Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
#ከልደት_በፊት_ተወለዱ
#ከጥምቀት_በፊት_ተጠመቁ
#new_challenge
ኦርቶዶክስ መሆን/መማርና መጠመቅ የምትፈልጉ በውስጥ አናግሩን። ወይም መማርና መጠመቅ የሚፈልግ ሰው ካወቁ ያሳውቁን/ያገናኙን።

#ከልደት_በፊት_ተወለዱ
#ከጥምቀት_በፊት_ተጠመቁ
#newchallenge
"ሃይማኖት አያድንም" የሚል ሰው ካጋጠማችሁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀት የሌለው መሆኑን እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ።
#ልዩ_ስጦታ
ሰብአ ሰገል በቤተልሔም ለተወለደው ንጉሥ ስጦታ ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤን አቀረቡ።
እኛስ ለአምላካችን የምንሰጠው ስጦታ ምንድነው? እርሱስ ከእኛ የሚፈልገው ስጦታ ምንድነው?
አንድ ነገር እንድንሰጠው ይፈልጋል። እርሱም፦ልባችንን ነው።
"ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ" (ምሳሌ ፳፫፥፳፮)
ከኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ውጪ ያላችሁ ወንድሞቻችን በአካል ብትርቁንም፣ አፋችሁ እውነቱን ባይመሰክርም ልባችሁ ሁሌም ከእኛ ጋር መሆኑን አረጋግጠናል።🙏
#ሰፋኒት_ሚዲያ
"የአማልክት አምላክ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ አንተ/ኢየሱስ ነህ" እያልክ ጸልይ ብላ ቤተክርስቲያን አስተምራህ ሳለ "ቤተክርስቲያን ኢየሱስ አታውቀውም" ከማለት በላይ ውሸትና ክህደት ከየት ይገኛል?🤔
ወዳጄ አንተ ነህ ቤተክርስቲያንን የማታውቃት!🙏

#ሰፋኒት_ሚዲያ
#Sefanit_Media
በቅርቡ ተደራራቢ የምሥራች አለኝ።🙏
በተለይ የሁለቱን ሰዎች በቪዲዮ ይዤላችሁ ብመጣ ደስ ይለኝ ነበር።...
የነበረበትን ሕይወትና ፈተና የተደረገለትንም ድንቅ ተአምር በዕንባ ያጫወትኝ ሰው...።
#ስለራሱ_ያጫወተኝን_በአጭሩ
👉 በሃይማኖቴ ሚስት አግብቼ እኖር ነበር። አጋጣሚ የባለቤቴ እግር ድንገት መንቀሳቀስ አቆመ። ማሳከሚያ ብርም ሆነ የሚያግዘኝ ዘመድ በአካባቢው አልነበረኝም። በአቅራቢያዬ የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ነበር። ባለቤቴ በራሷ መሄድ ስለማትችል ባለችኝ አህያዬ በጧት ወደ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ወሰድኳት። ከልቤ አልቅሼ "ቅዱስ ገብርኤል እርዳኝ ምን ላድርጋት እችላለሁ! ምንም እንደሌለኝ ታውቃለህ።" ብዬ ጸበል ገብታ ስትወጣ ዳነችልኝ። በአህያ የወሰድኳት ባለቤቴ በእግሯ ተመለሰች። "ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም፤ ቅዱስ ገብርኤል ረዳኝ፤ በጭንቅ ደረሰልኝ።" ብሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሱ።

ከጊዜያት በኋላ ሃይማኖቷን ትታ ያ የተደረገላትን ድንቅ ተአምር ረስታ ባለቤቴ የጴ*ጤ ቸርች መሄድ ጀመረች። እኔም ለትዳሬ ስል ሳላውቅ እሷን ተከትዬ መግባት ጀመርኩ። ልቤ ግን ቤተክርስቲያኔ/ሃይማኖቴ ላይ ነበር።

👉በቤተክርስቲያን አካባቢ ሳልፍ ዕንባዬ ይቀድመኛል። አንዳንድ ጊዜም መንገድ ቀይሬ እሄድ ነበር። እንደዚህ እየሆንኩ ለ11 ዓመታት ቆይቻለሁ። እንቅልፌን እንኳን ተኝቼ ማደር የጀመርኩት በቀደም ቤተክርስቲያን ግቢ የገባሁ ቀን ነበር።
👉በፕሮ**ታንት ባይፈቀድም ዓርብና ረቡዕን ማንም ሳያውቅ በግሌ እጾም ነበር። በዙሪያዬ ያሉት ሁሉ እንድበላና እንድጠጣ ይጋብዙኝ ነበር። ቃል አውጥቼ ባልነግራቸውም ልቤ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳሰበ ያወቁብኝ ይመስለኛል።
👉ፓስተሩ ሲያስተምር ሲዘምሩ፣ ሲያጨበጭቡ ሐሳቤ ሁሉ ቤተክርስቲያን ነበረች። ፓስተሩ ቀርቦ "ለምን አሜን! አትልም፣ ምን ሆነህ ነው? የቸገረህ ወይም የሚያሳስብህ ጉዳይ ያለ ይመስላል" ሲለኝ "ደህና ነኝ ነበር ለዚህኛው ቸርች አዲስ/እንግዳ ስለሆንኩ ነው" ነበር የምለው።" በማለት የንስሐ ዕንባ እያነባ ያጫወተኝና ለተከታታይ ቀናት አብረን ያሳለፍነው ሰው ዛሬ በይፋ ተመልሶ የሚወዳትና ሁሌም ከልቡ ካለችው ቤተክርስቲያን ኅብረት ተቀላቅሎ የደስታ ዕንባ አነባ!
ከ40 ዓመታት በላይ በፕሮ*ስታንት "ኅብረት" ነበር። "ወደ ቤተክርስቲያኔ ተመልሼ ነገ ብሞት አይቆጨኝም፤ ብቻ አንዴ ማኅተቤን እሠሩልኝ፤ የሚገባውንም ሁሉ አድርጉልኝ ውስጤ የሚያርፈው ያኔ ነው።" ያለኝ ቃል መቼም ከልቤ አይጠፋም።

"ቅዱስ ገብርኤልን'ማ እንዴት 'ረሳዋለሁ" እያለ መልአኩን ሲያነሳ ዕንባው የሚቀድመው ይሄው ዛሬ በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በይፋ ተመልሰ።

ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን!🙏

ሁኔታዎችን ሲጠብቁ፤ በትዳርና በአንዳንድ ጉዳዮች ተጠምደው የስንቶች ልብ ቤተክርስቲያንን እንደናፈቀ ቤቱ ይቁጠረው።
እባክዎ መማርና መጠመቅ/ ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ ከፈለጉና የሚፈልግ ሰው ካጋጠመዎት በውስጥ ያናግሩኝ።🙏
በውስግ ስለምታናግሩን ከወዲሁ እናመሰግናለን!🙏
@Sefanit_Media
~~~~
በሃይማኖታችን ጸንተን በመንፈሳዊ ሕይወታችን እንበርታ!
Let us stand firm in our faith and be strong in our spiritual life.
በሃይማኖታችን ጸንተን በመንፈሳዊ ሕይወታችን እንበርታ!
Let us stand firm in our faith and be strong in our spiritual life.
@Sefanit_Media
"የሕይወትን ዋጋ እንድትገነዘቡና በከንቱ አኗኗር እንዳታባክኑት ስለ እናንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ደም አስታውሱ።"
(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ)
@Sefanit_Media
እስኪ በድሎኛል ያሉትን ሰው ያስታውሱ። ያ ሰው "ሞተ" ቢባሉ ምን ይሰማዎታል? ደስታ ወይስ ጸጸት?

ግዴለም ሁላችንም ድንገት ሟቾች መሆናችንን እናስብና ሞት ሳይቀድመን ይቅር እንባባል!
የይቅርታ ልብ ይስጠን!🙏

@Sefanit_Media
#አትጨነቅ
ሰዎች አልተረዱኝም፤ ክፉ አደረጉብኝም ብለህ አትጨነቅ።
ለሰው ሁሉ መልካም ሁን።
ማድረግ ያለብህን ብቻ አድርግ።
መሆን ያለብህን ሁን።
በራስህ የሕይወት መስመር ብቻ ሩጥ።
ሁሉም በጊዜው ይገለጣል። ያኔ ያልተረዱህ በራሳቸው ያፍራሉ።

@Sefanit_Media
አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ከቃላት በላይ ነው።

የሆንከውን፣ የተሰማህን፣ ያስጨነቀህን፣ ያስደሰተህን፣ ያሳሰበህን...ነገር ሁሉ መናገር አድካሚ ነው።
ሆኖም ግን ሁሉም ነገር ካለፈልህና ካለፈብህ በኋላ ቢሆንም ሁሉም ሰው ያውቅልሃል፤ ይረ'ዳሃልም።
ዝምታህ ራስህን የምታደምጥበትና ከራስህ ጋር የምትሆንበት ሲሆን ደስ ይላል።

@Sefanit_Media
"Your mouth is the number one enemy of your life, if you want to live long, shut it up, and be wise." 🤐
"ረጅም ዕድሜ መኖር ከፈለክ አፍህ የሕይወትህ ጠላት ነው። ዝምታን መርጠክ  ጥበበኛ ሁን።"
@Sefanit_Media
አንዱ ፕሮቴስታንት "አምላከ ገብርኤል" ሲባል ሰምቶ "ገብርኤልን አምላክ ነው ትላላችሁ" አለኝ።...

ወንድሞቻችን ምናልባት አንድ ቀን አለማወቃችሁን ስታረጋግጡ በራሳችሁ ታፍራላችሁና ተረጋጉ።🙏

Join 👉 @Sefanit_Media
2025/03/04 07:41:41
Back to Top
HTML Embed Code: