Telegram Web
የኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ስለሚፈጸሙ የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀሎች መግለጫ ሰጠ

° "በርካታ ግለሰቦች የዚህ ድርጊት ሰለባ በመሆናቸው ተግባሩ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል" - ፖሊስ

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ከሰሞኑ የአንዳንድ የግለሰቦችን የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት "በመጥለፍ /ሀክ በማድረግ /" የቅርብ ከሚሏቸው ሰዎችን በማውራት ገንዘብ እንዲልኩላቸው በማድረግ የማጭበርበር ድርጊት የሚፈጽሙ ግለሰቦች መኖራቸውን ጠቅሶ የማስጠንቀቂያ መልዕክት አስተላልፏል።

አጭበርባሪዎቹ በተጠለፈው አካውንት ከግለሰቦቹ ጋር ቅርብ ቁርኝት አላቸው ብለው የሚያስቡትን ሰው ለግለሰቦች ገንዘብ መላክ እንደሚፈልጉና ገንዘቡ በሞባይል ባንክ እንዲላክላቸው የተላከውን ገንዘብ በጥሬ ገንዘብ እንደሚመልሱ በማስመሰል ወንጀሉን ይፈጽማሉ ነው ያለው።

ለዚህ ወንጀል ፖሊስ በዋነኛነት አጭበርባሪዎቹ የቴሌግራም የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ስለተቋረጠብኝ ብር መላክ አልቻልኩም በማለት የሚላክለትን አካውንት በመላክ ገንዘብ እንደሚያጭበረብሩ ጠቅሷል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ሙህዬ በሰጡት መግለጫ "አጭበርባሪዎች በሶሻል ሚዲያ የተሳሳተ እና ለራሳቸው ጥቅም የሚያስገኝ ዲጅታል ቁጥር በመላክ የኤልክትሮኒክስ ሲስተም በመጠቀም ከግለሰቦች የባንክ አካውንት በቴልግራም ግሩፕ ገንዘብ እየጠየቁ እየወሰዱ ይገኛሉ" ነው ያሉት።

አክለውም "አጭበርባሪዎቹ የሚፈልጉትን ቁጥር በመላክ ለማጭበርበር በሚመቻቸው ሲስተም ውስጥ በማስገባትና በሚያዙት ፎርሙላ መሠረት ሲስተሙን በትክክል እንድሞላ በማድረግ የግለሰቦቹ የግል ሶሻል ሚዲያ ሃክ  በማድረግ ወይም በመጥለፍ ወንጀል እየተፈጸመ ይገኛል" ብለዋል።

በርካታ ግለሰቦች የዚህ ድርጊት ሰለባ በመሆናቸው ተግባሩ አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣ  ማህበረሰቡ የማንኛውንም ባንክ ስያሜ በመጥቀስ የሚላኩ ቁጥሮችን ወደ ሲስተም ሳያስገባ ከተጠቀሰው ባንክ በመሄድ ወይም በመደውል ትክክለኛውን መረጃ ማግኘት እንደሚገባው አብራርተዋል።

ፖሊስ አጭበርባሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ ነው ያሉት ኃላፊው ማህበረሰቡ በዲጅታል አሰራሮች ላይ ተመስርተው የሚመጡ የማጭበርበሪያ ስልቶችን አውቆና በሚገባ ተገንዝቦ ራሱን ከአጭበርባሪዎች መጠበቅ እና አጭበርባሪዎች በህግ እንዲጠየቁ ለፖሊስ ጥቆማ መሰጠት እንዳለበትም አሳስበዋል።

⚠️ ይህንን የጥንቃቄ መልዕክት ያንብቡ https://www.tgoop.com/tikvahethmagazine/20798

@tikvahethmagazine
በቁጥጥር ሥር ውለዋል!

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር በአንቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበሩና የሃይማኖት ስም በማጥፋት ወንጀል የተጠረጠሩ ሦስት ተማሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ተማሪዎቹ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ በቲክቶክ ላይ ሲሳለቁ የሚያሳይ ቪዲዮ ከለቀቁ በኋላ በርካቶችን አስቆጥቷል።

በዚህ ድርጊት ላይ የተሳተፉ እና በማህበራዊ ገጾች ላይ የለጠፉ ሦስት ተማሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የአምቦ ዩኒቨርሲቲም የዲሲፕሊን ቅጣት ለማስተላለፍ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስተውቋል።

@tikvahethmagazine
#AddisAbaba

" አባታችንን አፋልጉን ! "

አባታችን ገብረማርያም መለሰ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰዓት በኃላ ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም።

እድሜያቸው 85 ዓመት ሲሆን መጥፋታቸውን ለፖሊስ አመልክተናል።

በሰዓቱ ለብሰውት የነበረው ጥቁር ጃኬት ነበር። ከዘራም በእጃቸው ይዘዋል።

መጨረሻ ጊዜ የነበሩበት ቦታ ወሰን 02 አካባቢ ነው።

ቤተሰብ ተጨንቋል አባታችንን አፋልጉን፤ መረጃ ለመስጠት 0911452386 ላይ ደውሉልን። " - ፈላጊ ቤተሰቦቻቸው

@tikvahethiopia
ሁሉንም በአንድ የያዘ ስማርት ካርድ ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር የያዘ፣ የመንጃ ፍቃድ ቁጥር ያለው እንዲሁም እንደ ኤቲ ኤም ካርድ የሚያገለግል ሁሉንም በአንድ የያዘ የነዋሪነት መታወቂያ ስማርት ካርድ ወደ ሥራ ለማስገባት በፕሮጀክት ደረጃ እየሰራ መሆኑን ጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያን ስማርት አርጎ አሁን ከምንጠቀምበት የተሻለ ተደርጎ ሰዎች የተለያዩ ካርድ ይዘው ከሚንቀሳቀሱ ሁሉንም አገልግሎቶችን በአንድ የያዘ ካርድ በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ ወደ አገልግሎት ለማስገባት በእቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኤጀንሲው ሰምቷል።

ካርዱ የሚሰራበት ዋነኛ አላማም አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ፣ ነዋሪዎች 3 ወይም 4 ካርድ ይዘው ከሚንቀሳቀሱ በ1 ካርድ ሁሉንም አገልግሎቶች አግኝተው አገልግሎት አሰጣጥና ተጠቃሚነትን ቀላል ለማረግ መሆኑን አሳውቋል።

ኤጀንሲው ለቲክቫህ እንደገለፀው ይህ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ትስስር ሊኖር እንደሚገባና በአሁኑ ሰዓትም ፋይዳ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ለወደፊት ደሞ ስራው ተጠናቆ ካርዱ ወደስራ ሲገባ ባንኮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት የጋራ ትብብር እንደሚፈጠርም ተገልጿል።

ይህ አገልገሎት በሚቀጥሉት 6 ወራት ውስጥ ወደ ስራ ለማስገባት እቅድ የተያዘለት ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ማሳያዎች (Samples) እየተሰራ ይገኛል።

አዲስ የሚሻሻለው የመታወቂያ አገልግሎት ፕሮጀክት ተግባር ላይ መዋል ሲጀምር ወይም የሚሻሻሉ፣ የሚጨመሩ ጉዳዮች ሲኖሩ ኤጀንሲው ለህዝብ በይፍ እንደሚያሳውቅም ነው ያስታወቀው።

@tikvahethmagazine
"ወቅቱ በጋና ነፋሻማ በመሆኑ ከድንገተኛ የእሳት አደጋ ተጠበቁ" - የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ

በስልጤ ዞን በሁልበራግ ወረዳ በቢላዋንጀ ቀበሌ በግምት ከቀኑ 6:30 አካባቢ በተከሰተው ድንገተኛ እሳት ቃጠሎ አራት የሳር ክዳን ቤቶች ከነ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንና በአንድ የሰር ክዳን ቤት ላይ መጠነኛ አደጋ መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል።

የእሳት አደጋው ወደከፋ ደረጀ ሳይደርስ ከሀለባ ዞን የእሳትና ድንጋተኛ አደጋ መቆጣጠሪያ መኪና ደረሶ በተደረገው ርብርብ እሳቱን መቆጣጠር መቻሉ ነው የተገለጸው።

⚠️ ወቅቱ በጋና ነፋሻማ በመሆኑ ሁሉም ማኅበረሰብ አከባቢውን፣ ንብረቱን፣ እራሱን ከድንገተኛ እሳት አደጋ እንዲጠብቅ የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethmagazine
"የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል" - IOM

መነሻውን ከጅቡቲ በማድረግ 35 ኢትዮጵያውያንን አሳፍሮ ወደ የመን ሲያቀና የነበረ የስደተኞች መርከብ በኃልኛ ንፋስ ተመቶ በደረሰው አደጋ የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል

አደጋው ቅዳሜ ዕለት (ጥር 10) መድረሱን፤ የ9 ሴቶች እና የ11 ወንዶች ህይወት ማለፉን የጠቀሰው ድርጅቱ በመርከቡ የነበሩ 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የየመን ዜግነት ያላቸው መርከበኞች ደግሞ በህይወት መትረፋቸውን ገልጿል።

@tikvahethmagazine
🖼️ ፍቅረ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ 🖼️

የህትመት እና ማስታወቂያ ፍላጎትዎትዎን ሃሳብዎን ከነገሩን ንድፈ-ሃሳቡን ከማውጣት ጀምሮ አይነ-ግቡዕ የሆነ ሥራ ሰርተን በራሳችን ማሽኖች አትመን ያሉበት ቦታ ድረስ መጥተን እናስረክብዎታለን።

ይደውሉ እና ይዘዙን ወረቀት ነክ ህትመቶች አልባሳት ላይ ህትመቶች እንዲሁም የተለያዩ ቁሶች ላይ እናትማለን። ከማስታወቂያ እና ህትመት ሥራ ጋር የተያያዘ ማማከርም እንሰጣለን።

ለነጋዴዎች እና አምራች ድርጅቶች ልዩ ቅናሽ አለን። ኑ አብረን እንስራ! ኑ አብረን እንደግ!

በዚሁ አጋጣሚ በፊት ተራራ የነበረው ስማችን ወደ ፍቅረ ህትመት ሥራ መቀየሩን ልንነግርዎ እንወዳለን።

☎️ ይደውሉ 0927361854 , 0799100230 , 0985257938

📱 TikTok 📱 Telegram 📱Facebook

📍 https://maps.app.goo.gl/heRTnskHQDUj2jgQ9
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
⌛️95% የተጠናቀቁ አፖርታማዎች

📍በቦሌ ቡልቡላ ከሁዳ ኢንጅነሪንግ!

👉በካሬ 96,600ብር ጀምሮ
👉የተናጥል ዲጅታል ካርታ ያላቸው
👉137 ካ.ሜ ባለ ሶስት መኝታ
👉በወለል 2 ቤቶች ብቻ
👉50% ቅድመ ክፍያ ቀሪውን በ6 ወር ከፍለው የሚጨርሱት
👉 የከርሰምድር ውሀ፣ስታንድባይ ጄኔሬተር፣የጋራ ሰገነት እና በቂ የመኪና ማቆሚያ ያላቸው

ለበለጠ መረጃ :- 0931333432 ወይም 0909340800
የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ከአውሮፓ ውጭ የሚመጡ ዜጎች ቤት እንዳይገዙ ሊከለክሉ ነው፡፡ 

ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ስፔን የገጠማትን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ ከአውሮፓ ውጭ የሚመጡ ዜጎች በሀገሪቱ  በቶችን እንዳይገዙ በከፊልና ሙሉ በሙሉ የሚያግደውን እቅድ ይፋ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ''ስፔን ውስጥ ቤተሰብ ኖራቸውም አልኖራቸውም ከአውሮፓ ውጭ የመጡ ዜጎች በኛ ሀገር ቤት መግዛት አይችሉም'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

ይህንን እና በውጪ ዜጎች የንብረት ይዞታ ታክስ ላይ ያለውን ታክስ በ100 % ለማሳደግ ጭምር እቅድ ያስቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እቅዳቸው ገና ወደ ህግ አውጪው ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።

ባለፈው ዓመት በስፔን ነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶችን ለማግኘት በመቸገራቸው ምክንያት የተቃውሞ ሰልፎችን ስፔን ተመልክታለች።

ማድሪድን ጨምሮ በታዋቂ ከተሞች የኪራይ ዋጋ መናር የአካባቢው ነዋሪዎች ከስፔን ገበያ ውጪ እየተደረጉ እንደሆነ እንዲሰማቸው አድርጓል።

በስፔን ውስጥ ከሚሸጡት አምስት ቤቶች ውስጥ አንዱ በውጭ ዜጎች የሚገዛ ሲሆን ብዙዎቹም ነዋሪ ያልሆኑ ናቸው።

ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውጭ የሆኑ ዜጎች በ2023 ብቻ 23,000 ቤቶችን መግዛታቸው ተሰምቷል፡፡

Credit : Reuters, Independent

@tikvahethmagazine
በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ቦንብ ፈንድቶ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ።

በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ አሳሊ ቀበሌ ልዩ ስፍራው ዱቤ 02 ንዑስ ተብሎ በሚጠራበት መንደር ቦንብ ፈንድቶ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን የደቡብ ምዕራፍ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፓሊስ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት የቦንብ ፍንዳታው የተፈጠረው ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ነው።

በዚህም ፍንዳታ በስድስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እና በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በተርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ነግረውናል።

ፖሊስ ባደረገው ማጣራት የአደጋው መነሻ ምክንያቱ የአንድ ግለሰብ አሮጌ መኖሪያ ቤት አፍርሶ በአዲስ ለመስራት በአከባቢው አጠራር ዳጉዋ (በደቦ) ሥራ ላይ የነበሩ ስምንት ሰዎች በቁፋሮ ወቅት ያገኙትን F1 የተባለ የእጅ ቦንብ ባለማወቅ በድንጋይና በመዶሻ በመቀጥቀጣቸው ፍንዳታው መከሰቱን አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ የእጅ ቦንቡ በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ተቀብሮ ሊገኝ እንደቻለ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ቦንቡ ከየት እንደመጣ፣ እንዴት ግለሰቡ ቤትስ ሊገኝ እንደቻለ ተጨማሪ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝና የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ኢንስፔክተር ደጀኔ ነግረውናል።

ህብረተሰቡ መሰል የፍንዳታ አደጋዎች እንዳይደርስ ምንነቱ የማይታወቅ ነገሮችን ሲያገኝ ከመቀጥቀጥ በመቆጠብ ለሚመለከተው አካል እንዲያሳውቅ እና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲሉም አሳስበዋል።

@tikvahethmagazine
#Konso 📶

በኮንሶ ዞን ከትናንት ጀምሮ የነበረው  የኔትወርክና የኢንተርኔት መቆራረጥ መንስኤ የ4G ኔትዎርክ ማሻሻያ እየተደረገ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል።

የኢትዮ ቴሌኮም ኮንሶ ሾፕ ሱፐርቫይዘር አቶ ጌቱ ጎዳ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ለአንድ ወር ያህል ጊዜ የሚቆይ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም ለተወሰኑ ጊዜያት የኔትወርክና የኢንተርኔት መቆራረጥ ለአጫጭር ደቂቃዎች ሊያጋጥም እንደሚችልና ህብረተሰቡ በትዕግስት እንዲጠባበቅ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

መረጃው የዞኑ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine
2025/01/23 05:31:05
Back to Top
HTML Embed Code: