Telegram Web
እ.ኤ.አ. በ2023 በትምራን በተደረገው ጥናት ሴቶች በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ውስጥ በጣም አናሳ እንደሆኑ ያሳያል። ይህም በዳኝነት 18% ብቻ ሲሆኑ፣ ይህም በርካታ ቦታዎች በወንዶች መያዛቸውን ያሳያል። እነዚህ ግኝቶች ይበልጥ አሳታፊ የሆነ፣ ሥርዓተ-ጾታ-የተመጣጠነ የፍትሕ ዘርፍ አስፈላጊነትን ያጎላሉ።

በዚህ ዐውድ፣ ትምራን ትርጉም ያለው የሴቶችን መሪነት ማምጣት በወሳኝ ዘርፎች ውስጥ ውክልናን በማረጋገጥ እንደሚጀምር በመገንዘብ በሕግ ዘርፍ ውስጥ ወደ አመራር እየገፉ ያሉትን ሴቶች ማጉላት አስፈላጊ እንደሆነ ታምናለች፡፡ ሴቶችን ወደ ጠበቆች ማኅበር አመራር ምርጫ ያሳዩትን ተነሣሽነት በእጅጉ ታበረታታለች፡፡ ይህ በዘርፉ የሚታየውን የሴቶች ተሳትፎ እና መሪነት ክፍተቶችን ለመፍታት እና የበለጠ ያሳተፈ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት ወሳኝ እርምጃ ነው።

በፌዴራል የጠበቆች ማኅበር አመራር የሥራ መደቦች ውስጥ የሚከተሉት ሴቶች በእጩነት ቀርበዋል።

ለፕሬዚዳንት፡-
• መሠረት አያሌው
• መሠረት ሥዩም

ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፡-
• ጀሚላ ክብረት
• ቤዛ ንጉሤ
• ማሪያ ካሕሣይ

ትምራን ከእነዚህ ሴት መሪዎች ጋር በድጋፍ በአንድነት እንድንቆም ታበረታታለች።
👏21
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበርን ለመምራት የሚወዳደሩ ሴቶች ሐሳቦቻቸውን የሚያቀርቡበት መድረክ ተካሄደ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበርን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም በሥራ አስፈጻሚነት ለመምራት የሚወዳደሩ ሴቶች ሐሳቦቻቸውን የሚያቀርቡበት መድረክ ታኅሣሥ 02 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተካሄደ።
መርሐ ግብሩ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እና ውሳኔ ሰጭነት ሚና እንዲጎልበት ለማድረግ ዓላማ ሰንቃ በምትንቀሳቀሰው ትምራን የተሰኘች ሀገር በቀል የሲቪክ ማኅበር እና የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር ትብብር የተዘጋጀ ነው።
በመድረኩ ላይ የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የትምራን ቦርድ አባል መስከረም ግርማ፣ ትምራን ላለፉት አምስት ዓመታት ሴቶችን ለአመራርነት ለማብቃት ስትሠራ መቆየቷን ገልጸው፣ የዕለቱ መርሐ ግብር በጥብቅና ሞያ ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ለአመራርነት እንዲመረጡ ለማስቻል ሐሳባቸውን የሚገልጹበት መድረክ ነው ብለዋል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ ኅብረት አባሆይ በበኩላቸው፣ ማኅበራቸው ሴት የሕግ ባለሞያዎችን ከተለማማጅነት ጀምሮ በማሳደግ ለተለያዩ ሓላፊነቶች እንዲበቁ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው፣ በመድረኩ ላይ ለዕጩነት የቀረቡት ሴት ተወዳዳሪዎች በኢትዮጵያ የሕግ ሞያ ውስጥ ሴቶችን የማብቃት እንዲሁም ዘርፉ ለወንዶችም፣ ለሴቶችም ምቹ እንዲሆን የማድረግ ሓላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።
በመድረኩ ላይ ቁልፍ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር ቦርድ አባል እና የኮቨናንት የጥብቅና ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ኅትመት አሰፋ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበርን ለመምራት ወደፊት የመጡ ሴት ጠበቃዎች የሚገጥማቸውን ማንኛውም ውጣ ውረድ አልፈው ለዚህ ደረጃ በመብቃታቸው አመስግነዋል። ለፕሬዚዳትነትም ሆነ ለሥራ አስፈጻሚነት የሚወዳደሩ ተመራጮች በሀገሪቱ የሕግ ዘርፍ ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ የማምጣት ሓላፊነት የተጣለባቸው መሆኑንም ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ለማኅበሩ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩት መሠረት አያሌው እና መሠረት ስዩም እንዲሁም ለሥራ አስፈጻሚነት የሚወዳደሩት ጀሚላ ክብረት፣ ቤዛ ንጉሤ እና ማርያ ካሕሣይ ሐሳቦቻቸውን ለኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር አባላት አቅርበዋል።
በፍትሕ ዘርፉ የሴቶች አመራርነት፣ ታማኝነት እና ቁርጠኝነት ሁሉን አካታች የሕግ ከባቢ እንዲኖር በማድረግ ጠንካራ ድምፅ ይፈጥራል።
የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 እንዲሁም የተጠቀሰውን ዐዋጅ ለማሻሻል በወጣ ዐዋጅ ቁጥር 1394/2017 መሠረት ለዕጩነት የሚያበቁት መሠረታዊ መመዘኛዎች ምንድን ናቸው?
ዕጩ #የሴት_ጠበቃዎች ትውውቅ ተካሄደ
- ነገ ቅዳሜ የመጨረሻው ምርጫ ይደረጋል፣
ከዕዝራ እጅጉ (ተወዳጅ ሚድያ)
የኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበርን በፕሬዚዳንትነት እና ሥራ አስፈፃሚነት ለመምራት የሚወዳደሩ ዕጩ ሴት ጠበቆች ናቸው ትምራን ባዘጋጀው የትውውቅ መርሀ-ግብር ላይ ስለማንነታቸው መግለጫ የሰጡት።
ዕጬዎቹ ራሳቸውን ሲያሰተዋውቁ የከረሙ ሲሆን ቅዳሜ ታህሳስ 4 /2018 ዓ.ም በግራንድ ኤሊያና ሆቴል በሚደረገው የመጨረሻ የድምፅ አሰጣጥ የማህበሩ መሪዎች ይታወቃሉ።
ለመሪነት ብቁ የሆኑ ሴቶችን በመደገፍ የሕግ ዘርፉን መጻኢ ገፅታ ለመለወጥ እንተጋለን በሚል መርህ በተዘጋጀው መርሀ-ግብር ላይ አምስት እጩዎች የሠሩበትን የሥራ ሂደትና እጩ ሆነው በቀረቡበት የሥራ ኃላፊነት ላይ ለመሥራት የተዘጋጁበትን ዓላማና ቁርጠኝነት ለትምራን አባላት፣ ለሙያ አጋሮቻቸው የኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበርና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች አቅርበዋል።
ታህሳስ 2/2018 በአያ ሆቴል በተካሄደው መርሀግብር ለፕሬዘዳንትነት የሚወዳደሩ መሠረት አያሌው እና መሠረት ስዩም እንዲሁም ለሥራ አስፈፃሚነት የሚወዳደሩት ጀሚላ ክብረት፣ቤዛ ንጉሴና ማርያ ካህሣይ ናቸው ሐሳቦቻቸውን ያቀረቡት።
ዕጩዎቹ ራሳቸውን ከማስተዋወቃቸው አስቀድሞ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ እትመት አሰፋ ከሰፊ ልምዳቸው ያካፈሉ ሲሆን ዕጬዎቹ ቢመረጡ ህዝብን ማገልገል እንዳለባቸው ገልፀዋል። አክለውም ሴቶች ቦታና አጋጣሚ ካገኙ ማገልገል የሚችሉበት ዕድል መኖሩን በመጠቆም ለሴት ጠበቆቹ መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።
ካሳለፉት የሥራ ቆይታና ተሞክሮ በመነሳት ሌሎች ሴቶች ላይ የሚደርስ ውጤታማ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ የገለፁት ዕጩዎቹ ሴት እህቶቻችን በሁሉም አቅጣጫ የላቁ ሆነው እንዲገኙ ማገዝ እንደሚሹ አንስተዋል። በበጎ ፈቃደኝነት፣ በትጋት፣ በመተባበር፣ በጎ ተፅዕኖ ማሳደርና ተሰሚነትን ከፍ ማድረግ ብሎም ሚዛናዊ አሰራርን መዘርጋት ላይ በትኩረት እንሠራለን ያሉት ዕጩ ሴት ጠበቆች ሥነምግባር ያላቸው፣ ሥራቸውን የሚያከብሩ ሙያተኞችን ለማፍራት ያላቸውንም ዝግጁነት አስታውቀዋል።
ቅዳሜ ታህሳስ 5/2018 ዓ.ም በሚደረገው የድምፅ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት መሳተፍ የሚችሉት የጥብቅና ፍቃድ ያላቸው ጠበቆች ሲሆኑ ዕጬዎቹ ከዛሬ ታህሳስ 4/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከነገ 2:30 የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን ማድረግ ይችላሉ።
የትውውቅ መርሀ-ግብሩን ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር ያዘጋጀችው ትምራን በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የምዝገባ ቁጥር 4834 የተመዘገበችና ሴቶች በሀገሪቷ ውስጥ በሚኖሩ እንቅስቃሴዎች ላይ ውሳኔ ሰጪና እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ የምትሠራ ሀገር በቀል ድርጅት ነች። ብቃት ያላት ጠንካራ ፖለቲከኛና መሪ ሴቶችን በቁጥር በዝተው እንዲገኙሜፈመ እየሠራች ትገኛለች። ዓላማዋ እንዲሳካም የሴቶችን አቅም በመገንባት፣ ሴቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡ የመደገፍ ሚናዋን እየተወጣች ትገኛለች።
በፍትህ ዘርፉ የሴቶች አመራርነት፣ ታማኝነት እና ቁርጠኝነት ሁሉን አካታች የሕግ ከባቢ እንዲኖር በማድረግ ጠንካራ ድምፅ ይፈጥራል። ሴቶችን ለአመራርነት መምረጥ ፍትህን ያጠናክራል፣ ውክልናን ያሻሽላል ብሎም የሕግ ዘርፉ ያለበትን ማኅበረሰብ እውነታ እንዲወክልም ዕድል እንደሚፈጥር ይታወቃል።
ይህን የምርጫ ቅስቀሳ እንዲደረግና መርሐ ግብሩ ዕውን እንዲሆን ሐሣቡን ያመነጩት ጠበቃ ቤዛ ሸዋንግዛው በፌደራል ፍርድቤቶች ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ሲሆኑ እርሳቸውም የትምራን ሲቪክ ማህበር ምክትል ሰብሳቢ እና ትምራንን ከመሠረቱት አንዷ ናቸው።ጠበቃ ቤዛ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር አባል ሲሆኑ በመርሐ- ግብሩ ላይም ይህን በጎ ሀሣብ በማፍለቃቸው በዕለቱ ምሥጋና ተቸሯቸዋል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ሁሉም የፌደራል ጠበቆች በአስገዳጅነት አባል የሚሆኑበት ሲሆን ከተመሠረተ ከ3አመት በላይ ያስቆጠረ ነው። ከ5000 በላይ አባላቶችም አሉት።
#ስለተወዳዳሪዎቹ:-
📌 ጠበቃ መሰረት አያሌው
የሕግ ባለሙያ መሆንን የልጅነት ህልሟ አድርጋ ያደገች ሲሆን፣ በሕግ የመጀመሪያ ድግሪን ከጅማ ዩኒቨርሲቲ እና በፖለቲካል ሳይንስ ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝታለች። በፍርድ ቤት በረዳት ዳኝነትና በዋና ሬጅስትራርነት ያገለገለች ሲሆን፣ በሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ሥራ አስፈፃሚነትና ም/ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም የጠበቆችን ደንብ በማሻሻል ሂደት በኮሚቴነት በንቃት ተሳትፋለች። ለፕሬዚዳንትነት ያቀረበችው ዋናው እይታ “እንደ ባለሙያ መከበር ሙያውን ማክበር”
" የሚል ሲሆን፣ ጠንካራ ማኅበር በመፍጠር የሙያውን ክብር ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መሆኗንም ገልጻለች።16 ዓመት የሥራ ልምድም አላት።
📌 ጠበቃ መሰረት ስዩም
በሕግ ማማከር እና ጥብቅና አገልግሎት ከ17 ዓመታት በላይ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ልምድ አላት። የማኩታ የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት መስራችና ማኔጂንግ ፓርትነር ስትሆን፣ በበርካታ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ፕሮጀክቶች ላይ አማክራለች። በአንካራ ዲክላሬሽን ፈራሚ ከሆኑ 11 የሕግ ልሂቃን ብቸኛዋ አፍሪካዊት ጠበቃ ስትሆን፣ የሪፎርም አማካሪ ጉባኤ አባል በመሆን በርካታ አዳዲስ ህጎች (እንደ ጸረ-ሽብር፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የንግድ ህግ፣ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት እና የፌዴራል ጥብቅና አዋጆች) እንዲረቀቁ የበኩሏን አበርክታለች። ለፕሬዚዳንትነት ከተመረጠች የአባላትን መብት ማስከበር፣ አቅም ማጎልበት፣ ገቢ ማሳደግ እና ጠበቆች በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ ያላቸውን ሚና ማጎልበት ላይ እንደምትሠራ ቃል ገብታለች።
📌 ጠበቃ ማሪያ ካህሳይ ገብረጊዮርጊስ
የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪዋን በሕግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኘች ሲሆን፣ በጠቅላላው ለሰባት ዓመታት በዳኝነት (በመጀመሪያ ደረጃና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ረዳት ዳኝነትና ዳኝነት) አገልግላለች። ከዚያም ወደ ግል ዘርፍ በመዛወር ከአስራ አራት ዓመታት በላይ በጠበቃነት ልምድ ያካበተች ሲሆን፣ ከስምንት ዓመታት በላይ ደግሞ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ነጻ የሕግ ድጋፍ በመስጠት ማኅበራዊ የሙያ ኃላፊነቷን ተወጥታለች።
📌 ጠበቃ ወ/ሮ ቤዛ ንጉሴ ደምሴ
በሕግ የ18 ዓመታት ልምድ ያላት ሲሆን፣ ከተመረቀች በኋላ በጋዜጠኝነት፣ ከዚያም በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሕግ ኤክስፐርትነት እና ረዳት ዳኝነት አገልግላለች። በፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ፣ የመጽሄት አዘጋጅ እና የጾታ ጉዳዮች ም/አስተባባሪ በመሆን የላቀ ተሳትፎ አድርጋ የአመቱ ምርጥ ሰራተኛ ተሸላሚ ሆናለች። በመቀጠልም ለ11 ዓመታት በፍርድ ቤቶች ጥብቅና ሰጥታለች። በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና ዋና ፀሀፊነት፣ እንዲሁም በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሕግ አማካሪ ጉባኤ ውስጥ አባል በመሆን አገልግላለች።
📌 ጠበቃ ወ/ሮ ጄሚላ ክብረት
በሕግ ሙያ የ16 ዓመታትና በጥብቅና ሙያ ደግሞ የ10 ዓመታት ልምድ አላት። በዓለም አቀፍ የኢንሹራንስ ኩባንያ የሕግ ክፍል ኃላፊነትና ለዘጠኝ ዓመታት የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር በመሆን በአመራር አገልግላለች። እንዲሁም የዘምዘም ባንክ የመጀመሪያ የምርጫና የሹመት ኮሚቴ ሊቀመንበር በመሆን የሥራ አመራር ብቃቷን አሳይታለች። የጀሚላ ክብረት እና አጋሮች (JKP) መስራችና ማኔጂንግ አጋር ስትሆን፣ ድርጅቷን በኮርፖሬትና በፋይናንስ ዘርፍ የሕግ አማካሪነት በመምራት ላይ ትገኛለች። ሥልጠናዎችን በለንደንና
በአሜሪካ በመከታተል እንዲሁም በእስላማዊ ፋይናንስ ልዩ የምስክር ወረቀት በማግኘት ዓለም አቀፍ ልምዶችን ከኢትዮጵያ አውድ ጋር አዋህዳለች።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበርን በፕሬዚዳንትነት እና ሥራ አስፈጻሚነት ለመምራት የሚወዳደሩ ዕጩ ሴት ጠበቆችን እናስተዋውቃችሁ!
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ 2018 ባደረገው ጥናት እንደሚያሳየው ከሴቶች ፈራሚዎች ጋር የሚደረጉ የሰላም ስምምነቶች ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆዩ እና ጠንካራ አፈጻጸም የሚያሳዩ ናቸው።
A United Nations 2018 research shows that peace agreements with women signatories last longer and achieve stronger implementation.
#Womenleadpeace hashtag#Womendefendpeace
#16daysofactivism
#WPS #TIMRAN@5 #Sheleadspeace
👍1
2025/12/13 02:44:24
Back to Top
HTML Embed Code: