Telegram Web
እንቁላሉን? 😱

👉 @Tafakur_mastenten 👈
ቁመተ - ሎጋዋ ይላታል ዘገባው፡
እቅጩን ለመናገር 1 ሜትር ከ91 ሳንቲሜትር ትረዝማለች፡፡
ክብደቷ ከአነስተኛ መኪና፣ ቁመቷ ደግሞ የማይክል ጆርዳንን የሚያክል የሚበልጥ ላም በሀገረ አውስትራሊያ

በአውስትራሊያ የምትገኘውና ኒከርስ የተባለችው ግዙፍ ቡሬ ላም የመገናኛ ብዙሃን ርዕሰ ዜና ሆና ሰንብታለች፡፡
ላሚቱ ቁመቷ ከዝነኛው አሜሪካዊ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማይክል ጆርዳን ቁመት ጋር እኩል ነው፡፡ እቅጩን ለመናገር 1 ሜትር ከ91 ሳንቲሜትር ትረዝማለች፡፡
ክብደቷም ቢሆን ከአነስተኛ መኪና አይተናነስም፤ ይበልጥ እንደሁ እንጂ፡፡ ቡሬይቱ ላም 1400 ኪሎ ግራም ትመዝናለች፡፡
ባለቤትነቷ የምዕራብ አውስትራሊያዊው ሰው የጆፍ ፒርሰን ነው፡፡ ፒርሰን የቁም ከብቶችን ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ የእርባታ ድርጅት አለው፡፡
ይህ ሰው ለኤቢሲ ኒውስ እንደተናገረው ኒከርስን በክብደቷ ምክንያት ኢክስፖርት ሊያደርጋት አልቻለም፡፡ ድርጅቱ በየጊዜው ብዙ ከብቶችን እየገዛ የሚሸጥ መሆኑም ኒከርስን እድለኛ አድርጓታል፡፡
ይህ ማለት ግን ኒከርስ ረብ-የለሽ ሆናለች ማለት አይደለም፡፡ ፒርሰን እንደሚለው ከሆነ ላሚቱ ለከብት እርባታ ድርጅቱ ትልቅ ፋይዳ አላት፡፡
ከብቶቹ በሙሉ የሚንቀሳቀሱት ቁመተ-ሎጋዋን ኒከርስን አጅበው ነው፡፡ ይህም ለግጦሽ በሚሰማሩበት ጊዜ በቀላሉ የት እንዳሉ ለማወቅ ያስችለናል ብሏል ሚስተር ፒርሰን፡፡
ምንጭ፡- ኢቢሲ

👉 @Tafakur_mastenten 👈
ውሻን ለምትፈሩ ሰዎች 😁
የባሰ ማስደንበርያ 😳
በማይቀለደው ?😱

👉 @Tafakur_mastenten 👈
እሁድን በ እንጦጦ ፓርክ ፈታ እያልን ነው 😎

እናንተስ ?
🐇 ወንዱ ጢንቸል ሚስቱን ለሌሎች የሚያስተዋውቀው ላይዋ ላይ ሽንቱን በመሽናት ነው::

ምንጭ :- የዕውቀት ማህደር

👉 @Tafakur_mastenten 👈
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጉሬዛ

ጉሬዛ ዛፍ ላይ የሚኖር እንስሳ ነው፡፡ በግንባሩ፣ በጉንጮቹና በአገጩ ላይ ነጭ ፀጉር አለው፡፡ በጅራቱ ጫፍና በጎኑ ነጭ አለው፡፡ በተረፈ ፀጉሩ ጥቁር ነው፡፡ ዋነኛ ምግቡ ቅጠላ ቅጠሎችና፣ በተጨማሪም ፍራፍሬዎች ነው፡፡ ጉሬዛዎች ብዙውን ጊዜ የሚበሉት ቅጠል ሲሆን፣ አንዳንዴ ያልበሰሉ ፍሬዎችና እንቡጦች ሲያገኙም ይበላሉ፡፡

የመኖርያ ክልላቸው ጠባብ ነው፡፡ ምክንያቱም ቅጠል የትም እንደልብ ስለሚገኝና የተወሰኑ ዛፎችን ቅጠል ስለሚበሉ ነው፡፡ በአገራችን ብዙ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ በአብዛኛው ቦታዎች እንደ ጻድቃን ይቆጠራሉ፡፡ ምክንያቱም  ዛፍ ላይ ቅጠላቸውን እየበሉ ነው የሚኖሩት፡፡ እናም፣ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ፣ የተከዙ መስለው ብዙ ሳይንቀሳቀሱ ስለሚታዩና፣ የባሕታዊን የመሰለ እይታ ስላላቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ኢሉባቡር ውስጥ ሰብል ከሚያጠፉ የጦጣ ዘሮች ውስጥ ጉሬዛዎችም የሚጠቃለሉ ሆነዋል፤ እዚያ ጻድቃን የሚላቸው የለም፡፡

👉 @Tafakur_mastenten 👈
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#እርግብ

እርግቦች በተፈጥሯቸው እጅግ ኢምንት Brain Size የተሰጣቸው ፍጡራን ናቸው፡፡ እርግቦች በጭንቅላት እርከን ከእንስሳት መካከል ከውራዎቹ መሐል ናቸው፡፡ ብልጥ ከሚባሉት እንስሣት ከድመት፣ ከውሻ፣ ከአይጥ፣ ከቺምፓንዚ፣ ከዶልፊን፣ ከአሣነባሪ፣ ከካንጋሩ፣ እና ከመሣሠሉት ጋር ሲነፃፀሩ ራሱ – እርግቦች – በቃ የዋህ መባላቸው እውነት ነው፡፡ አላህ ሱ.ወ ለእርግቦች የዋህነትን እንጂ ጭንቅላትን አልፈጠረባቸውማ፡፡ 1.2 ኪሎ ግራም ከሚመዝነው የሰው ልጅ ምጡቅ አዕምሮ ጋር የእርግቦችን ሚጢጢ አዕምሮ ካነፃፀርን – በቃ እኛ ሰዎች – ለእርግቦች – ጌታቸው ነን – ለማለት ይዳዳል፡፡

እርግቦች ጭንቅላት የላቸውም፡፡ ወይም ቴስታታቸው ኔፓ ነው፡፡ ግን ግን አንድ ነገር ልብ በል፡፡ በልጅነቱ እርገቦችን ያረባ፣ አሊያም የእርግቦችን ‹‹ኩኩ መለኮቴ›› ከጣራው ላይ እየሠማ ያደገ ማንም ሰው – የሚያውቀው አንድ ታላቅ የእርግቦች የተፈጥሮ ፀጋ አለ፡፡ የማፍቀር ፀጋ፡፡ እርግብ ሁሉ ያፈቅራል፡፡ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ያለመሰልቸት ቀኑን ሙሉ አንዳቸው የሌላኛቸውን ላባ ሲያክኩ ይውላሉ፡፡ ወንዱ የሴቷን እንቁላል ይታቀፍላታል፡፡ አንዱ ገላውን ሲታጠብ ውሃ በሌላኛዋ ላይ ይረጫል – ለጨዋታ፡፡ አንዱ ምግብ ሲያገኝ በመንቁሩ እየነካካ ሌላውን ይጣራል፡፡ ወንድና ሴት እርግቦች ተሳስመው ውለው ቢያድሩ አይጠግቡም፡፡ በቃ እርግቦች የማፍቀር ፀጋ የተሰጣቸው – ዝም ብለው ለማፍቀር እና ለመፈቃቀር – ፍቅርን ለመስጠትና ለመቀበል ዝግጁ ሆነው የተፈጠሩ – የምድሪቱ ፍቅር እስከ መቃብር ፍጡራን ናቸው፡፡

👉 @Tafakur_mastenten 👈
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
* ጊንጥ ውስኪ ወይም ኮምጣጣ ፈሳሽ ሰውነቷ ላይ ከተንጠባጠበ ህመሙን ስለማትቋቋመው ራሷን በራሷ ታጠፋለች::

👉 @Tafakur_mastenten 👈
#ጥያቄ


- የ ለሊት ወፍ አጥቢ እንስሳ ነች ::

⚫️ እውነት
🔴 ሀሰት
#አርማዲሎስ

የጦር መርከቡ

በቤት ውስጥ ፣ በላቲን አሜሪካ አርማዲሎስ አርማዲሎ ተብሎ ይጠራል ፣ ትርጉሙም “የኪስ ዳይኖሰርስ” ማለት ነው ፡፡ ይህ አገላለጽ ከዚህ እንስሳ ገጽታ ጋር ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ ካለው የሕይወት ቆይታ ጋር ይዛመዳል ፡፡

አርማዲሎስ ከ 55 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በምድር ላይ ታየ ፡፡ ከብዙ ዝርያዎች በተለየ እነሱ በሕይወት ተርፈው ማባዛታቸውን ቀጥለዋል ፡፡ ለመኖር ፣ እንደዚህ ላለው ረጅም ጊዜ ፣ ​​shellል ወይም ጋሻ ረዳቸው ፣ ስማቸው የመጣው።

አርማዲሎ እንስሳ ያልተጠናቀቁ ጥርሶች ትዕዛዝ ናቸው። በእርግጥ የዚህ አጥቢ እንስሳት ጥርሶች ሥሮች እና ኢሜል የላቸውም ፡፡ ውስጠ ግንብ እና የውሻ ቦዮች የላቸውም ፡፡ ዛሬ ወደ 20 የሚጠጉ የጦር መርከቦች አሉ ፡፡ መኖሪያቸው ደቡብ አሜሪካ ሲሆን በደቡብ ሰሜን አሜሪካ የሚኖረው አንድ ዝርያ ብቻ ነው ፡፡

👉 @Tafakur_mastenten 👈
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/11/05 07:50:49
Back to Top
HTML Embed Code: