Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ወንድማችንን መርሳት ቀላልና ተራ በደል አይደለም! ከባድ ቅጣትን የሚያስከትል ነው እንጂ፡፡ መክሊቱን የቀበረው ሰው ሁኔታ ይህን ያረጋግጥልናልና፡፡ ይህ ሰው በራሱ ሕይወት አልተነቀፈም፣ ምክንያቱም ስለ ተቀበለው አንድ መክሊት አልተወቀሰም፤ የተሰጠውን መክሊት እንዳለ ሳያበላሽ አስረክቧልና፡፡ ነገር ግን የተሰጠውን በአግባቡ ተጠቅሞ ሥራ ላይ ባለ ማዋሉና ባለ ማትረፉ በጌታው ተቀጣ።

ከዚህ የምንረዳው ምንም እንኳ ራሳችን ቅኖችና እንደሚገባ በአግባቡ የምንኖር ብንሆንና ቅዱስ ቃሉን ለመስማት ጥልቅ ፍቅር ቢኖረን እንኳ ለመዳናችን ይህ ብቻ አይበቃንም። የተሰጠን መክሊት ሊበረክት ይገባዋልና፣ መክሊታችን የሚበዛውም ከራሳችን ድኅነት ጋር ለሌሎች ድኅነት የሚሆን የሚቻለንን ነገር ስናደርግ ነው፡፡ በምሳሌ የተነገረው ሰው «እነሆ መክሊትህ አለልህ።» ማለቱ ራሱን ከጌታው ቁጣና ቅጣት ሊያድነው አልቻለምና፤ «ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው ይገባህ ነበር›› ተባለ እንጂ። (ማቴ. 25÷27።)

የጌታ ትእዛዝ እንዴት ቀላል እንደ ሆነ ትመለከቱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ ገንዘብ የሚያበድሩ ሰዎች ተበዳሪው ለማንም ያበድረው፣ ምንም ይሥራበት፣ የሚፈልጉት የተዋዋሉትን ወለድ ማግኘታቸውን ብቻ ነው፡፡ ተበዳሪው እንዳሰበው ማትረፍ ባይችል ይህ ለአበዳሪዎቹ ጉዳያቸው አይደለም፤ ያስያዘውን ሀብት ንብረትም ቢሆን ሽጦ እንዲከፍል ያደርጉታል እንጂ፡፡ እግዚአብሔር ግን እንዲህ አያደርግም፡፡ ከእኛ የሚፈልገው ለለዋጮች አደራ እንድንሰጥ ብቻ ነው፣ ከዚያ በኋላ ለሚከሠተው - ለትርፉ መጠን፣ አደራ የተሰጣቸው ሰዎች ስለ መመለስ አለመመለሳቸው ጉዳይ የእኛ ኃላፊነት አይደለም፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የሚናገረው ሰው መምከር እንጂ ማሳመን አይችልምና፡፡

ስለዚህም «እናንተን የምጠይቃችሁ አደራ ስለ መስጠት እንጂ ስለ ትርፉ መጠን አይደለም።» አለን:: ከዚህ የቀለለ ኃላፊነት ምን አለ? ሆኖም ያ አገልጋይ ጌታውን «ጽኑና ጨካኝ» አለው፡፡ ሰነፎችና ውለታ ቢሶች እንዲህ ናቸውና፤ ሁል ጊዜ የራሳቸውን ስህተትና ድካም በጌታቸው ማሳበብ ይወዳሉ:: ስለዚህም ይህ ሰው ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ ተጣለ፡፡

እኛም ይህ ቅጣት እንዳያገኘን ቢቀበሉትም ባይቀበሉትም በወንድሞቻችን ልቡና የምንችለውን ያህል ምክርና የእግዚአብሔር ቃል እናስቀምጥ፡፡ ቢቀበሉት ራሳቸውንም እኛንም ይጠቅማሉ፤ ባይቀበሉት ግን ራሳቸው የማይቀርላቸውን ቅጣት ይቀበላሉ፤ የእነርሱ አለማመን ግን በእኛ ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሊያደርስብን አይችልም። ምክር በመስጠት የራሳችንን ድርሻ ተወጥተናልና፤ ባይሰሙ ግን በመናገራችን የምንጎዳው አንዳች ነገር የለም፡፡ ባለ መምከራችንና ባለ መናገራችን እንጂ ባለ መሰማታችንና ማሳመን ባለ መቻላችን የሚያሳፍር ነገር የለምና፡፡


════• |❀:✧๑♡๑✧❀|:  ══════
✞✞✞❀
ምክረ አበው ወእማት ❀✞✞✞
════• ೋ•✧๑♡๑✧•  ══════
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❀✞ምክረ አበው ወእማት✞❀
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሰው ልጅ ለገንዘብ መገዛት የለበትም። ነገር ግን በሕይወት ለመቆየት ገንዘብ የግድ ያስፈልገዋል። አሁን በዚህ ዘመን እኛ ኦርቶዶክሳውያን በጣም እየተገፋን ያለነውም በEconomy(ገንዘብ) ስለደከምን ጭምር ነው። ስለዚህ በገንዘብ አቅም መጎልበት እና መጠንከር ይገባናል።

በቅርብ ያለ ወዳጄ crypto ላይ እየሠራ ያለምንም ልፋት ወደ 13,000 የሚጠጋ ብር አግኝቷል። እንዲሁም እስከ 25,000 ብር የሠሩም አሉ። ስለዚህ ወንድሞቼ እና እኅቶቼ እናንተም የቻላችሁትን ያህል dollar በመሰብሰብ እናንተም እንድትጠቀሙ ወንድማዊ ምክሬን እለግሳችኋለው።

በተረፈ አዳዲስ መረጃዎች ሲኖሩ ከዚህ ሥር ባለው channel እልክላችኋለው።
በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ 🙏

👇👇👇(Join በሉት)

Sheger Crypto
❀✞ ለምን ታስባለህ? ❀✞

ምእመን ወዳጄ ሆይ ማኅተመ ወልድ ያለህ፤
✞ ፈቃድህ ከሆነ እስኪ ልጠይቅህ፤
ካንተ አልፎ ለሁሉ እስኪታይ ጭንቀትህ፤
✞ ለምን ታስባለህ ስለ ወደፊት ነገህ፤
ረሳኸው እንዴ ጌታህ ምን እንዳለህ፤
✞ እስቲ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤
አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ ከጎተራ አይከቱ፤
✞ ይሁን እንጂ ይመግባቸዋል የክርስቶስ አባቱ፤
ከእነርሱማ እናንተ እጅግ ትበልጣላችሁ፤
✞ ስለዚህ ይብቃ! ይብቃ ጭንቀታችሁ፤
ነገን ስታስቡም ዛሬን አታባክኑ፤
✞ ይልቁን ሥሩባት ዛሬን አሁኑኑ።
አይዘሩም ሲል ደግም ጌታህ እግዚአብሔር፤
✞ ከድንጋይ እንዳትገኝ ጸጉርህን ስትቋጥር፤
አይበሩም አላለህምና ክርስቶስ ሲናገር፤
✞ አንተም አሁን በመነሳት በሀገር ሁሉ ብረር።

ግጥም - ዲ/ን ተክለ አብ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/29 16:58:53
Back to Top
HTML Embed Code: