#4thhachaluhundessaaward
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ 5ኛው የሙት ዓመት መታሰቢያ እና 4ኛው ዓመት " የሃጫሉ አዋርድ " የሽልማት መርሃ ግብር ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ እስካይ-ላይት ሆቴል ተካሂዷል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን ታድመዋል።
የ4ኛው አመት ሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ አሸናፊዎ፦
⚫ አንጋፍው አርቲስት አብዱላሂ ጂርማ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኗል።
⚫ ምርጥ የሙዚቃ ጠባቂ /music Care/- አርቲስት አሜ ጢቃ
⚫ ምርጥ ኬሮግራፈር -አርቲስት አለማየሁ ዳቢ
⚫ ምርጥ ሲኒማቶግራፈር- አርቲስት ሽመልስ ታደሰ
⚫ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ - አርቲስት ዘመን እሼቱ
⚫ ምርጥ የሙዚቃ አቀናባሪ- አርቲስት ሚራ ትሩቼልቫም
⚫ ምርጥ አዲስ ዘፋኝ-አርቲስት አሳንቲ አስቹ
⚫ ምርጥ ሴት ዘፋኝ-አርቲስት ለምለም ሀ/ሚካኤል
⚫ ምርጥ ወንድ ዘፋኝ-አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ
⚫ ምርጥ የግጥ ዜማ- አርቲስት ለሊሳ እድሪስ (ቢሊሌ)
⚫ ምርጥ የባህል ዜማ -አርቲስት አደም ሙሀመድ እና ሀሊማ አብዱራህማን (ሹቢቶ)
⚫ ምርጥ ዘመናዊ ዜማ - አርቲስት ጉቱ አበራ(ኢዮሌ)
⚫ ምርጥ አልበም- አንዱዓለም ጎሳ
ለአሸናፊዎች የዋንጫና ከ50ሺ እስከ 100ሺ ብር የንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።
የቀድሞ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደ/ር ታደሳ ቀነኣ አመራር ላይ በነበሩ ጊዜ የሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት ዩኒቨርስቲው ውስጥ ላይ በማቆም ላደረጉት አስተዋጽኦ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የአርቲስት ሀጫሉ ባለቤት ወ/ሮ ፋንቱ ደምሰው እንደተናገረችው "…ሽልማቱ አርቲስቶችን ለማበረታታት ያለመ ነው። …የተረሱ አርቲስቶችም ይበረታቱበታል። የሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ሀጫሉ የጀመራቸውን ስራዎች እና ያለማችውን ስራዎች ከግብ ለማድረስ አላማ አድርጎ ይሰራል" ብላለች።
@TikvahethMagazine
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ 5ኛው የሙት ዓመት መታሰቢያ እና 4ኛው ዓመት " የሃጫሉ አዋርድ " የሽልማት መርሃ ግብር ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ እስካይ-ላይት ሆቴል ተካሂዷል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን ታድመዋል።
የ4ኛው አመት ሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ አሸናፊዎ፦
ለአሸናፊዎች የዋንጫና ከ50ሺ እስከ 100ሺ ብር የንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።
የቀድሞ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደ/ር ታደሳ ቀነኣ አመራር ላይ በነበሩ ጊዜ የሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት ዩኒቨርስቲው ውስጥ ላይ በማቆም ላደረጉት አስተዋጽኦ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የአርቲስት ሀጫሉ ባለቤት ወ/ሮ ፋንቱ ደምሰው እንደተናገረችው "…ሽልማቱ አርቲስቶችን ለማበረታታት ያለመ ነው። …የተረሱ አርቲስቶችም ይበረታቱበታል። የሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ሀጫሉ የጀመራቸውን ስራዎች እና ያለማችውን ስራዎች ከግብ ለማድረስ አላማ አድርጎ ይሰራል" ብላለች።
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"በሚቀጥሉት 40 ወራት ውስጥ አፍሪካ በማዳበሪያ እራሷን ትችላለች"- አሊኮ ዳንጎቴ
ናይጄሪያዊው የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ አፍሪካ በመጪዎቹ 40 ወራት ውስጥ በማዳበሪያ ምርት እራሷን ትችላለች አሉ።
ዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካው ላይ የ2.5 ቢሊየን ዶላር ማስፋፊያ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን ይህም አፍሪካ ከውጪ የምታስገባውን ምርት በእጅጉ ይቀንሳል ተብሏል።
ቢሊየነሩ" አፍሪካ ከ40 ወራት በኋላ ከየትኛውም ቦታ ማዳበሪያ አታስገባም፤ 40 ወራት ብቻ ስጡኝ፥ ዳንጎቴ ከኳታር የበለጠ የዩራያ አምራች እንዲሆን እናደርገዋለን" ብለዋል።
አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ ከ6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በላይ በአመት ከሌላው አለም እያስገባች ሲሆን አሁን ያለው የዳንጎቴ ፋብሪካ በአመት 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም ገንብቷል።
የዳንጎቴ ፋብሪካ የድርጅቱን 37 በመቶ ምርት ለአሜሪካ ገበያ እያቀረበ መሆኑን ጠቅሶ ከማስፋፊያው በኋላ ምርቱን በእጥፍ በመጨመር የአፍሪካን ፍላጎት ያሟላል ተብሎ ይጠበቃል።
እንደ ግዙፉ የአፍሪካ ኤግዚም ባንክ ሪፖርት አፍሪካ በ2021 ከማዳበሪያ ሽያጭ 8.9 ቢሊየን ዶላር ገቢ ስታገኝ ትልቁን ድርሻ የሰሜን አፍሪካ ሃገራት ይይዛሉ ተብሏል።
ሞሮኮ እና ግብፅ 70 በመቶ የአፍሪካን የማዳበሪያ ሽያጭ ሲይዙ በድምሩ 6.23 ቢሊየን ዶላር አግኝተዋል።
ምንም እንኳን የተወሰኑ ሃገራት በማዳበሪያ እራሳቸውን የቻሉ ቢሆንም አብዛኞቹ አሁንም ከውጪ በሚገባ ምርት ላይ ጥገኛ ናቸው።
የዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካ በሚቀጥሉት ሁለት አመታትም በቀን 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ቢሊየነሩ ገልፀዋል።
በ2022 ስራውን የጀመረው የሌጎሱ የዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካ በናይጄሪያ የምግብ እጥረትን ለመቀነስ በዝቅተኛ ዋጋ እየሸጠ ሲሆን የናይጄሪያን የ1.5 ሚሊየን ቶን አመታዊ የማዳበሪያ ፍጆታም ለመሸፈን እየሰራ ነው።
በአመት ከ400 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ የሚያስመጣው የማዳበሪያ ፋብሪካው የናይጄሪያን የውጪ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።
የአፍሪካ የማዳበሪያ ዋጋ ከ15 ቢሊየን ዶላር የተሻገረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2030 ወደ 20 ቢሊየን እንደሚያድግ ይገመታል።
በምግብ እጥረት እና በውጪ ምንዛሬ ለምትፈተነው አፍሪካ የዳንጎቴ ፋብሪካ ሁነኛ መፍትሄ እንደሚሆን ሲጠቆም ቢሊየነሩ ዳንጎቴ የአህጉሪቱ መሪዎች የአህጉሪቱን ሃብትና ኢንቨስትመንት ባማከለ መልኩ አፍሪካን ተቀዳሚ አድርገው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት መስማማታቸው በቅርቡ ይፋ መደረጉም ይታወሳል።
Source: Reuters, Africa Fertilizer Watch

🛑ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
💎 ባለ 1 መኝታ በ 504,767 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp

#ሱስ
⚫ "ባለፉት 3 አመታት ከ19 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የሱስ ተጠቂዎች ስልጠና ቢሰጥም ከእነዚህ መካከል 1 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ከሱስ የወጡት" - በዘርፉ ላይ የሚሰራ ተቋም
⚫ "የማህበራዊ ሚዲያ ሱስ የቤተሰብን ትስስር ወደ ሚበጥስበት ደረጃ ላይ ደርሷል" - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
"እረፍት የሥነ ልቦናና ምክር አገልግሎት ማዕከል" ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት በሆነበት የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ካሂዷል።
በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱም የማዕከሉ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ መጋቢ ቢኒያም አዴሎ ባለፉት 3 አመታት በ "አይሰለጥንብኝም" ፀረ-ሱስ ንቅናቄ ማህበር" የተሰሩ ስራዎችን አስመልክተው ሪፖርት አቅርበዋል።
ሪፖርቱ ምን ይላል ?
በሪፖርቱ በሶስት አመታት ውስጥ በሀገራችን 19 ሺህ ለሚሆኑ በተለያዩ ሱሶች ለተጠቁ ዜጎች የስነልቦና ማማከር አገልግሎት እና ከሱስ እንዲወጡ ስልጠና መስጠታቸውን ገልፀዋል።
ከእነዚህ መካከል 1 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ከነበሩበት የሱስ ህይወት ወጥተው የተሻለ ህይወት እንድኖሩ ማድረግ መቻሉን እና በዛሬው እለትም የንቅናቄው አንድ አካል በማድረግ ማዕከል መክፈት መቻላቸውን ተናግረዋል።
ከ19 ሺዎች ውስጥ 95 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች፣ 3 በመቶ እማወራና አባወራዎች፣ ከ1 በመቶ በታች የተሀድሶ ታካሚዎች እና 1 በመቶ ወላጆችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት ማግኘታቸው ተመላክቷል።
በአገራችን ካለው የዜጎች ቁጥር ውስጥ ወደ 50 በመቶ የሚጠጉ ዜጎች በተለያዩ የሱስ አይነቶች እየተጠቁ ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይ ሶስት አመታት ውስጥ 30 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከሱሰኝነት እንዲላቀቁ አቅደን እየሰራን ነው ብለዋል።
ማኅበሩ እስካሁን ባካሄደው ንቅናቄ ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ ሱስ በዋናነት እየተጠቁ ነው ያሉ ሲሆን ይህም የተማሪዎችን ትኩረት ነስቷል፣ የእርስበርስ ግንኙነትን አበላሽቷል፣ ብዙ ሰዎችን ስሜታዊ እያደረገ ወደ ተለያዩ የሱስ አይነቶች እንደዲገቡ እያደረገ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
በአገራችን የሱሰኞችን ቁጥር ለመቀነስ የቤተሰብ፣ የሃይማኖት፣ የትምህርት እና የመንግስት ተቋማት እርብርብ እያደረጉ ቢሆንም ውጤቱ ግን አመርቂ አይደለም የተባለ ሲሆን ውጤት ለማምጣት የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል እርብርብ ያስፈልጋል ነው የተባለው።
ከሥነልቦና እስከ ፖሊሲ ልንጠቀምባቸው የሚገቡ መሳሪያዎች በተቀናጀ ሁኔታ አለመኖራቸው እና የግብአት አቅርቦት ማነስ የሱሰኞችን ቁጥር ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ላይ ተግዳሮት መሆኑን ተጠቅሷል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ምን አሉ ?
በዕለቱ የተገኙት ሚኒስትሯ ሱስን መከላከል የሚያስችል አዋጅ መውጣቱን አስታውሰው፥ በአዋጁ ላይ የፖሊሲ ክፍተት ያለው በመሆኑ ጠቅሰዋል።
አክለውም፥ ፖሊሲውን ከማስፈፀሚያ ስልቶች ጋር የተዋሃደ እንዲሆን የህግ ድንጋጌዎች እንዲወጡ የማድረግ ስራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የማህበራዊ ሚዲያ ሱስ የቤተሰብን ትስስር ወደ ሚበጥስበት ደረጃ ደርሷል ያሉ ሲሆን የሚዲያ አጠቃቀም እውቀት እና ክህሎት ላይ ማዕከሉ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

"የእናቶች እና ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት የሞት ምጣኔ ላይ ከፍተኛ መቀነስ ቢታይም አሁንም በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው" - የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት(EPHI)
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ የእናቶች እና ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት የሞት ምጣኔ ላይ ከፍተኛ መቀነስ ቢታይም አሁንም በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ ገልጿል።
ይህንንም ኢንስቲትዩቱ በጥናት ማረጋገጡን የተናገሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ፥ በኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናት የሞት መንስኤዎች እና አጠቃላይ የበሽታ ሥርጭት ትክክለኛ ቁጥራዊ መረጃዎች አለመገኘታቸው እንቅፋት መሆኑን ነው የተናገሩት።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፥ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ውስጥ የሚገኘው የብሔራዊ መረጃ አስተዳደር ቅመራና እና ትንተና ማዕከል (NDMC) ለሀገር አቀፍ ጤና አገልግሎት ግብዓት የሚሆኑ ማስረጃዎችን በመመርመር ሲያቀርብ የቆየ ቢሆንም አብዛኛዎቹ የመረጃ ምንጮች ሙሉነትና ወጥነትና የጎደላቸው መሆናቸውን ነው ያነሱት።
የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር መርጋ ደረሳ በአገራችን ከ100 ሺህ እናቶች ውስጥ 200 የሚሆኑት እናቶች በወሊድ ምክንያት እንደሚሞቱ የዓለም አቀፍ ጥናቶች ያሳያሉ ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አክለውም በክልሎች ላይ ያሉ የጤና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተገቢውን መረጃ በአግባቡ ባለማስቀመጣቸው ቁጥሩን እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም ያሉ ሲሆን ነገር ግን የሞት ምጣኔው ይቀንስ እንጂ አሁንም ችግሩ አለ ሲሉ አስረድተዋል።
የማኅበረሰቡ አኗኗር፣ የጤና ህክምና ፍላጎት አለመኖር፣ የጤና ተቋማት አስፈላጊ የሆነ ግብአት አለመኖር፣ የእርግዝና ክትትል በበቂ ሁኔታ አለመኖር ለእናቶች ሞት በሚፈለገው ልክ አለመቀነስ እንደምክንያት ይጠቀሳል።
የህፃናቶችን ሞት ማቆም ያልተቻለው ህፃናቶች በእናታቸው ማህፀን ውስጥ እያሉ ተገቢውን ክትትል አለማግኘታቸው እና ከተወለዱ በኋላም ያለው የአመጋገብ ሥርአት ዘልማዳዊ መሆኑ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ጤና ቢሮ ሃላፊዎች ጋር የእናቶችን እና የህፃናትን የሞት ምጣኔ ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ይህ የመግባቢያ ስምምነት የናሙና ምዝገባ ሥርዓት SRS መዘርጋት ሲሆን ዓላማው በኢትዮጵያ የእናቶችና ሕጻናት ሞት እና የሞት መንስኤዎችን እንዲሁም አጠቃላይ የበሽታ ስርጭት መለየት እና ያሉትን የክትትል ሥርዓቶች ለማጠናከር ያሰበ ነው።
በስምምነቱ መሰረት በጤና ነክ ዙሪየ ያሉትን ችግሮች ለመለየት በሃገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልልሎች በተመረጡ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ላይ ጥናት ለማካሄድ መታቀዱ ተጠቁሟል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@TikvahethMagazine
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ የእናቶች እና ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት የሞት ምጣኔ ላይ ከፍተኛ መቀነስ ቢታይም አሁንም በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ ገልጿል።
ይህንንም ኢንስቲትዩቱ በጥናት ማረጋገጡን የተናገሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ፥ በኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናት የሞት መንስኤዎች እና አጠቃላይ የበሽታ ሥርጭት ትክክለኛ ቁጥራዊ መረጃዎች አለመገኘታቸው እንቅፋት መሆኑን ነው የተናገሩት።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፥ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ውስጥ የሚገኘው የብሔራዊ መረጃ አስተዳደር ቅመራና እና ትንተና ማዕከል (NDMC) ለሀገር አቀፍ ጤና አገልግሎት ግብዓት የሚሆኑ ማስረጃዎችን በመመርመር ሲያቀርብ የቆየ ቢሆንም አብዛኛዎቹ የመረጃ ምንጮች ሙሉነትና ወጥነትና የጎደላቸው መሆናቸውን ነው ያነሱት።
የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር መርጋ ደረሳ በአገራችን ከ100 ሺህ እናቶች ውስጥ 200 የሚሆኑት እናቶች በወሊድ ምክንያት እንደሚሞቱ የዓለም አቀፍ ጥናቶች ያሳያሉ ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አክለውም በክልሎች ላይ ያሉ የጤና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተገቢውን መረጃ በአግባቡ ባለማስቀመጣቸው ቁጥሩን እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም ያሉ ሲሆን ነገር ግን የሞት ምጣኔው ይቀንስ እንጂ አሁንም ችግሩ አለ ሲሉ አስረድተዋል።
የማኅበረሰቡ አኗኗር፣ የጤና ህክምና ፍላጎት አለመኖር፣ የጤና ተቋማት አስፈላጊ የሆነ ግብአት አለመኖር፣ የእርግዝና ክትትል በበቂ ሁኔታ አለመኖር ለእናቶች ሞት በሚፈለገው ልክ አለመቀነስ እንደምክንያት ይጠቀሳል።
የህፃናቶችን ሞት ማቆም ያልተቻለው ህፃናቶች በእናታቸው ማህፀን ውስጥ እያሉ ተገቢውን ክትትል አለማግኘታቸው እና ከተወለዱ በኋላም ያለው የአመጋገብ ሥርአት ዘልማዳዊ መሆኑ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ጤና ቢሮ ሃላፊዎች ጋር የእናቶችን እና የህፃናትን የሞት ምጣኔ ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ይህ የመግባቢያ ስምምነት የናሙና ምዝገባ ሥርዓት SRS መዘርጋት ሲሆን ዓላማው በኢትዮጵያ የእናቶችና ሕጻናት ሞት እና የሞት መንስኤዎችን እንዲሁም አጠቃላይ የበሽታ ስርጭት መለየት እና ያሉትን የክትትል ሥርዓቶች ለማጠናከር ያሰበ ነው።
በስምምነቱ መሰረት በጤና ነክ ዙሪየ ያሉትን ችግሮች ለመለየት በሃገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልልሎች በተመረጡ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ላይ ጥናት ለማካሄድ መታቀዱ ተጠቁሟል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@TikvahethMagazine
🛑ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
💎 ባለ 1 መኝታ በ 504,767 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
💎 ባለ 1 መኝታ በ 504,767 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#AwashBank
አዋሽ ባንክ በ2024/25 በጀት ዓመት በዲጅታል የተከናወነ የገንዘብ ዝውውር መጠን 1 ትሪሊዮን መድረሱን አስታውቋል። ይህም በባንኩ ከተከናወኑት የገንዘብ ዝውውሮች ውስጥ ከ76 በመቶ በላይ ድርሻ አለው ነው ያለው።
ባንኩ በጀት ዓመቱን አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል። የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራው በተጠናቀቀው የሂሳብ አመት የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ከ64 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ መመዝገቡን እና ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 77 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው በዝርዝር ምን አሉ ?
- 52 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት የደንበኞቹን ብዛት ከ15 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ተችሏል፤
- ከታክስ በፊት 22.7 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዝግቧል፤
- 2300 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች የአዋሽ ኢ-ስኩል ማኔጅመንት ሲስተም ተጠቃሚ በማድረግ 3.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ክፍያ በዚህ መተግበሪያ ፈፅመዋል።
- ባንኩ በ2024/25 ብቻ ተቀማጭ የሂሳብ መጠኑን በ100 ቢሊዮን ለማሳደግ mission 100 Billion የተባለ እቅድ ቀርጾ በመስራት በአመቱ ውስጥ ብቻ 106 ቢሊዮን በላይ ማድረሱን እና አጠቃላይ የተቀማጭ መጠኑን 332 ቢሊዮን አድርሷል።
- በተጠናቀቀው በጀት አመት በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ለተሰማሩ ዜጎች ከ219 ቢሊዮን በላይ የብድር አገልግሎት ሰጥቷል።
- ከተሰጠው የብድር መጠን ውስጥ ከ16.6 ቢሊዮን በላይ የሚሆነው በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለታቀፉ ከ14 ሺህ በላይ ደንበኞች የተሰጠ ነው።
- በዲጅታል የብድር አገልግሎት ያለምንንም ማስያዣ ከ301 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቹ ከ493 ሚሊዮን ብር በላይ አበድሯል።
- ባንኩ ይህን የዲጂታል የብድር አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከሳፋሪኮም ጋር ለመስራት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ መመደቡን እና በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
- የባንኩ ተመላሽነታቸው አጠራጣሪ የሆኑ ብድሮች ምጣኔ በሂሳብ አመቱ ከ1.8 በመቶ በታች ማድረሱን እና ብሄራዊ ባንክ ካስቀመጠው የ5 በመቶ ጣሪያም ሆነ ባንኩ ካስቀመጠው እቅድ አንፃር የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
- በዚህ አመት ለነዳጅ፣ ለዘይት፣ ለትምህርት፣ ስኳር፣ ሩዝ፣ መድሀኒት እና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ለመንግስት ከ1.23 ቢሊዮን ዶላር ሰጥቷል።
- ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የስራ ፈጠራ ውድድር ፈስስ ተደርጓል።
- በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በቁሳቁስ እና በጥሬ ገንዘብ በተጠናቀቀው የሂሳብ አመት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ድጋፍ አድርጓል።

"ጤናና ጤና ነክ ከሆኑ መረጃዎች 20 በመቶው ብቻ ናቸው በዲጅታል የሚሰበሰቡት" - ጥናት
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባስጠናው ጥናት በኢትዮጵያ ጤናና ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎች የሚሰበሰቡት 80 በመቶ በወረቀት በመሆኑ የጤና ዳታዎችን ለመሰብሰብ መቸገሩን ገልጿል።
በጥናቱ የተሳተፉት በኢንስቲትዩቱ የዳታ ማከማቻ እና አስተዳደር አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሃፍቱ ረዳ፥ ጥናቱ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ሁሉንም የሀገሪቱን ክልሎችን አካቷል ብለዋል።
አቶ ሀፍቱ ረዲ ስለ ጥናቱ በዝርዝር ምን አሉ ?
ከክልል ጤና ቢሮዎች እና ኢንስቲትዩቶች ጋር በመሆን በጤናና ጤና ነክ ዙሪያ ጥናት አድርገናል። በዚህ ጥናትም ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዳታዎች በዩኒቨርሲቲዎች እና በጤና ሳይንስ ኮሌጆች ተገኝተዋል።
እነዚህ ዳታዎች የሚያሳዩት 20 በመቶ ብቻ በዲጅታል መረጃዎች እንደሚሰበሰቡ ነው። ሌላው በወረቀት ነው። ይህ ደግሞ በጤናው ዘርፍ ላይ ላሉ ክፍተቶች ምክንያት ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ዳታዎችን አንድ ላይ ለመሰብሰብ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአብዛኛው ተቋማት ተቀጣሪ ግለሰቦች መረጃዎች የእኔ ስለሆኑ አልሰጥም ይላሉ፣ ይህ ደግሞ ለስራችን ተግዳሮት ነው።
አንዳንድ ተቋማት ላይ የሚሰበሰቡ መረጃዎች በግለሰብ እጅ ላይ በመሆናቸው ግለሰቦች ከስራ ሲለቁ ይዘውት ይወጣሉ። በተለይም የአንዳንድ ተቋማት ፖሊሲዎች መረጃዎችን ለ3ኛ ወገን እንዳይሰጥ ይከለክላል።
ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎች በተደራጀ መልኩ አለመኖራቸው የጤና ስርአቱን ለመቀየር አስቸጋሪ ነው የሚያደርጉት፣ በተለይም አሁን ላይ በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ በሽታዎች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ አስቸጋሪ አድርገውታል።
በተጨማሪም ለምሳሌ የኤችአይቪ ኤድስ እና የወባ ስርጭት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፣ የእናቶችና ህፃናት ሞት በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም። ይህም ተጽዕኖው ከፍተኛ ነው።
መረጃ የህዝብ ነው፣ በመሆኑም ተቋማት መረጃን ለመስጠት የሚገድቡ ፖሊሲዎችን በሚቀርጹበት ስርዓት አፅኖት ሰጥተው ማየት አለባቸው።
ኢንስቲትዩቱ አሁን ላይ ያለውን የመረጃ ክፍት ለመቅረፍ ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር የዳታ ማዕከል ለማቋቋም እየሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

#SafaricomEthiopia
⚫ "በሚቀጥለው ሁለት ዓመት ተኩል ተጨማሪ 3000 የኔትወርክ ሳይቶችን በመገንባት የደንበኞቼን ቁጥር ከ25 እስከ 30 ሚሊዮን አደርሳለሁ" - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት የሚያገኙ የ90 ቀን ንቁ ደንበኞች 10 ሚሊየን መድረሳቸውን ተከትሎ ኩባንያው ለዋና ዋና አጋሮቹ የምስጋና መርሐግብር በትላንትናው ዕለት በሸራተን ሆቴል አካሂዷል።
በዚህ የምሥጋና መርሐግብር ላይ የኩባንያው ልዩ ልዩ ስኬቶች የቀረቡ ሲሆን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ3100 ሳይቶች ላይ የኔትወርክ ማማዎችን መትከሉን ገልጿል።
በዚህም 55 በመቶ በሚሆነውን የሀገሪቱ ክፍል የሳፋሪኮም ኔትወርክ ማዳራስ መቻሉን አስታውቋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ራሱ ከተከላቸው የኔትወርክ ማማዎች በተጨማሪ ከኢትዮ ቴሌኮም የኔትወርክ ማማዎችን በመከራየት የሚጠቀም ሲሆን በዚህም በየዓመቱ 5 ቢሊዮን ብር ክፍያ እንደሚፈጽም ገልጿል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄለፑት በዚህ የምስጋና መርሐግብር ላይ "አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለንን ፍቃድ ለማግኘት ብቻ አንድ ቢሊዮን ዶላር አውጥተናል። ይህ ውድ ዋጋ ቢሆንም ምን ያህል በኢትዮጵያ ገቢያ እምነት እንዳለን ያሳየንበት ነው።" ሲሉ ተናግረዋል።
በምሥጋና መርኃግብሩም ለኢትዮ ቴሌኮም፤ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃንል፤ ኖኪያ ሁዋዌ፤ ቮዳ ሜታል ኢንደስትሪ ጨምሮ ለተለያዩ አጋሮቹ እውቅና ሰጥቷል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዚሁ መድረክ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ የኔትዎርክ አገልግሎትን ሙሉ ለሙሉ ለማዳረስ ከ25,000 በላይ ሳይቶች ላይ ታዎሮችን መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም አሁን ላይ እንደ ሀገር ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 3100 እንዲሁም ኢትዮ ቴሌኮም 9000 በላይ ሳይቶች አሉ በጋራ ከግማሽ በላይ ደርሰናል ነው ያሉት።
በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ይሄንን ለመሙላትም 500 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል ብለዋል።
ዊም ቫንሄለፑት በመድረኩ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ 3ኛውን ፍቃድ ማግኘቱንም አብስረዋል። በዚህም "ሳፋሪኮም ፋውንዴሽን" የተሰኘ የበጎ አድራጎት ሥራን የሚሰራ ተቋም ፈቃድ ማግኘቱን ነው የገለጹት።
በዚህ ተቋም ከዚህ በፊት ሲሰሩ የነበሩ ልዩ ልዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች በትኩረት ይሰሩበታል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው "እኛ ከጀርባችን ብዙ የውጭ ተቋማት አሉ እኛ 1 ብር ስንሰጥ እነሱ 5 ብር ለመስጠት ቃል ገብተውልናል" ሲሉ ነው የተናገሩት።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፉ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ማዎጣቱን የገለጸ ሲሆን አብዛኞቹ ተጠቃሚዎችም ከ20 ዓመት በታች ያሉ ናቸው ብሏል።
ባለፉት ጊዜያት ከ10 ሺ በላይ ላፕቶፖችን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ተማሪዎች ማስጠቱም በመድረኩ ተነስቷል።
አሁን ላይ 900 ቋሚ ሰራተኞች እንዳሉት የገለጸው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 97 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ናቸው ሲል ገልጿል።
ከቋሚ ሰራተኞች በተጨማሪ ባለፉት 4 ዓመታት በተለያዩ አጋር ድርጅቶች በኩል ለ20,000 ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩን በመድረኩ አቅርቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@TikvahethMagazine
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት የሚያገኙ የ90 ቀን ንቁ ደንበኞች 10 ሚሊየን መድረሳቸውን ተከትሎ ኩባንያው ለዋና ዋና አጋሮቹ የምስጋና መርሐግብር በትላንትናው ዕለት በሸራተን ሆቴል አካሂዷል።
በዚህ የምሥጋና መርሐግብር ላይ የኩባንያው ልዩ ልዩ ስኬቶች የቀረቡ ሲሆን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ3100 ሳይቶች ላይ የኔትወርክ ማማዎችን መትከሉን ገልጿል።
በዚህም 55 በመቶ በሚሆነውን የሀገሪቱ ክፍል የሳፋሪኮም ኔትወርክ ማዳራስ መቻሉን አስታውቋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ራሱ ከተከላቸው የኔትወርክ ማማዎች በተጨማሪ ከኢትዮ ቴሌኮም የኔትወርክ ማማዎችን በመከራየት የሚጠቀም ሲሆን በዚህም በየዓመቱ 5 ቢሊዮን ብር ክፍያ እንደሚፈጽም ገልጿል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄለፑት በዚህ የምስጋና መርሐግብር ላይ "አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለንን ፍቃድ ለማግኘት ብቻ አንድ ቢሊዮን ዶላር አውጥተናል። ይህ ውድ ዋጋ ቢሆንም ምን ያህል በኢትዮጵያ ገቢያ እምነት እንዳለን ያሳየንበት ነው።" ሲሉ ተናግረዋል።
በምሥጋና መርኃግብሩም ለኢትዮ ቴሌኮም፤ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃንል፤ ኖኪያ ሁዋዌ፤ ቮዳ ሜታል ኢንደስትሪ ጨምሮ ለተለያዩ አጋሮቹ እውቅና ሰጥቷል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዚሁ መድረክ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ የኔትዎርክ አገልግሎትን ሙሉ ለሙሉ ለማዳረስ ከ25,000 በላይ ሳይቶች ላይ ታዎሮችን መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም አሁን ላይ እንደ ሀገር ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 3100 እንዲሁም ኢትዮ ቴሌኮም 9000 በላይ ሳይቶች አሉ በጋራ ከግማሽ በላይ ደርሰናል ነው ያሉት።
በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ይሄንን ለመሙላትም 500 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል ብለዋል።
ዊም ቫንሄለፑት በመድረኩ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ 3ኛውን ፍቃድ ማግኘቱንም አብስረዋል። በዚህም "ሳፋሪኮም ፋውንዴሽን" የተሰኘ የበጎ አድራጎት ሥራን የሚሰራ ተቋም ፈቃድ ማግኘቱን ነው የገለጹት።
በዚህ ተቋም ከዚህ በፊት ሲሰሩ የነበሩ ልዩ ልዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች በትኩረት ይሰሩበታል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው "እኛ ከጀርባችን ብዙ የውጭ ተቋማት አሉ እኛ 1 ብር ስንሰጥ እነሱ 5 ብር ለመስጠት ቃል ገብተውልናል" ሲሉ ነው የተናገሩት።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፉ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ማዎጣቱን የገለጸ ሲሆን አብዛኞቹ ተጠቃሚዎችም ከ20 ዓመት በታች ያሉ ናቸው ብሏል።
ባለፉት ጊዜያት ከ10 ሺ በላይ ላፕቶፖችን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ተማሪዎች ማስጠቱም በመድረኩ ተነስቷል።
አሁን ላይ 900 ቋሚ ሰራተኞች እንዳሉት የገለጸው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 97 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ናቸው ሲል ገልጿል።
ከቋሚ ሰራተኞች በተጨማሪ ባለፉት 4 ዓመታት በተለያዩ አጋር ድርጅቶች በኩል ለ20,000 ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩን በመድረኩ አቅርቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🛑ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
💎 ባለ 1 መኝታ በ 504,767 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
💎 ባለ 1 መኝታ በ 504,767 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Telegram ✅
ቴሌግራም በቻናሎች ላይ ተጨማሪ ያስተዋወቀው "Direct Message" የቻናል ተከታታዮች ግላዊ መረጃዎቻቸው ተጠብቆ ለቻናል አስተዳዳሪዎች መልዕክት የሚልኩበት መስመር ነው።
በዚህም የቲክቫህ ቤተሰቦች ለሚኖራችሁ ጥቆማ እና አስተያየት ከታች💬 ምልክቱን በመጫን ከዚህ ቀደም ከነበሩት የBot አማራጮች በተጨማሪ ጥቆማ ሀሳብ አስተያየታችሁን ልታደርሱን ትችላላችሁ።
#TikvahFamily 🩵
@TikvahethMagazine
ቴሌግራም በቻናሎች ላይ ተጨማሪ ያስተዋወቀው "Direct Message" የቻናል ተከታታዮች ግላዊ መረጃዎቻቸው ተጠብቆ ለቻናል አስተዳዳሪዎች መልዕክት የሚልኩበት መስመር ነው።
በዚህም የቲክቫህ ቤተሰቦች ለሚኖራችሁ ጥቆማ እና አስተያየት ከታች
#TikvahFamily 🩵
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጣሊያን ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውጪ 500 ሺ የሥራ ቪዛዎችን እንደምትሰጥ ይፋ አደረገች።
አውሮፓዊቷ ሃገር ጣሊያን ከ2026 ጀምሮ እስከ 2028 ድረስ ከአውሮፓ ህብረት ውጪ ላሉ ዜጎች አዳዲስ 500,000 የስራ ቪዛዎችን እንዳቀረበች ተዘግቧል።
ከፍተኛ የሰራተኛ እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ የሃገሪቱ ካቢኔ ይህንን ውሳኔ እንደወሰነ ሲገልፅ በቀጣይ አመት ብቻ ከ164 ሺህ በላይ ሰዎች በስራ ቪዛ ወደ ጣሊያን እንዲገቡ ይደረጋል ተብሏል።
በአውሮፓ ሶስተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት ጣሊያን የዜጎቿ ዕድሜ መግፋትና የውልደት ምጣኔ መቀነስ የምትፈልገውን የሰው ኃይል እንዳታሟላ አድርጓታል።
በ2024 የሞት ቁጥሯ ከውልደት መጠኗ የበለጠው ጣሊያን የህዝብ ቁጥሯም በ37,000 ቀንሷል ተብሏል።
ጣሊያን እስከ 2050 ድረስ 10 ሚሊየን ስደተኞችን ትቀበላለች ተብሎ ሲገመት የአሁኑን ውሳኔ የተከሰተውን የሰው ኃይል እጥረት በመቅረፍ አዎንታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ተብሏል።
Source: Reuters