📌ሰይጣንን እና ወንጀሎቻችንን ለማሸነፍ የሚረዱን አምስት ምልከታዎች!
①ኛ―አትዘውትር!
ማለትም ወንጀልን ልማድህ አታድርግ።በየዕለቱ የምታደርገው ነገር አይሁን።
•• አላህ እንዲህ ይላል፡-
إِنَّ الَّذِينَ اتَّقَوْا إِذَا مَسَّهُمْ طَائِفٌ مِّنَ الشَّيْطَانِ تَذَكَّرُوا فَإِذَا هُم مُّبْصِرُونَ
እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ፡፡ ወዲያውም እነሱ ተመልካቾች ይኾናሉ፡፡
አወ! የሕይዎትህን መሰረት ኢስቲቃማ አድርግ።ስህተት መስራትን ደሞ ከመንገድ(እንደመውጣት አድርግ) ልክ እንደተበላሸ መኪና። መኪናህ ሲበላሽ ትቆማለህ፣ ትጠግነዋለህ ከዛም መንገድህን ትቀጥላለህ።
ስለዚህ ወንጀል ስትሠራ ተመልሰህ ወደ ነበርክበት መንገድ ተመለስ። ምክኒያቱም አንድ ሰው ከመንገድ ወጥቶ እየሄደ ጉዞውን ከቀጠለ በመጨረሻ ወዴት እንደሚደርስ አያውቅምና።
ለዚህም ነው አብደሏህ ኢብኑ ዓባስ እንዳሉት፦
"لا صغيرة مع الإصرار"
«(ወንጀል ላይ) ከመዘውተር ጋር ትንሽ የሚባል ወንጀል የለም።» ይላሉ።
ማለትም…አንድ ሰው ትንሽም ወንጀል ቢሆን እዛ ላይ ከዘወተረ ትንሹ ወንጀል እንኳን ትልቅ ይሆናል ማለታቸው ነው።
②ኛ ወንጀልን በይፋ አታድርገው!
አደራህን የሰይጣን ድርጅት ውስጥ ሰራተኛ ከመሆን ተጠንቀቅ።ሰይጣን ሰዎችን ለመበከልና ለማጥመም እራሱን ዳዒ ያደረገ፤ ብዙ ሰዎችንም በድርጅቱ ውስጥ ቀጥሮ ወደ ወንጀል በመጣራት ወይም በግልፅ ወንጀልን በመፈፀም ላይ ተጣሪ አድረጓቸዋል።
ለዛም ሲባል ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- «የኔ ኡመት ሁላቸውም ይቅር ይባላሉ።(ወንጀልን)በ ግልጽ የሰሩትን ሲቀር!» ስለዚህ ወንጀልህን በግልፅ ከመፈፀም ተጠንቀቅ።
ወንጀልን በይፋ የሚሠሩ ሰዎች የሰይጣን አጋር ናቸው። ምክንያቱም ሌሎችንም ወደ ወንጀል ስለሚጋብዙ።
③ኛ ወንጀልን አታብዛ!
ሰይጣን ወንጀልን እንዳትተወው ቢያሸንፍህ እንኳ፤በተቻለህ መጠን ለመቀነስ ሞክር።
ከ ወንጀል መላቀቅ የማትችል ከሆነ ቢያንስ የምትሰራውን ወንጀልን ለመቀነስ ሞክር።
④ኛ― ተውበት እና ኢስቲጝፋር አድርግ!
ወንጀል ላይ ከወደቅክ ቶሎ ብለህ በተውባ እና በ ኢስቱግፋር አጥፋው።የሥራ መዝገቦቻችን እንደ ነጭ ሰሌዳ ነው። ወንጀሎቻቸን ደግሞ በላዩ ላይ በጥቁር ቀለም እንደተፃፉ ፁሁፍ ናቸው።ስለዚህ በሥራ መዝገብህ ላይ በ ወንጀል ጥቁር ቀለም ስትጽፍ እና በኃጢአት ስትበክል ወዲያውኑ በተውበት እና በኢስቲጝፋር አጥፋው። በየጊዜው ወንጀል ስትሠራ ወዳው ተውበትን ማድረግ ተለማመድ።
⑤ኛ― መጥፎውን በመልካም ተካ!
ወንጀልን መተው አለመቻልህ፣በተደጋጋሚ ወንጀል ላይ መውደቅህ ተስፋ እንዳያስቆርጥህ። አንተም በተደጋጋሚ መልካምን ስራ ስራበት። ምክንያቱም መልካም ስራዎች መጥፎ ስራዎችን ያጠፋሉና!
ስለዚህ ወንጀል በሰራህ ቁጥር ከሱ ብኃላ መልካም ስራዎችን አስከትል።ለሰዎች መልካምን መዋል፣ ቁርአን መቅራት፣ዚክር ማድረግ፣ ሰደቃ መስጠት፣የሱና ሶላቶችን መስገድ…መሰል ዒባዳዎችን ፈፅም።
📑ከሸይኽ ሃመደል-ዓቲቅ የቴሌ ግራም ቻናል ተወስዶ ከትንሽ ቃላት ቅያሬ ጋር ወደ አማርኛ የተመለሰ―
=www.tgoop.com/Sle_qelbachn1

30 ምክሮች ለሙስሊሟ እህቴ!
~
1- ሒጃብሽ ሰፋ ያለና ረዘም ያለ ይሁን ።
2- አካሄድሽ ረጋ ያለና አደብ የተላበሰ ይሁን ።
3- በየቀኑ ብታጠፊ በየቀኑ ወደ አላህ ተመለሺ።
4- በአለባበስሽና በሥነ-ምግባርሽ ለሌሎች ሴቶችና ለሴት ልጆችሽ ምሳሌ ሁኚ።
5- ሊፕስቲክ ተቀቢዎች በዝተዋል፤ ግና ብዙዎች ስላደረጉት ጉዳዩ ትክክል ነው ማለት አይደለም ።
6- አዝማሚያው ያላማረሽን ቅርርብ በአጭር ቁረጪ።
7- ስትቀመጭ ሰብሰብ ሰተር ብለሽ ተቀመጭ።
8- ያልተፈቀደልሽን ባዕድ ወንድም ሆነ ሊያገባሽ የሚፈቀድለትን የቅርብ ዘመድ አትጨብጭ።
9- ከላይ አላህን ሳይታዘዙ፤ ዉስጤ ንፁህ ነው አላህን ፈራለሁ ማለት ቅጥፈት ነው።
10- ከባዕድ ወንድ ጋር ስታወሪ መቅለስለስ በሽታ ያለበትን በሽታውን መቀስቀስ ነው።
11- መስመር እየሳቱ የሚመስሉ የስልክ ወሬዎችንና ቻቶችን ቁረጪ።
12- በማይረባ ነገር እና ማ/ዊ ሚዲያ ላይ ዉድ ጊዜሽን አታጥፊ።
13- ወንድ ከኋላ እየተከተለ ደረጃ አትው።
14- ሙዚቃ የተቆጣጠረዉን ልብ ቁርአን ለቆት ይወጣል ።
15- እየተኳኳሉና እየዘለሉ አላህን እና መልዕክተኛዉን እወዳለሁ ማለት ዉሸት ነው።
16- ሒጃብና ኒቃብ እየለበሱ መጥፎ መሥራት የኢስላምን ንጽሕት ሙስሊምን ሥም ጭምር ማጠልሸት ነው።
17- ሆነብለሽ ወንዶችን አትፈታተኚ።
18- በሐራም መንገድ ገንዘብም ሆነ ትዳር ባገኙት አትቅኚ።
19- ያለ ኒካሕ የተወለደ ልጅ አባት የለዉም ።
20- ደረትሽን አትክፈቺ አታሳብጪም።
21- ቀሚስሽን ከኋላም ሆነ ከፊት አትቅደጂ።
22- ፀጉርሽን አትጎዝጉዢ አትቀጥይ።
23- ሽቶም ሆነ ዶድራንት አትቀቢ።
24- ሊፍት ስትገቢ ከወንድ ጋር ብቻሽን አትግቢ።
25- ብቻሽን ባዶ ቤት ዉስጥ አትደሪ።
26- ተሰተሪ በሁሉም ነገር አላህ ይሰትርሻል።
27- ስትስቂ በስሱ፤ ሰታወሪ ድምጽሽ ዝቅ ይበል ።
28- በሥራ ቦታ ከሰዎች ጋር ባለሽ ግንኙነት ቀይ መስመር ይኑርሽ።
29- ተግባቢ እና ትህትና ያለሽ ሁኚ ።
30- በተቻለሽ መጠን አላህን ፍሪ።
አላህ ይሠትረን።

فليست هذه الدنيا بشيء ... تسوئك حقبة وتسر وقتا
وغايتها إذا فكرت فيها ... كفيئك أو كحلمك إذ حلمتا
سجنت بها وأنت لها محب... فكيف تحب ما فيه سجنتا
ምንም አየደለችም የዱንያዋ ህይወት
ዘመን አስደስታህ ታዝናለህ ሌላ ወቅት
ድካዋ'ኮ የሧ ስታስተነትናት
ወይ እንዳንተ ጥላ ወይ እንደ ህልምህ ናት
ታሥረሃል በውስጧ የሷ ወዳጅ ሆነህ
!?የታሰርክበትን እንዴት ትወዳለህ
ከታኢየቱል ኢልቢሪ የተወሰደ
ግርድፍ ትርጉም በኡስታዝ ሙሐመድሲራጅ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🛑 ወንጀሌ በዝቷል እጅግ በጣም ጨንቆኛል አላህ ግን ይቅር ይለኝ ይሁን ???
⭐️አዎን በሚገባ ተዉበት አድርግ እንጂ እጅግ በጣም ሩህሩህ አዛኝ የሆነዉ አላህ ይቅር ይልሃል አብሽር ከአንተ የባሱትንም ከልባቸዉ ወደ እርሱ ተመልሰዉ ይቅር ብሎዋቸዋል 100 ሰዉ ገድሎ ከልቡ ወደ ጌታዉ በመመለሱ ይቅር የተባለዉን ሰዉ ታሪክ እየሰማህ ለምን ተስፋ ትቆርጣለህ ???
በፍጹም አትቁረጥ ሸይጣን አይጫወትብህ ወንድሜ ወንጀል ዉስጥ ከጣለህ አንተ ደግሞ ወደ አላህ በመመለስ አንገቱን አስደፋዉ ።
እዝነተ ሰፊዉ ጌታችን በተከበረዉ መፅሀፉ እንዲህ ይላል :
۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡

የልብ ድርቀትን ለመከላከል
~
በዚህ ዘመን በልብ ድርቀት ያልተጠቃ ይኖር ይሆን? ሃሳብ ጭንቀታችን ዱንያ ብቻ ሆነ። ዒባዳችን ለዛ አጣ። መተዛዘን ጠፋ። ስግብግብነት ነገሰ። ስስት ከደም ከስጋችን ጋር ተዋሀደ። የዱንያ ምኞታችን ከመርዘም አልፎ ተንዘላዘለ።
ወንድሞች እህቶች ወላሂ! የልብ ድርቀት በጣም ሊያስጨንቀን የሚገባ ህመም ነው። የልብ ድርቀት አደገኛ ውጤት የሚያስከትል የአላህ ቅጣት ነው። ከዚህ ህመም ልባችንን እንዴት እናክም? ከዚህ የአላህ ቅጣት እንዴት እንውጣ? ጥቂት ሰበቦችን ልጠቁም። ራሴም ጤነኛ ሆኜ አይደለም። ከማጨስ እንደሚያጠነቅቅ አጫሽ፣ ከህመም እንደሚያስጠነቅቅ ህመምተኛ ቁጠሩኝ።
1- አላህን በማሰብ ራስን አጠቃላይ ከወንጀል መጠበቅ፣ የቅርብም ይሁን የሩቅን ሰው ከመበደል መጠንቀቅ፣ ግብይታችንን፣ ገቢያችንን ሐላል ማድረግ፣ የሰው ሐቅ እንዳይመጣብን መጠንቀቅ
2- ምላስን ከውሸት፣ ከመጥፎ ንግግር፣ ከሃሜትና መሰል ክፍተቶች መቆጣጠር፣ ጆሮዎቻችንን ሐራም ነገሮችን ከማዳመጥ፣ አይኖቻችንን ሐራም ነገሮችን ከመመልከት፣ እጆቻችንን ለሐራም ነገሮች ከመጠቀም፣ ልባችንን በክፋት፣ ምቀኝነት፣ ጥላቻ፣ ... ላይ ከመጥመድ መቆጣጠር
3- ዚክር ማዘውተር፣ በቋሚነት የቁርኣን ዊርድ መያዝ፣ ደጋግሞ ከልብ ዱዓእ ማድረግ፣ ተደቡር፣ ተፈኩር ማድረግ፣ በዱዓእ፣ በቁርኣን ማልቀስ
4- ከሰላት፣ ከፆም፣ ከሶደቃው፣ ... ከግዴታው ባለፈ ነፍል ዒባዳዎችን ማዘውተር
5- ሞትን፣ ቀብርን፣ ሂሳብን፣ ሲራጥን፣ ... ኣኺራን ማሰብ
6- ደግሞ ደጋግሞ ኢስቲግፋርና ተውበት ማድረግ
7- ቁርኣን በእርጋታ መቅራት፣ ኹሹዕ የሚያጋባ አቀራር ያላቸውን ቃሪኦች ማዳመጥ፣
8- ቀብር መዘየር፣ የታመመን መጠየቅ፣ ወላጆችን፣ ዘመድ አዝማድን፣ ጎረቤትን አቅም በፈቀደ መጠየቅ
9- ችግረኛን በገንዘብም፣ በሃሳብም፣ በጉልበትም፣ በእውቀትም መርዳት፣ ሶደቃ ማድረግ
10- የዙህድና የረቃኢቅ ኪታቦችን ማንበብ፣ ውስጥን ሰርስረው የሚገቡ ሙሓደራዎችን እየፈለጉ ማዳመጥ፣ የነብዩን ﷺ ሲራ፣ ራስን ለመታዘብ የሚያግዙ የሰለፎችን አስገራሚ ታሪኮች፣ የዑለማኦችን ጣፋጭ ወጎች በትኩረት መከታተል
11- በየትኛውም የዒባዳ መስክ ላይ ኢኽላስን አጥብቆ መፈተሽና ማቃናት።
12- ከራስ ጋር መተሳሰብ። ጊዜ አልፎ ጊዜ በተተካ ቁጥር ወደ ሞት እየቀረብን ነው። ከአምና ዘንድሮ፣ ከባለፈው በዚህኛው፣ ሳምንታችን፣ እለታዊ ውሏችን መሻሻል አለው? ወይስ ያው ነው? ወይስ ጭራሽ እየባሰበት ነው? ከዱንያችን በላይ ኣኺራችን ያሳስበናል? ድንገት ብንሞት ያለንበት ሁኔታ በፀፀት ጣት የሚያስነክስ አይደለም? ራሳችንን ለመለወጥ የምር እንታገል።
እኔ የራሴን ድክመቶች በመመልከት ድንገት የመጣልኝን ነው የፃፍኩት። ሁሉም ነገን አስቦ ዛሬ ራሱን ይመልከት።
﴿بَلِ الْإِنْسَانُ عَلَى نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ﴾
"በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡" [አልቂያመህ ፡ 14]
=
✍ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

የሱብሒ አዛን!
• ከሌሎች የሶላት አዛኖች በተለየ መልኩ በሱብሒ አዛን ላይ የምትጨመር ቃል አለች፡፡ «አሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም» ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡― የምትል፡፡ አዎን ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡
▶እንቅልፍ የሥጋ ጥሪ ነው፤ ደከመኝ አሳርፉኝ ይላል። ሶላት የአላህ ጥሪ ነው፡፡ አላህ ወደኔ ኑ እረፉ ይለናል፡፡
▶ እንቅልፍ ሞት ነው፤ ሶላት ደግሞ ሕይወት፡፡ በሶላትህ ነፍስ ዝራ፣ ከነፍስህ ጌታ ጋር ተገናኝ፡፡
▶ እንቅልፍን አካልን ያሳርፋል፤ ሶላት ግን ቀልብን ያረጋጋል፣ መንፈስን ያሰክናል፡፡
▶ ሶላት የአማኞች መለያ ናት፤ ጌታ እንደሌለው ባሪያ ያለ ሀሳብ ዥው ብለህ አትተኛ፡፡ ተለይተህ ተነሳ፡፡
▶ እንቅልፍ ሲበዛ ያሰንፋል፣ ለድካምም ለዱካክም ያጋልጣል፡፡ተነስቶ መስገድ ንቃትን ይሠጣል፣ አካልን ያፍታታል፣ ፊትን ያበራል፣ ወዝን ይመልሳል፡፡
▶ የማለዳ አየር የተለየና ፀጥ ያለ ነው፡፡ ለዒባዳም፣ ሀሳብን አሰባስቦ አላህን ለመማፀንም ምቹ ነው፡፡
▶ በሶላት የተከፈተ ቀን ድል አለው፣ በረከትና ስኬት አለው፡፡
▶ ሱብሒ ላይ የሚተኛ የሸይጣን ምርኮኛ ነው፤ ለሸይጧን ጆሮ የሠጠ ነው፡፡ አልነጋም ተኛ ይለዋል፡፡
የሱብሒ ጊዜ እንዴት ያማረ ጊዜና ዉብ ሰዓት መሠላችሁ!
☞ የሱብሒ ሶላት ሱንናው በዱንያ እና በዉስጡ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
☞ የሱብሒ ሶላት ግዴታው የአላህን ጥበቃና ዋስትና ያስገኛል፡፡
በርግጥም «አሶላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም'ን» እየሰሙ «ሐይየ ዐላ ሶላህ፣ ሐይየ ዐለል ፈላሕ'ን» እያዳመጡ መተኛት ይከብዳል።
ወዳጆቼ ለይል ቢያቅተን አሁን ላይ ሆነን ሱብሒን ብናስብ ምን ይለናል!?

«አንቱ ሰው ከሚወዱት ሰው መለያየት የበለጠ ምን የሚያሳምም ነገር አለ?»
«አላህን ማጣት! »
« እንዴት! »
« ጌታህን ለመጠየቅ ቁዋ እንደማጣት ህመም፣ በሰዎች ተከበህ ለጌታህ ባይተዋር እንደመሆን አስከፊ ስቃይ የለም። የኔ ልጅ የምትወዳቸውን ተለይተህ አላህን ካላጣህ ከህመምህ ትገዝፋለህ። ከምትወዳቸው ጋር ሆነህ የምትወዳቸውን የሰጠህን ካጣህ ግን በእርግጥም ህመምህን መግለጫ ምንም አታገኝም።
የኔ ልጅ የሚለይህን ማጣት ያቆስልሀል፣ ከማይለይህ መተጣጣት ግን ትርጉም አልባ ያደርግሀል።»
« አንቱ ሰው እወዶታለሁ! »
« ከጌታህ ከሚያራርቁህ ነገሮች ጌታዬ ይጠብቅህ!

ቀደምቶች እነዚህ ናቸዉ አንቺስ...ነፍሴ
abdu shikur abu fewzan
ቀደምቶች እነዚህ ናቸዉ አንቺስ...ነፍሴ!?
🎙አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን
🎙አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን