Telegram Web
አይደለም ምኞቴ

(#በእውቀቱ ስዩም)

አይደለም ምኞቴ
ለምለም አንገትሽ ላይ : ክንዶቼን መጠምጠም
ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ: ጭንሽ ማሃል መስጠም
እይደለም ምኞቴ

ከንፈርሽን ማለብ
ቀሚስሽን መግለብ
ከገላሽ ቆርሼ :ገላየን መቀለብ
ደረትሽን ማለም
ጡትሽን መሳለም
በቁንጅናሽ ጅረት : ገነቴን ማለምለም
አላማየ አይደለም::

ምኞቴን ልንገርሽ?

ካለሺበት ቦታ: ቀልቤን ማሰማራት
ወትሮ ካንቺ ጋራ: ቡና መጠራራት
ሰላም መገባበዝ: ትዝታ መጋራት

የጨለመ ፊቴን : ባይንሽ ጮራ ማድመቅ
በቃላትሽ መስከን: በሳቅሽ መጠመቅ
በጎ መንፈስሽን :ካይንሽ ላይ መሻማት
ርጋታሽን ማጥመድ : ዝምታሽን መስማት::

>>>>ሼር ያድርጉ>>>
@TkYEGITMABIYOT
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይህች በብዙዎች በምትታወቅበት ስሟ #የልጅ_ማኛ ትባላለች። በቲክቶክ ከ400ሺ በላይ ተከታይ ያላት ተፅዕኖ ፈጣሪ እንስት ነች።

- በኔ እይታ በርካታ አክቲቪስቶች ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ያለችበትን ሁኔታ በአቅማቸው ልክ ለመተንተን ጥረዋል። በርካታ የጥበብ ሰዎች በተሰደሩ ቃላት ግጥም ወጣቸው ላይ ቅኔን ቅመም አርገው ህዝብን እፎይ ለማስባል ጥረዋል። በርካቶች በየሰፈሩ ተሰብስበው በቡና ጨዋታ መሀል ግላዊ ሃሳብ ተለዋውጠዋል። ለኔ እንደሚገባኝ ግን ያም አለ ይህ ከዚህ ምስል በላይ ገላጭ አይደለም። እነሱም ይሄን ሲያዩ "እፎይ"ብለው እንደሚተነፍሱ አልጠራጠርም። የልጅ ማኛ አንድ የተከሰተን ነገር በቪዲዮ ቀርባ ስትናገር እንደው እንደወረደ ሳይሆን ታሪክ አጣቅሳ መዝገብ በርብራ "እንዴት ነው የማወራው እየገባችሁ ነው ወይ?" በሚል አይን አያየች ነው የምትጨርሰው። ይህ ያሳለፍናቸውን የጭንቅ አመታት ምንም ሳያወራ እየተናገረ ያለ ማንነታችን ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሁሉ ይህን ሲመለከት ፍንትው ብሎ የሚገለፅለት ሀቅ አለ። ነፃ ታሳሪ መሆኑ፣የቁም ሟች ስያሜ ማግኘቱ ፣አምላኩን የሚማፀንበት የእምነት ስፍራው መወጋቷን ...ሌላም ሌላም!!! እናንተን ምን ተሰምቷችሁ ይሆን?

«ክፉ ንጉስ መጣ
ደግ ንጉስ መጣ
ሁሉም ይኼዳሉ እንዳመጣጣቸው
ሳቅና ለቅሶሽን አይገዙትምና
ሁሉም ይኼዳሉ እንዳመጣጣቸው፣
ሳቅና ለቅሶሽን አይገዙትምና፣
አትፍሪ እናታለም ኑሪልን በጤና።»
ጂጂ

እህታችንን ከልብ እያመሰገንኩ ሀገራችን ኢትዮጵያ ፍክትክት ብላ የምናይበት ደግ ዘመን ይመጣ ዘንድ እመኛለሁ። ደግ ዘመን አምጣ🙏

(✍️ ኪዳ የገጠር ልጅ_ቅዱስ)
ሰኔ 2/2015


@TkYEGITMABIYOT
@TkYEGITMABIYOT

ብቻውን ነው በሏት!
ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ምስጋና አቀረበች

https://vm.tiktok.com/ZM2qRRDpd/
በግብረሰዶማውያን ላይ ያለኝ የግል ምልከታ ይህን ይመስላል። 👉👉👉 1hour ago

https://vm.tiktok.com/ZM2WrwWRg/
Alemayehu Gelagay "ማሰብ ባለመቻላችን ብቻ መጥፊያችን ደርሷል" ብሎ መናገሩን ተከትሎ ይመስለኛል Jhonny Habte ከመጥፋታችን በፊት ብሎ መቻልን ችሎ ሊያስችል ብቅ ያለው 😁 ... (ነሐሴ 2 - ማክሰኞ - ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት እንገናኝ ማለቱ። ያድርሰን🙏
ቤተሰቦች ይህን የምታዩትን ማስታወቂያ ሴቭ በማድረግ ዛሬ ነሀሴ 1 ከቀኑ 10:00 ሲሆን በፌስቡክ ገፃችሁ ላይ እኩል እንድንለቀው ትዕዛዝ ወርዷል። ሁላችንም በተመቸን ገለፃ በእኩል ሰዓት እንልቀቀው። ላልሰሙ ወዳጆች በውስጥ መስመር ሼር አድርጉላቸው🙏

የግጥም አብዮት
(አሸናፊው ፍቅራችን ነው)
መስከረም 1 ልደቱ ለሆነው ደራሲ እና ገጣሚ ዮሀንስ ኀብተማርያም ስጦታ ለመስጠት 300 ሰዎች እንደሚያስፈልጉ ተናግሬያለሁ። በመሆኑም ከነዚህ መካከል መሆን የምትሹ 350ብር በማዘጋጀት ወዲህ ኑ። ፍቅር ሰው ማኅሌት የተሰኘ መፅሀፉን እየወሰዳችሁ አዲሱን አመት ተቀበሉ ።

* * * * በሉ አሁኑኑ ስልካችሁን አንሱና ወርወር ወርወር አድርጉ። ከሌላ ሚዲያ ይልቅ ደራሲውን ይሄ መንደር በሚገባ ያውቀዋልና ፍቅራችሁን ግለፁ * * * *

1000160263664 = የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

15454571 = አቢሲኒያ ባንክ

ስም - ቅዱስ ታደሰ ንጉሴ

ቴሌ ብር = 0960262399

ደረሰኝ ለመላክ(ለማውራትም ጭምር) Telegram,Imo... - @TKida (0960262399)

መፅሀፉን ለመውሰድ 👉 6ኪሎ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መሄጃ - ሐበሻ ቡና ( በዚያ ይገኛል ) ውጥኔ ይሳካ ዘንድ ፈጣን ትብብር አድርጋችሁ አስደስቱኝ። መጪው አዲስ ዓመት ፍፁም የምትደሰቱበት እንዲሆን ከወዲሁ እመኛለሁ።
4_5764840091218350035.pdf
153.8 KB
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር
@TkYEGITMABIYOT
ናፍቆት
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እንዲህ እንደዛሬ...
በመሀከላችን
ንፋስ ሳይግባብን ፣ ፍጥረት ሳይፈጠር
በኔና አንቺ መሀል...
የነበረው ክፍተት ፣ አንድ ስንዝር ነበር።
አንቺ ሰማይ ሆነሽ እኔ ደግሞ ምድር!!!
............................................
በዚህ ስንዝር መሀል....
እስትንፋስ ያላቸው ሰዎች ተፈጠሩ
እነዚህ ሰዎችም....
ቅርብ ላለች ሰማይ
የምድርን ሀጥያት ይነግሯት ጀመሩ።
"ምድር ዘማዊ ነው
ምድር ሀጣዊ ነው
ብትሸሺው ይሻላል ይህ ዓለም ጠፊ ነው"
እያሉ ሲነግሯት የሰው ወሬ ሰምታ
ሰማይ ፊኛ ሆና...
ትለጠጥ ጀመረ ከኔ ተለይትል
በሰዎች እስትንፋስ...
ወደ ላይ ተነፍታ
ወደጎንም ሰፍታ።
.......................................
እንጂማ አውቃለሁ እንጂማ ታውቂያለሽ
የሰው ወሬ ሰምቶ ልብሽ ባይረበሽ
እንዲህ እንደዛሬ
ሳትርቂኝ በፊት ሰማይ ቅርብ ነበርሽ።
................................................
እንደውም እንደውም...
በዛ ስንዝር መሀል ያኔ የተፈጠሩ
እዛሬ ላይ ሆነው..
"ሰማይ ቅርብ ነበር" እያሉ ሚያወሩ
እድሜ የሰጣቸው
ጥቂት ሰዎች አሉ
የኔና ያንቺ ፍቅር የሚመሰክሩ።
.............................................
እንደውም እንደውም....
ሌላ አይነት ማስረጃ ሌላ አይነት ምስክር
ሰማይ ቅርብ ሳለሽ ምጣድ ሆኜ ምድር
እንዲህ እንደዛሬው...
ነፋስ አቀጣጥሎት
ነፋስ የሚያጠፋው እሳት ሳይፈጠር
የሰው ልጆች ሁሉ
በፀሐይ በርሀን ምግብ ያበስሉ ነበር።
.............................................
ፀሐይ ውበትሽ ነው ጠዋት የምሞቀው
ቀን ተቃጥዬበት ሌት የምናፍቀው።
ለሊት ላይ ያመኛል ህመሜም አንቺው ነሽ
ቀኑ ጨለማ ነው...
ነግቶ እስካይሽ ድረስ ትናፍቂኛለሽ።
...........................................
መቼ ነው ሚነጋው?
ፀሐዩ ውበትሽ ምድርን የሚከድነው
መርዙ መድሀኒትሽ...
በሽታዬን ገድሎ ህመሜን ሚያድነው
ካፈቀሩት ጋራ....
እንኳን ላንድ ለሊት
ላፍታ ያህል እንኳን መለያየት ሞት ነው።
.............................................
መቼ ነው ሚነጋው ልቤን ይበርደኛል
ንጋት ላይ የሚሸሽ..
ወረተኛ ፍቅር ጤዛው በዝቶብኛል
አንቺ የሌለሽበት...
ራሴን ሳስበው ራሴን ያዞረኛል።
ለራስ ምታት ህመም..
መድሀኒት እንዲሆን
በሽታን የሚገድል መርዝ ነው ሚቀመም።
...................................
እንጂማ አውቃለሁ እንጂማ ታውቂያለሽ
የሰው ወሬ ሰምቶ ልብሽ ባይረበሽ
እንዲህ እንደዛሬ.
ሳትርቂኝ በፊት ሰማይ ቅርብ ነበርሽ።
........................
እየሔዱ መጠበቅ

@TkYEGITMABIYOT
@TkYEGITMABIYOT
@TkYEGITMABIYOT
እውነት እውነት እልሃለሁ ከጠቀመክ

በተቻለህ አቅም ቶሎ ሊያውቁህ ጓደኛ ወዳጅ ሊያረጉህ፣ ቶሎ ሊቀርቡህ ከሚፈልጉ ሰዎች እድሜህን ሙሉ እራቅ። አየህ የፍቅር የጓደኝነት የጥቅም ነጋዴዎች መጀመሪያ የሚያደርጉት እንደዚያ ነው። ከተዋወቃችሁ በመጀመሪያው ቀን ፣ በእንቅልፍ ላይ ሆነ ገና ሳትነቃ አስር ጊዜ የት ነህ ምናምን እያሉ መልዕክት ይልኩልሃል። በቀን ሶስቴ ወይም  አራቴ እየደወሉ ልታስባቸው ባትፈልግም እንድታስባቸው ጓደኛ ወዳጅ እንድታረጋቸው ያስገድዱሃል።

በ " እንዴት መልካም ሰው ነህ" እየደለሉ፣ በ"ምርጥ ጓደኛ ነህ"  አፋዊ ቲያትር እየጨቀጨቁ ልብህን ከልባቸው ያዛንቃሉ።  በእውነቱ መልዓክ እንኳን እንደ እነሱ ንፁህ እና ፍፁም ሆኖ አታይም። የእናትህን ፍቅር የሚያስንቅ መውደድ ይሰጡሃል። ነጋዴ ደንበኛ እንዲስብ ከሸቀጡ ዋጋ እንደሚቀንስ ሁሉ እነሱም እራሳቸውን ዝቅ አድርገው በትህትና ያቀርቡልሃል።

ጨለማው ህይወትህ ውስጥ ብርሃን የገባ ይመስልሃል። ትጥበረበራለህ። ችግሬን የሚካፈል ደስታዬን የሚያግዝ የልብ ወዳጅ አገኘሁ ብለህ ጮቤ ትረግጣለህ አየህ፣ ብልጥ ካልሆንክ ነጋዴ ያታልሃል። ሊያመልኩህ ቤተ - መቅደስ ማቆም እስኪቀራቸው ለጓደኝነትህ ይሰግዱልሃል። በቀን አስሬ የቤትህን በር እያንኳኩ ይመጡብሃል። ሳታውቀው እንደ ድመት ኮቴያቸውን ሳያሰሙ ህይወትህ ቤተሰብህ ፍቅረኛህ ውሳኔህ አንተነትህ ውስጥ ገብተዋል። ቀና ስትል አጠገብህ ናቸው።  ሳይገባህ እነሱን መልመድ ትጀምራለህ። ሳትረዳው እነሱ እንዲመጡ በርህን ክፍት ትተህ በር በሩን ማየት ትጀምራለህ። አልገባህም እንጂ ለመልዓክ በቀረበ ፍፁም ባህሪያቸው  ተሸንፈሃል። እመን እንጂ ጃል ቀርበሀቸዋል። ዓይናቸውን ለማየት ቢሯቸው ወይ ቤታቸው ትሄዳለህ። ፍቅራቸውን ፍለጋ አሉ ወደተባሉበት ታዘግማለህ። ይሄ ድርጊት እነሱ ጋር ሲደርስ ታድያ ሁሉም ነገር አበቃ። እንደ አሳ አጥምደውህ የፍቅር ስጋህን ከበሉ በዃላ አንተ ጋ ምን ይሰራሉ። በተራህ እነሱን መከተል ትጀምራለህ። በተራህ ቤታቸውን ማንኳኳት ፣ በቀን አስሬ መፃፍ፣ በቀን ሶስት አራቴ መደወል ትጀምራለህ።

ከዛ ሚስጥሮችህን በሆዱ ሽፍንፍን አድርጎ ይዞ ህመምህን ታሞ ደስታህን ተጋርቶ ገመናህን ደብቆ በደግ ቀን ያጋራኸውን ሚስጥር በክፋ እና መከራ ቀን አውጥቶ ይዘረግፉታል የቤተሰቡ የእናቱ ልጅ የአብራኩ ክፋይ ያህል የሚቆጥርህ መስሎ የደስታህ የፌሽታህ የማግኘትህ የጥጋብህ ቀን ብቻ ጥራኝ የችግርህ የማጣትህ የመንጣትህ የመራብህን ገፅ አታሳየኝ አትደውል ይሉሀል!  ለራስህ የምትሰጠውን ቦታና ክብር የምትሰጠው ሽርፍራፊ ክህደትና አለመውደድን የማታሳየው በስስት አይንህ የምታየው ወዳጆቼ ነበሩ ወይ ትላለክ የልደትህን ቀን ብቻ እየቆጠሩ አብሮህ በልቶ ጠጥቶ ኪስ የሚያደኸይ ሳይሆን ከልደትህ ማግስት በኋላ እቅፍ አድርጎ አዲሱ አመትህ ላይ ምን አቀድክ የጉዞህን መስመር ንገረኝና ከመንገድህ እስከ መዳረሻህ ድረስ አብሬህ ልዝለቅ የሚል ወዳጄ ነው ብለህ ስታስባቸው የነበሩ ውሀ ይሆናሉ ጠላት ይሆኑብካል ቴክስቱ አይመለሱም። ስልክ አይነሱም። በዚህ ጊዜ ትንሽ የጥሞና ጊዜ ወስደህ ስታስበው ጅልም እብድም እንደነበርክ ይገባሃል።

ስልክህን ሞጭልፎ እንደ ሮጠው ሌባ ጓደኝነትህን ሰርቀው መሸሻቸው ያስተክዝሃል። ፍቅራቸው ይርብሃል። መገፋትህ ቁስል ሆኖ ይጠዘጥዝሃል። ምናልባት ከዚያ ወዲህ የመኖር እድሉ ካለህ እመነኝ "ሰው" በቃኝ ብለህ ትንሽ ዋሻህ ውስጥ ትመንናለህ።  እኔ ግን እልሃለሁ ሰዎች ሲቀርቡህ እንደ ጅል አግጥጠህ ከምትቀበላቸው መራቃቸውን እና አንተን መጥላታቸውን (በጊዜ ሂደት) አምኖ የሚቀበል ብስለት ይኑርህ። አለዚያ የሄደው የመጣው ሲያደማህ ደምህ ፈሶ ማለቁ ነው። የነፍስ ጓደኛ አጋር ህይዎት ጥሎ ፈተናውን ጥሎ ከፈረጠጠ ጓደኛ መሳይ ቶክሲክ ሰው ጋር ውል ቅደዱ !!

Nębā Stylę


@TkYEGITMABIYOT
@TkYEGITMABIYOT
@TkYEGITMABIYOT
ከህይወት መስፍን ሰለሞን ጋር ከዚህ በፊት የነበረንን ቆይታ አድምጡ🙏

https://vm.tiktok.com/ZM68JFsP4/

በእርግጥም ትታከማለች🙏
@TkYEGITMABIYOT
ይህን የምታዩ ወዳጆቻችን ካላችሁ ዛሬ ከ8:00 ጀምሮ በፌስቡክ ገፃችሁ እንዲሁም በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያዎቻችሁ ላይ ብቻውን ምንም ታግ ሳትጠቀሙ ትለጥፉ ዘንድ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።

#የሰው_መልክ

በቅርብ ቀን🙌
2024/11/20 01:29:00
Back to Top
HTML Embed Code: