Telegram Web
ጠቃሚ የህይወት መርሆዎች


🙏ደግ ሁን🙌

የምትችል ከሆነ ከማንም የበለጠ ደግ ሁን፤ ቢሆንም ደግነትህን አትናገር፡፡ ስለተረፈህ ሳይሆን ሰብአዊነት ኖሮህ ላንተ ከሚያስፈልግህ ሳትሰስት ለሌሎች አካፍለህ ኑር፡፡ "መስጠት የማያውቁ ሰዎች ሌሎች ሲሰጡ ይታመማሉ!!"

💐ቀና ብለህ ተጓዝ🙌

ዘወትር ቀና ብለህ ተጓዝ ምክንያቱም ራሱን ያጎበጠ ሰው መቼም ሌሎችን አቅንቶ አያውቅምና፡፡

🌸ችግሮችህን አስብ🙌

የገጠሙህን ችግሮች ችላ አትበላቸው ምክንያቱም ችግርን በጥቅም ላይ እንደማዋል ጣፋጭ ነገር የለምና፡፡

🍂እውቀትን የምትሻ ሁን🙌

ከሌሎች ሰዎች ለማወቅ የተዘጋጀህ ሁን ምክንያቱም የእብደት የመጀመሪያ ምልክት እራስን አዋቂ አድርጎ ማሰብ ነውና፡፡

መልካም አሳቢ ሁን፡፡🙌

ሁሉም ሰው ራሱን የሚያገኘው በየእለቱ በሚፈጥረው አስተሳሰብ መሠረት ነው፡፡
መጥፎ ቀን የምንለው መጥፎ ሃሳብ ያሰብንበት ቀን ነው፡፡ ስለሆነም ሁሌም መልካም ነገር እንዲገጥምህ መልካም የሆነውን ብቻ ተመልከት፡፡

🍁የቁሳዊ ድህነትን አትፈርበት፡፡🙌

የቁሳዊ ድህነትን አትፈርበት ምክንያቱም ምድር ላይ እጅግ የሚያሳፍረው ነገር ቢኖር የአዕምሮ ድህነት ነውና፡፡

🌴ለገባኸው ቃል ታመን🙌

ቃል ለመግባት የዘገየህ፤ ከገባህ ደግሞ የፈጠንክ ሁን፡፡

🌹ራስህን አሻሽል🙌

"የአንተን ውድቀት ለሚመኙ ስትል ራስህን አሻሽል"

🌱መጀመሪያ ራስህን እወቅ🙌

ጠንካራ ጎኖችህን ይበልጥ አጠንክርህ በድክመትህ ላይ ፈጥነህ ዝመትባቸው፡፡

🌺ህሊናህን አድምጥ🙌

የተፃፈውን ሁሉ አንብበህ በህሊና መዝገብህ ከመፃፍህ በፊት በህሊናህ ሚዛንህ አብጠርጥር፡፡ ሁሌም ለሕሊናህ እንጂ ለሰው አትገዛ ምክንያቱም የሰው ልጅ ዛሬ ወዳጅ መስሎ ቀርቦ ነገ ሊሸሽህ ይችላል ህሊናህ ግን በፀፀት እየወቀሰህ ዘወትር አብሮህ ይኖራልና፡፡

አንደበተ ርቱህ ሁን🙌

"ምላስህን ካልጠበካት እስዋ አትጠብቅህም" ጨዋ አንደበት የተዘጉ በሮችን ይከፍታል፡፡

💡ብልህ ሁን🙌

መከራን እና የተወረወረ ድንጋይን ዝቅ ብሎ ማለፍ ብልህነት ነው፡፡ ምክንያቱም ምድር ላይ ስትኖር ለመኖር መፈተን ለማለፍ መታገስ ግድ ነውና፡፡

🌿ሁልጊዜ ራስህን ሁን🙌

ራሱን ያወቀ ሰው ሁልጊዜ በኑሮው ደስተኛ ነው፡፡ ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር ማንነትህን ታጣና ህይወት ጣእሟን ታጣለች፡፡

🌸ሞራል ይኑርህ🙌

የማይዋዥቅ የህይወት ሞራል ይኑርህ ምክንያቱም ጠንካራ ሞራል የህይወት ተስፋ ነውና፡፡

🍃ባለህ ነገር ተደሰት🙌

ዛሬን ስለነገ በመጨነቅ ካሳለፍከው ዛሬን በቅጡ መኖር ይሳንሃል፡፡ ስላለህ ነገር እንጂ ስለሌለህ ነገር አታስብ ምክንያቱም ነገ የፈጣሪህ ነውና፡፡

እውነታን ተቀበል🙌

ተፈጥሮ የቸረችህን ማንነትህን አምነህ መቀበልን ትተህ ለማማረር ወይም ለመሸማቀቅ አትሞክር ምክንያቱም በተሰጠህ ተፈጥሮሯዊ ማንነትህ ላይ ያንተ ሚና የለበትምና፡፡ በማይለወጥ አንተነትህ ተደሰት ምክንያቱም ቁርጡን ያወቀ ሰው ምርጫ ይኖረዋልና።


❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
የት ልሁን ንገሩኝ

ከግራ ወይስ ከቀኝ
የት ሄጄ ልገኝ
ከማን ጋር ልመደብ
በየትኛው መዝገብ
በምን አይነት ስሌት በየትኛው ቀመር
እ-ን-ዴ-ት-ስ ልሳፈር 
የቱ ጎራ ልግባ ማንንስ ልከተል
ሄጄ የቱን ልምሰል

የት ልሁን ንገሩኝ
መጥታቹ አማክሩኝ
ብቻ.............. ከውነታዉ አካፍሉኝ
ምንም አትደብቁኝ
ላይነጋ ከመሸም
ብርሀን ከሸሸም
ግዴለም ልወቀው
መጀመሪያዬ ላይ ደርሼ እንዳየዉ

የት ልሁን ንገሩኝ
ግልምቢጥ  መንገዴ መርቶኝ ከምጠፋ
መድረሻዬን ልወቅ አንዴ ላግኝ ተስፋ

ተፃፈ በ ጃሒዝ

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
Cultivate your mind - it will blossom beyond your
expectations • The quality of your life is determined
by the quality of
your thoughts • There are no mistakes - only lessons.
See setbacks as
opportunities for personal expansion and spiritual
growth
• The Heart of the Rose
• Opposition Thinking
• The Secret of the Lake
The secret of happiness is simple: find out what you truly
love to do and then direct all of your energy towards doing
it. Once you do this, abundance flows into your life and
all your desires are filled with ease and grace.

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
«ጓደኛ ማፍራት ከፈለክ ብዙም አትቅረብ፣ አትራቅ፣ ፍላጎትህንና ታዕቅቦህን ከሚያስፈልገው በላይ አታድርገው። ቀስ በቀስ ቅረበው፤ እንደወደድከውም መስለህ መሀከላችሁ የተወሰነ ርቀት ይኑረው። በአንድ ጊዜ ዘለህ ጥብቅ የምትል ከሆነ ላይወድህ ይችላል። ቀስ በቀስ እየተገነባ የመጣ መቀራረብ የተሻለ ውጤት ይኖረዋል»

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
"ጥዋት ስትነሳ ምታስበው ነገር . . . ለዛሬ ብለህ ያዘጋጀኸው . . . ሁሉንም ለማድረግ አቅደህ ከቤትህ ስትወጣ ሌሎችም እንዳንተው የራሳቸው እቅድ ያላቸው አሉና ላንተ ጥቅም ስትል በነሱ መንገድ ላለመግባት ሞክር፡፡ ይህን ካደረክ የሁለታቹም ከመንገድ ፍፃሜው መልካም ይሆናል፡፡

💞 #መልካም_ቀን 💞

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
• በሌላ ሰዉ ትተካለህ አለቀ! ምንም ያህል ጎበዝ ብትሆን ቦታህን 'ከለቀክ' ካንተ የሚሻል ወይም ተመጣጣኝ ችሎታ ያለዉ ሰዉ ይተካሃል

• ሰዎች በልባቸዉ መኖርህን ከቁብም አይቆጥሩት

• የሆነ ሰዉ መልእክት ልከህለት ካልመለሰልህ ለምን አልመለሰልኝም ብለህ ሌላ አተካራ ዉስጥ አትግባ፡፡ በግድ የሆነ ጓደኝነትና የፍቅር ግንኙነት የትም አይደርስም

• ለነገሮች ትንተና አትስጥ፡፡ አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ ሰአት ብቻ እንጂ ስለእያንዳንዱ ነገር ገለፃ የምታደርግ ከሆነ እራስህን ታደክማለህ

• ሰዎችን መቼም ቢሆን ለመለወጥ አትነሳ፡፡ ማንም ቢሆን ላንተ ብሎ እራሱን አይቀይርም፡፡ ሲጋራ የሚያጨሰዉን ሰዉ 'አታጭስ' ስላልከዉ ማጨሱን አያቆምም ይልቅስ ለምን ማጨስ እንደማያስፈልገዉ የሚረዳበትን ፍንጭ አሳየዉ...እምቢ ካለ አፈግፍግ

• ከራስህና ከሚቀርቡህ ሰዎች ምረጥ ብትባል እራስህን ምረጥ፡፡ ይሄ እራስ ወዳድ መሆን ሳይሆን በከባዱ የህይወትህ ሰአት የራስ ማንነትህ ከሌሎቹ በተለየ መንገድ እንዴት እንዳሳለፈ ያዉቀዋል

• አንተ ጋር ብቻ ያለ ፍቅር ከምትወደዉ ሰዉ ዉስጥ ከሌለ እራስህን እያጎሳቆልክ ነዉና አሁኑኑ አቁም

• የመጥፎ ባህሪ ድግግሞሽ የህይወት መርዝ ነዉ

• ለማንም ቢሆን እራስህን ግልጥልጥ አድርገህ አታሳይ ምክንያቱም 90 ፐርሰንት የሚሆነዉ ሰዉ ማንነትህን እስከጥጉ ካወቀ በደካማዉ ጎንህ መጫወት ይጀምራል

• ሰዎች እንደሚወዱህ ቢነግሩህና ጥሩ ለመሆን ብትሞክርም አንተ ላይ መፍረዳቸዉን አያቆሙም

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
"አንተ ከምታውቀውና ከምታምነው በላይ ሌላ ማንነት አለህና እሱን ፈልገህ አግኝ"
💗

በሰው ልጅ ተፈጥሮ ውስጥ የምናገኘው አንድ አስቸጋሪ ባህርይ ቢኖር ለማንኛውም ድርጊቱ ወይም ጥፋቱ ኃላፊነቱን ወስዶ ወይም ተቀብሎ በሕይወት ለመቀጠል ድፍረት ማጣቱ (መነጠቁ) ነው:: ድርጊቱ ብቻ ሳይሆን በማንነቱም ቢሆን ኃላፊነትና ሸክሙን በአምላኩ፣ በቅዱሳኑ፣ በመምህራኑ ወይም ሌላ በሚያምንበት ነገር ላይ ጥሎ የእነሱን ይቅርታ ወይም ምህረት በመፈለግ ይጠመዳል:: ከዚህም የተነሳ ሕይወቱን የጭንቀትና የመከራ ብሎም የፍርሃት አድርጎ ከመቀበል በዘለለ ሌላ አማራጭ የሌለው ተስፋ ቢስ ፍጡር አስመስሎታል። እነሆ በማንኛውም የሕይወት አቅጣጫችን ዙሪያ ለምንፈፅማቸው ድርጊቶች ይቅርታና ምህረት ከምንለምንበት ፍርሀት ተሻግረን በራስ ፀንቶ ወደመቆም ድፍረት የሚወስደንን መንገድ እንቃኛለን።

በርካታ አሳባውያን የሚስማሙበት አንድ የሰው ልጅ የማንነቱ እውነት ቢኖር የፈፀመውን ማንኛውንም ድርጊት አምኖበትና ፈቅዶ መሆኑን ከመቀበል ይልቅ እንደስህተትና ኃጢአት በመቁጠር በንስሀና ይቅርታ ራሱን ቀፍድዶ በሌሎች ፊት የመቆሙ ጉዳይ ነው:: ይኸ ብቻም አይደለም:: የሰው ልጅ መከራ ምንጩም ሆነ ምክንያቱ ይኸው ስህተት ወይም ኃጢአት በማለት የሚፀፀትበትን ድርጊት በኃላፊነት ከመሽከም ይልቅ ወደሌላው ትከሻ ማሽጋገሩ ነው:: ነገር ግን የአንተን (የሰው ልጅ) ኃጢአትም ሆነ መከራ አልያም ጭንቀት የሚሽከም (የሚወስድ) ሌላ ማንም እንደሌለ ደግሞ ብትረዳ ጭንቀትህን ለማስወገድ የመጀመሪያውን እርምጃ እንደወሰድህ ይቆጠራል:: ከአንተ ከራስህ በቀር አንተን ተክቶ ፃድቅ ወይም ቅዱስ የሚያደርግህ ሊኖር አይችልምና:: ነገር ግን በድርጊትህ ምክንያት ከሚፈጠርብህ የኃጢአተኛነት ጭንቀት ወይም የቅድስና እርካታ ይልቅ ኃላፊነቱን ራስህ ብትወስድና ሕይወትን እንደነበረች በማስቀጠል (ወደኋላ ዞረህ ሳትመለከታት) በጉዞህ ብትቀጥል ያን ጊዜ በእውቀት መንቃት ለመጀመርህ ማረጋገጫ ይሆናል:: ኃጢአትም ሆነ ቅድስና ብለህ የምትጠራውን ነገር አንተ ለብቻህ እንደፈፀምከው ካመንክ ስለምን ምህረትም ሆነ በረከትን ፍለጋ ወደሌላ ትመለከታለህ?

እዚህ ላይ የሰው ልጅ የዘወትር ሃሣቡ፣ ጭንቀቱና ፍርሃቱ በሕይወት ውስጥ በአንዳች አጋጣሚ አምኖበት ከፈፀመው ድርጊቱ የሚመነጭ ለመሆኑ የሚካድ አይደለም:: በመሆኑም ዛሬ የሚያጋጥምህን መከራ ትናንት ተሳስቼ ፈፀምኩት ከምትለው ድርጊት (በአንተ ቋንቋ 'ኃጢያት') የተነሣ እንደመጣብህ እያሰብክና ይኸው ምክንያትህ በሚያተርፍልህም ጭንቀት ሕይወትን አስቀያሚ አድርገህ በመመልከት ልትቀጥል አይገባም:: ኃላፊነትና ነጻነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው! የሰው ልጅ ለማናቸውም ድርጊቱ ሌሎች ኃላፊነቱን ወስደው የሚቆሙለትና የሚሸከሙለት እንዳሉ በማመኑ ዘወትር የሚከተላቸውን "አዳኞቹን" (saviors) በፀፀት፣ በልመናና በንስሀ ከፊታቸው መቅረቡን ተለማምዶታል። ከዚህም የተነሳ ፈጣሪውን ብቻ ሳይሆን ፈጣሪውን ወክለው በምድር ላይ የተገለጡትን ሁሉ በመከተል የእነሱን ፈቃድና ትዕዛዝ ፈፃሚ ሆኖ በመቅረቡ አንድ ቀን በራሱ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ የፈፀመው ድርጊት "ኃጢአት" ቢኖር እንኳን ከእነሱ ምህረትና ይቅርታ ለማግኘቱ እርግጠኛ እስከሚሆን ድረስ ህይወቱን በጭንቀት መግፋቱ አይቀሬ ይሆናል:: በመሆኑም "የሰው ልጅ ይኸንና ያንን አታድርግ፤ እኔን ተከተል፤ እኔን እመን... እኔም አድንሃለሁ፤ እኔ ጠባቂህ ነኝ ወዘተ በሚለው የተስፋ ትዕዛዝና ቃላቸው የታመነባቸውን እየተከተለ የራሱን ማንነት ግን ለመጣል ተገዷል::
💗
ሀይለጊዮርጊስ ማሞ(ጲላጦስ)

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
"ጥዋት ስትነሳ ምታስበው ነገር . . . ለዛሬ ብለህ ያዘጋጀኸው . . . ሁሉንም ለማድረግ አቅደህ ከቤትህ ስትወጣ ሌሎችም እንዳንተው የራሳቸው እቅድ ያላቸው አሉና ላንተ ጥቅም ስትል በነሱ መንገድ ላለመግባት ሞክር፡፡ ይህን ካደረክ የሁለታቹም ከመንገድ ፍፃሜው መልካም ይሆናል፡፡

💞 #መልካም_ቀን 💞

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
ለራስህ ከንፈርን አትምጠጥ
(“ራስን ማሸነፍ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ)

“ደስተኛነት የምርጫ ጉዳይ ነው … በሕይወቴ ያሳለፍኳቸው ከባባድ ነገሮች ላይ ከማተኮር ይልቅ በየቀኑ እየሆነልኝ ባለው መልካም ነገር ላይ በማተኮር በተቻለኝ መጠን በእያንዳንዱ ቀን መደሰትን እመርጣለሁ … አካላችን ከዚህ በፊት ያሳለፍነው ልምምዳችን ማጠራቀሚያ ቦታ ነው፡፡ ስቃያችንና ደስታችን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በአካላችን ላይ መገለጡ የማይቀር ነው … መነጫነጭ ተይና መልካም መልካሙን መናገር ጀምሪ”፡፡

ስለሆነብህና ስለተበላሸብህ ነገር እያሰብክ ለራስህ ከማዘንና ከንፈርን ከመምጠት እስካልወጣህ ድረስ ወደፊት በማየት ሕይወትን ልታጣጥማት አትችልም፡፡ ለራስህ ከንፈርን በመምጠጥ ራስ-በራስ እያስተዛዘንክ ስትኖር ከሆነብህ ነገር የተነሳ የተበላሸብህን ነገር አልፈህ መሄድ አትችልም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ ከማድረግና ከማግኘት የተከለከልከውን በማሰብ አእምሮህ ሁሉ ስለሚያዝ ከዚያ አልፈህ ልታከናውን ከምትችለው ነገር ላይ አይኖችህ ይጋረዳሉ፡፡

በዓለማችን ውስጥ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ ሰዎች የደረሰባቸውና የተጎዱበት ሁኔታ ካመጣባቸው የስሜት ቁስል መዘዝ በቀላሉ መውጣት ስለሚያስቸግራቸው ከዚህና ከዚያ ሲንገላቱ ይኖራሉ፡፡ አንዳንዶቹ ከዚያ ሁኔታ የመውጫው መላ ስለሚጠፋባቸው ሲሆን ሌሎቹ ግን ለመልቀቅ ፈቃደኝነቱ ስለሌላቸው ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ከራስ-በራስ ኃዘን የመውጣት እርምጃ ራስን በማሸነፍ ውስጥ የሚገኘውን ድል እንድናጣጥም የሚረዳን እውነት መሆኑን ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡

ለራስህ ከንፈርን ትመጣለህ?
ራስህን መዝነው
1. የአንተ ችግር ከሌሎች ሰዎች ችግር ለየት ያለና የከፋ እንደሆነ ታስባለህ?
2. ሁል ጊዜ ክፉ ክፉው እድል እንደሚከተልህ ታስባለህ?
3. እጣ ክፍልህ የችግርና የመከራ እንደሆነ ታስባለህ?
4. የአንተን ችግር ማንም ሰው ሊገነዘበው እንዳልቻለ ይሰማሃል?
5. ማንም ሰው አንተን ለመርዳት እንደማይፈልግና ብቻህን እንደቀረህ ይሰማሃል?
6. ወጣ ብለህ ዘና ከማለት ይልቅ ለብቻህ ሆነህ ስለችግርህ የማስብ ልማድ አለህ?
7. በቀን ውሎህ ውስጥ ከሆነልህ መልካም ነገር ይልቅ የሆነብህን ክፉ ገጠመኝ መናገር ይቀናሃል?
8. ብዙ ሁኔታዎች ፍትሃዊ እንዳልሆኑ ስትናገር ራስህን ታገኘዋለህ?
9. የሌሎች ሰዎች ኑሮ ቀለል እንዳለላቸውና የአንተው ግን ከባድ እንደሆነ ታስባለህ?
10. ለሌላው ሰው የደረሰ እድል ለአንተ እንዳልተሰጠህና እንደተበደልክ ታስባለህ?

ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ በዚህ ምእራፍ ለተጠቀሱት ነጥቦች አስፈላጊ ትኩረት በመስጠት ለውጥን ለማስተናገድ ጥረት አድርግ፡፡

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
Dare to Be

When a new day begins, dare to smile gratefully.

When there is darkness, dare to be the first to shine a light.

When there is injustice, dare to be the first to condemn it.

When something seems difficult, dare to do it anyway.

When life seems to beat you down, dare to fight back.

When there seems to be no hope, dare to find some.

When you’re feeling tired, dare to keep going.

When times are tough, dare to be tougher.

When love hurts you, dare to love again.

When someone is hurting, dare to help them heal.

When another is lost, dare to help them find the way.

When a friend falls, dare to be the first to extend a hand.

When you cross paths with another, dare to make them smile.

When you feel great, dare to help someone else feel great too.

When the day has ended, dare to feel as you’ve done your best.

Dare to be the best you can –

At all times, Dare to be!


❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
ጽኑ ፍላጎት ይኑርህ
(“እይታ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

ለማደግ ከፈለግህ ራስህን ለማሻሻል ጽኑ ፍላጎት ሊኖርህ ይገባል፡፡ ራስን ማሻሻል ማለት ባሉበት ሳይረኩ ከዛሬ ሁኔታ የተሻለ ነገር ውስጥ ለመግባት አስፈላጊውን ነገር ማድረግ ማለት ነው፡፡ የተግባር ጥራትና ውጤት ስለተመኘሁት ብቻ አይመጣም፡፡ በሌላ አባባል የእኔ መሻሻል በቀጥታ ከተግባሬ፣ ከኑሮዬና ከገቢዬ መሻሻል ጋር ግንኙነት አለው፡፡

ብዙ ሰዎች ኑሮአቸው፣ የገቢ ምንጫቸውና የመሳሰሉት ነገሮች እንዲሻሻሉ ይመኛሉ፣ ራሳቸውን ስለማሻሻል ግን አስበውበትም አያውቁም፡፡ አእምሮዬ እንዲሻሻል ማንበብ የግድ ነው፡፡ የገቢ ምንጬ እንዲሻሻል እውቀቴንና ብቃቴን ማሻሻል የግድ ነው፡፡ የእኔነቴና የብቃቴ መሻሻል ዙሪያዬን ሁሉ የማሻሻልና ነገሮችን ለመልካም የመለወጥ ብርታትና ተጽእኖ አለው፡፡ ራስን በማሻሻል የተግባር ስኬት ውስጥ ለመግባት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ ትችላለህ፡፡

1. ማድረግ የምፈልገውንና የሚሳካልኝን አውቄ መተግበር ጀምሬአለሁ?
ማድረግ የሚሳካልህን ነገር ለይተህ እወቀውና በዚያ ዙሪያ መገንባትን ጀምር፡፡ የማይሳካልህ ላይ ከማተኮርና ከመድከም ይልቅ የሚሳካልህ ላይ በማተኮር መገንባት የበለጠ ውጤታማ ያደርግሃል፡፡ ብቃትህንና መድረስ የምትችልበትን ደረጃ በሚሳካልህና በቀላሉ በሚፈስስልህ ሁኔታ እንጂ በሚያቅትህና በሚያታግልህ ነገር አትመዝነው፡፡

2. ይህንን ተግባር ማደግ የሚገባው ደረጃ ድረስ አሳድጌዋለሁ?
የሚሳካልህንና የምትፈልገውን ለይተህ መተግበር ከጀመርክ በኋላ ትኩረትህ ያንን ተግባር ወደ ማሳደግ ይሁን፡፡ በቅጡ ካላዳበርካቸው የትም ከማያደርሱህ ጥቃቅን ችሎታዎች ጋር ብቻ ከምትታገል በአንድ ነገር በሚገባ መብሰል ውጤቱ የላቀ ነው፡፡ ቢያንስ በአንድ ነገር እስከጥጉ የደረሰን እውቀት ለማዳበር ወስን፣ ያንንም ተከታተል፡፡

3. ለእርማት ልቦናዬ ክፍት ነው?
“አውቃለሁ፣ ማንም ሊመክረኝና ሊያርመኝ አይችልም” የሚል አመለካከት ያለው ሰው ራሱን ለኋላ ቀርነት ያቀረበ ሰው ነው፡፡ እኛ ያላየነውን የሚያዩ፣ የማናውቀውን ደግሞ የሚያውቁ በርካታ ሰዎች በዙሪያችን እንዳሉ በማመን ራሳችንን ለእርማት መክፈት ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ ከሌላው የመማር “ቀላልነት” የታላላቅ ሰዎች እይታ ነው፡፡

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
Don't just learn, experience.
Don't just read, absorb.
Don't just change, transform.
Don't just relate, advocate.
Don't just promise, prove.
Don't just criticize, encourage.
Don't just think, ponder.
Don't just take, give.
Don't just see, feel.
Don’t just dream, do.
Don't just hear, listen.
Don't just talk, act.
Don't just tell, show.
Don't just exist, live.

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
የጊዜ ፈተና!
ሰዎችን ጊዜ እንዲፈትናቸው ፍቀዱ!

አንድ የስነ-ልቦና አዋቂ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- “ማንኛውም ሰው ያልሆነውን መስሎ በመኖር ወይም በአስመሳይነት ከሶስትና ከአራት ወራት በላይ የመቆየት አቅም የለውም፡፡ ሰዎች በዚህ ጊዜ ውስጥ እውነተኛ ቀለማቸውንና እናንተን የቀረቡበትን እውነተኛ የመነሻ ሃሳብ አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት መግለጣቸው አይቀርም”፡፡

ሰዎችን ጊዜ እንዲፈትናቸውና እውነተኛ ቀለማቸውን እንዲያወጣው የመፍቀዳችን እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ የእኛ የቤት ስራ ግን መዘንጋት የለብንም፡፡ አንዳንድ ሰዎች እኮ “ጊዜ” የተሰኘው እውነተኛ ፈታኝ የቤት ስራውን በመስራት ሰዎችን ማንነት ቀስ በቀስ ቢገልጥላቸውም እነሱ ግን ያንን ለማየት የሚያስችል ንቃቱም የላቸወም፡፡ ጊዜ እውነቱን ሲያወጣልን ያንን ለማየት የተከፈተና የነቃ አይን ከሌለን ምንም ትርጉም የለውም፡፡

ከሰዎች ጋር ያገናኛችሁ ሁኔታ የፍቅር፣ የንግድም ሆነ ሌላ የአጋርነት ሂደት፣ ምንም ነገር ውስጥ በፍጹም ብችኮላ አትግቡ፡፡ ሰዎቹ ላይ ላዩን የተቀቡት አርቴፊሻል ቀለም እየፈዘዘ ሄዶ እውነተኛው ቀለማቸው እስከሚወጣ ድረስ ልባችሁን ጠብቁ፡፡

የጊዜን እውነተኛ ፈታኝነት ለመጠቀም የሚከተሉትን መርሆች አትዘንጉ . . .

1. የሰዎቹን ንግግርና ተግባር በሚገባ ተከታተሉ፡፡
ለሰዎች ጊዜን ስትሰጡ ንግግራቸውና ተግባራቸው በሚገባ አጢኑ፡፡ ዛሬ የተናገሩትን ነገ ያለመድገማቸውን፣ ታሪካቸው የመለዋወጡንና ተግባራቸው አንድ ወጥ የመሆኑንና ያለመሆኑን በሚገባ ብትመለከቱ ምልክቶችን ማየታችሁ አይቀርም፡፡

2. ካለማቋረጥ ውስጣችሁን አድምጡ፡፡
ከሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት ውስጣችሁ የሚከለከላችሁንና የሆነ የተዛባ ነገር እንዳለ የሚሰማችሁን ነገር በፍጹም አልፋችሁ አትሂዱ፤ በሚገባ እስቡበት፡፡

3. ወጥመድን ለዩ፡፡
በዚህ አውድ መሰረት “ወጥመድ” ማለት አንድ ነገር ትክክል እንዳልሆነ እያወቃችሁት ነገር ግን ሰውየው ከሚያሳያችሁ የሚጠቅም የሚመስል ሁኔታ የተነሳ አልፋችሁ ስትሄዱና በጓጓችሁለት ነገር ምክንያት ስህተቱን ከማየት ስትጋረዱ ነው፡፡

4. የውሳኔ ሰዎች ሁኑ፡፡
አንድ ግንኙነት ወይም መንገድ እንዳማያዛልቃችሁ አውቃችሁ ሳለ ነገር ግን ከተለያዩ ጥቅሞች ወይም ዋጋ የሚያስከፍል ሁኔታ የተነሳ ከውሳ እንዳትገቱ መጠንከር አስፈላጊ ነው፡፡ ምን ያህል ብልሆች ብንሆንም የውሳኔ ሰዎች ካልሆንን ከመሳት አናመልጥም፡፡

Dr Eyob Mamo

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
አስባችሁታል🤔🤔
#የሚከራይ_ቤት_አለ
#እንጀራ_እንሸጣለን
ተብሎ በየአንዳንድ የቤት አጥር ላይ እንደሚለጠፈው ሁሉ
#እንቅልፍ_እንሸጣለን
#ሰላም_እንሸጣለን
#ደስታ_እንሸጣለን
ተብሎ ቢፃፍ ኖሮ የህይወት ስርዓትስ እንደዛ ቢሆን ኖሮ ምን እንሆን ነበር?? እስኪ አስቡት #እንቅልፍን ምንከራይ ቢሆን ወይም በስልካችሁ ላይ እንደምትሞሉት ካርድ ወይም ደግሞ (package)
#እለታዊ
#ሳምንታዊ
#ወርሃዊ እንዲሁም
#አመታዊ
እንደሚባለው ልክ እንደዛ #እንቅልፍንም እየገዛን ምንኖር ቢሆን ኖሮ 🙆‍♂🙆‍♂ እባክህ ጓደኛዬ የእንቅልፍ package አለቀ ለማታ ያስፈልገኛል እስኪ ግዛልኝ አይነት ነገር ቢሆን ህይወታችን #OMG አልቀን ነበር
.
.
.
.
.
ግን እንደዛ አይደለም በጭራሽ 🙅‍♂🙅‍♂🙅‍♂ ምን ያህሎቻችሁ ግን እግዚአብሔርን ስለዚህ ነገር አመስግናችሁታል ?

#የፈጠርከኝ_አምላክ_ሆይ_ስለ.........አመሰግናለሁ 🙏🙏

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
#ሀ_ሲ_ኔ
በአስደናቂ ለውጦች የተሞላ መልካም ቀን ይሁንላችሁ ❤️

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀


ㅤ ♡ ❍ㅤ     ⎙       ⌲
         ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ
"አሁን ላይ ምን ዓይነት ለውጥ እናስብ ? ካልን ምላሹ ይኸው ነው። ከመማር ከማስተዋልና ከማመሳሰል በሚወለድ ብይን ፤ ሰው ትልቅ ሰው የሚሆነው በሌሎች ልብ ውስጥ መቆየት እስከቻለ ብቻ መሆኑን እስክናምን ድረስ በሀሳቦች መብሰልሰል ግድ ነው። ለራስ ብቻ ወይም ወደ  ራስ ብቻ በሚመለከት አስተሳሰብ እንኳን ሀገርን እራስንም ወደ መለወጥ አያስኬድም። "

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
                                         

ㅤ       ♡         ❍ㅤ     ⎙       ⌲
         ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ
"የሰው ልጅ የልምምድ ውጤት ነው። በልምምድ እንጂ በመወለድ ብቻ ሰው መሆን አይችልም። ከማፍቀር እስከ መቆርቆር ይለማመዳል። ማፍቀርን ያህል ነገር እንኳ አውቆ አይወለድም ። እርሱን ብቻ አይደለም፤ መጥላትን ሳይቀር ይለማመዳል። ከማወቅ እስከ መናቅ፣ ከመወለድ እስከ መታነቅ፣ ከመድቀቅ እስከ ማድቀቅ፣ ከመጋባት እስከ መፋታት፣ ከስንፈት እስከ ጥረት...ከመርመጥመጥ እስከ መፈርጠጥ፣ ከቆመጥ እስከ ነፍጥ..ተለማምዶት እንጂ ተሰጥቶት አይደለም። ከክህደት እስከ እምነት ካልተለማመደ አይችልም። ከራሱ ያገኘው ማንነት የለውም። ....በመለማመድ አሁን የደረሰበትን እንጂ ወደፊት የሚሄድበትን ማንም ሊያውቅ አይችልም።"

📖ክቡር ድንጋይ

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀

ㅤ ♡ ❍ㅤ     ⎙       ⌲
         ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ
#Photo_of_the_day

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀

ㅤ ♡ ❍ㅤ     ⎙       ⌲
         ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ
"በዓለም ላይ ከሁሉ አስከፊው እስር ቤት የሰው አእምሮ ባመነጨው ውሸት ሲጠፈርና በዚያ ቀንበር ውስጥ ሲኖር ነው።

እውነተኛ ነፃነት የኅሊና ነፃነት ነው። የኅሊና ነፃነት ደግሞ እውነትን በማወቅና በመኖር ነፃ ከወጣ አእምሮ ብቻ የሚገኝ ፀጋ ነው።"

📖የተቆለፈበት ቁልፍ

❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
❀꧁@ThinkBig1 Channel꧂❀
                          
ㅤ      ♡         ❍ㅤ     ⎙       ⌲
         ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ
2024/11/19 21:41:56
Back to Top
HTML Embed Code: