† በዓለ ጰራቅሊጦስ †
★ ፕሮቴስታንት ይህንን በዓል ከኦርቶዶክስ እንንጠቅ ማለታችሁ ዕብሪተኝነትና ሕገ ወጥነት ነው።★
★ በዓለ ጰራቅሊጦስ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለሁለት ሺህ ዘመናት በካላንደር ስታከብረው የኖረች ከጌታችን ዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው።★
ጰራቅሊጦስ የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡ በዓለ ጰራቅሊጦስ በሌላ ቃል በዓለ ጰንጠቆስጤ በመባልም ይታወቃል፡፡ ይኸውም በግሪክ ቋንቋ በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣ የመከር በዓል) ማለት ነው /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፱፻፮ እና ፱፻፯/፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ፲፪/12ቱ ደቀ መዛሙርት፣ ፸፪/72 ቱ አርድእት፣ ፭፻/500 ባልንጀሮችና ፴፮ቱ/36 ቅዱሳት አንስት በኢሩሳሌም ከተማ በአንድነት ኾነው ለጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ በሚያርግበት ጊዜም «እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ» /ሉቃ. ፳፬፥፵፱/24፥49 ሲል ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ባረገ በ፲ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡
በሐዋርያት ሥራ እንደ ተጻፈው በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ ኹሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጣና የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በኹሉም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ኹላቸውም መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ኹሉ መናገር ጀመሩ /ሐዋ.፪፥፩-፬/2፥1-4 ፡፡ ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ጰራቅሊጦስ ይባላል፡፡
ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ ከ፶ኛው/40፤ ከዐረገ ከ፲ኛው/10 ቀን ጀምሮ እስከሚቀጥለው እሑድ ድረስ ያለው ወቅትም ዘመነ ጰራቅሊጦስ ተብሎ የሚጠራ ሲኾን፣ ይህ በዓል ካህናተ ኦሪት ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ይቀበሉበት ነበርና በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ይባል ነበር፡፡ በበዓለ ጰራቅሊጦስም ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለውበታልና በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ገብቶበታል፡፡
የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብፅ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ኾነው ኹሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው፡፡ የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በ፶/50 ኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚኾነውን በዓለ ሠዊት ያከብሩ ነበር፡፡
ከግብፅ እስከ ከነዓን ምድር የደረሰው የእንስሳት መሥዋዕት ሲጠናቀቅ በ፶ኛው ቀን ይሰባሰብ የነበረው የአይሁድ ጉባኤም መንፈስ ቅዱስ ከወረደበት ዕለት ጀምሮ ተበትኗል፡፡ መሥዋዕተ ኦሪቱ በአማናዊው መሥዋዕት በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም እንደ ተለወጠ ኹሉ ጉባኤ አይሁድም በኢየሩሳሌም ከተማ በተሰበሰቡ በቅዱሳን ሐዋርያት ጉባኤ ተለውጧል (ተቀይሯል)፡፡ ይህችውም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ «ከኹሉ በላይ በምትኾን፣ ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን» እንዳሉ ሠለስቱ ምእት /ጸሎተ ሃይማኖት/፡፡
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጎልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡ ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ከዕብራይስጥ ቋንቋ በተጨማሪ ፸፩/71 ቋንቋዎች ተገልጸውላቸው ምሥጢራትን መተርጐም ጀምረዋል፡፡ ሐዋርያት በየገአሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ ከአይሁድ ወገን አንዳንዶቹም ሐዋርያትን *ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የኾነ ያልኾነውን ይቀባጥራሉ* ይሏቸው ነበር፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ዐሳባቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ « ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ዳሩ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ /ኢዩ.፪፥፳፰/2፥28 ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው » በማለት ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት፣ ምሳሌ የመሰሉለት አምላክ ወልደ አምላክ መኾኑን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መኾኑን እንደሚመሰክሩ በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡
በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም «ምን እናድርግ» ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ ንስሐ ገብተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገራቸው፡፡ በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል /ሐዋ.፪፥፩-፵፩/2 ፥1-41፡፡ ይህም ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ያደረባቸው የማሳመን ጸጋና ተአምራትን የማድረግ ኃይላቸው እንደ በዛላቸው ያመላክታል፡፡
ይህ ዕለት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠበት፤ ብዙ ሺሕ ምእመናን የተገኙበት ዕለት በመኾኑ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን በማለት ይጠሩታል፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት *በዚህች ቀን በሦስት ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና በላያችን ኃይልን ሞላ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው በአዲስ ቋንቋ ተናገርን፤* በማለት በዕለቱ ያዩትንና የተደረገላቸውን፣ እንደዚሁም ስለ በዓሉ ታላቅነት ከመሰከሩ በኋላ ይህንን በዓል ማክበር እንደሚገባ አዝዘዋል፤ በአንጻሩ በዚህ ወቅት (በበዓለ ኀምሳ) መጾምና ማዘን ተገቢ አለመኾኑን ተናግረዋል /ዲድስቅልያ ፴፥፴፰-፴፱፤ ፴፩፥፷፱-፸/ 30፥38-39፤ 31፥ 69-70፡፡
የጰራቅሊጦስ መዝሙርና ምንባባት
በዓለ ጰራቅሊጦስ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲኾን በዕለቱ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሚዘመረው የቅዱስ ያሬድ መዝሙርም ይትፌሣሕ የሚለው የትንሣኤ መዝሙር ነው፡፡ እንደ መዝሙሩ ኹሉ በጰራቅሊጦስ በዓል በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎችም በትንሣኤ ዕለት የተነበቡት ምንባባት ናቸው፡፡
እነዚህም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ፣ በማረጉና መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት በመላኩ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ቈርሶ፣ ደሙን አፍስሶ የሰውን ልጅ ከዘለዓለም ሞት በማዳኑ የሰው ዘር ብቻ ሳይኾን የሰማይ መላእክት፣ የምድር ፍጥረታት ሳይቀሩ ሐሤት እንደሚያደርጉ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም በመንጻቷ የጌታችንን ትንሣኤ በደስታ እንደምታከብር ያስረዳሉ፡፡
ከበዓለ ጰራቅሊጦስ በኋላ ባሉት ሰንበታት (እሑዶች) የሚዘመሩ መዝሙራት ትንሣኤን፣ ዕርገትን፣ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ የሚያስረዱ ሲኾኑ፣ ዓላማቸውም ከሙታን ተለይቶ ለተነሣው፣ አዳምና ልጆቹን ከዲያብሎስ ባርነትና ከሲኦል ላወጣቸው ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ ነው፡፡

ከዚሁ ኹሉ ጋር ለማሳሰብ የምንፈልገው ቁም ነገር በዓለ ጰራቅሊጦስን ተከትለው ሁለት ዐበይት አጽዋማት ይጀመራሉ፡፡ እነዚህም ጾመ ሐዋርያት እና ጾመ ድኅነት (ረቡዕና ዓርብ) ሲኾኑ፣ ቍጥራቸውም ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ ነው፡፡ ስለኾነም ኹላችንም ልንጾማቸው እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ታዝዟል፡፡ ይህም ከቀደሙ አባቶቻችን ጀምሮ የመጣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓት እንጂ እንግዳ ሕግ አይደለም፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚናገሩት በብሉይ ኪዳን ነቢዩ ሙሴ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበለውን ሕገ ኦሪት ለሕዝቡ ከማስተማሩ በፊት ጾሟል /ዘፀ.፴፬፥፳፰/ 34፥28፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም የተስፋውን ቃል መፈጸም እየተጠባበቁ እግዚአብሔርን ውረድ፤ ተወለድ እያሉ ይጾሙ፣ ይጸልዩ ነበር፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ጾም የምግባር መሠረት መኾኑን ሊያስተምረን ወንጌልን ከመስበኩ አስቀድሞ ጾሟል /ማቴ.፬፥፩-፲፩/4፥1-11 ፤ ሐዋርያትም በበዓለ ኀምሳ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ሕገ ወንጌልን ለሕዝቡ ከማስተማራቸው አስቀድሞ ጾመዋል፡፡
እኛም እነርሱን ተከትለን፣ በእነርሱ ሥርዓት በመመራት፣ በሐዋርያት ላይ ያደረው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብት በእኛም ላይ እንዲያድርብን በየዓመቱ ጾመ ሐዋርያትንና ሌሎችንም አጽዋማት መጾም እንደሚገባን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስኗል /ፍት.ነገ. ፲፭፥፭፹፮/15፥586 ፡፡
ጾመ ድኅነት ስሙ እንደሚያመለክተው የመዳን ጾም ማለት ሲኾን፣ ይህም በብሉይ ኪዳኑ አጽዋማት በጾመ አስቴር እና በጾመ ዮዲት የተተካ የሐዲስ ኪዳን ጾም ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን በሐማ ምክንያት በእስራኤል ላይ ታውጆ የነበረው ሞት በጾመ አስቴር እንደ ተሻረ ኹሉ፣ በሐዲስ ኪዳንም በዕለተ ረቡዕ በጌታችን ላይ በተፈጸመው ምክር የሰይጣን ሴራ ፈርሷልና በጾመ አስቴር ምትክ ረቡዕን እንጾማለን፡፡
እንደዚሁም በብሉይ ኪዳን በጾመ ዮዲት ምክንያት ሆሎሆርኒስ ድል እንደ ተደረገበት ኹሉ፣ በሐዲስ ኪዳንም መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ በከፈለው መሥዋዕትነት ዲያብሎስ ድል ተደርጓልና በጾመ ዮዲት ምትክ ዓርብን እንጾማለን፡፡ የእነዚህ የሁለቱ ቀናት (የረቡዕና ዓርብ) ጾም ጾመ ድኅነት ይባላል፡፡
በአጠቃላይ ጾመ ሐዋርያትና ጾመ ድኅነት እንደ ጾመ ነነዌና ዐቢይ ጾም የበዓላትና የአጽዋማት ማውጫ ቀመርን ተከትለው የሚመጡ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል የሚመደቡ ጾሞች ናቸው፡፡ የጾመ ሐዋርያት ፋሲካ (መፈጸሚያ) የቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በዓለ ዕረፍት (ሐምሌ ፭/5 ቀን) ሲኾን፣ ጾመ ድኅነት ግን ከበዓለ ኀምሳ በስተቀር ዓመቱን ሙሉ የሚጾም ጾም ነው፡፡
ዕለተ ረቡዕ የጌታ ሞት የተመከረበት፤ ዓርብም አምላካችን የተሰቀለበት ዕለት ነውና በመስቀሉ መሥዋዕትነት ያገኘውን ድኅነት ዘወትር ማሰብ ስለሚገባን ሁልጊዜ እንድንጾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ሥርዓት ተሠርቶልናል፡፡ በዚህ ዓመት ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፪/2፤ ጾመ ድኅነት ደግሞ ሰኔ ፬/4 ቀን ይጀመራሉ፡፡ በመኾኑም እንደ ክርስቲያን የምንጠቀመው በራሳችን መልካም ተግባር፤ የምንወቀሰውም በራሳችን መጥፎ ድርጊት መኾኑን ተረድተን ይኼ የቄሶች፤ ይኼ የመነኰሳት ነው የሚል ሰበብ ሳንፈጥር ኹላችንም በአንድነት ብንጾማቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ የምናገኘው ጸጋና ሀብት ይበዛልናልና ራሳችንን ለጾም እናዘጋጅ፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በደስታ እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ እንዳቆየን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ኾነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይኹን፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፕሮቴስታንት ይህንን ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን መንግሥት ከኦርቶዶክስ ነጥቆ ለእኛ ይስጠንና ካላንደር ላይ ይቀመጥልን እያሉ አባቶች በሕግና በቀኖና ቀመር ሰርተው ያወረሱንን መንፈሳዊ በዓላችንን ካልነጠቅን እያሉ በየቦታው የሚንጫጩት እጅግ ሕገ ወጥነትና ወልጌነት ስለሆነ ሥርዓተቸውን ይዘው እንዲቀመጡ ከወዲሁ ማሳሰብ እንወዳለን።ሁልጊዜ ኦርቶዶክስ ላይ እየተንጠለጠሉ መቀላወጥ ነውርም ወንጀልም ነው።
ለሌሎችም ሼር አድርጉት

† መንፈስ ቅዱስ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አለ? †
ክፍል- 1
አንዳንዶች በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሲሰራ አይታይም፣ምዕመናን በመንፈስ ሲሞሉ አይታዩም፣በጉባዔዎቻቸው መሐል የመንፈስ ቅዱስ ኃይል አይገለጥም ይላሉ።ይህ መሰረተ ቢስ ዕይታቸው ፍጹም ከእውነት የራቀ መሆኑን ቀጥለን እንመለከታለን።
ቤተ ክርስቲያንን የሚመራት መንፈስ ቅዱስ/Holy Spirit/ ነው። መንፈስ ቅዱስ ከቤተክርስቲያን ለዓይን ጥቅሻ ያህል እንኳ ተለይቶ አያውቅም፣መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያን እስትንፋስ ነው።ቤተ ክርስቲያን ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንደ ተናገረው ከእግዚአብሔር የተወለደችው በርደተ መንፈስ ቅዱስ ነው
ቤተ ክርስቲያን የተወለደችውም ያደገችውም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው ። በመሆኑም የቤተ ክርስቲያን ሕይወቷ መንፈስ ቅዱስ ነው ። የቤተ ክርስቲያን ሕይወት የሆነ መንፈስ ቅዱስም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሥራዎችን ያከናውናል ለምሳሌ የሚከተሉትን እንመልከት
፩. መንፈስ ቅዱስ ምዕመናን የእግዚአብሔር የጸጋ ልጅነትን እንዲያገኙ በዳግም ልደት/second born/አማኞችን ትወልዳበታለች።
‹‹ኢየሱስም መለሰ እንዲህ ሲል፡- እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው›› (ዮሐ 3፤5-6) ተብሎ የተጻፈው መለኮታዊ ቃለ እግዚአብሔርም የሚያስገነዝበው ይህንኑ ነው፡፡ኦርቶዶክሳውያን ገና ወደ ቤተክርስቲያን ሕብረት በጥምቀት ስንቀላቀል የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ እንቀበላለን።ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ተወልደን የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆች እንሆናለን።
፪.መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን(ምዕመናንን) ለአምልኮተ እግዚአብሔር ያነሣሣል
መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን ለእውነተኛ አምልኮት እንደሚያነሳሳና ቤተክርስቲያንም በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ምሪት እንደምታመልክ መለኮታዊ ቃሉ ይጠቁመናል፡፡ ‹‹እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነን።›› ፊል 3 ፣ 3 ። ኤፌ 5 ፣ 18-19)
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወንጌልን ትሰብካለች መንፈስ ቅዱስም በቤተክርስቲያን (በምእመናን) ላይ አድሮ የጽድቅ ሕይወትን እንዲኖሩ፣በቅድስና እንዲያድጉ ኃይልና ብርታትን ይሰጣል፣መንፈስ ቅዱስ በምዕመናን ልብ ውስጥ ሰርፆ የክርስቶስን ፍቅር ዕለት ዕለት እንዲያስቡ በመስቀል በተደረገው ዘለዓለማዊ ድኅነት ሕይወትን እንዲያገኙ በእምነት ያበረታል።እራሳቸውን ለክርስቶስ ጀንደረባ ያደረጉ ቅዱሳንንም ዓለምን ንቀው በገዳማት እንዲመንኑ ጽናትን ይሰጣል፣ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ ፍቅር መከራና ስቃይን በጽናት እንዲታገሱ ያበረታል።
‹‹መንፈስም ፊልጶስን፡- ወደዚህ ሠረገላ ቅረብና ተናገኝ አለው›› (የሐዋ 8 ፣ 23)
‹‹መንፈሱና ሙሽራይቱም፡- ና ይላሉ›› ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደ ተጻፈ ። ራእ 22 ፥ 7 ።
መንፈሱ የተባለው መንፈስ ቅዱስ ፥ ሙሽራይቱም የተባለችው ማኅበረ ምእመናን ናቸው ።
፫. መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያንን መሪዎች ይሾማል
ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከዲቁና እስከ ፕትርክና ያለውን የቤተክርስቲያን የአገልግሎት ሹመት የምትሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ነው።ከክርስቶስ የተቀበለችውንና በቅዱሳን ሐዋርያት በኩል እስከ ዘመናችን ድረስ ባሉ ብፁዓን አበው ተላልፎ የመጣውን የክህነት ተዋረድ/Apostolic Succession/ አክብራ ይዛ የቀጠለችው በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ጥበቃ ነው።
‹‹በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።›› ሐዋ 20 ፥ 28 ።
ዛሬም ነገም ቢሆን መንፈስ ቅዱስ ባልመረጣቸው በሥጋዊ አሠራር በተመረጡ ሰዎች የምትመራ ቤተክርስቲያን ወደ እውነት ለመድረስ አትችልም ፣ መሪዎቿ በመንፈስ ቅዱስ አልተሾሙምና ስለዚህ ሹመት እንደ አባቶቻችን ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ሊሆን ይገባል ። የሐዋ 1 ፥25-26 ። 13 ፥ 2 ።
፬. መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን መሪዋና ጠባቂዋ ነው፤የወደፊቱን ክፉም ሆነ በጎ ነገር ይገልጥላታል።
ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ዕለት ዕለት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባላት ጥብቅ ሕብረት ከመንፈስ ቅዱስ ቀጥተኛ ምሪት እየተቀበለች የክርስቶስን መንጋ በትምህርት፣በሥርዓትና በመመሪያ ትጠብቃለች።ቤተክርስቲያኒቱ በመንፈስ ቅዱስ የምትመራ በመሆኗ ማንም እንዳሻው ተነስቶ በክህነትና በእረኝነት አገልግሎት ልሰማራ ቢል ቤተክርስቲያኒቱ አትፈቅድም።
‹‹መንፈስ ግን በግልጥ፡- በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞት ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያዳመጡ ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል ፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው ፥ እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ ፥ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል እንዲርቁ ያዝዛሉ ። እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና ፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም ፤ በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት ይየተቀደሰ ነውና።»
1ጢሞ 4 ፥ 1-3 ።
የቤተክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ውሳኔና ቀኖናዊ ድንጋጌዎች እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የሚከወን በጸሎትና በፈቃደ እግዚአብሔር የሚተላለፍ መመሪያ ነው።
‹‹ለጣዖት ከተሠዋ ፥ ከደምም ፥ ከታነቀም ፥ ከዝሙትም ፥ ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና ። ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ ጤና ይስጣችሁ›› ተብሎ እንደ ተጻፈ ። የሐዋ 15 ፥ 28-29 ።
የሐዋርያት ሁለተኛ ሲኖዶስ ውሳኔ የተጠናቀቀውና ውሳኔው የጸደቀው በመንፈስ ቅዱ አማካይነት መሆኑን አንባቢ ልብ ይበል ።
ከዚህ በተጨማሪ ቤተ ክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስትሄድ ይባርካታል ፣ ለእግዚአብሔር አልገዛ ስትል ደግሞ ይገሥጻታል ። ይህንንም እውነት በእስያ ለነበሩት ሰባት አብያተ ክርስቲያናት መንፈስ ቅዱስ በላከው መልእክት ይታወቃል (የዮሐንስን ራእይ ም.2-3 ልብ ብለው ያንብቡ) በእያንዳንዱ መልእክት መዝጊያ ላይ ‹‹መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ›› የሚል ቃል ተጽፏል፡፡
★ መንፈስ ቅዱስ በኦርቶዶክሳውያን ሕይወት ውስጥ ★
እኛ ኦርቶዶክሳውያን በመንፈስ ቅዱስ የምንመራ የእግዚአብሔር መንፈስ አድርቦን የምንኖር የእግዚአብሔር ልጆች ነን።የእግዚአብሔር መንፈስ የሰላምና የመረጋጋት መንፈስ ስለሆነ በተረጋጋ መንፈስ ሆነንም እንጸልያለን፣እንዘምራለን፣ቃሉን እንሰብካለን በአጸደ መቅደሱ በእርጋታ መንፈስ እንመላለሳለን።ሌሎች ቤተእምነቶች መንፈስ ቅዱስ ወረደብን እያሉ የሚጮኹት፣የሚንፈራገጡት፣የሚንዘፈዘፉት፣የሚያጓሩት፣የሚንከባለሉት በእግዚአብሔር መንፈስ ሳይሆን በጥልቁ የመናፍስት መንፈስ ነው።የእግዚአብሔር መንፈስ የሰላም መንፈስ እንጂ የሁከት መንፈስ አይደለም።
መንፈስ ቅዱስ ለሕይወታችን ሕይወት ነው ። ቀዳማዊ አዳምን ከፈጠረ በኋላ እግዚአብሔር ለሰዎች ሕይወትን የሰጠው እፍ በማለት በመለኮታዊ እስትንፋሱ ነበር ። ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው የሆነው በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ነው ። ዘፍ 2 ፥ 7 ።

ኢዮብም ‹‹የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወትን ሰጠኝ›› በማለት የተናረው ይህንኑ ከላይ የጠቀስነውን በጥንተ ፍጥረት መንፈስ ቅዱስ ለሰው ልጅ ሕይወትን ሰጭ መሆኑን ነበር ። ኢዮ 33 ፥ 4
በበደል ምክንያት የሰው ልጅ ንጽሐ ጠባይዕ ካደፈ በኋላ እንደ ገና የተጎሳቆለው መንፈሳዊ ሕይወት የታደሰው የተቀደሰው በመንፈስ ቅዱስ ነው ። ከዚህ የሚከተሉት የሐዲስ ኪዳን ቃላትም ግልጽ የሚያደርጉት ይህንኑ እውነት ነው ።
ቅዱስ ጳውሎስ ንጽሐ ጠባይዓችን የታደሰው ሁለተኛ ከእግዚአብሔር የተወለድነው በመንፈስ ቅዱስ ነው ይለናል ። ቲቶ 3 ፥ 5 ።
ባለቤቱ ደግሞ ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለድን ሕይወት እንደሌለን ተናግሮ ሁለተኛ ተወልደን ሕይወትን የተላበስንበት መንፈስ መንፈስ ቅዱስ ነው ይለናል ። ዮሐ 3 ፥ 3-8 ።
★ እኛ ኦርቶዶክሳውያን በመንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን በማመን ዳግም ተወልደንበታል ። ቲቶ 3፣5 ። ዮሐ 3 ፣ 3-8)
★ እኛ ኦርቶዶክሳውያን በመንፈስ ቅዱስ የክርስቶስ ቤተሰቦች ሆነናል ። ይህንን በተመለከተ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና ። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል» ። ብሏል ። 1ቆሮ 12 ፥ 13 ።
★ ቤተክርስቲያን (ምእመን) በመንፈስ ቅዱስ አንድ የኢየሱስ ክርስቶስ አካል ቤተሰብ ናት ። የሰው ዘር ሁሉ በክርስቶ ካመነ ባሪያም ቢሆን ጨዋም ቢሆን ወንድም ቢሆን ሴት ትልቅም ትንሽም ቢሆን ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ አንድ አካል አንድ ቤተሰብ ነው ።
★ እኛ ኦርቶዶክሳውያን አምነን የተቀበልነው የእግዚአብሔር መንፈስ በሕይወታችን ውስጥ ይኖራል ። በውስጣችን መንፈሰ እግዚአብሔር ለመኖሩ ሐዋርያው የሚከተለውን እንዲህ በማለት ጽፏል ። ‹‹የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን ››1ቆሮ 2 ፥ 12 ። 3 ፥ 16 ።
ሐዋርያው ቅ. ጳውሎስ ሁላችን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች ነንና ሰውነታችንን በቅድስና ልንጠብቀው እንደሚገባ ያስረዳ ሲሆን ፣ በተጨማሪም የእግዚአብሔር መንፈስ የሚኖርበት አካላችንን በኃጢአት በጣዖት ብናረክሰው እግዚአብሔር እኛነታችንን በመዓት እንደሚያፈርሰው በቊ.16 የማስጠንቀቂያ ቃል ጽፎልናል ።
ክርስቲያን ወንድሜ እኅቴ ሆይ ! የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆነውን አካላችንን ከጣዖት ፥ ከዝሙት ፥ ከርኩሰት ፥ ከስካር ፥ ከመዳራት ጠብቀነዋልን ? በውስጣችን ያደረውን መንፈስ ቅዱስን አላስመረርነውምን ? እርሱ ቅዱስ መንፈስ ነውና ፤ እኛ ግን ከንቱና ርኩስ ሥራ ከሠራን መንፈስ ቅዱስ አብሮን ሊኖር አይችልም መንፈስ ቅደሱን አሳድፈነዋል ስለዚህም ንስሐ ገብተን የመንፈስ ቅዱስን ጸጋና ኃይል ዳግም ልንቀበል እንችላለንና ንስሐ እንግባ።
ክፍል ፪ ይቀጥላል
ለሌሎችም አጋሩት

† አንድ መልአክ በአንድ ጊዜ ሁሉም ቦታ እንዴት ይገኛል?
" እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ።"
" I am Gabriel l stand in the presence of God " ሉቃ 1፥19
★ ሼር በማድረግ ሰዎች እንዲማሩበት አድርጉ ★
አንዳንድ ሰዎች አንድ መልአክ በአንድ ጊዜ ሁሉም ቦታ መገኘት እንዴት ይችላል? ይህ የፈጣሪን ሥልጣን መጋፋት ነው ይላሉ።ተሳስተዋል።ረቂቁን የመላዕክት ተፈጥሮና ከአዕምሮ በላይ የሆነውን የረቂቁን መንፈሳዊ ዓለም አሠራር በሥጋዊ ውስን አዕምሮ መገደብና በውስን ተፈጥሯዊ የማሰብ ብቃታችን ረቂቁን የመላዕክት ባሕርይና የመንፈሳዊው ዓለም አሰራርን መርምሮ ለመድረስ መሞከር ፍጹም ሞኝነት ነው።
አንድ ነገር በጣም ልናስተውል ይገባል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለካህኑ ዘካርያስ በተገለጠለት ጊዜ " እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ" ብሎታል ይህንን ቃል መልአኩ ለምን ተናገረው ብንል ስለ ሁለት ነገር ነው አንደኛው ሚስትህ ኤልሳቤጥ ትጸንሳለች ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ ሲለው ዘካርያስ ለመልአኩ ሚስቴ እርጅታለች እንዴት ሊሆን ይችላል ባለ ጊዜ " እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ።"አለ "መቆም" ማለት መማለድ መለመን ማለት ነው።በተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መቆም መማለድ እንደሆነ ተገልጿል።" የተመረጠ ሙሴ በመቅሰፍት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ባይቆም ኖሮ እስራኤልን ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።" ተብሎ ተጽፏል መዝ 105፥ 23 ።ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር የምቆም ነኝ ብሎ መናገሩ ስለ አንተና ስለ ባለቤትህ በእግዚአብሔር ፊት ለምኜ፣ማልጄ ነበር ማለቱ ነው።
ሁለተኛ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ ማለቱ እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ መላዕክቱም አሉ የእግዚአብሔር ፊት ወዴት ነው ? ብንል እግዚአብሔር ረቂቅ ስለሆነ በሁሉም ቦታ ሁሉ አለ ስለዚህ እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ ቅዱሳን መላዕክቱ አሉ።ይህም እንደ እርሱ አምላክ የሚያሰኛቸው ሳይሆን በመለኮት ሥልጣን፣ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው መንፈሳዊ ረቂቅ ጸጋ እርሱ ባለበት ቦታ ሁሉ እነርሱም አሉ።
‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል›› (መዝ. 33፥7)
የሚገርመው ግን እግዚአብሔርን ለማይፈሩ፣በኃጢአትና በበደል ለሚመላለሱ ሰዎች ግን እንኳን በአንድ ጊዜ ለሁሉም ባሉበት ቦታ ሊደርስ ሁሉም ሰዎች ተሰብስበው መልአኩ ወዳለበት ቢመጡ እንኳ አይረዳቸውም።
በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቅዱሳን መላዕክት " ዓይኖቻቸው ብዙ የሆነ ክንፎቸቸውም ብዙ የሆነ" ተብሎ ተጽፏል።ይህ ማለት ሰውነታቸው በዓይን የተዥጎረጎረ፣ በክንፍ የተሸፈነ ማለት ሳይሆን በአንድ ቦታ ሆነው ሁሉ ቦታ ያለውን ማየት የሚችሉ ከማይክሮ ሰከንድ በታች በሆነ ፍጥነት በሁሉ ቦታ ፈጥነው መድረስ የሚችሉ ማለት ነው።
የእንግሊዘኛውን ቨርዥን ብንመለከተው በደንብ ግልጽ ያደርገዋል "l am Gabriel l stand in the presence of God" ይህም ማለት እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ መልአኩም አለ።እግዚአብሔር ረቂቅ አምላክ ነው እነርሱም ረቂቃን ናቸውና እርሱ ባለበት ሁሉ እነርሱም አሉ።
ስለዚህ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥርዓቷ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስለሆነ አልተሳሳተችም።በአንድ ቀን በተለያየ ሃገርና ቦታ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ስናከብር የእግዚአብሔርን ክብር እያወጅን ስለሆነ በሁሉም ቦታ እግዚአብሔርም መልአኩም በክብር አሉ።
አንድ ቅዱስ መልአክ ክብሩ ከፀሐይ ክብር ይበልጣል እንጂ አያንስም አንዲቷ ፀሐይ በአንድ ጊዜ የተለያየ ቦታና የተለያየ ሀገር የመድረስ ተፈጥሯዊ ፀጋ አላት የእግዚአብሔር መልአክ ደግሞ ከፀሐይ በላይ ሥልጣን ስላለው በአንድ ጊዜ ሁሉም ጋር መገኘት ይችላል።ይህ ማለት የእግዚአብሔርን ሥልጣን መጋፋት ሳይሆን እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ መልአኩም እንደሚገኝ ማስረገጥ ነው። "በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ነኝ" ያለውም እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ መልአኩም እንደሚኖር ማረጋገጫ ነው።እግዚአብሔር ደግሞ የሌለበት ቦታ የለም።
" ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።"
(የዮሐንስ ራእይ 18:1)
ከነፋስ ይልቅ ነፍስ ትረቃለች፤ ከነፍስ ይልቅ ደግሞ መላእክት ይረቃሉ፤ ከመላእክት ደግሞ ሥላሴ ይረቃል ።በውስን አዕምሯችን ረቂቃኑን ለመገደብ አንሞክር።ከአዕምሮ በላይ የሆነብንን ነገር ዕፁብ ድንቅ ብለን ማለፍ ክርስቲያናዊ ጠባይ ነው።
በምድራዊ ቴክኖሎጂ እንኳ ብንመለከት አንድ የኮምፒውተር ሰርቨር በተለያዩ ሀገር ያሉ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኮሚፒውተሮችን በተመሳሳይ ሰዓትና ደቂቃ የሰከንድ ልዩነት ሳይኖር መረጃ ይሰጣል መረጃም ይቀበላል።ሰው የፈጠረው ሰርቨር በአንድ ጊዜ ሁሉም ጋር መሥራት ከቻለ እግዚአብሔር የፈጠረው አንድ ቅዱስ መልአክማ ከሰዎች የእጅ ሥራ ውጤት በሰባት እጥፍ እንደሚበልጥና አንዱ ለሁሉ መድረስ እንደሚችል በእምነት ልንረዳ ይገባል።አሁን የምንጠቀምበትን የፌስቡክ አፕልኬሽን የሚቆጣጠረው አንድ ሰርቨር ነው።በዓለም ዙሪያ ያሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን በሙሉ የሚቆጣጠራቸው አንድ ሰርቨር ነው።የሰው ልጅ የእጁ ሥራ ዓለምን እንዲ መቆጣጠርና በአንድ ጊዜ ለሚሊየኖች ተደራሽ መሆን ከቻለ አንድ ቅዱስ መልአክ ከዚህ በላይ ሊሰራ እንደሚችል መንፈሳዊ አዕምሮ ያለው ሰው በቀላሉ የሚረዳው ሐቅ ነው።
" መንፈሳዊ ሰው ሁሉን ይመረምራል።" ተብሎ ተጽፏል
ደግሞ አንድ ነገር አንርሳ ምድር በጣም ግዙፍና ሰፊ የምትመስለን ለእኛ ለሰው ልጆች ነው።በእግዚአብሔርና በመንፈሳዊ ኃይላት በቅዱሳን መላዕክት ዘንድ ግን የእኛ ዓለም እጅግ በጣም ትንሿ ናት ያውም የመሬት አብዛኛው ክፍል በውሃ የተሸፈነ ነው።የብሱ ላይ ከሚኖረው ሕዝብ ስንቱስ ነው ቅዱሳን መላዕክትን በአንድ ቀን የሚያከብረው? ከዘጠኙ ፕላኔት ግዙፉ ጁፒተር ነው ስፋቱ 139 ሺ 820 ኪሜ ዳያሜትር ነው።የእኛ መኖሪያ መሬት ግን 32 ሺ 742 ኪሜ ዳያሜትር ስፋት ነው ያላት ይህችን መዳፍ የምታክል ዓለም ለመላዕክት እንደ ግዙፍ ዓለም አድርገን አናስበው።መዳፋችሁን ዘርግታችሁ የምትመለከቱትን ያህል ነው ሰማያውያን ኃይላት ይህቺን ምድር የሚያዩዋት።እኛ በእነርሱ ዘንድ በጣም ኢምንት ነን።
ቅዱስ ገብርኤል አንድ ሲሆን ከእግዚአብሔር በተሰጠው ፀጋና ሥልጣን በዓለም ዙሪያ ላሉ ሰዎች ሁሉ ከዓይን ጥቅሻ ባነሰ ፍጥነት ደርሶ ይራዳል።
የመልአኩ ፈጣን ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን።
መ/ር ታሪኩ አበራ
እባካችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉት

† ኢየሱስ ምርጫ ሳይሆን ብልጫ ነው †
ክፍል 2
★ኦርቶዶክሳውያን በቀላሉ እምነታቸውን የሚቀይሩበት ምክንያት በዚህ ጽሑፍ በስፋት ተገልጿል።★
★ዶ/ር ዛኪር ስለ ኢየሱስ ያውቃል ኢየሱስ ግን በሕይወቱ ውስጥ የለም።ኢየሱስን በሕይወቱ የማይኖር ክርስቲያን ሁሌም ኢየሱስ ያሉትን ሁሉ ሲቃወም ይኖራል።★
በክፍል 1 ጽሑፍ ላይ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሰዎች ለምን እንደሚወጡና በሌሎች የሚነጠቁበትን ምክንያት በስፋት አስቀምጫለሁ ሌሎች ምክንያቶች ደግሞ እንደሚከተለው ቀርበዋል።በማስተዋል ይነበብ ለሌሎችም ትምህርት እንዲሆን ሼር አድርጉት።
2. #ኢየሱስን አለመኖር
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሠረቷ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች የኢየሱስ ስም ተጠርቶ ጠንከር ብሎ ሲሰበክ የሚጨነቁት ኢየሱስን ሕይወት አድርጎ ካለመኖር የተነሳ የሚመጣባቸው ችግር ነው።ምላሳችን በዘልማድ ኢየሱስ ሕይወቴ ነው ይላል እንጂ ልባችን ከክርስቶስ በጣም የራቀ ነው።
አንዳንድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋዮችና ምዕመናን ትልቁ ችግራችን ኢየሱስን እየኖር ነው አይደለም። ሰማዕታት ዋጋ የከፈሉለትና ቅዱሳን ዓለምን ንቀው በቅድስና የኖሩለት የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር በውስጣችን የለም። ስለ ኢየሱስ መናገርና ኢየሱስን መኖር እጅግ ከፍተኛ ልዩነት አላቸው።አንዳንድ ስለ ኢየሱስ እናውቃለን የሚሉ ሰባክያንና ዘማርያን ሳይቀሩ የኢየሱስ ስም ጠንከር ተደርጎ ሲሰበክ መንፈሳቸው ሲታወክና ለተቃውሞ ደም ሥራቸው ሲገታተር ብዙ ጊዜ እንመለከታለን።እንደዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች ትልቁ ችግራቸው ዕውቀት ማጣት ብቻ ሳይሆን ሕይወት ማጣትም ጭምር ነው፣ስለ ኢየሱስ የሚያውቁት እንደ ማትስና ፊዚክስ ያለ ዕውቀት ነው እንጂ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የተለወጠ ሕይወት የላቸውም።ኢየሱስ እውቀት ሊሆነን ሳይሆን ሕይወት ሊሆነን የመጣ ጌታ ነው።ክርስቶስን በሕይወቱ የማይኖር ክርስቲያን ከመሐመዳውያን ያልተለየ ግብዝ ነው።ዶ/ር ዛኪር ስለ ኢየሱስ ብዙ ያውቃል ኢየሱስ ግን በሕይወቱ ውስጥ የለም።ኢየሱስን በልቡ ላይ ንጉሥ አድርጎ ያልሾመ ክርስቲያን ሁሌም ኢየሱስ ያሉትን ሁሉ ሲቃወም ይኖራል።ኢየሱስን መኖር ማለት ኢየሱስን በመምሰል ሕይወት ውስጥ መመላለስ ማለት ነው።ቅዱስ ጳውሎስ እኔ ኢየሱስን እንደምመስል እናንትም እኔን ምሰሉ ያለው፣እኔ እየኖርኩት ያለውን ክርስቶስን እናንተም ኑሩት ማለቱ ነው።ክርስቶስን የሚመስል ሰው ፍቅር ገንዘቡ ነው፣ትሕትና ሕይወቱ ነው፣ክርስቶስን የሚመስል ሰው ይቅርታ ኑሮው ነው፣ምህረት እርካታው ነው፣ኢየሱስን የሚመስል ሰው ጠላቱን ይወዳል፣ስለ ሚሳሳቱ ሰዎች አብዝቶ ይጸልያል፣ኢየሱስን የሚመስል ሰው ለፍርድ አይቸኩልም፣በማንም ላይ ጣቱን አይቀስርም፣ኢየሱስን የሚመስል ሰው ለውዳሴ ከንቱ አይጣደፍም፣እርሱ እንዲከብር ወንድሙን አያዋርድም፣ኢየሱስን የሚመስል ሰው ስለ እህቱ አብዝቶ ይጸልያል፣እንጂ የስድብን ቃል ከቶ ከአንደበቱ አያወጣም።ኢየሱስን መኖር ያለ ጥርጥር ታላቅ ምሥጢር ነው።
የብዙ ኦርቶዶክሳውያን ችግራችን ይሄ ነው፣አባቶቻችን የኖሩትን ክርስቶስን እኛ ግን ጨርሶ አናውቀውም፣አንዳንድ ሰባክያን ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ መስበክ ደስ ይለናል ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ ኢየሱስ የኖረውን ሕይወት ግን በጣታችን አንነካውም።ብዙ ምዕመናን ስለ ድንግል ማርያም ሲሰበክና ፣ሲዘመር ነፍስ አይቀርላቸውም ፤ እናቱ «እርሱን ስሙት»ያላቸውን ጌታ ላለመስማት ግን አንገታችንን የጠመዘዝን በጣም ልበ ደንዳኖች ነን።የኢየሱስን ስም እየተቃወሙ የድንግል ማርያም ወዳጅ ነኝ ማለት በክርስትና ላይ ማላገጥ ነው።ኢየሱስ ምርጫ ሳይሆን ብልጫ ነው። «ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬና በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች» ብላ ድንግል ማርያም ያመሰገነችው እኛም እንደ እርሷ ኢየሱስን እንድናመሰግን ምሳሌ ሆና እያስተማረችን መሆኑን በማስተዋል ልንረዳ ይገባል።
እኔ በራሴ አገልግሎት እንደታዘብኩት ስለ ነገረ ቅዱሳን ስሰብክ ብዙዎች ደስታቸውን ሲገልጹ እመለከታለሁ፣ለበረከት እያሉም ትምህርቱን ለሌሎች ሲያካፍሉም አስተውላለሁ፣ስለ ኢየሱስ ስሰበክ ግን ሲቀዛቀዙ እመለከታለሁ።ወገኖቼ ኢየሱስ ሲበርደን የምንደርበው ሲሞቀን የምናወልቀው ልብስ ሳይሆን የሕይወታችን ራስ ነው።ኢየሱስ ዋና እንጂ ተከታይ አይደለም፣ኢየሱስ ጽድቃችን እንጂ መጽደቂያችን ብቻ አይደለም፤ቅዱሳንን ቅዱስ ያሰኛቸው የኢየሱስ ደም እንጂ ከባሕርያቸው የተገኘ ጽድቅ አይደለም።የቅዱስን የተጋድሎ ዓላማ ዓይናችን ክርስቶስን እንዲመለከት ለማድረግ ነው እንጂ እርሱን ረስተን ስለ እነርሱ ተጋድሎ ብቻ እየሰበክን ዘመናችንን እንድንጨርስ አይደለም።
የቅዱሳን ወዳጆች ከሆንን ቅዱሳን የኖሩትን ክርስቶስ እኛም እንኑረው፣ቅዱሳን ስለ ኢየሱስ ስም የከፈሉትን ዋጋ እኛም እንክፈል፣ቅዱሳን ጠርተው የማይጠግቡትን ኢየሱስን እኛም ጠዋት ማታ ኢየሱስ፣ኢየሱስ፣ኢየሱስ እያልን በሙሉ ኃይልና ስልጣን ስሙን እየጠራን ለስሙ እየዘመርን፣በስሙ አጋንንትን እያስጨነቅን ዘመናችን በፊቱ ይለቅ።
3. #ፍርሐት
አንዳንድ ዘማርያንና ሰባክያን ሐሞታቸው የፈሰሰ፣ወኔ የከዳቸው በመንፈስ ሳይሆን በሥጋ ስሜት የሚያገለግሉ ፍጥረታውያን ናቸው።ኢየሱስ የሚለውን ስም ላለመጥራት ምላሳቸው እሳት ውስጥ እንደገባ ጅማት ሲኮማተር ብዙ ጊዜ እናያለን።በናዝሬቱ በኢየሱስ ስም ተነሳና ተመላለስ ተብሎ የተጸፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላለመጥራት አስር ጊዜ ሲቀባቡ፣ድሪቶና ታኮ ሲለጣጥፋ ይውላሉ።እንዲህ ዓይነቶቹ አገልጋዮች ለእግዚአብሔር መንግስት የሚሰሩ ሳይሆን ቢዝነስ የሚሰሩ ነጋዴዎች ናቸው።የሕዝብን ስሜት እያዳመጡ ሕዝቡን ይከተሉታል እንጂ የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ እያዳመጡ ኢየሱስን ተከትለው ሕዝብ እነርሱን እንዲመስላቸው ምሳሌ የሚሆኑ አይደሉም።
ፍርሐት በሽታ ነው።እንዲህ ዓይነቱ በሽታ ደግሞ ተላላፊ ነው፣ከአገልጋዩ ወደ ምዕመኑ በቀላሉ ይተላለፋል።እልልታና ጭብጨባ እየናፈቅን መድረክ ላይ የምንወጣ ከሆነ ሕዝቡን ቲፎዞ እንጂ አማኝ ሳናደርገው ነው የምንወርደው።አጨብጭቦ የገባ ደግሞ አጨብጭቦ ለመውጣት እጅግ የተጋለጠ ነው።ዛሬ የፌስቡክ አርበኛ ሆነው ኢየሱስ የሚለውን ሁሉ ሲሳደቡና ጥላሸት ሲቀቡ የሚውሉ የፌስቡክ ጭፍሮች የእነዚህ አገልጋዮች የእጅ ሥራ ውጤት ናቸው።በአርአያቸውና በአምሳላቸው የፍርሐትን እስትንፋስ በአፍንጫቸው እፍ ብለው ፈጥረዋቸዋል። በተለይ በዚህ ዘመን አብዛኛው አገልጋይ የእሳት ዳሩን ጴጥሮስ ሆኗል። ኢየሱስን በሩቅ እየተመለከተ የኢየሱስ ነኝ ማለት ግን ጭንቅ ሆኖበታል። በፍርሐት ቆፈን ተቀፍድዶ፣የመንደር እሳት ዳር ቁጭ ብሎ የጎሪጥ እያየ በእሳት ዳር ጨዋታ ዘመኑን የሚፈጅ በጸጋው የሚያላግጥ ያልታደለ ገብረ አካይ ሞልቷል።ወንድሜ የምትሞቀው እሳት አንድ ቀን ጨርሶ ሳይበላህ ኢየሱስን ስበክና ሙት፣መረብህን በዓሳ የሞላውን ጌታ እንደ ዓሳ እየተሙለጨለጭክ አታሳዝነው፣አንተን አገልጋይ ለማድረግ ባላፈረብህ ጌታ አንተ ኢየሱስ ብለህ ለማገልገል እንዴት ታፍራለህ?ከአንተ ስም በላይ የእርሱ ስም ለምዕመናን ክብርና ሕይወት ነው።ስሜ ይጠፋል ብለህ ስሙን አትሸሽገው።ያለ እርሱ አንተም የለህም።ቢያንስ እንጀራ የወጣልህ በኢየሱስ ሞት በተገኘው ክርስትና መሆኑን ለኅሊናህ ንገረው።በክርስቶስ መቅደስ ሊሰበክ የሚገባው የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

ዘማሪዋ እህቴ ሆይ ኢየሱስ እያልሽ ሳትዘምሪ ዘመንሽ ቢጋመስም ቀሪ ዘመንሽን ለስሙ ሳትሰስቺ የከንፈርሽን መስዋዕት ሰዊለት ፣ከካሴት ንግድ በላይ የኢየሱስ ደም ዋጋው የከበረ ነው።
ኢየሱስ እያልኩኝ ከዘመርኩኝ ካሴት አይሸጥም ብለህ ስሙን የሸሸግከው አንተም ዘማሪው ወንድሜ ሆይ ዘመንህን ሙሉ ንስሐ ገብተህ አልቅስ፣ ደሙን ሳይሳሳ ያፈሰሰልህን ጌታ አንተ ለስምህ ሳስተህ በገንዘብ ከለወጥከው እመነኝ አንተ የይሁዳ ታናሽ ወንድሙነህ።ዝማሬህን አሊያም የሥራ ፊልድህን ለውጥ። አገልግሎት በመንፈስና በእውነት የምንኖረው ሕይወት እንጂ ገቢና ወጪ እያሰላን የምንቀምረው ንግድ አይደለም።
በፍርሐት መንፈስ የምታገልግሉ ሰባክያንና ዘማርያን እባካችሁ የድንግል ማርያምን ስም ካሴት ማሻሻጫ አናድርገው ።የልጇ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እግዚአብሔር በሰጣችሁ ጸጋ በመንፈሳዊ ኃይልና ስልጣን ግለጡት ።እናንተ ሐሞተ ቢስ ሆናችሁ ትውልዱን ፈሪና ደንባራ አታድርጉት።
4 #የአጋንንት እስራት
የኢየሱስ ስም ሲጠራ ክፋኛ የሚቃወሙት በአጋንንት እስራት ውስጥ ያሉ ሰዎች ናቸው።ሰይጣን በኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ስለ ተቀጠቀጠ ይህንን ስም የሚጠሩትን ሁሉ በተለያየ መንገድ ሲቃወምና ስሙ እንዳይጠራ ለማሸማቀቅ ብዙ ሲደክም ይውላል።አብዛኛው በሶሻል ሚዲያ ላይ የኢየሱስ ስም ተጠርቶ ሲሰበክ፣ሲዘመርና ሲጻፍ ሲሳደቡና ሲነቅፋ የሚውሉት ሰዎች የአጋንንት መንፈስ የያዛቸው ናቸው ሰይጣን በውስጣቸው አድሮ ክፋ ያናግራቸዋል፣ክፋ ያሳስባቸዋል፣ክፋ ያጽፋቸዋል እነርሱ ግን አያውቁትም።ለቤተክርስቲያን የሚታገሉ ይመስላቸዋል።እግዚአብሔር በስድብ አይከብርም።መጽሐፍ የስድብ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ ነው የሚለው ተሳዳቢዎች ከእግዚአብሔር መንግስት የተለዩ ናቸው።
አንዳንድ ወንድሞችና እህቶች ሳታውቁት የአጋንንት ተከታይ ሆናችኋልና ራሳችሁን ጠብቁ፣የአጋንንት መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች የሚናገሩትንና የሚጽፋትን እያስተላለፋችሁ የአጋንንት ተባባሪ አትሁኑ። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የዕውቀት፣የጥበብና የቅድስና መፍለቂያ እንጂ የስድብ ፋብሪካ አይደለችም።ለኦርቶዶክስ እምነቴ ብላችሁ ስትሳደቡ የምትውሉ ሰዎች ኦርቶዶክስን በስም እንጂ በሕይወት የማታውቋት፣የዕውቀት ድርቀት ያጠቃችሁ ሰዎች ናችሁና ከጥልቅ እውቀት እየቀዳችሁ ነፍሳችሁን አለምልሙ።
ኢየሱስ ፍቅሩን በልቡናችን ጣዕሙን በከንፈራችን ያኑርልን።
እባካችሁ ለሌሎችም ሼር በማድረግ ትውልዱን በክርስቶስ ፍቅር እንድረስ።