😊ዘመን አመጣሹ ዘረኝነትን እናወግዛለን በሚሉ አራዳ ነን ባዮች እየተፈጠረ ያለዉ ፅንፈኝነት ደግሞ በሰፈርና በከተማ መለያየት ሆኗል
አንዱ EBS ላይ አቤት የእንትን ሰፈር ልጆች ብሎ ፕሮግራም ይሰራል
አንዱ EBC ላይ የእንትን አከባቢ ልጆች ዘረኝነትን አያዉቁምኮ እያለ ይቀደዳል
አንዱ ፋና ላይ “ኧረ እኛጋ ይሄ የለም” እያለ ራሱን ከሰዉነት (ሰዉ ከመሆን) አዉርዶ በመንደር ይፎካከራል። ይከራከራል። እንግዲህ አዲሱ ጠባብነት ይሄ ነዉ።
በአጭሩ ብስለትንና ክፉን መቃወምን ከሰዉነት(ሰዉ ከመሆን) አዉርደህ በሌላ ነገር የገለፅከዉ ቀን ችግር አለ ማለት ነዉ። ደግሞ በሰፈር በመንደር እየተፎካከርክና እየፎከርክ እኛኮ እያልክ የምታወራ ከሆንክ ያንተስ ልዩነት ምኑጋ ነዉ? አልሸሹም ዞር አሉ ይልሃል እንዲህ ነዉ። እያስተዋልን እንጓዝ!! ዘረኝነትና ፅንፈኝነት በሆኑ ክልሎች ብቻ ወይም በሆኑ ብሔሮች ብቻ ያለ ችግር አይደለም። ይቺ በቄላ ካደረች አትቆረጠምም እንዲሉ ዛሬ እርድና መስሎን ተንከባክበን የምናሳድጋት መንደርተኝነት ነገ ከሰዉነት አልፋና ጎልታ እንዳትታይ ሚድያዎቻችን ሊጠነቀቁ ይገባል።
@sewmehoneth

🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏
ያገባችሁ ወንድም እህቶቼ ይቺን ፅሑፍ አደራ ሳትሰለቹ አንብቡልኝ፤ ያላገባችሁም ቢሆን ለወደፊት ይጠቅማችኀልና አንብቡት፡፡
"ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው። የማትናደፍ ንብ ከፈለክ ከዝንብ ጋር ተጋባ"
✍በዲ/ን ዳንኤል ክብረት✍
ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው። ለማሩ ስንል ንድፊያውን መታገሥ፡፡ ቆይተህ ደግሞ ንድፊያውን መልመድ፡፡ገበሬ ቀፎ ሰቅሎ ንብ ሲያንብ፣ ንብ እንደምትናደፍ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም፡፡ የማትናደፍ ንብ ከፈለገ በየደጁ ቆሻሻ ፍለጋ የምትጓዘው ዝንብ ነበረችለት፡፡ ዝንብ ምን ጠባይዋ ሸጋ
ቢሆን፤ ጠብ የሚላት ግን ሌላ ነገር ነው፡፡ይህን ያውቃል ገበሬው፡፡ እያወቀም ንብ ያንባል፡፡ ማነብ ብቻ ሳይሆን ከንብ ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻልም ያውቃል፡፡ንብ ትናደፋለች፤ ግን እንዳትናደፍ ማድረግም ይችላል፡፡ የምትወደውና የማትወደው ሽታ አለ፡፡ ስትቀርብህ ምን ማድረግ እና ምን አለማድረግ እንዳለብህ ገበሬው ያውቃል፡፡
በሀገራችን ንብ አትገደልም፤ ነውር ነው፡፡ብትነድፍም አትገደልም፡፡ የንቧን ማር ለመውሰድም ንቧን ገድሎ፣ አጥፍቶ፣ ጎድቶ ወይም አሰቃይቶ ሳይሆን በጭስ ራሱን እየተከላከለ፣ ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ፣ ወደ ንቧ ቀፎ ገብቶ ነው ማሩን የሚቆርጠው፡፡ ንቧም ሳትጎዳ፣ ማሩም ሳይጠፋ፣ እርሷም ሳትናደፍ፡፡
ትዳርም እንዲህ ነው፡፡ አኗኗሩን ነው ማወቅ፤ የንቧን ንድፊያ የመቀነሻውን መንገድ ነው ማወቅ፣ የማሩን አቆራረጥ መንገድ ነው ማወቅ፡፡ ደግሞም‘ኮ አስገራሚው ገበሬው የሚከባከበው ይህቺኑ የምትናደፈውን ንብ መሆኑ ነው፡፡
የምትቀስመው አበባ ትፈልጋለች፣ ንጹሕ አካባቢ ትፈልጋለች፣ ከጉንዳንና ከአውሬ ነጻ የሆነ ቀፎ ትፈልጋለች፡፡ ግን ትናደፋለች፡፡ ደግሞም ማር ትሰጣለች፡፡ትዳር አስደሳች ነገር ብቻ ሳይሆን አስመራሪ፣ አስጠሊታ፣ ጨጓራ አንዳጅ፣ ልብ አቃጣይም ክፍል አለው፤ ይናደፋል፡፡ግን ደግሞ ክብካቤም ይፈልጋል፡፡ ንጹሕ ልብ፣ ታማኝ ኅሊና፣ ቻይ አንጀት፣ ታጋሽ ሆድ፣ ጠቢብ አእምሮ፣ አሳላፊ
ልቡና ይፈልጋል፡፡ ለምን ቢሉ? ማር ይሰጣልና ታገሱ.''
🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌
🔊SHARE AND JOIN

ችግሩ ከዘርፌ አይደለም ውስጣችን ካለው ጥላቻ እንጂ!!
(አሌክስ አብረሃም)
ዘፋኝ ፣ አመንዝራ፣ ከሃዲ፣ ከመጠጥና ጭፈራ ቤት ከመጣ ሰው ምን ይጠበቃል፣ ጸጋዋን የተገፈፈች፣ የሃሰት ነብይ ገረድ፣ ነጋዴ ፣ ጋለሞታ፣ ይድፋሽ ፣ መናለበሉኝ በቅርብ ታብዳለች፣ እዛው አንዱ ጲንጤ ጋር ተኝታ ይሆናል ፣ ቆሻሻ ፣ አሰዳቢ ፣የገሃነም ልጅ ፣ ወደጥልቁ ወረደች ወዘተ... ሰሞኑን ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ላይ ከሚወርዱባት ስድበና ዘለፋዎች በትቂቱ !! ይሄ ነገር እንደው እንዲሁ በሚተራመሰው በፖለቲካውም በእምነቱም ፌስቡክ ላይ ሲሰዳደብ በሚውለው ሰው ብቻ ቢሆን ባልከፋ ፣ ግን እንዴት የእግዜብሔርን ቃል አስተምራለሁ ከሚል የእምነት ሰው ፣ ሰለእኩልነትና ነጻነት እታገላለሁ ከሚል ጦማሪ እንዲህ አይነት ዘለፋ ይወጣል?
ለመሆኑገና መቸና መቸ ጣጥላው የመጣችው የዘርፌ ዘፋኝነት እንዴት ነው ዛሬ የታያችሁ ? እስቲ ዙሩና ተመልከቱ በአደባባይ አንቱ ከተባሉት ዘፋኞች ብዙዎቹ እምነታቸው ምንድነው? ለነሱስ ሲያጨበጭብ የሚውለው ማነው? ጌታ የተሰቀለበትን የሚያክል መስቀል ደረታቸው እና ጡታቸው ላይ እያነጠሩ በየቴሌቪዥናችን እስክስ ሲሉ የሚውሉ ጨፋሪዎቻችንን በየቤታችን በዓል ማድመቂያ ከማድረግ ባለፈ ደፍረን ተናግረናቸዋል እንዴ? ወይስ አይናችን ላይ ከተደቀኑት የኛው ሺ ከሚሊየን ዘፋኞችና ተወዛዋዦች ዘርፌ ድሮ ጣጥላው የመጣችው ዘፋኝነት ገዘፈብን?ዘፋኝነትን የምናወግዝ እኛው ነን? በቅርቡ አንድ ዘፈን አቁሞ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆነ ልጅ እንደገና ወደዘፈን ዓለም ተመለስኩ ማለቱን ተከትሎ <<እንኳን እግዜብሔር ረዳህ>> የሚል መዓት ኮሜንት አንብበናልኮ! ተሳስታለች ብለን ካሰብን ልጅቱን ማስተማር አንድ ነገር ነው ከዛ ያለፈ ዘመቻ ግን ችግሩ ከዘርፌ ሳይሆን ውስጣችን ካለው ጥላቻ መሆኑን የሚያሳይ ነው!
በቃ የኛ እምነት ካልሆነ ሌላው መታለል ፣ መጭበርበር ፣ ጅልነት ነው ? የፈለገችውን እምነት የመከትል ፣ በፈለገችው መንገድ ለማምለክ የማንም ፈቃድ አያስፈልጋትም! ከሷ አልፎ አንድን እምነት የዘፈን ቤት የጭፈራ ቤት እያሉ መዝሙሩን መዝለፍ ስርዓቱን ማንቋሸሽ አንድ መልስ ሲሰነዘር ግን አገር ይያዝ ማለት ጠብ አጫሪነት ነው! እውነቱን ለመናገር ሰዎች ከአንድ እምነት ወደሌላ ይሄዳሉ ይመጣሉ ምንም የሚገርም ነገር የለውም ! በተለይ የፕሮቴስታንት እምነት በሚሊየን የሚቆጠሩ አማኞች ከሌሎች እምነት የፈለሱበት እምነት መሆኑ ግልጽ ነው! ታዲያ ለምን ዘርፌ ላይ ኡኡታው በረታ? ታዋቂ ስለሆነች? ምናልባትም ተጽእኖዋ ከብዶ ሌሎችንም ወደእምነቱ ይዛ ልትሄድ ትችላለች ከሚል ፍርሃት? እንደዛ ከሆነ ትላንት እምነታቸውን የቀየሩትን በተመሳሳይ መንገድ ተሳድበን አሸማቀን ብዙ አይነት ስም ለጥፈን አልመለስናቸውም ! ነገም ማንንም በዚህ መንገድ ማስቆም አንችልም! ብቸኛው መንገድ በፍቅር እውነትን ማስተማር ብቻ ነው!
ይህን ማድረግ ካልቻን ግን ማንኛችንም የማንንም እምነት ወሳኝም አዛዥም አይደለንም ! የራሷን መንገድ መርጣ በምትፈልገው መንገድ የሄደች ሴት ላይ ከመረባረብ ሚሊየኖች ያውም የኛ የምንላቸው በየጫትና ሺሻ በየዘፈንና ዝሙት ቤቱ ታስረው ቁጭ ብለዋልና እነሱ ላይ ተረባርቦ መመለሱ ይቅደም!በተረፈ ዘማሪት ዘርፌ ያንን ብዙዎቻችን መውጣት አቅቶን አስር አይነት ስም እየሰጠን እና ርኩሰትን ቅድስና እያስመሰልን <<ተቻችለን>> የምንኖረውንና የምንዞረውን የዘፋኝነት የመጠጥ የርኩሰት ዓለም ትተሽ ወደመንፈሳዊው ዓለም መግባትሽና በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስታገለግይ በመዝሙሮችሽ በኩል ትውልድ ስታንጭ ለብዙዎች የፈጣሪን ማጽናናትንም ብርታትም ስታስተላልፊ መቆየትሽ ለብዙዎች ዓርያ የሚሆን ተግባር ነበር!
አሁንም ላመንሺበት ነገር የማህበረሰቡን ትችት ሳትፈሪ በግልጽ አቋምሽን ገልጸሽ በመረጥሽው የእምነት ተቋም መቀጠልሽ ከመንፈሳዊው ዓለም ባለፈ ሰለነጻነት ሰለግል ምርጫና መብት እሰብካለሁ ለሚለው በእንዲህ አይነት ወቅት ደግሞ ተገልብጦ የሰው እምነት ካልመረጥኩ ለሚለው <<የነጻነት ታጋይ>> ህያው የሆነ አስተማሪ ተግባር ነው! ባለሽበት ይመችሽ ! ኦርቶዶክስ ውስጥ ሁነሽ የዘመርሽው መዝሙር የእምነት ድንበር ተሻግሮ ፐሮቴስታንቱን እንዳስመለከ ዛሬም ፕሮቴስታንት ሁነሽ የምትዘምሪው መዝሙር ድንበር ሳያግደው እግዜብሔርን ለሚወዱ ሁሉ መጽናኛ እንደሚሆን እምነቴ ነው ! ምክንያቱም የምትዘምሪለት ጉዳይ ድንበር የማያግደው እውነት እንደሆነ አምናለሁና !!

When all African countries have victory day, Ethiopia 🇪🇹 has been celebrating Independent day for the past 123 years and we call it ❤️#Adwa ❤️ Happy victory day for all Ethiopian Members 🙌
#Ethiopia - The only uncolonized country in Africa 😍
#123_years_ago_today
@sewmehoneth
#Ethiopia - The only uncolonized country in Africa 😍
#123_years_ago_today
@sewmehoneth
#ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም(የኬንያ አጋጣሚያቸው)
"...ኬንያ ናይሮቢ አንዲት መዝናኛ ቤት ተገኝቼ እየተዝናናሁ ነው። ቤቱ እንደ ፓርቲ ቤት ያለ ነው። ባንዱ ጥግ መጠጤን ይዤ፣ የዳንሱ ወለል ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚደንሱ ወጣቶችን አያለሁ። በዚህ መሃል የባሕር ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ እንግሊዛዊያን ነጮች ገቡ። አንዱ እንግሊዛዊ ቀጥታ ወደ ዳንስ ወለሉ ሄደና ከወዳጁ ጋር እየደነሰ ያለውን ኬንያዊ በካልቾ መታው። ኬንያዊው ተርበድብዶ የሴት ወዳጁን ጥሎ ገሸሽ አለ። እንግሊዛዊውም ከዛች ኬንያዊት ጋር መደነስ ጀመረ። በእንግሊዛዊው ድርጊት በጣም ተናደድኩ። ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ወደ ዳንስ ወለሉ አመራሁ። እኔም እንግሊዛዊውን በካልቾ ጠልዤ ኬንያዊቷን ተቀበልኩ። ጥቂት ካስደነስኳትም በኋላ ለተቀማው ኬንያዊ አስረከብኩ። ይህን ፈፅሜ ወደ መቀመጫዬ ሳመራ እንግሊዛዊው የጠየቀኝ አንድ ጥያቄ ነበር ፦ "ኢትዮጵያዊ ነህ?" የሚል።
*ለዚህ ላበቁን መሪዎቻቻንና ጀግኖቻችን ላቅ ያለ ክብር ይገባል።*
©አንተነህ ብርሃኑ
👇ሼር👇ጆይን👇ሼር👇

ባል የሚስቱን ጆሮ ጤንነት መጠራጠር ጀምሯል።ሲያናግራት አትመልስም ግራ ገባው።ቢጨንቀው ለቅርብ ወዳጁ አንድ ሀኪም "ባክህ የሚስቴ ጆሮዋ ጤና አይመስለኝም ።የማናግራትን ሁሉ አዳምጣ አትመልስልኝም ።እርግጠኛ ሳልሆን ደግሞ ወደ ህክምና ይዣት ልመጣ አልሻም ምን ባደርግ ይሻላል? "ሲል ይጠይቃል ።
"ምን ችግር አለው ማታ ቤት ስትገባ 10 ሜትር ያክል ራቅ ብለህ ጥያቄ ጠይቃት፤ካልመለሰች 2 ሜትር ያክል ጠጋ ብለህ ከ8 ሜትር ጠይቃት ፤እሱንም ካልመለሰች ከ6 ሜትር ፤ከዛም ካልሆነ ከ4.. እያልክ አናግረኻት የህመሟን መጠን፤ የመስማት ችሎታዋ ከምን እንደደረሰ ለይተህ ስታበቃ እርግጠኛ ሰትሆን በግልጽ ነግረሃት ወደ ህክምና ይዘሃት ና"
ማታ ወደ ቤት ሲገባ የ10 ሜትር ክፍተት ለመጠበቅ ሌላ ክፍል ሄዶ
"ውዴ እራት ምንድነው? "
ጭጭ!!
ከ8 ሜትር
"እማ እራታችን ምን ይሆን? "
መልስ የለም!
ከ6 ሜትር
"እረ እናት እራት..."
ፅጥ!
እያለ እያለ እየቀረበ መጥቶ ጆሮ ግንዷ ስር ሲደርስ "ለእራት ምን እያበሰልሽ እንደሆነ አምስት ግዜ ጠየኩሽ እኮ "
" እህ እኔም አምስት ግዜ ጎመን ብዬ መለስኩልህ እኮ!"
**
ወደ ሰው ከመጠቆምህ በፊት የችግሩ መንስኤ እኔም ልሆን እችላለሁ ብለህ (ል)መርምር ለማለት ታህል የተለጠፈች!
©ኤፍሬም ጀማል

★"በታክሲ ስትሄድ አንድ ጋጠወጥ ሰው ቢገጥምህና የማይሆን ቃል ቢናገርህ ለርሱ ቦታ አትስጠው አንዱ ፌርማታ ላይ ይወርዳል ፣ ከዚያ በኋላ አታገኘውም ። አንተን ግን ቀኑን ሙሉ ሲበጠብጥህ ይውላል ።"
★"ቁንጫ የጠረጉት ዕለት ባለጌም የመከሩት ዕለት ይብሰዋል" እንዲሉ ምክር ለሁሉ አይሰጥም ፣ መልስ ለሁሉም አይመለስም ፣ ክርክር ከሁሉም ጋር አይደረግም ። "
🎤መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ
የእኛ ሰው "ኑሮዬን አሳምርልኝ ሳይል "አሟሟቴን አሳምርልኝ" የሚለው አለም ላይ ያለ ነገር በሙሉ ከንቱ መሆኑን ለማመላከት ነው፡፡
✔እንደው ልባችን ተሰውሮ፤ አስተሳሰባችን ተበርዞ እንጂ ባዶ እጃችንን እንደመጣን ባዶ እጃችን ነው እኮ የምንሄደው፡፡
ለዚህም ነው ፀሀፊዊ "በገንፎ ተጀምሮ በንፍሮ ለሚዘጋ ህይወት አንጣላ እንዋደድ" ያለው፡፡
ዛሬ ሁላችንም፤ ማለትም ትናንት መልካም የነበርን መልካምነታችንን የምናስቀጥልበት፤ መጥፎ የነበርንም ከቀኑ ጋር አዲስ ማንነት ተላብሰን መልካም ሰው የምንሆንበት ደስ የሚል ቀን ነው፡፡

ቬሎና ቦሎ
(አሌክስ አብረሃም)
የዮርዳኖስ የሰርግ ቪዲዮ ከሌሎች የሰርግ ቪዲዮወች የሚለየው ሰርጉ ላይ የትራፊክ
ፖሊስ አጭር ትእይንት ስለተካተተበት ነበር እንዴት ማለት ጥሩ ነው
ለዮርዳኖስ ሰርግ ጊዜ አጃቢ ሁነን ለምሳ ወደሙሽሪት ቤት እየሄድን ነበር ድንገት
ከሰማይ ዱብ ያለ የሚመስል የትራፊክ ፖሊስ የሙሽራውን መኪና ከነሙሽሮቹ አስቆመና
‹‹መንጃ ፈቃድ ›› አለ ኮስተር ብሎ ፍጥነቱና መኮሳተሩን ለተመለከተው በሙሽሮቹ መኪና
ጥንዶቹ ሳይሆኑ ጥንድ ፈንጅወች ተጭነዋል የሚል ጥቆማ የደረሰው ነበር የሚመስለው
‹‹ምን አጠፋሁ ሙሽራ እኮ ነው የጫንኩት ›› አለ ሹፌሩ
‹‹ እሱን ማን ጠየቀህ የመኪናው ቦሎ አልታደሰም ›› ብሎ ሹፌሩ ጋር ክርክር ገጠመ ::
ድፍን ሚዜ ወርዶ ትራፊክ ፖሊሱን መለመን ጀመረ
‹‹ኧረ በናትህ ሙድ የለውም ሰርግና ሞት አንድ ነው ሲባል አልሰማህም ምናለ ብታልፈን
ለዛሬ ›› አለች አንዷ ግማሽ ጀርባዋ የተራቆተ መዘነጥ ያለመደባት የምትመስል ዘናጭ
በያዘችው አበባ የትራፊክ ፖሊሱን አይን ልትመነቁለው ደርሳ ነበር
‹‹እኮ ...ይሄ መኪና ‹ቴክኒካል› ችግር ቢኖርበትስ በሰርጋችሁ ቀን ሃዘን ሆነ ማለት
አይደል ...ሰርግና ሞት አንድ ነው ማለት ያነው አደጋ ሙድ የለውም ብሎ አያልፍም ››አለ
ሙሽሪትን በአይኑ እየቃኘ
‹‹እሱማ ልክ ነህ ግን አሁን ሙሽሮቹን ጭነን ወደምርመራ እንሂድ እንዴ ›› አለ አንዱ
ሞቅ ያለው ሹፌር በማሾፍ
‹‹ ሙሽራ ጭነህ እንጦሮጦስ ከመውረድ ይሻላል ›› አለና ኩም አደረገው
የሙሽራው ንስሃ አባት ወርደው ትራፊክ ፖሊሱን ለመኑት ‹‹የኔ ልጅ ቃሉ እንደሚል
እ.....ጋብቻ ቅዱስ ... ምኝታውም ንፁህ ነውና ማበረታታት ነው ያለብን ›› እያሉ ስብከት
ጀመሩ
‹‹አባቴ እኔ መች መኝታቸውን ህገወጥ ነው አልኩ መኪናቸውን እንጅ ›› አለ ትራፊኩ
ቀዝቀዝ ብሎ ነበር
በብዙ ልመና ትራፊክ ፖሊሱ የሙሽሮቹን መኪና ከለቀቀ በኋላ አንዷ ከጎኔ የተቀመጠች
በጣም ቆንጆ እና ነብሷን እስክትስት የዘነጠች ወጣት (ለሰርግ አጃቢነት የተፈጠረች
የምትመስል ) እንዲህ አለች
‹‹....ትራፊክ ፖሊሱ ሙሽሪት ሰፈር ነበር በፊት ጠይቋት እንቢ ብለዋለች ወ.......ይ
ወንዶች ! ››
አሙቁልኙ እንዲህ አለ በዜማ
‹‹የኛ ሙሽራ ባለቬሎ
አስቆማት ባለቦሎ
አስቆማት
ባለ ቦሎ
.... እልልልልልልልልል ቦሎው ያልታደሰ መኪና ተከትለን ወደሰርጉ ቤት .... ይሄ ሁሉ
ሲሆን ካሜራ ማኑ እየቀረፀ ነበር ፡፡ የሰርግ ቪዲዮውን ስናየው ታዲያ የትራፊክ ፖሊሱና
የሰርገኛው ንትርክ አጠቃላይ ሰርጉን ‹ቬሎና ቦሎ› የሚል ‹ከሆሊውድ የመጡ
ባለሙያወች › የተሳተፉበት የፍቅር ኮሜዲ ፊልም አስመስሎት ነበር ፡፡ (የሰርግ ኮሜዲ
የሚባል የለም ብየ ነው )

ለፈገግታ
ባል ለሚስቱ የሆነ መረጃ እያነበበላት ነው። በሁለቱ መካከል የነበረው የሃሳብ ምልልስ ይህን ይመስላል: -
ባል 👉 «ሴት ልጅ በቀን ውስጥ ከአንደበቷ የሚወጡት የቃላት ብዛት ሶስት ሺህ ሲጠጉ የወንድ ልጅ ግን አንድ ሺህ ብቻ አንደሆነ ታውቂያለሽን ???
.
.
ሚስት 👉 «በሚገባ አውቃለሁ፤ ምክኒያቱም እኛ ሴቶች ነገር ለማይገባቸው ደደቦች የተናገርነውን ቃል በደንብ እንዲረዱት ሁለት ጊዜ ደጋግመን ለመናገር ስለምንገደድ ነው» 😲
.
.
ባል 👉 «ምን ማለት ነው ??» 😝
.
.
ሚስት 👉 «አየህ አይደል! ያልኩትን ነገር መድገም አለብኝ» 😃

🌺ያለ ምክኒያት ወደድኳት🌺
ከአያሌ መልከ-መልካሞች ከብዙ ቆንጆዎች መሀል፣
"ስለምን ወደድካት?"ብባል፤
እወዳታለው እንጂ ፍቅሯ ጨርቄን እስኪያስጥለኝ ምክኒያትማ የት አለኝ?
አይኗን፣ፀጉሯን....ብዬ እንዳልል በውበቷ ተገድጄ ስንት ዞማ-ስንት አይናማ በየ እለቱ ያልፋል ደጄ
መልካሙ ስብዕናዋ፣ ፀባይዋ፣ ባህሪዋ እንዳልል፣
በሻካራ አመሏ ነው አንድ አንጀቴን የምታቃጥል፤
ምክኒያትማ የለኝም እኔ ምን አውቅላታለው?
ብቻ እንዲሁ እወዳታለው።

ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ ቀን ጠባቂዎቻቸውን ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ።
አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ።
ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። ሰውዬው እየተመገበ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር። ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማዴባ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነው መሰለኝ ።
እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር"ይላቸዋል ማዴባም "አይደለም!ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር ። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናብኝ ነበር" አሁን ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ሀገር በመቻቻል እና በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም ።
ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም !!!
ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና!

ዶ/ር ምህረት ደበበ
ባዶ በርሜል ስታንከባልለው ይጮሀል፡፡በዛው ልክ በውሀ
የተሞላን በርሜል ስታንከባልለው ድምፅ የለውም፡፡ሲንከባለልም
በእርጋታ ነው፡፡የሰው ልጅም እንደዛ ነው፡፡ ጭንቅላቱ ባዶ የሆነ
ሰው ከመጮህ እና ከመቸኮል የዘለለ ማድረግ ሚችለው ነገር
የለም፡፡ በእውቀት የተሞላ ሰው ግን ዝምተኛ እና የተረጋጋ ነው፡፡
በጮህን እና በቸኮልን ልክ ጭንቅላታችን ይገመታል፡፡ ራሳችንን በእውቀት እንገንባ !!

"የዛሬ መቶ ዓመት ማንኛችንም አልነበርንም ። ከመቶ ዓመት በኋላ አንዳችንም አንኖርም። ይህንን ከልባችን ማሰብና አስረግጠን መረዳት ብንችል ትንሽ መተዛዘን፣ የተሻለ መተሳሰብ፣ ያለንን ተከፋፍለንና ተረዳድተን አብረን በሠላም መኖር እንችል ይሆን? አገር የጭንቅላታችንን እንጂ የቆዳ ስፋቷን ያህል አይደለችምና ።"
ዶክተር ምህረት_ደበበ
@sewmehoneth
ዶክተር ምህረት_ደበበ
@sewmehoneth
የመጀመሪያው እምቢታ!
«ዘውድአለም ታደሠ»
«ሰላም ነው ስሜ» አለችኝ!
«ሰላም የሚባሉ ሴቶች ብዙ ግዜ ፀረሰላም ናቸው ይባላል» አልኳት!
«ይሆናል ...» ብላ ሳቀች!
ሰላምን ካገኘኋት ገና ሰላሳ ደቂቃ አይሞላኝም። ሰው ሰላም ሊል ወደኋላ የቀረ ጓደኛዬን ቆሜ ስጠብቅ ድንገት በኔ በኩል መጣች። ልከኛ ነች። ያልተዝረከረከ ውበት አላት የምላት አይነት! መሃከለኛ ቁመት፣ መሃከለኛ ፀጉር፣ መሃከለኛ የሰውነት ቅርፅ ... በመሃከለኛ እርምጃ ስትመጣ የማላውቀው ሃይል የሆነ ነገር በል በል አለኝ!
አጠገቤ ስትደርስ «እንተዋወቅ» አልኳት! የምር በቃ ይሄን ነው ያልኳት! ማነሽ? ወዴት ነሽ? ገለመሌ የለም፣ አለ አይደል ልክ ፊልም ላይ እንደምናያቸው አክተሮች መጀመሪያ አስቆ ፣ አባብሎ፣ አሽኮርምሞ “እጅ ፅሁፍሽ እንዴት ነው?” ምናምን ብሎ መጀንጀን የለ እንዲሁ ድርቅ ብዬ እንተዋወቅ!
«ሰላም እባላለሁ» አለችኝ!

«ፀሃይ ነው ለምን ትንሽ አረፍ ብለሽ ቡና ምናምን ጠጥተሽ መንገድሽን አትቀጥዪም?» አልኳት!
«እሺ» አለችኝ!
ጓደኛዬን ጥዬ አንዱ ካፌ ይዣት ገባሁና ሻይ ቡና ብለን ስንወጣ «ለክፉም ለደጉም ቁጥር ብንለዋወጥ» አልኳት!
«እሺ» አለችኝ። (ልጅቷ እምቢ አታውቅም ጎበዝ)
ቁጥሯን ተቀብዬ ደወልኩላትና ጥቂት አውርተን «ነገ ከተመቸሽ እንገናኝ» አልኳት
«እሺ ....!»
ብዙ ግዜ ተገናኘን! ተቀራረብን! ወደድኳት! ፈራ ተባ እያልኩ «ወደድኩሽ» አልኳት። ትንሽ አስባ «እሺ» አለችኝ።
«ፍቅረኛዬ ብትሆኚ ደስ ይለኛል»
«እሺ ....»
የእሺታዋ ብዛት ግራ ቢገባኝም ወድጄዋለሁ። ምንም ነገር አትቃወም! እምቢ አታውቅ! አትጨቃጨቅ! በቃ ሁሉን እሺ ነው! እንዲህ ቦታ እንሂድ? እሺ! እንዲህ እናርግ? እሺ! ... ሁለት አመት ከአምስት ወር ሆነን አንድም ቀን ፀባይዋ ሳይለወጥ! አንድም ቀን ኮምፕሌን ሳታደርግ! እንዲሁ ግራ እንዳጋባችኝ ሁለት አመት ከአምስት ወር በፍቅር!!
ቀለበት ከኪሴ አውጥቼ «አግቢኝ» አልኳት!
«እሺ ....!»
የሆነ ነገር ይደብረኝ ጀምሯል! አለ አይደል የሆነ ውድን ነገር በርካሽ ስናገኘው «ይሄ ነገር ፎርጂድ ይሆን እንዴ?» ብለን የምንጠራጠረው አይነት? ቆይ እስከዛሬ በኔ ስሜት፣ በኔ ፍላጎት፣ በኔ እቅድ ብቻ ኖረች! የራሷ ስሜትስ? የራሷ ፍላጎትስ? የራሷን ህልም የት አርጋው ነው ሰው ህልም ውስጥ ጭልጥ ብላ ምትጠልቀው?
ተጋባን!
«ልጅ እንውለድ?»
«እሺ!»
ግራ ታጋባኝ ነበር! አሁን ግን የእሺታዋን ጋጋታ እንደድንዛዜ አየሁት። አለ አይደል ስሜትን ካለማዳመጥ የሚመጣ፣ ፍላጎቷን ሳታውቅ የምትኖር ነፋሱ ወደነዳት የምትንሳፈፈ ፌስታል ያህል ቀለለችኝ! በቀደዱላት ቦይ የምትፈስ ወራጅ ውሃ መሰለችኝ! አዎ ውሃ! ከገደቧት የምትረጋ፣ መንገድ ከሰጧት የምትጓዝ፣ እሳት ላይ ሲጥዷት የምትሞቅ፣ ፍሪጅ ሲጨምሯት የምትበርድ ብርጭቆ ውስጥ ሲያረጓት ብርጭቆውን የምትመስል፣ በስኒ ሲጨልፏት የስኒውን ቅርፅ የምትይዝ ፣ የራሷ ቅርፅና መልክ የሌላት ውሃ መሰለችኝ! ተራ ውሃ!
ለምን አመሸህ? ለምን ይሄን አላረግክም? ብሎ ጭቅጭቅ እሷጋ የለም! እንኳን ባመሽ ባድር በነጋታው ምንም እንዳልተፈጠረ በፈገግታ ትቀበለኛለች! ብስጭት ብዬ ስናገራት መልስ አትሰጥም! ይሄን አርጊ ያን አታርጊ ስላት ለምን? የለም «እሺ» ነው! በቃ እሺ ብቻ!
በጓደኞቼ ሚስቶች እቀናለሁ። ሲቆጡ ቁጣቸው ውስጥ የኔነት አለ። ሲቀኑ ቅናታቸው ውስጥ ስስት አለ! ሲከፉ መከፋታቸው ውስጥ ፍቅር አለ! የኔዋ ግን .... በቃ በድን! ታግዬ እንኳ ላስከፋት የማልችል፣ ሁሉን ነገር ከመቀበል ውጪ እምቢ የማታውቅ ግኡዝ ፍጥረት ትመስለኛለች!
አንዳንዴማ ነካ ሚያድጋት ሁሉ ይመስለኛል! እኔው አጥፍቼ እኔኑ ይቅርታ ስትጠይቀኝ ብግን እላለሁ። አስከፍቻት ውዬ ስመለስ ከበር በፈግታ ስትቀበለኝ እየተወነች ይመስለኛል! አውቄ የማይሆን ሃሳብ ስነግራት ስትቀበለኝ ጩህ ጩህ ይለኛል! አንዳንዴ ስጋ የለበሰች አሻንጉሊት ያገባሁ ሁሉ ይመስለኛል! በኔ ፍላጎትና መጠን ዲዛይን የተደረገች ሮቦት ትመስለኛለች!
ሰለቸኝ! በድን አቅፌ የምተኛ መሰለኝ። ለካ ጠብ ብቻ ሳይሆን ቅጥ የለሽ ሰላምም ይረብሻል! ለካ አለመስማማት ብቻ ሳይሆን ዝም ብሎ መስማማትም ይጨንቃል! «እንኳን ሰው ድንጋይና ድንጋይ እንኳ ይጋጫል» ይላሉ አበው እንዴት ነው ሰው እንደዚህ ሆኖ ሚኖረው?
በተጋባን ባመቱ «እንፋታ» አልኳት
«እሺ!» አለችኝ!
ለምን? የለ! ድንጋጤ የለ! በቃ «እሺ ብቻ!» ...ፊቷ ላይ ግን የሆነ ሃዘን መሳይ ነገር አይቻለሁ! ቢሆንም ይሄንንም «እሺ» ብላ መቀበሏ የበለጠ አናደደኝ! ከዚች ጋማ መኖር አልችልም። አልኩት ራሴን! ጠኋት ተነስቼ ወደምሄድበት እሄዳለሁ ቤቱን እሷ ቤቢን ይዛ ትኑርበት። ልጄ ሲናፍቀኝ እንደው እየመጣሁ አየዋለሁ! አልኩ በሆዴ!
በጠኋት ሻንጣዬን ይዤ ልወጣ ስነሳ እሷ ቀድማኝ ቤቢን ይዛው ሄዳለች! ቁምሳጥኑ ውስጥ እኔ የገዛሁላት ልብሶች ብቻ ቀርተዋል! ፍሪጁ ላይ አንድ ወረቀት ተለጥፏል። ጠጋ ብዬ አየሁት
«ራስህን ጠብቅ» ይላል!
ግራ ገባኝ! እንዳሰብኩት ነፃነት አልተሰማኝም። የሆነ ሃዘንና ድብርት የቀላቀለ ነገር ይሰማኛል። ሳምንቱን ሙሉ ሰከርኩ! ከሳምንት በኋላ ደወልኩላት! ስልኳን አታነሳም። በህቷ ስልክ ስደውል ቤተሰብ ጋር እንዳለችና ልታናግረኝ እንደማትፈልግ ነገሩኝ! ይሄን ስሰማ የሆነ ደስ ነገር አለኝ! ማለት አለ አይደል እሷም እንደሰዉ እንደምትከፋ በማወቄ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ!
አንድ ወር ቆይቼ ደወልኩላት። አሁንም አታነሳም። ግራ ተጋባሁ! ጨነቀኝ! ምንም ያልበደለችኝን ሚስቴን ምን ሁኚ ብዬ ነው ያባረርኳት? ትዳሬን ምን ይሁን ብዬ ነው ያፈረስኩት? ምን አርጊ ምን ፍጠሪ ነው ያልኳት ቆይ? ፀፀት ሁለመናዬን ወረረኝ! ቢቸግረኝ የቅርብ ጓደኛዬን ይቅርታ ጠይቆ እንዲያመጣት ላኩት። እሷ ማንንም ስለማታስከፋ እሺ እንደምትለው እርግጠኛ ነበርኩ!
ለማሰቢያ የሚሆን ግዜ እንዲሰጣት ነግራው አሰናበተችው። በሳምንቱ የፍቺ ወረቀት ላከችልኝ! ምድርና ሰማይ ዞረብኝ! ወረቀቱን በእጄ አንጠልጥዬ ስበር ቤተሰቧ ቤት ሄጄ በሩን አንኳኳሁ።
ራሷ ከፈተች! ፊቷ ላይ ምንም አይነት ለውጥ አላየሁም። አይኖቿ ላይ ግን እንለያይ ስላት ያየሁትን ሃዘን አይቻለሁ።
«ምንድነው ይሄ?» አልኳት
«እንፋታ ብለኸኝ የለ? የፍርድቤት መጥሪያ ነው» አለችኝ። ድምጿ ውስጥ የቀድሞ ልስላሴዋ የለም። ሌላ ሴት ነው ምትመስለው።
እግሯ ላይ ወድቄ ይቅር እንድትለኝ ለመንኳት! ዝም ብላ ስታየኝ ቆይታ አንድ ቃል ከአፏ አወጣች
«እምቢ!»
ጆሮዬን አላመንኩም። እምቢ የሚለው ቃል ለካ እንዲህ ያማል? እምቢታዋ ውስጥ ከእሺታዋ የሚበልጥ ጥንካሬ አለ! እምቢታዋ ጨካኝ ነው! ያስፈራል ! ከዚያን ቀን ወዲህ ለመታረቅ ያልፈነቀልኩት ድንጋይ ያልሰደድኩት ሽማግሌ የለም! ነገር ግን ሁሉም እምቢታዋን ለማሸነፍ የሚያበቃ ጥንካሬ አልነበራቸውም!
እምቢታዋ ዘልአለማዊ ነው!

ስርና ዘራችንን ማወቅ
ስርና ዘራችንን ማወቅ ማለት ከምን አይነት ሁኔታ እንደመጣንና የመጣንበት ሁኔታ ምን አይነት ተጽእኖ እንዳደረገብን መለየት ማለት ነው፡፡ ከቤተሰባችንም ሆነ ከኖርንበት ሕብረተሰብ የተቀበልናቸው መልካም ነገሮች እንዳሉ ሁሉ፣ ጤና ቢስንም ነገር ወርሰናል፡፡
አስተዳደጋችን በራሳችንም ሆነ በአካባቢያችን ላይ ባለን አመለካከታችን ላይ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ሁለት ምላሾች ከእኛ ይጠበቃሉ፡፡ በአንድ ጎኑ፣ ከአመጣጣችን የወረስናቸውን ጎጂ ነገሮች ለይቶ በማወቅ ማስወገድ፡፡
በሌላ ጎኑ ደግሞ ከአመጣጣችን የተቀበልናቸውን መልካም ነገሮች ለእድገታችን መጠቀም፡፡
ስርህንና ዘርህን ለማወቅ የሚከተሉትን ሃሳቦች ማሰላሰል ትችላለህ፡-
1. ሃገርህን ቃኛት
የተወለድክባትና ያደክባት ሃገር በአንተ ላይ ያመጣችውን ተጽእኖ ለመለየትና ለማስወገድ ይህንን ጥያቄ ጠይቅ፣ “የተወለድኩባት ሃገር ምን አይነት አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ያወጣች አገር ናት?”
2. ሕብረተሰብህን ተመልከተው
ብዙውን ጊዜህን ያሳለፍክበት ሕብረተሰብ በአንተ ላይ ያመጣውን ተጽእኖ ለመለየትና ለማስወገድ ይህንን ጥያቄ ጠይቅ፣ “ያደግሁበት ሕብረተሰብ ምን አይነት አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ያፈራ ሕብረተሰብ ነው?”
3. ቤተሰቦችህን አስተውላቸው
ያሳደጉህ ቤተሰቦችህ ወደ አንተ ያስተላለፉትን የዘር ተጽእኖ ለመለየትና ለማስወገድ ይህንን ጥያቄ ጠይቅ፣ “ያደግሁበት ቤት ምን አይነትን ቤተሰብ ያቀፈና ምን አይነት ልጆች ያፈራ ቤት ነው?”

የመለየት ብልሃት
ምንም ያህል ሁኔታዎችን የመቆጣጠር ብቃት እንዳለን ብናስብም እንኳን አንዳንድ ሁኔታዎች ሙሉ ለሙሉ ከእኛ ቁጥጥር ውጪ እንደሆነ ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡
መቆጣጠር የምትችለው
በሕይወትህ በሚገባ በማሰብ፣ እቅድ በማውጣትና አስፈላጊውን እንቅስቃሴ በማድረግ መለወጥ የምትችላቸው ነገሮች ብዙ ናቸው፡፡ በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ እንድታተኩር ትመከራለህ፡፡ ለምሳሌ፣ ጤና-ቢስ አመጋገብ ዘይቤና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ የሚያመጣውን ጠንቅ አስበህ ስትፈራ ውለህ ከምታድር ይልቅ፣ ሁኔታው በቁጥጥርህ ክልል ውስጥ ስለሆነ ያንን በማድረግ ለውጥ ማምጣት ትችላለህ፡፡ በተቃራኒ ደግሞ፣ ድንገተኛ አደጋ ይደርስብኛል ብለህ የምትሰጋ ከሆነ ይህ ሁኔታ ከአንተ ቁጥጥር ውጪ ስለሆነ ከመጨነቅና ሲፈሩ ውሎ ከማደር ይልቅ ተረጋግቶ ስራህ ላይ ማተኮር ይበጅሃል፡፡
መቆጣጠር የማትችለው
በሕይወትህ ምን ያህል ብትጨነቅ፣ እንቅልፍ አጥተህ ብታድርና ብትሯሯጥ በፍጹም ለውጥን ልታመጣ የማትችላቸው ሁኔታዎች ብዙ ናቸው፡፡ አንዲት አነስተኛ ጠፈራማ አካል ወደ መሬት አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየተወረወረች በመምጣት ላይ እንዳለችና ይህቺ አካል በዚህ አመት ውስጥ በማንኛውም ሰዓት በመሬት ላይ ትወድቃለች የሚል ዜና ብትሰማ፣ ምርጫህ ሁለት ነው፡፡ አንደኛው፣ ምርጫህ “በተኛሁበት እኔ ላይ ወድቃ ትገድለኝ ይሆን?” በሚል ፍርሃት ቁጭ ብሎ ማደር ነው፡፡ ሁለተኛውና የተሻለው ምርጫህ ግን፣ “መቼና የት እንደምትወድቅ ስለማላውቅ የየቀን ተግባሬ ላይ ላተኩር” በማለትና መቆጣጠር የማትችለው ሁኔታ እንደሆነ በመቀበል በተረጋጋ ሁኔታ ኑሮህን መቀጠል ነው፡፡
ለምሳሌ፣ ጤና-ቢስ አመጋገብ ዘይቤና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ የሚያመጣውን ጠንቅ አስበህ ስትፈራ ውለህ ከምታድር ይልቅ፣ ሁኔታው በቁጥጥርህ ክልል ውስጥ ስለሆነ ያንን በማድረግ ለውጥ ማምጣት ትችላለህ፡፡
ይህ ሃሳብ በአጭሩ ሲጠቃለል፣ መቆጣጠር በምትችላቸውና በማትችላቸው ሁኔታዎች መካከል በመለየት፣ መቆጣጠርና መለወጥ የምትችላቸው ላይ ማተኮር፣ በፍጹም ከአንተ ቁጥጥር ውጪ ከሆኑት ሁኔታዎች ላይ ደግሞ ሃሳብህን ማንሳት ወሳኝ ነው፡፡ ይህ ብልሃት ፍርሃትን በሚገባ ለመያዝና ከፍርሃት ስሜት አጉል ተጽእኖ በላይ ለመኖር በምናደርገው ጥረት ቀዳሚነቱን የያዘ ብልሃት ነው፡፡