እርሱ በፍፁም ፍቅር፤ በፍቅር ጥግ ወዶን ነበር......
.....እኛ ዘበትንበት፤ተፋንበት፤ገረፍነውም፤ጎኑንም በጦር ወጋነው፤የእሾህ አክሊልም ደፋንበት፤መራራም አጠጣነው፤ሰቀልነውም ገደልነውም እንጂ......💔

ቶሎ ቶሎ ልኑር ጊዜውን ላብቃቃ
አመት የሚሉትን አርግልኝ ደቂቃ
ደቂቃ ሚሏትም ላመት ህይወት ትብቃ !
ቶሎ ተ ፈራገጥ ቶሎ ል ፈራገጥ
እረገጥከኝ አትበል አንተም እኔን እርገጥ !
ለየትኛው ጌዜ ለየትኛው አመት
ለየትኛው ወዝህ ለየትኛው ውበት !
..................................................
...............................................
...................................... !
Ab!

እቺ ጥርሴ ሞኟ
ውሸት ተክናለች
ለሚያያት ሰው ሁሉ
ሁሌ ትስቃለች....
እቺ ጥርሴ ሞኟ
መች ትመስልና
ደስታዋ ሚያበቃ
ያየ እንዳያዝንላት
በሳቅ ተደብቃ
✍️አላዛር ብዙዬ [ AB ዘ-ማርያም ]
ውሸት ተክናለች
ለሚያያት ሰው ሁሉ
ሁሌ ትስቃለች....
እቺ ጥርሴ ሞኟ
መች ትመስልና
ደስታዋ ሚያበቃ
ያየ እንዳያዝንላት
በሳቅ ተደብቃ
✍️አላዛር ብዙዬ [ AB ዘ-ማርያም ]
ባሞገሰ አፏ ትሸረድዳለች
ጥሩ ነህ እያለች
መጥፎ ታስባለች
የስሜት ተመሪ የስሜት አሸርጋጅ
አፏ ፍፁም ሌላ ልቧ እኔን ወዳጅ
OB'SUN(jah)
ጥሩ ነህ እያለች
መጥፎ ታስባለች
የስሜት ተመሪ የስሜት አሸርጋጅ
አፏ ፍፁም ሌላ ልቧ እኔን ወዳጅ
OB'SUN(jah)
በፈጣሪ አላምንም የሚለውን ፍልስፍናውን አብራርቶ ሳይጨርስ ታክሲ መጥቶ ተጋፍተው ተሳፈሩ ...ውስጥ ገብተውም ማብራራቱን ሊቀጥል ሲል አቋርጦት ...ቆይ አንተ አሁን በዚህ ታክሲ ሹፌር ታምናለህ በብቃቱ እርግጠኛ ነህ ብሎ ጠየቀው ....እንዴ ምን ሆነሀል ሹፌሩን የት አውቀዋለው ብሎ መለሰለት ...ታዲያ ለምን ትሳፈራለህ በእግርህ ነበር እኮ መሄድ የነበረብህ ....ጦር ሀይሎች ድረስ በእግሬ እሱማ ከአቅሜ በላይ ነው ብሎ መለሰለት ....አየህ ምድር ላይ ስትኖር ካንተ በላይ የሆኑ ነገሮች ያጋጥሙሀል ቤትህ እርቆህ አንድ ማንነቱን የማታውቀው ሹፌር አምነህ ታክሲ ውስጥ እንደምትገባው ሁሉ ....ወደፊት ከዚህ በላይ ከአንተ አቅም በላይ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙህ ይሄን ፍልስፍናህን ምትቀይር ይመስለኛል ...
ወንድሜ እንኳን ፈጣሪን ሰውን ካላመንክ እዚህ መኖር አትችልም
Ab!
ወንድሜ እንኳን ፈጣሪን ሰውን ካላመንክ እዚህ መኖር አትችልም
Ab!
ይህ ስዕል ድሮ አውሮፓ ውስጥ የተፈጠረን እውነተኛ ታሪክ የሚያሳይ ነው።
=====
ይህች ሴት : አባቷ በስርቆት ወንጀል ተከሶ ሞት ይፈረድበታል።
የሞቱ አፈፃፀምም: እስር ቤት ተዘግቶበት ምግብ በመከልከል በርሃብ እንዲሞት ነበር።
ሴት ልጁ : የሞቱ ቀን እስኪደርስ : አባቷን በቀን አንዴ እንድታየው ተፈቀደላት። ምግብ ይዛ እንዳትገባ በደንብ እየተፈተሸች : የ6 ወር ልጇን አቅፋ : የሞቱን ቀን የሚጠብቀውን አባቷን ጎብኝታ መውጣት ጀመረች።
አስገራሚው ነገር : ሰውየው ለ 4 ወር ሳይሞት በሰላም ቆየ።
በጉዳዩ እንግዳነት የደነገጠው እና ግራ የተጋባው የእስር ቤቱ አስተዳደርም : እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በድብቅ መከታተል ሲጀምር : በቀን አንዴ ልትጎበኘው የምትገባው ሴት ልጁ ጡቷን እያጠባችው እንደምትሄድ ደረሰበት።
ይህንንም ክስተት ለፍርድ ቤቱ አሳወቀ። ጉዳዩ አነጋጋሪ ሆኖ የብዙዎችን ልብ ነካ።
የዚህች ሴት የብልሃት ፤ የፍቅር እና የርህራሄ ጥግ : አባቷ ፍርዱ ተሽሮለት በነፃ እንዲለቀቅ ምክንያት ሆነ።
ታሪኩን የሚገልፀው ይህ ስዕልም በውድ ዋጋ በመሸጥ ታሪክ አስመዘገበ።

አባት የመጀመርያም የመጨረሻም የሆነ ብቸኛ ልጁን ሊድር ድል ያለ ሰርግ ደግሶ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆቹን ጠርቶ የምሳ ግብዣውን እየተዟዟረ ይመለከታል።
‹‹ማን ቀረ ማን መጣ›› የሚለውን በትኩረት እየተመለከተ ሳለ የቅርብ ጎረቤቱን ከእይታው ያጣዋል። ግራ በመጋባት እየተዟዟረ ቢመለከትም ጎረቤቱንም ሆነ የጎረቤቱን ልጆች ሊያይ አልቻለም።
‹‹የልብ ወዳጄ በዛሬ ቀን እንዴት ከጎኔ ይጠፋል›› እያለ በንዴት ስሜት በመብሰልሰል ላይ ሳለ ድንገት የጎረቤቱ ልጅ ብቅ አለና በፍጥነት ትንሽ ምግብ ቀማምሶ ትቶ ወጣ።
ይህን ትዕይንት የተመለከተው ደጋሽ በንዴት ተብከነከነ። የአባቱ በደስታው ግዜ አለመገኘት ሳያንሰው ልጁ መጥቶ በምግቡ አላግጦ መውጣቱ አበሳጨው።
በዚህ መሀል የሙሽራው አጃቢዎች ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት ጉዞ ሊጀምሩ መኪናቸውን ማንቀሳቀስ ሲጀምሩ ምግቡን ቀማምሶ በፍጥነት የወጣው የጎረቤቱ ልጅ ሙሽራውን ለማጀብ ከግቢ መኪናውን ይዞ ይወጣል።
አባት ተበሳጨ፣ ንዴቱን መቆጣጠር ቢያቅተው በቁጣ መንፈስ ተሞልቶ ወደ ጎረቤቱ ልጅ በመሄድ፦‹‹አባትህ ጎረቤቴ ሁኖ ደስታዬ ላይ አልተገኘም፣ ታላላቅ ወንድሞችህም እንደዝያው፤:ታድያ አንተ ምን አስበህ ነው በምግብ አላግጠህ ትተህ የወጣኸው? አሁን ተመለስ ያንተን አጃቢነት አንፈልግም›› ብሎ መለሰው። ልጁም እቤቱ ገባ፤ ሰርገኛዎችም ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት አቀኑ።
በመጨረሻም አጃቢዎች ሙሽሮችን ይዘው ወደ ቤት በመግባት የደስታቸው ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ቀኑ ሲጨልም ሁሉም ተበታትኖ ሰርግ ቤቱ በሙሽሪት እና በሙሽራው ጭር አለ።
አባት አሁንም በጎረቤቶቹ ንዴት እየተብሰለሰለ ነው። ድንገት ከመሸ ያለ ወትሮው የጎረቤቱ ጊቢ ተከፈተ። የሙሽራው አባት እየተመለከተ ነው።
የጎረቤቱ ልጆች በትከሻቸው አንዳች ነገር ተሸክመው ከቤታቸው ሲወጡም ተመለከተ። ፍፁም ዝግታ እና እርጋታም በሚስተዋልበት እርምጃ ልጆቹ ይራመዱ ጀመር።
የሙሽራው አባት ጠጋ አለ። ፦‹‹ምንድነው?ማንን ነው የተሸከማችሁት ›› ሲልም ጠየቃቸው።
‹‹አባታችን ጠዋት ሞቶ ነው፤ ሲሞትም በሱ ለቅሶ ምክንያት ያንተ ደስታ እንዳይስተጓጎል መሞቱን ከሰርግህ በፊት ለማንም እንዳንናገር እና ድምፅ አውጥተን እንዳናለቅስ ተናዞልን ነበር። ለዝያ ነው ድግሱ ላይ መገኘት ያልቻልነው። ›› በማለት አባታቸውን የተሸከሙት ልጆች ጉዳያቸውን አስረዱ።
ደጋሽ ተፀፀተ፦ ‹‹እኔ በሱ ቦታ ብሆን ይህን የማድረግ አቅም አይኖረኝም ነበር›› ሲልም የቁጭት እንባ ያነባ ጀመር።
በህይወታችን ችላ ያሉ እየመሰሉ በቁስላቸው ደስታችንን ላለማበላሸት ሲሉ ከአከባቢያችን የሚርቁ ሰዎች አሉና ልብ ያለው ልብ ይበል።
Sefwan Ahmedin
አሻም
getu wendesen🙏🙏🙏🙏