ይቀያየራሉ
๏ ቁርአን ግን ምንም አይነት
ስህተትም ሆነ መቀያየር የሌለበት
ብቻኛው የአላህ ንግግር ነው
๏ የዛሬ 1400 አመት እራሱ ነበር
እስካሁንም ወደፊትም እራሱ ነው

 ذَٰلِكَ الْكِتَابُ لَا رَيْبَ ۛ فِيهِ ۛ هُدًى لِلْمُتَّقِينَ
" ይህ መጽሐፍ (ከአላህ ለመሆኑ) ጥርጥር
የለበትም ለፈራህያን መሪ ነው ፡፡"
[በቀራህ 2]

አላህን መፍራትን
ሶስት ቦታዎች ላይ ፈልግ
① በቀልብህ ውስጥ
 الَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِالْغَيْبِ
" ለነዚያ በሩቁ ነገር የሚያምኑ"
[በቀራህ 3]

② በሰውነትህ ውስጥ

وَيُقِيمُونَ الصَّلَاةَ
" ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ"
[በቀራህ 3]

③ በብርህ ውስጥ
وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنْفِقُونَ
" ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚቸሩ ለሆኑት "
[በቀራህ 3]
https://www.tgoop.com/joinchat-TcSd56N1aJTYW5oA
💜 የቁርአን ህግጋትን መከተልና መተግበር
◉ ለነፍስ ተቅዋን ይጨምራል
◉ ለአእምሮ ደግሞ ጥበብን ይሰጣል
 
(قُلْ تَعَالَوْا أَتْلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمْ عَلَيْكُمْ ۖ أَلَّا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا ۖ وَلَا تَقْتُلُوا أَوْلَادَكُمْ مِنْ إِمْلَاقٍ ۖ نَحْنُ نَرْزُقُكُمْ وَإِيَّاهُمْ ۖ وَلَا تَقْرَبُوا الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ ۖ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُمْ بِهِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
« ኑ‥ ጌታችሁ በእናንተ ላይ እርም ያደርገውን ነገር
(በእርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ» በላቸው
«በእርሱ (በአላህ) ምንንም ነገር አታጋሩ
ለወላጆችም በጎን ሥራ (ሥሩ)
ልጆቻችሁንም ከድህነት (ፍራቻ) አትግደሉ
እኛ እናንተንም እነርሱንም እንመግባችኋለንና
መጥፎ ሥራዎችንም ከእርሷ የተገለጸውንም
የተደበቀውንም ሁሉ አትቅረቡ
ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ
በሕግ ቢሆን እንጂ አትግደሉ
ይህን ታውቁ ዘንድ (አላህ) በእርሱ አዘዛችሁ ፡፡»
[አንዓም 151]

ጭንቅላትህ ውስጥ ቁርአን መኖሩ ሳይሆን
ስነምግባርህ ውስጥና ተግባርህ ውስጥ
አንድ አንቀፅም ብትሆን መኖሩ ነው ዋናው ።
https://www.tgoop.com/joinchat-TcSd56N1aJTYW5oA
💜 የአላህ ፍቅር ውስጥህ ሲኖር
ብርሃኑ ልብህን ያበራና ጀሰድህን
#ለፈጅር ሰላት ይቀሰቅስሃል ።

ፍቅሩን ይስጠን
💜 ልብህ ፈገግ የምትልበት
ቦታ ላይ ብቻ ቆይ ።

መልካም ቀን
💜 #ፈጅር ሰላት
አለፈህ ማለት የቀን ውሎህ
ደስታ እና በረካ አለፈህ
ማለት ነው ።
💜 ምናልባት በበደል የፈለግከውን
ነገር ልታገኝ ትችል ይሆናል‥ ነገር ግን
ከተበዳይ በመጣች አንዲት ዱዓ ምክኒያት
ሁሉን ነገር ታጣለህ ።
💜 ነቢዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) መድየን ከደረሰ በኋላ ቤት ፣ ስራም ሆነ ሚስት አልነበረውም ። መልካም ነገርን ሰራና ከዛም ወደ ጥላው ዘወር ብሎ እጁን ወደ ሰማይ አነሳና " ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ ።" አለ ።
በዚያኑ ቀን ፀሐይዋ ሳትጠልቅ ቤት ፣ ስራም ሚስትም አላህ ረዘቀው ።

መልካም ነገር ከሰራችሁ በኋላ እስቲ ይህን ዱዓ ሞክሩት‥
💜 ከአኺራው ጀነት በፊት
በዱንያው ጀነት ውስጥ እራስህን
ማግኘት ከፈለግክ #ፈጅርን በጀማዓ
ስገድ ።
2025/02/11 11:40:23
Back to Top
HTML Embed Code: