Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
3010 - Telegram Web
Telegram Web
🙏🙏🙏

#ለጥንቃቄ🚨

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ?

1. ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦

ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

2. በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦

በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

3. በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦

ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

4. መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦

የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።
Forwarded from Biranaye Tube (Tesfa🌱SEED)
#zoo

28 ቀን ቀረው። በዚህች ጊዜ ብትሰሩ እንኳን በ 1 ወር ከ 10,000 በላይ ታገኛላችሁ።

Start here...👇👇👇
http://www.tgoop.com/zoo_story_bot/game?startapp=ref718657460

Join us...
    ✦✺ @Biranayetube ✺✦
    ✦✺ @Biranayetube ✺✦
ጦርነት ላይ ሆነን እናመሰግናለን
ረሃብ ላይ ሆነን እናመሰግናለን
ስደት ላይ ሆነን እናመሰግናለን
እ የ ተ ገ ደ ል ን እናመሰግናለን
መፈናቀል ላይ ሆነን እናመሰግናለን
መሬት እየተንቀጠቀጠም ቢሆን እናመሰግናለን ።

#እግዚአብሔር_ይመስገን።

የአእላፋት ዝማሬ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 10:00 ጀምሮ።
- ስርአት ሚያከብር ህዝብ
- ድምጼ ይሰማ ብለው የማይጯጯሁ ዲያቆናት እና ዘማሪያን
- በከበሮ ትርኢት ማይሰሩ ከበሮ መቺዎች
- ህዝብ የማይረብሹ የካሜራ ባለሙያዎች
- ትህትና ያላቸው አስተናጋጆች
- አላስፈላጊ ንግግር የማያረግ መርሀ ግብር መሪ
- ያልተጎተተ እና ያልትሯሯጠ አዘማመር
- ትክክለኛና የተመጠነ ሜሴጂንግ
- ያሬዳዊውን በአግባቡ የያዘ የመዝሙር ምርጫ
- አስደናቂ ቅንጅት
- በጣም ብዙ ሎጀስቲካል አቅም

ብቻ ብዙ ብዙ ጥሩ ነገሮች ነበሩ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿን በአግባቡ ከተጠቀመች ምን መስራት እንደሚቻል አይተናል፡፡

መልካም በዓል!
ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ: ጽሁፉ እንዲህ ይላል

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል: ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው::

ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል: የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነው: እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለስኩላቸው

አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው - "ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይ ሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል"

ቀጠሉ እማማ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም" 50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው
ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩም: የመጣውን ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት

ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት!

ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝ

"ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነበር: የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?"

በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት😍
የአሜሪካ ፊልም ማምረቻዋ ሆሊውድ መገኛ ሎስአንጀለስ በከባድ የሰደድ እሳት እየነደደች ትገኛለች።

እስካሁኗ ሰዓት ድረስ 57 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሀብትና ንብረቶች ወደ አመድነት የተቀየሩ ሲሆን ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል

በአራት አቅጣጫ የተነሱትን እነዚህን አውዳሚ እሳቶች ለመቆጣጥ ከአቅም በላይ የሆኑ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ተለያየ አቅጣጫ እየተዛመቱ ይገኛሉ።
Romance scam
በሀገራችን በብዛት እየተስፋፋ ያለው romance ( ፍቅር መሰል) scam ምንድን ነው?

Romance scam ማለት አንድ ያልታወቀ ወይም fake ማንነት ያለው ሰው ገንዘብ ወይም ሌላ አስፈላጊ ነገር ለማግኘት ሲል ሰዎችን በጾታዊ ፍቅር የሚቀርብበት የscam አይነት ነው።

በዚህ scam ብዙ የሃገራችን ሴቶች ለፍተው ያገኙትን ገንዘብ ተጭበርብረዋል። ከዚህ በተጨማሪ በፍቅር ሰበብ የዕርቃን ፎቶ፣ ሚስጥራዊ የፅሁፍና የድምፅ መልዕክት በማስላክና እንደ መያዣ በመጠቀም ማስፈራራት ወይም ገንዘብ መጠየቅ ይስተዋላል።

ስለዚህ እባካችሁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የፍቅር ግንኙነት ስትጀምሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።

ለማንም ሰው ቢሆን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ምንም አይነት የግል ስብዕናን የሚያጎድፍ ማንነትን የሚያጋልጥ ፎቶ፣ ቪዲዮ ወይም የድምፅ መልዕክት አትላኩ።
ነጋችሁን እንዳታበላሹ!!
ባህል ወይስ ሃይማኖት
ይህ ባህል ነው ባህሉም ኤርትራ ውስጥ ዲያቆን ሲያገባ፣ የሚፈጸም ስርአት ነው።
የጎሽ ቀንድ ምልክትነቱ፣ ጎሽ በህይወቱ አንድ ሴት ብቻ ነው የሚኖረው። አስገራሚው ነገር ጎሽ ሚስቱን በሞት ቢያጣ እንኳ ሌላ ሴት ጎሽ አያገባም። ስለዚህ ዲያቆን አንዴ ካገባ ሌላ ማግባት እንደሌለበት ለማሳየት ነው !

በኤርትራ ብቻ ሳይሆን አልፎ አልፎ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎችም ስርዓቱ ይፈጸማል ....

በድጋሚ ለማስታወስ ይህ ባህል ነው፥ የቤተክርስቲያን ስርዐት አይደለም። ግን ምሳሌው ይበል የሚያሰኝ የሚደንቅም ነው ....።

በነገራችን ላይ ቤተክርስቲያን ጥንቅቅ ተደርጋ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተሞሸረች ተጠናቃም የተሰራች ናትና ለሁሉ ትክክለኛ መልስ አላት ::

ባህልና የቤተክርስቲያን ስርዓት የሚጋጭባችሁም አይነ ልቦናችሁን ያብራላችሁ ከማለት እና ስለ እናንተ ከልብ ከመጸለይ ውጭ ምንም ልንላችሁ አንችልም።
መምህር ሐይሉ ከጎንደር ዩንቨርስቲ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል:-

"ስለ 'ኖራ' ምንነት በጥሬው ከማንሳቴ በፊት ስለ እድሳት ወይንም renovation አንድ ነገር ማለት ፈለግኩ። አጠር ባለ አማርኛ ሲገለፅ የቅርስን ታሪካዊ የስነ-ህንፃ እሴት በጠበቀ መልኩ፣ ይዘቱን ሳይቀይር መጠገን ወይንም ማጠናከር ማለት ነው። በፋሲለደስ ግንብ ላይ የተደረገው ከዚህ የተለየ ነገር አይደለም።

"ኖራ የድንጋዮቹ ማያያዣ ንጥረ ነገር እንጂ በራሱ ቀለም አይደለም።

"በተፈጥሮ ኖራ ሂደቱ መጀመርያ ነጭ ሲሆን ቀጥሎ አይቮሪ ወይም ቦላእማ ከለር በመቀጠል ካኪ ሲቆይ ይቀላል።

"አባቶቻችን ታሪካዊውን ግንብ ሲሰሩ ኖራን መጠቀማቸው ላይ ምንም ጥያቄ የለም። የኖራ ሚና ለቀለምነት ሳይሆን ግብአቶችን ለማያያዣ ነው። ለዚህ አገልግሎት ከመዋሉ በፊት ከ6 ወራት በላይ ያህል እንደሚቀበርም ይነገራል።

በጣና ውስጥ ያሉ እድሜ ጠገብ ገዳማት፤ እነ ናርጋ ስላሴ፣ እነ ዳጋ እሰጢፋኖስ፣ እነ ጣና ቂርቆስ ሲታደሱ በዚሁ መንገድ ነው የታደሱት። የተቀባ አንድም ቀለም የለም።"
ስፔናዊው አትሌት ኢቫን ፈርናንዴዝ እና ኬንያዊው አትሌት አቤል ሙታይ በአንድ የሀገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ላይ ለሜዳልያ ፉክክር እያደረጉ ነበር።

ኬንያዊው አቤል ሙታይ ውድድሩን እየመራ ስፔናዊው ኢቫን ፈርናንዴዝ ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ እየተከተለው ትንቅን ላይ ነበሩ።

በድንገት ግን ከውድድሩ ፍጻሜ መስመር ላይ ሊደርሱ በግምት 10 ሜትር ገደማ ሲቀራቸው ኬንያዊው የውድድሩ መሪ አቤል ሙታይ ውድድሩን ያጠናቀቀ መስሎት በስህተት ውድድሩን አቋርጦ ቆመ:: ይህንን ክስተት የተመለከተው ስፔናዊው ሯጭ አቤል ሙታይ ውድድሩን እንዲቀጥል እና መስመሩን እንዲያቋርጥ ከኃላው ሆኖ ይጮህበት ጀመር

የስፓኒሽ ቋንቋ ጆሮውን ቢቆርጡት የማይሰማው አቤል ሙታይ ምን እንደተፈጠረ ሊገባው አልቻለም:: በመሆኑም ስፔናዊው ሯጭ ኢቫን መስመሩን አቋርጦ ውድድሩን ከማሸነፍ ይልቅ አቤል ሙታይን በመግፋት ውድድሩን አሸንፎ የወርቅ ሜዳልያውን እንዲያሸንፍ አደረገው።

ውድድሩ መጠናቀቁ ተከትሎ አንድ ጋዜጠኛ ለኢቫን ጥያቄ አቀረበለት ...

"ለምን እንደዚያ አደረግክ?"

"የእኔ የህይወት ህልም አንዳችን ሌላችንን በመግፋት አሸናፊ እንድንሆን ማገዝ ነው:: ህልሜ እርስ በእርሱ ተደጋግፎ አሸናፊ የሚሆን ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው" ሲል መለሰለት።

"ለምን ኬንያዊው እንዲያሸንፍ አደረግክ ?" ደግሞ ጠየቀው

"እኔ እንዲያሸንፍ አላደረግኩትም:: እሱ መጀመርያም ሊያሸንፍ ነበር"

"ግን እኮ አሸንፈህ የወርቅ ሜዳልያውን ማጥለቅ ትችል ነበር" ጋዜጠኛው አሁንም ጠየቀው

"ድል የማድረግ መርሁ እና ጣእሙ ምንድነው? እንዲህ ሆኖ የማሸንፈው ሜዳሊያ ክብሩ ምንድነው? እናቴ ይህንን ስታይ ምን ትለኛለች?" ሲል ጋዜጠኛውን አስደመመው

Moral of the story 👉አሸንፍ...ሌሎችም እንዲያሸንፉ አድርግ!
"የዓለም ብርሃን ኢትዮጵያ ናት" የምትሉ ሰዎች አርፋችሁ ተቀመጡ። ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚባል የጅል ስብስብ ነው። የምሬን ነው። የዓለም ብርሃን ክርስቶስ ነው። እንጂ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ሆናም አታውቅም። አትሆንምም። የዓለም ብርሃን ማነው? ክርስቶስ! ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን አይደለችም።

ማነው ያላችሁ እንደዚህ? ከቤቱክርስቲያን ሰውን ለማጥፋት የሚዘየድ ስብስብ ነው። ብር ካጣችሁ ነግዱ። እውነቴን ነው። ነግዱ፣ ሥሩ። የኢትዮጵያ ስው ብር መናቅ ይወዳል። ሥራ መናቅ ይወዳል። ...ደሞ ለሁሉት ሺ ብር ይላል። ወይ ጥጋብ! እንደው እኔንተ እንደው። አንዳንዱ ደሞ ኩራት ራት ነው ይላል። እንደው ከመቼ እለት ወዲህ ነው ኩራት ራት ሆኖ የሚያውቀው? እስቲ እንደው ቅመሰው፤ እየኮራህ ሶስት ቅን ተኛና ሲሉበልብህ ታገኘዋለህ።

እንደው እውነቴን ነው ሥሩ ይልቅ። ኩሬት ራት ሆኖ አያውቅም። ሲራክ ምን አለ? ሶስት ሰዎች ነፍሴን አበሳጯት አለ። ሴሰኛ ሽማግሌ። ንፉግ ባለጸጋ እና ትእቢተኛ ደሀ። እኛ ኢትዮጵያውያን [ማለት] መፎከር ምንም አይሰራም። መስራት መጽደቅ ነው።

አባ ገብረኪዳን 💛
የቡና የጤና ጥቅሞች

የፍየሏን ባህርይ መቀያየር የተመለከተው እረኛው ካሊድ ለፍየሏ መነቃቃት የሰጣትን የቡና ተክል ማግኘቱ እና በተለያዩ መንገዶች መጠቀም መጀመሩ ይታወሳል።

በዚህ መንገድ የጀመረው የሰው እና የቡና ግንኙነት እያደገ መጥቶ አሁን ላይ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳጅ እና በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ለመሆንም በቅቷል።

መገኛውን ኢትዮጵያ ያደረገው የቡና ተክል በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አገራት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ምንጭ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ ይህ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ መላው አለም የተሰራጨው ቡና ከሚፈጥረው መነቃቃት በተጨማሪ የጤና ጥቅሞች እንዳሉትም የተለያዩ ጥናቶች አመላክተዋል።

በቡና ላይ የተደረጉ የተለያዩ ጥናቶችን በመጥቀስም ቡና በርካታ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ቢቢሲ በገጹ አስነብቧል፡፡
አስበው ቻይናዊ ሆኖ ቲክቶክን አላውቅም ሲል ።

ለአንድ ከቻይና ወጥቶ ለማያውቅ ሰው ፡ በአለም ላይ አብዛኛው ሰው ስለሚያውቀው ስለቲክቶክ ብታወራው. . እሱ ደሞ ምንድነው ነው የሚልህ ። አያውቀውም ።

ቲክቶክን የሚያስተዳድረው ByteDance ኩባንያ በቻይና ባለሀብት እዛው ቤጂንግ ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም ፡ ቲክቶክ ግን ቻይና ውስጥ በVPN ም ሆነ በሌላ ዘዴ እንኳን እንዳይሰራ አድርገውታል ።
......
በአንድ ወቅት በተለያየ ዘዴ ሀክ አድርገው በድብቅ ጥቂት ሰወች ሊጠቀሙ ሞክረው ነበር ፡ ሆኖም የካምፓኒው IT ባለሙያዎች ይህንን ክፍተት አስተካክለው ቲክቶክ ቻይና ውስጥ ፈፅሞ እንዳይሰራ አድርገዋል ።
ለምን ከተባሉ መልሳቸው ከህዝባችን ስነ ልቦና ጋር አይሄድም ፡ በሚል ሲሆን በቲክቶክ ምትክ በዚሁ ካምፓኒ Douyin የሚል ከቲክቶክ ጋር የሚመሳሰል ግን ጠበቅ ባለ ስርአትና ደንብ የሚተዳደረውን ( ጨዋ እና ስርአት ያለው ) አፕ ለህዝባቸው ለቀዋል ።
.............
ዛሬ በአሜሪካን ውስጥ የተዘጋው ቲክቶክ በአሜሪካን 150 ሚሊየን የሚደርሱ ተጠቃሚዎች ነበሩት ፡ ነገ ከነገ ወዲያ አዲሱ ተመራጭ ትራምፕ ሌላ ህግ ካላመጡ ልክ እንደ ቻይና ሁሉ ቲክቶክም በአሜሪካን አይሰራም ማለት ነው ።
......
በአለም ዙሪያ በ30 ሀገራት 150 ሺህ ሰራተኞች ያሉት ይህ ካምፓኒ ቲክቶክ ለህዝብ የሚጠቅም ቢሆን በሀገሩ ቻይና ላይ እንዳይሰራ አያደርገውም ነበር ። በነገራችን ላይ ByteDance ካምፓኒ በአመት እስከ 120 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለቻይና ያስገባል ።
ከትራምፕ የትላንት ንግግር በጥቂቱ:-

* "እኔ በስልጣን በምሆንበት ጊዜ ሁሉ ከአሁን ጀምሮ በአሜሪካ ላይ ሁለት አይነት ፆታ ብቻ ይኖራል ወንድ እና ሴት።"

ቀጥለውም ልጆቻችን ልክ እንደ ማሽን ጾታቸውን የሚመርጡበት ጊዜ አብቅቷል ብለዋል።

በተጨማሪ ፆታቸውን የቀየሩ ወንድም ሆነ ሴቶች ለፆታቸው እውቅና እንደማይሰጥና ላደረጉትም ተግባር በስራቸው ጨምሮ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ እገዳ እንደሚጣልባቸው ተነግሯል።

* "የአሜሪካ ወርቃማ ጊዜ አሁን ይጀምራል"

* " አሜሪካን አስቀድማለሁ"

* "ከአሁን በኋላ የአሜሪካ ማሽቆልቆል ያበቃል!!"

* "በፈጣሪ ፈቃድ የተረፍሁት አሜሪካን ዳግም ታላቅ ለማድረግ ነው"
(ላይፍ ሴፍ አዲስ)
ሰይፉ የተዋጣለት የ ፕሮግራም አቅራቢ ነው!…በ ኢትዮጵያ የቴሌቭዥን ታሪክ(በመዝናኛው) እንደሱ ረጅም አመት የቆየ ሰው ያለ አይመስለኝም!

ሲቀልድ ያምርበታል! ኮሜዲን በድርቅና ሳይሆንበተፈጥሮ የተቸረ ሰው ነው!

ሚቸለውን ነገር ብቻ አውቆና ጠንቅቆ ስለሚሰራ ይሄ ሁሉ አመት ሳይንገጫገጭ በመዝናኛው ኢንዱስትሪ ሳይንገጫገጭ ዘልቋል!

ታዋቂ ስለሆኑ ብቻ ፕሮግራም አቅራቢነት ውስጥም ትወና ውስጥም ያለ ተሰጥአቸው ዘው እያሉ ለሚያቦኩ ሰዎች ጥሩ ምሳሌ ነው!!

ሰው የሚችለውን ነገር ብቻ ሲሰራ ምን ያህል ውጤታማ እንደሚሆን ጥሩ ማሳያ ነው!…በእርርግጥ ከ ማዝናናቱም ባሻገር ዝናውን ለመልካምና ለበጎ ተግባር ያዋለ ሰው ነው ሰይፉ!…ይመቸው🫡:
:
:
ወደዚህኛው ጉዳይ ስንመጣ ደግሞ እኚህ ባልና ሚስት ዶክተሮች ከምንምና ከምንም በላይ ሰብአዊነትና Ethics ምን ያህል ዋጋ እንዳለው አሳይተውኛል!

ብዙ እውቀት ያላቸው ነገር ግን ትህትና እና ስነምግባር የሌለቸው ሰዎች እልፍ ናቸው!

ታመ ሀኪም ቤት ስትሄድ እንኳን በስርአቱ የማያዳምጥህ! የሚያመናጭቅህ ዶክተር አለ!

አንተ ተጨንቀህ ህመምህን እያወራኸው እሱ ተሽክካሪ ወንበሩ ላይ ተለጥጦ ስልክ የሚያወራ ሀኪም አለ!…ሰባተኛ ሰማይ መንበረ ፀባኦት ላይ ብትወጣ!

ሰባተኛ ምድር በርባኖስ ላይ ብትወርድ! የአለማትን እውቀት ሁሉ ጠቅልለህ ብትይዝ ስነምግባር ከሌለህ ከንቱ ነህ!

እና እነዚህ ሁለት ጥንድ ዶክተሮች ከህክምና ዕውቀታቸው በላይ ሰውንTreat የሚያደርጉበት መንገድ! ስነምግባራቸው! ለዛቸው እጅግ ደስ ይላል! ለአንድ ታማሚ ጥሩ ፊት ማሰየት ማለት የህመሙን የተወሰነ ክፍል ማቃለል ማለት ነው

እናንተ ደስ የምትሉ የልብ ሀኪሞች!! ልባችሁን!…መልካምነታችሁን ሳይቀይርባችሁ እስከመጨረሻው እንዲያዘልቃችሁ ልባዊ ምኞቴ ነው!…እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ!
ምንም ጋር አይያያዝም!

እንዲያው ዛሬ ሳነብ ገርሞኝ ነው።

አንበሳ ማለት ነው (የጫካው ንጉስ) ከአጠቃላይ ዕድሜው ከ65-75 በመቶ የሚሆነውን የሚያሳልፈው በእርሃብ ነው። በቃ ይርበዋል።

ስንት ስምና ዝና የሸፈነው ርሃብ አለ እናንተ?!
ለምንድነው ከስራ ይልቅ ቢዝነስ ያልመረጥኩት ?😕

በቻይና ውስጥ በጣም ሀብታም ሰው "ሙዝ እና ገንዘብ በዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጡ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ ሊገዛ እንደሚችል ስለማያውቁ ነው

እንዲያውም ሥራ እና ንግድ ለሰዎች ብታቀርቡ, መስራትን ይመርጣሉ ምክንያቱም አብዛኛው ሰው ቢዝነስ ከደመወዝ የበለጠ ገንዘብ እንደሚያስገኝ ስለማያውቅ ድሆች ከሚሆኑባቸው ምክንያቶች አንዱ የንግድ ሥራ እውቅና ባለማግኘታቸው ነው።

እድሎች በትምህርት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜ ያሳልፋሉ, እና በትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩት ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለደሞዝ መሥራት ነው።
መቄዶንያን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁ ቀን የተሰማኝን የጥፋተኝነት ስሜት ልገልጸው አልችልም:: ምጽዋትን በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ መስበክ ቀላል ነው:: እንደብንያምና አብረውት እንደሚያገለግሉ ወንድሞችና እኅቶች ራስን መመጽወት ግን ከባድ ነው::

ከአረጋውያኑና ከአእምሮ ሕሙማኑ ጋር አብረው እየኖሩና አብረው እያደሩ ፤ ለማየት የሚቀፍፍ ቁስል ያለባቸውን በፍቅር እያቀፉና እየመገቡ ፤ መጸዳጃ ቤት መሔድ የማይችሉና በዳይፐር የሚጠቀሙ በሺህ የሚቆጠሩ ሕሙማንን ከአልጋቸው ሳይነሡ እንዲጸዳዱ መርዳትና ማጠብ ፤ ከየትኛው ሆስፒታል በላይ በሺህ ከሚቆጠሩ ከአእምሮ ሕሙማን ጋር ያለ ምንም ልዩ ጥበቃ አብሮ መዋልና ማደር : ነዳያንን ለማገልገል ነዳይ ሆኖ መኖር የቻሉትን ብንያምና አብረውት ያሉ ሰዎች ማየት ብቻ ንስሓ እንድትገባና ምንኛ ጨካኝ ልብ ነው ያለኝ እንድትል የሚያደርግ ነው::

መቄዶንያ የአእምሮ ሕሙማንና አረጋውያንን መርዳት ብቻ ሳይሆን ከረዳቸውና ጤናቸው ከተመለሰ በኋላ እዚያው መቄዶንያ ተቀጥረው እንዲሠሩ በማድረግ ሕይወታቸውን ከተረጂነት ወደ ረጂነት የሚቀይር ተቅዋም በመላው ኢትዮጵያ 44 ቅርንጫፎች ያሉት

የፊታችን የካቲት 1 2017 ዓ.ም. በሰይፉ ኢቢኤስ ዩቲዩብ ቻናል በሚደረግ የገቢ ማሰባሰቢያ ይጠናቀቃል ተብሎ በሚጠበቀው ግዙፍ ሆስፒታልና የአረጋውያን ማእከል ሲጨመርበት ትልቁ የድሆች መጠጊያ መሆኑ የማይቀር ነው::

መነኮሳት ካህናትና ዲያቆናት እንዳሉ ሁሉ በርካታ ሼሆችና የእስልምና ምሁራንም ብዙ ናቸው:: ክርስቲያኖች በየዕለቱ ኪዳን የሚያደርሱበት ፣ ሙስሊሞች የሚሰግዱበት ፣ ፕሮቴስታንቶች የሚያመልኩበት የተለያየ ሥፍራ ተዘጋጅቶላቸው እምነታቸውን በየመምህሮቻቸው ይማራሉ::

መቄዶንያ በአጭሩ የተባረከ ትንሽ ቤተ ክርስቲያን ነው::

ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!
አንዳንድ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ የተሳሳቱ ነገሮች እንደሚያዩ እና ያም እንደሚያሳዝናቸው ይነግሩኛል። እኔም ለእነዚህ ሰዎች ይህን እላቸዋለሁ...

ዝምብን አግኝታችሁ “እዚህ አካባቢ አበባ አይተሻል?” ብትሏት፡- “ስለ አበቦቹ እንኳን የማውቀው ነገር የለም። ባይሆን እዚያ ጋር የምታየው ክምር ላይ የፈለግኸውን ቁሻሻ ልታገኝ ትችላለህ” ብላ ልትመልስልህ እና ንጹሕ ያልሆኑ ብዙ የቆሻሻ ዓይነቶችን ልትዘረዝርልህ ትችላለች።

ንብን አግኝተህ ደግሞ “እዚህ አካባቢ የተጣሉ ቆሻሾች አይተሽ ይሆን?” ብለህ ብትጠይቃት፣ “ቆሻሻ ነገሮች? ኸረ እኔ ምንም አላየሁም። ይህ ቦታ እኮ ልዩ ልዩ መዓዛ ባላቸው አበቦች የተሞላ ነው” ስትል ልትመልስልህ እና በአትክልቱ ስፍራ ያሉትን አበቦች አንድ በአንድ ልታስቆጥርህ ትችላለች።

አየህ! ዝምብ የቆሸሹ ነገሮች የት ሊገኙ እንደሚችሉ ብቻ ስታውቅ፣ ንብ ግን ውብ የሆኑ አበቦች መኖሪያ ወዴት እንደሆነ ታውቃለች።

አሁን ላይ እንደ ተረዳሁት ከሆነ አንዳንድ ሰዎች ንብን ሲመስሉ ሌሎች ደግሞ ዝንብን ይመስላሉ። ዝንብን የሚመስሉት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ክፉን ነገር ብቻ እያሻተቱ የሚፈልጉ እና ሐሳባቸውም በዚያ የሚዋጥባቸው ናቸው። እነዚህ ሰዎች የትም ቦታ ቢሆን ጥሩ ነገር አይታያቸውም።

ንቧን የሚመስሉት ግን በሚያዩዋቸው ነገሮች ሁሉ ውስጥ ጥሩን ነገር ያስተውላሉ።

ምንጭ፡ St. Paisios of Mt. Athos, "Good and Evil Thoughts”
"በአካውንትህ ውስጥ ካለ ብር 86,400 አንድ መናኛ 10 ብር ቢሰርቅህ፣ በብስጭት የቀረህን 86,390 ወርውረህ፣ 10 ብር ፍለጋ በመኳተን ጊዜህን ታባክናለህ ወይስ ኑሮህን ትቀጥላለህ?!"

ዐየህ፦ በቀን ውስጥ 86,400 ሴኮንዶች አሉ። መጥፎ አመለካከት ባለው አንድ ግለሰብ የ10 ሴኮንድ አስቀያሚ ንግግር ወይም በሆነብህ ቅፅበት ሳቢያ ቀሪ 86,390 ሴኮንዶችህን አታበላሽ። ለአንድ ገፅ ስህተት 1000 ገፅ መፅሐፍ በመቅደድ ከማባከን ተቆጠብ።

ተራ ነገር በማሳደድ የዕድሜ ካቦችህ እንዲናዱ በፍፁም አትፍቀድ! በምንም ሁኔታ ወደኋላ ዕያየህ ወደፊትህን አታዘግይ።"
2025/06/30 05:00:47
Back to Top
HTML Embed Code: