#Update
አሜሪካ 'Midnight Hammer' ብላ በሰየመችውና በኢራን ላይ በፈፀመችው የለሊቱ ጥቃት እስካሁን ምን እናውቃለን ?
አጠቃላይ የኦፕሬሽኑ መረጃ
🕒 ኦፕሬሽኑ የ25 ደቂቃ እርዝማኔ ነበረው።
✈️ በጥቃቱ አሜሪካ 125 የጦር አውሮፕላኖችን ተጠቅማለች።
🛵 በጥቃቱ አሜሪካ 7 B-2 የተሰኙ የከባድ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን ተጠቅማለች።
🚀 በጥቃቱ አሜሪካ በኢራን ላይ 14 GBU-57 የተሰኙ እያንዳንዳቸው 30,000 ፓውንድ የሚመዝኑ ቦምቦችን ጥላለች። እነዚህ ቦምቦች በጥቅም ላይ ሲውሉም በአለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
🎯75 ኢላማቸውን የማይስቱ ተተኳሾች ተተኩሰዋል።
🚢 በጥቃቱ የአሜሪካ የጦር መርከቦች ተሳትፈዋል።
የኦፕሬሽኑ አፈፃፀም
የኦፕሬሽኑ አላማ የኢራንን የኒውኪሊየር መሰረተ ልማቶች ማውደም መሆኑ ሲነገር ጥቂት ቁልፍ ሰዎች ብቻ ስለ ኦፕሬሽኑ እንዲያውቁት ተደርጓል።
አሜሪካ በኢራን ላይ የአየር ድብደባ ከመፈፀሟ በፊት የአሜሪካ የጦር መርከቦች በኢስፋህን በሚገኙ መሰረተ ልማቶች ላይ የክሩዝ ሚሳኤል ጥቃት አድርሰዋል።
ኢራንን ለማዘናጋት በርከት ያሉ የB-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ ምዕራብ እንዲበሩ ሲደረግ ከቦምብ ጣይ አውሮፕላኖቹ ጋር ነዳጅ የሚሞሉ የጦር ጀቶችን እና ተዋጊ ጀቶች ወደ ኢራን የአየር ክልል እንዲገቡ ተደርገዋል።
ዋናዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ ቦታው ለመድረስ 18 ሰዓት በርረዋል።
አሜሪካ የጦር አውሮፕላኖቿን ወደ ኢራን የአየር ክልል ካስገባች በኋላ በከፍተኛ ፍጥነት እንዲበሩ እና በትልቅ ከፍታ እንዲበሩ አድርጋለች።
የአሜሪካ B-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ሁለት 30,000 ፓውንድ የሚመዝነውን ቦምብ በመጀመሪያ ዙር በፎርዶው ጣቢያ የጣሉት ሲሆን በሶስቱ ጣቢያዎች ጥቃቶች የተፈፀሙት በ25 ደቂቃዎች ውስጥ ነው።
በኦፕሬሽኑ ወቅት ከኢራን የሚኖርን ጥቃት ለመከላከል በርካታ የጦር አውሮፕላኖች ቦምብ ጣዩን አውሮፕላን ቢያጅቡም ከኢራን ምንም አይነት እርምጃ ሳይወሰድ አውሮፕላኖቹ የኢራንን የአየር ክልል ለቀው ወጥተዋል።
ፔንታጎን ይህንን የተደራጀ እና ዘመናዊ ኦፕሬሽን መፈፀም የምትችለው አሜሪካ ብቻ ነች ሲል ገልጿል።
@TikvahethMagazine

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤230👎49🤣35🕊20👏12🤔5🔥4🤷♂3🤝3💯1
በሶሪያ በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት የ22 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ ደዌላ ሰፈር ውስጥ በሚገኘው ቅዱስ ኤሊያስ ቤተክርስትያን ላይ አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 22 ሰዎች ሲሞቱ ከ63 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።
ጥቃቱ የተፈጸመው በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ሲሆን እሁድ በጸሎት ሰዓት ምዕመናን ባሉበት ነው።
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በሰጡት መግለጫ ፦
"ISIS አሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት ያለው አጥፍቶ ጠፊ በዋና ከተማው ደማስቆ ደዌላ አካባቢ በሚገኘው የቅዱስ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባት ተኩስ ከከፈተ በኋላ በተቀጣጣይ ፈንጂ ራሱን አጠፋ” ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።
የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል ተሰግቷል።
Source : SANA
Photo : Social Media

😢420❤108💔23🤬18🤔10👍8👎1🤣1🤝1
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ አንድ የ3 ዓመት ህፃንን ጨምሮ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።
በአዲስአበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ረፋድ ላይ ባጋጠመ የመኪና አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መርዕድ ደበሌ በአደጋው ህይወታቸው ካለፉት ውስጥ የ3 ዓመት ህፃን እንደሚገኝበት እና በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
አክለው አደጋው ሊከሰት የቻለው ከሃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-78979 ኢት የሆነ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-04273 ኢት ከሆነ ሌላ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው ብለዋል።
አውቶቡሱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ከገባ በኋላ ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ሃይሌ ጋርመንት ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-77970 ኦሮ ከሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር መጋጨቱን ገልፀዋል።
አደጋው በደረሰበት አካባቢ ላይ የቆመ አንድ ሰው እና በጉዞ ላይ የነበሩ ሌሎች ሁለት ተሽከርካሪዎች በአውቶቡሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉ ሲሆንየአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ ዋና ኢንስፔክተር መርዕድ ደበሌ አመላክተዋል።
መረጃው: የአዲስ አበባ ፖሊስ ነው።

😢108❤51💔11🤔3
አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ የአለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ በ2 በመቶ ጨምሯል።
የነዳጅ ዋጋ ከጥቃቱ በኋላ ባለው የመጀመሪያ የንግድ ቀን በ2 በመቶ ሲጨምር ጦርነቱ በዚሁ ከቀጠለ ዋጋው ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል።
የአሜሪካ ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ2.38% ሲጨምር የአለም አቀፍ መለኪያው ብሬንት በ2.34% በመጨመር አንድ በርሜል በ78.81$ እየተሸጠ ነው።
ኢራን በቀን ከ3 ሚሊየን በርሜል በላይ ነዳጅ ለብቻዋ የምታመርት ሲሆን ወሳኙን የሆርሙዝ ሰርጥ ከዘጋች ዋጋው ከዚህም በላይ ያሻቅባል።
የኢራን ፓርላማ የሆርሙዝ ሰርጥን ለመዝጋት መወሰኑን ተከትሎ አሜሪካ ለቻይና ጥሪ አድርጋለች።
የኢራን ከፍተኛው የደህንነት ምክር ቤት ሰርጡን በተመለከተ የሚሰጠው ውሳኔ በሚጠበቅበት ጊዜ አሜሪካ ለኢራን ዋነኛ አጋር ጥሪ አድርጋለች።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ ቻይና ኢራን ሰርጡን እንዳትዘጋ እንድታደርግ ጠይቀዋል።
ማርክ ሩቢዮ ቻይና በሰርጡ ላይ በጣም ጥገኛ ነች ያሉ ሲሆን የሰርጡ መዘጋት ከአሜሪካ ኢኮኖሚ በላይ የሌሎችን ሃገራት ኢኮኖሚ ይጎዳል ብለዋል።
ቻይና ከኢራን ቀዳሚዋ የነዳጅ ገዢ ሃገር ስትሆን በሰርጡ በኩል ደግሞ በቀን ከ5 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ በላይ ወደ ሃገሯ ታስገባለች።
90 በመቶ የሚሆነው የኢራን የነዳጅ ምርት ለቻይና እንደሚሸጥም ተገልጿል።
Source: CNN, CNBC

❤103🕊23😢6🤝3
ኢራን በኳታር በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ሰነዘረች።
ኢራን በኳታር አል ኡዴይድ የአየር ሰፈር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሷን የገለፀች ሲሆን ለአሜሪካ ጥቃት የተሳካ ምላሽ ሰጥቻለሁ ብላለች።
ኳታር የአየር ክልሏን ከጥቃቱ በፊት መዝጋቷን ገልፃ የነበረ ሲሆን ከጥቃቱ በፊት የኢራን ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜክሺያን ምላሽ ሳንሰጥ አንተውምም ብለው ነበር።
በተጨማሪ ኢራን በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ማዘዣ ላይም ጥቃት ሰንዝራለች።
ኢራን ወደ ኳታር የላከችው የሚሳኤል ቁጥርም አሜሪካ ከጣለችባት የቦምብ ቁጥር እኩል መሆኑን ገልፃለች።
በጥቃቶቹ ስለተባለ ጉዳት የተባለ ነገር የሌለ ሲሆን፤ አሜሪካም የሰጠችው ምላሽ የለም።
Source: AP

1👏109❤65🤣41🕊14👎9👍5🤔5💔2
ኳታር በኢራን የአሜሪካ ጦር ላይ የተፈፀመው ጥቃት ሉዓላዊነቴን የጣሰ ተግባር ነው አለች።
የአሜሪካ ጦር ዋነኛ መቀመጫ የሆነችው ኳታር የኢራንን ተግባር ኮንናለች።
የኳታር የመከላከያ ሚኒስትር በበኩሉ ከኢራን ወደ አሜሪካ የጦር ማዘዣ የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን አክሽፌያለሁ ብሏል።
ነገሩን የአሜሪካው ፔንታጎን እና የደህንነት መስሪያ ቤቷ በቅርበት እየተከታተሉት እንደሆነም ተዘግቧል።
በተጨማሪ ኳታር ለጥቃቱ ተገቢውን ምላሽ የመስጠት መብት አለኝ ብላለች።
በሌላኛዋ የአሜሪካ ጦር መቀመጫ ባህሬንም የአደጋ ጊዜ ደውሎች ተሰምተዋል።
ፎቶ: በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ሰማይ ላይ የታዩ ፍንዳታዎች / አልጀዚራ

❤138🤔31👎22🕊13👍8💔7🤣6😢5🤬3
"የኢራን ጥቃት በጣም ደካማ ነው” ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
የአሜሪካው ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ጥቃት “በጣም ደካማ ነው” ሲሉ ምሽቱን በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።
ከተተኮሱት 14 ሚሳኤሎች 13ቱን ማክሸፋቸውንና አንዱ ጉዳት በማያደርስ መልኩ እንዲያልፍ መደረጉን ተናግረዋል።
"እንኳን ደስ አለሽ አለም፣ ጊዜው የሰላም ነው!" ያሉት ትራምፕ “ምንም ህይወት እንዳይጠፋ እና ማንም እንዳይጎዳ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስለሰጡን ኢራንን ማመስገን እፈልጋለሁ።" ነው ያሉት።
አክለውም "ምናልባት አሁን ኢራን በቀጠናው ወደ ሰላምና ስምምነት ማምረት ትችል ይሆናል፤ እስራኤልም ተመሳሳይ ነገር እንድታደርግ አበረታታለሁ" ሲሉ ነው የገለጹት።

🤣314❤151👎44🕊35🤔10👍6🤬5🔥3😢2👏1
የኢንተርንሺፕ ጥሪ ፦ በጋዜጠኝነት፣ ኮሚኒኬሽን እና ተያያዝ ዘርፎች #የተመረቃችሁ ፍላጎት ያላችሁ ወጣቶች አመልክቱ።
ለ3 ወራት የሚቆይ።
የተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ እና CV ያስፈልጋል።
ብዛት 6 ሰው (3 ወንድ እና 3 ሴት)
የትራንስፖርት ወጪ እንዲሁም ምሳ ይሸፈናል።
በየስድስት ወሩ በተመሳሳይ ሌሎች የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
አድራሻ ፦ አዲስ አበባ
ማስረጃችሁን ፦ በ @tikvahmagbot ላይ ይላኩ።
ለ3 ወራት የሚቆይ።
የተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ እና CV ያስፈልጋል።
ብዛት 6 ሰው (3 ወንድ እና 3 ሴት)
የትራንስፖርት ወጪ እንዲሁም ምሳ ይሸፈናል።
በየስድስት ወሩ በተመሳሳይ ሌሎች የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
አድራሻ ፦ አዲስ አበባ
ማስረጃችሁን ፦ በ @tikvahmagbot ላይ ይላኩ።
❤69🙏4👍3🕊1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔥 የመጀመርያው ቀን እጅግ የተለየ ነበር — 2ተኛው ቀን በፍጹም እንዳያመልጥዎ!
የBig 5 Construct Ethiopia እና የEast Africa Infrastructure & Water Expo አጀማመሩ እጅግ ደማቅ ሆኗል! በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ሹማምንት ተመርቆ የተከፈተው ደማቅ የንግድ አውደ ርዕይ፣ ለንግድ፣ ለፈጠራ እና ለዓለም አቀፋዊ ትሥሥሮች ሁነኛ መድረክ መሆኑን አስመስክሯል።
በመጀመሪያው ቀን ካልተገኙ:
✅ ከ20+ ሀገራት የተውጣጡ 180+ የምርት መለያዎችና አገልግሎቶች
✅ በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታው ዘርፍ ባለሙያዎችና ሙያዊ ትሥሥር
✅ የምርት ሙከራዎች፣ አዳዲስ ምርቶች እና በሲፒዲ የተረጋጠላቸው ትምህርታዊ ውይይቶች አምልጠዎታል!
ነገር ግን አልረፈደም! አውደ ርዕዩ በነገው ዕለትም ይቀጥላል!
✔️ የትም የማይገኙ የምክክር መድረኮች፣ አዳዲስ ሙያዊ ትውውቆች እና በርካታ ዕድሎች እርስዎን እየጠበቁ ነው!
📍 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ
🕙 ከጠዋቱ አራት ሰዓት ጀምሮ!
🎟 አሁኑኑ በነጻ ይመዝገቡ: https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Ethiopia

❤28🤬1
"ደንብ በተላለፉ ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ በተወሰደ እርምጃ ወደ 397.6 ሚሊየን ብር መሰብሰብ ተችሏል" ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻፀሙን የገመገመ ሲሆን በተያዘው አመት 69.8 በመቶ ደንብ መተላለፍን መቀነስ መቻሉን ገልጿል።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያሌው ታደሰ በተያዘው አመት በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ መተላለፍን መቀነስ ቢቻልም አሁንም የደንብ ጥሰቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።
አክለውም በከተማችን ጨለማን ተገን በማድረግ እና ቀንም ህገወጥ ግንባታወች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀው ህገወጥ የመሬት ወረራ እና ግንባታ ካለፉት አመታት አንፃር በተያዘው አመት መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል።
አያይዘው ህገወጥ ግንባታ የሚያከናውኑ አካላትን በማህበረሰቡ ጥቆማ መሰረት እና በደንብ አስከባሪዎች ቁጥጥር እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 72 ወንዞችን ከብክለት ለመከላከል ውስጥ ለውስጥ በመሄድ ቆሻሻ የሚለቁ ቱቦዎችን በመለየት ሰፊ ስራ ሰርተናል ብለዋል።
በዚህም በተደረገ ቁጥጥር ከብክለት እንድቆጠቡ የተነገራቸው ተቋማት ከድርጊታቸው ባለመቆጠባቸው በተደጋጋሚ መቀጣታቸውን አውስተዋል።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው ደንብን በማስከበሩ ረገድ ከቁጥጥር ውጭ በቸልተኝነት የአሰራር ጉድለት የፈፀሙ የተቋሙ ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ባደረሱ፣ ደንብ በተላለፉ ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ በተወሰደ እርምጃ ወደ 397.6 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።
በሪፖርቱ ላይ በተቋሙ የሚታዩ ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ ከ10 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች ተደጋጋሚ ስልጠናዎች መሰጠታቸው ገልፀው ይህ በቂ ስላልሆነ በተቻለን መጠን እያሻሻልን ለመሄድ እየሰራን ነው፣ አሁንም በተማረ የሰው ሃይል ተቋሙ እንዲመራ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በተያዘው አመት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ላይ 284 ቅሬታዎች ከተለያዩ አካላት ዘንድ መቅረቡን እና ምላሽ መሰጠቱን ተወስቷል።
በቀጣይ አመት በቴክኖሎጂ የታገዘ የቁጥጥር ስራ ለመስራት በሂደት መሆኑን አንስተው በ2022 ዓ.ም በከተማዋ ምንም አይነት የደንብ ጥሰት እንዳይኖር አቅዶ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

👎177❤76🤣19😢8👏4🤔4
ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ወደ ውጪ በሚላከው የነዳጅ ምርት ክፍያ ላይ አልተስማሙም ተባለ።
የባህር በር የሌላት ደቡብ ሱዳን የምታመርተውን ነዳጅ በሱዳን በኩል ለውጪ ገበያ የምታቀርብ ሲሆን ለዚህም በምትከፍለው ክፍያ ዙሪያ ከሱዳን ጋር ከስምምነት መድረስ አልቻለችም።
ደቡብ ሱዳን ነዳጇን በፖርት ሱዳን በኩል ስትልክ ትከፍል የነበረው ክፍያ ላይ ሱዳን ከሎጅስቲክስ ወጪ የተነሳ ማሻሻያ ማድረጓ ሃገራቱ እንዳይስማሙ አድርጓቸዋል ተብሏል።
በጦርነቱ ምክንያት የነዳጅ ምርቷን ለአለም ገበያ ማቅረብ ያልቻለችው ደቡብ ሱዳን በ2024 በኢትዮጵያ አድርጋ በጂቡቲ ለመላክ የሚያስችላትን የነዳጅ ቱቦ ለመስራት ማቀዷን መግለጿ ይታወሳል።
Source :Oilprice
@Tikvahethmagazine

❤45🕊2😢1
TIKVAH-MAGAZINE
#Coffee ☕️ በዓለም አቀፉ የቡና ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ የታየ ዝቅተኛው የቡና ዋጋ ተመዝግቧል። ለዋጋው መቀነስ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ የአረቢካ ቡናን በዋነኝነት በምታመርተው ብራዚል በቂ ዝናብ በመኖሩ ካለፈው አመት የተሻለ የቡና ምርት በመጠበቁ ነው። የቡና ዋጋ ባለፈው ሚያዝያ ወር በፓውንድ ሪከርድ የሆነ 4.11 ዶላር ደርሶ እንደነበር ሲታወስ ቡና ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ዋጋው በሚቀጥሉት…
#Coffee ☕️
⚫ "ባለፉት 11 ወራት ብቻ 409 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጪ ሀገር ተልኳል፣ በቀጣይ አመት 1.3 ሚሊዬን ቶን ቡና ለማምረት እየተሰራ ነው"
⚫ "በየሳምንቱ ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ ተመን እየወጣ ለቡና ላኪዎች ማኆበር በየሳምንቱ መረጃ ይሰጣል" - ቡናና ሻይ ባለስልጣን
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በመጭው አመት 1.3 ሚሊየን ቶን የቡና ምርት ለማግኘት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ዑመር የቡና ምርትን ከማሳደግ አንፃር በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑን እና ውጤታማ መሆን መቻሉን አንስተው ባለፉት 11 ወራት 409 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዝርዝር ምን አሉ?
የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ስራዎችን ተሰርተዋል። ላለፉት በርካታ አመታት በየአመቱ ከ400 እስከ 500 ሺህ ቶን ብቻ ነበር ማምረት የተቻለው። በዘንድሮው አመት ግን 1.1 ሚሊየን ቶን ማምረት ተችሏል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የምርት ትንበያ ከየትኛውም አለም ሀገሮች በተሻለ ሁኔታ እየተሰራበት ነው። የትኛው አካባቢ ምርታችን ሊቀንስ እንደሚችል፣ በምርት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመለየት እና ምን ያክል ምርት ሊገኝ እንደሚችል የትንበያ ስራዎች ይሰራሉ።
አሁን ላይ ያለውን የቡና ምርት መጨመር የተቻለው በመንግሰት ኢንሼቲቭ ላለፉት ሶስት አመታት ከ8 ቢሊየን በላይ የቡና ችግኝ በመተከሉ ነው። ከእነዚህ ውስጥም ግማሽ የሚሆነው ወደ ምረት እየገባ ነው።
ከወቅታዊ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሎጅስቲክ ችግር በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አገሮች ይከሰታል። አሁንም ሊከሰት ይችላል፣ ባለፈው ዓመትም በዚሁ ጉዳይ ተመሳሳይ ችግር ገጥሞን ነበር። አሁን ላይ ግን ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው።
ወደ ውጪ አገር የሚላክ የቡና ምርት በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር የኮንቴይነር እጥረት ይከሰታል። ችግሩ በያዝነው ወርም ገጥሟቸው እንደነበር እና ከጅቡቲ ባዶ ኮንቴይነር በማስመጣት ፈተናል።
በተጨማሪም ከቡና ምርት በተያዘው አመት 2.44 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። ኢትዮጵያ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ዝቅተኛ የቡና ዋጋ ተመን ስሌለላት ማግኘትን የሚገባትን የውጭ ምንዛሬ እና ገቢ ሳታገኝ ቆይታለች ሲሉ ተናግረዋል።
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የገበያ አማራጭ ግብይትና ኮንተራት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ትዛዙ ኢዶሳ በበኩላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በየሳምንቱ ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ ተመን እያወጣ መሆኑን እና ተመኑንም ለቡና ላኪዎች ማህበር በየሳምንቱ መረጃው እንድኖራቸው ይሰጣል ብለዋል።
የዋጋ ተመን ማውጣት ያስፈለገው የሀገርን ገቢ ለማሳደግ እና ነጋዴዎች ተከራክረው ከፍ ባለ ዋጋ መሸጥ እንዲችሉ ነው፤ ነጋዴዎች የሽያጭ መረጃ እያገኘን አይደለም የሚሉት ተቀባይነት የለውም፣ ምክንያቱም በየጊዜው Update እያደረግን በማህበራቸው በኩል እያሳወቅን ነው። መረጃ አልደረሰኝም የሚል ካለ ቢሮ እየመጣ መውሰድ ይችላል ነው ያሉት።
በየሳምንቱ የሚወጣውን ዝቅተኛ የዋጋ ተመን ለሁሉም ሰው ይፋ የማይደረገው የውጪ አገር ነጋዴዎች ኢትዮጵያ የቡና መግዣ ዋጋ ተመን አውጥታለች በማለት በዝቅተኛው የዋጋ ተመን ነው የምንገዛው እንዳይሉ እና ማግኘት ያለብንን ገቢ ላለማጣት ነው ሲሉ ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

❤85👎41👍4🔥3😢2🤔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎬 Day 2 Recap – A Hub of Deals, Products & Possibilities.Big 5 Construct Ethiopia and East Africa Infrastructure & Water Expo delivered another impactful day of business, innovation, and opportunity at Millennium Hall, Addis Ababa. Exhibitors from 20+ countries showcased cutting-edge products, live demos, and tailored solutions. Tomorrow is the final day — don’t miss out. https://www.big5constructethiopia.com/Tikvah_Magazine
❤10