"ኢትዮጵያ በአመት የማር ምርት የማምረት አቅሟ 500 ሺህ ቶን ቢሆንም 10 በመቶውን ብቻ ነው የምታመርተው"- ጥናት
ኢትዮጵያ በአመት የማር ምርት የማምረት አቅሟ 500 ሺህ ቶን ቢሆንም በዘርፉ ባሉ ተግዳሮቶች 10 በመቶውን ብቻ እንደምታመርት አንድ ጥናት አመላከተ።
ጥናቱን ያጠኑት በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት መሪ ተመራማሪ እና የእንስሳት ፖሊሲ ምርምር ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ቤኛ ሲሆኑ 22 የዘርፉ ተዋናኞች ተካተውበታል።
ዶክተር ደሳለኝ ቤኛ በኢትዮጵያ የንብ አረባቡ እና አመራረቱ 92 በመቶ የሚካሄደው በባህላዊ ዘዴ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ዶክተር ደሳለኝ ቤኛ በዝርዝር ምን አሉ ?
የዓለም የማር ፍላጎት እየጨመረ ቢመጣም ኢትዮጵያ ጥራት ባለው የግብአት አቅርቦት ውስንነት፣ በቂ መሠረተ ልማት ባለመሟላቱ እና ለንብ አናቢዎች በቂ ሥልጠና ባለመሰጠቱ ማምረት ከሚገባት በጣም ዝቅተኛ እያመረተች ትገኛለች።
ደረጃቸውን የጠበቁ የምርት ጥራት ማረጋገጫ ዘዴዎች አለመኖራቸው በዓለም ገበያ ያላትን ተወዳዳሪነትም በእጅጉ እየጎዳው ነው።
በጥናቱ ማረጋገጥ እንደተቻለው የምናመርትበት ቴክኖሎጅ የችግሩ መንስኤ ነው። የንብ አረባቡ እና አመራረቱ 92 በመቶ የሚኣሄደው በባህላዊ ዘዴ ነው። ይህ ደግሞ ለአመራረት ምቹ አይደለም።
ምክንያቱ ደግሞ ማሩ ሲቆረጥ የሞቱ ንቦች አብረው ይቀላቀላሉ፣ የማሩ እንጀራ እና ማሩ አንድ ላይ ይሰባበራል። ጥራቱንም በእጅጉ እየጎዳው ነው።
ለማምረቻ እና ለምርት ውጤቶች የሚሆኑ የግብአት አቅርቦት የለም፣ ያሉትም ጥራታቸው ከፍተኛ ችግር አለበት።
ምርቱም ምግብ ነክ በሆኑ እና ባልሆኑ እንደ ስኳር ባሉ ነገሮች እየተከለሰ ለገበያ እየቀረበ ነው። በጥራት ጉድለት ላኪዎችም በአለም አቀፍ ገበያው ላይ ተወዳዳሪ አለመሆናቸውን በግልፅ አስቀምጧል።
በዘርፉ የተሰማሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶች የራሳቸውን ፕሮጀክት አላማ ወይም ሪፖርታቸውን ለማሳካት ብቻ ነው የሚሰሩት። ይህ ደግሞ ዘርፉን እየፈተነው ነው።
የአረባብ ዜዴውን ማዘመን፣ ለአምራቾች የቴክኖሎጅ አጠቃቀምን ማስተማር፣ የፀረ ተባይ ኬሚካሎችን አጠቃቀም ግንዛቤ መስጠት፣ በዘርፉ ያሉ ፖሊሲዎች ተግባራዊ የሚሆኑበትን ሁኔታ መፍጠር አስፈላኪ መሆኑን ገልፀዋል።
የላኪዎችን አቅም ማሳደግ እና ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ አርሶ አደሮችን በማሰባስብ እንድያመርቱ ማድረግ፣ የማር ምረት መያዣ እቃዎችን ጥራት ማሳደግ፣ ባለሀብቶችን ወደ ዘርፉ ማምጣት ለችግሮቹ መፍትሄ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@TikvahethMagazine

❤56👍12👎6🔥6🤣5🙏2🕊1
በ9 ወር ውስጥ 2722 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሞተዋል፣ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው የትግራይ ክልል ነው :- የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት በ9 ወር ውስጥ 2722 ሰዎች በትራፊክ አደጋ መሞታቸውን እና በአመቱ መጨረሻ ላይ ሁሉም መረጃዎች ሲሰባሰቡ የሞት መጠኑ ከፍተኛ ጭማሪ ሊኖረው እንደሚችል ገልጿል።
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ምክትል ስራ አስኪያጅ መሀመድ ሀሰን የባለፉት አመታት ሪፖርቶችን በማሰባሰብ የትራፊክ አደጋ በምን ደረጃ ላይ መሆኑን የሚያሳይ ጥናት አድርገናል ብለዋል።
አቶ መሀመድ ሀሰን ስለጥናቱ በዝርዝር ምን አሉ?
የአለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ በ2023 ይፋ ባደረገው ሪፖርት በየአመቱ 1.19 ሚሊየን ገደማ ሰዎች ይሞታሉ፣ ከዚህ ውስጥ 13 በመቶ የሚሆነውን ኢትዮጵያ ትይዛለች።
በየአመቱ ከ3 እስከ 4 ሺህ ሰዎች ይሞታሉ፣ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ህፃናት እና ከ15-29 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ናቸው። በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ ሀገር ምን ያክል እየተጎዳች መሆኑን መገንዘብ ተችሏል።
በ2016 ዓ.ም በፌዴራል ፖሊስ በኩል በተደረገ ሪፖርት 3111 ሰዎች ሞተዋል። 10 ሺህ ዜጎች ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ወደ 4 ቢሊዮን አካባቢ የንብረት ውድመት ደርሷል።
በ2017 ዓ.ም ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር 489 አካባቢ አደጋዎች ጭማሪ አለው፣ ከባለፈው አመት ዘጠኝ ወር ጋር የዘንድሮው አመት ሲነፃፀር 21 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
አሽከርካሪዎች ለአደጋ የሚጋለጡበት ምክንያት ምንድን ነው ?
- ከተፈቀደላቸው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር፤
- እርቀትን ጠብቆ አለማሽከርከር
- በአሽከርካሪዎች የሥነ-ምግባር ጉድለት፤
- ሹፌሮች ያለምንም እረፍት እስከ 72 ስአት ማሽከርከር ተጠቃሽ ናቸው።
አደጋዎች የሚበዙት ምቹ በሆኑበት ቦታ ላይ ነው።
በትግራይ ክልል በ9 ወር ውስጥ 264 ዜጎች ሞተዋል። ይህ የሆነው አደጋዎች ከተከሰቱበት እስከ 1 ወር የህክምና አገልግሎት አግኝተው ህይወታቸው የሚያልፉትንም ስለተካተቱ ነው። ይሁን እንጅ በ2017 ዓ.ም የትራፊክ አደጋ የመጨመር አዝማሚያ ላይ ነው።

❤97😢51🕊12👍6🔥4🙏1
#Et_Coders -- Online Summer Bootcamp & SAT Preparation Program
ልጆችዎ ከቤታቸው ሆነው የትም ሳይወጡ በዚህ ክረምት በ online
👉 Computer Basics
👉 Website Development
👉Computer programming with Python
👉 How to use AI + AI guided website development
ያስተምሯቸው።
እንዲሁም scholarship apply ለምታደርጉ ለ SAT ፈተናቹ
እነዚህን አዘጋጅተናል 👇👇👇
👉በፈተናው መሰረት ሁሉንም የ English Reading/Writing እና Maths topic የተብራራ ጥናት
👉ከፈተናው ጋር ተመሳሳይነት ያለው mock exam መስራት
👉ከዚህ በፊት ከተፈተኑ ሰዎች የልምድ ልውውጦችን ማግኘት
ምዝገባ ሃምሌ 4 ይጠናቀቃል። የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ሃምሌ 7 የጀምራል።
ክፍት ቦታዎች እየሞሉ ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ።
ለመመዝገብ: በስልክ ቁጥራችን
📞0944352126
📞0979779772 ይደውሉ።
ወይም ዌብሳይታችንን በመጎብኘት ይመዠገቡ
www.etcoders.com
#etcoders #Bootcamp #onlineclass #SATprep

❤19👍2🤔1
አስቸኳይ የደመወዝ ብድር ይፈልጋሉ?
ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ/ማ አለልዎት!
✅ ፈጣን የደመወዝ ብድር – በ 30 ደቂቃ ውስጥ ያግኙ!
✅ ቀላል ሂደት: ያመልክቱ ➡️ ያረጋግጡ ➡️ ገንዘብ ይቀበሉ!
✅ ለቋሚ የመንግስትና የግል መስሪያ ቤት ሰራተኞች ብቻ.
አሁን ያመልክቱ: https://forms.gle/9Z4Tys3LqeFTr91v9
ጥያቄ አለዎት? በቴሌግራም ያግኙን: www.tgoop.com/Digafmfip ወይም ይደውሉ #6575.
ፈጣን፣ደህንነቱ የተጠበቀ፣አስተማማኝ።
ተደራሽነት ያለገደብ!
ድጋፍ አነስተኛ ብድር አቅራቢ አ/ማ

❤14🙏3
"የትኛውም ቦታ ያለው ሞት እንዲመዘገብ የሚያስገድድ ህግ አውጥተናል" የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት
በትራፊክ አደጋ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና ህይወታቸው ላለፈ ዜጎች ከዚህ በፊት ይሰጥ የነበረው የካሳ ክፍያ ትንሽ በመሆኑ በየሰፈሩ በሀገር ሽማግሌዎች በመቶ ሺዎች ድርድሮች ነበሩ።
ይህም የሚደርሱ አደጋዎች በአግባቡ ሳይመዘገቡ እንዲቀር እና ጉዳቶቹን ለመመዝገብ አስቸጋሪ እንዳደረገው ይታመናል።
በትሪፊክ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች የሚሰጠው የካሳ ክፍያ መጨመሩ ይህንን ተግዳሮት ይቀንሰዋል ሲባል ሌሎች አጋዥ ህጎችም ተግባራዊ መደረግ ጀምረዋል።
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አባሶ በትራፊክ አደጋ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና ህይወታቸው ላለፈ ዜጎች ከዚህ በፊት ይሰጥ የነበረው የ50ሺህ ብር ካሳ ወደ 250 ሺህ ብር ከፍ መደረጉን ያስታውሳሉ።
አሁን ላይ በየትኛውም የሀገሪቷ ክፍል ውስጥ ያሉ ዜጎች የዚህ አደጋ ሰለባ የሆነ አካል ጥያቄ አቅርቦ ካሳውን መውሰድ እንደሚችል ነው ያነሱት።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጀማል አባሶ ምን አሉ?
ከሚደርሱት አደጋዎች 68 በመቶ በአሽከርካሪዎች ጥፋት ነው፣ 14 በመቶ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ማነስ ነው።
በየዓመቱ አደጋዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ የሆኑ ስራዎችን እንሰራለን፣ እንደክማለን፤ ግን የምናመጣው ለውጥ በጣም፣ በጣም ትንሽ ነው፣ ይህ ደግሞ የሞት ምጣኔው ላይ ካለፉት ዓመታት ልዩነት የለውም።
የትኛውም ቦታ ያለው ሞት እንዲመዘገብ የሚያስገድድ ህግ አውጥተናል። ከዚህ በፊት በየሰፈሩ በእርቅ የሚያልቁ ጉዳዮች ነበሩ። ይህ የሆነው ከመንግስት ይሰጥ የነበረው ካሳ ትንሽ ስለነበር ነው።
ምን ያክል ሰው እንደተጎዳም ፖሊስ መዝግቦ ወደ ሪፖርት ቋት አያስገባም ነበር። በዚህም ትክክል መረጃ እንዳናገኝ ተፅዕኖ አሳድሮብን ቆይቷል።
አሁን ላይ በአካል ላይ ጉዳት ለደረሰበት ወይም ለሞተ ሰው 250 ሺህ ብር፣ ለአስቸኳይ ህክምና 15 ሺህ ብር ይከፈላል፣ በንብረት እና በተሽከርካሪ ላይ ለደረሰ ጉዳት ይሰጥ የነበረው ካሳ ከ100ሺህ ወደ 200 ሺህ ከፍ ተደርጓል። ይህ መሆኑ በየሰፈሩ ከመደራደር ይልቅ ወደ ኢንሹራስ ተቋማት እንዲመጡ አድርጓል።
የካሳ ጥያቄ ያለው ሰው በኢንሹራንስ ተቋማት በመምጣት መጠየቅ ይችላል ያሉ ሲሆን በየሰፈሩ በእርቅ ያለቀ ጉዳይ ካለም ህጉ ስለሚያስገድድ እንደሀገር መረጃው እንዲመዘገብ መደረጉን እና የአደጋዎችን መጠን እየታወቀ ነው።
አደጋ አድርሰው የሚሰሩ አሽከርካሪዎች ቢኖሩም አደጋ ለደረሰበት ሰው ካሳ ይሰጠዋል።
አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የትራፊክ አደጋዎች ሲከሰቱ በአቅራቢያው ያሉ ጤና ተቋማት እስከ 15 ሺህ ብር የሚያስወጣ የህክምና እርዳታ የማድረግ ኃላፊነት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ተሰጥቷቸዋል።
በዓለም አቀፍ ኢትዮጵያ በመኪና ብዛት ትንሽ፣ በአደጋ ብዛት ደግሞ ቀዳሚ ናት። የአለም ሀገራት የትራፊክ አደጋን ዜሮ ለማድረግ እየሰሩ ባሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያ በየአመቱ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን፣ ሙህራንን፣ ህፃናትን እያጣች ነው። ችግሩን ለመቀነስ ጉዳዩ የፖለቲካ ይዘት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethMagazine

❤49👍5👎2🔥1🤔1🕊1
ኢትዮጵያ ከእንስሳት እርባታ ከ7.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከወተት እና ከበሬ ምርት በየዓመቱ ገቢ ታገኛለች። ሆኖም ግን ዘርፉ በተለይም በመኖ አቅርቦትና ጥራት ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈተነ ይገኛል።
በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የእንስሳት ፖሊሲ ምርምር ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ደሳለኝ ቤኛ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ በመኖ አቅርቦት ችግር ምክንያት የማኅበረሰቡን የእንስሳት ተዋፅዖ ፍላጎት ማሟላት አለመቻሉን በተካሄደ ጥናት መለየቱን ገልፀዋል።
በሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ በከተሞች መስፋፋት እና የኑሮ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ በ2050 የእንስሳት ተዋጽኦ ፍላጎት አሁን ካለው ፍላጎት በ5 ወይም በ8 እጥፍ እንደሚያሻቅብ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች እንደሚጠቁሙ ኃላፊው ያነሳሉ።
ዶ/ር ደሳለኝ ቤኛ በዝርዝር ምን አሉ ?
ኢትዮጵያ ውስጥ የመኖ ምርት እ.ኤ.አ በ2020 ከነበረው 120 ሚሊዮን ቶን በ2024 ወደ 200.5 ሚሊዮን ቶን አድጓል። ሆኖም ይህ ጭማሪ አሁንም እያደገ የመጣውን ፍላጎት አላሟላም።
"የመኖ ፍላጎት እና አቅርቦት አልተጣጣመም፣ የግጦሽ መሬቶች ለእርሻ ስራ እየዋሉ ተመናምነዋል። በዚህ ልክ የእንስሳቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነው።
እንስሳቶች በየቀኑ 2 በመቶ ክብደት መጨመር አለባቸው የሚሉ አለም አቀፋዊ እሳቤዎች አሉ፣ ግን እኛ ሀገር ሲታይ ሰፊ ልዩነት መኖሩን ያሳያል።
በመኖ አምራቾች ላይ ተጥሎ የነበረው ግብር ከዚህ በፊት መንግስት ያነሳ ቢሆንም በዘንድሮው ዓመት መንግስት መልሶ በመጣሉ ለአምራቾች ተግዳሮት እንደሆነባቸው በጥናቱ ተገኝቷል። መንግስት ታክሱን ለማንሳት ማሰብ አለበት።
የእንስሳት ዘርፉ እራሱን የቻለ ፖሊሲና የተረጋጋ ተቋማዊ አደረጃጀት የለውም፣ ከሰብል ምርት ጋር ተጨፍልቋል። ይህ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረታቸው ወደ ሰብል ሆኗል።
ስለዚህ የራሱ አደረጃጀት እና ፖሊሲ ሊኖረው እና መዋቅሩን ለብቻው በማውጣት፣ ወደ ሚኒስቴርነት ሊወስደው ይገባል የሚል ምክረ-ሀሳብ ያቀርባሉ።
በድርቅ ለተጎዱ እንስሳቶች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጊዜያዊ መፍትሄ ከሚሰሩ ይልቅ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንዲያመጡ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራበት እንደሚገባ በዘርፉ ለበርካታ አመታት ጥናት ያጠኑ ሰዎች ያነሳሉ።
አሁን ያለንበትን ችግር ለመቅረፍ የተሻሻለ የእንስሳት ዝርያን ማዳቀል መፍትሄ አንደሆነ በጥናቱ የተካተቱት አጥኝዎች ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤74👍8🙏2🤝2🕊1
"ኤምባሲው ምንም አይነት ኮንፈረንስ አላዘጋጀም" - በቴል አቪቭ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢሚባሲ
በእስራኤል ቴል አቪቭ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በኤንባሲው ስም ምንም አይነት ኮንፍረንስ አልተዘጋጀም ሲል እወቁልኝ ብሏል።
በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት በደቡባዊ እስራኤል አሽዶድ ከተማ ከጁላይ 25-30 የሚቆይ ኮንፈረንስ እንደተዘጋጀ በማስመሰል ሰዎች ገንዘብ እንዲያስገቡ እየተጠየቀ ይገኛል ሲል ነው የገለጸው።
"በተጠቀሰው ጊዜ በኤምባሲው ምንም አይነት ኮንፈረንስ ያልተዘጋጀ መሆኑንና በፎቶ እየተዘዋወረ ያለው የግብዣ ደብዳቤ ፍጹም ሐሰትና ለማጭበርበር የተዘጋጀ ስለሆነ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ እናሳስባለን" ብሏል ኤምባሲው።
ፎቶ: ኤምባሲው ለማጭበርበር ተግባር እየዋለ ነው ሲል ያጋራው የግብዣ ደብዳቤ።

❤58🤣16👎7🕊2🤯1🤬1🙏1
አፋልጉን !
በፎቶው የምትመለከቷት ህፃን የምስራች ትባላለች።
ሰኔ 10 ቀን 2017 ከቀኑ 4 ሰዓት አካባቢ ሱቅ ሄዳ አልተመለሰችም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የት እንዳለች አይታወቅም።
ቤተሰብ ጭንቀት ላይ ይገኛል።
የምስራችን የተመለከታችቱ ወይም ያለችበትን ቦታ የምታውቁ ካላችሁ ከታች ባላት የስልክ ቁጥሮች በመደወል አሳውቁን።
ስልክ፡ 0912449027 / 0916815100
@tikvahethmagazine

😢125❤50🙏11🤔5👍2
የገዛ የ12 ዓመት እህቱን የደፈረው ተከሳሽ በ15 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ!
በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ የ12 ዓመት ታናሽ እህቱን የደፈረው ተከሳሽ በዛሬው ዕለት በችሎት ቀርቦ ጥፋተኛ ተብሏል።
ተከሳሹ ድርጊቱን ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እህቱን በማታለል ወደ ጫካ ከወሰደ በኋላ መፈጸሙን የክስ መዝገቡ ያስረዳል።
ተከሳሹ በዐቃቤ ህግ ድርጊቱን ስለመፈጸሙ የቀረበበትን ክስ ሙሉ በሙሉ መፈጸሙን በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል በዝርዝር አምኗል።
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የቁጫ ወረዳ ፍ/ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
መረጃው የቁጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

👎243💔83🤬62❤54🤔16😢14👍4🤯4🕊3🤷♂2
🎁ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
💎 ባለ 1 መኝታ በ 487,118 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🛍️🛒ሱቆች ከ 50 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ
- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️ 0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp

❤15🔥1
በ2050 አፍሪካ በታዳሽ ኃይል የተነሳ 5 ትሪሊየን ዶላር ከማውጣት ትድናለች ተባለ።
ፓወርሺፍት አፍሪካ ባወጣው ሪፖርት አፍሪካ ፊቷን ወደ ታዳሽ የኃይል ምንጮች በማዞር በ2050 አምስት ትሪሊየን ዶላር ወጪ ከማውጣት ከመዳኗ በተጨመሪ በአኅጉሪቱ ያለውን የኃይል እጥረት ትፈታለች ሲል አስቀምጧል።
በዚህም እ.ኤ.አ በ2050 ከ3-5 ትሪሊየን ዶላር ወጪ በመቆጠብ በዓመት እስከ 150 ቢሊየን ዶላር ትርፍ እንደምታገኝ ይጠቁማል።
ይህም ማለት አፍሪካ ለነዳጅ፣ የድንጋይ ከሰል እና ጋዝ ግዢ የምታወጣውን 8 ትሪሊየን ዶላር ያድንላታል።
ይህ ወጪም የታዳሽ ኃይሎቹን መሰረተ ልማት ለመገንባት ከሚያስፈልገው ገንዘብ በሁለት እጥፍ የሚበልጥ ነው።
በሪፖርቱ እንደተቀመጠው አፍሪካ 1 በመቶ የሚሆነውን መሬቷን በመጠቀም ብቻ ከፀሐይ ኃይል 480,000 ጊጋዋት ኃይል ማመንጨት ስትችል አኅጉሪቱ ከኢነርጂ ዘርፉ ጋር የተያያዘ 2.2 ሚሊየን ስራዎች መፍጠር ያስችላታል።
በአፍሪካ አሁንም 640 ሚሊየን ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል የሌላቸው ሲሆን 75 በመቶ ያህሉ የኃይል ምንጭ የተፈጥሮ ጋዝና የድንጋይ ከሰል ናቸው።
Source: CNR

❤54🤔6🕊4👍3🙏2
በመዲናዋ የሠራተኞችን ደኅንነት በማያስጠብቁ ገንቢዎች ላይ ምርመራ ሊደረግ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ከሀምሌ 5/2017 ዓ.ም ጀምሮ የግንባታ ቦታዎችን የሚመረምር አዲስ ግብረ-ሃይል ወደ ስራ እንደሚገባ ገልጿል።
በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኢንጂነር አበበ እሸቱ ይህ አዲስ ግብረ ኃይል በኮንስትራክሽን ቦታዎች ላይ በመንቀሳቀስ የሠራተኞችን ደኅንነት የማያስጠብቁ ወይም የደኅንነት ህጎችን የማያሟሉትን እንደሚለዩ ተናግረዋል።
ይህን ግብረ-ኃይል ማሰማራት ያስፈለገው እ.ኤ.አ ከ2022 ጀምሮ ደኅንነታቸው ባልተጠበቁ ቦታዎች ላይ ቢያንስ 142 ሠራተኞች መሞታቸውን ተከትሎ መሆኑን እና ይህ የሞት መጠን እያሻቀበ መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ አደጋዎች በማመላከታቸው ነው ተብሏል።
በኮንስትራክሽን የሥራ ዘርፍ ከተሰማሩት ሠራተኞች ውስጥ 99 በመቶ የሚሆኑት መደበኛ የደኅንነት ሥልጠና እንደሌላቸው በጥናት ተገኝቷል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፥ "በከተማችን የግንባታ ስራዎች በሚካሄዱባቸው ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ የተለያዩ አደጋዎች ይከሰታሉ፣ ስጋቶችም አሉ። ለዚህ መንስኤው ሰራተኞች ስልጠና አለመውሰዳቸው እና ገንቢዎች ለሰራተኞች የሚሆኑ የደህንነት መጠበቂያ ግብአቶችን ባለማቅረባቸው ነው" ሲሉ ነው የገለጹት።
በግንባታ ቦታዎች ላይ በተለያዩ ምክንያቶች የሞቱ ሰራተኞች ቁጥር ይገለፅ እንጂ ተሸፋፍኖ የሚቀር ያልተቆጠሩ ሠራተኞች ስለመኖራቸውም ነው የተነገረው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ከተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ሠራተኞችን በመመደብ 2681 ግንባታዎችን መመልከት መቻሉን አንስቷል።
ከእነዚህ ውስጥም 1300 አካባቢ የሚሆኑት ብቻ ለሠራተኞቻቸው ሄልሜንት እና አንፀባራቂ ማሟላት የቻሉት። ይህ ማለት ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ህጎችን እያከበሩ አይደለም።
አብዛኞቹ ሠራተኞች አደጋ ላይ መሆናቸውን ተመልክተናል ያሉት ዳይሬክተሩ፥ የህንፃ ግንባታ ደኅንነት ያልጠበቀ ኮንተራክተር ወይም አልሚ የ50 ሺህ ብር ቅጣት እንደሚጣልበት በህግ ደረጃ ተቀምጧል ብለዋል።
አክለውም፥ አዲስ ግብረ ሀይሉ በሚለያቸው ግንባታዎች ቦታዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ጠቁመዋል።

❤66👍24🔥6👏5🤔1🙏1🕊1
ዲኤስቲቪ በሞባይል መተግበሪያው ላይ ሽልማት የሚያስገኙ ጨዋታዎችን አስጀመረ።
መልቲቾይዝ በማይ ዲኤስቲቪ መተግበሪያ ውስጥ ደንበኞቹ አሁን ከስፖርት እና ከፕሮግራሞቹ ጋር የተያያዙ ጌሞችን መጫወት እንደሚችሉ ይፋ አድርጓል።
መልቲቾይዝ አክሎም ደንበኞቹ ጌሞቹን በሚጫወቱበት ወቅት የቦክስ ኦፊስ ፊልም፣ የፓኬጅ እድገት እና የፕሮግራም መግቢያ ትኬቶችን የመሳሰሉ ሽልማቶችን ያገኛሉ ብሏል።
ጌሙ ባለፈው ሳምንት የጀመረ ሲሆን በአማካይ ሰዎች በአንድ ጊዜ ቆይታ እስከ 41 ደቂቃ ድረስ እየተጫወቱት መሆኑም ተገልጿል።
Source: Mybroadband

❤13
ናይጄሪያ በኢንጂነሪንግ የተመረቁ ተማሪዎቿ ተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲማሩ ማስገደድ ልትጀምር ነው።
ናይጄሪያ ከፖሊቴክኒክ እና ዩኒቨርሲቲዎቿ በኢንጂነሪንግ ዘርፍ የተመረቁ ተማሪዎች ከምርቃታቸው በኋላ የአንድ ዓመት ትምህርት በግዴታ እንደሚማሩ ገልፃለች።
የትምህረት ፕሮግራሙ ወጣቶቹ ከብሔራዊ አገልግሎታቸው በፊት በቂ ተግባራዊ እውቀት እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው ተብሏል።
እንደዚህ ያለ የትምህርት ማዕቀፍ ከ40 ዓመት በፊት ይሰጥ እንደነበር አመራሮች ሲገልፁ እንደ ህግ እና ጤና ባሉ ዘርፎች የነበረው አሁን በአዲስ ስያሜ እና ሁኔታ በኢንጂነሪንጉም እንደሚጀመር ተመላክቷል።
ተመራቂዎች ከምርቃታቸው በኋላ ለአንድ አመት በሬዚደንሲ እንደሚቆዩ እና አንድ ሰው በኢንጂነርነት ለመታወቅ እንደ አንድ መመዘኛ እንደሚታይ ተገልጿል።
በተጨማሪ መንግስት ለተመራቂዎቹ በወር 75,000 ናይራ ለመስጠት ማቀዱ ሲነገር ፕሮግራሙ ተወዳዳሪ ኢንጂነሮችን ለማፍራት ይረዳል ተብሏል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም ለኢንጂነሮች እና ለቴክኖሎጂስቶች የሚከፈለውን ክፍያ በተመለከተም ውይይት እንደሚኖሮ እና ማሻሻያ እንደሚደረግ ተገልጿል።
Source: Punch

❤80🤣44👏11😢5🙏1🕊1