Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
152 - Telegram Web
Telegram Web
ሰላም ይድረሶት ሆዴ ❤️

አንዲት ሴት ወደ እናታችን ዓኢሻ رضىالله عنها በመምጣት እንዲህ አለች ፦
"ወደ አላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ቀብር ዉሰጂኝ" በማለት ጠየቀቻት። ዓኢሻምرضى الله عنها ነብዩصلى الله عليه وسلم  የተቀበሩበትን ክፍል በመክፈት አሳየቻት። ወደ ውስጥም ገባች። በነብዩصلى الله عليه وسلم  ትዝታ ለቅሶዋን ጀመረች። ማቆም አልቻለችም። የጥንቱን መልካም ዘመን የኋሊት አስታወሰች። በወህይ የደመቀውንና በነብዩصلى الله عليه وسلم  እስትንፋስ የተሞለውን  ህይወት በህሊናዋ ቀርፃ በፍቅራቸው መውጅ በሀሳብ ሰጠመች። ሀዘኗ በርትቶ ለቅሶዋና እንባዋ ሀድ አልነበረዉም። እናም የመጨረሻ እስትንፋሷ እዛዉ ተቋረጠ። የሰይዳችንንصلى الله عليه وسلم  ዶሪህ ተንተርሳ ላትመለስ አሸለበች።

❀በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
እንደ ፈለግሽ ዋሺ እንደ ፈለግሽ አጥፊ
አንቺ በዋሸሽው ልደረግ ቀጣፊ
አንቺ ባወራሺው ይበሉኝ ለፍላፊ
አንቺ ባጠፋሽው በሰራሺው ሰራ
ሁሉም ሰው ይውቀሰኝ ይበሉኝ ከሰራ
አንቺን ከሚነኩሽ እኔን ይደብድቡኝ
እኔን እንዳሻቸው አዋርደው ያቅሉኝ
ሌላው ሁሉ ይቅር አንቺን ያክብሩልኝ
እኔ ልጎሳቆል አንቺ ተመቺቶሽ
የኔ መስመር ያውጣ ያንቺ ፊት ለስልሶ
እናቴ አንቺ ነሽ የቤቴ ምሶሶ ❤️
ሰይዲ ሸይኽ አል-ሸዕራዊይ رحمه الله እንዲህ ብለው አሉ፡-

‹በትዕግስት እንዳትታክት ተጠንቀቅ ፡ እርሱ ቢሻ ፍላጎትህን በዐይን ጥቅሻ (ፍጥነት) ያሣካልህ ነበር። እርሱ የተስፋህ እንባ ወይም የጭንቀትህ ጩኸት የሚሰወርበት አይደለም ፤ እርሱ ሁኔታህንና እራስህን ማስተካከል አያቅተውም ፤ ነገር ግን አጥብቀው የሚጠይቁትን ይወዳል... 【እኔ ዛሬ በትዕግሥታቸው ምክንያት መነዳኋቸሁ…】 ብሎም የለ?.. ስለዚህ ረጋ በል.. ምትኩ ታዕምር መሆኑ አይቀርም።›

ጌታ ሆይ! ብቻ በለው

#ትንሹ አሚር

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
💚💚💚 የ ሀሚሱ ጀባታ💚💚💚
አኢሻ ረዲየላሁ አንሀ ለነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እስቲ በእርሶ ላይ ካለፉ አስቸጋሪ ቀናቶች ውስጥ ከዋነኞቹ ንገሩኝ አለቻቸው እሳቸውም ከጣኢፍ አባርረውኝ ወደ ቀርነል መማዚሎች የሄድኩ ጊዜ ነበር አሉአት የዛን እለት በደሉ ሲበዛ እጆቼን አንስቼ
✿ጌታዬ ሆይ አልኩኝ ቅሬታዬን ለአንተ አቀርባለሁ የጉልበቴ/የአቅሜንም ማነስ ፡ አንተ ደግሞ የእኔም የተበዳዮች /የደካሞች ጌታ ነህ ወደ ማን ነው የምትተወኝ ወደ ጠላት ነውን እያሰቃየኝ ወዳለው ?
ወይስ ወደ አንተ ጉዳዬን የምትቆጣጠር ወደሆንከው ጌታዬ በኔ ላይ ተቆጥተህ ካልሆነ ምንም ችግር የለውም አሳቸው እያሉ ነው የአንተ ቁጣ ከሌለበት በደሉ ሁላ ቀላል ነው
የአንተ ይቅርታ ለኔ ከሁሉም ነገር የተሻለ ነው ከዛም ተቀምጠው ዱአቸው ቀጠሉ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ሰይዲና ጅብሪል ወለይሂ ሰላም አንተ ሙሀመድ ሆይ ከኔ ጋር ተራራ መላኢካ አላህ ልኮልህ ይዤልህ መጥቻለሁ ነብያችን ሲናገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ከጅብሪል ውጪ ሌላ መላኢካ ያየሁት ይላሉ ከዛም የተራራው መላኢካ እነዚህን ሰዎች እነዚህን ሁለት ተራራ ላጣብቅባቸው ሲላቸው እሳቸውም ወደፊት ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ ላኢላሀ ኢለላህ የሚል እንዲፈጥርልኝ እመኛለሁ ተዋቸው አትንካቸው ብለው መላኢካውን መልሰው ዱአ አደረጉ

ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
" የአለሙ አይነታ የኸልቁ ጨረቃ
ለአለማት እዘነት ነበሩ ጠበቃ "
በሰለዋት እንበርታ

#ትንሹ አሚር
በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
ተግቼ ብጸልይ እጆቼን ዘርግቼ፣
ቤቴ ባዶ ቢቀር ያለኝን መጽውቼ፣
ቀኑን ሙሉ ብጾም እስኪቆረጥ አንጀቴ፣
ዘወትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ፣
በቀራ ባቀራ በመዲና ሀረም ግርማ፣
ብመድህ ሰለዋት በሚጣፍጥ ዜማ፣
ፍቅርን ብሰብክ ምስጢር አመስጥሬ፣
ብናገር ባስተምር ትርጉሙን ዘርዝሬ፣
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴ፣
ሐሜት ክርክር ካልጠፉ ከቤቴ💨
በዜሮ ይባዛል ፍቅር በማጣቴ።
#ትንሹ አሚር

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
የኢስነይን ሀለት

እየተኙ እንቅልፍ ማጣት፣
ሳይተኙ መቃዠት፣
እየጠጡ ጥማት፣
ውሀ በሌለበት መርካት፣
እያዪ አለማየት፣
በብርሀን እይታን ማጣት፣
በጨለማ አይን ማግኘት፣
እየኖሩ በቁም መሞት፣
እየሞቱ ህይወት መዝራት፣
እያገኙ ማጣት፣
እያጡ እንደ ማግኘት፣
ወደ ኃላ ሄደው ከፊት መገኘት፣
እየመሩ መተው መጨረሻ መቅረት፣
አንዳንዶች ደርሰው ጥጉ ላይ የክፋት፣
ሌሎች ደሞ አላቸው የሚገርም ደግነት፣
የማይገባ ስሜት፣
እያንዳንድዋ ስንኝ እያንዳንድዋ ቃላት፣
የዚ አለም የሰዎቹ ትክክልኛ ሀለት።

✍️✍️✍️✍️✍️
#ትንሹ አሚር

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
የጀይላኔ ጀባታ

አክባሪ ተንቆ ተከባሪ ልቆ፣
አዳማጭ ተረስቶ ተናጋሪ ደምቆ፣
ከማወቅ መታወቅ ከማየት መታየት፣
ከመውደድ መወደድ ከመስማት መሰማት፣
ከሚመኝ ኗሪ ጋር ያለኝ የኔ ልዩነት፣
በምጓዘው መንገድ በማልፋቸው ቀናት፣
ከሙስጠፋ ውጪ ሌላ ያለው የኔ ሀያት፣
ልቤም ታማሚ ነች ነፍሴም ዱርዬ ናት፡፡

#ትንሹ አሚር

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
ገጠመኝ ፴፪ :- የሆድ ነገር...!
[]==== ቀበጥዋ አንሰበት❤️❤️=======[]

   ታላቁ ዓሊም ኢማም ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና ዘንድ አንድ አዕራቢይ ( ገጠሬ) ለብዙ ቀናት ሐዲሶችን ሲያደምጥ ፣ ሲማር ቆየና ወደ ቤተሰቦቹ መመለስን አሰበ ።

  ኢማሙም እንደው እስከዛሬ ከሰማቸው ሐዲሶች በውስጡ የተቀመጡትን ፣  ያረሳቸው ፣ ቁምነገር የያዘባቸውን ሐዲሶች እንዲነግራቸው ጠየቁት ።

እሱም
" ሶስት ሐዲሶች ናቸው ። እነሱም
አንደኛው:-  የእናታችን ዓኢሻ (ረ ዐ) ሐዲስ ነው የአላህ ነብይ (ሰ ዐ ወ) ጣፋችን ነገር ይወዱ ነበር ማለታቸው ።
ሁለተኛው: - የአላህ መልዕክተኛ ( ሰ ዐ ወ) " የመንገደኛ ሰው (የጉዞ ላይ) ፆም መልካምነት የለውም !" ማለታቸው ።
ሶስተኛው ፡- የአላህ ነብይ ( ሰ ዐ ወ)  " ዒሻ ሰላት ደርሶ እራት ከቀረበ እራቱን አስቀድሙ! " ማለታቸው ። " ብሎ አረፈው ።

~ ወደ ሰው ልብ አጭሩ መዳረሻ ሆዱ ነው !

#ትንሹ : አሚር


#ትንሹ አሚር

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
💚💚💚💚 የጀይላኒ ጀባታ 💚💚💚💚

• እነሆ ጀግና! እነሆ የመርካቶ ዛሂድ..! ዛሊከ ፈድሉላህ

<< ሙሐባ♡ እውነተኛ ቅዱሱን ፍቅር የኡ
ስታዝ ፈድሉ ሙሪዶች ጋር ፈልገው! >>

እንደ ቀልድ ዓመት...!
የበርካታ ሱቆች ባለቤት ሆኖ ቤት ቪላም ይሁን ኮንዶሚኒየም ቤት አልገዛም! መኖሪያው አንዋር መስጂድ ነበር።

ትልቅ ገቢ ኖሮት መስጂድ እየዋለ እያደረ ያውም መሀል መርካቶ ነጋዴዎች የመኪና አዳዲስ ሞዴሎችን በሚያቆሙበት ቢሊዮን ብሮች በሚንቀሳቀሱበት ነጋዴዎች መናሀሪያ መሀል መርካቶ... ገጠር ዛውያ ላይ ዛሂድ መሆን ቀላል ነው ምንም የዱንያ ብልጭልጭ ከእይታህ ይሰወራል... ኡስታዝ ፈድሉ እኮ መርካቶ መሀል ሆኖ 100 ካሬ ያልገዛ.. አዲስ የለበሰውን ቆንጆ ልብስ ከወር ቡሃላ መርካቶ ዙሪያ ያሉ ሚስኪኖች ለብሰውት ታየዋለህ...

ፆም ያበዛል የኸሚስና የኢሥነይን ቀበኛ ሱንይ ጿሚ ነው... በ24 ሰዓት አንዴ ሳይሆን በ72 ሰዓት አንዴ ብቻ ሊበላ ይችላል...

ሚንሁም መን ተረከ ሹርበን ወመእከላ
ሚንሁም መን ተረከ ዘውጀተን ወማላ

መስጂድን መኖሪያ ቤቱ ማድረጉ ብቻውን እንዳይገርምህ ትዳር አድርጎ የያዘው ደግሞ ከላሙላህን ቁርአንን ነበር። ስንትና ስንት ወዳጆቹ ቆነጃጅት ቢክራ ልጆቻቸውን እንዳርህ ጀባ ብለውታል ኡስታዝ ፈድሉ እንደ ሸይኽ አሕመድ አመዴ ውልም አላሉበት። ሚስት ሳይኖረው ብዙ ወጣቶችን የመኸር እየከፈለ ቤት እየተከራየ ብዙዎችን ባለትዳር አድርጓል...

ኡስታዝ ፈድሉ የረሱለላህን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፍቅር ልክ እንደ አሚና አረገዘ... ሀምዛ ኢብን ዓብዱልሙጠሊብ ለነቢ እንደተሰዋ ኡስታዝ ፈድሉ ለዲን ሙሐመዲያ ሸህዋውን ንብረት መያዝን ሰዋ። ሰልማን አል-ፋሪስ ለረሱለላህ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም 5 ግዜ በባርነት እንደተሸጠ ኡስታዝ ፈድሉ በዒልሙ ጥልቀት ኢማምና መሪ መሆን እየቻለ የቲሞችን ሚስኪኖችን ኻዳሚ በመሆን ነፍስያውን ሸጠ...

ሸዋል በሚወዳት የኢሥነይን ሌሊት ከአንዋር መስጂድ ወደ ዓለመል በርዘኽ መኖሪያ ሲቀይር ልብሶቹ ኪታቦቹ ገንዘቦቹን ሁሉ ለሚገባቸው ሰዎች አከፋፍሏል... ኡስታዝ ፈድሉ የሙሪዶቹ ሕይወት ላይ ከእናት ከአባታቸው በላይ ጠልቆ እየገባ ሕይወታቸውን እየቀየረ ያረገላቸውን ለማንም እንዳይናገሩ አደራ ይጥልባቸው ነበር...

ሪደላህን የአላህን ውዴታ በመሻቱ አላህ መውደድን ወዶት ረዲየላሁ ዓንሁ ወአርዳ ዓንሁ ናስ በሰዎችም አስወደደው።

ለስላሳ ለወጣቶች ገራም ለሴቶች ሩሕሩህ

ሀገር ከቀየረ ዓመት ሞለው... ታዲያ ሙሪዶቹ ደረሶቹ በየቀኑ ፋቲሐ ይቀሩለታል... ዛቱ ሙሐመድይ ሲፈቱ መለክይ መሆኑን ትንሽ ቀናት አብሮ ያሳለፈ ወዳጁ ለወር ሲናገረው ያንን ቂሳ ታገኛለህ...

ኡስታዝ ፈድሉ ቤት አይግዛ እንጂ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ያሉ ወዳጆቹ በውጭም ባገርም ባሉ ሙሒቦቹ ጋር በየቀልባቸው በየቤታቸው እየተወሳ አብሯቸው ውሎ አብሯቸው ያነጋል...

ሚስት አይኑረው እንጂ የዘመናችን ሴቶች ባላቸውን ከሚያፈቅሩት በላይ ኡስታዝ ተፈቅሯል እየተፈቀረ ነው... ይፈቀርማል ፍቅሩ ስጋዊ አይደለም አል-ሑቡል ሐቂቂይ...

በስጋ ልጅ አይኑረው እንጂ
እኔ አንተን እንጂ ~ አላውቅ አባቴን
በኡስታዝ ፈድሉ ረሳሁ ~ የቲምነቴን

የሚሉለት ከኮልፌ እስከ ፒያሳ ከተክለ ሀይማኖት እስከ ቦሌ... ደቦል ደቦል የሩሕ ልጆች አሉት።

ኡስታዝ ፈድሉ ق እንደ አባበክር ሲዲቅ ሙሉ ሀብት ንብረቱን ለዲኑ አዋለ። ወዲህ ደግሞ እንደ አባ-ዘር አል-ጊፋርይ.. አል-ፋቲሐ!

# ትንሹ አሚር

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
Audio
#Tnshu amir

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
የ ለይለተል ጁመዕ ጀባታ

አሰላም አለይኩም ያሰይደል ወራ
የፀደዩ ፍካት  የረቢዑ  ጮራ
የጀማሉ ሚበር  የማማር ኮረብታ
የዉበት ጥግ  ኖት የማይመናታ
በረቢዑ ሰኞ  በኢስነይኑ ንጋት
ዘለቁልን ነቢ  የአለሙ መብራት
የረቢዑ ንጉስ   የፀደዩ ሸጋ
የተወዣበረዉ   ከዉኑ ባንቱ ረጋ

ባትመጡማ  ነቢ  ሆነዉ የኛ  ፈንታ
ምድርስ መች ልትኖር  በኑር እንዲህ በርታ
ቀንና  ሌሊቱን  መለየት  ተስኖን
ያላንቱማ  ነቢ   ደካማ  ነበርን 
ረሱሉ ባይመጡማ  አላህ ባይልካቸዉ
ምድር በጨለማ  ነበር  ምትዋጠዉ

የበጎነት ቀንዲል  የከዉኑ አይነታ
አላህ አንቱን  ሰጠን  አርጎ የኛ ፈንታ
የምርጦች  ምርጥ  ኖት የኛ ረሡለላ
አይኔም ሌላ አትመኝ ማየት ካንቱ ሌላ
ይዉረድቦት ነቢ   ሠላትም ሠላምታ
ሣይቋጥ ዳዒም   ሣይሆን የተገታ
በቤተሠባቹ በአህለል በይቱ ሁላ
የአላህ ሰላም ይወረድቦ የአለሙ አይነታ

#ራህመት
#Tenshu amir

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
🖤🖤🖤 አንሰንበት🖤🖤🖤

አንት ጥቁር ደመና ብሶቴን አልቅሰው፣
ወንጀል ያሰረውን መች ይፈታዋል ሰው፣
ኢማኔ ጎደሎ እርምጃዬ አንካሳ፣
ንግግሬ ጥፉ ባህሪዬ እንሰሳ፣
ወይ አምኜ አላምን ወይ ክጄ አልከዳ፣
ወይም አልጠቀም ወይም አልጎዳ፣
ሲመሽም ሲነጋ ሀረሙን እመኛለሁ፣
እምነቴን ጠርጥሬ ትርጓሜ አጣለሁ፣
ሁሉንም ተመልካች አይምሮዬን ሰሪ፣
እንዳላየ ሁኖ ያልፈኛል ፈጣሪ፣
አንዳዴ ስወደው ደሞም ሰቃወመው፣
ወይ ቁጣው ምህረቱ ከወዴት ነው ያለው።

#Tenshu amir

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
💚💚💚 መልካም ልደት ለኔው ነቢ💚💚💚
እና ለኔ

ለቀሪዋ እድሜ ለትንሿ ጊዜ
ከስንፍና ወንጀል ርቄ ከትካዜ
በንስሃ አጊጬ በጠይባ ላይ ቆሜ
ከጸናው በሀረሙ ረውዳውን ሰልሜ
ከሙዕሚኖች ህይወት ከሰሃባ ተጋድሎ
ከሰማዕታት ገድል ብጋራ በቶሎ
ካበቃኸኝ ጌታ ለዛች መልካም ዕለት
አይቀርም መቆሜ ለምስክርነት።

" አይ ሰው "

ምንም ቆዳ ቢያምር በቀለም ቢነከር
ምን ሸክላ ቢሆን ገላ እንኳን ቢጠቁር
ምንም ሀብታም ቢሆን በድሀ ቢወጠር
ምንም ቱጃር ቢሆን ቪላ ውስጥ ቢኖር
የሰው ልጅ እኩል ነው ሲገባ ወደ አፈር

ልክ እንደሞተ ነፍሱ ስትወጣ
ስጋውም ሸተተ ሊቀበር ሲወጣ
ይሸኛል በለቅሶ ህዝቤ ተተራምሶ
የመጣው ይሄዳል እንባውን አፍስሶ
ይንቀባረራል እተተንጎማለለ
ተራው መሆኑን መች አስተዋለ።

✍️ ትንሹ አሚር

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
❤️ ❤️ ❤️ መገርገቢያ ጀባታ ❤️ ❤️ ❤️

ሠይዲ አንተ ጀነቲ ዑምደቲ ወያ ቡግየቲ
አጂድኒ ፊል አሒበቲ

ሠይዲ አንተ ሐቢቢ ወአንተ ኡሚ ወአቢ
ኹዝ ቢየዲ ዒንደ ሺደቲ

ፈቁልኒ ተዓል ኢለይና ወአንተ ሚን መሕቡውቢና
ኡክቱብና ዓለልዙምረቲ

ሠይዲ አንተ ራሐቲ ሐቢቢ ወሓላወቲ
አርሢልኒ ጃረል ቁበቲ

እነዚህ ውብ ስንኞች

<<ወልሰላት ዓላ ሣዳቲ ወልሠላም ዓላ ዑምደቲ
ወሏሂ አንተ ጀነቲ ሣኪኑ ረውዲል ጦይበቲ>>

ከሚለው የሠይዲ ሠይድ አበልራሙዝ(ቀ.ሢ) መድሕ ውስጥ የተመዘዙ ናቸው:: መገን አሕለል ሑቦች, መገን አገላለፅ😍 ሙሉ ሥንኞች እጅግ ውብና ሁሉ እኔ እብስ የሚሉ ናቸው:: ኢንሻአሏህ ሙሉ መድሑ ከድምፅ ጋር በቅርቡ ይለቀቃል::

#Amir Tenshu

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
💚❤️💚 ሂስነይን 💚💚

አንቱ የሙሂቦች የጠይባ ዳር አፈር፥
የሰዎቹ ምስለኔ አለም አሳች ፍጡር፥
ርዕስ የለሽ ፍቅር የመሰንበት ውልም፥
የህብረ ቀለም ጎራ አንቱ የሀቅ ዓለም፥
በይ ቃሌን ተቀበሉ ቃሎትን ላኩልኝ፥
ከልቦት ልባችን ፍቅራችን እንዲናኝ፥
ከራዕማው ከፍታ ከሰማይ ሰማያት፥
ተቀምጠው አያለሁ ከሙሂቡ ሀያት፥
ከሐረማቸው ከደሪሀቸው መንበር ላይ፥
ሀሳቤ እንዲሰምር ተቀምጠው እንዳይ፥
ቀን ሌት አስሳለሁ የመላውን ጉሬ፥
አንድ ቀን ሰምሮልኝ ሆኖልኝ ነገሬ፥
እመጣሎታለው ተነስቼ በእግሬ፥
ከሐረሞት ጠብቁኝ ቀን በመሸ ጊዜ፥
እንደው እንዳልመጣ  ቢበዛ መዘዜ፥
ከአባቶቻችን ሀገር ናፍቆትን አርግዤ፥
ድንገት እመጣለሁ አንድ እራሴን ይዤ።

#ትንሹ አሚር

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
አል‐ኢማመ–ሻፊዒይ ይላሉ : ‐

« በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛትን እወዳለሁ ፤ ይበልጥ በጁሙዓ ለሊት`ና ቀን ማብዛትን ደሞ በጥብቅ እወዳለሁ ። »

📗አል‐ኡም

أَمِـــنْ تَــذَكُّــرِ جِــيــرَانٍ بِــذِي سَــلَــمِ
مَـزَجْـتَ دَمْـعًـا جَـرَى مِـنْ مُـقْـلَـةٍ بِدَمِ
😢

አል‐ቡሰይሪይ

اللهم صل على نبيِّنا مُحَمَّدٍ كلَّما ذَكَرَهُ الذَّاكِرُونَ،
وغَفَل عن ذِكْرِهِ الغافِلُونَ


#Tenshu amir

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
        💖 ማሸር ገበያ ሙባረክ💖

አንቱ ትልቁ ሰው
ተምሞ የጠረቃው ለህልቁ የበቃው
የውበትሁ ጉላት ዝንቱን የማይደርቀው
እንደ ጣና ሙላት ማይረግፈው ማይነጥፈው
እንደ አባይ ፍላት ሲፍህ ሆነ ዛትሁ የተሸበረቀው
በመለኮታዊ ክብ ክብ የጠደቀው
💚በኑር ተሸብቦ በኑር የታጠቀው
ማማር መታመርን ካንቱ የሸቀቀው
ቁንጅናን ቁንጀታን ካንቱ የተመረቀው
የዝናዎት ብስራት በኢንጂን። 💓በተውራት
ዝንቱን የታወቀው- - - -
እንዳንቱ ትልቅ ሰው የለኝም የማቀው

اللهم صل على نبيِّنا مُحَمَّدٍ كلَّما ذَكَرَهُ الذَّاكِرُونَ،
وغَفَل عن ذِكْرِهِ الغافِلُونَ


#Tenshu amir

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
❤️የኸሚስ ጀባታ❤️
💚የሙሃባ ቅኔ💚
የፍቅር ጉዞ ንቆ
ለብቻ እንዳልሄደ፣
ደግሞ አንቱን ወደደ!!
መዋደድን ፈርቶ
ከኋላ እንዳልቀረ፣
አንቱን አፈቀረ!!
ያ ግትሩ ልቤ. . .
በሠዎች ተከቦ ባይተዋር የሆነ
ለፍቅር ወገነ፤
ፅድቅናን ከወነ፤
አይኑ ተከፈተ ለሠው ልጅ አዘነ!!
ለእዝነት ለራሮት በሩን ያልከፈተ
በአንቱ ተለወጠ፤
ለሰው ተደሠተ፤
በፍቅሮ ታድሶ በአቅሙ መፀወተ
መርምሬ የማልፈታዎት
የሁል ቀን ቅኔ ኖት. . .
የሙሃባ ቅኔ ኖት።።።
ያለ እኔ ይሁንታ፤ያለ ገዛ ፈቃዴ
ከትናንቱ አደገ አንቱን በመውደዴ!
ላንቱ በማበዴ ሙሃባዎት ውዴ
በፍቅሮት ምህዋር ላይ ሠላም ስላገኘሁ
ሁሉም የዓለም ኸልቅ ቢያፈቅሮት ተመኘሁ!!


اللهم صل على محمد و على آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد اللهم بارك على محمد و على آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد🤍
#አሚር ትንሹ

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
💚💛ልዩ ኸሚሰ💚💛
🍃 #ዛሬ #ከምታይዋቸው #ውድና #ምርጥ #ቴክስት #ነው

➊ ☞ #ነብዩ  ﷺ አሉ በኔ ላይ በየቀኑ 1000 ሰለዋት የሚያደርግ ሰው
በጀነት ሳይበሸር አይሞትም።

➋ ☞ #ነብዩ  ‏ ﷺአሉ በኔ ላይ በየቀኑ 100 ሰለዋት የሚያደርግ አላህ
100 ሀጃውን ያወጣለታል 70 በጀነት 30 በዱንያ።

➌ ☞#ነብዩ ﷺ አሉ ሲነጋ 10 ሲመሽ 10 ሰለዋት ያደረገ የኔን ሸፈኣ
የቂያማ ቀን ያገኛል።

➍ ☞#ነብዩ  ﷺ አሉ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያለ አላህ 10 ሰለዋት
ይልበተል 10 ሀጥያት ይሰርዝለታል 10 ደረጃ ከፍ ያረገዋል።

➎ ☞ #ነብዩ   ﷺ     አሉ ማንም ሰው ሰላም አይለኝ ም አላህ ሩሄን
መልሶልኝ ሰላምታውን ብመልስለት እንጂ።

➏☞#ለኔ የመጀመርያ ሰዎቼ የቂየማ ቀን እነዚያ በኔላይ በብዛት ሰለዋትን
ያደረጉብኝ ናቸው።
ታድያ ምን እየጠበቅን ነው እኛም ሰለዋት በማብዛት ለረሱት ይሄንን
መልእክት ሰደቃ ጃርያ በማሰብ. ብናስተላልፍ የቂያማ ቀን ያላሰብነው
ስንት ሀሰናት ይጠብቀናል ።
👏የአጅሩ ተካፋይ እንሁን

ለምታውቃቸው ሙስሊሞች ሁሉ ላኩ።

‏﷽
۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى
النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا
عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ ﷺ
#ትንሹ አሚር

በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
🍀🍀🍀
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
ሰይዱል ዓሪፊን ሰይዱና ኑር ሁሰይን ባሌ ረ.ዐ
====== 💚 💕======
*
ብርሀናማ ጨረቃ በጀማዱልሳኒ አጋማሽ ላይ ስትዘልቅ ከወደ ባሌ አናጂና ደማቅ የአሺቆች መዐድ  ይኖራል ገልገለ ጎበና መውሊድ
*
ሰባት ክፍለ ዘመናትን የኋሊት መለስ ብለን ስንቃኝ ከታሪክ ብራና ላይ ይሄንን በወርቃማ ቀለም ተከትቦ እናገኛለን.. ከገውሱል አዕዞም ..💚ሰይድ ዐብዱልቃዲር አል-ጀይላኒ መድረሳ ምሩቅ የሆኑ 405 ተማሪዎች💚 በሸይኽ አባዲር እየተመሩ ወደ ጥንታዊቷ ሀረር ከተማ ይዘልቃሉ በዚህ እንቁ ስብስብ ውስጥ ሸይኽ ኢብራሂም የተባሉ ፈርጥ ነበሩበት
*
💚 💕 ሸይኽ ኢብራሂም ቁረይሺይ ናቸው፣ የዘር ሀረጋቸው ከአቂል ቢን አቡጧሊብ ይመዘዛል.. ይህም አህለልበይት ያደርጋቸዋል የኋላ ኋላ ከወደ ባሌ አናጂና ቀበሌ ዘልቀው እመት ማኪዳ ጋር በትዳር ይጣመራሉ መልካም ፍሬዎችንም ያፈራሉ የሀበሻውን የብርሃነ ቀንዲል  ተወዳጁ ልዑልም ከፍሬዎቻቸው መካከል ናቸው።
*
💚ሸይኹ ሰቀለይን ቁጥቡል ሀበሻ ሰይዱል ዓሪፊን ሰይዱና ኑር ሁሰይን ባሌ … አቢዮ በመባል ይታወቃሉ..ከ400 አመታት በላይ በህይወት እንደኖሩ ተዘግቧል ሀበሻን በማቅናት ወደርየለሽ ገድል ፈፀመዋል..ሰለእርሳቸው የህይወት ታሪክ አያሌ ምሁራን ጥልቅ ጥናት አድርገዋል..ግለ ታሪካቸው "ረቢዐል ቁሉብ"ደግሞ ከመሻኢኾቻችን ዘንድ እጅግ ውዱ ንብረት፣ የተከበረው ካዝናቸው ነው። አንድ ውብ ንግግራቸውን ለናሙና
*
      «ድር ፤ ለሸረሪት ብቸኛ መንገዷ ብቻ ሳይሆን ሌላን የማያስጉዝ ጭምርም ነው ቦይም ዉሃን'ንጂ ሌላን አያሳልፍም ውሃውም ያለ ቦይ ሲፈስ  አጥፊ ነው ልክ እንዲሁ የአዋቂዎች መንገድም አዋቂዎችን ብቻ የሚያስጉዝ ነዉ»
            ሰይዱና ኑር ሁሰይን ባሌ ረ.ዐ 
ትንሹ አሚር
በቴሌግራም
❀ይ🀄️🀄️ሉን!
👇👇👇
https://www.tgoop.com/Tenshu6793
2025/01/21 10:18:08
Back to Top
HTML Embed Code: