#SafaricomEthiopia
⚫ "በሚቀጥለው ሁለት ዓመት ተኩል ተጨማሪ 3000 የኔትወርክ ሳይቶችን በመገንባት የደንበኞቼን ቁጥር ከ25 እስከ 30 ሚሊዮን አደርሳለሁ" - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት የሚያገኙ የ90 ቀን ንቁ ደንበኞች 10 ሚሊየን መድረሳቸውን ተከትሎ ኩባንያው ለዋና ዋና አጋሮቹ የምስጋና መርሐግብር በትላንትናው ዕለት በሸራተን ሆቴል አካሂዷል።
በዚህ የምሥጋና መርሐግብር ላይ የኩባንያው ልዩ ልዩ ስኬቶች የቀረቡ ሲሆን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ3100 ሳይቶች ላይ የኔትወርክ ማማዎችን መትከሉን ገልጿል።
በዚህም 55 በመቶ በሚሆነውን የሀገሪቱ ክፍል የሳፋሪኮም ኔትወርክ ማዳራስ መቻሉን አስታውቋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ራሱ ከተከላቸው የኔትወርክ ማማዎች በተጨማሪ ከኢትዮ ቴሌኮም የኔትወርክ ማማዎችን በመከራየት የሚጠቀም ሲሆን በዚህም በየዓመቱ 5 ቢሊዮን ብር ክፍያ እንደሚፈጽም ገልጿል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄለፑት በዚህ የምስጋና መርሐግብር ላይ "አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለንን ፍቃድ ለማግኘት ብቻ አንድ ቢሊዮን ዶላር አውጥተናል። ይህ ውድ ዋጋ ቢሆንም ምን ያህል በኢትዮጵያ ገቢያ እምነት እንዳለን ያሳየንበት ነው።" ሲሉ ተናግረዋል።
በምሥጋና መርኃግብሩም ለኢትዮ ቴሌኮም፤ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃንል፤ ኖኪያ ሁዋዌ፤ ቮዳ ሜታል ኢንደስትሪ ጨምሮ ለተለያዩ አጋሮቹ እውቅና ሰጥቷል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዚሁ መድረክ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ የኔትዎርክ አገልግሎትን ሙሉ ለሙሉ ለማዳረስ ከ25,000 በላይ ሳይቶች ላይ ታዎሮችን መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም አሁን ላይ እንደ ሀገር ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 3100 እንዲሁም ኢትዮ ቴሌኮም 9000 በላይ ሳይቶች አሉ በጋራ ከግማሽ በላይ ደርሰናል ነው ያሉት።
በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ይሄንን ለመሙላትም 500 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል ብለዋል።
ዊም ቫንሄለፑት በመድረኩ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ 3ኛውን ፍቃድ ማግኘቱንም አብስረዋል። በዚህም "ሳፋሪኮም ፋውንዴሽን" የተሰኘ የበጎ አድራጎት ሥራን የሚሰራ ተቋም ፈቃድ ማግኘቱን ነው የገለጹት።
በዚህ ተቋም ከዚህ በፊት ሲሰሩ የነበሩ ልዩ ልዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች በትኩረት ይሰሩበታል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው "እኛ ከጀርባችን ብዙ የውጭ ተቋማት አሉ እኛ 1 ብር ስንሰጥ እነሱ 5 ብር ለመስጠት ቃል ገብተውልናል" ሲሉ ነው የተናገሩት።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፉ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ማዎጣቱን የገለጸ ሲሆን አብዛኞቹ ተጠቃሚዎችም ከ20 ዓመት በታች ያሉ ናቸው ብሏል።
ባለፉት ጊዜያት ከ10 ሺ በላይ ላፕቶፖችን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ተማሪዎች ማስጠቱም በመድረኩ ተነስቷል።
አሁን ላይ 900 ቋሚ ሰራተኞች እንዳሉት የገለጸው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 97 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ናቸው ሲል ገልጿል።
ከቋሚ ሰራተኞች በተጨማሪ ባለፉት 4 ዓመታት በተለያዩ አጋር ድርጅቶች በኩል ለ20,000 ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩን በመድረኩ አቅርቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@TikvahethMagazine

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤154👍29👎17👏8🙏4🕊4🔥2🤝1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Telegram ✅
ቴሌግራም በቻናሎች ላይ ተጨማሪ ያስተዋወቀው "Direct Message" የቻናል ተከታታዮች ግላዊ መረጃዎቻቸው ተጠብቆ ለቻናል አስተዳዳሪዎች መልዕክት የሚልኩበት መስመር ነው።
በዚህም የቲክቫህ ቤተሰቦች ለሚኖራችሁ ጥቆማ እና አስተያየት ከታች💬 ምልክቱን በመጫን ከዚህ ቀደም ከነበሩት የBot አማራጮች በተጨማሪ ጥቆማ ሀሳብ አስተያየታችሁን ልታደርሱን ትችላላችሁ።
#TikvahFamily 🩵
@TikvahethMagazine
ቴሌግራም በቻናሎች ላይ ተጨማሪ ያስተዋወቀው "Direct Message" የቻናል ተከታታዮች ግላዊ መረጃዎቻቸው ተጠብቆ ለቻናል አስተዳዳሪዎች መልዕክት የሚልኩበት መስመር ነው።
በዚህም የቲክቫህ ቤተሰቦች ለሚኖራችሁ ጥቆማ እና አስተያየት ከታች
#TikvahFamily 🩵
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤30🕊9👍2
ጣሊያን ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውጪ 500 ሺ የሥራ ቪዛዎችን እንደምትሰጥ ይፋ አደረገች።
አውሮፓዊቷ ሃገር ጣሊያን ከ2026 ጀምሮ እስከ 2028 ድረስ ከአውሮፓ ህብረት ውጪ ላሉ ዜጎች አዳዲስ 500,000 የስራ ቪዛዎችን እንዳቀረበች ተዘግቧል።
ከፍተኛ የሰራተኛ እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ የሃገሪቱ ካቢኔ ይህንን ውሳኔ እንደወሰነ ሲገልፅ በቀጣይ አመት ብቻ ከ164 ሺህ በላይ ሰዎች በስራ ቪዛ ወደ ጣሊያን እንዲገቡ ይደረጋል ተብሏል።
በአውሮፓ ሶስተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት ጣሊያን የዜጎቿ ዕድሜ መግፋትና የውልደት ምጣኔ መቀነስ የምትፈልገውን የሰው ኃይል እንዳታሟላ አድርጓታል።
በ2024 የሞት ቁጥሯ ከውልደት መጠኗ የበለጠው ጣሊያን የህዝብ ቁጥሯም በ37,000 ቀንሷል ተብሏል።
ጣሊያን እስከ 2050 ድረስ 10 ሚሊየን ስደተኞችን ትቀበላለች ተብሎ ሲገመት የአሁኑን ውሳኔ የተከሰተውን የሰው ኃይል እጥረት በመቅረፍ አዎንታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ተብሏል።
Source: Reuters

❤237👍39🤝12🤔11🙏5👎1
🛑ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ፤ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
💎 ባለ 1 መኝታ በ 487,118 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮት
🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ
- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp

❤23
TIKVAH-MAGAZINE
ናይጄሪያ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት እንዲተገበር ጠየቀች። የናይጄሪያ የውጪ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ቢያንካ ኦጁክዉ በናይጄሪያ ከሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ገረመው ጋር መወያየታቸውን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። በውይይታቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የያዙ የናይጄሪያ ዜጎች በአዲስ አበባ እንግልት እየደረሰባቸው ነው ሲሉ ተናግረዋል። በአዲስ…
#Update
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ከናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር የዲፕሎማቲክ እና የሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት በተፈረመው የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ተወያይቷል።
ስምምነቱ የዲፕሎማቲክ እና የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ የሁለቱ አገራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶች እና ዜጎች ለሥራ ጉዳይ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ቪዛ ለማግኘት የሚያስፈልጉትን ቅድመ ሁኔታዎችና የሚወስደውን ጊዜ ለማስቀረት ያለመ ነው ተብሏል።
ምክር ቤቱ በስምምነቱ ላይ ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቆ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
ናይጄሪያ በተደጋጋሚ በአዲስ አበባ በኩል ትራንዚት አድርገው የሚሄዱ ዲፕሎማቶች እየተጉላሉ ስለመሆኑ በመግለጽ የሁለትዮሽ ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን ስትጠይቅ ነበር።
በቅርቡም በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ገረመው ከሀገሪቱ የውጪ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ቢያንካ ኦጁክዉ ጋር በነበራቸው ውይይት በዚሁ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ቀርቦ "በፓርላማ መፅደቅ ያስፈልገዋል" የሚል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

❤52👍6👎1
በቀጣይ 3 ዓመት ውስጥ እንጦጦ ላይ ያሉ ባህር ዛፎች ሙሉ በሙሉ ይነሳሉ ተባለ።
በአዲስ አበባ ተራራማ ቦታ በእንጦጦ ላይ የሚገኙት ባህር ዛፎች በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚነሱ እና በሀገር በቀል ዛፎች እንደሚተኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታውቋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ባህር ዛፍ ውሃ የመምጠጥ አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ መዲናዋ የከርሰ ምድር ውሃን በአግባቡ እንዳትጠቀም ማድረጉን ተናግረዋል።
ባህር ዛፎቹ ሲነሱ ግን በእጥፍ በሀገር በቀል ዛፎች እና ስነ ምህዳሩን ለማስተካከል በሚችሉ ዛፎች እየተተኩ መሆኑን ነው ኃላፊው የገለጹት።
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከተጀመረ ወዲህ ከእንጦጦ ተነስተው ወዳ መሀል ከተማ የሚፈሱት ወንዞች የውሃ መጠን መጨመሩንም ጠቅሰዋል።
መረጃው የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ነው።

👎154👍114❤52🤣20🤔12🤯2🙏2🤬1
የአለም ጤና ድርጅት ሀገራት በሲጋራ፣ አልኮል እና የስኳር መጠጦች ላይ ጭማሪ እንዲያደርጉ ጠየቀ።
ድርጅቱ በምርቶቹ ላይ የሚደረገው የታክስ ጭማሪ የ50 ሚሊየን ሰዎችን ህይወት ያድናል ብሏል።
የአለም ጤና ድርጅት በ2035 ሀገራት በሲጋራ፣ አልኮል እና የስኳር መጠጦች ላይ የሚጥሉትን ታክስ በ50 በመቶ ለመጨመር እንዲችሉ የሚገፋፋ ንቅናቄ ጀምሯል።
ድርጅቱ '3 by35' ሲል የሰየመው ኢንሼቲቭ ገቢ ከማስገኘት በተጨማሪ መከላከል የሚቻሉ ገዳይ በሽታዎችን በመቀነስ የሚሊዮኖችን ህይወት ይታደጋል ብሏል።
የዓለም ጤና ድርጅት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የብዙሃኑን ህይወት እንደሚቀሙ በመጥቀስ እነዚህን ምርቶች ከመጠቀም በሚመጡት እንደ የልብ ህመም ፣ ካንሰር እና ሌሎችም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አሁን ላይ 75 በመቶ የሰው ልጅ የሞት ምክንያት እየሆኑ ነው ሲልም ገልጿል።
የታክስ ጭማሪው የምርቶቹን ፍጆታ በመቀነስ ለመንግስታት ተጨማሪ ገቢ ያመጣል የሚለው ድርጅቱ ወደ ትግበራ ለመግባት ጊዜው አሁን ነው ብሏል።
ንቅናቄው በሚቀጥሉት 10 አመታት በሲጋራ፣ አልኮል እና የስኳር መጠጦች የሚጣልን የኤክሳይዝ ታክስ በመጨመር 1 ትሪሊየን ዶላር ለማሰባሰብ ያለመ ሲሆን የተገኘው ገንዘብም ለሀገራት ልማት እና የጤና ተደራሽነት ይውላል ተብሏል።
ከ2012-2022 ባሉት 10 አመታት 140 ሀገራት በምርቶቹ ላይ የታክስ ጭማሪ እንዳደረጉ ሲመላከት ደቡብ አፍሪካ እና ኮሎምቢያ በጥሩ ምሳሌነት ተነስተዋል።
ድርጅቱ አንዳንድ ሃገራት እነዚህን ምርቶች ለሚያመርቱ ኢንዱስተሪዎች ማበረታቻ ይሰጣሉ በሚል ሲተች ሃገራቱ እንደዚህ አይነት ማበረታቻዎችን እንዲያነሱም ጠይቋል።

❤112👏26🤣10👎7🤔6🤬6👍3🙏1
TIKVAH-MAGAZINE
#4thhachaluhundessaaward የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ 5ኛው የሙት ዓመት መታሰቢያ እና 4ኛው ዓመት " የሃጫሉ አዋርድ " የሽልማት መርሃ ግብር ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ እስካይ-ላይት ሆቴል ተካሂዷል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን ታድመዋል። የ4ኛው አመት ሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ አሸናፊዎ፦ ⚫ አንጋፍው አርቲስት አብዱላሂ ጂርማ የህይወት…
ሽልማቱ ተሰርዟል!
የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ባዘጋጀው 4ኛው የሃጫሉ አዋርድ ላይ በምርጥ ወንድ ድምጻዊ ዘርፍ አሸናፊ አድርጎ የመረጠውን የአርቲስት አንዷለም ጎሳን ሽልማት መሰረዙን ገልጿል።
ሽልማቱ በተለይም የወጣት ቀነኒ አዱኛ ጥቃትን የሚያመለክቱ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በስፋት በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ከተለቀቁ በኋላ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።
በዚህም ሽልማቱ እንዲነሳ የ24 ሰዓት የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄዎች ሲካሄዱ ነበር። ውሳኔውም ይኸው የሰዓት ገደብ ካበቃ ከሰዓታት በኋላ የተላለፈ ነው።
ፋውንዴሽኑ በመግለጫው ሽልማቱን ጉዳዩን ከሚመለከተው የህግ አካል የተጻፈ ደብዳቤ ይዘን የሸለምን ቢሆንም ከህዝብ በደረሰን አስተያየት ውሳኔያችን ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል ሲል ገልጿል።
አክሎም "ስለተፈጠረው ስህተት ህዝባችንን ይቅርታ እየጠየቅን ለአርቲስት አንዷለም ጎሳ የሰጠነው ሽልማት የተሰረዘ መሆኑን እናሳውቃለን ሲል አስታውቋል።

👍402👏90❤84👎14💯8🤬5😢5🤔3🙏2🕊1🤣1
ናሚቢያ መንግስታዊ የቀብር ሥነ-ስርዓቶችን በጊዜያዊነት ማገዷን አስታወቀች
ናሚቢያ ለታዋቂ ሰዎች፣ ለባለስልጣናት እና ለተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች በመንግስት የሚፈፀመውን የቀብር ሥነ-ስርዓት አግዳለች።
እገዳው እስከ ሚያዚያ 2026 ይቆያል ሲባል፤ እገዳውን ማንሳት የሚችሉትም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ነቱምቦ ናንዲ ናቸው።
የናሚቢያ መንግስት በ2024/25 ብቻ ለቀብር ስነስርዓት 2.2 ሚሊየን ዶላር አውጥቷል።
የቀድሞ የሀገሪቱ ፕረዚዳንት ሳም ኑጆማ የቀብር ሥነ-ስርዓት ከመፈፀሙ በፊት አስክሬኑን በሀገሪቱ ለማዞር ብቻ 30 ሚሊየን የናሚቢያ ዶላር ወጥቷል።
7 ሰዎች ያሉበት ኮሚቴ በመንግስት የሚፈፀሙ የቀብር ሥነ-ስርዓቶችን በተመለከተ ግምገማ ያደርጋል የተባለ ሲሆን ከግምገማው በኋላ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
Source: BBC

❤71🤣28👍8🙏2👎1
📍ዱባይ ላይ ባለ 3 መኝታ ቤት ታውን ሃውሶችን ከ 160 ካሬ ጀምሮ በተለያዩ የካሬ አማራጮች ለሽያጭ አቅርበናል።
👉ቪላ ቤቶች
👉 አፓርትመንት
💰3% ቅድመ ክፍያ ብቻ
📌 በረጅም ጊዜ የአከፍፈል ሁኔታ
ለኢትዮጵያኖች በሚመች የአከፍፈል ሁኔታ አቀርንቦሎታል።
📍 በጣም ተፈላጊ በሆነ መገኛ ቦታ
👉 ለኤርፖርት
👉 ለሞል
ለዳውን ታውን የቅርብ እርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ለኑሮ በጣም አመቺ እና ተስማሚ ናቸው
📌እነዚህ ቤቶች እየተገነቡ ያሉት በእውቁ ሊዮስ ኢንተርናሽናል የሪሊስቴት አልሚ ነው
☎️ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +971529180516 ያገኙናል

🤣49❤38👎3🤔2🕊2