👉 ከትንሣኤ በኋላ ያሉ የዕለታት ስያሜ
🛑 ሰኞ
ማዕዶት ይባላል፡-
🛑 ማክሰኞ
ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
🛑 ረቡዕ
አልአዛር ይባላል፡-
🛑 ሐሙስ
አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
🛑 አርብ
ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
🛑 ቅዳሜ
ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
••
🛑 እሁድ
ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡-
••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️
••
🛑 ሰኞ
ማዕዶት ይባላል፡-
ማዕዶት ማለት መሻገር ፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ፣ ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከሲኦል ወደ ገነት ፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡🛑 ማክሰኞ
ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
🛑 ረቡዕ
አልአዛር ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡🛑 ሐሙስ
አዳም ሐሙስ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡🛑 አርብ
ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
🛑 ቅዳሜ
ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡••
🛑 እሁድ
ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡-
በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️
••
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም ፤
በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ ”
•••••••••••
❤️ ልደታ ማርያም ❤️
••••••••••••
ባንቺ ምክንያት የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል እውን ሆንዋል እና የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው። የእርሷ እርሱን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለድ ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ሕሊና የሚታወቅ መሆኑን ያስረዳናል። (ኢሳ ፯:፲፬ ፱:፮)
••
የእመቤታችን ልደት ( ልደታ ለማርያም ) የዓለም መዳን የማይቀር መሆኑ ለታወቀበት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መንገድ የጠረገ ልደት ነው እንላለን።
••
👉🏼 እርሱ ብርሃን እርሷ የብርሃን እናት ናት ( ዮሐ፰:፲፪ )
👉🏼 እርሱ እውነተኛ ደስታ እርሷ የደስታ መፍሰሻ ናት። ( መሀልይ ፬:፲፭ )
👉🏼 እርሱ የባሕርይ አምላክ እርሷ ደግሞ ወላዲተ አምላክ ( Theotokos ) ናት::
••
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በአል አደረሳችኹ። ጣእሟ ፣ ፍቅሯ ፣ በረከቷ ይደርብን🙏
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

❤️ #ቅዱስ_ሚካኤል
•••
በክንፈ ረድኤትክ ጠባቂዬ ፣ ከስህተት ታዳጊዬ ፣ ተንከባክበክ በቸርነት ጌጥ የምታስጌጠኝ ሩህሩህ አባቴ ዛሬም ከእኔ ደካማው አትለየኝ አሜን!
•••
ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ የታመነ ሁሉ ከመከራና ከጭንቀት ይድናል። የእግዚአብሔር አገልጋይ ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ ረዳት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ጥበቃው ፣ ረድኤት፣ በረከቱና አማላጅነቱ አይለየን ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ከጭንቀትና ከመከራ ይጠብቀ አሜን!
••••

በጠባቅዎች መሃል ኬፋን ከእንቅልፉ አንቅቷል
የተዘጋውን ደጃፍ አልተሳነውም ማለፍ
ሚካኤል እየመራው ጴጥሮስ እግሩ የቀናው
አውቆታል ልቡ በርቶ ዘለለ ስሙን ጠርቶ
•••
የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው
ለጶርዓ ሰው ለማኑሄ እንደነገረው
በመሰዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ

👉🏼 ቅዱስ ማር ሚናስ
••
የክርስቶስ ምርጥ ጭፍራ ከገንዘብ ይልቅ ጽድቅን የመረጠ እንደ ምሳሌው እንደጨረቃ ለደመቀና እንደ ፀሓይም ብሩህ ለኾነ ለሚናስ ሰላምታ ይገባል
••
ለእስትንፋስከ ሚናስ ሆይ እንደ አፈውና ርኄ እንደተባሉ ሽቱዎች ፤ በአራቱ ማዕዘን ለሚአውድ እስትንፋስህ ሰላምታ ይገባል ፤ ኤሎሄ የተባለ የኢየሱስ ምስክሩ የተመረጥክ ሚናስ ሆይ ፤ በቤተ መቅደስህ ምስጋና የሚያቀርቡትን ባርካቸው ከጥፋትም አድናቸው •••• ቅዱስ ማር ሚናስ ወር በገባ በ15ኛው ቀን መታሰቢያ በዓሉ ነው በረከቱ ይደርብን
••
በቅዱሳን አባታቶችን ምልጃ ጸሎት ከዘረኝነት ደዌ ከፍቅር ረሐብ ከዝሙት እሳት ከክሕደት አሽክላ መድኃኔዓለም ይሰውረን የእግዚአብሔርን ቸርነት የቅዱሳንን ተራዳኢነት ለመመስከር ያብቃን ቅዱስ ማር ሚናስ ስሙን ስንጠራ ከአይን ጥቅሻ ከአባ ቄርሎስ ጋር ከተፍ ይበልልን ድንቅን ያድርግልን።
••••••

መከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የአለሟን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺ ደግነት
ባርያሽን ሰውሪኝ ከአስጨናቂው ሞት
••
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ
••
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችንን
ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምትጠብቀኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ አንተ እንድትጠብቀኝ በአምላክ ቸርነት በዛሬው ዕለት ለአንተ ተሰጥቻለሁና አእምሮዬን አብራልኝ፡፡ ኃጢአትን እንድንቅ ፣ እግዚአብሔር መፍራትን እንድጨምር ፣ በማንም ላይ እንዳልፈርድ ፣ ድሀ አደጉንም እንዳልረግጥ ፣ በሐሰተኛ አንደበት እንዳላታልልና ከክፉ ሥራዎች ጋር ሁሉ እንዳልተባበር ጠብቀኝ፡፡
••
በችግሬ ግዜም ኃይልህና እርዳታህ አይለየኝ፡፡ አንተ ቅዱስ መልአክ ሆይ! ከዲያብሎስና ከዓለም ጋር በማደርገው ውጊያ ፈጥነህ ደርሰህ እርዳኝ፡፡
••
እኔ ባርያህ ዕለቱን ሁሉ ጌታን በማክበር ለቃሉ በመታዘዝ ፣ አማላጅነትህንና ጥበቃህን ረዳት አድርጌ በቅድስና ለመኖር እንድችል በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንድመራ አድርገኝ፡፡
••
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ክብር ምስጋና ይገባሃል ዛሬም ዘውትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
••
በችግሬ ግዜም ኃይልህና እርዳታህ አይለየኝ፡፡ አንተ ቅዱስ መልአክ ሆይ! ከዲያብሎስና ከዓለም ጋር በማደርገው ውጊያ ፈጥነህ ደርሰህ እርዳኝ፡፡
••
እኔ ባርያህ ዕለቱን ሁሉ ጌታን በማክበር ለቃሉ በመታዘዝ ፣ አማላጅነትህንና ጥበቃህን ረዳት አድርጌ በቅድስና ለመኖር እንድችል በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንድመራ አድርገኝ፡፡
••
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ክብር ምስጋና ይገባሃል ዛሬም ዘውትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
Video
❤️ ግንቦት 21|| ደብረ ምጥማቅ
•••
ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ።
•••
እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል። አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ።
•••
ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል ።
•••
ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል። ሁለተኛም ደግሞ የጻድቃን አንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ።
•••
ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር።
•••
እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል።
•••
እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ።
•••
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን አሜን::
•••
ስንክሳር ዘተዋሕዶ

👉🏼 ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ አባ ተክለሃይማኖት ሀገርህን ኢትዮጵያን እኛን ልጆችህን በክንፎችህ ከልለን ፣ በበትረ መስቀልህ ባርከን አሜን‼️‼️
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🛑 #ማስጠንቀቂያ - ለወላጆች በሙሉ
••
👉 ሕፃናት ልጆቻችሁን በሰንበትም ይሁን በሌላ ቀን ለምታስቆርበለ ወላጆች ቅዳሴ አሃዱ ብሎ ሲጀመር ጀምሮ በቅዳሴው መሳተፍ ይገባችኋል። ከአቅም በላይ ከሆነ ቅዱስ ወንጌል ከመነበቡ በፊት ድረሱ አለዚያ ከእግዚኦታ በኃላ እየመጣችሁ አታስቆርቧቸው። በተለይ ቤተሠችሁ ከቤተክርስቲያን ቅርብ የሆነ።
••
👉 ለማስቆረብ ስትመጡ ረዥም ቀሚስ ፣ ከሰውነት ጋር ያልተጣበቀ ልብስ ፣ ሻሽ ፣ ረዥም ነጠላ መልበስ ግዴታ ነው ሲሆን ጠፍር ቀለምና ከንፈር ማቅለሚያ ብ፣ ብልጭልጭ ነገሮችን አለመጠቀም።
••
📎 ክርስቲያናዊ አለባበስና ክርስቲያናዊ ስርዓት ሊኖራችሁ ይገባል።

⛪ ግንቦት 26 || አቡነ ሀብተማርያም
••
በገድል የተጠመዱ ኮከብ ገዳማዊ የጽድቅ የትሩፋት ሕይወታቸው እንደ ባሕር አሸዋ የበዛላቸው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሀብተማርያም ልደታቸው ነው።
••
የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በስጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር
••
ለዮስቲና አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም
••
ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የገድሉና የትሩፋቱ ዜና እስከ ዓለም ዳርቻ ይደርሳል በህይወተ ስጋ ሳለ በፈጣሪው እግዚአብሔር ፍቃድ የብዙዎችን ሰዎች ነፍሳት ከሲኦል ያወጣል እንደ መላእክትም ክንፈ ፀጋ ተሰጥቶታል፤ በሰው አካል ከስጋ ሆኖ ሳለ በተመስጦ ወደ ሰማይ የሥላሴን የአንድነትን የሦስትነትን ምስጢር ያያል አላት የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና ነሃሴ 26 ቀን ጸነሱ፡፡
ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታቸው እጅግ
ያመረ ጻዲቅ ወለደች።
••
በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ...

በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ይጸልዩ ነበር፡፡ ባደጉም ጊዜ ይህን ጸሎት ደጋግመው ይጸልዩ ነበር።
••
ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ ሚስት አጩላቸው፤ እርሳቸው ግን የድንግልናን ህይወት በመምረጥ ከወላጃቸው ቤት ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡
••
ዛሬ ይሰበይ ገዳም ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ለሦስት ወራት ጽሙድ እንደበሬ ትጉህ እንደ ገበሬ እንዲሉ በጾም በጸሎት ተጠምደው ሳለ መታሰቢያህን በዚህ ዋሻ አደርግልሃለሁ በማለት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል።
••
👉 አቡነ ሀብተ ማርያምም ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ ገድላቸውንና ትሩፋታቸውን በማብዛት በሳምንት አንድ ጊዜ ቅጠልን ብቻ የሚመገቡ ሆኑ፡፡
••
👉 አርባ አርባ ቀን ሰማንያ ሰማንያ ቀንም የሚጾሙበት ጊዜ ነበር፡፡
👉 በሌሊትም ወደ ጥልቅ ባሕር እየገቡ በየቀኑ 150 መዝሙረ ዳዊት፣ 4ቱአራቱን ወንጌላትና ሌሎች የጸሎት መጽሐፍትን ይደግሙ ነበር፡ ፊታቸውም እንደ ንጋት ምሥራቅ ኮከብ ያበራ ጀመር፡፡
••
👉 ቅዱስ ሚካኤል ከእርሳቸው እንዳይለይ የዘወትር ጠባቂ አድርጎ ሰጣቸው
👉 ከገድላቸው ከትሩፋታቸው ብዛት የእሳት የብርሃን ሰረገላ የተሰጣቸው።
••••
👉 7 አክሊላት የተሰጡት ቅዱስ አባት ናቸው
❤️ ስለ ንፅሕ ክህነትና ማዕጠንት
❤️ ስለምናኔ
❤️ ስለ ድንግልና
❤️ ስለ ወንጌል ፍቅር
❤️ ስለ ቂምና በቀል ስላለመያዝ
❤️ ስለ ተባረከ ምንኩስና
•••
👉በጸሎትህ አምኖ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ፣ ስምህን የጠራውን ዝክርህን ያዘከረውን ሁሉ የሀብተ ማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በኅሊና ያሰበውን በልቡናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ።
•••
በዓለ ጊዜ እረፍታቸው በደረሰ ጊዜ ጌታ ተገልጦላቸው ስለ ተጋድሎአቸውና ስለንጽህናቸው ሰባት አክሊል እንደሚቀበሉ ነግሯቸዋል።
•••
ህዳር 26 ቀን ዐርፈዋል በደብረሊባኖስ ገዳም መካነ ቅዱሳን ይገኛልን ። የአባታችን አቡነ ሀብተማርያም ረድኤት በረከት በሁላችንም ይደርብን።
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
••
ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ ሚስት አጩላቸው፤ እርሳቸው ግን የድንግልናን ህይወት በመምረጥ ከወላጃቸው ቤት ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡
••
ዛሬ ይሰበይ ገዳም ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ለሦስት ወራት ጽሙድ እንደበሬ ትጉህ እንደ ገበሬ እንዲሉ በጾም በጸሎት ተጠምደው ሳለ መታሰቢያህን በዚህ ዋሻ አደርግልሃለሁ በማለት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል።
••
👉 አቡነ ሀብተ ማርያምም ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ ገድላቸውንና ትሩፋታቸውን በማብዛት በሳምንት አንድ ጊዜ ቅጠልን ብቻ የሚመገቡ ሆኑ፡፡
••
👉 አርባ አርባ ቀን ሰማንያ ሰማንያ ቀንም የሚጾሙበት ጊዜ ነበር፡፡
👉 በሌሊትም ወደ ጥልቅ ባሕር እየገቡ በየቀኑ 150 መዝሙረ ዳዊት፣ 4ቱአራቱን ወንጌላትና ሌሎች የጸሎት መጽሐፍትን ይደግሙ ነበር፡ ፊታቸውም እንደ ንጋት ምሥራቅ ኮከብ ያበራ ጀመር፡፡
••
👉 ቅዱስ ሚካኤል ከእርሳቸው እንዳይለይ የዘወትር ጠባቂ አድርጎ ሰጣቸው
👉 ከገድላቸው ከትሩፋታቸው ብዛት የእሳት የብርሃን ሰረገላ የተሰጣቸው።
••••
👉 7 አክሊላት የተሰጡት ቅዱስ አባት ናቸው
❤️ ስለ ንፅሕ ክህነትና ማዕጠንት
❤️ ስለምናኔ
❤️ ስለ ድንግልና
❤️ ስለ ወንጌል ፍቅር
❤️ ስለ ቂምና በቀል ስላለመያዝ
❤️ ስለ ተባረከ ምንኩስና
•••
👉በጸሎትህ አምኖ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ፣ ስምህን የጠራውን ዝክርህን ያዘከረውን ሁሉ የሀብተ ማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በኅሊና ያሰበውን በልቡናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ።
•••
በዓለ ጊዜ እረፍታቸው በደረሰ ጊዜ ጌታ ተገልጦላቸው ስለ ተጋድሎአቸውና ስለንጽህናቸው ሰባት አክሊል እንደሚቀበሉ ነግሯቸዋል።
•••
ህዳር 26 ቀን ዐርፈዋል በደብረሊባኖስ ገዳም መካነ ቅዱሳን ይገኛልን ። የአባታችን አቡነ ሀብተማርያም ረድኤት በረከት በሁላችንም ይደርብን።
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
••
እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም {ማቴ፣11÷11}
•••
መጥምቁ ዮሐንስ በያለንበት ከክፉ ነገር ይጠብቀን! አሜን፫

❤️ #እግዚአብሔር_ዐረገ
❤️እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ አደረሳችሁአደረሰን 🙏
••
የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡
••
ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡
••
እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡
•

ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
••
እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡
••
ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡
••
ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡
••
አምላክ በእልልታ ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። መዝ ፵፮ ፡ ፭
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
••
እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡
••
ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡
••
ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡
••
አምላክ በእልልታ ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። መዝ ፵፮ ፡ ፭
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tgoop.com/Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ሰኔ 12 || #ቅዱስ_ሚካኤል
••
እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን‼️
••
ታሪኩ እንዲህ ነውቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ እርሷም በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ደገኛ ሴት ናት፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደ ደረሰባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ ባሏም ታሞ ሞቶ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኩሴ መስሎ አጋንንትን መነኮሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡
••
እርሷም "ከቤትገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ" አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም "እኛማ በነግህ ጸልየናል?" አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን."... እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ" አላት፡፡

ቅድስት አፎምያም "አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ አትጸልዩ ያልከኝ ጌታ ምጽዋት አበድር እመስዋዕት ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? እርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም ታዲያ ጥንት በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?" ብላ ሞገተችው፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ ከላይ እንዳየነው ..በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡
••
በሰኔ 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድር ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን ፣ ያዕቆብን ፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡
••
ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታበቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና "የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?" በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡ ለጊዜው " በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም" ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ። ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእርሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ በመቀጠልም ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ሰይጣናዊ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡
••
ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን "ድረስልኝ" እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደ የመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ 12 ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡
••••
#ቅዱስ_ሚካኤል ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን 🙏
•••••••