Telegram Web
"እብዱ ደራሲ"
(ተስፋኣብ ተሾመ)

አንዲት መንፈስ መጥታ ማሪያም ነኝ አለችኝ፤ ከዛም ጩቤ ይዤ እንዲዞር፥ ጓድ መንግስቱ ሃይለማርያምን እንድገድል፥ በየጎዳናውም እንድሰግድ አዘዘችኝ። እኔም ሳላመነታ ታዘዝኳት"

ከላይ ያለው ንግግር የልጅ ጨዋታ ቢመስልም የታላቅ ደራሲ እና ጋዜጠኛ የእለት ተዕለት ገጠመኝ ነው።
እሱ እውነተኛ ሰው ሳይሆን በልብወለድ የተሳለ አይታመኔ ገፀባህርይ ይመስላል። ጎዳና ተዳዳሪነት ፥ ልመና፥ የአሮጌ መፅሐፍ ነጋዴነት ፥ የአእምሮ መታወክ(እብደት)፥ ደራሲነት ከህይወት ጓዳናዎቹ መካከል ናቸው።

ትክክለኛ ስሙ ሂሩይ ሚናስ ሲሆን አውግቸው ተረፈ የሚለው የብእር ስሙ ደግሞ ዝነኛ ሆኗል። ለሁለት አመታት ያህል የአይነስውር መሪ ነው። በልመና ስራ የተሰማራን አይነስውር ይመራል፥ በልመና የተገኘውን ገቢ ለእኩል ተካፍሏል።

በጎጃም ደጀን የተወለደው ሂሩይ በ1950ቹ የእህል ለማኝ ነበር። በልመና ያገኘውን እህል በመሸጥ የእለት ተዕለት ኑሮውን መርቷል።

እንደማንኛው ሰው ትዳር መሰረተ፥ ጎጆ አቆመ። ከትዳር በኋላ ሚስቱ ልጅ ስትወልድ ጭንቅ መጣ። እመጫት ሚስቱን የሚያበላት ነገር አልነበረውም። ደራሲው አላመነታም። ወደ ሆቴል አቅንቶ ትርፍራፊ ለምኖ ይዞላት ሄደ። ወላዷ ሴት ትርፍራፊ መብላት አልሆንልሽ ብሏት 'በረሃብ ብሞት ይሻለኛል' አለች። የሚያደርገው ግራ የገባው ደራሲ ተንሰቅስቆ አለቀሰ፥እንደ ህፃን ልጅ ተነፋረቀ።

ለ3 አመታት ያለ አናጋሪ ብቻውን በአንድ ቤት የኖረው አውግቸው የአእምሮ መታወክ ችግር ክፉኛ ጎድቶታል። "ከ1972-1974 ቀን በቀን ጫት እየቃምኩ ከጠዋት እስከማታ ማንበቤ እና በዚህ ወቅት ሳላቋርጥ እበሳጭና እንቅልፍ አጣ ስለነበርኩ ነው ያበድኩት። እንቅልፍ ማጣት፥ ብዙ ማንበብ ፥ የገንዘብ እጦት አሳብዶኛል" ይላል።

ለእንቅልፍ ችግሩ መድሃነት ፍለጋ ሃኪም ዘንድ ሄዶ ነበር። አለመታደል ሆነና ለችግሩ የተሰጠው መድሃኒት ሌላ ችግርን ፈጠረበት። የተሳሳተ መድሀኒት ተሰጥቶት እግርና ወገብ ለሚያሸማቅቅ በሽታ ዳርጎት ብዙ ርቀት መራመድ የማይችል ሆኗል። ቀሪ እድሜውን ሁሉ በዛች የተሳሳተች መድሃኒት ጦስ ሲቸገር ኖሯል።

በእብደት ዘመኑ 'ማሪያም ነኝ' የምትል መንፈስ የምታናግረው ሲሆን እሱ ለመንፈሷ ከመታዘዝ ውጪ የሚያደርገውን አያውቅም። በየመንገዱ እንዲሰግድ ታዘዋለች። ሳያመነታ ይተዘዛል። በጎዳና መሓል በግንባሩ ተደፍቶ ለሱ ብቻ ለምትታየው መንፈስ ይሰግዳል። መንፈሷ ጩቤ እንዲይዝ አዛው ጩቤ ታጥቆ መዞር ጀምሯል። የጩቤው አላማ ያስቃል። 'በታጠቅከው ጩቤ ከሰይጣን ጋር ትፋለምበታለህ' ብላዋለች።

ለደራሲው 'ማሪያም ነኝ' ብላ ራሷን ያስተዋወቀችው መንፈስ ነገረ ስራ ሁሉ ግራ አጋቢ ነው። አንድ እለት የተለየ ተልዕኮ ሰጠችው። "ወደ ቤተመንግስት ሂድ ከጓድ መንግስቱ ሃይለማርያምጋ ፍልሚያ ግጠም፥ ፕሬዝዳንቱን ሳትገድል እንዳትመለስ" አለችው። ሳያመነታ ታዘዛትና ወደ ቤተመንግሥት አቀና።
ቤተመንግሥት ሄዶ ጠባቂዎቹን "ጓድ መንግስቱ ሃይለማሪያምን ፍልሚያ ገጥሜ ልገድለው ስለምፈልግ አገናኙኝ" አለ።

በድርጊቱ የተቆጡ ጠባቂዎች ሊገድሉት ይችሉ ነበር። ነገር ግን የአእምሮ መታወክ እንዳለበት በመታመኑ በይቅርታ ተሸኘ።

መንፈሷ ሌላ ተልዕኮ ሰጠችው። "በባህርዳር በኩል ወደ ሱዳን ሂድ፥ ትራንስፖርት አትጠቀም፥ ከአዲስ አበባ እስከ ሱዳን ያለውን መንገድ በእግርህ ተጓዝ" አለችው። ደራሲና ጋዜጠኛ አውግቸው ተረፈ ሳያቅማማ ታዘዛት። ጉዞ ከጀመረ በኋላ በእጁ የያዘውን ገንዘብ ሁሉ በመንገዱ ጨረሰ።...

ደብረ ማርቆስ ሲደርስ ወደ አእምሮው ቢመለስም የሚባለው የለውም። በኪሱ አንዳች ገንዘብ ስላልነበረ ወደ ፖሊስ ጣቢያ አቀና። "የድርጅቴን ገንዘብ ሰርቄ ስለጠፋው እሰሩኝ" አላቸው። አለመታደል ሆነና ፖሊስ ጣቢያው ምግብ አልነበረውም። ይኸን ሲያውቅ አላመነታም፥ የለበሰውን ሱሪ አውልቆ በ15 ብር ሸጠ።

አውግቸው አንድ የተለየ ነገር ያደርግና መንፈሷ ትታው ስትሄድ ያደረገውን በማስታወሻው ይፅፋል።

..... "እብድ ማለት ሰይጣን ያለበት ማለት አይደለም። የአእምሮ ችግር ተጠቂ ሰዎችን ማግለልና ማሰቃየት ችግራቸውን ማባባስ ነው" ይል ነበር አውግቸው ተረፈ።

በነገራችን ላይ "እብዱ" የሚል ዝነኛ መፅሐፍም አለው።


@Tfanos
@Tfanos
"ስብሃ ነጋ ሌባ እና ነፍሰ ገዳይ ነው"
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

ሌፍተናንት ጀነራል ዮሐንስ ገብረመስቀል ከቀደሙ ወያነዎች መካከል ነው። 1968 ጀምሮ በትጥቅ ትግል ተሳትፏል። ህወሀት መራሹ ጦር ደርግን አሸንፎ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ጦር ይዞ ወደ አዲስ አበባ ከገቡ የህወሓት ወታደሮች መካከል ነው።

በትግራይ በረሃ ትጥቅ ትግል የጀመረው ዮሐንስ ገብረመስቀል ጀነራልነት ድረስ ደርሷል። በነኚህ ሁሉ አመታት ከመለስ ዜናዊ እስከ ፃድቃን ከአቦይ ስብሃት እስከ ሳሞራ የኑስ ጋር አብሮ ሆኖ ተፋልሟል። ከነርሱም ጋር ተሟግቷል።

ሌ/ ጀነራል ዮሐንስ "አዙሪት" የተሰኘ መፅሐፍ ያሳተመ ሲሆን በመፅሐፉ ገፅ 50 ላይ ስብሃት ነጋን በጠንካራ ቃላት ተችቷል። "ስብሃት ነጋ ሶስት መለያ ባህሪዎቹ ሌብነት ገዳይነት እና የትግራይን ጥቅም ለሌሎች አሳልፎ መስጠት ነው" ብሏል።

የፀሐፊውን ምክኒያቶች እናንሳ

በትጥቅ ትግሉ ወቅት የህወሓት ታጋዮች ለሻዕቢያ ድጋፍ ያደርጉ ነበር። በፀሐፊው አገላለፅ አንዳንዴ የትጋራይ ልጆች ለኤርትራ አማፂያን አላግባብ ህይወት ይገብራሉ። በስመ ገናናው የቀይ ኮከብ ዘመቻ ወቅት ከደርግ ጋር ለመፋለም ሻዕቢያ 6 ሺ ሰራዊት ሲያሰልፍ ህወሃት ደግሞ ከሻዕቢያ ጎን በመሰለፍ 4500 ሰራዊት አሰልፎ ተዋግቷል። በዛ ጦርነት የህወሓት ተዋጋዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የቀይ ኮከብ ዘመቻ ከከሸፈ በኋላ በኤርትራ ምሽግ የነበሩ የሻዕቢያ ወታደሮች ከምሽግ ወጥተው እረፍት እንዲያደርጉ ሲፈቀድ ሻዕቢያን ለማገዝ የሄዱት የህወሓት ወታደሮች ግን የሻዕቢያን ቦታ ጭምር ሸፍነው በምሽግ ለመቆየት ተገደዱ።
ፀሐፊው በገፅ 32 "ከሃዲያኑ (የህወሓት) አመራሮች የትግራይን ወጣት ለሻዕቢያ አመራር አሳልፈው ሸጠውታል" ይላል።

ለቀይ ኮከብ ዘመቻ የህወሓት ታጣቂዎች በይፋ ከመላካቸው በፊትም ጀምሮ በስውር ለሻዕቢያ ይሰጡ ነበር።

ህወሃቶች "መብታችንን እናስከብር" ብለው የሚቀላቀሏቸውን ወጣቶች ስልጠና በሚል ሽፋን ወደ ኤርትራ ይልካሉ። እኚያው ወጣቶች ከሻዕቢያ ጋር ተሰልፈው የጦርነት ሲሳይ ይሆናል።

የካቲት 1972 አ.ም 5 ሺ ምልምል ወታደሮች የጦር መሳሪያ ታመጣላችሁ ተብለው ወደ ኤርትራ ተላኩ። ምልምሎቹ በውሃ ጥም ተቃጥለው የተባሉበት ቦታ ቢደርሱም የተባለው ጦር መሳሪያ አልነበረም። ሳህል ሲደርሱ የገጠበቃቸው የሻዕቢያ ስልጠና ነበር። 5 ሺዎቹ የትግራይ ወጣቶች ስልጠናቸውን ከጨረሱ በኋላ 3ሺዎቹ ምሽግ ገብተው ለሻዕቢያ እንዲዋጉ ተፈረደባቸው።

ከዚህ ክስተት በኋላም ብዙ ሳይቆይ ሌላ 2300 ምልምሎችን ህወሃት ለተመሳሳይ አላማ ወደ ኤርትራ ላካቸው።

የህወሓት ታጋይ የነበረው ሌፍተናንት ጀነራል ዮሐንስ ገብረመስቀል ህወሃትን "የሻዕቢያ መሳሪያ" ይላል በመፅሐፉ። ገፅ 45 ላይ የህወሓት አመራሮች የሻዕቢያን ጥያቄዎች ለማሟላት ሁልጊዜም ዝግጁ መሆኑን ፅፏል።
ህወሃቶች "ለትጋራይ መብት" ለመታገል በረሃ የወረዱ ወጣቶችን እየገበሩ የሻዕቢያን እቅድ እና ስትራቴጂ ደጋግመው ፈፅመዋል። በትግራይ ወጣቶች ኪሳራ ሻዕቢያ ትርፋማ እንዲሆን አድርገዋል።

ከ1972- 1976 ድረስ ባሉት አመታት እስከ 40 ሺ የሚደርሱ የትግራይ ወጣቶች "ስልጠና" በሚል ሽፋን ህወሃቶች ወደ ኤርትራ የላኳቸው ሲሆን አብዛኞቹ ለሻዕቢያ ደህንነት ሲባል ባደረጉት ጦርነት ህይወታቸውን ከፍለዋል።

ስብሃት ነጋ "የኢሳያስ የቁርጥ ቀን ባለሟል" እንደሆነ መፅሐፉ ያብራራል። የትግራይ ወጣቶች ለሻዕቢያ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ሲከፍሉ ዋና ተዋናዩ ስብሃት ነጋ መሆኑ በመፅሐፉ ተገልጿል።

ፀሐፊው ኢሳያስ ከአረብ ሐገራት በሚያገኘው ረብጣ ገንዘብ ስብሃትን ገዝቶታል ይላል።

አድራጊ ፈጣሪው ስብሃት "ጨካ*ኝ ፥ ሞት ፈራጅ ሌ.ባ ፥ የትግራይን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ..." ወዘተ ስለሆነ የትግራይ ወጣቶች ለሻዕቢያ ጥቅም ሞተዋል ይላል ሌፍተናንት ጀነራሉ።

ከላይ እንደጠቀስኩት ፀሐፊው ከ 1968 ጀምሮ ታጋይ ነበር። በባድመ ጦርነት የተሳተፈ ፥ በኢህአዴግ ዘመን እስከ ጀነራልነት የደረሰ ፥ ውጭ ሐገር ሄዶ የተማረ እና ሰላም ለማስከበር ከሐገር ውጭ የተሰማራ ሰው ነው።
የእርሱ መፅሐፍ በአንዳንድ ጉዳዮች ምናልባትም "ከፈረሱ አፍ መስማት" እንደሚባለው ነው።


@Tfanos
@Tfanos
ሀ፥ ልጅ ሆነን በሬዲዮ ዘፈን እንሰማ ነበር። ያኔ ከምንሰማቸው ዘኖች መካከል "ኑደሬ ጋሞ ጎፋ" የሚለው ዘፈን በማይገባኝ ምክኒያት ይመስጠኛል።
ትንሽ ከፍ ስል የጋሞዎች ዜማ ደስ ይለኝ ጀመረ።

ለ፥ ከተወሰነ አመት በፊት ወደ አርባምንጭ ሄድኩ። ያኔ በጣም በቁምነገር ሽማግሌዎችን አናገርኳቸው። የጋሞን የሽምግልና ባህል ፥ የህዝቡን አኗኗኗር ወዘተ አሰረዱኝ። ወደ ሻሸመኔ ስመለስ "ጋሞች ደስ ሲሉ" እያልኩ ነበር።

ሐ፥ አሰፋ ጫቦን አለመውደድ አይቻልም። አሰፋን የማይወድ ሰው አሰፋን ያላነበበ ቢሆን ነው። "የትዝታ ፈለግ" የተሰኘውን ምርጥ መፅሐፍ ሳነብ ድጋሚ ጋሙዎችን ወደድኩ። "እንዴት ያለ ምርጥ ህዝብ ነው" አልኩ።

መ፥ ጋሙኛ እሰማለሁ። (በእርግጥ ይሄ ግነት ነው። የምሰማው ምናልባት የቋንቋውን 25 በመቶ ነው) ቢሆንም እሰማለሁ ካልኩ እሰማለሁ።

ሠ፥ ዛሬ ለጓደኞቼ በወሬ መሐል ጋሙዎችን እንደምወዳቸው ነገርኳቸው። ልብ አድርጉ በሞቀ የፖለቲካ እና የታሪክ ወሬ መሐል ነው ስለጋሙ ያወራሁት።

ረ፥ ለአንዳንድ ሰዎች "ብሔሬ ጋሙ ነው" ብዬ ነግሬ ሁላ አውቃለሁ።

ሰ፥ ብሔር በምርጫ የሚሰጥ ቢሆን ኖሮ ጋሞ እሆናለሁ።

ጋሞይ ጊታ
ዶርዜ ዳሮ


@Tfanos
እናት ፓርቲ "የጣሪያና ግድግዳ/ የንብረት ግብር" በማለት የአዲሳባ ከተማ አስተዳደር የሚሰበስበው ግብር ሕገ ወጥ ነው በማለት ክስ መስርቶ ነበር።
ክሱን ሲከታተል የነበረው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የእናት ፓርቲ ክስ ትክክል መሆኑን አምኖ ተቀብሏል። በዚህም መሰረት ግብሩ እንዲታገድ ወስኗል።

ይህ ምን ይነግረናል?

አንዳንድ የመብት ድፍጠጣዎች ምንጫቸው የኛ አለመጠቅ ውጤት መሆኑን አያስረዳንም?


@Tfanos
የመግደ.ያ ዛፍ
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *
በአንድ ዘመን በሐገራችን ኢትዮጵያ ሰዎች እየተሰቀሉ የሚገደሉባት ስመ-ጥር ዛፍ ነበረች፥ የሞት ዛፍ።

ከጥንት ጀምሮ መንግስታት ከባድ ወንጀል ፈፅመዋል ያልዋቸውን በሞት ሲቀጡ ነበር።
ከሞት ፍርደኞች መካከል አንዳንዶች አንገታቸው ላይ ገመድ ሲገባ ሌሎች ደግሞ በሰይፍ ይቀላሉ። ከፍሎቹ ደግሞ የጥይት ሲሳይ ይሆናሉ።

የነገራችን አስረጅ ይሆን ዘንድ የአልሃንድሮ ዴልባዩን "ቀይ አንበሳ" መፅሐፍ ምስክር ጠርተን ወጋችንን እንቀጥል።

አዲሳባ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከቢጤዎቿ ሁሉ የምትለይ ዛፍ ነበረች። ከሌሎች ዛፎች የለያት ሰዎች የሚሰቀሉባት መሆኗ ነው። የዛፏ ግንዱ ዙሪያውን በሞላ የሰው ገላ ተሸክሟል።
ዴል ባዩ በመፅሐፉ "ይቺ ዛፍ አመቱን ሙሉ የሬሳ ማከማቻ ሆና ታገለግላለች" ብሏል።

የተሰቀሉ ሰዎች በድን ዝናብ ሲወግረው፥ ፀሐይ ሲመታው፥ ነፋስ ሲያወዛውዘው ይውላል።
እጃቸው የፊጢኝ የታሰሩ ፥ አፋቸው ጨርቅ የተወተፈበት ፥ አይናቸው የወጣ አስክሬ.ኖች ይታያሉ። ሬሳቸው የተንጠለጠለበት ገመድ እስኪበጠስ እንደተሰቀሉ ይቆያሉ።

አከባቢው ሞት የሚያንዣብበት ቢሆንም እንቅስቃሴ ይደረጋል። አንዳንድ ሰው ቆም ብሎ የተሰቀሉትን በአርምሞ ያያል። የሆነኛው አስክሬን ላይ ትኩረት በማድረግ ማዘንና ከንፈር መምጠጥም ይኖራል።

በዛፏ አከባቢ አነስተኛ ፍርዶች ይሰጣሉ። ቀማኛ ፥ ማጅራት መቺ፥ ወዘተ እንደየጥፋቱ ይቀጣል። እንደ ፍርዱ ደረጃ አንድ እጅ ይቆረጣል ወይም አንድ እግር አሊያም ሁለቱም ይቆረጣል። ጆሮ እና ምላስም እንደአላስፈጊ ነገር ተቆርጦ ሊወገድ ይችላል።

ከእለታት በአንዱ የጎሳ አለቃ የነበረ ተዋጊ በርካታ ወታደሮችን ከገደለ በኋላ በቁጥጥር ስር ዋለ። ለፍርድ ቀርቦ ሞት ተፈረደበት። በዛፏ ላይ ተሰቀለ። በተሰቀለበት አይኖቹን አሞሮች በሉት


@Tfanos
"ጃኮ" የሚባል አዲስ የማህበራዊ ትስስር ገፅ መጥቷል። ብዙ ነገሩ ከቲክቶክ ጋር ይመሳሰላል። ዛሬ ገብቼ አየሁት። በ0 ፎሎወር የመጀመሪያ ቪዲዮ ጫንኩበት 😂

ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ዝቅ አድርጎ ማየት እያበቃ ነው። ተገዳዳሪ ሆነዋል። ላወቀበት ደግሞ በጣም ጠቃሚ ነው።

ይህ ማህበራዊ ገፅ በዛሬ ግምገማዬ እንደተረዳሁበት በቀላሉ ገንዘብ የሚሰራበት ጭምር።

በአጭሩ ሊንክ አስቀምጥላችሁ። ለራሳችሁም ክፈቱ። እኔንም ፎሎ አድርጉ። (እናንተንም አደርጋለሁ)

(የድሮ ሰዎች ጫካ መንጥረው ቦታ ይይዙና ሰው ሲበዛ ሃብታም ይሆናሉ። ጫካውን መንጥረን ቦታ እንያዝ 😀
አውዳመት አልወድም።

ሻሸመኔ እያለሁ ከቤተሰብ ቤት ወጥቼ ተከራይቼ መኖር ጀመርኩ። ለስሙ ተከራየሁ እንጂ በቀን አንዴ ቤት እሄዳለሁ። ሄጄ ምንም አልሰራም። እገባለሁ፥ ከዛ እወጣለሁ። አንዳንዴ እገባና "ዳዊት የት ሄዶ ነው?" እላለሁ። ዳዊት ወንድሜ ነው። ቢኖር ምንም አልልም እኮ። ዝም ብዬ እጠይቃለሁ።

ሁለት ቀን ብቀር ምህረት (እናቴ) ትደውላለች። አመት በአል ሲሆንስ? አመት በአል ሲሆን ቤት ላልሄድ እችላለሁ። ለምን ቀረህ አልባልም። ለበአል ቀን የማደርገው ምንም የተለየ ነገር የለም። ጓደኞቼም "እንኳን አደረሳችሁ" ባልላቸው አይከፉብኝም። ሰዎችም "እንኳን አደረሰህ" ባይሉኝ ቅር አይለኝም። የበአል መሰባሰቡም ሆነ ምግቡ ስሜት ሰጥቶኝ አያውቅም።

ልጆች ለበአል ልብስ ስገዛላቸው ደስተኛ እንደሚሆኑ ይታወቃል። እኔ ከልጅነቴም ለዚህ ነገር ስሜተ ቀዝቃዛ ነኝ። ልብስ ተገዝቶልን ወንድሞቼ ሃሴት ሲያደርጉ እኔ ልብሱን ከምንም ሳልቆጥር ኳስ ልጫወት እሄዳለሁ። በሂደት ይሄን ስሜቴን ቤተሰብ ለመዱት።
ልጅ ሆኜ ዶሮ ወጥ ተሰርቶ መብላት አስጠልቶኝ ለእኔ ለብቻዬ ሽሮ ተሰርቶ ያውል።

ነገር ግን አንዳንድ በአላትን በተመለከተ ልዩ ስሜት የሚፈጥሩብኝ ነገሮች አሉ። ምግቡ ፥ ድባቡ ፥ ወዘተ ሳይሆን መዝሙሮች ልዩ ስሜት ይፈጥርብኛል።

ለምሳሌ ፋሲካ ሲደርስ የተስፋዬ ተስፋዬ ጫላን "ገናናው የእኛ ኢየሱስ" እና የአዲሱ ወርቁን "ደሙን ለእኔ አፍስሶ" ደጋግሜ እሰማለሁ። በዓል እንደሆነ እንዲሰማኝ ያደርገኛል። በተለይ ተስፋዬ ጫላን ስወደው ልክም የለኝም። ሲደብረኝ ፥ ግራ ሲገባኝ ፥ ከሰው ስጣላ ፥ ደስ ሲለኝ ፥ የተሳካልኝ ሲመስለኝ ተስፋዬ ጫላን እሰማለሁ።

ለሰሞነ ፋሲካ "ገናናው የእኛ ኢየሱስ" የሚለውን ስሰማ አጥንቴ ድረስ ይሰማኛል። "የጴንጤ ብሔራዊ መዝሙር ገናናው የእኛ ኢየሱስ ነው" እንደምል ጓደኞቼ ያውቃሉ።

ጥምቀት ሲደርስ ደግሞ "በእደ ዮሐንስን ተጠምቀ..." የሚለውን መዝሙር እሰማለሁ። እሰማለሁ ስል ደጋግሜ ነው የምሰማው። ትላንት ከእንቅልፌ ስነቃ ዩቲዩብ ላይ ገብቼ ሰማሁ። ዛሬም ስሰማ አረፈድኩ።

በተለይ "ሰማያዊ ሰማያዊ ሰማያዊ ፥ ኢየሱስ ናዝራዊ" የሚለው ቦታ ዝም ብሎ ደስ ይለኛል። ደጋግሜ እሰመዋለሁ።

አውዳመት አልወድም አልኩ አይደል? ነገር ግን አውዳመት ሲደርስ ደጋግሜ የምሰማቸው እና ደስ የምሰኝባቸው መዝሙሮች አሉ።

በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ፥ ኢየሱስ ናዝራዊ
ሰማያዊ ሰማያዊ፥ ሰማያዊ ሰማያዊ
ሰማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ
.
አዳም ያጠፋውን ፥ልጅነት ሊያስመልስ
በሰላሳ ዘመን፥ ተጠመቀ ኢየሱስ
እርሱ አምላክ ሲሆን፥ ፈጥሮ የሚገዛ
ወረደ ወደ ምድር ፥እንዲሆነን ቤዛ

ሰማያዊ ሰማያዊ ፥ ሰማያዊ ሰማያዊ
ሰማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ


@Tfanos
ሐገርህን ትወዳለህ? ሐገርህን የምትወድ ከሆነ በሐገርህ የሚፈፀምን ኢ -ፍትሃዊነት አውግዝ። ማግለልን ተቃወም። ከገፊ ስርአት ጋር አትተባበር!

1+1 ስንት ነው? ይሄ ጥያቄ ተራ ነው አይደል? ማንም ያውቀዋል አይደል? አንዳንድ ጉዳዮች እንደዛ ናቸው። ማንም ሊገነዘባቸው ይገባል። ሰዎች ሐይማኖታቸው የሚያዘውን የማድረግ መብት አላቸው የሚለውን ማወቅ ለሁሉም ሰው የተገባ እውቀት ነው። አሳዛኙ ነገር ግን አንዳንዶች ይሄን ይረሱታል።

የሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ክልከላ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ "ይሄን የወሰኑ ሰዎች ንቃተ ህሊናቸው የት ድረስ ነው?" ብዬ ሳስብ ነበር። የተማሪዎቹን መብት ለማክበር የተለየ ጥበብ አይፈልግም። አማካይ ንቃተ ህሊና በቂ ነበር።

የማንም መብት ሲጣስ ሐገሩን የሚወድ ሁሉ መደንገጥ አለበት!
ሰዎች መብታቸው በተደፈጠጠ ቁጥር በገዛ ሐገራቸው ባይተዋርነት ይሰማቸዋል። በሰዎች ባህል ፥ እምነት ፥ እሴት ላይ የሚደረግ የመብት ረገጣ ብሔራዊ ስሜትን ይጎዳል። ሐገራዊ አንድነትን ያላላል።

ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ ስለ ሴኩላሪዝም መናጋገር ያሳፍራል።

የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ላይ የተፈፀመው የመብት ጥሰት ወንጀል ነው። ወንጀል ብቻ ሳይሆን ሐገራዊ ስሜት የሚጎዳ ነውር ጭምር ነው።


@Tfanos
2025/02/25 13:13:30
Back to Top
HTML Embed Code: