👆ይሄ አስጨቂ ጊዜና ሰአት መጣ አይደል??
እውነት በጭንቅ በመከራ በሀዘን ትካዜ ያላችሁ የእናቴ ልጆች ፈጣሪ አምላካችን እርሱ ይድረስላችሁ🙏 እባክህ ለኛም ልብ ይሰጠን ዘንድ ታላላቆችን አስነሳ ያየና የያየማ ልብ ያለ ይድን ዘንድ

#የካሌብ_ፅሁፎች
ሰላም ለእናንተ ይሁን! እንዴት አላችሁ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እስኪ በአሁኗ ሰዓት ላይብረሪ ውስጥ ተቀምጬ በሓሳብ ጭልጥ ብዬ የሞነጫጨርኳትን ግጥም አይሉት ብሶት ድርሰት አይሉት እልህ ብቻ ከዓቅሜ እና ጠባብ እውቀቴ በላይ ስለሆነችው ስለ....
እናት ሃገር ኢትዮጵያዬ 💚💛❤️አጠር ያለች ጽሁፌን ላካፍላችሁ መልካም ንባብ.....
ምን ተብሎ እንደሚጀመር እንኳን በቅጡ የማላውቅ ሰው ደፍሬ ስላንቺ ስለጻፍኩ በመጀመሪያ ይቅር በይኝ ....እናም ምን ልበልሽ እማ ???
የገነት ምሳሌ የአዳም አሻራ
የሆነሽ ሃገራችን ። እምዬ አንቺ እኮ ምሥራቅ ነሽ የፀሐዩ መውጫ! እባክሽ <<የሚያደርጉትን አያውቁም እና ይቅር በላቸው>> እያልሽ በተሰበረው ልብሽ ቃተሽ ለምኝልን። ከእሳቱ ጥፋት አሳልፊን እማ🙏
.....ግን እኮ ያወቅን መስሎን ነው!ብንዘልፍሽ ደግሞ ክብርም ስለሌለን እንጂ ልክሽን አውቀን አይምሰልሽ... የእውነት ያንቺን ክብር..... በጥቂቱ እንኳ የተረዱት እማ ከሕመምሽ መርጠው መርገፍን ወደዋል በፍቅርሽ
!! እኛ እኮ እውነት ስለሌለን አይደል ያጣነው እውነትሽን!? የያዝነው ሐይማኖት እንጂ የታለን እምነቱ ምንስ ነበረበት እሩቡን ቢያውሰን ከጥንቱ ???ለነገሩ እሱ መች ከልክሎን መርጠን እንጂ ባቢሎንን😭
...ቢሆንም የጥፋት ማሰናከያ ስላለ መሐላችን ስለታወረም ብርህ ህሊናችን ስለቀረበም ጥፋታችን ስለከፋ ሐጥያታችን ከበፊቱ ይልቅ ዛሬ አልቅሽልን!😭 ለምኝልን እጅሽን ዘርግተሽ ጸልይልን ለሚሰማሽ ፈጣሪያችን 🙏
ብቻ ይቅር ብለሽ ጥሪን/ኝ የእነ ኢትኤል የእነ ሄኖክ ሃገር....ቀና ብለሽ የተነሳሽ እና ያየሁ እለት ይውሰደኝ አምላክሽ እኔ ለአሑኑ በዚህ አበቃሁ 👐
📣ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት👇
👉 @TheHabesha0 👈

🌼 እንኳን ለአዲሱ ዓመት ለ 2017 ዓ.ም አደረሳችሁ 🌼 #ከካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ
#ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ ✊ ዳግም አንዳይጨልም ምድርሽ
ጥንትም ተገብሯል ዛሬም ይቀጥላል ይሄው ነው ታሪክሽ !
በፍቅር በአንድነት አርነት የሚያወጣን እሱ እኮ ነው ተስፋሽ 🤲
/እዚህችው የሞነጫጨርኳት መልዕክት ናት/
እናም ወገኔ ሆይ ያለፈው ሲያልፍ ዛሬም እንዳያልፈን ማለፋችን ላይቀን እንደተለመደው
♥ ኢትዮጵያሁን
♥ አፍሪካሁን
♥ ሰው ሁን
የምንጊዜውም መልእክታችን ነው
''ሰላም ፣አንድነት እና ፍቅር ፈጣሪ አብዝቶ እንዲያድለን ከልብ እመኛለሁ ።''
ፈጣሪ በቃ ይበለን መልካም አዲስ ዓመት 🙏
✍️#ካሌብ_ነኝ_ከህብረ_ብሔር_መናገሻ_አዲስ_አበባ 🌸 01/01/2017
🔊 ይህንን ድህረ-ገጽ ለመቀላቀል👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0

ሰላም ለሁላችሁም ውድ #የካሌብ_ጽሑፎች ቤተሰብ ! ዛሬ አጠር ያለች አስተማሪ ታሪክ ላጋራችሁ መጥቻለው መልካም ቆይታ።
አንድ ወላጅ አባት ከመሞቱ በፊት ለወንድ ልጁ እንዲህ አለው። ይሄን የምትመለከተውን ሰአት የሰጠኝ የኔ አባት ለአንተ ደግሞ አያትህ ነው ይህ ሰአት ከ 200 አመት በላይ ይሆነዋል። ዛሬ ይሄን ሰአት ላንተ መስጠት እፈልጋለሁኝ ነገር ግን ከመስጠቴ በፊት ከመንገዱ ባሻገር ወዳለው የሰአት መሸጫ ሱቅ ሂድና ይሄን ሰአት ለመሸጥ እንደምትፈልግ ንገራቸው ስንት እንደሚያወጣም ጠይቃቸው። አለው!!
.***
ልጁም ወደ ሰአት መሸጫው ሄዶ ሰአቱን አሳይቶ መሸጥ እንደሚፈልግ ለባለ ሰአት ሻጩ እና አዳሹ ነገረው!! ሰአት ሻጩም ሰአቱን ከተመለከተ በኋላ በ 5 ዶላር ብቻ እንደሚገዛው ነገረው!! ምክንያቱም ሰአቱ እጅግ ያረጀ እና ያፈጀ በመሆኑ ምክንያት ከፍተኛ ዋጋው 5 ዶላር ብቻ መሆኑን ደግሞ ነገረው። ልጁም በፍጥነት ይሄንንም መጥቶ ለአባቱ ነገረው!!
.***
አባቱም ልጆንን አሁን ደግሞ ወደ ቡና መሸጫ ሱቅ ሂድ አለው ልጁም ወደ ቡና መሸጫ ሱቅ ሄደ ለቡናም 5 ዶላር ከፈለ ተመልሶም ወደ አባቱ መጣ አባቱ ለልጁ ማስተማር የፈለገው ትልቅ ቁምነገር ስላለ አሁን ደግሞ ይሄን ሰአት ይዘህ ወደ ሙዜም ሂድ አለው!!
.***
ልጁም የአባቱን ትህዛዝ ሰምቶ ሰአቱን ይዞ ወደ ሙዜም ሄደ ሙዜም እንደደረሰም በሙዜሙ የሚገኙ ሰዎች ለአሮጌው ሰአት ሚሊዮን ዶላሮች እንደሚሰጡት ነገሩት!! ልጁም ይሄኔ ወደ አባቱ በአስቸኳይ መጥቶ እንዲህ አለ። አባዬ የሙዜሙ ባለቤቶች ለሰአቱ ሚሊዮን ዶላሮች እንደሚሰጡኝ ነገሩኝ አለው!!
.***
አባትየውም ልጁን ጠርቶ ወደ እራሱ እያስጠጋ እንዲህ አለው!! ልጄ ሆይ ዛሬ አንድ ነገር ልነግርህ እወዳለሁኝ የምነግርህን ነገር በልብህ መዝገብ ላይ አኑረው ለህይወትህም መመሪያ ይሁንህ በሄድክበት በገባህበት እና በወጣህበት ሁሉ በህሊናህ አሰላስለው የህይወትህም መመሪያ አደርገው!!
.***
ትክክለኛ ቦታ የተክክለኛ ዋጋ ትክክለኛ ስፍራ ነው!! በየትኛውም ግዜ እና ሰአት ላይ እራስህን በትክክለኛ ቦታ ካስቀመጥቀው እና በትክክለኛ ቦታ ከተገኘህ ዋጋህ በትክክልም የሚመጥንህ ነው!! ያንተን ዋጋ የሚወስነው ትክክለኛው ቦታ ላይ ብቻ መገኘትህ እና መቀመጥህ ነው!!
.***
ስለዚህ ሁሌም እራስህን ባልተገባ ስፍራ ላይ አታስቀምጠው ፤ ባልተገባም ስፍራ ላይ አትዋል ፤ ስፍራው ዋጋህን ያሳንሰዋል ጥቅምህንም ያወርደዋል!! ይህ የምትመለከተው ሰአት እኮ በትክክል ሰአት ነው!! ነገር ግን በሰአት መሸጫ ውስጥ ቢቀመጥ ከዘመኑ ጋር ስለማይሄድ ማንም አይፈልገው ዘመን አልፎበታል አርጅቷል አሮጌ ነው!! ነገር ግን ሙዚየም ቦታው ነው!! ማንም ሊያደርገው የማይፈልገውን ሰአት ብዙ ዶላሮች ከፍሎ ግን ይጎበኘዋል!! እናም ልጄ ስፍራህን እወቅ በትክክለኛው ቦታ ተገኝ!!
.***
ዛሬ ላይ በትክክለኛው ቦታ ላይ ባለመቀመጣችን ዋጋችንን ያሳነስን ሁላችን ከዚህ ትልቅ ነገር ልንማር ይገባል!! የት ነው ያለነው? ዋጋችንን ያሳነሰው እና ያቀለለን ነገር ምንድነው ስፍራው ወይስ እኛ? እራሳችንን እንጠይቅ!! ለራሳችን ክብር እንስጥ እራሳችንንም እናክብር !! ዋጋችንን አናርክሰው ካሌብ ነበርኩ ለዛሬ በዚሁ አበቃሁ መልካም አዳር ተመኘሁ 🙏 የነገ ሰው ይበለን 🙏 ፈጣሪ ሐገራችንን ይጠብቅልን።
♥ ኢትዮጵያ ሁን
♥ አፍሪካሁን
♥ ሰው ሁን
🔊 ይህንን ድህረ-ገጽ ለመቀላቀል👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0

ኢትዮጵያዊነት ሳንፈልገው በግድ የተጫነብን ዕዳ ሳይሆን የተዋብንበት ጌጣችን፣ የከበርንበት
ዘውዳችን፣ የወረስነው ቅርሳችን ነው፡፡
ሰላም👐 በያላችሁበት እንደምን አላችሁ ቤተሰቦች? በቅርቡ እንደ ከዚህ በፊቱ ፩ ጥናታዊ ጽሁፍ ይዤ የምመለስ ይሆናል እስኪ እንነቃቃ ታድያ 💪
የጥናታዊው ጦማር አርዕስት
#ኢትዮጵያ_እና_ኢትዮጵያዊነት
እስከዛ በተለመደው ቤተሰባዊ ስሜት ሰዎችን ወደዚህ ጋብዙ እንሰባሰብ ሃሳብ አስተያየታችሁንም በነፃነት ፃፉ አስቀምጡ ይሄ የኢትዮጵያዊነት የሐገር ፍቅር የሚደምቅበት ስለ ሰውነት የሚነሳበት ማረፊያችን ቤት ይሁን ዝለናልና በብዙ ድካም ችግር ፈተና። በዛውም የምንማርበት የምንዝናናበት የምንሻሻልበት የእውቀት አድማሳችንን የምናሰፋበትና እይታችን ላይም ከተጫነው ዳፍንቶች ለመላቀቅ ለኛ ትውልድ የምንማማርበት ለቀጣዩም ለታሪክ የሚቀመጥ ጥቂት አሻራ ይሁን።
ፍቅር አንድነትን ከጥንት ከመሰረቱ ከታሪካችን እንማር ፍቅር ያሸንፋል ጥላቻንም ያጠፋል!

ሰላም ለሁላችሁም ውድ ቤተሰቦች 🙌 እንዴት አላችሁ ?
ዛሬ ስለ #ኢትዮጵያና_ኢትዮጵያዊነት የተጦመረ ጦማር ይዤ እመለሳለው ባልኳችሁ መሰረት በጣም ባልረዘመ በጣምም ባላጠረ መልኩ በተለያዩ መንገዶች በሰበሰብኩት ተጨባጭ መረጃዎችና ግላዊ እይታዎች...
ጨመቅ ባለ መልኩ! ድምዳሜ የሚመስል ነገር ግን ያልሆነና የበኩሌን ታናሻዊ ጥናታዊ ጽሑፌን ይዤላችሁ መጥቻለው። በዚሁ አጋጣሚ ይሄ ቢስተካከል ይሄ ቢታረም ብላችሁ የምታስቡትን ማንኛውም ሃሳብ አስተያየቶች በውስጥ መስመሬ በ 👉 @Kalebadane777 ወይም በመወያያ ስብስባችን በ 👉 @ye_kaleb_tsehufoch
በመግባት አርሙኝ አበረታቱኝ አግዙኝ። 🙏 ከኔ ጋር ስላላችሁ እያመሰገንኩ ወደ ጽሑፉ አመራችኋለው መልካም ንባብ።
በቀደመው ዘመን ኢትዮጵያዊነት መከበሪያ፣ መታፈሪያ እና ተፈልጎ የማይገኝ ማንነት ነበር፡፡ አገራችን ኢትዮጵያም የፍትህ አደባባይ፣ የስደተኞች መጠጊያ፣ ለግፉዓን ዘብ የምትቆም፣ በእምነቷ የምትታወቅ መንፈሳዊት ሀገር ነበረች፡፡ዛሬ በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ ኀያላን መንግሥታት እንደ ሀገር ሳይቆሙ እና መኖራቸውም ሳይታወቅ ኢትዮጵያ ኀያል ገናና እና በስልጣኔዋ የታወቀች ስለመሆኗ የጥንት መዛግብት ተባብረው ይመሰክራሉ::
በማኅበራዊ ገጾች ከሚሰራጩት ጽሑፎች መረዳት እንደሚቻለው በስደት ባሉ አንድአንድ ወገኖች ኢትዮጵያዊነት ከጎሰኝነት በታች የሆነና ከዚህም አልፎ በጥቂቶች የተጫነ ማንነት ተደርጎ በመወሰድ ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከአብሮነት ልዩነትን፣ ከትልቅነት ትንሽነትን መርጠው የፈጠራና የተዛባ ታሪክ በመጥቀስ ኢትዮጵያዊነትን በማንኳሰስ ጎሰኝነትን ለማንገስ እና የአገር አንድነትን ለማፍረስ ሲቃዡ ይስተዋላል፡፡ ለመሆኑ ከሦስት ሺህ ዘመናት በላይ በአያት ቅድመ አያቶቻችን ዘርፈ ብዙ መስዋእትነት ተከብሮ የኖረው ኢትዮጵያዊነትና የአገር አንድነት አዲስ እንደተፈጠረ ማንነት የመነጋገሪያ ርእሰ ጉዳይ ሆኖ ከማየት በላይ ምን የሚያሳፍር ነገር አለ?
በመሆኑም ያለውን የወረወረ ፈሪ አይባልምና እኔም በኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ መነሻ ዙሪያ የበኩሌን አስተዋጽኦ ለማበርከት ይህችን መጣጥፍ ሳቀርብ የጎደለውን ሞልታችሁ የተሳሳተውን አርማችሁ በጥሞና እንደምታነቡልኝ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ የጽሑፉ ዋና አላማ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያ በጥንቱ መዛግብት እንዴት እንደተገለፁ ማሳየት እንጂ መረጃዎችን መተንተን ወይም መተቸት አይደለም።
ክፍል ፩ / አንድ / ስያሜ
እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ እጅግ ጥንታዊ የሆነና ያልተቋረጠ ረጅም የመንግሥትነት ታሪክ ያላት አገር ነች፡፡ ብዙዎቹ እንደሚስማሙበትና የታሪክ ድርሳናት እንደሚነግሩን የኢትዮጵያ የመንግሥትነት ታሪክ ከሦስት ሺህ ዓመታት በላይ ወደ ኋላ ይሳባል፡፡
አገራችን ‹‹ኢትዮጵያ›› የሚለውን የስያሜዋን ምክንያት በተመለከተ ሦስት አይነት ትውፊታዊ ግምቶች ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያው ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከግሪክኛ ቋንቋ የተወሰደና ትርጉሙም ፊቱን ፀሃይ ያቃጠለው (burned face) ማለት ነው ይላል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በቅዱስ መጽሐፍ በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሰውና ኢትዮጵያን ያቀና ነው ተብሎ የሚነገርለት የካም ልጅ ኩሽ (ዘፍ 10÷6) “ኢትዮጵስ” በሚባለው ሌላኛው ስሙ ምክንያት አገራችን ኢትዮጵያ ተብላ መጠራት እንደጀመረች ያትታል፡፡ ሦስተኛው በቅድመ ልደት ክርስቶስ በአገራችን ከነበሩ ነገሥታት መካከል አንዱ ’ኢትዮጵስ’ ይባል ስለነበር አገራችንም በኢትዮጵስ ኢትዮጵያ የሚለውን መጠሪያ አግኝታለች የሚለው ግምት ነው፡፡ የኔም የግል ምልከታዬ ወደዚህኛው ያጋደለ ነው ከነገስታት ማለትም ጥንታዊ እና በጣም ረዥም ትንሽም ሊያወዛግብ መረጃ ተጨማሪ ሊፈልግ የሚችል እውነታ ቢሆንም እዚህ ጋር ማየት እና ማስተዋል ያለብን ከዚህ በፊት ስለ መልከጼዴቅ እና ፫ቱ ( ሦስቱ ) ልጆቹ በተለይም #ኢትኤል ስለተባለው ኢትዮጵስ ዙርያ ባለው ታሪካዊ ማስረጃና መረጃ ላይ የተመረኮዘ ነው።
ያም ሆነ ይህ ’ኢትዮጵያ’ የሚለውን የአገራችን መጠሪያ ስም ከክርስቶስ ልደት ስምንት መቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ በጽሑፍ መዛግብት ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡
ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ለመጠቀም ጥንታውያን ግሪኮች የመጀመሪያዎቹ እንደሆኑ ይነገራል ለዚሁም ከክርስቶስ ልደት ስምንት መቶ ዓመታት በፊት የነበረው የታላቁ ባለቅኔ ሆሜር ኦልያድና ኦዲሴ የተባሉ ድርሰቶችና የታሪክ አባት ተብሎ የሚጠራው ከክርስቶስ ልደት አራት መቶ ዓመታት በፊት የነበረው የሄሮዶቱስ መጽሐፍ ዓይነተኛ ምስክሮች ናቸው፡፡ ከጥንት ግሪኮች በፊት ኢትዮጵያ በጥንት ግብፃውያን የኩሽ ምድር ተብላ ትጠራ እንደነበር የሚያመክቱ ማስረጃዎችም አሉ፡፡ አገራችን አቢሲኒያ: ምድረ ሀበሻ ወዘተ የሚባሉ ሌሎች መጠሪያዎችም እንደነበሯት ይታወቃል ሁሉም የራሱ ታሪክና ምክንያት ያለው ሲሆን ሰፋ ያለ ጥናታዊ ምርምር የሚሻ ነገር የመስለኛል፡፡
ኢትዮጵያ የሚለው ስም በቅዱስ መጽሐፍ ከአርባ ጊዜ በላይ ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ ለአብነት ያህል በእብራውያን (አይሁዶች) ዘንድ ቶራህ ተብሎ በሚታወቀው እና ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1400 ዓመተ ዓለም ገደማ እንደተጻፈ በሚታመነው በመጀመሪያው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ክፍል በኦሪት ዘፍጥረት ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች ቀድማ በሁለተኛነት ተጠቅሳለች (ዘፍጥረት 2÷13)፡፡
ኢትዮጵያ ከሚለው ጥንታዊ መጠሪያ ጋር የቀደምት ነዋሪዎቹ (የሕዝቦቹ ) ማንነት ጉዳይ ተያይዞ መነሳቱ የማይቀር ነው፡፡ በቁጥር ቀላል የማይባሉ ሰዎች ኢትዮጵያ ማለት በግሪክኛ ፊቱን ፀሃይ ያቃጠለው (burned face) ማለት ስለሆነ ቀደምት ነዋሪዎቹም ጥቁር (deep dark skin) ሕዝቦች ነበሩ ብለው ይገምታሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ተጨማሪ የታሪክ መዛግብትን በአስረጅነት በመጥቀስ ኢትዮጵያ ከመሠረቱ ጥቁሮችን ጨምሮ ስብጥር መልክ (mixed color) ሕዝቦች መኖሪያ ነበረች ይላሉ፡፡ ለምሳሌም በቅዱስ መጽሐፍ ነብዩ ኤርምያስ ‹‹ኢትዮጵያዊ መልኩን: ነበር ዝንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን›› (ኤር 13÷23) የሚለውን በመጥቀስ በንፅፅር የተነገረ የኢትዮጵያውያንን ሕብረ ቀለም (መልከ ብዙኀነት) የሚያመለክት ነው ይላሉ፡፡ ግሪካዊ ሆሜር በኦልያድ ቅኔው የኢትዮጵያ ሰዎች በውበት የተደነቁ ናቸው በማለት ገልጿቸዋል፡፡ የታሪክ አባት ሄሮዶቱስ ደግሞ በሦስተኛው መጽሐፍ ኢትዮጵያውያን ከሰዎች ሁሉ በውበትና በቁመት የሚበልጡ ኃያላን ናቸው ይላል፡፡ ከነዚህ እና ከመሳሰሉት ጥንታዊ መዛግብት በመነሳት አገራችን ‹‹ኢትዮጵያ›› የሚለውን ስያሜ ያገኘችው በዚያን ዘመን በነበረው መልከዓ ምድራዊ ክልል ይኖሩ የነበሩ የቀደምት የሕዝቦቿን ህብረ መልክዕ (ስብጥር የቆዳ ቀለም) መሠረት በማድረግ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ግምት አለ፡፡
ለዛሬ በዚሁ ይብቃና ነገ በቀጣይ ክፍል አጠቃላይ ስለ ወሰነ ክልል ( የግዛት ስፋት ) ምን ይመስል ነበር የሚለውን ይዤ እመለሳለው ።
ምንጭ እና ማጣቀሻ
📌 ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በመንግስቱ ጎበዜ
📌 መጽሐፍ ቅዱስ
ፍቅር አንድነትን ከጥንት ከመሰረቱ ከታሪካችን እንማር ፍቅር ያሸንፋል ጥላቻንም ያጠፋል!
♥ ኢትዮጵያ ሁን
♥ አፍሪካሁን
♥ ሰው ሁን
ይህ የካሌብ ጽሑፎች የቴሌግራም ድህረገጽ ነው!

ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ ቤተሰቦች ዛሬ ስለ #ኢትዮጵያ_እና_ኢትዮጵያዊነት በሚል አርዕስት የጀመርኩላችሁን ጥናታዊ ጽሑፍ ቀጣይ ክፍል ይዤ መጥቻለው እንደተለመደው በልዩ ትኩረትና ማስተዋል ይነበብ መልካም ቆይታ።
ክፍል ፪ ( ሁለት ) ወሰነ ክልል
የጥንቷን ኢትዮጵያ ወሰነ ክልል በተመለከተ ከዚህ እስከዚህ ድረስ ነበር ብሎ በትክክል ለመናገር አያስደፍርም፡፡ እንደ ጥንታዊ መዛግብቱ ከሆነ እጅግ ሰፊ የሆነና በተለያየ ዘመናት አንዴ ሲሰፋ ሌላ ጊዜ ጠበብ ሲል የነበረ ሆኖም ግን የዛሬዋን ኢትዮጵያ ማዕከል ያደረገ እንደነበር መረዳት አያዳግትም:: ከክርስቶስ ልደት በፊት 1400 ዓ.ም. ገደማ የተጻፈው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ (ኦሪት ዘፍጥረት) ከኤደን ገነት የሚመነጨው ሁለተኛው ወንዝ ጊዮን የኢትዮጵያን መሬት ይከባል በማለት የዛን ጊዜዋ ኢትዮጵያ መሠረቷ የአሁኗን ኢትዮጵያን ጭምር እንደሚያካትት ይጠቁማል (ዘፍ. 2÷1)::
በሌላ የብሉይ ኪዳን የዕብራውያን መጽሐፍ ‹‹አርጤክስ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ በ127 አገሮች ላይ ነገሠ (አስቴር 1÷1÷8÷9) በማለት መልክዓ ምድራዊ ፍንጭ ሰጥቷል:: ከክርስቶስ ልደት በፊት 687 ዓ.ዓ. ገደማ የነበረው ነብዩ ኢሳያስ ደግሞ ቲርሐቅ የተባለው ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ግብፅ ድረስ ያስተዳድር እንደነበረ ገልጿል (ኢሳ. 37 ÷9-11፣ 1ኛ ነገሥት 19:9)፡፡ የዚህ ጥቁሩ ፈርኦን በመባል የሚታወቀው ኢትዮጵያዊ ንጉስ በአርኪኦሎጂ ጥናትም የተረጋገጠ ሲሆን ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ690-664 ዓ.ዓ. ግብፅን ያስተዳድር አንደነበር ተመዝግቧል፡፡
የጥንት ግሪኮች ኢትዮጵያ ደግሞ ሰፊ መልከዓ ምድራዊ ግዛትን ያካለለ ሲሆን ከግብፅ በስተደቡብ ያለውን አጠቃላይ የምስራቅና የመካከለኛው አፍሪካ ክፍል ‹‹ኢትዮጵያ›› በማለት ይጠሩት ነበር፡፡ ሆሜር በድርሰቶቹ ኢትዮጵያ ትሮይንና የዓረቡን ምድር ትገዛ እንደነበር ገልጿል፡፡ ሄሮዱቱስ ስለኢትዮጵያ ሲያነሳ የአባይ ወንዝና ትልቁን ሐይቅ በማመልከት የመልከዓ ምድራዊ ጥቆማ ሰጥቷል፡፡ ፕሊኒ የተባለው ሌላው ግራካዊ ኢትዮጵያ በጥንቱ ዘመን ሃያልና ዝነኛ እንደነበረችና ሶሪያንና እስከ ሜድትራኒያን የባህር ዳርቻ ድረስ ትቆጣጠር እንደነበር ጽፏል፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት 60 ዓ.ዓ. ገደማ የነበረ ዲኦዶረስ ሲኩለስ የተባለ ጸሐፊ ደግሞ ኢትዮጵያ የግብፅ ትውፊትና ስልጣኔ መነሻ መሆኗንና ኢትዮጵያውያን እስከ ህንድ ውቅያኖስ ድረስ ያስተዳድሩ እንደነበር ገልጿል፡፡ በተመሳሳይ ዘመን የነበረ ትራቦ የተባለ ሌላኛው የግሪክ ጸሐፊ የኢትዮጵያ ግዛት ዓረብን ብቻ ሳይሆን እስከ አውሮፓ ድረስ እንደሚዘልቅ አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ የግዛት ክልል ቀይ ባህርን ተሻግሮ ደቡብ ዓረቢያ ድረስ ይዘልቅ እንደነበር የታዋቂዎቹ ኢትዮጵያውያን ነገሥታት የ4ኛው መቶ ክ/ዘመኑ ኢዛናና የ6ኛው መቶ ክ/ዘመኑ ካሌብ የመታሰቢያ ሃውልት ጽሑፎች አይነተኛና ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡ አስቀድሞ እንደተገለጸው ምንም እንኳ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ወሰነ ክልል በትክክል ለመናገር ባይቻልም ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ3ኛውና ከ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ጀምሮ ያሉ ማስረጃዎች የዚያን ጊዜዋ ኢትዮጵያ አክሱምን ማዕከል ያደረገና ከአሁኑ ኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይነት ያለው እንደነበር ያመለክታሉ፡፡
ለዛሬ በዚሁ አበቃሁ በቀጣይ ክፍል እስክመለስ መልካም ቆይታ 👐
• ኢትዮጵያዊነት ሳንፈልገው በግድ የተጫነብን ዕዳ ሳይሆን የተዋብንበት ጌጣችን፣ የከበርንበት

ኢትዮጵያዊነት ክብር እንጅ ውርደት ሽልማት እንጅ ቅጣት አይደለም❗️
🔔 ቻናሉን ለመ🀄️ላ🀄️ል 👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0
🔔 ቻናሉን ለመ🀄️ላ🀄️ል 👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0
ሰላም በያላችሁበት 🙌 እንደምን አላችሁ ቤተሰብ ? በቀጣይ.....
ክፍል ፫ ( ሦስት ) የጥንት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን መታወቂያዎች ምን ይመስል ነበር!?
...በሚል አርዕስት እንደምመለስ በተናገርኩት መሰረት መጥቻለው መልካም ንባብ🙏
የጥንቷ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በሌሎች ዘንድ የተከበሩ፣ የሚታፈሩ፣ የሚደነቁ፤ በእምነታቸው ቀናኢነት፣ በፍትሃዊነት፣ በደግነት፣ በትህትና እና በሌሎች መሰል መልካም ምግባራት የሚታወቁ እንደነበር የሚመሰክሩ በርካታ መዛግብት አሉ፡፡ ግሪካዊ ባለቅኔ ሆሜር ኢትዮጵያውያን በጠባይ ጭምቶችና ትህትናን የተሞሉ ናቸው በማለት ጽፏል፡፡ ሆሜር በማከልም ኢትዮጵያውያን በፍትሃዊነት እና እኩልነት የታወቁ በመሆናቸው አምላክ ከመኖርያው ከሰማይ ወርዶ ዘወትር እነርሱን ይጎበኝ ከእነርሱም ጋር በዓል ያደርግ ነበር ብሎ ገልጿል፡፡ በተመሳሳይ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረው የቢዛንታይኑ እስጢፋኖስ ኢትዮጵያውያን በፍህታዊነታቸው ምክንያት በአምላክ የተወደዱ ነበሩ በማለት ገልጿል፡፡ በመቀጠልም ይሕ ጸሐፊ ኢትዮጵያ በምድራችን መጀመሪያ የተመሠረተች አገር ነች፡፡ ኢትዮጵያውያንም አምልኮተ እግዚአብሔርን በማስተዋወቅና ህግን በመስራት በዓለም የመጀመሪያ ህዝቦች ናችው ብሏል፡፡
በቅዱስ መጽሐፍ ኢትዮጵያውያን በእምነታቸው የታወቁ በምግባራቸው የተደነቁ እንደነበሩና አገሪቱም ሀገረ እግዚአብሔር እንደሆነች በተደጋጋሚ ተገልጿል፡፡ መዝሙረኛው ንጉሥ ዳዊት ‹‹ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች›› (መዝ. 67 (68)÷31) በማለት የገለጸው አንዱ ማሳያ ነው፡፡ እስራኤላውያንን ከግብፅ የፈርኦኖች አገዛዝ ነፃ ያወጣቸውና ባህረ ኤርትራን ከፍሎ ያሻገራቸው ሙሴ ኢትዮጵያዊቷን ለጋብቻ መርጧል (ዘኁልቁ 12÷1)፡፡ ከኢትዮጵያዊ አማቱም ልዩ ልዩ ምክሮችን ይቀበል ነበር፡፡ በቤተመንግሥት ባለሟል የነበረው ኢትዮጵያዊ አቤሜሌክ ነብዩ ኤርምያስን ከጉድጓድ እንዲወጣ አድርጎ ከሞት አትርፎታል (ኤር. 38÷7¬-13)፡፡ በትንቢተ አሞፅም “የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁም” (አሞፅ 9÷7) በማለት በእግዚአብሔር ዘንድ ልቀው የተገኙ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ነብዩ ኢሳኢያስ ግብፅን ይገዛ የነበረው ቲርሐቅ የተባለው ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን ከአሦራውያን ጥፋት እንዳዳነ ጽፏል (ኢሳ. 137÷10-11)፡፡ ነብዩ ናሆም ኢትዮጵያና ግብፅ የነነዌ ጠንካራ ደጋፊዎች እንደነበሩ ገልጿል (ናሆም 3÷9)፡፡ የሰለሞንን ጥበብ ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዘችው ንግሥት ሳባ ‹‹አንተን የወደደ በእስራኤልም ዙፋን ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን›› (1ኛ ነገ.10÷25) በማለት እምነቷን ገልፃለች: ፈጣሪዋን አመስግናለች፡፡ በትንቢተ ሶፎንያስ ‹‹ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ የተበተኑት ሴት ልጆቼ ቁርባኔን ያመጡልኛል›› (ሶፎንያስ 3÷10) በሚል ተመዝግቧል፡፡ መዝሙረኛው ንጉሥ ዳዊት ኢትዮጵያውያንን የፅዮን ልጆች ብሎ ጠርቷቸዋል (መዝ 86(87) ÷ 4-5) ፡፡በዘመነ ሃዲስ የትንቢተ ኢሳኢያስን መጽሐፍ በማንበብ ላይ የነበረውን ኢትዮጵያዊውን የንግሥት ህንደኬ ባለሟል (ጃንደረባው) ሐዋርያው ፊሊጶስ የምታነበውን ታስተውለዋለህን ብሎ ሲጠይቀው የሚመራኝ (የሚነግረኝ) ሳይኖር ይህ እንዴት ይሆናል በማለት የመለሰው መልስ ፍፁም ትህትናውንና መንፈሳዊነቱን ይገልጻል (የሐዋ. ሥራ 8÷26-40) ፡፡
ስለነብዩ ሙሐመድ የህይወት ታሪክ በሚያወሳው ታላቁ የእስልምና የትውፊት መጽሐፍ ነብዩ ሙሐመድ በወገኖቻው በመካ ቋሪሾች ሲሳደዱ ለነበሩት ተከታዮቹ ‹‹ወደ አቢሲኒያ ብትሄዱ ማንንም የማያሳድድ ደግ ንጉሥ ታገኛላችሁ:: ይህ አገር የእውነተኞች ምድር በመሆኑ እግዚአብሔር ከመከራችሁ ያሳርፋችኋል›› በማለት ወደ ኢትዮጵያ እንደላካቸው ተዘግቧል፡፡ በወቅቱ የነበረው ክርስቲያኑ የኢትዮጵያ ንጉሥም ከየት መጣችሁ፣ እነማን ናችሁ፣ እምነታችሁ ምንድን ነው ሳይል በክብር ተቀብሎ ማረፊያ በመስጠት ክፉውን ቀን እንዲያሳልፉ አድርጓቸዋል፡፡ ከዚያ ቀደም ብሎ ከልዩ ልዩ የግሪክና የሮማ ግዛት በሃይማኖታቸው ምክንያት የተሰደዱ ክርስቲያን መነኮሳት ኢትዮጵያ መጠጊያ እንደሆነቻቸውና እነርሱም በምድረ ኢትዮጵያ ገዳማትን በማስፋፋትና መጽሐፍትን በመተርጎም ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ እንደነዚህ ታሪኮች ከሆነ ኢትዮጵያ እምነት፣ ቀለምና ዘር ሳትለይ የስደተኞችን መብት በማክበር በዓለማችን ቀዳሚዋ አገር ሳያደርጋት አይቀርም፡፡
በርካታ ጥንታዊ መዛግብት ኢትዮጵያ ሃያል አገርና በልዩ ልዩ ማዕድናት የበለፀገች ምድር እንደነበረች ይገልፃሉ፡፡ ግሪካዊ ባለቅኔ ሆሜር ኢትዮጵያውያን በጉልበት ሃያላን ነበሩ በማለት ጽፏል፡፡ ሄሮዶቱስ ደግሞ የአባይ ወንዝ የሚመነጭበት፣ የወርቅ ማዕድን በብዛት የሚገኝበት ትልልቅ ዝሆኖች ያሏት እና የተለያዩ ዓይነት ዛፎች (ዕፅዋቶች) የሚበቅሉባት አገር እንደሆነች መዝግቧል፡፡ ዴኦዶሮስ የተባለው ጸሐፊ ደግሞ ኢትዮጵያ ሀብታም፣ በወርቅ ማዕድን የበለፀገች፣ ጠንካራ አስተዳደር ያላት፣ በጠንካራ ነገሥታትና በህግ የምትመራ አገር እንደነበረች ገልጿል፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ዛራህ የተባለ ኢትዮጵያዊ የጦር መሪ በሚሊዮን የሚቆጠር ሰራዊት ይመራ እንደነበር ተገልጿል (2ኛ ዜና 14÷9)፡፡ የሳባ ንግሥት ለጠቢቡ ንጉሥ ሰለሞን በርካታ የከበሩ ማዕድናትን በስጦታ ማበርከቷ ተጽፏል (1ኛ ነገሥት 10÷1-13)፡፡ በነብዩ ኢዮብ ደግሞ ኢትዮጵያ ከጥበብ ጋር የተነፃፀረ ቶጳዝዮን የተባለ የከበረ ማዕድን መገኛ እንደሆነች ተጠቁሟል (ኢዮብ 28÷9)::
ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረው ማኒ የተባለው ጸሐፊ አክሱምን ማዕከል ያደረገው የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም ኃያላን መንግሥታት መካከል በሦስተኛ ደረጃ አስቀምጧታል (መንግሥታቱም ሮም፣ ፐርሺያ፣ አክሱምና ቻይና ነበሩ)፡፡ የቢዛንታይኑ ንጉሥ ኮንስታንቶስ 2ኛ (ነገሠ እ.ኤ.አ 335-336 ዓ.ም) ኢትዮጵያን ከጎኑ ለማሰለፍ የዲፕሎማቲክ መልዕክት በመላክ ጥረት አድርጓል፡፡ ሌላኛው የቢዛንታይን ንጉሥ ጁሰቲን ቀዳማዊ (ነገሠ እ.ኤ.አ 518-526 ዓ.ም) በደቡብ ዓረቢያ የሚገኙ ክርስቲያኖችን ከአይሁድ መከራ እንዲታደጋቸው ለኢትዮጵያዊ ንጉሥ አፄ ካሌብ ተማፅኖ ማቅረቡ ይታወቃል፡፡ አፄ ካሌብም ባደረገው ዘመቻ ክርስቲያኖችን ነፃ አውጥቷል፡፡ ተከታዩ የቢዛንታይን ንጉሥ ታዋቂው ጁስቲንያን (ነገሠ እ.ኤ.አ 526-565 ዓ.ም) ደግሞ ከፐርሺያ ጋር ሊያካሂድ ላሰበው ጦርነት የኢትዮጵያን ድጋፍ ለማግኘት የዲፕሎማቲክ መልዕክተኞቹ መላኩ ታውቋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ማሳያዎች አገራችን ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለሌሎች ሕዝቦችና አገሮች ደህንነትና ነፃነት ታደርግ የነበረውን ድጋፍና በወቅቱ የነበራትን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት፣ ክብርና ሚና የሚያመለክቱ ናቸው፡፡
በጥንቱ የታሪክ ዘመን ስለነበረው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ብዙ ነገር ለማንሳት ቢቻልም አንባቢን ላለማሰልቸት ይህንን ጥናታዊ ጽሑፍ በመጨረሻና ማጠቃለያው ክፍል በሆነው ክፍል ፬ ( አራት ) የሚጠናቀቅ ይሆናል አብራችሁኝ ስለነበራችሁ እያመሰገንኩ ለዛሬ በዚሁ አበቃሁ ፡፡

በ #ኢትዮጵያ_እና_ኢትዮጵያዊነት አርዕስት ሳቀርብላችሁ የነበረው ጥናታዊ ጽሑፍ የመጨረሻው ክፍል በሆነው የማጠቃለያ ክፍል የማደርሳችሁ ይሆናል በቀጣይ በልዩ ጥናታዊ ጽሑፎችና የተለያዩ የምርምር ጽሑፎችን ይዤ የምመለስ ይሆናል ፈጣሪ ሐገራችንን ይጠብቅልን።
ይህ የካሌብ ጽሑፎች የቴሌግራም ድህረገጽ ነው።
💚 @TheHabesha0 💚
💛 @TheHabesha0 💛
❤️ @TheHabesha0 ❤️
ይህ የካሌብ ጽሑፎች የቴሌግራም ድህረገጽ ነው።
💚 @TheHabesha0 💚
💛 @TheHabesha0 💛
❤️ @TheHabesha0 ❤️
ክፍል ፫ ( ሦስት ) የማጠቃለያና የመጨረሻው ክፍል
አስቀድሞ ከቀረበው ጽሑፍ መረዳት እንደሚቻለው የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ምሥረታ በጥቂት ጎሳዎች፣ በውስን የቦታ ክልል፣ በጥቂት ቋንቋ ተናጋሪዎች ወዘተ የተወሰነ አልነበረም፡፡ ከታሪክ እንደምንማረው የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የመሠረት ድንጋይ ለማስቀመጥ ዘር፣ ቋንቋ፣ ጎሳ፣ ቀለም፣ የተወሰነ የቦታ ክልል በመስፈርትነት አልተቀመጠም፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሁሉም የአገራችን ሕዝቦች መኖሪያና ማንነት እንጅ ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ መስጠት ያልተጻፈ ማንበብ ብቻ ሳይሆን ራስን የመግደል/ አጥፍቶ የመጥፋት/ ወንጀል መፈጸም ነው፡፡ በዘመናችን የሚገኙ አንድ አንድ ጎሰኞች ወደኋላም ወደፊትም መሄድ የማይችሉ የአእምሮ ህሙማን በመሆናቸው ዛሬ የሆነ ነገር ላይ ተቸክለው ከትናንት የማይማሩ ለነገ ደግሞ የማይኖሩ ናቸውና ሊታዘንላቸው ይገባል፡፡ እነዚህ ሰዎች ትናንትን ስለማያውቁ መሰረት የላቸውም ነገንም እንዳያዩ ራእይ አልባ ናቸው፡፡
የጥንቱ ዘመን ኢትዮጵያ ግዛት አልፎ አልፎም ቢሆን በስተሰሜን እስከ ግብፅ ድረስ፣ ቀይ ባህርን ተሻግሮ እስከ ደቡብ አረቢያ እንዲሁም በርካታ የምስራቅ አፍሪካ አካባቢዎችን ያካትት እንደነበረ የታሪክ መዛግብት ይመሰክራሉ፡፡ በአንፃሩ በዘመኑ የምንገኝ ሰዎች የዛሬዋን ኢትዮጵያ እንደ ገና ዳቦ ሸንሽነን ሸንሽነን /በሃሳብም ቢሆን/ የት ልናደርሳት እንደሆነ አይታወቅም፡፡ የቀድሞዋ ኢትዮጵያ የስደተኞች መጠጊያ፣ የደካሞች ምርኩዝ፣ የችግረኞች ተስፋ፣ የፍትህ ማዕከል፣ የእውነተኞች ምድር እንዳልነበረች፣ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ደግሞ ልጆቿ መጠጊያ የሌላቸው ስደተኞች፣ ርዳታ የሚለምኑ ርሃብተኞች፣ የሌሎችን ድጋፍ የሚሹ ደካሞች፣ በፍትህ እጦት የሚሰቃዩ ምስኪኖች ሆነዋል፡፡
በጥንቱ ዘመን ምድቧ ከኃያላን መንግሥታት ጋር ሆኖ በማንነቷ ታፍራና ተከብራ የዓለም ቁንጮ የነበረችው አገር ዛሬ በማናቸውም መስፈርት የዓለም ግርጌ ላይ ተቀምጣ ልጆቿ አንገታቸውን ሲደፉ በየሄዱበት ሲገፉ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ እርስ በርሷ የምትለያይ መንግሥት ትጠፋለች እንደተባለው: ለዚህ ሁሉ ውርደትና መከራ ካበቁን ነገሮቸ አንዱና ዋነኛው ከአብሮነት ልዩነትን፣ ከመተባበር መነቃቀፍን፣ ከአንድነት መነጣጠልን፣ ከኢትዮጵያዊነት ጎሰኝነትን፣ ከቅንነት ምቀኝነትን፣ ከመደጋገፍ መጠላለፍን መምረጣችን ነው፡፡ አሁንም ከታሪክና ከሌሎች የማንማርና በዚሁ የምንቀጥል ከሆነ አወዳደቃችን የከፋ እንዳይሆን ያስፈራል፡፡ ስለሆነም የአብሮነታችንን ጥንታዊ መሠረት እንወቅ፣ የጎሰኝነት ድሪቷችን እናውልቅ፣ ኢትዮጵያዊ አንድነታችን እናጥብቅ፡፡
በመሠረቱ መታወቅ የሚገባው:-
• ኢትዮጵያዊነት ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋ እንጅ ለድርድር የሚቀርብ የሸቀጥ ዕቃ አይደለም፡፡
• ኢትዮጵያዊነት የደም ማተባችን እንጅ ሲያሻን የምናጠልቀው ሳንፈልግ የምናወልቀው
አርቴፊሻል ጌጥ አይደለም፡፡
• ኢትዮጵያዊነት ሳንፈልገው በግድ የተጫነብን ዕዳ ሳይሆን የተዋብንበት ጌጣችን፣ የከበርንበት
ዘውዳችን፣ የወረስነው ቅርሳችን ነው፡፡
• ኢትዮጵያዊነት ክብር እንጅ ውርደት ሽልማት እንጅ ቅጣት አይደለም፡፡
• ኢትዮጵያዊነት አንድነት በብዙኀነት ብዙኀነት በአንድነት የሚመሰጠርበት የህብር ቅኔ፣
በጎሰኞች የማይፈታ ሰምና ወርቅ ነው፡፡
• ኢትዮጵያዊነት የማይነቃነቅ ፅኑ መሠረት፣ ዘመን የማሽረው ማንነት፣ የማይቋረጥ ጅረት ነው፡፡
• ኢትዮጵያዊነት ዘመንን ከዘመን ትውልድን ከትውልድ የሚያገናኝ ህያው ድልድይ ነው፡፡
• ኢትዮጵያዊነት በጎሰኞች ጫጫታ የማይፈርስ በደም የተገነባ የመስዋዕትነት ታሪካችን ነው፡፡
• ኢትዮጵያዊነት በወጀብና አውሎ ነፋስ የሚፈርስ የድቡሽት ቤት ሳሆን በፅኑ መሠረት ላይ
የተጣለ የአብሮነት ሃውልት ነው፡፡

#የካሌብ_ጽሑፎች ✍ | በድጋሚ የተለጠፈ |
«ኢትዮጵያ በላይ ዘለቀ፣ አፄ ቴዎድሮስ፣ አፄ ሚኒሊክ እያሉ በማላዘን ሀገር ልትቀጥል አትችልም፣ እቅጩን ማወቅ አለብን፣ እኛ ዛሬ ስራ መስራት አለብን፣ ከሞተው በላይ ዘለቀ ይልቅ ካለው ጎጃሜ ጋር ተግባባ፣ ካለፉት አፄ ሚኒሊክ ይልቅ ዛሬ ካሉት ከሸዋ አማራ ሰው ጋር ተቀራረብ፣ ከሞቱት ይልቅ ካሉት ጋር እንኑር፣ ኢትዮጵያኖች የሞተ ማድነቅ ይወዳሉ፣ ስለሚወዱት አይደለም የቆመውን ለማበሳጨት ነው።»
🗣መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ
━━━━━━━━━━━━
♥ ኢትዮጵያ ሁን
♥ አፍሪካሁን
♥ ሰው ሁን
📣ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
«ኢትዮጵያ በላይ ዘለቀ፣ አፄ ቴዎድሮስ፣ አፄ ሚኒሊክ እያሉ በማላዘን ሀገር ልትቀጥል አትችልም፣ እቅጩን ማወቅ አለብን፣ እኛ ዛሬ ስራ መስራት አለብን፣ ከሞተው በላይ ዘለቀ ይልቅ ካለው ጎጃሜ ጋር ተግባባ፣ ካለፉት አፄ ሚኒሊክ ይልቅ ዛሬ ካሉት ከሸዋ አማራ ሰው ጋር ተቀራረብ፣ ከሞቱት ይልቅ ካሉት ጋር እንኑር፣ ኢትዮጵያኖች የሞተ ማድነቅ ይወዳሉ፣ ስለሚወዱት አይደለም የቆመውን ለማበሳጨት ነው።»
🗣መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ
━━━━━━━━━━━━
♥ ኢትዮጵያ ሁን
♥ አፍሪካሁን
♥ ሰው ሁን
📣ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
የካሌብ ጽሑፎች
Photo
ሰላም🙌 እንደምን አላችሁ ውድ የካሌብ ጽሑፎች ድህረገፅ ቤተሰቦች ዛሬ በአንዲት አጠር ያለች አስተማሪና አስገራሚ ጦማር ተመልሻለው! መልካም ንባብ...
.....የ15 ዓመቷ አና ፍራንክ በምስጢራዊው ቤት ውስጥ ከሞት ተደብቃ እያለች ስለ ትዕግስት፣ ግብረ-ገብነት፣ አመለካከትና ፅናት እንድህ ትለናለች:
“ወረቀት ከሰዎች ይበልጥ ትዕግስተኛ ነው።” ለወረቀት ችግርህን ደስታህን ሀዘንህን ጭንቀትህን ለሰው የማትነግረው ሚስጥርህን ልታጫውተው ልትነግረው ትችላለህ። ይሰማሃል አይሰለችህም አያፌዝብህም፤ ፊቱን አያዞርብህም የፈለከውን ያህል በርካታ ሀሳብህን አብዝተህ ብትገልፅለት በትዕግስት ያደምጥሃል ይቀበልሀል።
ትልልቅ ሰዎች ሰለሁሉም ነገር የራሳቸው የሆነ የገነቡት አመለካከት አላቸው (አመለካከታቸው ትክክል ይሁን አይሁን ሌላ ጥያቄ ነው) እናም አንድ ነገር ከመወሰናቸው ወይም ከማድረጋቸው በፊት አይወዛገቡም አይጨነቁም፡፡
ለኛ ለወጣቶቹ ግን ሚዛናችንን ጠብቀን የራሳችን የሆነ አመለካከት ይዘን ለመቆየት ችግሩ እጥፍ ድርብ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ "ግብረ-ገብ" የሚባሉት ነገሮች ሁሉ እየተንኮታኮቱና እየተደረመሱ ባለበት በዚህ በዘቀጠ ጊዜ፡፡ አዎ አሁን ባለንበት ዘመን ትልቁ ችግር ግበረ-ገቦች፣ ጥሩ አመለካከቶች፣ ብሩህ ራዕዮች፣ የሚያማልሉ ተስፋዎች... ወዘተ ሁሉ ከውልደታችን ጀምሮ አብረውን በውስጣችን ሲያድጉ ይቆዩና በመጨረሻው ግን መሃል መንገዳችን ላይ እንደግዙፍ ሀውልት ተገትሮ ከሚጠብቀን አፀያፊ እውነታ ጋር መላተምና እንደመስታወት ተንኮታኩቶ መርገፍ ነው፡፡
ትክክል ናቸው፣ ጥሩ ናቸው፣ ተገቢ ናቸው፣ ላከብራቸው ይገባኛል ብየ የማምንባቸው ነገሮች ሁሉ እንደት እስከዛሬ ከአዕምሮየ አውጥቼ እንዳልጣልኳቸው በእውነቱ የሚገርም ነው፡፡ ምክነያቱም ካለው እውነታ አንፃር ሲታዩ የእብድ ወይም የጅል አመለካከቶች የሚመስሉና ይዞ ለመቆየት እጅግ የሚያዳግቱ ናቸው፡፡
ያም ሆኖ አሁንም እንደያዝኳቸው ነው ያለሁት፤ እንደያዝኳቸው እንደምቆይም እርግጠኛ ነኝ፡፡ ምክነያቱም «የሆነው ሁሉ እንዳለ ሆኖ አሁንም ቢሆን ሰዎች ከስር መሰረታቸው (በተፈጥሮ) ጥሩወች ናቸው ብዬ አምናለሁ።»

ለመላው የክርስትና እምነት አማኞች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ።
መልካም በዓል !
💚 @TheHabesha0 💚
💛 @TheHabesha0 💛
❤️ @TheHabesha0 ❤️
መልካም በዓል !
💚 @TheHabesha0 💚
💛 @TheHabesha0 💛
❤️ @TheHabesha0 ❤️
ሰላም እንደምን አላችሁ? ውድ የካሌብ ጽሑፍ ቤተሰቦች ዛሬ ደግሞ #ቃላቶቻችንና_ተውሷቸውን እስኪ እንወቅ !!
የኛ የመሰሉን ለኛ ባዕድ ቃላትና ትክክለኛ አማርኛ ፍቻቸው።
1. ኮሌጅ------ መካነ ትምህርት
2. ዩኒቨርስቲ------መካነአእምሮ
3. ሌክቸር .......ትምህርተ ጉባኤ
4. ሌክተቸረር.........መምህረ ጉባኤ
5. ዲን —--- ሊቀ ጉባኤ
7. ቢሮ........ መስሪያ ቤት
8. ባንክ..... ቤተ ንዋይ
9. ሲቪል ሰርቪስ...... ሰላማዊ አገልግሎት
10. Custom ...... ኬላ
11. ኮምፒተር...... መቀመሪያ
12. ዲግሪ..... ማዕረግ
13. ሚኒስተር..... ምሉክ
14. ማስ ሚዲያ..... ምህዋረ ዜና
15. ፎቶ ግራፍ ..... ብርሃናዊ ስዕል
16. ራዲዮ.... ንፋሰ ድምፅ
17. ፖሊስ ...... የህግ ዘበኛ
18. ኢንተርኔት.... የህዋ አውታር
19. ሎሬት.... አምበል፣ ተሸላሚ የቅኔ
20. ዶክተር ..... ሊቀ ሙህር
21. ኢምባሲ ..... የእንደራሲ ፅ/ቤት
22. ዲፕሎማት ..... የመንግስት መልክተኞች
23. ኢኮኖሚክስ... ስነ ብዕል
24. ሀዋላ...... ምህዋረ ንዋይ
25. ሳሎን ..... እንግዳ መቀበያ
26. ቱሪዝም..... ስነ ህዋፄ
27. ስካን... ምክታብ
28. ፕሬዝዳንት.... ሊቀ ሀገር/ ሙሴ
29. ቴሌኮሚኒኬሽን.... ምህዋረ ቃል
30. ቪዛ ..... የይለፍ ፍቃድ
31. ፓስፖርት..... የኬላ ማለፊያ
ካሌብ ነበርኩ መልካም 🌆 ምሽት ።
ይቀጥላል.....
━━━━━━━━━━━━
♥ ኢትዮጵያ ሁን
♥ አፍሪካሁን
♥ ሰው ሁን
📣ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
የኛ የመሰሉን ለኛ ባዕድ ቃላትና ትክክለኛ አማርኛ ፍቻቸው።
1. ኮሌጅ------ መካነ ትምህርት
2. ዩኒቨርስቲ------መካነአእምሮ
3. ሌክቸር .......ትምህርተ ጉባኤ
4. ሌክተቸረር.........መምህረ ጉባኤ
5. ዲን —--- ሊቀ ጉባኤ
7. ቢሮ........ መስሪያ ቤት
8. ባንክ..... ቤተ ንዋይ
9. ሲቪል ሰርቪስ...... ሰላማዊ አገልግሎት
10. Custom ...... ኬላ
11. ኮምፒተር...... መቀመሪያ
12. ዲግሪ..... ማዕረግ
13. ሚኒስተር..... ምሉክ
14. ማስ ሚዲያ..... ምህዋረ ዜና
15. ፎቶ ግራፍ ..... ብርሃናዊ ስዕል
16. ራዲዮ.... ንፋሰ ድምፅ
17. ፖሊስ ...... የህግ ዘበኛ
18. ኢንተርኔት.... የህዋ አውታር
19. ሎሬት.... አምበል፣ ተሸላሚ የቅኔ
20. ዶክተር ..... ሊቀ ሙህር
21. ኢምባሲ ..... የእንደራሲ ፅ/ቤት
22. ዲፕሎማት ..... የመንግስት መልክተኞች
23. ኢኮኖሚክስ... ስነ ብዕል
24. ሀዋላ...... ምህዋረ ንዋይ
25. ሳሎን ..... እንግዳ መቀበያ
26. ቱሪዝም..... ስነ ህዋፄ
27. ስካን... ምክታብ
28. ፕሬዝዳንት.... ሊቀ ሀገር/ ሙሴ
29. ቴሌኮሚኒኬሽን.... ምህዋረ ቃል
30. ቪዛ ..... የይለፍ ፍቃድ
31. ፓስፖርት..... የኬላ ማለፊያ
ካሌብ ነበርኩ መልካም 🌆 ምሽት ።
ይቀጥላል.....
━━━━━━━━━━━━
♥ ኢትዮጵያ ሁን
♥ አፍሪካሁን
♥ ሰው ሁን
📣ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
"ለመኖር ብላ እንጂ ለመብላት አትኑር" የሚል መፈክር የሚመስል ሀሳብ (አቋም?) የሚያራምዱ ሰዎች አጋጥመውኝ፣ "እና ለምንድነው የምትኖሩት?" ብዬ ጠይቄአቸው አላውቅም ነበር። አሁን ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሜ ልጠይቃችሁ፣ ለመኖር ትበላላችሁ፤ ለምንድነው የምትኖሩት? እ??????
ምንጭ;- እዚህ ቤት #BamU
🔊 ይህንን ድህረ-ገጽ ለመቀላቀል👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
ምንጭ;- እዚህ ቤት #BamU
🔊 ይህንን ድህረ-ገጽ ለመቀላቀል👇
@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
#ሞክሼ...❓❓
ከ መጽሐፈ ምንኃር
🖊በተለምዶ የዘወትር የጽሑፍ ተግባራችን ሞክሼ እያልን የምንጠቀምባቸው ሆሄያት በዓይነት አራት በዝርዝር ደግሞ ዘጠኝ ናቸው ።በተለምዶ "ሞክሼ" ይባሉ እንጂ ሞክሼ የሚባል ትርፍ ፊደል የለም ።ፊደላቱ በሥነ ጽምፅ ትምህርት መካነ ፍጥረታቸው ባሕርየ ፍጥረታቸው መካነ ሙጻአቸው ቀመራቸው መልክዐ ፊደላቸው የየራሳቸው ነው ።በዚህም ምክንያት ሞክሼ ተብለው መጠራት አይችሉም ።እነዚህን ፊደላት ጠንቅቀው የሚጽፉ ጸሐፍት ጥቂት ቢኖሩም እናታቸውን ወይም መገኛ ግሣቸውን የሚያውቁ ግን መኖራቸው ያጠራጥራል ።ሳያውቁ በስሕተት እጃቸው እንዳመጣ የሚጽፉ ደግሞ አያሌ ናቸው።
🖊በአጠቃላይ ሞክሼ በመባል የሚታወቁት ፊደላት ትርፎች ሳይሆኑ ቀዋምያን ፊደላት መሆናቸውን ልናስተውለው ይገባል ።ፊደላቱ ራሳቸውን ችለው ትርጉም የሚያስተላልፉ የየራሳቸው ምሥጢርና ቀመር ያላቸው ናቸው ።ለምሳሌ በምሥጢር በኩል ያየናቸው እንደሆነ ንጉሡን "ሠ" ተጠቅመን "ሠረቀ" ብለን ብንጽፍ ወጣ የሚለውን ቃል ያስገኝልናል ።"ሰረቀ" ብለን በእሳቱ "ሰ " ብንጠቀም ደግሞ ሌባ ሽፍታ ቀማኛ የሚለውን ትርጉም ያስገኛል ። <<ሠዐለ>> ሳለ ለሥዕል ሲሆን <<ሰአለ>> ስንል ደግሞ ለመነ የሚል ፍቺ ይዞ ምልጃን ያመላክታል ። <<ሰዐለ>> ሳለ የጉንፋን ነው ።እነዚህ ኹለት ፊደላት ያለ ቦታቸው ከገቡ ቋንቋውን ብላሽ ምሥጢሩንም ፈራሽ ያደርጉታል ማለት ነው ።
🖊ሌላ ምሳሌ እንጨምር "ሀብት " የሚለውን ቃል በብዙኀኑ "ኀ" ብንጽፈው "የወይን ጭማቂ " የሚል ትርጉም ይሰጣል ።በሐመሩ "ሐ" ተጠቅመን ብንጽፈው ደግሞ ማመንዘር ይሆናል ።በሃሌታው "ሀ" ተጠቅመን ብንጽፈው "ንብረት " ማለት ይሆናል ።
📖ስለዚህ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚመጥን ይህ ታላቅ ቋንቋ አማርኛ ከላይ ከመፈጠሪያ ምንጩ ከግዕዝ ጨምሮ ልዩ ነው ። በብዙ ተመራማሪ ምሁራን ብዙ የተባለለት ወደፊትም ብዙ የማናውቀውን ያልገባንና የተሰወረብንን ቀመር እንደሚገልፅልን እሙን ነው። በተለይ የግዕዝ ቋንቋ ሰፊ ምርምርንና ሁለንተናዊ እውቀትን ይፈልጋል።
📚 መጽሐፉን ያላነበባችሁ እንድታነቡት እየጋበዝኩ ለተሻለ ህይወት ለተሻለ ኑሮ ሁሌም መማር ካለን ካወቅነው ላይ መጨመር መልካም ነው። ራሴው ካሌብ ነበርኩ የነገ ሰው ይበለን ።
#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው✍
━━━━━━━━━━━━
📣 የቴሌግራም ድህረገጻችንን ላልተ🀄️ላ🀄️ላችሁ ከታች ያስቀመጥኩላችሁን ሰማያዊ መስፈንጠሪያ /Link በመጫን ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ👇 ለሌሎችም በቅንነት ያጋሩ!