Telegram Web
#Update

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና (EHPLE) ከሚያዝያ 1-3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

እያንዳንዱ ተፈታኝ 200 ጥያቄዎች ይቀርቡለታል፦ 100 ጥያቄዎች በጠዋት መርሐግብር እና 100 ጥያቄዎች በከሰዓት መርሐግብር፡፡

ተፈታኞች ፈተና ማዕከል እንዲደርሱ የሚጠበቀው ጠዋት 1፡30 እና ከሰዓት 7፡00 ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

(የፈተና መርሐግብር፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ የሚያስፈልጉ ሰነዶች እንዲሁም ወደ ፈተና ማዕከል ይዞ መምጣት የተከለከሉ ነገሮች እና ሌሎች መረጃዎች ከላይ ተያይዘዋል፡፡)  

ለተጨማሪ መረጃ፦
952 ወይም 0115186275 / 0115186276

@tikvahuniversity
ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ።

የኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከብሬክስሩ ትሬዲንግ አ.ማ ጋር በመተባበር ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች የተዘጋጀ የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኤርምያስ ሞሊቶ እንደገለጹት፦

ተማሪዎች የህይወት ክህሎትን ሲያዳብሩ የሚጎዳና የሚጠቅማቸውን እንዲለዩ፣ መነሻና መድረሻቸውን እንዲያውቁ፣ በዓላማ እንዲመሩና በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።

በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጤና ቋሚ ኮሚቴ አባልና የሴቶች ኮከስ የኦዲት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ቤዛ ተሾመ በበኩላቸው፦

በ11 የሀገራችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሴት ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና እንደሚሰጥና በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው ስልጠና አንዱ አካል መሆኑን አንስተው፦

አክለውም ዶ/ር ቤዛ ስልጠናው ሴት ተማሪዎች በህይወት ዘመናቸው ያላቸውን ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት፣ የራሳቸውን እምቅ አቅምና ፀጋ በመጠቀም ካስቀመጡት ግብ ለመድረስና ዓላማቸውን በስኬት ለማጠናቀቅ እንደሚረዳቸው ገልፀዋል።

በብሬክስሩ ትሬዲንግ አ.ማ ተመራማሪና አንጋፋ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ጉዲሳ ነገን መቅረፅን፣ ጊዜ አጠቃቀምን፣ በህይወት ወሳኝ ጉዳዮችን እንዴት መወሰን ይቻላል?፣ በራስ መተማመንን እንዴት መገንባት ይቻላል? የሚሉ ሀሳቦችን የዓለም ዓቀፍ እና የሀገራችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን ልምድና ተሞክሮ በማቅረብ ስልጠናውን ሰጥተዋል።

በስልጠናው በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጤና ቋሚ ኮሚቴ አባልና የሴቶች ኮከስ የኦዲት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ በሆኑት ዶ/ር ቤዛ ተሾመ እና የሰው ሀብት ልማትና ስምሪት የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል በሆኑት በወ/ሮ መናሄል አምራን በኩል የህይወት ተሞክሮና ልምድ ለሴት ተማሪዎች ቀርቧል።

መጋቢት 27/2017 ዓ.ም

ዘገባው የህዝብ ግንኙነት እና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

Let Your Light Shine in the Society!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
ድረ ገጽ:- www.wcu.edu.et
ፌስቡክ:-Wachemo University-WCU
Telegram channel-https://www.tgoop.com/Wcuniversity
YouTube-Wachemo University-wcu youtube
P.O.Box 667
SOPHOS AFRICA
Vision Sharing workshop for wachemo University Students

ሶፈስ አፍሪካ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ፣በአሜሪካ እንዲሁም በእንጊሊዝ  ህጋዊ ፈቃድ አግኝቶ ማህበረሰብን እያገለገለ ይገኛል።

ሶፎስ አፍሪካ ለህዝብ ጥቅም በመቆም መልካም እሴቶችንና መርሆችን በማስማማት ድህነትን ለመከላከል የቆመ ትልቅ ድርጅት ነው።

ይህ ድርጅት ዋቸሞ ዩኒቨርስቲን ተመራጭ በማድረግ ለተማሪዎች መሰረታዊ የሆነ የህይወት ለውጥ እንዲመጣ ለማስቻል Resilient and flourishing Society! በሚል ርዕስ ወርክሾፕ አዘጋጅቷል።

በዚህም መርሃግብር ተገኝታችሁ እንድትጠቀሙ በክብር ተጋብዛችኋል።

ቦታ :የመመረቂያ አዳራሽ
ጊዜ:ሚያዝያ 1 ረቡዕ ከሰዓት 8:30

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

👇👇👇👇
For real and complete information visit  
https://www.tgoop.com/WCUSU
#Update

ከሚያዝያ 1-3/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ አመልካቾች፥ የፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (Orientation) እና የሙከራ ፈተና (Mock Exam) ማክሰኞ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት የሚሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ኦረንቴሽኑ የሚሰጠው መመረቂያ አዳራሽ እንደሆነ አውቃችሁ 8:00 በጊዜ እንድትገኙ እናሳስባለን።

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

👇👇👇👇
For real and complete information visit  
https://www.tgoop.com/WCUSU
Wachemo University Students' Union pinned «ኦረንቴሽኑ የሚሰጠው መመረቂያ አዳራሽ እንደሆነ አውቃችሁ 8:00 በጊዜ እንድትገኙ እናሳስባለን። የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት 👇👇👇👇 For real and complete information visit   https://www.tgoop.com/WCUSU»
SOPHOS AFRICA

Vision Sharing workshop!

የቦታ ለውጥ: SMART ROOM 1
2025/04/09 13:25:19
Back to Top
HTML Embed Code: