Telegram Web
ሰላም እንዴት አመሻችሁ ውድ #የካሌብ_ጽሑፍ_ቤተሰቦች ? ዛሬ በጣም እጥር ምጥን ባለች ጦማር መጥቻለው። ብዙ ማንበብ ለሚሰለቻችሁ ነው ይሄኛው ዙር 😁

መልካም ንባብ... 🤗

በአንድ ወቅት አንድ ሰው ሳይኮአናሊስስ ጆርጅ በርናርድ ሾውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ "ከዚህ ሁሉ እድሜ በኋላ ያንተ የህይወት ፍልስፍና ምንድን ነው?"


ጆርጅም መለሰ፡-

`` በሕይወቴ ውስጥ የእኔ ፍልስፍና በጣም ቀላል ነው። እነሱ ከሚፈቅዱት በላይ ወደ ሰዎች አልቀርብም፤ ሰዎችም ከሚገባቸው በላይ እንዲቀርቡኝ አልፈቅድም..!።

ምን ያክሎቻችን ሰዎችን ወደኛ ማቅረብ
ከነበረብን በላይ በማቅረባችን ምክንያት ብዙ ዋጋ ከፈልን ? አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በተቃራኒው ሰዎችን ከሚፈልጉት በላይ በመቅረብ በማወቅም ሆነ ባለማወቅም ፈተና ሆንባቸው። እና በአጭሩ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው ✔️ ር ቀ ታ ች ን ን እንጠብቅ ለማለት ነው ።

ዛሬም ራሴው ( @KalebAdane777 ) ✍️ ነበርኩ የነገ ሰው ይበለን ደና እደሩልኝ !
━━━━━━━━━━━━
📣 ድህረገጻችንን ላልተ🀄️🀄️ላችሁ ይህንን በመጫን ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ👇

@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
👍4🙏2👏1
March 8 በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች ቀን ተሰጥቶት እንዲከበር የተደረገው ለምንድን ነው? ምንስ ከጀርባው አለ ? ከእኛ ከነፃነት ምድር ከባለታሪኮቹና ከአማኞቹ ምድር ያለው የተገፋ ድምጽና ዕይታዎችስ ምን ይመስላሉ? የኢትዮጵያውያን ሴቶችስ ምን ይመስሉ ነበር?

የሚሉትን አጠቃላይ ሃሳቦች በዚሁ #በካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ  እንድናቀርብላችሁ ከፈለጋችሁ 👍 በማድረግ ሃሳባችሁን ግለፁልኝ። ሌላ ብዙ ማተኮር ያለብን ነገሮች አሉ ከዚህ የበለጠ የምትሉም በመንካት ሃሳባችሁን ግለፁልን።

በሌላ በማንኛውም ነገር ዙርያ እንዲቀርብላችሁ የምትፈልጉት ሃሳብና አስተያየቶችንም በ @kalebAdane777 ላይ በውስጥ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።
#ሴት_ኢትዮጵያዊያንን_በአርበኝነት 👆 ማንነት ታሪካቸው ተፈጥሮአዊ ጸጋን ከአማናዊው አምላካቸው ብቻ የተቸራቸው ናቸውና በልጃቸው ስም ላይ እንኳን ለመጠሪያነት ለምን ስሜ ካልሆነ ብለው ታሪክን ፣ተፈጥሮን ፣ ሐይማኖታዊ እሳቤን ከመናድ ይልቅ እውነተኛ ተፈጥሮአዊ ማንነትና እኩልነታቸውን አጣጥመው ያወቁ ብልሆችም ናቸው።  ባለማወቅ በዘመናዊው ባርነት ጠልፈው  እንዳይጠመዱን የአባት እናቶችሽ ጥንታዊ ታሪካቸው ይጮሃል ይጣራል ስሚ🗣።   #ህንደኬ ሆይ የት ነሽ? ሳባ እናቴ ሆይ ተነሺ መስክሪ ጣይቱ እመቤቲቱ እናቲቱ ሆይ ተነሺና ምሪው ይህንን ግራዘመም ትውልድ   ! በፍቅራችን መሃል በእውነታችን መሃል ልዩነትን ምን አመጣው? ታሪክ ከሰጠን ድንቅ ነገር መሃል ይሄ አንዱ የኩራት ታሪካችን ነው።  ዛሬ ክፍል አንድን እጀምርላችኋለው ...... መልካም 🌆 ምሽት።

@TheHabesha0 🤏 Join
የካሌብ ጽሑፎች:
ውድ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊያት! የእናቴ ልጆች እንደምን አመሻችሁ? በድምፃችሁ መሰረት በአለምአቀፍ ደረጃ እየተከበረ ስላለው የሴቶች ቀን ክፍል አንድ ይዤላችሁ መጥቻለው።

#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው

እባካችሁን❗️ ረዘም ቢልባችሁም በትዕግስት ጊዜ ሰጥታችሁ ለማንበብ ሞክሩ ---መልካም ንባብ።

በፈረንጆቹ March 8 ቀን ሲመጣ፣ "የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን" በሚል ስያሜ፣ በየማዕዘኑ ድምጾች ይሰማሉ። በዓሉ ለሴቶች መብት መከበርና እኩልነት መረጋገጥ የሚውል እንደሆነም ሽፋን ባለው መልኩ ይነገራል። ነገር ግን ይህ በዓል ከእኛ ባህልና ታሪክ ጋር ምን ያገናኘዋል? በመጀመሪያ ዓለማቀፋዊ በዓል ማለትስ ምንድን ነው?  ይህንንስ ቀን ካላከበራችሁ የሚል አዋጅ ከየት መጣ? የሚሉ ብዙ ብዙ ጥያቄዎችን አይፈጥሩባችሁም? ለእነዚህ ጥያቄ Google ስታደርጉ የምታገኟቸው መልሶችን እዚህ በስፋት በማምጣት አንባቢን ማድከም አልፈልግም። 
እኔ ትክክለኛው የእኛ የኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ማንነታችን ላይ ተመርኩዤ ለማቅረብ እሞክራለው!

ይህ በዓል፣ ከምዕራባውያን አገራት የመጣ፣ በብዙ የምርምር ጋዜጠኞችና ተመራማሪዎች ዘንድ በብዙ ጥያቄዎችና ጥርጣሬዎችም የታጀበ ነው። ለዛሬ ወደያዝኩት መረጃና መልእክት አዘል ጦማር ከልብ አስተውላችሁ እንድትከታተሉኝ አደራ እያልኩ እመራችኋለው ተከተሉኝ...

እነዚህ ማኅበራት ማለትም #ኢሉሚናቲ #illuminates ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ ፣ በዓለም ላይ የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸም የሚጥሩ፣ በሰው ልጆች አእምሮ ውስጥ የራሳቸውን እምነት ለመትከል የሚጥሩ ናቸው።

ታዲያ ይሄንን ስል አይ #ኢትዮጵያ በቃ ሁሉን ነገር ከኢሉሚናቲ ጋር ማያያዝ ? አይ አለማወቅ አይ ኋላ ቀርነት የምትሉም እህት ወንድሞቼ ትኖራላችሁ ለናንተ ስለዚህ ማህበር በደንብ ገና ብዙ ስለምሰራና ሌሎች በነሱ ዙሪያ የሚሰሩም ብዙ ጀግና ሰዎችን እግዚአብሔር ስላስነሳ ቅዱስ መጽሐፍም ምን እንደሚል መለስ ብላችሁ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ተመራመሩ አንብቡ።

እኛ፣ እልፍ ታሪክና እልፍ በዓላት ያሏት ሀገር ላይ ተቀምጠን፣ ይህን መጤ በዓል በድብቅ ዓላማው ሳናውቅ እንዴት ልንቀበል እንችላለን?

በአለምዓቀፍ ደረጃ  እንዲታወጅ የተደረገውም

#ክላራ_ዜትኪን ዓለም አቀፋዊ የሴቶች ቀን እንዲከበር በ1910 በዴንማርክ ኮፐንሃገን በተካሄደው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሶሻሊስት ሴቶች ኮንፈረንስ ላይም ያቀረበችው ሀሳብ  ተቀባይነት አገኝቶ እንደነበር ነው ተ.መ.ድ ይፋዊ ድህረገጹ ላይ አስፍሮት የምናገኘው ።

እዚህ ጋር 👉 እንደ ዓለም ዓቀፍ ሁኔታ የምናያቸው ነገሮች አሉ ለምሳሌ ቅኝ ግዛትን ብናነሳ ለየትኛውም ሀገር በታሪኩ ያስተናገደው ክስተት ነበር  ግን ግን እምዬ ኢትዮጵያ ክብር ለአምላኳና ለታጋይ አርበኞቿ  ከዛ ወጥመድ አምልጣለች ስለዚህ ይህች ሃገር በባርነት በበታችነት እንደ አለማችን ሴቶች ዝቅ ይደረጉ ከነበር ይህ እሷን እንደማይመለከት ግልፅ ነው። ኢትዮጵያ ያራሷ ባህል እምነትና ታሪክ ያላት በመሆኗ ከሌሎች እልፍ ሃገራት አንፃር ሳይሆን ከራሷ ታሪካዊ አመጣጥ ብቻና ብቻ ይሆናል ማለት ነው በዚህ ዙሪያ ያላት አቋም ።

አስቡት እስኪ ለምሳሌ እኛ የዚህ ትውልድ አካል ሁነን ይህንን ነገር ስንቀበል በመልካም አይተን ታሪኩንም መቀበላችንን እያረጋገጥን ነው በተዘዋዋሪ። ❗️ ከባድና አደገኛ ነገር እዚህ ላይ ነው። ለምሳሌ ሌሎች ሀገራት ከ ቅኝ ግዛት ነፃ የወጡበት ቀን ሲያከብሩ በዛ ውስጥ በባርነት የኖሩበትን ዘመንም ለታሪክ እያሰቡና እያስቀመጡ ነው።  እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን ቅኝ ሊገዙ  የመጡትን አሳፍረን የላክንበትን የነፃነት ድላችንን ስናገብር ከዛ በፊትም በማንም እንዳልተገዛንና እንዳልተደፈርን ለታሪክ እያዘከርን ነው ስለዚህ በባርነት ወድቆና ተገዝቶ ከሚመጡ ነገሮች ነፃ ነን ማለት ነው ለዛም ነው የራሳችን ያልተበረዘ ታሪክ ማንነት ያለን ነን የምንለው። ተደባልቀን መቼስ ከባርነት እስራት የተፈታንበት ቀን እያልን አናከብር!

በቀደምት ታሪክም እኛ ኢትዮጵያውያን ቀድሞኑ፣ ለሴቶች ከፍ ያለ ቦታና ክብር የሰጠን ህዝቦች መሆናችንን በመረጃና ማስረጃም ማየት እንችላለን። ከጥንት #ንግሥት_ሳባንና በተለይ  ግብፅ ላይ ይገዙ የነበሩ ሴት ኢትዮጵያዊ ፈርዓናት እነ ህንደኬን ፣  ከቅርብ ታሪካችንም እቴጌ ጣይቱን ማየት እንችላለን በዛን ዘመን በምዕራቡ ምድር ላይ ምን እየተካሄደ ነበር ስለ ሴቶች?

ታድያ እነሱ ያመጡብንን በጭፍን ከመቀበል ይልቅ፣ ታሪኩንና አመጣጡን በጥልቀት እንመርምር ። [ እዚህ በስፋት ለማንሳት ስለማይመች ነው ]

ከራሳችን ባህል፣ታሪክ፣ እሴትና እምነታችን ጋር የማይጣጣሙትን በግልፅ እንቃወም። የራሳችንን ማንነት ጠብቀን፣ ለሴቶቻችን ከድሮ ከጥንት የሰጠነውን አለም ይወቅ ይረዳ አዲስ ነገር የለም ከዘፍጥረት ከመነሻው አዳምና ሔዋን 1 ናቸው ሊበላለጡም አይችሉም የየራሳቸው ተፈጥሮአዊ አፈጣጠር አላቸውም ስለዚህ እኛ ይህንን አካሄድና አስተሳሰብ አራሚ መስሎ ገብቶ ለማዛባትና የራስ የግል አላማን ለማስፈፀም መሞገት ፋይድቅ ቢስ ነገር ነው።

ኢትዮጵያውያን፣ የራሳችን ማንነት፣ የራሳችን ታሪክ፣ የራሳችን እሴት አለን ስንል እሺ ስንጠቀምበት ያንን አይ እንደዛ እኮ አይደለም ካሉ ዳግማዊ አድዋ ዳግማዊ ማይጨው ዳግማዊ ካራማራ እዛ ጋር ነው። እርግጥ ነው በሴቶች ዙርያ ብዙ ሄላ ቀር አመለካከትና እሳቤዎች ያሉባቸው ቦታዎች ይኖራሉ ነገር ግን ያሉንን ታሪካዊ እሳቤዎች ጠብቀን፣ ለሴቶቻችን ክብር የምንሰጥበትን፣ የራሳችንን መንገድ እንፍጠር ታሪክ እንዳናበላሽ።

በአብዛኛውን ጊዜ አንድን ነገር #አጀንዳ ለማድረግ የሚሞክሩትም በዛ ውስጥ በስውር ብዙ ነገሮችን በቀስታ ከማላመድ ቀስ በቀስ እስከመጨረሻው ወደራሳቸው Philosophical እሳቤና Historical እቅዳቸው ውስጥ የሚፍቁትን በመፋቅ የሚጨምሩትን በመጨመር ስለሚሰሩ ነው።

በቀላሉ ይህንን የሴቶች ቀን ይከበር ሲሉ እነሱ ያው ዓላማ ብለው በግልፅ ከተናገሯቸው ነገሮች እንኳን ተነስተን ስናየው ለምን የሚል ጥያቄ መፍጠሩ አይቀርም ሴቶች ዛሬም የበታች እንደሆኑ መልሶ ድርጊታቸው በተዘዋዋሪ ይናገራል። ለምሳሌ የአካል ጉዳተኞች ቀን የሚከበረው አካል ጉዳተኞች ከጤናማ ሙሉ አካል ካለው አንፃር የሆነ ነገር ስለጎደላቸው / እክል ስላለባቸው እና ያ ደግሞ በተለያየ መንገድ ከአስተሳሰባችን ጨምሮ ያሉ ነገሮችን ብናስተካክል፣ ብንተባበር ከማንም የተሻለ እንደማንኛውም ሰው ትልቅ ስራን መስራት እንደሚችሉ ለማሳየት ነው።

ስለዚህ እዚ ጋር ማየት ያለብን ሴቶች በምን ጉድለት ነው መበረታታት ያለባቸው ታሪካዊ መነሻውስ እኛን ይመለከታል ወይ ነው ጥያቄው? እኩል የሆኑ ነገሮችን እኮ ሚዛን ላይ ብናስቀምጥ ሚዛኑ መወዛወዙ አይቀርም ብዙ ....እስኪረጋ ድረስ ነገር ግን እኩል ናቸውና መርጋቱ አይቀርም ያ የመርጋት ደረጃ ላይ ሲደርሱ ያለው ኑሮ የቀደምት ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን ታሪክ ነው። ያሁኑ ትውልድስ ከነዚህ አያት ቅድማያቶቻችን ታሪኩን አራግፎ ይቀበል ??ወይስ ከምዕራባውያን?? ይሄ የእያንዳንዳችን ጥያቄ ቢሆን ደስ ይለኛል።

ይቀጥላል....
━━━━━━━━━━━━
📣 ድህረገጻችንን ላልተ🀄️🀄️ላችሁ ይህንን በመጫን ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ👇

@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
━━━━━━━━━━━━
👍82
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በዘመናት መካከል ለስውሩ ማህበር አባላት የእግር እሳት 🔥 ነው !

@TheHabesha0 @TheHabesha0
👍5
ሰላም ለሁላችሁም ቤተሰቦች በአለምአቀፍ ደረጃ እየተከበረ ስላለው የሴቶች ቀን በአል #ክፍል_ሁለት ይዤላችሁ መጥቻለው።

"በቀደመው ክፍል ላይ...የራሳችንን ማንነትና ታሪክን ጠብቀን፣ እያንዳንዱን ነገሮች ከበስተጀርባቸው ይዘው የመጡትን ስውር ዓላማ እንመርምር " ካልን በኋላ፣ እስቲ እነዚህ የስውሩ ማኅበር አባላት ዓለማቀፋዊ በዓላትን እንዴት እንደሚጠቀሙባቸው ለማሳያ እንመልከት።

እነዚህ ማኅበራት ዓለም አቀፋዊ በዓላትን እንደ መድረክ በመጠቀም የራሳቸውን አጀንዳ በስውር ያሰራጫሉ። ለምሳሌ፣ የሴቶች ቀን ሲከበር፣ የራሳቸውን ፍልስፍናና እምነት የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን በዘዴ ያስተላልፋሉ ። በዓሉን እንደ ሽፋን በመጠቀም፣ የሰዎችን አስተሳሰብ ቀስ በቀስ ወደ ራሳቸው አቅጣጫ ለመሳብ ይሞክራሉ ለምሳሌ የሃሎዊን ( ሰይጣን አምልኮ ) የመሳሰሉትን የግብረሰዶማውያን ቀንና ሌሎችን ጨምሮ ማንሳት ይቻላል። ቀስ በቀስ በዓለማችን ላይ በስፋት እየተስፋፉና ከመገፋት ይልቅ ልዩ ጥቅምና ይፋዊ ነፃነትን ተጎናፅፈው ማየት እየተለመደ ነው። ታድያ ይህ እንዴት ይቻል ነበር ያለ ዙፋን ያዢ ተብዬ ሰዎችና ተፅእኖ ፈጣሪ የሚባሉ ሰዎች እገዛ ውጪ።

ይህንን የሚያደርጉትም በብዙ ሚስጥራዊም ሆነ አንዳንድ ግልፅ መንገዶችን በመጠቀም ነው ለምሳሌ፡-

✔️ በመልዕክቶች: በዓሉን አስታከው በሚሰራጩ መልዕክቶች ውስጥ የራሳቸውን እምነትና ፍልስፍና የሚያንጸባርቁ ቃላትንና ሐሳቦችን ያካትታሉ ያም ለታሪክ የሚቀመጥ መሆኑ ይታወቃል።

✔️ ዓለማችን ላይ ያሉ ትላልቅ ድርጅቶችን በመጠቀም: በዓሉን ለማክበር በሚደረጉ ዝግጅቶች ላይ የራሳቸውን ድርጅቶችና አባላት ያሳትፋሉ ከዛም በገንዘብም በሌሎችም ጥቅማጥቅም አማካኝነት ብዙ ጉዳዮች ይፈፀማሉ።

በሚዲያ: በዓሉን የሚዘግቡ ሚዲያዎች የራሳቸውን መልዕክት እንዲያስተላልፉ ያደርጋሉ እንጂ ያ በአል ከየት እንደመጣ? ታሪካዊ አመጣጡን እንዲሁም ለምን ያቺ ሃገርስ ያንን በአል እንደተቀበለች ከታሪኳ ከባህሏና ከሃይማኖቷ አንፃር ምንም አይነት ምርምር ሲደረጉ አይታይም ።

በእነዚህና ሌሎች ሚስጥራዊ እጅግ የተራቀቀቁ መንገድ ፣ ዓለም አቀፋዊ በዓላትን በመጠቀም የሰዎችን አስተሳሰብ ቀስ በቀስ ይለውጣሉ። ሰዎችም ሳያውቁት የነሱን እምነትና ፍልስፍና እንዲቀበሉ ያደርጋሉ።

በተቃራኒው፣ ኢትዮጵያ ለዓለም አርዓያ መሆን የምትችል አገር ነች። ምናልባትም ፈር ቀዳጅ ብንላት አንሳሳትም የኢትዮጵያ ታሪክ ቀድሞውኑ ከጥንት ታሪካችን ለሴቶች ክብርን የሰጠ መሆኑን ከንግሥት ሳባ ጀምሮ እስከ እቴጌ ጣይቱ ድረስ፣ ከዛ በፊት ስላለው ካነሳን ትልቅ ታሪካዊ ምርምር ስለሚፈልግ እንጂ የኢትዮጵያ ሴቶች በታሪካችን ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ። ያውም ንግስተ ንግስት ብሎ እስከመሾም ድረስ በዛ ዘመን ያደረገች እምዬ እናት ሐገራችን ታሪኳን ማፋለስና ማዛባት ያለፈውንም መካድ ስለሚሆን ትልቅ ጥንቃቄ ይፈልጋል ከሚሉት ወገን ነኝ እኔም በግሌ።

የጥንት ኢትዮጵያዊያን ታሪክ በግልፅ የሚያሳየው ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ለሴቶች እኩልነትና ክብር ትልቅ ቦታ ያውም የትም ያልተደፈሩ ልክ እንደ #የሴቶች_ግዛት ሴቶች ብቻ የሚኖሩበት የሚሰለጥኑበት እና ለትላልቅ ዓላማ ከመሰማራችምታቸው በፊት የሚዘጋጁበትም ትላልቅ #የሴቶች_ገዳማት እንደነበሩ ይታወቃል ገዳማቶቹም መርጠው እስከመጨረሻ በምንኩስና ህይወት የሚኖሩትን በቋሚነት ይዘው ሌሎች መንፈሳዊ ህይወትን እና የመሳሰሉትን የተግባር ትምህርቶችንም ቀስመው የሚወጡ እንደነበሩና በተለይም በአክሱማይ ራሚሱ ዘመን ትላልቅ ስራ እንደተሰራም ይታወሳል መነሳት ባለበት ዓውድ በሰፊው ይዤላችሁ እመለሳለው ።

ስለዚህ፣ ኢትዮጵያ የራሷን እሴቶችና ታሪክ በመጠበቅ፣ ለዓለም አርዓያ መሆን ትችላለች ከፈለጉ ።
እኛ ኢትዮጵያውያን፣ የራሳችንን ማንነትና ታሪካችንን ጠብቀን፣ እያበላለጥን ዝቅ ብለሽ ነበር ከእንግዲህ ከፍ ትያለሽ !!! ተገፍተሽ ነበር ከእንግዲህ ማንም አይገፋሽም እያልን ስለምን ምንም ያላሉትን እልፍ ኢትዮጵያዊያን ሴቶችን እናት እህቶቻችንን አካሄድ ከተማ ውስጥ ተቀምጠን ተምረናል አውቀናል ብለን (ያው ለነገሩ የነሱን ትምህርት😁) ያለ ማስተዋልና ስሜታዊነት ብቻ ዝም ብለን እንጫናለን።

በስተመጨረሻም ትልቅ ውይይት አድርገንበት በእውነትና ትልቅ ሐሳብ ገዢነት ተስማምተን ፩ ቅርፅ እንደምንይዝ ተስፋ አደርጋለው።

የሆነው ሁኖ ግን ወዳጆቼ እንደተለመደው አንድ ጥያቄ ጠይቄያችሁ ይህንን ርዕሰ ጉዳይ ልቋጨው... ዛሬ ላይ ያሉ ብልሹ አሰራር እና አካሄድ ከየት የመጡ ናቸው?? ማለቴ...ማንን መከተል ከጀመርን ጀምሮ ነው የሚጀምረው??? በተጨማሪም እኛ ከጥንት ከድሮው ዘመንናት ታሪካችን ማንገስን ከየት ተምረን ነው? ያንን ያደረገ ኩሩ የሐገሬ ሕዝብ ስለ ሴት ልጅ ምንዓይነት አመለካከት ኑሮት ነው ዓለም በኋላቀርነት በጥብቅ ተይዛ ታሪካዊቷ የኢትኤል ምድር ግን አምላካዊ ትዕዛዝና ተፈጥሮአዊ ድርሻን በመረዳት እስከ ከዋክብት ስያሜ ድረስ ሴትን ልጅ አክብረዋል። ሂዱና ጠይቁ የጥንቷ ምስር ያሁኗ ግብፅ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ነገስታትን ዛሬም ድረስ ሲያመልኳቸው ህንድ ላይ ራሱ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች አማልክት ናቸው ብለው ሐውልትና ቅርፅ እየሰሩ እንዳመለኩና

እንደሚያመልኳቸው ለታሪክ ይቀመጥ። እባካችሁን የእናቴ ልጆች ደሜ የሆናችሁ ኢትዮጵያዊ ሴቶች ሆይ ትክክለኛውን ክብራችሁን እወቁ ታሪካችሁን ግለጡ እዛ ጋር እውነት አለ ስሜታዊነትና ነባራዊ ሁኔታን ብቻ ይዞ አጀንዳ ማራገብ የኋላ የኋላ ለዘመናዊ የባርነት ቀንበር መውደቂያ መንገድ ነውና ንቁ ማለት እፈልጋለው። በዚህ ዙርያ በእውነት ነው የምላችሁ መጽሐፍትን ይዤ Live ተቀምጬ መወያየትም ሆነ ማንኛውም ግር ያላችሁና መጠየቅ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች ወይም ደግሞ በፍፁም ብላችሁ የምታስቡ እህቶቻችንም በውስጥ ✔️ @KalebAdane777 ላይ ማድረስ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም በመወያያ ስብስባችን ላይ ሌሎችም ይማማሩበት ዘንድ ሐሳብ አስተያየታችሁን አስቀምጡ። በ Reactions ስሜታችሁን የማሳየትም መብታችሁም የተጠበቀ ነው በሌላ አርዕስት እድክመለስ ድረው መልካም ቆይታ ይሁንላችሁ #ካሌብ ነበርኩ መልካም 🌆 ምሽት።

#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው
━━━━━━━━━━━━
📣 ድህረገጻችንን ላልተ🀄️🀄️ላችሁ ይህንን በመጫን ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ👇

@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
━━━━━━━━━━━━
👏6👍31
መላው ግብፅን የገዛች ኢትዮጵያዊት ንግስት
ንግስት ኒካንታ ቅንዳኬ ( ህንድኬ ) ፪ኛ ከ730–720 ቅ.ል.ክ  #የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ ላይ ከዚህ በፊትም ስለዚህች ጠንካራ 👸 የንግስና ዘመን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ጽፌ ነበር 🔎 bar ገብታችሁ ፈልጉ!

ስለ ሴቶችና ጥንታዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ካነሳን ይሄ ነው!
በስነፈለግና ምርምርም ቢባል ጥንት ቀዳማዊ እንስት ስሟን ዛሬም የምታገኙት #ካስዮጵያ/ ካስዮፒያ ማሳያ ናት ለዚህ። እንደነ ንግስት ሳባ ያሉትን ዓለም የተስማማባቸውን ታሪክ ትተን ለመደባበቅና ለማዳፈን የሚያሴሩበትን ወርቃማ ታሪካችንን እንግለጥ።  የሰው ልጅን እግዚአብሔር በጾታ ከፍ ዝቅ አላደረገም እንደየፈጠረላቸው ተፈጥሯዊ ልዩነት አከበራቸው እንጂ! ለዚህ ደግሞ ምንም መፈክር ምንም #አጀንዳ አያስፈልገውም።

ታሪክ ልክ ከላይ እንዳነሳናቸው እንስት ጀግኖች በተግባር ሰርቶ መገለጥን ነው።  ያልተዘመረላቸው ሴቶችና የተዘመረላቸው ሴቶችን ብናነፃፅር እንኳን ለኛ ኢትዮጵያዊያን የመልስ ውጤቱ የተገላቢጦሽ ነው እናም ወገኔ ኑ እንመለስ ወደኋላ!  ያኔ የተሰበረውን ድልድይ ጠግነን በአንድነትና ፍቅር የዘር ልዩነትና ጥላቻን ካጠፋን ያኔ ኢትዮጵያዊነት ማንም አይገታው....ይፈካል ይደምቃል!

ሐገራችንን እግዚአብሔር አምላክ ከዲያብሎስ ሴራ ይጠብቅልን ፍቅር ይንገስባት! በቅንነት ለሌሎችም አጋሩ

ድህረገጹን ለመቀላቀል ከስር ያለውን 🔗 Link 👇 በመንካት Join ማድረግ ትችላላችሁ።

@TheHabesha @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
🔥82👍1🙏1
ጥንቃቄ ⚠️

ሰላም ውድ #የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ ቤተሰቦች ከላይ በምስሉ ላይ እንደምታዩት አይነት Link 🔗 ስትነኩት ❗️ Hacker ሮች ቀጥታ አካወንታችሁን ነው የሚጠልፉት እባካችሁ ጥንቃቄ አድርጉ ።
ሊንኩን ተጭናቹ እንዳትገቡ  ከምታምኑት  ሰውም
ጭምር ቢላክላችሁ  እንዳትነኩት የነዛ ሰዎች
አካወንትም በራሱ ተጠልፎባቸው ነው ያ መልእክት የደረሳችሁ!

ጥንቃቄ ጥንቃቄ ለሁሉም ሼር አድርጉት ይህ የነካችሁ ካላችሁ በቀጥታ አካወንታቹ ሀክ ተደርጓል ማለት ነው scamer  ናቸው።

መፍትሔ❗️

ከላይ የላኩላችሁ የመጀመሪያው ፎቶ ላይ ባስቀመጥኩልቅችሁ መልኩ setting በማስተካከል የተጠለፈባችሁን አካወነት በፍጥነት አስመልሱ። ያልገባችሁና እገዛ የምትፈልጉ ሰዎች ካላችሁ 👉 @KalebAdane777 ላይ ማድረስ ትችላላችሁ።

Settings -> devices -> በቀይ የተፃፈውን Terminat All Other session  የሚለውን ተጭናቹ  ok በማለት 24  ሰአት ሳይቆይ አስወግዱት 24  ሰአት ከቆይ እናንተን ሙሉ ለሙሉ የማስወገድ ሀይል አለው።

ለሁሉም ይህንን የጥንቃቄ መልእክት Share/Forward አድርጉት።

#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው
━━━━━━━━━━━━
📣 ድህረገጻችንን ላልተ🀄️🀄️ላችሁ ይህንን በመጫን ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ👇

@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
━━━━━━━━━━━━
🙏7
በቲክቶክ እየተካሄደ ያለው የሃይማኖት ንጽጽር ወይስ የሐይማኖት ጦርነት እውነታውስ ምንድን ነው?

ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የካሌብ ጽሑፍ ቤተሰቦች ፣ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቲክቶክ ላይ እያየን ያለው ነገር ምንድን ነው?

በቅርብ ጊዜያት፣ ቲክቶክ ላይ እየተካሄደ ያለው የሃይማኖት ንጽጽር እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ጥያቄው፣ እውነትስ ከየት ወዴት እያመራች ነው? የሚለው የብዙሃኑን ቀልብ መሳቡም ይስተዋላል!

እናንተ ጥያቄ እንዳቀረባችሁልንና ከዛም  በአብዛኛው ሰው ድምጽ እንድናቀርብ ከተፈለገ  ይህን ስሜታዊ ጉዳይ ለመመርመርና ከታሪካችን ከማንነታችንና አሁን ካለንበት ዘመን አንፃር የምንዳስስ ይሆናል። ግን፣ ብቻችንን አንችልም! የእናንተ ድምጽ ያስፈልገናል በተለያዩ መንገዶች ተሳተፉ።

እውነቱን እንፈልጋለን! ይህ የሃይማኖት ንጽጽር  ወዴት እያመራ ነው? ብለው ሐሳብ የገባቸውም ብዙ ናቸው።

እናንተ ድምፃችሁን አሰሙን! በቲክቶክ ላይ እየተካሄደ ስላለው የሃይማኖት ንጽጽር ያላችሁንም  ሃሳብ አካፍሉን ።

አስተያየታችሁንም; በውስጥ በ ✔️ @KalebAdane777 ም ሆነ በኮሜንት መስጫው እና በመወያያ ስብስባችን ላይ በነጻነት አድርሱን ይህ የዛኛው ህዝብ ስሜት ትንሹ ማሳያ ሊሆንም ስለሚችል! ።

ይህ ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው! አብረን እውነቱን እንፈልግ! እንደተለመደውና ሁሌም እንደምንላችሁ!

ፍቅር አንድነትን ከጥንት ከመሰረቱ ከታሪካችን እንማር  ፍቅር ያሸንፋል ጥላቻንም  ያጠፋል!

ኢትዮጵያ ሁን 
አፍሪካሁን
ሰው ሁን

🔊 ይህንን ድህረ-ገጽ ለመቀላቀል👇

@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0

ይህንን አርዕስት አስመልክቶ ጽሑፍ እንድናዘጋጅ የምትፈልጉ ከስር በማድረግ ሌሎቻችሁም ይቅር የምትሉ በማድረግ ሐሳባችሁን አሳዩን።
👍6🔥1
የካሌብ ጽሑፎች ✍️
Photo
አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ⚠️የቴሌግራም አካውንታችሁ በሃገሮች (በጠላፊዎች ) ሲጠለፍ ሰዎች ከላይ በማስጠንቀቂያ በላኩላችሁ መልኩ ያለ ራሳቸው ፍቃድ ነፃ ፕሪምየምና የመሳሰሉትን Link 🔗 ይልኩባችኋል እነሱም ላይታያቸው ይችላል ሰው ካልነገራቸው።

ከላይ የምታዩትን አይነት መልእክት የያዘ ሊንክ ከማንኛውም ከምታውቋቸው የቅርብ ሰዎች ቢላክላችሁም በፍፁም በፍፁም እንዳትከፍቱት

ከከፈታችሁት የቴሌግራም አካውንታቸው ወዲያውኑ ይሄንን malware ያዘጋጁት ሰዎች እንደምታዩት ጠላፊ ሃከሮች ናቸውና ይሄንን ሲስተም በመጠቀም ያለ ባለቤቱ ፍቃድ መልእክት ከመላክና የሰዎችን አካውንት ከመጥለፍ ያለፈ ብዙ ችግር ይፈጥርባችኋል በተለይ በተለይ  ቴሌግራም ዋሌታችሁ ላይ ገንዘብ ያላችሁ ሰዎች ተጠንቀቁ። #scammer ናቸው።

እኛም በፍጹም እንዳትነኩት ይሄንን ሊንክ ነፃ ፕሪምየምና / ስጦታ መቀበያ ምናምን የሚባሉ ደህንነታቸው ያልታወቀ link አይጠቀሙ እያልን ነው ግን ብዙ ሰው የሰማ አይመስለኝም❗️⚠️

አሁንም ከላይ በላኩላችሁ መልኩ አካውንታችሁን አስመልሱ ፣ጠብቁ ፣ ጥንቃቄ አድርጉ ።

ላልሰሙት በማሰማት ከዚህ ወጥመድ ሰዎችን ይታደጉ ራሶንም ይጠብቁ። መልካም ቀን
#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው
ጽ_ነው
━━━━━━━━━━━━
📣 ድህረገጻችንን ላልተ🀄️🀄️ላችሁ ይህንን በመጫን ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ👇

@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
━━━━━━━━━━━━

ቻንላችን ውስጥ ሲገቡ ከስር #MUTE የሚል ፅሁፍ ካልመጣላችሁ አንድ ጊዜ በመንካት /🔇 UNMUTE/ በማድረግ ስትመለከቱት Mute የሚል ጽሑፍ እንደመጣልዎት ያረጋግጡ! ያኔም ይተዉት ይህን በማድረግ የተለያዩ መረጃዎችና የተለመደው ጽሁፎቻችንንም በሰዓቱ በፍጥነት ያግኙ እናመሰግናለን።
👍6🙏2
“ጦርነት ሲጀምር-ፖለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ፡፡ ባለፀጎች ምግብ ያቀርባሉ፡፡ ድሆች ልጆቻቸውን ይለግሳሉ፡፡ ጦርነቱ ሲያበቃ-ፖለቲከኞች ቀሪ ጥይቱን ይሰበስባሉ፡፡ ባለፀጎች ከጦርነቱ በተረፈው ሐብታቸው ማደግ ይጀምራሉ፡፡ ድሆች ግን ልጆቻቸውን በመቃብር ስፍራ ይፈልጋሉ”

#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው

በዚሁ አጋጣሚ ይህንን ምርጥ መጽሐፍ ያላነበባችሁ ቤተሰቦች እንድታነቡት እጋብዛችኋለው። መልካም 🌆 ምሽት።

━━━━━━━━━━━━

📣 የቴሌግራም ድህረገጻችንን ላልተ🀄️🀄️ላችሁ ከታች ያስቀመጥኩላችሁን ሰማያዊ መስፈንጠሪያ /Link በመጫን ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ👇 ለሌሎችም በቅንነት ያጋሩ!

ኢትዮጵያ ሁን 
አፍሪካሁን
ሰው ሁን

@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
😭6👍2
ሰላም ውድ "የካሌብ ጽሑፎች" የቴሌግራም ድህረገጽ ተከታዮች፣ነገ በአንድ ልብ የሚነካና አስተማሪ በሆነ አንድ ቃል ላይ ብቻ ተነስቶ ብዙ የሚያስቃኝ ፍልስፍናዊ ይዘት ያለው ጽሑፍ ነገ ምሽት የምለቅላችሁ ይሆናል።

ቃሉ "ስናዳሪ" ይሰኛል -እስኪ ከዚህ በፊት ቅሉን የምታውቁት ምንን ያመለክታል? ለምንስ ዓይነት ሰዎች ይህ ቃል ተሰጠ? የሚሉ ጥያቄዎችን እስከዛ ሓሳብ አስተያየታችሁን ብታጋሩን ደስ ይለናል።

"…ለሆዱ ያደረ ሰው ስጋው በህሊናው ላይ ትነግሳለች። ለስጋው ንግስና ስኬት ነባር አላማውን በውራጅ፣ ነፍሱን በሀራጅ ይሸጣል።"

ይህንን ዓይነት እውነትና ሌሎች በርካታ ቁም ነገሮችን በቅርቡ በሙሉ ጽሑፋችን ይዘን እንቀርባለን። ቻናላችንን በመቀላቀል የመጀመሪያዎቹ ተደራሲያን ይሁኑ!

#ስናዳሪ #ክህደት #ሆድ_አምላኪነት #የካሌብ_ጽሑፎች #በቅርቡ #ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው

ድህረገጹን ለመቀላቀል ከስር ያለውን 🔗 Link 👇 በመንካት Join ማድረግ ትችላላችሁ።

@TheHabesha @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
👍11🙏2
የካሌብ ጽሑፎች ✍️
ሰላም ውድ "የካሌብ ጽሑፎች" የቴሌግራም ድህረገጽ ተከታዮች፣ነገ በአንድ ልብ የሚነካና አስተማሪ በሆነ አንድ ቃል ላይ ብቻ ተነስቶ ብዙ የሚያስቃኝ ፍልስፍናዊ ይዘት ያለው ጽሑፍ ነገ ምሽት የምለቅላችሁ ይሆናል። ቃሉ "ስናዳሪ" ይሰኛል -እስኪ ከዚህ በፊት ቅሉን የምታውቁት ምንን ያመለክታል? ለምንስ ዓይነት ሰዎች ይህ ቃል ተሰጠ? የሚሉ ጥያቄዎችን እስከዛ ሓሳብ አስተያየታችሁን ብታጋሩን ደስ ይለናል።…
ሠላም ክቡራን "የካሌብ ጽሑፎች" የቴሌግራም ድህረገጽ  አባላት ከትንሽ ዝምታ በኋላ ተመልሰናል  እንዴት ናችሁ? 🙌

ትላንት ቃል በገባሁላችሁ መሰረት በዛሬው ጦማራችን ውስጥ፣ አንዲት ቃልን ብቻ ወስደን በፍልስፍናዊ ዕይታና በግንዛቤያዊ  ሂስ ላይ ተመርኩዘን በጥልቀት በመመርመር የሰውን ልጅ ውስብስብ ተፈጥሮ እና የኑሮውን አንዳንድ  እውነታዎችን ለመዳሰስ እንሞክራለን አብራችሁን ቆዩ።

ቃሉ ከላይ እንደነገርኳችሁ ስናዳሪ ይሰኛል  ---ስ ና ዳ ሪ---

"ስናዳሪ" ። ይህ ቃል በቀረበው ፍቺው መሰረት ከሥነ-ልቦናዊ ከሞራላዊ እና ከማህበራዊ አንጻር በርካታ ቁም ነገሮችን የያዘ ረቂቅ ጽንሰ-ሐሳብን ይወክላል።

"ስናዳሪ" የሚለው መገለጫ ገና ወደዚህ ዓለም ሳይመጣ ህልሙ የከሸፈን ወይም በሆነ ስህተት ተፈጥሮ ለህዝብ ነጻነት እንቅፋት የሆነን ማንነት ያመለክታል። ይሁን እንጂ የዚህ ጽንሰ-ሐሳብ ዋና እምብርት የሚገኘው ግለሰቡ የጋራ እሴቶችን አሳልፎ በመስጠት፣ የሀገርን ደህንነት በመናድ፣ እና የብዙሃኑን ህይወት በመቅጠፍ የራስን ጊዜያዊ ጥቅም ሲያስቀድም በሚታየው አሳዛኝ እውነት ላይ ይሆናል ማለት ነው።

ከዚህም ባሻገር "#ስናዳሪ" በራሱ የእምነት መርሆዎች ላይ በመሳለቅ የራስን ክብር በሌሎች ስቃይ ላይ ራሱንና የራሱን ፍላጎቶች ብቻ ለመገንባት ሲሞክር ይታያል።

ለምሳሌ;- የመንግስትን ሃብት ለግል ጥቅሙ በማዋል በግዴለሽነት ለራሱን ሐሰተኛ ትውስታ በመፍጠር ራሱን ከመሰል ስህተተኞቹ ጋር ቀላቅሎ የራሱ አንዳች ነገር ሳይኖረው እንዲሁ ለመኖር የሚደረገው ጥረት የዚህ ዓይነቱ ማንነት ምን ያህል ከእውነተኛ የሞራል መርሆዎች እንደራቀ ማሰቡ ቀላል ነው።

የሚገርመው ደግሞ ''ስናዳሪን'' ካስተዋልነው ለሥጋዊ ፍላጎቱ ያደረ ሰው አእምሮው በስሜቱ ቁጥጥር ስር እንደሚወድቅ ያሳየናል። በዚህ ሁኔታ፣ እንዲህ አይነት ግለሰብ ለጊዜያዊ ደስታ እና ሥልጣን ሲባል የረጅም ጊዜ ዓላማውን አሳልፎ ይሰጣል፣ እናም የነፍሱን ክብር እጅግ በሆነ ዋጋ ይሸጣል። ይህ የሚያሳየው የውስጣዊ እሴቶች መዳከም እና የውጫዊ ተጽዕኖዎች የበላይነት ሲኖር የሚከሰትን አሳዛኝ የሰው ልጅ ድክመት ነው።

በተጨማሪም "ስናዳሪ" ምንም ያህል ዕውቀት ቢኖረው ወይም ከፍተኛ ቦታ ቢይዝ ከእውነት እና ከፍትህ ጎን ሊገኝ እንደማይችል የታመነ ነው። ምክንያቱ ደግሞ #ስናዳሪ "አድራሻው ከሆዱ ስር ነው"  ተብሎ ይታመናል ።

ይህ አገላለጽ አስተሳሰቡ በግዴለሽነት እና በስሜታዊነት ፍላጎቶች የተገደበ፣ ከምክንያታዊነት እና ከሥነ ምግባራዊ መርሆዎች የራቀ መሆኑንን ያመለክታል ፣ "ስናዳሪ" የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ የሥልጣን ጥመትን፣ የራስ ወዳድነትን እና የሞራል ዝቅጠት የሚያሳይ ጥልቅ ምሳሌ ነው።

ይህንን በመገንዘብ፣ ይህንን ጽሁፍ በተለያየ አጋጣሚ የምታነቡ የእናቴ ልጆች ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ከዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብና ኑሮ በመራቅ፣ ታናሽ ታላቅ ሳትሉ  በልምምድም ከህይወታችን ውስጥ በማውጣት ለእናት ሐገራችን  እና ለሐይማኖተኛና ቅን ማህበረሰብ ግንባታችን  የበኩላችንን አስተዋጽኦ ልናደርግ ይገባል።

ሁሉም ነገር ግን ከራስ ይጀምራልና ከየራሳችን እንጀምር! በራሱ ዓይን ውስጥ ያለውን ትልቅ ምሰሶ ሳያይ በሌላ ሰው ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለማውጣት ለሚተጉትም ፈጣሪ ማስተዋሉን ይስጣቸው /ይስጠን 🙏

ህይወት ሰው የዘራውን የሚያጭድባት ለማያስተውል ስውር መድረክ ነች!
ፍቅር ይበልጣል ምህረት ያድናል!

ለዚህ አስተማሪና ፍልስፍናዊ ዕይታ ጽሑፍ ጊዜ ስለሰጡን እናመሰግናለን የእናንተንም ጥልቅ ሀሳቦች እና አስተያየቶች ከስር ማካፈል ትችላላችሁ  እኔ ታዳጊ #ጋዜጠኛ_ካሌብ_አዳነ ነበርኩ ።በቀጣይ በሌላ ጽሁፍ እስክንገናኝ ሰናይ ጊዜ 🌆

ድህረገጹ አስተማሪና ጠቃሚ ሁኖ ካገኛችሁት ለወዳጅ ዘመድዎ #share #Forward #React #comment በማድረግ ይደግፉን

#ስናዳሪ #ፍልስፍና #ሞራል #ጋዜጠኛ # #ፍትህ #ማህበረሰብ #የካሌብ_ጽሑፎች

📣ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት👇

👉 @TheHabesha0 👈
👉 @TheHabesha0 👈
👍8🔥3👏1
#ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ሀይል ወሥልጣን ፡አሰሮ ለሠይጣን፤
አግአዞ #ለአዳም፡ሠላም እምይዕዜሰ ፤
ኮነ፡ ፍስሓ ወሠላም።

ለመላው የክርስትና እምነት አማኞች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ/ን ! በብርሃናዊው ክቡር ትንሣኤው ደግሞ አብረን እንሳተፍ ዘንድ ከልብ እንትጋ ጥላቻን እናርቅ ይቅርታን ፍቅርን አንድነትንና ጥንታዊ መከባበራችንን እንመልስ። 🙏 እናት ሐገራችንን እምዬ ኢትዮጵያን በምህረቱ ይመልከታት!

#ኢትዮጵያ_ሁን 
#አፍሪካሁን
#ሰው_ሁን

#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው

👉 @TheHabesha0 👈
👉 @TheHabesha0 👈
11
Audio
ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ? ቤተሰቦች እንኳን #ለብርሀነ_ትንሳኤው_በ ? አደረሳችሁ እያልን
አንድ አጠር  ያለ ግጥም በዓሉን ምክንያት በማድረግ አቅርበንላችኃል። እንደምትወዱት ተስፋ አደርጋለሁ ተጋበዙልኝ በድጋሚ መልካም በዓል ይሁንላችሁ/ይሁንልን። [ reposted ]

ገጣሚ፦#ኤፍሬም_ስዩም

የግጥሙ ርዕስ:- #የጅራፍ_ንቅሳት

ግጥሙን ወደእናንተ የሚያደርሳችሁ ከ6 ዓመታት በላይ የቆየው #የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው

#share #Forward #React ይደረግ

👉@TheHabesha0👈
👉@TheHabesha0👈
🙏10👍1
ስለ ፩ እናት ሐገራችን ዝም አንልም
ኢትዮጵያ ርስታችን ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ኪዳናችን ነው! እ ን ጠ ብ ቀ ው

ይህ👆 የካሌብ ጽሑፎች በቅርቡ በ YouTube #ዘብ-ኢትዮጵያ በሚል ስያሜ ወደናንተ የተለያዩ መረጃዎችን ለማቅረብ ሽር ጉድ እያለ የሚገኝበትን ሑኔታ የሚያስቃኝ ምስል ነው ። እንደተለመደው በ ኢትዮጵያዊ የቅንነት መንፈስ በሐቀኝነት ለመስራት የሚተጉትን እናበረታታ ካሁን ሰዓት ጀምሮ ይሄንን አካውንት በ Official YouTube ገጽ ለማግኘት ከስር ያለውን Link በመጫን Subscribe ማድረጎን አይርሱ!👇👇👇


https://youtube.com/@zebethiopia?feature=shared

በቅርቡ የተለያዩ ነገሮችን ከትክክለኛው የጋዜጠኝነት ሙያና ተግባር ጋር ይዞላችሁ ለመቅረብ ስራ ላይ ነውና በትዕግስት ይጠብቁን! ሐሳብ አስተያየትና ማንኛውንም አይነት ጥቆማዎችን በቴሌግራም በ 👉 @KalebAdane777 ላይ ያድርሱን ሠናይ ጊዜ!
👍4👏31
ሰላም ለሁላችሁም እንዴት ናችሁ ቤተሰቦች ትንሽ ዝም ያልኩት በእውነት ነው የምላችሁ ከብዙ ሰዎችና ከህይወት እየተማርኩ ስለሆነ ነው። አውቃለሁ የሰው ልጅ ሁሌም እንግዳ እንደሆነና በየእለቱ አዳዲስ የማያውቃቸውን ነገሮች እንደሚማር ግን ባሁኑ ሰዓት በአንዳንድ ነገሮች ላይ መደመም እያጠቃኝ ይመስለኛል😁

እና ግል በአጭሩ እየተመለስኩ ነው እኔ ! ሁላችንም ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስ የት ነን ?? ወዴት እያመራን ነው🤔


ፍቅር ይንገስ ጥላቻም ይርከስ ማለትም ለመሸመት ሳይሆን ዳግም ላይመለስ
ገንዘብ ያረግነው ለት ሰው መሆናችንን ፈንቅሎ እንዳያፈርስ!


#ኢትዮጵያ_ሁን 
#አፍሪካሁን
#ሰው_ሁን

#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው

👉 @TheHabesha0 👈
👉 @TheHabesha0 👈
9👍1👏1
2025/07/09 04:36:42
Back to Top
HTML Embed Code: