Telegram Web
ሞዴል ፈተና አስመልክቶ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ

• ለ አዲሰ አበባ ተማሪዎች ብቻ በአ.አ ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀው የ 12ኛ ና 8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ነገ ጥዋት ይጀምራል።

• ይህ ፈተና ተማሪዎች ምን ያህል ለብሄራዊ ፈተና ተዘጋጅቷል የሚለውን ለመገምገም ብቻ የተዘጋጀ ነው። በዚሁ አጋጣሚ የአ.አ ተማሪዎች ሆነው ስልክ ያሌላቸው ተማሪዎች ፈተናው ግዴታ አይደለም በሉልኝ።

•የ ሞዴል ፈተናውን ማንኛውም ከአ.አ ውጪ ያሉ ተማሪዎችም መፈተን ይችላሉ። ነገር ግን መልሱን ለራሳችሁ በመያዝ መልሱ ሲመጣ ለራሳችሁ እርማት ትሰጣላችሁ።

• የፈተናውን ጥያቄዎች እዚው 🏢በትምህርት ሚንስቴር 🌎 ቴሌግራም ቻናላችን በሰዓቱ ታገኛለችሁ።

ከነዚህ ውጭ ያሉ ጥያቄዎች ካሉ ጠይቁ።
#ቻናላችነን🇪🇹 ላልገቡ በአፋጣኝ share አርገው ፈተናው ሊሰጥ ደቂቃዎች ቀርተዋል እና። #ያስገቡአቸው

👉 https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAE0QKKtUOAYfYSfXug
AFAAN ORO.MODEL AFAAN OROMOO K 8.pdf
231 KB
ቀን 13/ 09 / 2012 ዓ/ም

Biiroo Barnoota magaalaa finfinneetti Qormaanni afaan oromoo kutaa 8ffaa waan gadhiifameef baratoonni akka hojjattan beeksisaa, maatiin barattootaa deeggarsa akka taasiftan.
@timhirt_minister
@timhirt_minister
THURSDAY , 21 05 2020 , Tv schedule
@timhirt_minister
@timhirt_minister
ቀን 13 / 09 / 2012 ዓ/ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ የ 12ኛ ክፍል ባዮሎጂ ወይም ኢኮኖሚክስ ሞዴል ፈተና ከ 5 ደቂቃ በሃላ የሚቀርብ በመሆኑ ተማሪዎች ተገቢዉን ዝግጅት በማድረግ እንድትጠብቁ እየጠየቅን ለፈተናዉም 3 ሰሃት የተሰጣችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
@timhirt_minister
@timhirt_minister
BIOLOGY MODEL EXAM GRADE 12_.pdf
374.7 KB
ቀን 13 / 09 / 2012 ዓ/ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ የ 12ኛ ክፍል #ባዮሎጂ ሞዴል ፈተና እንደሚከተለዉ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎች እራሳችሁን እንድትፈትሹበትና ወላጆችም ተገቢዉን እገዛ እንድታደርጉላቸዉ እና በአግባቡ ፈተናዉን መውሰዳቸዉን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን
@timhirt_minister
@timhirt_minister
ECONOMICS MODEL EXAM GRADE 12.pdf
181.3 KB
ቀን 13 / 09 / 2012 ዓ/ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ የ 12ኛ ክፍል #ኢኮኖሚክስ ሞዴል ፈተና እንደሚከተለዉ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎች እራሳችሁን እንድትፈትሹበትና ወላጆችም ተገቢዉን እገዛ እንድታደርጉላቸዉ እና በአግባቡ ፈተናዉን መውሰዳቸዉን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን፡፡
@timhirt_minister
@timhirt_minister
ለተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የትምህርት በቤቴ የጥያቄና መልስ ውድድር የሽልማት መርሐ ግብር በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የአፍሪኸልዝ ቴሌቭዥን ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሜሎን በቀለ በተገኙበት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
@timhirt_minister
@timhirt_minister
የ12ኛ ክፍል ፈተና ዕጣ ፈንታ!

የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዕጣ ፈንታ ምን ይሁን፣ ፈተናው በተያዘው ዓመት ይሰጥ ወይስ ይተላለፍ የሚለው ውሳኔ ከፌደራሉ መንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መግለጹን አሐዱ ቴሌቭዥን ዘግቧል

እንደሥራ ኃላፊዎቹ መረጃ ውሳኔው በ15 ቀናት ውስጥ ይታወቃልም ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን እንደቴሌግራም ባሉ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ማስተማር እንዲቀጥሉ ቢልም ስኬታማ ሆኖ አልቀጠለም፡፡

ከዚህም አልፎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰዎች መሰብሰብ መከልከልም ተማሪዎች ቢዘጋጁ እንኳን ፈተናው በምን አግባብ ይሰጣል የሚለውን ምላሽ አልባ አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተናዎችን በቴሌግራም ገፁ አውጥቶ ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲፈትሹ እያደረገ ነው፡፡
@timhirt_minister
@timhirt_minister
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካደዳሚክ ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት፤ዶ/ር ኢን/ ፍስሃ ጌታቸው በኮቪደ-19 ወረርሺኝ ምክንያት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ሂደት በተመለከተ ፦

• የ PhDት/ት ሙሉ በሙሉ በኦንላየን የሚቀጥል ይሆናል፡፡

• የመመረቂያ ጥናታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ያሉ የ PhD እና የማስተርስ ተማሪዎችም ከት/ት ክፍሎች እና አማካሪዎቻቸው ጋራ በመነጋገር ከ ሰኔ 29-ሀምሌ 15/2012 ዓ.ም ጥናታቸውን የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ሴኔትም ምርቃታቸውን በማፅደቅ የት/ት ሰነዳቸው የሚዘጋጅላቸው ይሆናል፡፡

• ኮርስ በመውሰድ ለይ የነበሩ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎችን እና የቅድመ ምረቃ (under graduate) ተማሪዎችን በተመለከተ፤ መምህራኖቻቸው በዩኒቨርሲቲው Student Information System(SIS) ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ውጤታቸውን ለመመልከት በሚጠቀሙበት user name እና password በመግባት መምህራኖቻው የሚያስቀምጡላቸውን የማስተማሪያ ሰነድ እያነበቡ እንዲቆዩና፤ ወደ ት/ት በሚመለሱ ሰዓት የአጭር ጊዜ ማካካሻ ት/ት ወስደው ፈተና በመፈተን ወደ ሚቀጥለው ሴሚስተር የሚሸጋገሩ ይሆናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዩኒቨርሲተው የSMS መላኪያ 8232 የተላከላቸውን የብሄራዊ ቤተ መፃሕፍት Link መጠቀም ይችላሉ፡፡

የሚሰጡ መመሪያዎችን በአግባቡ በመተግበር እራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንከላከል!
@timhirt_minister
@timhirt_minister
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ የተላለፈ መልዕክት

በቀጣይ የሚኖረው የመማር ማስተማር ጊዜን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው ዝርዝር አካሄድ አውጥቷል፡፡

በመሆኑም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችም ሆነ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ከላይ በፎቶው ላይ የቀረበውን እንድታነቡ እና በመመሪያው መሰረት ዝግጅት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

የ2012 ሁለተኛ ሴሚስተር እና የ2013 የትምህርት ዘመን እጅግ በጣም አጭር ስለሚሆን ተማሪዎች እንዳትዘናጉ ተብላቹሃል !!!

#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ
@timhirt_minister
@timhirt_minister
👆ቀን 14/09/2012
የዛሬ የትምህርት ፕሮግራም
@timhirt_minister
@timhirt_minister
CIVIC MODEL EXAM GRADE 12 .pdf
302 KB
ቀን 14 / 09 / 2012 ዓ/ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ የ 12ኛ ክፍል ሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ሞዴል ፈተና እንደሚከተለዉ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎች እራሳችሁን እንድትፈትሹበትና ወላጆችም ተገቢዉን እገዛ እንድታደርጉላቸዉ እና በአግባቡ ፈተናዉን መውሰዳቸዉን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን::
2025/07/10 12:22:10
Back to Top
HTML Embed Code: