Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
2991 - Telegram Web
Telegram Web
ህይወትህን የሚቀይረው የሆነ ቀን ደስ ብሎህ ያስቀመጥከው ብር አይደለም! ወይ የሆነ ቀን በጥሩ ሙድ የሰራኸው ስፖርት ወይ ያነበብከው መፅሀፍ አይደለም!

ወዳጄ ህይወትህን የሚቀይረው በየቀኑ እየደጋገምክ የምታደርገው ልማድ ነው!

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
እንደው በክፉ አትዩብኝና 😜

ከሙዚቃ ክሊፕ መጨረሻ "ምስጋና ለልዑል አምላክ እግዚአብሄር .... ማዳናለም ጌታ ክርስቶስ ..... " ምን ማለት ነው???

እኔ ሀይማኖተኛ ሆኜ ሳይሆን ግን 'ዘፋኝ መንግስተ ሰማያትን አይወርስም' ያለውን እግዜር ራሱን የዘፈኑ ተባባሪ /ፕሮዲውሰር/ ማድረግ ትንሽ አይዋቀጥም??....

ሰርቆ 'እንዳልያዝ ስለረዳኸኝ አመሰግንሃለሁ' እንደማለት አይደል?? ያው ሁለቱም ሀፅያት ነው ብዬ ነው.....

እንደው ነገሩን ነው... የሆነ ሙዚቃ መጨረሻው ላይ አንብቤው ተዋቅጦብኝ ነው...

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
አንድ ድረገፅ ስለማይክ ታይሰን እንዲህ አለ።

ማይክ ታይሰን በ58 አመቱ ከ31 ዓመት በታች በሆነ ሰው ጋር ለ16 ደቂቃ ቦክስ ገጠመ። ገጠመና ተሸንፎ 20 ሚሊዮን ዶላር ወሰደ። በደቂቃ 1 ነጥብ 25 ሚሊዮን ዶላር መኾኑ ነው። እና አኹንም ታይሰንን እብድ ነው ትሉታላችሁ? 🤣

እሱ አላበደም - እንዲያውም ገንዘብ እንዴት ማካበት እንዳለበት ጠንቅቆ የሚያውቅ ብልህ ሰው ነው። 🤓

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
The 1960s will remember Pele.
The 1970s will remember Cruyff.
The 1980s will remember Maradona.
The 1990s will remember Ronaldo Nazario.
The 2000s will remember Zidane/Dinho.
The 2010s will remember Cristiano.

And football history will always remember Lionel Messi 🇦🇷🐐

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
ፒያሳ የእሳት አደጋ ተከስቷል

በተለምዶ ፒያሳ ደጃች ውቤ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ነው የእሳት አደጋው የተከሰተው።

የእሳት አደጋው የተከሰተበት ስፍራ ላይ ቻይኖች ሲሚንቶ እና ኮንክሪት የሚያዘጋጁበት ስፍራ ነው

በስፍራው ሲሚንቶና ኮንክሪት ለማዘጋጀት የሚጠቅሙ ኬሜካሎች እንዳሉ ነው የተነገረው።

እንደዚሁም ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅም በዚሁ ስፍራ እንዳለ ነው የተነገረው።

ለተለያዩ አገልግሎት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎችም አደጋው በደረሰበት ቦታ መኖሩን ተመልክተናል።

እሳቱን ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው ደርሰው እርብርብ እያደረጉ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ፖሊስም ባካባቢው ደርሶ ጥበቃ እያደረገ ነው የሚገኘው።

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
አይሪሽ ቦክሰኛ "#Conor_McGregor" ስለ ሚስቱ ስናገር

"ለ 8 ዓመታት አብረን ቆይተናል እና ከደብሊን 30 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው አየርላንድ ውስጥ ያለ ስፍራ ተከራይተን አፓርታማ ውስጥ እንኖር ነበር. እኔ አልሰራም ምክንያቱም ሁሉንም ጊዜዬን በስፖርት አሳልፌያለሁ. ሁልጊዜም ጀግና መሆን ህልሜ ነበር...እናም የገንዘብ እጥረት ቢኖርም, አመጋገቤን ለመንከባከብ ብብዙ ጥረት ታደርጋለች ቆንጆ የአትሌት ምግብም በሷ ልፋት አገኛለሁ

ከጠንካራ ስልጠና ወደ ቤት ያለ ጉልበት እና በብዙ ድካም ስመለስ ሁልጊዜ እንዲህ ትለኝ ነበር፡- "ኮኖር ማክግሪጎር፣ ይህን ማድረግ እንደምትችል አውቃለሁ እናም ታደርገዋለህ።"

አሁን ከ 50 እስከ 70,000 ተመልካቾች ፊት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በመታገል አገኛለሁ። አሁን የትኛውንም መኪና፣ የትኛውንም ልብስ፣ የትኛውንም ቤት መግዛት እችላለሁ፣ እሷ ግን ምንም አልጠየቀችኝም፣ ግን በዚህ አለም ላይ ምርጡን ይገባታል።

እሷ ሁል ጊዜ ከጎኔ ነች እና ማንኛውንም ነገር ማድረግ እንደምችል ትነግረኛለች ! ወደዚህ ቦታ ደርሻለሁ ለእርሷ ምስጋና አለኝ....ብቻዬን አልተወችኝም። "

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
ዶናልድ ትረምፕ በመጪው ጥር ስልጣን ላይ ሲወጡ ፆታቸውን የቀየሩ 15 ሺ የአሜሪካ ወታደር አባላትን ከስራ እንደሚያባሩ ይጠበቃል።

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
- በኢንጂነሪንግ ተመርቀህ ስራ ስለማትንቅ የሳፋሪኮም ሲም ሻጭነት ትገባለህ

- በህይወቱ ሀ ሁ ሂ ብሎ ከማያውቀው "ይሄን ነገር በመቶ" እያለ ጦስኝ ከሚሸጠው ልጅ ቀጠና ትመደባለህ

- ደምቦች መጥተው "ይሄን ነገር በመቶ" ከሚሉት ጋር ያሳድዱሃል

- ሮጠህ ትንፋሽ ለመውሰድ ስትቆም ደምቡ ከኋላ ዠልጦህ ትዞራለህ

- ዞረህ ስታየው አንድ ዲፓርትመንት አብረህ የተማርከው ልጅ ነው

- ልትመረቅ ስትል "ስራ ሳንንቅ ጀምረን የሚገባን ቦታ እንደርሳለን" ተባብለህ ቃል ከተገባባችሁት እከኮች አንዱ ነው

- ተቃቅፈህ ትላቀሳለህ

- ከኋላ ስለመታህ አዝኖ ሲም ልግዛህ ሲልህ በሼም በነፃ ትሰጠዋለህ

ቻው ተባብለህ ትለያያልህ...

- "ዲቻ ይዤ ቢሆን እራት እዘጋ ነበር ቲሽ" እያለ ሲሙን እየሰበረ ይብሰከሰካል

-አንተም በነፃ ስለሰጠኸው ሲም ቁጭ ብለህ ብቻህን ታለቅሳለህ
.
.
.
Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
Facebook be like "people you may know" and list girls I have no chance of knowing...😭😂😝

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
የምራቸውን ነው 'ሐዋዝ ወደ ቤተክርስቲያን የተመለሰው ነውር ሠርቶ ነው' የሚሉት?

መቼም ነውር ሠርቶ ለመሸሸግና ጻድቅ ጻድቅ ለመጫወት የት ይቀላል አልልም። ግን "ታድሰናል። በጸጋው ድነናል። ንስሀና ሥራ አያስፈልገንም።" እያሉ፣ እነሱ ጋ የነበረን ሰው ነውር መቁጠር እንዴት ቻሉበት? "በጌታ" ነኝ ምንም ብሠራ ደሙ አድኖኛል፣ ካሉ ወዲህ ነውር ጌጥ መሆኑም አይደል? ያም ይቅር ቤተክርስቲያን የነፍስ ሆስፒታል ናት። የጻድቃን ጉባዔ ሳይሆን፣ የመጽደቅ ተስፋ ያላቸው፣ እንደቸርነትህ ማረን የሚሉ ምዕመናን ያሉበት ስብስብ ነው።

የእውነት ካሳሰባችሁና እግዚአብሔርን ከፈራችሁ፣ ቢያንስ ስለ ወንድማችሁ ደስታ እና የአእምሮ ሰላም ደስ ይበላችሁ። ግድ ተያይዘን እንጥፋ አለ እንዴ? ደግሞ ምናለ ወደራስ ማየት ቢቻል? እሱ አንድ ጊዜም ተገፍቼ ወጣሁ አለለም። እዚያ ስላሉትም ሲያወራ የወዳጅነት ፍቅር እና ናፍቆት እንዳለው፣ ግን ነፍሱን ማዳን ስላለበት የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዳስበለጠ ነው። በዚህ ልክ ለምን ይረብሻቸዋል?

"በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? ወይም ወንድምህን፥ ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ። አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።" ~ ማቴዎስ ፯: ፬-፭

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
ይህ ሰው ዋሬን ቡፌት ይባላል የካፒታሊስቶች ቁንጮ የዓለማችን ቁጥር 1 በቢሊየን ዶላር የሚያንቀሳቅስ ባለሃብት ነው።

ይህ ሰው አሁን ላይ እድሜው እየገፋ ሲሄድ ሞት እንደቀረበው አውቀ። እናም "ራቁቴን ተወለድኩ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ወሰደ። (ኢዮብ 1:21) የሚለው የመጽሐፍ ቃል ትዝ አለው በገዛ ፈቃዱ ወሰነ የሃብቱን 99.5 ከመቶ ለበጎ አድራጎት ለማዋል ቃል ገባ ይህም 150 ቢሊየን ዶላር ገደማ ማለት ነው።

ሐብቴ ለልጆቼ ለዘመዶቼ ሳይሆን ለወደቁት እና ለተራቡት ይሁንልኝ አለ መኖር ማለት ገንዘብ መሰብሰብ በድሎት መኖር እና መሞት ብቻ አለመሆኑን ገብቶታል መኖር ትርጉሙ መስጠት መሆኑ ገብቶታል

ዋሬን ቡፌት ይህን ሁሉ የወሰነው በጣም አንባቢ እና የመጽሐፍ ወዳጅ ስለሆነ ነበር በቀን ውስጥም ብዙ ሰዓቱን በንባብ የሚያሳልፍ ባለጠጋ ነበር "የንባብ ኃይልን "እዚህ ጋር ታዩታላችሁ በሉ በቀን 1 ሰዓት ለንባባችሁ ስጡ ለመንፈሳዊ ሕይወታችሁ ሲጨንቃችሁ ሲከፋችሁ የሕይወትን ቃል ታገኛላችሁ እና አንብቡ ኑሮንስ ለመሻሻል ለቢዝነሳችሁም ለስራችሁ ለእድገታችሁ ቢሆን አንብቡ

እናንብ በጎውን እናስብ መልካም ቀን፡፡

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
#ማነው_ጥፋተኛው?
(ከናይጀሪያን ፔጅ የተወሰደ)

ሰውዬው አገር ሰላም ብሎ ወደ ቤቱ ሲመጣ ሚስቱ ከወንድ ጋር ስትማግጥ እጅ ከፍንጅ አገኛት። ባልሆዬ ሚስቱን ያማገጠበት ሰው ጋር ድብድብ እንደመፍጠር፣ ነገር አለሙን ችላ ብሎ ወደ ሳሎን ተመለሰና መፅሃፍ ቅዱሳዊ ቪዲዮ ማየት ጀመረ።

ወይዘሮ ሚስትና ውሽሜ በከፍተኛ ፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ነው።

ውሽሜ እንደምንም ልብሱን ለባበሰ እና ወደ ሳሎን መጥቶ እየተንተባተበ ወንጀሉን መናዘዝና ይቅርታ መጠየቅ ጀመረ። አባዋርዮው ግን ፍፁም በተረጋጋ ስሜት "ችግር የለውም በህይወት ውስጥ ሊከሰት የሚችል ፈተና ነው፤ መሄድ ትችላለህ" ሲል አሰናበተው። ሰውዬውም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ ወጥቶ ሄደ።

ሚስትዮዋ የመኝታ ሰዓት እስኪደርስ ከመኝታ ቤት አልወጣችም ነበር።

ባልዮው ቲቪውን አጠፋፋና ወደ መኝታ ቤቱ ገብቶ ያ መጥፎ ድርጊት የተፈፀመበት አልጋ ላይ ብርድልብሱን ተጠቅልሎ ተኛ።

ሚስትዮዋ ወለሉ ላይ ተቀምጣ እየተንሰቀሰቀች ታለቅስ ነበር። ባልዮው ምንም ነገር አልተናገራትም፣ አልጠየቃትምም።

ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ ሚስቱን ሞታ አገኛት። ራሷን በራሷ አጥፍታለች። ፖሊስ ግን ባልዮውን በወንጀል ድርጊት ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር አዋለውና ጭራሽ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል 20 ዓመት እስራት ተፈረደበት።

#ጥያቄ: በዚህ ሂደት ውስጥ ኢፍትሃዊነት የተንፀባረቀው በማን በኩል ነው

1.ባል
2.ሚስት
3.ህጉ እራሱ?

(ሃሳብ አስተያየት ስጡበት፣ እንወያይበት)
_//___

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ ቪዲዮ የተቀረፀው ዲሴምበር 31 1999 በፈረንጆቹ አቆጣጠር ነው

የ10 አመቱ ወይም የክፍለ ዘመኑ የ 100 አመታት አይደለም የሚሊኒየሙ የ1 ሺ አመት የመጨረሻዋ ቀን በመሆኗ እቺን ታሪካዊ ቀን እለቱን በቪዲዮ ትልልቅ ሚዲያዎች እንደዚ ቀርፀው ለታሪክ አስቀምጠውት ነበር

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
አንድ ባለስልጣን አማኑኤል ሆስፒታልን እየጎበኙ አንድ በሽተኛ ያጋጥማቸውና ጠጋ ብለው

ወደዚህ እንዴት ልትመጣ ቻልክ ማለቴ የህመምህ መንስኤ ምንድነው?' ብለው ይጠይቁታል ።
በሽተኛውም እንዲህ ሲል መለሰ...

"ጌታዬ ይሄ ሁሉ መዓት የወረደብኝ አንዲት መናጢ ሴት ሳገባነው።

ይሀውሎት አንዲት አግብታ የፈታችና ቆንጆ ሴት ልጅ ያለቻት ወይዘሮ አገባለው።

እናም ይህቺ ቆንጆ ልጅ የእንጀራ ልጄ ሆነች ማለት ነው። ከዛ አባቴ አንድ ቀን ሊጎበኘን ይመጣል። በዚህች ቆንጆ ልጅ ፍቅር ይከንፍና በግድ ያገባታል።

ስለዚህ የእንጀራ ልጄ የእንጀራ እናቴ ሆነች ማለት ነው። ባለቤቴም ለኔ አንድ ወንድ ልጅ ትወልድልኛለች።

በመሆኑም የኔ ልጅ ለእንጀራ እናቴ ወንድም ስለሆነ ለአባቴ ደግሞ ዋርሳ ሆነ ማለት ነው። ምክንያቱም አባቴ የእንጀራ ልጄን አግብቷልና።

እና እንደነገርኩህ የእንጀራ ልጄ አባቴን ስታገባ እሷ በመጀመሪያ የእንጀራ እናቴ ሆነች። በኋላ ላይ ደግሞ ወንዱ ልጄ ለእንጀራ እናቴ ወንድም ስለሆነ እርሱ ደግሞ በተዘዋዋሪ አጎቴ ሆኖ እርፍ!

ሚስቴ ደግሞ የእንጀራ እናቴ እናት ስለሆነች የእንጀራ አያቴ ሆና እርፍ!

የእንጀራ እናቴ የእንጀራ ልጄ መሆኗን አትርሳ። እንዲሁም የራሴ የገዛ ሚስቴም የእንጀራ ልጅ ልጅ መሆኔንም አትዘንጋ። ይሄ ማለት ደግሞ የእንጀራ አያቴን ስላገባሁ ለሚስቴ የእንጀራ የልጅ ልጇ እና ባሏ ብቻ ሳልሆን የራሴም አያት መሆኔ ነው።

ወደዚህ ወደ አማኑኤል ሆስፒታል አብጄ የመጣሁበት ምክንያቴም ይሄው ነው!" አላቸው።

ከዚያማ ባለስልጣኑም ይህን ጉዳይ ሲያምሰለስሉ ከቆዩ በኃላ እሳቸውም የአማኑኤል ሆስፒታል ደንበኛ ሆነው አረፉት!

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
በዚህ ምድር ብለን በምንጠራው ፕላኔት ውስጥ ካሉ ፍጥረቶች ሁሉ አንተ የላቅክና እጅግ የመጨረሻው ጠቃሚ ፍጥረት ነህ፡፡

ነገሩ ለጊዜው ግልፅ ሆኖ ባይታይህም የተፈጠርክበት አንዳች ምክንያት አለ፡፡ባይሆንማ ኖሮ እንደብዙ ያልተለመዱ ፅንሶች ጭንጋፍ ሆነህ በቀረህ ነበር፡፡

የሰው ልጅ የከበረ ሀብቱ ትጋቱ ነውና የተፈጠርክበትን ምክንያት ፈልጎ በማግኘት ላይ ትጋ!

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
በአካል ባውቅህ ብዬ እመኛለሁ

ማንም ባንተ ልክ የጥንካሬ'ን ተምሳሌት መሆንን አላሳየኝም ፥ በፈጣሪህ የምታምንበት መንገድ ፥ ይሄን የመሰለ አቋም ይዘህ ወጣትነት ሳያሸንፍህ አንድምም ቀን ያለመሰላቸት ለአመታት ለእናትህ የለገስካቸው እንክብካቤ አንተ እንጂ ሌላ ማንም አይችለውም ይሄ ከፈጣሪ መሰጠትን ይፈልጋል!! ያንተ ፅናት ማንም ወጣት አልተላበሰውም ማንም!!

እጅግ በጣም ነው ማከብረው ምደነቅበት ሚያሳዝነኝ በሺ ለሚቆጠር ሰዎች አርአያ የሚሆን ወጣት ነው!!

አንተ'ን የመሰለ ሰው ለምን ሰይፉ'ና ሌሎች ሚዲያዎች እንደማያቀርቡት አይገባኝም ፥ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ተከታዮች ኖሮህ ለምን ማስታወቂያ ጭምር እንደማያሰሩህ አላውቅም 💔

የልፋትክን አይቶ አንድ ቀን የእናትህን ልሳኗን ከፍቶት ስሜቷን ብታጋራክ ሁሉም እመኛለሁ ፤ ላንተ ምን አይነት ምርቃት ይሆንህ ይሆን ?

የክፍለ ዘመኑ ምርጡ ወጣት ነህ

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
በአንድ ወቅት በአንድ ክፍል ውስጥ በሚማሩ ተማሪዎች መሃል አንዱን ጓደኛቸውን prank ሊያደርጉት ፈለጉና ከጀርባው ላይ 'I'm stupid' እኔ ደደብ ነኝ የሚል ወረቀት ለጠፉበት።

ከዚያም ጓደኞቹ በሙሉ በእሱ ላይ መሳቅ ይጀምራሉ ። ከቆይታ በኋላ ግን የሂሳብ መምህራቸው ገባ። መምህሩም እንደገባ አንድ ከባድ ጥያቄ ጥቁር ሰሌዳው ላይ በመጻፍ እንዲመልሱ ጠየቃቸው። ከዚያ ጀርባው ላይ ከተለጠፈበት በስተቀር ሌሎቹ ከብዷቸው ዝም አሉ።

በመጨረሻም ያው ልጂ ወጣና ጥያቄውን በትክክል ሰርቶ አሳያቸው። መምህሩም ከጀረባህ የተለጠፈውን ያወቅክ አትመስለኝም በማለት በእጁ እያነሳለት ወደ ክፍል ተማሪወቹ እየተመለከተ እናንተን ከመቅጣቴ በፊት ሁለት ነገር እነግርሃለሁ፥

በመጀመሪያ በሂይዎትህ ውስጥ ሰዎች አናንተን ከጉዞህ ለማስተጓጎል ብዙ ስያሜወችና ያልተገቡ ነገሮችን ይጭኑብሃል።

የክፍል ጓደኞችህ ያደረጉብህን ነገር ብታውቅ ኑሮ ከመቀመጫህ አትነሳም ነበር። በሂይዎትህ ውስጥም ማድረግ ያለብህ ነገር ሰዎች የሚሰጡህን መለያዎች ችላ ማለትና ለመማር፣ ለማደግና ለመሻሻል ጥረት ማድረግ ነው።

ሁለተኛ ስለስቲከሩ ከጀርባህ ስለተለጠፈው ነገር የሚነግርህ ታማኝ ጓደኛ እንደሌለህ ያሳያል።ነገርግን ብዙ ጓደኛ መኖሩ አይደለም ቁም ነገሩ ዋናው ለጓደኞችህ የምታጋራው ታማኝነት ነው።

ከጀርባህ የሚከላከሉልህ፣ የሚጠብቁህና ሰለ አንተ የሚጨነቁልህ ጎደኞች ከሌሉህ አንተ ብቻህን ትሻላለህ።

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
2024/12/29 19:45:39
Back to Top
HTML Embed Code: