tgoop.com/Terbinos/12743
Last Update:
👉🏼 በሱባዔ ጊዜ
••
በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወይም ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ መዝ.5፡3፤ መዝ.133፡2፤ ዮሐ.11፡41፡፡
••
በሱባዔ ወቅት በቅደም ተከተል መጸለይ አለብን፡፡ መጀመሪያ « በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አአትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀል በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ መላ ሰውነቴን በትእምርተ መስቀል አማትባለሁ » እያለ ሰጊድን ከሚያነሣው ሲደርስ መስገድ መስቀልን ከሚያነሣ ላይ ስንደርስ ማማተብ ይገባል፡፡
••
በማስከተል አቡነ ዘበሰማያት ፣ መዝሙረ ዳዊት ፣ ውዳሴ ማርያምና ሌሎች በመዝገበ ጸሎት የተካተቱትን መጸለይ ፤ ቀጥሎ አቡነ ዘበሰማያት ፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን፣ ጸሎተ ሃይማኖትን ከጸለይን በኋላ አቡነ ዘበሰማያት መድገም፤ ከዚያ 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይባላል፡፡ ሌላው በሱባዔ ጊዜ ከተሓራሚ የሚጠበቀው ነገር ኃጢኣቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ነው፡፡ ሲያለቅስም ለእያንዳንዱ በደል እንባ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡
••
በመጨረሻም ሱባዔ የገባ ሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡
•••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
BY ❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Share with your friend now:
tgoop.com/Terbinos/12743