Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
🎙️🗣️ካርሎስ ቴቬዝ

"አንድ ቀን ታላቋ ልጄ መኪና እንድገዛላት ጠየቀችኝ ራሷን እና ታናሽ እህቷን ወደ ትምህርት ቤት እንድትነዳ፣ መኪና ከፈለገች ገንዘብ አጠራቅማ ራሷን መግዛት አለባት አልኳት።

እሷም 'አንተ ካርሎስ ቴቬዝ ነህ እንዴት ለሴት ልጅህ መኪና አትገዛም?'

እኔም፣ 'በማክዶናልድ አስተናጋጅነት ብትሰራ ግድ የለኝም። ልክ እኔ እንዳደረግኩት ማለፍ ያለብህ ልምድ ነው።'

የመጀመሪያ መኪናዬ? ያገኘሁት በ21 ዓመቴ ነው፣ ግን ስላገኘሁት ብቻ ነው። ከዚያ በፊት ለአባቴ ቤት ገዛሁ። ጠንክሬ ሰርቻለሁ። ከባድ ነው, ግን መማር አለባት. " ለእሱ መስራት አለባት!

ቴቬዝ ታላቅ አባት ነው። ልጅን እንደዚህ ነው የምታሳድጉት ልጆች የስራ ዋጋን ማስተማር አለባቸው

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
"የኔ ጋርድ እኔ ቤት የሚበላበት ምክንያት የለም ። ደሞዙ ይበቃዋል"

በእግር ኳስ ውጤታማ ሆኜ ገንዘብ ያገኘሁት ለሌላው ልሰጥ አደለም ። ኤቶ የተቸገሩ ሰወችን መርዳት ፈለገ ማለት እኔም መርዳት እፈልጋለሁ ማለት አደለም። ኤቶ ኤቶ ነው ፡ እኔ ደግሞ እኔ ነኝ። አሁን የደረስኩበት ቦታ ለመድረስ የደከምኩት ገንዘቤን ለሌላ ሰው ለመስጠት አደለም፡ ይህ የኔ ገንዘብ ነው። የኔ ብቻ።

ጄርሚ ሳንቲም አይሰጥም እያሉ ቤተሰቦቼ ሁሉ ሲያማርሩ ሰማለሁ አዎ ፡ አንድም ቀን ለቤተሰቤም ሆነ ፡ ለማንም በልግስና ገንዘብ ሰጥቼ አላውቅም ፡ ወደፊትም መስጠት አልፈልግም።

ለመሆኑ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኜ ገንዘብ ባላገኝ ማን ይሰጠኝ ነበር። ርህራሄ ፡ ሰብአዊነት እና ልግስና የሚባሉት ቃላት በኔ ዘንድ ቦታ የላቸውም ። ሌላ ቀርቶ የኔ ሴኪውሪቲ ጋርድ አንድም ቀን እኔ ቤት አንድ ሳህን ምግብ ሰጥቼው አላውቅም። በደሞዙ መብላት ይችላል።

ይህን ያለው በአንድ ወቅት የካሜሩን ብሄራዊ ቡድን አባልና፡ በቼልሲ ሪያል ማድሪድ ኒውካስል እና በሌሎች በርካታ  ክለቦች ሚሊዮን ዶላሮች እየተከፈለው ይጫወት የነበረው ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ጄርሚ ኒጅታፕ ነው።

የጄርሚን ታሪክ እዚህ ላይ ፖዝ አርገን. .ስለ ኤቶ ደግሞ እናውራ

በዛው ወቅት ከሱ ጋር የቡድን አጋር የነበረውና ፡ ለማድሪድ ፡ ባርሳ ፡ ሚላን ቼልሲ ኤቨርተንና በሌሎች ክለቦች ሲጫወት አለም በእግር ኳስ ኮከብነቱ የሚያውቀው ሳሙኤል ኤቶ  ደግሞ ፡ ከላይ ካነሳነው ተጫዋች በተቃራኒ. .. ሲፈጥረው አዛኝና ደግ ልብ ያለው ፡ የተቸገሩትን የሚያግዝ ፡ ወጣቶችን ለውጤት ለማብቃት የሚጥር ፡ በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ስፖንሰር የሚያደርግ ፡ በበጎ አድራጎት ስራው የሚታወቅ ነው።

አሁን ላይ ሁለቱም ከእግር ኳስ አለም ከተሰናበቱ አመታት የተቆጠሩ ሲሆን ያ ኤቶ የተቸገሩ ሰወችን ስለረዳ እኔ መርዳት አለብኝ ማለት አደለም። ኤቶ ኤቶ ነው እኔ ደግሞ እኔ ነኝ ያለው ሰው  በተጫዋችነት ዘመኑ ያፈራው ሀብት እየተመናመነ ሄዶ ፡ በአሁኑ ወቅት ፡  ከአምስት ሚሊየን የማይበልጥ ገንዘብ በባንክ አካውንቱ የነበረው ሲሆን በቅርቡ የ12 አመት ትዳሩን በመፍታቱና ከሚስቱ ጋር በመካፈሉ፡ የሀብቱ መጠን ከዛም በታች ወርዷል። ስራን በተመለከተ ደግሞ. . በቅርቡ  የተጫዋቾች ወኪል ለመሆን የሚያግዘውን  ፊፋ የሚሰጠውን ኮርስ ተምሮ ዲፕሎም አግኝቶ በዚህ መስክ ለመሰማራት እየሞከረ ነው።

ያ ሺህዎችን የሚያስተምረው ፡ የተቸገሩ ሰወችን ለአመታት በገንዘቡ ሲያግዝ የኖረው፡ ሳሙኤል ኤቶ የበጎ አድራጎት ድርጅት የሚባል መስርቶ በገንዘቡ የሚረዳው ሳሙኤል ኤቶ ደግሞ ፡ ትላልቅ ኢንቨስትመንቶችን የሚያንቀሳቅስ የግል ጄት ባለቤትና፡ በአሁኑ ወቅት የካሜሩን እግር ኳስ ፕሬዝደንትና፡ እንደ ፎርብስ መረጃም፡ መቶ ሚሊየን የሚጠጋ ገንዘብ ያለው፡ በቅንጡ ቪላ ውስጥ የሚኖር፡ በሁሉም ሰው ዘንድ የሚወደድ እና የሚከበር ሰው ነው።

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
#self_confidence

ናይጄሪያዊው ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች ቪክቶር ቦኒፌስ ለባየር ሊቨርኩሰን የፈረመ ሰሞን አስቤዛ ለመግዛት ጀርመን ውስጥ የሚገኝ አንድ የቱርክ ሱፐርማርኬት ይገባል።

እና የሚፈልገውን የምግብ አይነት እያነሳ በያዘው ዘምቢል ውስጥ እያስቀመጠ እያለ የሱፐርማርኬቱ ተቆጣጣሪ ከኋላው ሆኖ ሲከተለው ተመለከተ።

ቪክቶር የሱፐር ማርኬት ተቆጣጣሪ ተመድቦ የሚከተለው እሱን ብቻ እንደሆነ ተረድቷል። በሱፐር ማርኬቱ ያለው አንድ ጥቁር እሱ ነው፡ ለዛም ነው የሚከተለው።

ይህን እንደተረዳ ወደ ተቆጣጣሪው ዞሮ "እንካ ያዝ" ብሎ ዘምቢሉን ዘረጋለት : ተቆጣጣሪው አልገባውም

ቪክቶር ደገመለት "ጠባቂዬ እንደመሆንህ ዘምቢሉን የመያዝ ግዴታ አለብህ፡ የጋርድ ስራህን አትርሳ እንጂ" አለው።

በዚህ ጊዜ የሱፐር ማርኬቱ ተቆጣጣሪ በንዴት "ማነው ያንተ ጋርድ ያደረገኝ ?"

ቪክቶር እየሳቀ "ታዲያ የኔ ጋርድ ካልሆንክ ምን በሄድኩበት ትከተለኛለህ" ሲለው፡ ተቆጣጣሪው በመጣበት እግሩ ሀፍረቱን ተከናቦ ጥሎት ሄደ

ቪክቶር ቦኒፌስ በከለሩ ምክንያት ሊያሸማቅቀው የመጣውን ሰው በራስ መተማመን ስሜት በዚህ መልኩ የመልስ ምት ሰጥቶ የሚፈልገውን ገዝቶ ወጣ።

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
እስከ አሁን...

Gofundme: 48% of the 40k Dollars

CBE: 2,380,052.66 ብር

Telebirr: 257,537.22 ብር

Zemen Bank: 20,534 ብር

ላይ ደርሰናል ።

Y'all came through ።
ፈጣሪ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጣችሁ ።

Gofundme : https://gofund.me/0c436fef

ስም: Daniel Basazinew Haile

CBE: 1000259462774

Telebirr: 0941219026 (Zinash)

Zemen Bank: 1091410061152012

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
አለሁ ማለት ከንቱ!

ታላላቅ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ በየሐይማኖቱ ያሉ ሰባኪወች ዘማሪወች፣ሀብታሞች ፣ በጎ አድራጊወች ወዘተ...በማህበራዊ ሚዲያ ያላቸውን የተከታይ ቁጥር የተወዳጅነታቸው መለኪያ ሲያደርጉት እና ሲታበዮ ይታያሉ።

ይችን ነገር ስሙ... ራሻያዊዋ ሱፐር ሞዴል አይሪና ሸይክ የታዋቂው ኳስ ተጨዋች ክርስቲያን ሮናልዶ ፍቅረኛ ነበረች፤ ብዙ ሚሊየኖች ኢንስታግራም ላይ ይከተሏታል ያንቆለጳጵሷታል። ያው በቁንጅናዋ እንደሚከተሏት ነበር ሚዲያው ሁሉ የሚያራግበው።

እና አንድ ቀን ክርስቲያን ሮናልዶ ጋር ፍቅራቸው አልቆለት ተለያዮ... አጅሪት በብስጭት "ከአሁን ጀምሮ ከራሴ ማንነት ይልቅ የክርስቲያኖ ፍቅረኛ ስለሆንኩ ብቻ ፎሎው ያደረጋችሁኝ አንፎሎው አድርጉኝ" ብላ ለጠፈች። በ24 ሰዓት ውስጥ 11 ሚሊየን ህዝብ አንፎሎው አድርጓት ጭር። በዘራችሁ አይድረስ! በሶሻል ሚዲያ ታሪክ እንዲህ አይነት የአንፎሎው ጎርፍ ታይቶ አይታወቅም! በእርግጥ አሁን የራሷን ተከታይ አፍርታለች።

ምን ለማለት ነው ... የአገራችን ታዋቂወች ... የሚከተላችሁ ህዝብ ከስራችሁ የተኮለኮለው ለምትመሯት አገሩ፣ ለምትሰብኩለት ዕምነቱ፣ ለምትነግሩት መረጃ ፣ ለምትረዷቸው ሚስኪኖች ሲል እንጅ እናንተን በግላችሁ ወዶ ላይሆን ይችላል የት አውቋችሁ? አንድ ቀን ከስልጣን ወይም ከተደገፋችሁት መድረክ ስትወርዱ ጥላችሁ ራሱ የማይከተላችሁ ጥላ ቢስ ልትሆኑ ትችላላችሁ። አለሁ ማለት ከንቱ

(አሌክስ አብርሃም)

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
መዋቢያ እቃዎችን እና ልብሶችን እንደምንገዛ ሁሉ የአእምሮችንን ውበት መጠበቂያ መጻሕፍትን እንሸምት እናንብ በጎ እናስብ፡፡

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
እህተ ማርያም እንዲህ አደረገች: እንዲህ አከበረች: እንዲህ አለች
.
ፍቅርሲዝም እንዲህ አለ: ይህንን አደረገ: ከእገሌ ጋር ተሟገተ
.
እገሌ የተባለ "አገልጋይ ነኝ" ባይ መፅሃፍ ቅዱስ በላ: ማርያምን በአካል አገኛት: እየሱስን በስልክ አናገረው
.
እገሌ የተባለ "attention seeking Bastard” ከሶስት ሚስቶቹ ጋር ይኖራል: ሲተኛ ተገልብጦ ነው: ሲራመድ እየበረረ ነው

ይኸውልህ ይሄ ቀልድ አይደለም - It is a well articulated project ሃይማኖትን የማኮሰስ: ባህልን የመገርሰስ: care-less ትውልድ የመጠንሰስ ፕሮጀክት ነው

"ቀልድ ነው: ፈታ ይበሉ ተዋቸው: አታካብድ ዝም ብለህ: እነሱ ባይኖሩ በምን ዘና እንል ነበር" እያልክ ራስህ ላይ አውቆ-እብዶችን አታንግስ

ሀገርህን የምትወድ ከሆነ: ለልጆችህ የምትተዋት ምድር የሚያሳስብህ ከሆነ - ለእነዚህ ሰዎች እና እነርሱን ለሚያስተዋውቁ ገጾች - እምቢ በል: አውግዝ: አታበረታታ

ንቃ
.
ብቃ
.
በራስህ ቁም!!

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1911፣ ታዋቂው የሞናሊዛ ሰዕል ፣ከተሰቀለበት ሙዚየም ተሰርቆ ነበር ! እና በዛ ዓመት ስዕሉ ተሰቅሎበት የነበረውን ባዶ ግድግዳ የጎበኘው ሰው ቁጥር ሳትሰረቅ በፊት የሞናሊዛን ስዕል ከጎበኘው ሰው ቁጥር በጣም ይበልጥ ነበር። እዚህ ጋ ነበረች እየተባባለ። ምንም ቅኔ ዘወርዋራ ነገር የለውም በቃ ይበልጥ ነበር ነው

ግን የምንጎበኘው ባዶ ነገር አልበዛባችሁም? እዚህ ጋ ነበርንኮ ምናምን እያልን ?

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
ምግብ አይበላም ፡ በቂ እንቅልፍ ካገኘ ቆይቷል ፡ ከጭንቀት ጋር በተያያዘ የምግብ መፈጨት ችግር ስላጋጠመው ለሳምንታት የሚወስደው ሾርባ ብቻ ነው።

ይህ ሰው በማንቸስተር ሲቲ ታሪክ ትልቁን ስኬት ያስመዘገበ 6 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ የሻምፒየንስ ሊግ ፡ ኮሚኒቲ ሼልድ ፡ ሱፐርካፕ በአጠቃላይ 18 ዋንጫ ያስገኘ ምርጡና ውጤታማ አሰልጣኝ ነበር።

ሆኖም ይህ ድል ብቻ የለመደ አሰልጣኝ ነገሮች እንዳሰበው ሳይሆን ቀርቶ በዚህ የውድድር አመት ውጤት ከሱ ራቀ።

ከዛስ ፤ የሌላውን ተውት ፡ ትችትና ጥላቻው በራሱ ክለብ ደጋፊዎች ባሰ። ለአመታት ባለድል እንዳላደረገ ያ ሁሉ ሙገሳ ከመቅፅፈት ወደ ጥላቻና ስድብ ተሸጋገረ

እየደገፉ ያሉት ማሸነፍና መሸነፍ ግድ የሆነበት የእግር ኳስ ጨዋታን መሆኑን የረሱ እስኪመስል ለአመታት ባለድል ሲያደርጋቸውን የቆየውን አሰልጣኝ በስድብ አሸማቀቁት።

ይህ የደጋፊዎች ጭካኔና ስድብ ከታዳጊ ልጁ ጋር እየሄደ ሁሉ የሚያጋጥመው ነገር ሆነ። በእርግጥ ነው ማንም መሸነፍ ደስ አይለውም። በተለይ እንደ ፔፕ ጋርዲዮላ አይነት ውጤታማ አሰልጣኝ ፡ አደለም የደጋፊ ትችትና ስድብ ተደምሮበት ይቅርና ፡ ውጤት ማጣቱ በራሱ ህመም ሆኖ ሳለ ፡ ሰውየው የሚያደርገው እስኪጠፋው ማዋከብ እና የተደረገለትን የማይቆጥር ፡ ይሉኝታ የሌለው ደጋፊ መሆን ብዙም ደስ አይልም።

ፔፕ ጋርዲዮላ በቅርቡ አድርጎት በነበረው ኢንተርቪው ፡ ወደፊት ወደ ሌላ ክለብ ሄዶ ማሰልጠን እንደማይፈልግ እየተንገሸገሸ ተናግሯል። ማረፍ እፈልጋለሁ ፡ ሌላ ክለብ ለማሰልጠን ምንም ሀሳብ የለኝም ነበር ያለው።

እንደው የቅርብ ጊዜ ስለሆነ የዚህን ሰው ነገር አነሳን እንጂ ውጤት ሲጠፋ ፡ ተጫዋቾችንና አሰልጣኞችን መፈጠራቸውን እስኪጠሉ ድረስ መስደብና ማማረር በእግር ኳሱ አለም እየተለመደ ያለ የጭካኔ ተግባር ነው።
#ይህም_አለ

ሚስት ባሏን ደሀ ነህ ብላ በፈታች በማግስቱ ባል የሚሊዮን ዶላሮች ሎተሪ አሸነፈ

ሰውዬው ለተወሰነ ጊዜ ሥራ አጥ ነበር እና ሚስቱ በሂደቱ ላይ እምነት መጣል ትዕግስት ስለሌላት ወደ ፊት ለመቀጠል ወሰነች። ሆኖም የፍቺ ሰነዶችን ከፈረመ ከአንድ ቀን በኋላ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ የሚለዉጠውን ሎተሪ አሸንፏል።

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
............
አንበሳ ባስ ውስጥ ዋሌቱን ከ860 ብር ጋር በቅፅበት የተሰረቀው ግለሰብ እንዲህ እያለ ሲጮህ ተደመጠ:-
" እዩ ተናግሪያለሁ ! ዋሌቴን አሁን እዚሁ ነው የተነጠኩ። ብትመልሱልኝ ይሻላል። ካልመለሳችሁልኝ በ1993 ዓ.ም ህዳር 14 አባቴ የሠራውን ታሪክ እደግመዋለሁ"

በማለት በቁጣ ተናገረ፤ ተሳፋሪዎቹ በሙሉ ተደናገጡ።
ሰውየው በመቀጠል...
"አባቴ ይሙት ባሱ ሳይንቀሳቀስ ህዳር 14/1993 የሞተውን የአባቴን ታሪክ እንዳልደግመው ለመጨረሻ ጊዜ ተናግሪያለሁ"

እያለ ሲዝት 5 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዋሌቱን ገልጦ ለማየት እንኳን ፋታ ያላገኘው ፍሬሽ ሌባ መሬት ላይ ይጥለውና እራሱ አንስቶ "ይሄው ዋሌትህ" በማለት ይመልስለታል።

ባሱ ውስጥ የነበሩ በእድሜ ገፋ ያሉ ተሳፋሪዎችም
"እሰይ ተመስገን ሊጨርሰን ነበር" እየተባበሉ ኣውቶብሱ ጉዞውን ቀጠለ።

የባሱ ተሳፋሪዎች ሰውየው መረጋጋቱን ካስተዋሉ በኋላ የ1993ቱን ታሪክ ለመስማት ቋምጠው :-
"አባትህ በ1993 ህዳር 14 ምን ነበር ያደረጉት እባክህ ?" በማለት ፈራ ተባ እያሉ ሲጠይቁት ምን ብሎ ቢመልስላቸው ጥሩ ነው ?

"አባቴ ዛሬ በህይወት የለም። ነፍሱን ይማረውና ህዳር 14/ 1993 ላይ እንዲህ እንደኔ አንበሳ ባስ ወስጥ ለታከሲ መሳፈሪያ እንኳን ሳያስቀሩ ሌቦች ገንዘቡን ሰርቀውት ጃኬቱን እንደ እብድ እያውለበለበ ከሳር ቤት ፈረንሳይ ድረስ በእግሩ ነበር የሄደው።

እኔም ዛሬ ብሬን ባትመልሱልኝ ኖሮ ያው የታክሲም ስለሌለኝ በእግሬ ወደ ቤቴ በመሄድ የአባቴን ታሪክ እደግመው ነበራ" ብሏቸው እርፍ፡፡

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
ባኢስ!

ብዙ ግዜ የቲክቶክ ቪዲዮ ስመለከት ባኢስ የተባለ ሰው አያለሁ።

በባኢስ ውስጥ ነገን አያለሁ፤ ከቀልዱ እና የማስታወቂያ ስራው ባለፈ ህይወቱን እንማርበት:-

ምናልባት ከቅርብ ግዜ በፊት ባኢስን ከቅርብ ወዳጂ ዘመዶቹ ወይም የአካባቢው ሰዎች ውጭ የሚያውቀው ይኖራል ብዬ አልገምትም ፤ የሚያውቁትም ከዚህ እድሜው በኋላ ህይወቱ በዚህ ልክ ይቀየራል ብለው ይጠብቃሉ ብዬ አላስብም።

አሁን ግን በፊልም፣ ሙዚቃ ወይም ሌሎች እውቅና ሊያመጡ በሚችሉ ዘርፎች ከተሰማሩ ግለሰቦች ያልተናነሰ እውቅና ሲኖረው በስራዎቹም ኑሮዉን በጥሩ ሁኔታ እየመራ እንደሆነ ያስታውቃል።

እኔም ፈጣሪ እድሜ ይስጠን እንኑር እንጂ የቀረ፣ የቆመ፣ ያበቃ ነገር እንደሌለና ሁሉም ነገር የዘገዬ ቢመስልም በግዜው ውብ ይሆናል፤ የረፈደ ነገር የለም ብዬ እንዳስብ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ተስፋ የቆረጥን የባኢስ ህይወት፣ የእኛ ቀን እንደሚመጣ እና ነገን ተስፋ እንድናደርግ ያደርገናል።

በተስፋ ነገን ለማየት እንጓጓ መቸም ቢሆን ከዛሬ ነገ የተሻለ ነው።

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
#ሲሳይ

አዲስ አበባ ከተማ እጁ ላይ የቀረችለት ብቸኛው ሰው ነው‼️

አዲስ አበባ ሳር እያነጠፈች፣ ትዝታ እየቀበረች፣ የዘመናት ውሏ እየፈረሰ ዳቦ እየተቆረሰ በሄደ ቁጥር አንድ ሰው የማይጠገብ ትዝታዋን ጓዳ ጎድጓዳዋን ከብብቷ ውስጥ ገብቶ ጠረኗን እየማገ ብቻውን ይመዘግበው ይዟል።

በብዙዎች ልብ ውስጥ ልትቀር ጥቂት የቀራትን ከተማ በልዩ ጥበብ ከትበህ ለትዝታ ስለምታስቀርልን እናመሰግናለን!

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
በዚህ ምድር ብለን በምንጠራው ፕላኔት ውስጥ ካሉ ፍጥረቶች ሁሉ አንተ የላቅክና እጅግ የመጨረሻው ጠቃሚ ፍጥረት ነህ፡፡

ነገሩ ለጊዜው ግልፅ ሆኖ ባይታይህም የተፈጠርክበት አንዳች ምክንያት አለ፡፡ባይሆንማ ኖሮ እንደብዙ ያልተለመዱ ፅንሶች ጭንጋፍ ሆነህ በቀረህ ነበር፡፡

የሰው ልጅ የከበረ ሀብቱ ትጋቱ ነውና የተፈጠርክበትን ምክንያት ፈልጎ በማግኘት ላይ ትጋ!

Join us...
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
    ✦✺ @Tesfa_Biranaye ✺✦
አንድ ቀን አንድ የስነ-ልቦና መምህር ወደ ክፍል ገብቶ ተማሪዎቹን "ዛሬ ጌም ብንጫወት ምን ይመስላችኋል አላቸው?"

ምን አይነት ጌም እንደሆነ ሲጠይቁት፣ እሱን አብረን እናየዋለን አለና ከመካከላችሁ አንድ ፈቃደኛ ተማሪ እፈልጋለሁ አለ። አንድ ተማሪ እጅ አወጣና ጌሙ ተጀመረ።

መምህር:- "ሰላሳ በህይወትህ የምትወዳቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ፃፍ!" አለው።

ተማሪው:- ከቤተሰቦቹም፣ ከሩቅ ዘመዶቹም፣ ከጓደኞቹም እያለ የሰላሳ ሰው ስም ፃፈ።

መምህር:- "አሁን ከፃፍካቸው ውስጥ ብታጣቸው ግድ የማይሰጥህን አምስት ሰዎችን ስም ሰርዝ" አለው።

ተማሪውም አምስት ስም ሰረዘ ሰረዘ።
መምህሩ:- "አሁን ደግሞ የአስር ሰዎችን ስም ሰርዝ አለው"።

እንዲህ እንዲህ እያለ የአራት ሰዎች ስም ቀረው(የእናቱ፣ የአባቱ፣ የልጁና የሚስቱ)
መምህር:- "ከነዚህ ከ4ቱ ሰዎች ሁለቱን ሰርዝ አለው።"

ተማሪው: በከፍተኛ የሀዘን ስሜት ተውጦ የወላጆቹን ስም ሰረዘ።

መምህር:- "አሁን የቀሩህ ሁለት ሰዎች ሚስትህና ልጅህ ናቸው ከሁለቱ አንዱን አስቀርተህ አንደኛቸውን ሰርዝ አለው።"

ተማሪ:- በሃዘን እያነባ የልጁን ስም ሰረዘ። ተማሪዎቹ በሁኔታው ግራ ተጋብተው መጨረሻውን ለማወቅ ጓጉተዋል።

መምህር:- "ሚስትህ ብትሞት ሌላ ሚስት ማግባት ትችላለህ፣ እንዴት ከወላጆችህና ከልጅህ አብልጠህ ሚስትህን መረጥካት?" ሲል ጠየቀው።

ተማሪውም:- "ወላጆቼን አጥብቄ ብወዳቸውም እድሜያቸው ገፍቷልና በሞት ትተውኝ ይለዩኛል። ልጄም በፍቅር ተንሰፍስፌ ባሳድገውም ሲያድግ ጥሎኝ ወደሚስቱ ይሄዳል። በህይወት እስካለሁ ድረስ መቸም ቢሆን የማትለየኝ ሚስቴ ናት። ሚስቴ የኔ የምርጫ ጉዳይ ሳትሆን ስጦታዬ ናትና ለዛ ነው እሷን ያልሰረዝኩት" ብሎ መለሰ።

አብረውት የሚማሩት ተማሪዎች በመልሱ ተደስተው አጨበጨቡለት። መምህሩም አብሮ አጨበጨበለት!
ዝነኛው የሲያትል Gum Wall በታሪኩ ለሁለተኛ ጊዜ ሊፀዳ ነው ።
.....

በ1990 ዎቹ መጀመሪያ ላይ በሲያትል በሚገኝ አንድ የገበያ አዳራሽ ውስጥ በሚገኝ ሲኒማ ቤት ፡ ፊልም ለማየት የተሰለፉ ሰወች ያኝኩት የነበረውን ማስቲካ እንደቀልድ በግድግዳው ላይ መለጠፍ ጀመሩ ። በጥቂት ጊዜያት ውስጥም ግድግዳው በሙሉ በማስቲካ ተሞላ
.....
በ2009 በተሰራው Love Happens በተሰኘው የፍቅር ፊልም ላይ ፡ ጄኔፈር አኒስተንና አሮን ኤከርት በዚህ ስፍራ ተገኝተው ያኘኩትን ማስቲካ በግድግዳው ከለጠፉ በኋላ ደግሞ ፡ ስፍራው ይበልጥ ዝነኛ ሆኖ ፊልሙን ያዩት ሁሉ እየሄዱ የማስቲካ አሻራቸው ያስቀምጡ ጀመር ።
.....
ሆኖም ፡ ከቀን ወደቀን የሚለጠፈው ማስቲካ እየበዛ በመሄዱና ግድግዳውን እንዳይጎዳው በማሰብ. . በ2015 ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲፀዳ በተደረገበት ወቅት እያንዳንዱ ሰው የሚለጥፈው ተጠራቅሞ 2,350 ፓውንድ የሚመዝን ማስቲካ ከግድግዳው ላይ ተነስቶ የተጣለ ቢሆንም ፡ ብዙም ሳይቆይ ግድግዳው እንደገና በማስቲካ ተሸፍኖ የጎብኝዎችን ትኩረት ሲስብ ቆይቷል ።

......
በተናጠል ቀላል የሚመስሉ ድርጊቶች በህብረት አስደናቂ ነገር መፍጠር እንደሚችሉ ማሳያ የሆነው ይህ የማስቲካ ግድግዳ ከዚህ በተጨማሪም, ውበት እና ጥበብ ባልተመለዱና እንግዳ በሆኑ መንገዶች እንደሚፈጠሩ የሚያሳይ ነገር ነው ።
የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ አሸናፊዎች
***

• የዓመቱ ምርጥ ሜዲካል ኮንቴንት ክሬተር - ዶ/ር ሀረገወይን ሙሴ

• የዓመቱ ምርጥ አነቃቂ ኮንቴንት - ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ

• የዓመቱ ምርጥ የስዕል፣ ግጥምና ሌሎች አርትስ ኮንቴንት- ሲሳይ

• የዓመቱ ምርጥ መላ ሽልማት - I store by sophi

• የዓመቱ ምርጥ ኤዲቲንግ ኤንድ ኢፌክት -ሲሳይ

• የዓመቱ ምርጥ ሙዚቀኛ እና ፕሮዲዩሰር - ዮንዚማ

• የዓመቱ ምርጥ ሶሻል ኢምፓክት ኮኒቴንት - ዶ/ር አብይ ታደሰ

• የዓመቱ ምርጥ የንግድ እና ትምህርታዊ ይዘት ተሸላሚ - ሚስ ፈንዲሻ/Miss Fendisha/

• የዓመቱ ምርጥ ዳንስ ኤንድ ፐርፎርማንስ አሸናፊ- ጃዝሚን/jazmin_ hope1/

• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት- ኤላ Review

• የዓመቱ ምርጥ ሪቪው ኮንቴንት ልዩ ተሸላሚ- Baes

• የዓመቱ ምርጥ ስፖርት ኤንድ ፊትነስ ኮንቴንት - ቶማስ ሀይሉ

• የዓመቱ ምርጥ ላይቭ ስትሪመር ተሸላሚ - ታኩር ሌጀንድ

• የዓመቱ ምርጥ ላይፍ ስታይል ኮንቴንት ተሸላሚ - Miss leyu

• የዓመቱ ምርጥ ሴት ፈኒየስት ተሸላሚ - ባዚ

• የዓመቱ ምርጥ ወንድ ፈኒየስት ተሸላሚ - ኤላ ትሪክ/Elatick

• የዓመቱ ምርጥ ሚመር አዋርድ ተሸላሚ- I did it በዘነዘና

• የዓመቱ ምርጥ ትራቭል ኮንቴንት አዋርድ- አቤል ብርሃኑ
🙏🙏🙏

#ለጥንቃቄ🚨

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ?

1. ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦

ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

2. በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦

በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

3. በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦

ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

4. መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦

የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።
2025/01/01 19:21:37
Back to Top
HTML Embed Code: