ኒጀር በፈረንሳዩ ድርጅት ኦራኖ ስር የነበረውን የዩራኒየም ድርጅት ሙሉ ለሙሉ በመንግስት ስር ልታስገባው ነው።
ኒጀር በፈረንሳዩ ኦራኖ ስር ያለውን የሶማይር የዩራኒየም ድርጅት ከሚመረተው በላይ ዩራኒየም በድርሻ መልክ እየወሰደ ነው ብላ የከሰሰች ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዲሆን እንደምታደርገውም አስታውቃለች።
ሶማይር በፈረንሳዩ ድርጅት ኦራኖ እና በመንግስት ድርጅቱ ሶፓሚን ጥምረት የተመሰረተ ድርጅት ሲሆን በሀገሪቱ ባለው ብቸኛው የዩራኒየም ማውጫ ላይ የሚሰራ ተቋምም ነበር።
ኒጀር ከ439 ሺህ ቶን በላይ የዩራኒየም ክምችት እንዳላት ሲገመት ይህም ከአለም ምርጥ 10 ውስጥ ያስገባታል።
በ2022 ኒጀር ከ2020 ቶን በላይ ዩራኒየም ያመረተች ሲሆን ይህም የአለም ምርት 5 በመቶ ይሆናል።
አብዛኛው ምርቷን በኒውኪሊየር ኃይል ላይ ጥገኛ ለሆነችው ፈረንሳይ ታቀርብ ነበር።
እንደ ኒጀር፣ ማሊ እና ቡርኪናፋሶ ባሉ የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት በቅርብ አመታት የመፈንቅለ መንግስት ከተፈፀመ በኋላ በሃገራቱ እና በቀድሞ ገዢዋ ፈረንሳይ መካከል ጥሩ ግንኙነት የሌለ ሲሆን ሃገራቱ ትኩረታቸውን ወደ ሩሲያ በማድረግ ላይም ይገኛሉ።
Source: AP
@TikvahethMagezine

❤107👏24👍17🔥7👎1
#Update
የእስራኤል እና የኢራን ጦርነት ከተጀመረ 9ኛ ቀኑን ይዟል።
በ9ኛ ቀን ከተሰሙ ዋና ዋና ነገሮች መካከል፦
⚫ እስራኤል 3 የኢራን ጀነራሎችን መግደሏን እና የኢስፋህን የኒውኪሊየር ጣቢያ ላይ ጥቃት መፈፀሟን ገልጻለች። የጦርነቱ ጊዜ ያልተገደበ መሆኑን የእስራኤል አመራሮች አንስተው ሲናገሩ የእስራኤል ጦርም እስራኤላውያን ለትልቅ ተልዕኮ እንዲዘጋጁ አሳስቧል።
⚫ የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ አሜሪካ በጦርነቱ ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ስትሳተፍ ነበር ሲሉ ገልጸዋል። በአሜሪካ "የዲፕሎማሲ ክህደት" ተፈፅሞብናል ያሉት ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላ አሜሪካን ለማመን እንደሚቸገሩ ገልፀዋል።
⚫ ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት በሁለቱ ሃገራት መካከል ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ኢስፋህን በእስራኤል ጥቃት የተፈፀመበት ሥሦስተኛው የኢራን የኒውኪሊየር ጣቢያ መሆኑን አስታውቋል።
⚫ እስራኤል በኢራን ዋነኛ የነዳጅ አምራች አካባቢ በሆነው ኩዜስታን ላይ ጥቃት አድርሳለች። ጥቃቱ ወታደራዊ ኢላማዎችን ኢላማ ማድረጉን የእስራኤል ጦር አስታውቋል።
⚫ የኢራን የጤና ሚኒስትር ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ 430 ኢራናውያን መሞታቸውን እና 3000 የሚሆኑት መጎዳታቸውን አስታውቋል።
⚫ በእስራኤል ጥቃት ታባታቢይ አይዛር የተባለ የኒውኪሊየር ሳይንቲስት መገደሉን ኢራን ይፋ አድርጋለች። አይዛር ከባለቤቱ ጋር በቤቱ ሲገደል እስራኤል ከጦርነቱ መጀመር ወዲህ የገደለችው ስድስተኛው የኢራን የኒውኪሊየር ሳይንቲስት ሆኗል።
⚫ እስራኤል ለሊቱን ከኢራን ከ40 በላይ ድሮኖች እንደተላኩባት እና ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የአየር መከላከያዋን ጥሶ እንደገባ ገልፃለች። የድሮን ጥቃቱም በሰሜናዊ እስራኤል ጉዳት ማድረሱ ሲነገር በትናንቱ የሃይፋ የሚሳኤል ጥቃት የተጎዱ ሰዎች ቁጥር 31 ደርሷል።
⚫ እስራኤል ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ 99 በመቶ የሚሆኑትን ከኢራን የተላኩባት ድሮኖች አክሽፌያለሁ ብላለች። እስራኤል የአየር መከላከሏ ከ470 በላይ የኢራን ድሮኖችን መጣሏን ነው የገለጸችው።
⚫ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በተደጋጋሚ ለእስራኤል ኢራን የኒውኪሊየር የጦር መሳሪያ የመታጠቅ ፍላጎት እንደሌላት ነግሬያለሁ ማለታቸው ተነግሯል። ፕሬዚዳንት ፑቲን ሩሲያ የኢራንን ሰላማዊ የኒውኪሊየር ፕሮግራም ትደግፋለች ፤ እንደዛ የማድረግም መብት አላት ነው ያሉት።
⚫ አሜሪካ በርካታ የዩኤስ ቢ-2 ቦምቦችን ዛሬ ምሽት ከኦክላሆማ ከሚገኘው ከዋይትማን አየር ሃይል ጣቢያ ወደ ምዕራብ ማጓጓዟን CNN ገልጿል። ይህም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወታደራዊ በኢራን ላይ የአየር ጥቃት ለመውሰድ ከወሰኑ ጥቅም ላይ ይውላሉ ተብሎ እንደሆነ ነው የተነገረው።
⚫ የእስራኤል ጦር የኢራን አብዮታዊ ዘብ የቁድስ ኃይል አዛዥ እንዲሁም የኢራን አብዮታዊ ዘብ የፍልስጤም ኃይል መሪ ሰዒድ ኢዛዲን መግደሉንም አስታውቋል። የኢራን አብየታዊ ዘብ አመራሮቹ ስለመገደላቸው በይፋ ያለው ነገር የለም።
Source: CNN, NBC
Photo : Reuters
@TikvahethMagazine
የእስራኤል እና የኢራን ጦርነት ከተጀመረ 9ኛ ቀኑን ይዟል።
በ9ኛ ቀን ከተሰሙ ዋና ዋና ነገሮች መካከል፦
Source: CNN, NBC
Photo : Reuters
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤181👎34🕊17👏8🤔5🤣2🔥1
አሜሪካ በይፋ ወደ ጦርነቱ ገብታለች!
አሜሪካ በኢራን የሚገኙ የኑውክሌር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች። የአሜሪካው ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥቃቱን "በጣም ውጤታማ" ሲሉ ነው የገለጹት።
ዋና አላማችን የኢራንን የኒውክለር መሰረተ ልማት ማጥፋት ነው ያሉት ፕረዚዳንቱ "በአለም ቁጥር አንድ የሽብር ደጋፊ መንግስት የሚፈጥረውን የኒውክሌር ስጋት እናስቆማለን" ሲሉ ነው የተናገሩት።
ፕረዚዳንቱ በሰጡት መግለጫ ጠ/ሚ ኔታኒያሁን ያመሰገኑ ሲሆን "ጥሩ የቡድን ሥራ ሰርተናል ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነት ጥምረት ታይቶ አይታወቅም ነበር" ብለዋል።
"ዛሬ ማታ ያደረግነውን ሊሰራ የሚችል ምንም አይነት ወታደራዊ ኃይል በዓለም ውስጥ የለም፤ ለዚህ የሚቀርብ እንኳን የሚያደርግ የለም" ሲሉ በመግለጫቸው አንስተዋል።
Photo : ዋይትሀውስ / ጥቃቱን ካዘዙበት ክፍል (Situation Room)

👎175👏82❤66🕊27🤔7🤣4👍3🤬1
#Quate : "ወደ ኑክሌር ጦርነት እየሄድን ነው!
ውጤታማ ዓለምአቀፍ አመራር የሚያስፈልግበት ጊዜ አሁን ነው!
አሁን ያለው ቀውስ አንድነትን እና ቆራጥ እርምጃ መሰረታዊ ጉዳይ ነው።
ሰላም ከሁሉ የተሻለ መድኃኒት ነው!"
- የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም

❤185👎41👍18😢9🕊7🤣3
#IAEA
በኢራን የፎርዶን ጨምሮ በሦስት የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች እስካሁን ከጣቢያ ውጭ የጨረር መጠን መጨመር እንዳልተመዘገበ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ድርጅት አስታውቋል።
@TikvahethMagazine
በኢራን የፎርዶን ጨምሮ በሦስት የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች እስካሁን ከጣቢያ ውጭ የጨረር መጠን መጨመር እንዳልተመዘገበ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ድርጅት አስታውቋል።
@TikvahethMagazine
🙏86❤19🤔19👏12🕊5😢4
"አሜሪካ ከኢራን ጋር አደገኛውን ጦርነት ጀምራለች" - የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አሜሪካ የኢራንን የኒውኪሊየር መሰረተ ልማቶች በማጥቃት አደገኛውን ጦርነት ጀምራለች ብሏል።
በተጨማሪ ሚኒስቴሩ "አለም አሜሪካ በዲፕሎማሲያዊ ንግግር መሃል ዲፕሎሚሲን እንደካደች መርሳት የለበትም " በማለት እስራኤልን "ዘር ጨፍጫፊ እና ህግ የማታውቅ" ሲል ከሷታል።
የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አክሎም አሜሪካ የፈፀመችው ተግባር የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ያለ ሲሆን "ለተፈፀመው ወንጀል እና ለሚመጣው አደጋ የአሜሪካ መንግስት ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል" ብሏል።
ሚኒስቴሩ ኢራን የአሜሪካን ወረራ በአስፈላጊው መንገድን የመከላከል ሙሉ መብት አላት ብሏል።
Source: CNN

❤104🤣28👍11🕊9🤝3👎2😢2👏1
አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት ለመፈፀም የB-2 የጦር አውሮፕላኖችን መጠቀሟ ተገለፀ።
በተጨማሪ አሜሪካ በጥቃቱ በአለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 30,000 ፓውንድ የሚመዝነውን የ'Massive ordinance Penetrator' ቦምብ ጥቅም ላይ ማዋሏ ተዘግቧል።
የB-2 አውሮፕላኖች 30,000 ፓውንድ(15 ቶን) የሚመዝኑ ሁለት 'Massive ordinance Penetrator' መሸከም ሲችሉ ቦምቦቹ የተሰሩት ከምድር በታች በጥልቀት የተሰሩ እንደ ፎርዶው የኒውኪሊየር ጣቢያዎችን ለማውደም ነው።
የአሜሪካን B-2 የጦር አውሮፕላን ውዱ የጦር አውሮፕላን እንደሆነ ሲነገር አንዱን ለመስራትም 2.1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ያስወጣል።
ቦምቦቹ ከምድር በታች እስከ 61 ሜትር ያለን ነገር እና 18 ሜትር ውፍረት ያለውን ኮንክሪት ጥሰው መምታት ይችላሉ።
የB-2 ቦምብ ተሸካሚ አውሮፕላን በራዳር ውስጥ የመግባት ዕድሉ በጣም አነስተኛ እንደሆነም ተገልጿል።
Source: ABC

❤145👎47🕊20😢6👏5🔥3🤯2
አሜሪካ በኢራን ላይ የአየር ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ሀገራት ምን አሉ ?
🇬🇧 የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ኢራን በአሜሪካ ጥቃት ከተከፈተባት በኋላም ኢራን ወደ ድርድር እንድትመለስ ጠይቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የኢራን የኒውኪሊየር ፕሮግራም ለአለም ስጋት ነው ፤ ኢራን በፍፁም የኒውኪሊየር የጦር መሳሪያ መታጠቅ የለባትም" በማለት "አሜሪካም ያንን ስጋት ለማስወገድ እርምጃ ወስዳለች" ብለዋል።
🇮🇶 የኢራቅ የመንግስት ቃለ አቀባይ ባሲም አላዋዲ የአሜሪካ ጥቃት ለቀጣናው ትልቅ ስጋት ነው ብለዋል። የአሜሪካ እርምጃ ግጭቱን ያባብሰዋል ያለችው ኢራቅ አሁንም የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ ጠይቃለች።
🇺🇳 የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግጭቱ ከቀን ወደ ቀን ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ ነው በማለት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ ገልፀዋል።
🇱🇧 ሌባኖስ በጠቅላይ ሚኒስትሯ ናዋፍ ሳላም በኩል ባወጣችው መግለጫ ሃገራቸው እየተካሄደ ባለው ቀጣናዊ ጦርነት መሳተፍ አትፈልግም ብለዋል።
☃️ በኢራን እንደሚደገፉ የሚታመኑት ሃማስ እና ሁቲ የአሜሪካን ጥቃት ሲያወግዙ ሁቲ ኢራን ከአሜሪካ እና እስራኤል ጋር በምታደርገው ጦርነት ድጋፉን እንደሚሰጥ ገልጿል።
☃️ የሁቲ የፖለቲካ ቢሮ ሁሉም የሙስሊም ሃገራት ከእስራኤል እና አሜሪካ በተቃራኒ እንዲሆኑም ጠይቋል።
በተጨማሪ፦
አሜሪካ በጦርነቱ እንዳትሳተፍ ሲጠይቁ የነበሩት ኃያላኑ ሩሲያ እና ቻይና እስካሁን በይፋ ያሉት ነገር የለም።
ሌላኛዋ የኢራን አጋር ሰሜን ኮሪያም ነገሩን ከዳር ቆማ እየተመለከተች ሲሆን የእነዚህ ሃገራት ተሳትፎ ምን እንደሚሆን እየተጠበቀ ይገኛል።
@TikvahethMagazine
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የኢራን የኒውኪሊየር ፕሮግራም ለአለም ስጋት ነው ፤ ኢራን በፍፁም የኒውኪሊየር የጦር መሳሪያ መታጠቅ የለባትም" በማለት "አሜሪካም ያንን ስጋት ለማስወገድ እርምጃ ወስዳለች" ብለዋል።
በተጨማሪ፦
አሜሪካ በጦርነቱ እንዳትሳተፍ ሲጠይቁ የነበሩት ኃያላኑ ሩሲያ እና ቻይና እስካሁን በይፋ ያሉት ነገር የለም።
ሌላኛዋ የኢራን አጋር ሰሜን ኮሪያም ነገሩን ከዳር ቆማ እየተመለከተች ሲሆን የእነዚህ ሃገራት ተሳትፎ ምን እንደሚሆን እየተጠበቀ ይገኛል።
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤127🕊21🤔14🤣8👍3
"ሰላማዊ የኒውክሌር ፕሮግራሜን አላቋርጥም" ኢራን
የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ባዜሽኪያን አገራቸው የኒውክሌር እንቅስቃሴዋን "በምንም አይነት ሁኔታ" እንደማታቆም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ፕረዚዳንቱ ይህን የተናገሩት ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት ነው።
ቴህራን ለውይይት እና ለትብብር ክፍት መሆኗን አንስተው፤ ሰላማዊ የኒውክሌር ፕሮግራሟን ለማስቆም የሚደረገውን ማንኛውንም ጫና ግን ውድቅ እንደምታደርግ መግለጻቸውን የኢራን የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

❤139🤣46👍28🕊10👎9👏6😢4🤔2🔥1
#Coffee ☕️
በዓለም አቀፉ የቡና ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ የታየ ዝቅተኛው የቡና ዋጋ ተመዝግቧል።
ለዋጋው መቀነስ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ የአረቢካ ቡናን በዋነኝነት በምታመርተው ብራዚል በቂ ዝናብ በመኖሩ ካለፈው አመት የተሻለ የቡና ምርት በመጠበቁ ነው።
የቡና ዋጋ ባለፈው ሚያዝያ ወር በፓውንድ ሪከርድ የሆነ 4.11 ዶላር ደርሶ እንደነበር ሲታወስ ቡና ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ዋጋው በሚቀጥሉት 15 ወራት እየቀነሰ እንደሚቀጥል መላምታቸውን አስቀምጠዋል።
የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር በበኩሉ በሪፖርቱ ቡና ላኪዎች ሊደናገጡ አይገባም ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ ምን አሉ?
"ወጣው መረጃ የአገራችን ቡና ላኪዎች ሊደናገጡ አይገባም። የዋጋው ልዩነት የተለመደ እና በየጊዜው የሚፈጠር ነው።
የዋጋው ማሽቆልቆል የሚጠበቅ ነው። አንድ ሀገር ገና ሳታመርት የቡናው ዛፍ በአበባ ላይ እያለ የሚቀጥለው ምርት ይሄን ያክል ይሆናል ተብሎ ይገመታል።
የቡና ዛፍ ደግሞ ሁለት ሶስት ጊዜ ያብባል። በዚህ ሪፖርት መደናገጥ አያስፈልግም፣ ሪፖርቱም ከአንድ ወር በኋላ ይቀየራል።
በሪፖርቱ እየተጠቀሱ ያሉት ግምቶች የቆዩ ወይም የተለመዱ ናቸው። በሪፖርቱ በእጥፍ ይጨምራል ስለተባለ ይሆናል ማለት አይደለም፣ እንደዚህ ያሉ መረጃዎች የገበያውን ዋጋ አይወስኑትም።
የሀገራችን ቡና ላኪዎች በዚህ መረጃ መደናገጥ የለባቸውም፤ ሪፖርቱ ከወጣ በኋላ ዋጋው ይቀንሳል፣ ይጨምራል፣ ይህ የሚረብሽ አይደለም እስካሁንም የነበረ እና የተለመደ ነው፣ መረጃው መውጣቱ ለውጥ አያመጣም" ሲሉ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

❤59👍19🤣15🕊4👎3😢1
#Update
የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አባስ አራጋቺ አሜሪካ በሃገራቸው የፈፀመችውን ጥቃት በተመለከተ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር ነገ ወደ ሞስኮ እንደሚያመሩ ተናግረዋል።
ፑቲን ትናንት በሰጡት መግለጫ ሩሲያ የኢራንን ሰላማዊ የኒውኪሊየር ፕሮግራም እንደምትደግፍ መግለፃቸው የሚታወስ ሲሆን ሩሲያ አሜሪካ ኢራንን እንዳታጠቃም ስታስጠነቅቅ ቆይታለች።
ሩሲያ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ የአሜሪካ ጥቃት ኃላፊነት የጎደለው እና የዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ብላለች።
Source: TRT, Anadolu

❤155🤣45👍24🕊6😢3🤔2🤝1
የአሜሪካ ም/ፕረዚዳንት የኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋት መጥፊያዋ እንደሚሆን ገለጹ።
የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ሃገራቸው አሜሪካ ወደ ጦርነት ውስጥ የገባችው ከኢራን ጋር ሳይሆን ከኒውኪሊየር ፕሮግራሟ ጋር እንደሆነ ተናግረዋል።
በ100% መተማመን የአሜሪካ ጥቃት የኢራንን የኒውኪሊየር ጣቢያዎች አጥፍቷል ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ "ወደ እንደዚህ አይነት የደህንነት መረጃዎች መግባት አልፈልግም፤ የአሜሪካ የምሽቱ ጥቃት ግን የኢራንን ኒውኪሊየር የመታጠቅ አቅም በእጅጉ አዘግይቶታል" ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምሽቱ ጥቃት የኢራን የኒውኪሊየር ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን ሲገልፁ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ብቻ መግለፃቸው ይታወሳል።
ኢራን አሜሪካን ካጠቃች ከባድ ኃይል እንደሚጠብቃት የተናገሩት ም/ፕረዚዳንቱ " እኛ ንፁሃንን ኢላማ አላደረግንም፤ ከሶስቱ የኒውኪሊየር ጣቢያዎች ውጪ እንኳን ባለ ወታደራዊ ቦታ ላይ ጥቃት አልፈፀምንም" ብለዋል።
ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ ያለውን የመርከብ እንቅስቃሴ ልትረብሽ ትችላለች በሚል የተጠየቁት ጄዲ ቫንስ "እሱ ለኢራን መጥፊያዋ ይሆናል" ሲሉ መልሰዋል።
ቫንስ " ኢራናውያን በጦርነት ጥሩ አይደሉም፤ በፕሬዚዳንቱ የተሰጣቸውን የሰላም ዕድል ሊጠቀሙ ይገባል " ብለዋል።
SOURCE: NBC NEWS

❤119🤣70👎14🕊6🔥5👏4👍2
ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ለመዝጋት የደኅንነት ምክር ቤቱን ውሳኔ እየጠበቀች ነው።
የአለም 20 በመቶ የነዳጅ ምርት የሚቀርብበትን የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲዘጋ የኢራን ፓርላማ ሲወስን የደኅንነት ምክር ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ እየተጠበቀ እንደሚገኝ የኢራን የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ የጦርነቱ ሂደት ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመራ ሲሆን ስለ ሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት የተጠየቁት የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም ብዙ አማራጮች በእጃችን አለ፤ ሊሆን ይችላል ብለው መልሰዋል።
የአያቶላህ አሊካሚኒ ከፍተኛ አማካሪም ሃገራቸው በአሜሪካ በተጠቃች በኋላ ኢራን ሰርጡን መዝጋት እንዳለባት እና የአሜሪካን መርከብ ማጥቃት እንዳለባት ሲገልፁ ነበር።
የምክር ቤቱ ውሳኔ የአለምን ኢኮኖሚ በተለየ ሁኔታ የነዳጅን ዋጋ ሊያሻቅብ የሚችል ሲሆን የሚሰጠው ውሳኔ ይጠበቃል።

❤140🤣26🕊12🤔10🔥7🤝6👎4👏4🤯2
#Quate "ከመካከለኛው ምስራቅ በተለይ ከኢራን አስደንጋጭ ዜናዎችን እየሰማን ነውጦርነት ቁስልን ከመፍጠር ውጪ መፍትሄ አያመጣም።
በየቀኑ ብዙ ህዝብ እየተሰቃየ ነው። በተለይ በጋዛ እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ሰዎች ከምንጊዜውም በላይ እርዳታ በሚሹበት ሰዓት ተረስተዋል።
ዛሬ ከየትኛውም ጊዜ በላይ የሰው ልጅ እያለቀሰ ነው። ጦርነቱ የማይሽር ጠባሳ ከመጣሉ በፊት ሁሉም የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጦርነቱ እንዲቆም መስራት ይገባል።
ዲፕሎማሲ መሳሪያዎችን ዝም እንደሚያስብል ተስፋቸውን በማስቀመጥ ሃገራት መፃኢያቸውን ደም በማፍሰስ ሳይሆን በሰላም መገንባት አለባቸው።"
ፖፕ ሊዮ 14ኛ - አዲሱ የሮማን ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ

❤147👎26🕊22🙏6👍5🤣5🤷♀1🔥1
#Update
አሜሪካ 'Midnight Hammer' ብላ በሰየመችውና በኢራን ላይ በፈፀመችው የለሊቱ ጥቃት እስካሁን ምን እናውቃለን ?
አጠቃላይ የኦፕሬሽኑ መረጃ
🕒 ኦፕሬሽኑ የ25 ደቂቃ እርዝማኔ ነበረው።
✈️ በጥቃቱ አሜሪካ 125 የጦር አውሮፕላኖችን ተጠቅማለች።
🛵 በጥቃቱ አሜሪካ 7 B-2 የተሰኙ የከባድ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን ተጠቅማለች።
🚀 በጥቃቱ አሜሪካ በኢራን ላይ 14 GBU-57 የተሰኙ እያንዳንዳቸው 30,000 ፓውንድ የሚመዝኑ ቦምቦችን ጥላለች። እነዚህ ቦምቦች በጥቅም ላይ ሲውሉም በአለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
🎯75 ኢላማቸውን የማይስቱ ተተኳሾች ተተኩሰዋል።
🚢 በጥቃቱ የአሜሪካ የጦር መርከቦች ተሳትፈዋል።
የኦፕሬሽኑ አፈፃፀም
የኦፕሬሽኑ አላማ የኢራንን የኒውኪሊየር መሰረተ ልማቶች ማውደም መሆኑ ሲነገር ጥቂት ቁልፍ ሰዎች ብቻ ስለ ኦፕሬሽኑ እንዲያውቁት ተደርጓል።
አሜሪካ በኢራን ላይ የአየር ድብደባ ከመፈፀሟ በፊት የአሜሪካ የጦር መርከቦች በኢስፋህን በሚገኙ መሰረተ ልማቶች ላይ የክሩዝ ሚሳኤል ጥቃት አድርሰዋል።
ኢራንን ለማዘናጋት በርከት ያሉ የB-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ ምዕራብ እንዲበሩ ሲደረግ ከቦምብ ጣይ አውሮፕላኖቹ ጋር ነዳጅ የሚሞሉ የጦር ጀቶችን እና ተዋጊ ጀቶች ወደ ኢራን የአየር ክልል እንዲገቡ ተደርገዋል።
ዋናዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ ቦታው ለመድረስ 18 ሰዓት በርረዋል።
አሜሪካ የጦር አውሮፕላኖቿን ወደ ኢራን የአየር ክልል ካስገባች በኋላ በከፍተኛ ፍጥነት እንዲበሩ እና በትልቅ ከፍታ እንዲበሩ አድርጋለች።
የአሜሪካ B-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ሁለት 30,000 ፓውንድ የሚመዝነውን ቦምብ በመጀመሪያ ዙር በፎርዶው ጣቢያ የጣሉት ሲሆን በሶስቱ ጣቢያዎች ጥቃቶች የተፈፀሙት በ25 ደቂቃዎች ውስጥ ነው።
በኦፕሬሽኑ ወቅት ከኢራን የሚኖርን ጥቃት ለመከላከል በርካታ የጦር አውሮፕላኖች ቦምብ ጣዩን አውሮፕላን ቢያጅቡም ከኢራን ምንም አይነት እርምጃ ሳይወሰድ አውሮፕላኖቹ የኢራንን የአየር ክልል ለቀው ወጥተዋል።
ፔንታጎን ይህንን የተደራጀ እና ዘመናዊ ኦፕሬሽን መፈፀም የምትችለው አሜሪካ ብቻ ነች ሲል ገልጿል።
@TikvahethMagazine
አሜሪካ 'Midnight Hammer' ብላ በሰየመችውና በኢራን ላይ በፈፀመችው የለሊቱ ጥቃት እስካሁን ምን እናውቃለን ?
አጠቃላይ የኦፕሬሽኑ መረጃ
🎯75 ኢላማቸውን የማይስቱ ተተኳሾች ተተኩሰዋል።
የኦፕሬሽኑ አፈፃፀም
የኦፕሬሽኑ አላማ የኢራንን የኒውኪሊየር መሰረተ ልማቶች ማውደም መሆኑ ሲነገር ጥቂት ቁልፍ ሰዎች ብቻ ስለ ኦፕሬሽኑ እንዲያውቁት ተደርጓል።
አሜሪካ በኢራን ላይ የአየር ድብደባ ከመፈፀሟ በፊት የአሜሪካ የጦር መርከቦች በኢስፋህን በሚገኙ መሰረተ ልማቶች ላይ የክሩዝ ሚሳኤል ጥቃት አድርሰዋል።
ኢራንን ለማዘናጋት በርከት ያሉ የB-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ ምዕራብ እንዲበሩ ሲደረግ ከቦምብ ጣይ አውሮፕላኖቹ ጋር ነዳጅ የሚሞሉ የጦር ጀቶችን እና ተዋጊ ጀቶች ወደ ኢራን የአየር ክልል እንዲገቡ ተደርገዋል።
ዋናዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ ቦታው ለመድረስ 18 ሰዓት በርረዋል።
አሜሪካ የጦር አውሮፕላኖቿን ወደ ኢራን የአየር ክልል ካስገባች በኋላ በከፍተኛ ፍጥነት እንዲበሩ እና በትልቅ ከፍታ እንዲበሩ አድርጋለች።
የአሜሪካ B-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ሁለት 30,000 ፓውንድ የሚመዝነውን ቦምብ በመጀመሪያ ዙር በፎርዶው ጣቢያ የጣሉት ሲሆን በሶስቱ ጣቢያዎች ጥቃቶች የተፈፀሙት በ25 ደቂቃዎች ውስጥ ነው።
በኦፕሬሽኑ ወቅት ከኢራን የሚኖርን ጥቃት ለመከላከል በርካታ የጦር አውሮፕላኖች ቦምብ ጣዩን አውሮፕላን ቢያጅቡም ከኢራን ምንም አይነት እርምጃ ሳይወሰድ አውሮፕላኖቹ የኢራንን የአየር ክልል ለቀው ወጥተዋል።
ፔንታጎን ይህንን የተደራጀ እና ዘመናዊ ኦፕሬሽን መፈፀም የምትችለው አሜሪካ ብቻ ነች ሲል ገልጿል።
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤230👎49🤣35🕊20👏12🤔5🔥4🤷♂3🤝3💯1