Telegram Web
#GlobalBank

🟢  "የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል አገልግሎት አስጀምሪያለሁ" - ግሎባል ባንክ

🟢 "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የባንክ ካፒታል ዕድገት ዝቅተኛ ጣሪያ በቀረው ጊዜ ውስጥ እናሳካለን" - ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

አገልግሎት መስጠት የጀመረው የዲጂታል ባንኪንግ ማዕከል የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ገንዘብ ገቢ ማድረግና ወጪ ማድረግ፣ ቀሪ ሂሳብና የሂሳብ መግለጫ ማሳየት፣ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን መመንዘር፣ የተለያዩ ክፍያዎችን መፈፀም ያስችላል ተብሏል።

በተጨማሪም ያለ ኤቲኤም ካርድ አገልግሎት ማግኘት፣ ቼክ መመንዘርና ገቢ ማድረግን  ጨምሮ ደንበኞች የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት መጠቀም በሚፈልጉበት ወቅት በማዕከሉ በመገኘት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጁ ታብሌቶች መጠቀም እንደሚችሉም ገልጿል፡፡

ባንኩ በመግለጫው ማዕከሉ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ክፍል ያለው መሆኑንና ተቀዳሚ (corporate) ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው የቪዲዮ ባንኪንግ አገልግሎት ማገኝት የሚያስችላቸው አገልግሎትም እንደሚሰጥ ጠቅሷል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ይህ ማዕከል ሥራ መጀመሩ ባንኩ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር የባለአክሲዮኖችን ጥቅም ከፍ ከማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።

ባንኩ በዘንድሮው አመትም ከታክስ በፊት ብር 757.6 ሚሊዮን ማትረፉን የገለጸ ሲሆን የቅርንጫፍ ብዛቱንም ወደ 238( ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት ) ከፍ ማድረግ ችሏል። በአሁን ሰዓትም ባንኩ ከ 1.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት አሳውቋል፡፡

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደ/ር ተስፋዬ ቦሩ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የባንክ ካፒታል ዕድገት ዝቅተኛ ጣሪያ በቀረው ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳካ ገልጸዋል።

ባንኩ የተቀማጭ ሂሳቡን  ከ 20.6 ቢሊዮን ብር በላይ ያደረሰ መሆኑንና የባንኩ ጠቅላላ ሃብት ደግሞ ከ 26.6 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱንም አስታውቋል።

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሜክሲኮ አካባቢ  ለዋና መ/ቤት ግንባታ በተረከበው  5,550 ካ.ሜ ቦታ ላይ የወደፊት የዋና መ/ቤት ህንፃ ለመገንባት በሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ እየሰራ  እንደሆነም ለማወቅ በላከልን መግለጫ ጠቅሷል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ልጆችን ሥርዐት ስናስተምር መከተል የሚገቡን መርሆች

1፡ ተከታታይነት /be consistent/ እና ግልጽነት ሊኖር ይገባል

ልጆችን ሥርዐት ለማስያዝ ተከታታይነትና ግልጽነት ሁለት ቁልፍ ነገሮች ናቸው። ህጻናት በቤት አከባቢ ሊከውኑት የሚችሉትን ተግባር መስጠት ተገቢ ሲሆን ህጻናት የተጫወቱበትን እቃ እንዲሰበስቡ ማስተማር ተገቢ ነው።

በመጀመሪያው የተግባር ወቅት አብሮ መሳተፍ ያስፈልጋል፣ ቦኃላ ላይ ለነሱም ይቀላቸዋል። ልጆች ሃላፊነታቸውንንና ገደባቸውን እንዲሁም ወላጅ ከነሱ የሚጠብቀውን ነገር በደንብ ማሳወቅ አለብን።

2፡ ጽኑና የማያወላዉል አፍቃሪ መሆን አለብን

በሚያጠፉበትና ትዛዝን በማይቀበሉበት ጊዜ ጽኑና ሚዛናዊ መሆን፤ ቅጣታችንንም በፍቅር ማድረግ ይገባናል። በምንቀጣቸው ጊዜ እንዲታረሙና እንዲስተካከሉ እንደሆነ በመጀመሪያ ላይገነዘቡ ይችላሉ፣ ነገር ግን እንደምንወዳቸው ና እንዲታረሙ እንደሆነ ልንገልጽላቸው ያስፈልጋል። የምንወስዳቸዉ እርምጃዎች ተደጋጋሚና ጽኑ ከሆኑ ልጆች ትዛዝን ይከተላሉ።

3፡ አካላዊ ቅጣትን ማስወገድ

አካላዊ ቅጣት ብዙን ጊዜ ክርክርን ያስነሳል፣ ትክክልም ነው፣ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የበዛ አካላዊ ቅጣት በልጆች አካል ላይ ጉዳት ከማድረሱም በላይ ልጆች በማኅረሰቡ ላይ እንዲያምጹ ሊደርጋቸው ይችላል። ከአካላዊ ቅጣት ይልቅ ሌሎች የቅጣት አይነቶችን ብንተገብር ይመረጣል።

[ @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የቀረበ ]

@tikvahethmagazine
🚨 #Alert

"ማዜ ብሔራዊ ፓርክ ትላንትና ማታ አካባቢ በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በማሻ ሞርካ ቀበሌ እርሻ ማሳ የተነሳው ሰደድ እሳት ከቁጥጥር በላይ እየሆነ ስለሆነ የሚመለከተው ኢትዮጵያዊ እገዛ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።" - ማዜ ብሔራዊ ፓርክ

#Update : በማዜ ብሔራዊ ፓርክ የተነሳው ሰደድ እሳት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፓርኩ ገልጿል። የእሳቱ መነሻም በመጠራት ላይ ይገኛል ብሏል።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🟢 ''ሥራውን ካጠናቀቅን ከአንድ ወር በላይ ሆኖናል ከሥራው አስቸኳይነት አንፃር በብድር ጭምር ነው የሰራነው" - ቅሬታ አቅራቢዎች

🟢 ''ከ 270 በላይ ለሚሆኑ ኮንተራክተሮችና ማኅበራቶች ከፍያለው '' የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ቢሮ

ከ600 በላይ የሚሆኑ ማኅበራት እና ኮንተራክተሮች የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰራንበትን ክፍያ በተባለው ቀን ውስጥ አልከፈለንም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

"እያንዳንዱ ማህበር እና ኮንተራክተር ከ 3 እስከ 40 ሚሊየን ብር ወጪ አድርጓል፤ ቤቶቹም አልቀው ነዋሪ ገብቶባቸዋል። ሆኖም ግን ክፍያ እስከአሁን አልተከፈለንም" ሲሉ ነው ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት።

በተጨማሪም ቅሬታ አቅራቢዎቹ "ሥራውን በሁለት ሳምንት ውስጥ ካጠናቀቃችሁ በአንድ ሳምንት ውስጥ ክፍያችሁን እንፈፅማለን የሚል ቃል ገብተውልን ነበር" ሲሉ ክፍያቸው በጊዜ አለመፈጸሙን አስረድተዋል።

አያይዘውም፥ ''ሥራውን ካጠናቀቅን ከአንድ ወር በላይ ሆኖናል ከስራው አስቸኳይነት አንፃር በብድር ጭምር ነው የሰራነው" በማለት ክፍያው መዘግየቱ ጫና እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሽመልስ ታምራትን ጠይቀናል። ዋና ዳይሬክተሩ ለሁሉም ኮንትራክተሮች እና ማህበራቶች ክፍያቸውን ለመፈፀም ጥረት እያደረግን ነው የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት በዝርዝር ምን አሉ ?

ዳይሬክተሩ የከተማ አስተዳደሩ በጫረታ የሚሸጡ የንግድ ቤቶችን ወደ መኖሪያ ቤት ለመቀየር የወሰነውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የንግድ ቤቶችን በፍጥነት በመቀየር ለዜጎች ለማስረከብ የተለያዩ ማኅበራትንና ኮንተራክተሮችን ማሰማራቱን ገልፀዋል።

በዚህም ከ400 የማያንሱ ኮንትራክተሮች እና ማኅበራት እንደተሳተፉ እንዲሁም ሥራውንም ሰርቶ ለማጠናቀቅ 57 ቀናቶች መውሰዳቸውን ዳይሬክተሩ አክለዋል።

ክፍያቸውን በተመለከተ ላነሳንላቸው ጥያቄ በከተማችን በተለያዩ ቦታዎች በኮርፖሬሽኑ ስር ባሉ ቅርንጫፎች አማካኝነት እንደ አፈፃፀማቸው የክፍያ ሰነዶቻቸው በሂደት እየመጣ እየተከፈላቸው ነው ብለዋል።

"ከሁሉም ቅርንጫፎች ሂደቱን ጨርሶ የመጣውን እየከፈልን ነው እስካሁን ከ270 በላይ ለሚሆኑ ኮንተራክተሮች እና ማህበራቶች ክፍያቸው ተሰጥቷቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ክፍያ ያልተሰጣቸው ኮንትራክተሮች እና ማኅበራቶች ደግሞ አፈፃፀማቸው በቅርንጫፎች ተገምግሞ ሂደቱን ጠብቆ ባለመምጣቱ መዘግየቱን ነው ያነሱት።

በቢሮ ደረጃ ቅሬታ ያቀረቡ ኮንትራክተሮች እና ማኅበራቶች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ ከቅሬታ አቅራቢዎች መካከልም ይህ ዘገባ እስከ በተጠናከረበት ድረስ የተከፈላቸው ስለመኖራቸውም ጠቁመዋል።

እስካሁን ክፍያ ላልተሰጣቸው ማኅበራቶች እና ኮንተራክተሮች ክፍያቸውን ለመክፈል በቢሮ ደረጃ እየተሰራ መሆኑንም ነው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፥ "ነዋሪውን ለመታደግ ሥራው  በአስቸኳይ ሌት ከቀን ነው የተሰራው፤  ክፍያቸውም ቅደም ተከተላቸውን ተከትሎ እየተፈፀመ ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
"ከ10 ሄክታር በላይ የፓርኩ ክፍል በቃጠሎ ወድሟል" የማዜ ብሔራዊ ፓርክ

ትናት ማምሻውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ የማዜ ብሔራዊ ፓርክ አከባቢ የተነሳዉ እሳት ሌሊቱን ሙሉ ሳይጠፋ ማደሩንና በፓርኩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የማዜ ብሔራዊ ፓርክ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ጬማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በአከባቢው ከፓርኩ አቅራቢያ ከሚገኝ ሞርካ ቀበሌ አንድ አርሶ አደር የማሳ ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅት እያካሄደ ከነበረዉ ቃጠሎ የወጣ እሳት ምሽት 12 ሰዓት አከባቢ በፓርኩ ዙሪያ የሚገኝን 5  ሄክታር ቦታ ካወደመ በኋላ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ገደማ የፓርኩን ክፍል ማዉደም መጀመሩን የገለፁት አቶ መስፍን ከወቅቱ ነፋሻማነትና የሰዓቱ ምቹ አለመሆን የእሳት ማጥፋትን ስራ ፈትኖት እንደነበር አስታዉቀዋል።

የእሳት ማጥፋት ስራዉ ከዛሬ ማለዳ ከ12 ሰዓት ጀምሮ በተደራጀ መልኩ በአከባቢው ነዋሪዎች፣በፀጥታ መዋቅርና በእሳት አደጋ ብርጌድ ርብርብ ሲደረግበት ቆይቶ ከፓርኩ ዉጪ 5 ሄክታር ከፓርኩ ክፍል ደግም 10 ሄክታር በላይ ካወደመ በኋላ ረፋዱ አራት አከባቢ በቁጥጥር ስር መዋሉን አቶ መስፍን አስታዉቀዋል።

አቶ መስፍን አክለዉም እስካሁን በተደረገዉ ማጣራት ከፓርኩ ስነ ምህደር ዉድመት ባሻገር በአራዊቱ ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልፀዉ በእሳት ማጥፋቱ ስራ ከተሳተፉት የአከባቢዉ ነዋሪዎች ፣የፀጥታ መዋቅር አባላትና በሃይለማርያምና ሮማን ፋዉንዴሽን የተቋቋመው የእሳት አደጋ ብርጌድ በተጨማሪ ከወላይታ ወደ ሳዉላ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የግልና ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ሕዝቡን በማጓጓዝ ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ምስጋና አቅርበዋል።

የማዜ ብሔራዊ ፓርክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ እና ጎፋ ዞኖች መካከል ቁጫ ወረዳ አከባቢ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ 460 ፣ከሐዋሳ 235 እንዲሁም ከጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ 196 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።

የፓርኩ አጠቃላይ ስፋት 220 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆንበሀገራችን በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘዉ የስዋይኔ ቆርኬ ጨምሮ አንበሳ፣ አቦሸማኔ፣ የቆላና ትልልቆቹ አጋዘኖች፣ አምባራይሌና ከርከሮን ጨምሮ 39 የተለያዩ አጥቢ እንስሳቶች፣ 196 የአዕዋፋት ዝርያዎች እና ከ80 በላይ የእፅዋት አይነቶ እንደሚገኙበት ከማዜ ብሔራዊ ፓርክ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethmagazine
የአሜሪካ የጦር ኃይል በሶማሊያ በሚገኘው የISIS ቡድን ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመ።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሶማሊያ በሚገኘው የ ISIS እንዲሁም ከሱ ጋር ግንኙነት ባላቸው አሸባሪ ቡድኖች ላይ ባስተላለፉት ወታደራዊ ትዕዛዝ የአየር ጥቃት ተፈጽሟል።

"በዋሻ ውስጥ ተደብቀው ያገኘናቸው እነዚህ ገዳዮች ለአሜሪካ እና ለአጋሮቻችን ስጋት ነበሩ" ሲሉ ፕረዚዳንቱ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። 

አክለውም፥ "በጥቃቱ አሸባሪዎችን ገድለናል፤ የሚኖሩባቸውን ዋሻዎችም አውድመናል። ይህም ሰላማዊ ዜጎችን ሳይጎዳ የተፈጸመ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው የተካሄደው በጎሊስ ተራሮች (ሰሜናዊ ሶማሊያ) አካባቢ ሲሆን የተፈጸመውም ጠዋት አከባቢ ነው ተብሏል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሶማሊያ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ባለስልጣን ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠው፤ የሶማሊያ መንግስት ድርጊቱን እንደሚቀበል ገልጸዋል። “ሶማሊያ የአሸባሪዎች መሸሸጊያ ልትሆን አትችልም” ሲሉም ነው የገለጹት።

የሶማሊያ ፕረዚዳንት ጽ/ቤትም በX ገጹ ጥቃቱ መፈጸሙን ገልጾ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ አሜሪካ ዓለም አቀፍ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት እንደግፋለን ሲል ገልጿል።

የአሜሪካው ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፥ "የእኛ ወታደራዊ ኃይል ይህን ጥቃት ከዓመታት በፊት አቅዶት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ባይደን እና አጋሮቹ ፈጥነው እርምጃ አልወሰዱም። እኔ ግን አደረግኩት" ሲሉም ነው የጠቀሱት።

በጹሑፋቸው ላይም ለISIS እና ለሌሎች አሜሪካ ላይ ጥቃት ለሚሰነዝሩ ሰዎች ሁሉ ያለን መልዕክት “እናገኛችኋለን፣ እናም እንገድላችኋለን!” የሚል ነው። ሲሉ ነው የገለጹት።

አሜሪካ በሶማሊያ ለዓመታት በሪፐብሊካን እና በዲሞክራቲክ አስተዳደር ሥር የአየር ጥቃትን ስታደርግ ቆይታለች። ባለፈው ዓመት ከሶማሊያ ጋር በመተባበር በፈጸመችው በአሸባሪዎች ላይ ባነጣጠረው ጥቃትም የቡድኑን ሦስት አባላት መገደላቸውን የአሜሪካ ጦር ኃይል አስታውቆ ነበር።

Credit : Reuters , VOA , 📸 U.S.Africa Command

@tikvahethmagazine
2025/02/02 19:29:07
Back to Top
HTML Embed Code: