tgoop.com/Terbinos/12776
Last Update:
እንኳን ለአምላክ ወሰብእ ለቅዱስ አማኑኤል ዓመታዊ በዓል አደረሰን።
••
ጥቅምት 28 || " የምስራቁ ነፋስ አንበጣዎችን አመጣ። " ዘጸአት 10፤13
••
የበዓሉ መሰረትና ታሪክ ይህ ነው በወርሐ ጥቅምት እንዲህ ሆነ በሱዳን በኩል የመጣ አንበጣ የኢትዮጵያን ምድር ከል መስሎ ወረሳት የተዘራው ሳይሰበሰብ የአንበጣ እራት ሊሆን ሆነ። ንጉሠ ሸዋ ሣህለ ሥላሴ
ወደ ታላቁና ተአምረኛው ሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል ደብር ሄደው እንባቸውን በእጃቸው አቁተው አዝነው ቅዱስ አማኑኤል ፈጣሪዬ አምላኬ ሆይ የመጣው የአንበጣ መንጋ ከጠፋ ሕዝቤ ከሰቀቀን ድኖ የዘራውን አጭዶ ከጎተራ ከገባ በአዋጅ ነጋሪት ጎስሜ ቀንደ መለከት አስነፍቼ ድብ አንበሳ ነጋሪት አስመትቼ ታቦትህን በካህናቱ አስወጥቼ አከብራለሁ ብለው ስዕለት ያደርጋሉ የአንበጣው መንጋ ሰማይ ያርግ ምድር ይስረግ ሳይታወቅ አንድ ሰብል ሳያጠፋ ከኢትዮጵያ ምድር ይጠፋል በዓሉም በዚያ ምክንያት ተጀመረ የአባቶቻችን ስም ላለመጥራት ታሪክ አናድበስብስ መሰረቱ ይህ ነው።
••
በበዓሉ የሚከብረው ስሙ የሚወደሰውም ወሰብእ ቅዱስ አማኑኤል ነው ቸርነቱ የተገለጠበት ተአምራቱ የታየባት እምርት እለት። በአባቶቻችን መዲና አዲስአበባ መርካቶ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ደብር ሁላችንም ተገኝተን እናክብር።
••
አምላካችን በቸርነቱ ይመልከተን ምድራችንን የወረረውን የዘረኝነት አንበጣ ያጥፋልን በየልቦናችን ያቆምነውን የዘረኝነት ጣኦት በኃይለ መለኮቱ ያቅልጥልን አስተዋይ ለሕዝብ የሚያስብ መሪ አይንሳን እኛንም ገባርያነ ሰላም ያድርገን ከዘረኝነት ደዌ ከፍቅር ረሐብ ከዝሙት እሳት ከክሕደት አሽክላ ይሰውረን በፈቃዳቸው ላበዱ ፈውስን ብረት ላነሱ ትዕግስቱን ያድልልን አሜን አሜን አሜን
BY ❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Share with your friend now:
tgoop.com/Terbinos/12776