Telegram Web
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እዛው ቅኔ ማኅሌት ውስጥ የተቀረጸውን ተመልክታችሁ ፍረዱ! ሺርክ ትልቅ ኃጢአት ነው። የአሏህን ሐቅ አሳልፎ መስጠት ለጀሀነም የሚያዘወትር ዙልም ነው።
"ኑ በጨለማ ተመላለሱ የጥላቻን ሕይወት እንድትቀምሱ"
ቃሉ ኡመቱል ኦርቶዶክሲያህ
ሞኖጌኔስ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥47 ፡-"ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

"ዘ" ማለት በግዕዝ "የ" ማለት ሲሆን "ዘ-"ፍጥረት" ማለት "የ-ፍጥረት" እንዲሁ "ዘ-"ልደት" ማለት "የ-ልደት" ማለት ነው። ኦሪት ዘፍጥረት በግዕዙ "ዘልደት" ሲባል፣ በእንግሊዝኛ "Genesis" ሲባል፣ በግሪክ ሰፕቱአጀንት "ጌነሲስ" Γένεσις ይባላል፥ ትርጉሙ "ልደት" ማለት ነው። ሰማይ እና ምድር ደግሞ የተፈጠሩ እንጂ በእማሬአዊ የተወለዱ አይደሉም፥ ልደቱ በፍካሬአዊ ፍጥረቱን የሚያሳይ ነው፦
ዘፍጥረት 2፥4 የሰማይ እና የምድር "ልደት" መጽሐፍ ይህ ነው። Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς,

"ጌኔሲስ" γένεσις የሚለው ቃል "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "የሆነ" ማለት ሲሆን "ልደት" ማለት ነው። ኢየሱስ "ልደት" ያለው ፍጡር ሲሆን ይህ ልደቱ እናቱ ማርያም ማኅፀን ውስጥ ከመንፈስ ቅዱስ መፀነሱ ነው፦
ማቴዎስ 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። Τοῦ δὲ Ἰησοῦ Χριστοῦ ἡ γένεσις οὕτως ἦν. μνηστευθείσης τῆς μητρὸς αὐτοῦ Μαρίας τῷ Ἰωσήφ, πρὶν ἢ συνελθεῖν αὐτοὺς εὑρέθη ἐν γαστρὶ ἔχουσα ἐκ πνεύματος ἁγίου.

በተመሳሳይ እዚህ አንቀጽ ላይ "ልደት" ለሚለው የገባው ቃል "ጌኔሲስ" γένεσις ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "የሆነ" ማለት ነው፥ ኢየሱስ ያለ ወንድ ዘር ከማርያም የማኅፀን ፍሬ "የሆነ" ተአምር ነው፦
ማቴዎስ 1፥20 ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና። τὸ γὰρ ἐν αὐτῇ γεννηθὲν ἐκ Πνεύματός ἐστιν Ἁγίου·

"የተፀነሰው" ለሚለው የገባው ቃል "ጌኔቴን" γεννηθὲν ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ጌናኦ" γεννάω ነው፥ የቀጥታ ትርጉም የሚባሉት "Literal Standard Version" እና "Young's Literal Translation" በግልጽ "begotten" ብለው አስቀምጠውታል። "የተወለደው" ከመንፈስ ቅዱስ አሠራር ስለሆነ አምላክ ያ የተወለደውን ሰው "ወልጄሃለሁ" ብሎታል፦
ዕብራውያን 1፥5  እኔ ዛሬ "ወልጄሃለሁ"። ἐγὼ σήμερον γεγέννηκά σε;

እዚህ አንቀጽ ላይ "ወልጄሃለሁ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ጌኔካ" γεγέννηκά ሲሆን ሥርወ ቃሉ በተመሳሳይ "ጌናኦ" γεννάω ነው፦
"ጌታም አለኝ፦ "አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁ" መዝሙር 2፥7 ምንም እንኳን ያ ቀን በትንቢት የተነገረ ቢመስልም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ ተወለደ በእርሱም ይነገር ዘንድ ነው"።
Expositions on the Psalms (Augustine)  Psalm Chapter 2 Number 7

"እኔ ዛሬ ወለድሁ" የሚለው እምቅድመ ዓለም ሳይሆን ከድንግል መፈጠሩን ካሳየ ዘንዳ አምላክ "አባት" ሰው "ልጅ" የተባለበት ከዚህ አንጻር ነው፦
ዕብራውያን 1፥5 እኔ አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል። καὶ πάλιν Ἐγὼ ἔσομαι αὐτῷ εἰς Πατέρα, καὶ αὐτὸς ἔσται μοι εἰς Υἱόν;

"ፓቴራ" Πατέρα ማለት "አባት" ማለት ሲሆን "ሁዮን" Υἱόν ማለት "ልጅ" ማለት ነው፥ በግዕዝ አባት "አብ" ሲባል ልጅ "ወልድ" ይባላል። አምላክ አባት የሚሆነው ከዳዊት ወገብ ለሚወጣ ዘር እንጂ ለመለኮት በፍጹም አይደለም፦
2ኛ ሳሙኤል 7፥12 ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፥
2ኛ ሳሙኤል 7፥14 እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።
"ዘር" ፍጡር እንጂ ፈጣሪ እንዳልሆነ እሙን እና ቅቡል ነው። ማኅፀን ውስጥ ያለውን ሽል ያለ ዘርአ ብእሲ ያስገኘው አንዱ አምላክ "አብ" ሲባል የተገኘው ሰው ደግሞ "ወልድ" ተባለ፦
ሉቃስ 1፥35 "ከ-አንቺ" የሚወለደው ቅዱስ የአምላክ ልጅ ይባላል። διὸ καὶ τὸ γεννώμενον ἅγιον κληθήσεται Υἱὸς Θεοῦ.

"የሚወለደው" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ጌኖሜኖን" γεννώμενον ሲሆን "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "ሆነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "የሚሆነው” ማለት ነው፥ "ከ" የሚለው መስተዋድድ "አንቺ" በሚለው ቃል ላይ መነሻ ሆኖ መግባቱ በራሱ ኢየሱስ ከማርያም መገኘቱን ያሳያል። ያለ ወንድ ዘር በሴት ብቻ የተገኘ ብቸኛ ልጅ ስለሆነ "ሞኖጌኔስ ሁዮስ" μονογενὴς υἱός ተብሏል፦
1ኛ ዮሐንስ 4፥9 አምላክ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። ὅτι τὸν Υἱὸν αὐτοῦ τὸν μονογενῆ ἀπέσταλκεν ὁ Θεὸς εἰς τὸν κόσμον.

"ሞኖጌኔስ" μονογενὴς የሚለው ቃል  "ሞኖስ" μόνος እና "ጌኑስ" γένος ከሚል ሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ሞኖስ" μόνος ማለት "ብቸኛ" ማለት ሲሆን "ጌኑስ" γένος ማለት ደግሞ "የተወለደ" ማለት ነው። እንደ በጥቅሉ "ሞኖጌኔስ ሁዮስ" μονογενὴς υἱός ማለት "የተወለደ ብቸኛ ልጅ"only begotten son" ማለት ነው። አምላክ ፆታ የለውም፥ አይባዛም አይከፋፈልም። ተራሮች የተፈጠሩ ቢሆንም በፍካሬአዊ እንደተወለዱ ይናገራል፦
አሞፅ 4፥13 እነሆ ተራሮችን "የሠራ"፥
መዝሙር 89(90)፥2 ተራሮች "ሳይወለዱ"፥ πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι

"ሳይወለዱ" ማለት "ሳይሠሩ" "ሳይፈጠሩ" ማለት ከሆነ እንግዲያውስ "ወልጄሃለሁ" ሲል "ፈጥሬካለው" ማለት ነው። ዓለም ሳይፈጠር በመለኮታዊ ዕቅድ ውስጥ "የወለደው" ማለት "የፈጠረው" ከማርያም ማኅፀን ነው፦
መዝሙር 109(110)፥3 ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማኅፀን "ወለድኩህ"። ἐκ γαστρὸς πρὸ ἑωσφόρου ἐγέννησά σε.

"ጋስትሮስ" γαστρὸς ማለት "ማኅፀን" ማለት ሲሆን ፈጣሪ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ በመለኮታዊ ዕቅድ ከማርያም ማኅፀን እንደፈጠረው ያሳያል። ግዕዙ "ከርሥ" ሲለው "ማኅፀን" ማለት ነው፥ ማኅፀን ውስጥ "የሚያስሆን" አምላክ ሲሆን "የሚሆን" ደግሞ ሰው ነው። "ወለደ" ማለት "ፈጠረ" በሚል የመጣ ነው፦
ዘዳግም 32፥15 የፈጠረውንም አምላክ ተወ። וַיִּטֹּשׁ֙ אֱלֹ֣והַ עָשָׂ֔הוּ
ዘዳግም 32፥18 የወለደህን አምላክ ተውህ። וַתִּשְׁכַּ֖ח אֵ֥ל מְחֹלְלֶֽךָ

ዐውዱ ላይ መወለድ መፈጠርን ለማመልከት ከመግለጽም በተጨማሪ አንዱ አምላክ ለእስራኤል "አባት" የተባለው "ፈጣሪ" የሚለው ቃል ለማሳየት ነው፦
ዘዳግም 32፥6 የገዛህ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህ እና የመሠረተህ እርሱ ነው። הֲלוֹא־ הוּא֙ אָבִ֣יךָ קָּנֶ֔ךָ ה֥וּא עָֽשְׂךָ֖ וַֽיְכֹנְנֶֽךָ׃

በዕብራይስጥ "አብ" אָב ማለት በተመሳሳይ "አባት" ማለት ሲሆን "የፈጠረህ" የሚለው የግሥ መደብ በራሱ አምላክ "አባት" የተባለው ስለፈጠረ መሆኑን በግልጽ ተቀምጧል፦
ኢሳይያስ 1፥2 ልጆችን "ወለድሁ" አሳደግሁም፥ እነርሱም አመጹብኝ። υἱοὺς ἐγέννησα καὶ ὕψωσα, αὐτοὶ δέ με ἠθέτησαν.

"ወለድሁ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤጌኒሳ" ἐγέννησα ሲሆን መፈጠርን የሚያሳይ ነው፥ እስራኤል "አንድያ ልጅ" የተባለው ለዚያ ነው፦
ዕዝራ ሱቱኤል 4፥58 "የምወደው የበኵር አንድያ ልጄ" ያልኸን እኛ ወገኖችህ ግን በአሕዛብ እጅ ገባን።

እዚህ ድረስ ከተግባባን መርየም፦ "ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? ስትል አሏህ በጂብሪል "አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፦
3፥47 ፡-"ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ይህንን በቀላሉ ከተረዳችሁ ወደ ዲኑል ኢሥላም እንድትመጡ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ይህ ቻናል የተለያዩ ኢሥላማዊ መጽሐፍቶችን እና ሌሎች አገልግሎቶችን የምታገኙበት ነው፦
https://www.tgoop.com/merkatobusiness
ጌታ ነኝ?

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥164 በላቸው «እርሱ አሏህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲሆን ከአሏህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጂ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

"ረብ" رَبّ ማለት "ጌታ" "አስተናባሪ" "ባለቤት" ማለት ሲሆን ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ አንድ ጌታ አምላክ ነው፦
ማርቆስ 12፥29 እስራኤል ሆይ ስማ! ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው። اسْمَعْ يَا إِسْرَائِيلُ. الرَّبُّ إِلَهُنَا رَبٌّ وَاحِدٌ.

በዐረቢኛው ባይብል እዚህ አንቀጽ ላይ "ጌታ" ለሚለው የገባው ቃል "ረብ" رَبّ እንደሆነ ልብ አድርግ! ነገር ግን ኢየሱስ ለሐዋርያቱ "እንዲሁ ነኝና" ብሎ ለመለሰበት የገባው ቃል "ረብ" رَبّ ሳይሆን "ሠይድ" سَيِّد ነው፦
ዮሐንስ 13፥13 እናንተ መምህር እና ጌታ ትሉኛላችሁ፥ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ። أَنْتُمْ تَدْعُونَنِي مُعَلِّماً وَسَيِّداً وَحَسَناً تَقُولُونَ لأَنِّي أَنَا كَذَلِكَ

እዚህ አንቀጽ ላይ ሐዋርያት "ጌታ" ላሉት የገባው ቃል "ሠይድ" سَيِّد እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ሠይድ" سَيِّد በስም መደብ "አለቃ" "አውራ" "ራስ" "የበላይ" "ጌታ" ማለት ነው፥ "ሠይድ" سَيِّد በቅጽል መደብ "ለዘብተኛ" "ደግ" "ንዑድ" "ስቡት" "ሕሩይ" "ጥበበኛ" ማለት ነው። ስለዚህ ኢየሱስ "እንዲሁ ነኝና" ያለው ሐዋርያት "ሠይድ" سَيِّد ስላሉት እንጂ "ረብ" رَبّ ስላሉት አይደለም፥ በተመሳሳይ ሣራ ለአብርሃም፦ "ሠይዲ" سَيِّدِي ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት
1ኛ ጴጥሮስ 3፥6 እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ “ጌታዬ” ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት። وَهَكَذَا كَانَتْ سَارَةُ تُطِيعُ إبْرَاهِيمَ وَتُنَادِيهِ «سَيِّدِي.»

ስለዚህ "ጌታ" ማለት እልቅና እና ክብርን፣ ሥልጣን እና ሹመትን፣ አለቅነትን እና መሪነትን ለማመልከት ይመጣል። "እኔ ጌታ ነኝ" ለማለትማ ተወዳጁ ነቢያችንም"ﷺ"፦ "እኔ ጌታ ነኝ" ብለዋል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 209
አቢ ሠዒድ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እኔ የአደም ልጆች ጌታ ነኝ"። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ أَنَا سَيِّدُ وَلَدِ آدَمَ
ሢልሢለቱ አስ ሶሒሕ መጽሐፍ 4, ሐዲስ 100
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "እኔ በትንሣኤ ቀን የሰዎች ጌታ ነኝ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ أنا سَيِّدُ الناس يوم القيامة

ቅሉ እና ጥቅሉ እነዚህ ሐዲሳት ላይ "ጌታ" ለሚለው የገባው ቃል "ሠይድ" سَيِّد እንጂ "ረብ" رَبّ አይደለም፥ ነቢዩላህ የሕያ "ሠይድ" سَيِّد ተብሎአል፦
3፥39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት፦ «አሏህ በየሕያ ከአሏህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታ፣ ድንግል እና ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል» በማለት ጠሩት። فَنَادَتْهُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَهُوَ قَآئِمٌۭ يُصَلِّى فِى ٱلْمِحْرَابِ أَنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًۢا بِكَلِمَةٍۢ مِّنَ ٱللَّهِ وَسَيِّدًۭا وَحَصُورًۭا وَنَبِيًّۭا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

የትንሣኤ ቀን ሰዎች አሏህን "ጌታችን" ሲሉ እና መሪዎቻቸው "ጌቶቻችን" ሲሉ ይለያያል፦
33፥67 ይላሉም "ጌታችን" ሆይ! እኛ "ጌቶቻችንን" እና ታላላቆቻችንን ታዘዝን፡፡ መንገዱንም አሳሳቱን። وَقَالُوا۟ رَبَّنَآ إِنَّآ أَطَعْنَا سَادَتَنَا وَكُبَرَآءَنَا فَأَضَلُّونَا ٱلسَّبِيلَا۠

ልብ አድርጉ! ሰዎቹ የትንሳኤ ቀን ሰዎችን “ሣደተና” سَادَتَنَا ሲሉ አሏህን ግን “ረበና” رَبَّنَا ብለው ተጠቅመዋል። በኢሥላም ሸሪዓህ "ሠይዲ" سَيِّدِي አክብሮትን ለማሳየት ለሰዎች ብንጠቀምበትም "ረቢ" رَبِّي ማለት ግን አይቻልም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 40, ሐዲስ 14
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከእናንተ መካከል ማንም ባሪያዬ አይበል፥ ሁላችሁም የአሏህ ባሮች ናችሁ። ነገር ግን ሎሌዬ ይበል! "ረቢ" አይበል አይበል፥ ነገር ግን "ሠይዲ" ይበል። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يَقُولَنَّ أَحَدُكُمْ عَبْدِي ‏.‏ فَكُلُّكُمْ عَبِيدُ اللَّهِ وَلَكِنْ لِيَقُلْ فَتَاىَ ‏.‏ وَلاَ يَقُلِ الْعَبْدُ رَبِّي ‏.‏ وَلَكِنْ لِيَقُلْ سَيِّدِي ‏"‏ ‏.‏

አምላካችን አሏህ የሁሉ ነገር ረብ ሲሆን ከአሏህ በቀር ሌላን ረብ እፈልጋለሁን? እረ በፍጹም፦
6፥164 በላቸው «እርሱ አሏህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲሆን ከአሏህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጂ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ሥሉሳውያን ክርስቲያኖች ሆይ! ኢየሱስ እራሱ "ጌታ ፈጠረኝ" የሚለው ጌታውን፣ "ጌታዬ" የሚለው ጌታውን፣ ጌታው ኢየሱስን "ባሪያዬ" የሚለውን፣ ጌታው ኢየሱስ በማዕረግ ጌታ ያደረገውን አንዱን ጌታ አምላክ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ያ ጀመዓህ አሠላሙ ዐለይኩም

የኡሥታዛችን አቡ ሀይደር "ቀዷ ወል ቀደር" የሚለው መጽሐፉ ሰውዲ 550 ፍሬ አለ። የምትፈልጉ ልጀች እኅት ፎዚያን 009660507751537 አግኛት!
ሌሎቻችን ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን።
አሏህ ሁሉን ዐዋቂ ነው!

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥11 "አሏህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አምላካችን አሏህ ሁሉንም "ነገር" ዐዋቂ ነው፥ "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን ይህም ነገር አጠቃላይ ፍጥረትን ሁሉ ያጠቃልላል፦
65፥11 "አሏህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ይህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች "ዐሊመሏህ" عَلِمَ اللَّه የሚለው ቃል ወስደው "አሏህ ሁሉን ዐዋቂ ነውን? ብለው ይጠይቃሉ፦
2፥235 አሏህ እናንተ በእርግጥ የምታስታውሷቸው መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ عَلِمَ اللَّهُ أَنَّكُمْ سَتَذْكُرُونَهُنَّ
2፥187 አሏህ እናንተ ነፍሶቻችሁን የምትበድሉ መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ عَلِمَ اللَّهُ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَخْتَانُونَ أَنفُسَكُمْ

"አል ማዲ" الْمَاضِي ማለት "አላፊ"Past" ማለት ሲሆን "ዐሊመ" عَلِمَ አላፊ ግሥ ነው፥ አሏህ ቀድሞ ማወቁ ችግሩ ምንድን ነው? "አሏህ ዐወቀ" ማለት ጥንቱንም ማወቁን ያሳያል እንጂ በዐማርኛ "ዐወቀ" ማለት ያላወቀውን ዐወቀ ማለት አይደለም። ተመሳሳይ የሰዋስው አወቃቀር ከባይብል በንጽጽር እንመልከት! "የደ ኤሎሂም" יֵּ֖דַע אֱלֹהִֽים ማለት በአላፊ ግሥ "አምላክ አወቀ" ማለት ነው፦
ዘጸአት 2፥25 አምላክ የእስራኤልን ልጆች አየ፥ አምላክ በእነርሱ ያለውን ነገር "አወቀ"። וירא אלהים את בני ישראל וידע אלהים׃

"የደ" יֵּ֖דַע ማለት "አወቀ" ማለት ሲሆን አላፊ ግሥ ነው፥ "አምላክ ቀድሞ ማወቁ ችግሩ ምንድን ነው? "አምላክ ዐወቀ" ማለት ጥንቱንም ማወቁን ያሳያል እንጂ በዐማርኛ "ዐወቀ" ማለት ያላወቀውን ዐወቀ ማለት አይደለም" ካላችሁ ይበል የሚያስብል እና ይሁን የሚያሰኝ ነው፥ እንግዲያውስ የቁርኣኑን አናቅጽ በዚህ መልክ እና ልክ ተረዱት! በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ ይህንን ቻናል የዲኑል ኢሥላም የብርሃን አድማስ ለማስፋት እና ለኩፋሮች ተደራሽነት እንዲሆን ሊንኩን በየቻናሉ፣ በየግሩፑ፣ በየኮሜንት መስጫ እንድታጋሩልን ከታላቅ ትህትና ጋር እንደጠቃለን። ኢንሻላህ
https://www.tgoop.com/Wahidcom
ሡጁዱል ዒባዳህ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

18፥110 «በጌታውም "አምልኮ" አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا

"ዒባዳህ" عِبَادَة የሚለው ቃል "ዐበደ" عَبَدَ ማለትም "አመለከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "አምልኮ" ማለት ነው፦
18፥110 «በጌታውም "አምልኮ" አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا

"ሡጁድ" سُجُود የሚለው ቃል "ሠጀደ" سَجَدَ ማለትም "ሰገደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ስግደት" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ሡጁዱል ዒባዳህ" سُجُود الْعِبَادَة ማለት "የአምልኮ ስግደት" ማለት ነው፦
6፥56 «እኔ እነዚያን ከአሏህ ሌላ የምትጠሩዋቸውን ከማምለክ ተከልክያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّي نُهِيتُ أَنْ أَعْبُدَ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ
7፥206 እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት መላእክት እርሱን ከማምለክ አይኮሩም፥ ያወድሱታልም፡፡ ለእርሱ ይሰግዳሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيُسَبِّحُونَهُ وَلَهُ يَسْجُدُونَ ۩

የባሕርይ ስግደት"Ontological Prostration" ለአንዱ አምላክ ብቻ የሚቀርብ የአምልኮ ስግደት ሲሆን ለአንዱ አምላክ ለአሏህ ብቻ የሚቀርብ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ፣ መዋረድ ነው፦
22፥77 እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! በሶላታችሁ አጎንብሱ፣ "በግንባራችሁም ተደፉ"፣ ጌታችሁንም አምልኩ፣ ትድኑ ዘንድ መልካምን ነገር ሥሩ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩

"በግንባራችሁም ተደፉ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ኢሥጂዱ" اسْجُدُوا ሲሆን በሶላት ውስጥ ያለው ሡዱድ ለአሏህ ብቻ የሚቀርብ ሡጁዱል ዒባዳህ ነው፥ የትም ሆነን ሁሉን ለሚችል፣ ሁሉን ለሚያውቅ፣ ሁሉን ለሚያይ፣ ሁሉን ለሚሰማ መለኮት የሚቀርብ ስግደት የአምልኮ ስግደት ነው። ፍጡራን ግን ሁሉንም የመቻል፣ የማወቅ፣ የማየት እና የመስማት ባሕርይ ስለሌላቸው ለእርሱ በሩቅ የሚቀርብ ስግደት ሺርክ ነው፦
35፥18 የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን በሩቅ የሚፈሩትን፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱትን ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا تُنذِرُ الَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُم بِالْغَيْبِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ
26፥218 በዚያ ለሶላት በምትቆም ጊዜ በሚያይህ ተመካ፡፡ الَّذِي يَرَاكَ حِينَ تَقُومُ
26፥219 በሰጋጆች ውስጥ መዘዋወርህንም በሚያየው ጌታህ ላይ ተመካ፡፡ وَتَقَلُّبَكَ فِي السَّاجِدِينَ

የትም ቦታ ሆነህ የሚያይህ፣ የሚሰማህ እና የሚያውቅህ መለኮት ብቻ ሆኖ ሳለ መላእክት፣ ነቢያት፣ ጻድቃን እና ሰማዕታት ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ተመልካች እና ሁሉን ሰሚ መለኮት ስላልሆኑ ለእነርሱ በሩቅ የሚቀርበው ስግደት ሺርክ ነው፦
4፥36 አሏህንም አምልኩ! በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا

በችሎታው፣ በዕውቀቱ፣ በማየቱ፣ በመስማቱ ሁሉን ያካበበ አንድዬ እያለ ውስንነት ያለቸውን ፍጡራን በመለማመን ስግደት ማቅረብ ታላቅ በደል ነው። አምላካችን አሏህ "እኔነት" ያለው ነባቢ መለኮት ነው፥ ከእርሱ በቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ ስለሌለ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ" "እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" ይለናል፦
20፥14 እኔ አሏህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ፡፡ ሶላትንም እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي
21፥92 ይህቺ ኡማህ አንዲት ኡማህ ስትሆን በእርግጥ ኡማችሁ ናት፥ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ፡፡ إِنَّ هَـٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም "እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጂ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

ከጥንት ጀምሮ "እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ነቢያትን ሲልክ የነበረውን አንዱን አምላክ አሏህ ማምለክ ምንኛ መታደል ነው? እናንተ ሰዎች ሆይ! ቅጣትን ትጠነቀቁ ዘንድ እናንተን እና እነዚያንም ከእናንተ በፊት የነበሩትን የፈጠረውን ጌታችሁን አምልኩ፦
2፥21 እናንተ ሰዎች ሆይ! ቅጣትን ትጠነቀቁ ዘንድ እናንተን እና እነዚያንም ከእናንተ በፊት የነበሩትን የፈጠረውን ጌታችሁን አምልኩ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

ክርስቲያኖች ሆይ! የአምልኮ ሐቅ ገንዘቡ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሡጁዱ አት ተሒያህ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥34 ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

"ተሒያህ" تَحِيَّة የሚለው ቃል "ሐያ" حَيَّا ማለትም "አከበረ" "ሰላም ሰጠ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "አክብሮት" "ክብር" "መከባበር" ማለት ነው፦
25፥75 እነዚያ በመታገሳቸው የገነትን ሰገነቶች ይመነዳሉ፥ በእርሷም ውስጥ "አክብሮት" እና ሰላምታን ይስሰጣሉ፡፡ أُولَـٰئِكَ يُجْزَوْنَ الْغُرْفَةَ بِمَا صَبَرُوا وَيُلَقَّوْنَ فِيهَا تَحِيَّةً وَسَلَامًا
33፥44 በሚገናኙት ቀን "መከባበሪያቸው" ሰላም መባባል ነው፥ ለእነርሱም የከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ تَحِيَّتُهُمْ يَوْمَ يَلْقَوْنَهُ سَلَامٌ ۚ وَأَعَدَّ لَهُمْ أَجْرًا كَرِيمًا

እነዚህ አናቅጽ ላይ "አክብሮት" "መከባበር" ለሚለው የገባው ቃል "ተሒያህ" تَحِيَّة ነው፥ በጥቅሉ "ሡጁዱ አት ተሒያህ" سُجُود الْتَحِيَّة ማለት "የአክብሮት ስግደት" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አምላካችን አሏህ ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ያለው ስግደት የአክብሮት ስግደት ነው፦
2፥34 ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

ቁርኣን ከመውረዱ በፊት የአክብሮት ስግደት በሩቅ ሳይሆን በአካል የአክብሮት ስላምታ መስገድ ሐላል ነበረ፥ የዩሡፍ እናት እና አባት እንዲሁ ወንድሞቹ የአክብሮት ስግደት ለዩሡፍ ሰግደዋል፦
12፥4 ዩሡፍ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ አሥራ አንድ ከዋክብትን፣ ፀሐይን እና ጨረቃን በሕልሜ አየሁ፥ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ يُوسُفُ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ إِنِّي رَأَيْتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوْكَبًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ رَأَيْتُهُمْ لِي سَاجِدِينَ
12፥100 ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው፡፡ አለም፦ ለእርሱም ሰጋጆች ኾነው ወረዱለት፡፡ «አባቴም ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፡፡ ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት፡፡ وَرَفَعَ أَبَوَيْهِ عَلَى الْعَرْشِ وَخَرُّوا لَهُ سُجَّدًا ۖ وَقَالَ يَا أَبَتِ هَـٰذَا تَأْوِيلُ رُؤْيَايَ مِن قَبْلُ قَدْ جَعَلَهَا رَبِّي حَقًّا

የጸጋ ስግደት"Graceful Prostration" ከአሏህ በስጦታ የተቸረ የአክብሮት ስግደት ሲሆን ነገር ግን ይህ የአክብሮት ስግደት ሲለጠጥ ለመላእክት፣ ለነቢያት፣ ለጻድቃን እና ለሰማዕታት መለኮት ባልሆኑበት ሁኔታ ሰዎች እየተለማመኑ ሲሰግዱ ወደ የአምልኮ ስግደት እየተቀየረ ሲመጣ ቁርኣን ሲወርድ ተከለከለ፥ አሏህም "እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ" ብሎናል፦
41፥37 ሌሊት እና ቀን ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፥ ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

ተወዳጁ ነቢያችንም"ﷺ" በሐዲስ ላይ የአክብሮት ስግደትን ከልክለዋል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 1926:
ዐብደላህ ኢብኑ አቢ ዐውፋ እንደተረከው፦ ”ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ከሻም ምድር በተመለሰ ጊዜ ለነቢዩ”ﷺ” ሰገደ፥ እሳቸውም፦ “ሙዓዝ ሆይ! ይህ ምንድነው? አሉት። እርሱም፦ “ሻም ምድር ሄጄ ነበር፥ ለኤጲስ ቆጶሳቶቻቸው እና ለጳጳሳቶቻቸው ሲሰግዱ ተመለከትኩ። ይህንን ለእርሶ በራሴ ልሠራው ተመኘሁ” አለ። የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ይህንን በፍጹም እንዳትሠሩ!”። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي أَوْفَى، قَالَ لَمَّا قَدِمَ مُعَاذٌ مِنَ الشَّامِ سَجَدَ لِلنَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ مَا هَذَا يَا مُعَاذُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَتَيْتُ الشَّامَ فَوَافَقْتُهُمْ يَسْجُدُونَ لأَسَاقِفَتِهِمْ وَبَطَارِقَتِهِمْ فَوَدِدْتُ فِي نَفْسِي أَنْ نَفْعَلَ ذَلِكَ بِكَ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ فَلاَ تَفْعَلُوا
ዛሬ ላይ ዐበይት ክርስትና በሚባሉት በካቶሊክ፣ በምሥራቅ ኦርቶዶክስ"Eastern Orthodox" እና በጽባሕ ኦርቶዶክስ"Oriental Orthodox" ለመላእክት፣ ለነቢያት፣ ለጻድቃን እና ለሰማዕታት "የአክሮት ስግደት" እየተባለ የሚሰገደው ስግደት ጸሎት፣ ልመና፣ ተማጽኖ ስላለበት የአምልኮ ስግደት ነው፥ ምክንያቱም ዱዓእ እራሱ ዒባዳህ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 2
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ "ዱዓእ ዒባዳህ ነው"። عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ إِنَّ الدُّعَاءَ هُوَ الْعِبَادَةُ ‏”‏ ‏.‏

"ዱዓእ" دُعَآء የሚለው ቃል “ደዓ” دَعَا ማለትም “ለመነ” “ጠራ” “ጸለየ” “ተማጸነ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ልመና” “ጥሪ” “ጸሎት” “ተማጽንዖ” ማለት ነው፥ ከፈጠረን አምላክ ከአሏህ ውጪ "ድረሱልን እርዱን" የሚባሉት ፍጡራን ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች መለኮት ስላልሆኑ አያውቁም፣ አይሰሙም፣ አያዩም፦
7፥194 እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው፥ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው ለእናንተ ይመልሱላችሁ። إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
46፥5 እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን ከአሏህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡ وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُو مِن دُونِ اللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَن دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ

በትንሣኤ ቀን አሏህ ከእርሱ ሌላ በዱዓእ የሚያመልኳቸውንም ይሰበስብና እያወቀ፦ «እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን?» ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ መልሳቸውም፦ «ጥራት ይገባህ "ከእነርሱ ይልቅ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፥ እንደሚሉት አይደለም፥ ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ፦
34፥40 ሁሉንም በሚሰበስባቸው እና ከዚያም ለመላእክቶቹ፦ «እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን የሚኾነውን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ يَقُولُ لِلْمَلَائِكَةِ أَهَـٰؤُلَاءِ إِيَّاكُمْ كَانُوا يَعْبُدُونَ
34፥41 መላእክቶቹም፦ «ጥራት ይገባህ "ከእነርሱ ይልቅ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፥ እንደሚሉት አይደለም፥ ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ፡፡ قَالُوا سُبْحَانَكَ أَنتَ وَلِيُّنَا مِن دُونِهِم ۖ بَلْ كَانُوا يَعْبُدُونَ الْجِنَّ ۖ أَكْثَرُهُم بِهِم مُّؤْمِنُونَ

መላእክት፣ ነቢያት፣ ጻድቃን እና ሰማዕታት በትንሣኤም ቀን ማጋራታቸውን ይክዳሉ፥ ከእነርሱ ስም በስተኃላ አምልኮውን የሚጋሩት ሸያጢን ናቸው።
ክርስቲያኖች ሆይ! "የአክሮት ስግደት" እያላችሁ የምሰግዱት ስግደት ጸሎት፣ ልመና፣ ተማጽኖ ስላለበት የአምልኮ ስግደት ነውና የአምልኮ ሐቅ ገንዘቡ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአክብሮት ስግደት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

41፥37 ሌሊት እና ቀን ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፥ ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

"ሻኻህ" שָׁחָה የሚለው የዕብራይስጥ ቃል፣ "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω የሚለው የግሪክ እና "ሡጁድ" سُّجُود የሚለው የዐረቢኛ ቃል "ስግደት"prostration" ማለት ነው፥ ለአንድ አምላክ በሁሉም ስፍራ የሚቀርበው ስግደት የአምልኮ ስግደት ሲሆን ለፍጡራን በአካል ሲገናኙ ለሰላምታ የሚቀርበው ስግደት የአክብሮት ስግደት ነው፦
ዘፍጥረት 23፥7 አብርሃም ተነሣ፥ "ለ-"ምድሩ ሕዝብ እና "ለ-"ኬጢ ልጆች "ሰገደ"። וַיָּ֧קָם אַבְרָהָ֛ם וַיִּשְׁתַּ֥חוּ לְעַם־הָאָ֖רֶץ לִבְנֵי־חֵֽת׃

እዚህ አንቀጽ ላይ አብርሃም ለ-"ምድሩ ሕዝብ እና ለ-"ኬጢ ልጆች ያቀረበውን የአክብሮት ስግደት "ሻኻህ" שָׁחָה ሲሆን በግሪክ ሰፕቱአጀንት "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω በዐረቢኛ "ሡጁድ" سُّجُود ነው። ስለዚህ "አሏህ ለመላእክት ለአደም ስገዱ" ሲል "የአክብሮት ስግደት ነው" ስንል እርር እና ምርር ብላችሁ የሚያንጨረጭራችሁ እና የሚያንተከትካችሁ ምን ይውጣችሁ ይሆን? እንቀጥል፦
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም "ይስገዱልህ"። יַֽעַבְד֣וּךָ עַמִּ֗ים [וְיִשְׁתַּחוּ כ] (וְיִֽשְׁתַּחֲו֤וּ ק) לְךָ֙ לְאֻמִּ֔ים

እዚህ አንቀጽ ላይ ይስሐቅ ያዕቆብን “ይስገዱልህ” ሲለው "ያምልኩህ" ማለቱ ነው? የዮሴፍም ወንድሞች ለዮሴፍ በምድር ላይ በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱለት፦
ዘፍጥረት 42፥6 የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግምባራቸው ተደፍተው "ሰገዱለት"። וַיָּבֹ֙אוּ֙ אֲחֵ֣י יֹוסֵ֔ף וַיִּשְׁתַּֽחֲווּ־לֹ֥ו אַפַּ֖יִם אָֽרְצָה׃

ለዮሴፍ እንደተሰገደለት ተጨማሪ ጥቅስ ዘፍጥረት 43፥26 ዘፍጥረት 43፥28 ዘፍጥረት 44፥14 ተመልከቱ! ሩት ለቦኤዝ በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፦
ሩት 2፥10 በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት። וַתִּפֹּל֙ עַל־פָּנֶ֔יהָ וַתִּשְׁתַּ֖חוּ אָ֑רְצָה

ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ከአንዱ አምላክ ከያህዌህ ጋር ለእሴይ ልጅ ለንጉሡ ለዳዊት ራሳቸውን አዘንብለው ሰገዱ፦
1ኛ ዜና 29፥20 ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ። וַיִּקְּד֧וּ וַיִּֽשְׁתַּחֲו֛וּ לַיהוָ֖ה וְלַמֶּֽלֶךְ׃

"ሰገዱ" በሚል በአንድ ግሥ እና "እና" በሚል መስተጻምር ተጫፍሮ መጥቷል፥ ስግደቱ ለያህዌህ የአምልኮት ለዳዊት ደግሞ የአክብሮት ነው። በእስራኤል ባህል ለሰላምታ እርስ በእርስ በግምባር ተደፍቶ መስገድ የተለመደ ነው፥ 1ኛ ሳሙኤል 20፥41 1ኛ ሳሙኤል 25፥23 2ኛ ሳሙኤል 18፥28 2ኛ ሳሙኤል 19፥18 1ኛ ነገሥት 1፥23 ተመልከት!

በአዲስ ኪዳን የአክብሮት ስግደት ቀጥሏልን? እንዴታ ያለ ጥርጥር ቀልሏል፥ ሐዋርያት ለኢየሱስ የአክብሮት ስግደት ሰግደውለታል፦
ሉቃስ 24፥52 እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። καὶ αὐτοὶ προσκυνήσαντες αὐτὸν ὑπέστρεψαν εἰς Ἰερουσαλὴμ μετὰ χαρᾶς μεγάλης,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ስግደት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω ሲሆን ኢየሱስ በሰጠው ምሳሌ ውስጥ ዕዳውን መክፍል ያልቻለው ባሪያ ለጌታው መስገዱ በእስራኤል ባህል ስግደት አክብሮትን ለማመልከት እንደሚመጣ ጉልኅ ማሳያ ነው፦
ማቴዎስ 18፥26 ስለዚህ ባሪያው ወድቆ "ሰገደለትና"፦ ጌታ ሆይ፥ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ" አለው። πεσὼν οὖν ὁ δοῦλος προσεκύνει αὐτῷ λέγων Μακροθύμησον ἐπ’ ἐμοί, καὶ πάντα ἀποδώσω σοι.
እዚህ አንቀጽ ላይ "ስግደት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω ነው። የእስር ቤት ዘበኛው ለጳውሎስ እና ለሲላስ ሰግዷል፦
የሐዋርያት ሥራ 16፥29 መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስ እና ከሲላስ ፊት ተደፋ። αἰτήσας δὲ φῶτα εἰσεπήδησεν καὶ ἔντρομος γενόμενος προσέπεσεν τῷ Παύλῳ καὶ Σιλᾷ,

የአክብሮት ስግደት ባይኖር ኖሮ በፊታቸው ሲሰግድ ዝም ይሉት ነበር? ራእይ የፊላድልፍያ ጉባኤ ኤጲስ ቆጶስ ለሆነው ሰው እንደሚሰገድለት ይናገራል፦
ራእይ 3፥9 እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት "ይሰግዱ" ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ። ἰδοὺ ποιήσω αὐτοὺς ἵνα ἥξουσιν καὶ προσκυνήσουσιν ἐνώπιον τῶν ποδῶν σου, καὶ γνῶσιν ὅτι ἐγὼ ἠγάπησά σε.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ስግደት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω በ King James Version ላይ "worship" ብሎታል፥ "ዎርሺፕ" የሚለው ቃል "ዋጋ"worth" እና "ነት"ship" ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን "ዋጋነት"worthy-ship"፣ "ማክበር" እና "አክብሮት" ማለት ነው። ዮሐንስ ለመልአኩ ሁለት ጊዜ ሰገደለት፦
ራእይ 19፥10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። καὶ ἔπεσα ἔμπροσθεν τῶν ποδῶν αὐτοῦ προσκυνῆσαι αὐτῷ.
ራእይ 22፥8 በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ። ἔπεσα προσκυνῆσαι ἔμπροσθεν τῶν ποδῶν τοῦ ἀγγέλου

ሁለት ጊዜ ሰግዶለት ሁለት ጊዜ "እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፥ ለአምላክ ስገድ" ብሎ አስጠንቅቆታል፥ እንደ ጴጥሮስ ለትህትና ይሆን? አይመስለኝም፦
የሐዋርያት ሥራ 10፥25 ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተገናኝቶ ከእግሩ በታች ወደቀና ሰገደለት። ጴጥሮስ ግን፦ “ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ፥” ብሎ አስነሣው።

ምናልባት በንያው የአምልኮ ስግደት ሰግዶ ይሆን? አናውቅም። አብርሃም እና ሎጥ ለመላእክት ሰግደዋል፦
ዘፍጥረት 18፥2 ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ።
ዘፍጥረት 19፥1 ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ።

መላእክት ወደ ሰዎች ሲመጡ እና ሰዎች እርስ በእርስ ሲገናኙ መስገድ የአክብሮት ስግደት ነው፥ ነገር ግን መላእክት እና ሰዎች የችሎታ፣ የዕውቀት፣ የማየት እና የመስማት ውስንነት ስላለባቸው በአካል ሳይገናኙ በገይብ ለእነርሱ መስገድ የአምልኮ ስግደት ነው። በተጨማሪ በላይ በሰማይ ያሉትን የመላእክትን ምስል ሆነ በታች በምድር የሰዎችን ምስል ሠርቶ መስገድ ሆነ ማምለክ የተከለከለ ነው፦
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም።

ለመላእክት ሆነ ለሰዎች "የአክብሮት ስግደት" እያላችሁ የአምልኮ ስግደት የምትሰግዱ እንዲሁ የተቀረጸ ምስል ለሆኑት ለመስቀል እና ለስዕል የጸጋ ስግደት የምትሰግዱ ቶሎ ብላችሁ በንስሓ ወደ አሏህ እንደትመለሱ ጥሪያችን ነው። አሏህን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፦
41፥37 ሌሊት እና ቀን ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፥ ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"በግ ሁልጊዜ "ይበላኛል" ብሎ የሚፈራው እና የሚጠነቀቀው ተኩላን ነው፥ ነገር ግን አሳድጎ፣ አስብቶ እና ተንካባክቦ አርዶ የሚበላው በሚያምነው እና በሚታመንለት በገዛ እረኛው ነው። ከውጪ ከሚመጣ የኩፋሮች ጥቃት ይልቅ ጉያችሁ ሥር ያሉትን ሙናፊቃን እንጠንቀቅ! ከኩፍር ይልቅ ኒፋቅ ዲንን የሚሰረስር ዝገት ነው። አሏህ ከኒፋቅ ሸር እና ደባ እንዲሁ ከሙናፊቃን ተንኮል እና ሴራ ይጠብቀን! አሚን።"

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የግብፅ ኦርቶዶክስ፦ "ድንግል ማርያም ከአዳም የመጣው ድቀተ ባሕርይ አግኝቷቷል" ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ደግሞ፦ "ድንግል ማርያም ከአዳም ከመጣው ድቀተ ባሕርይ ተጠብቃለች" የሚል እምነት አላቸው፥ የግብፅ ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ ውስጥ ውስጡን እየሠሩ እንደሆነ በቂ መረጃዎች እየወጡ ነው።
«ለአደም ስገዱ»

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥34 ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

አምላካችን አሏህ ለመላእክት«ለአደም ስገዱ» በማለት አዘዛቸው፦
2፥34 ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

የአዳም እና የሔዋን ታሪክ ላይ ሚካኤልም ወጥቶ መላእክቱን ሁሉ ጠራ፡- "ጌታ አምላክ እንዳዘዘው ለአምላክ መልክ ለአዳም ስገዱ" አለ፦
"ሚካኤልም ወጥቶ መላእክቱን ሁሉ ጠራ፡- "ጌታ አምላክ እንዳዘዘው ለአምላክ መልክ ለአዳም ስገዱ" አለ።
Life of Adam and Eve Chapter XIV(14) Number 1

ቀሌምንጦስ ዘሮም"Clement of the Rome" ከጴጥሮስ የተቀበለው ንግግር ተብሎ በሚታመነው መጽሐፍ ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ ወደ አዳም ራሳቸውን አዘንብለው ለአዳም እንደሰገዱ ይናገራል፦
ቀሌምንጦስ 1፥41 አራዊት፣ እንስሳት፣ ወፎች እና "እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ" ወደ አዳም ተሰበሰቡ ከፊቱም ቁመው ራሳቸውን አዘነበሉ "ለ-"አዳም ሰገዱ"።

"እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ" ማለት መላእክትን ይጨምራል፥ ምክንያቱም መላእክት ፍጡራን ኑባሬዎች ናቸውና፥ ፍጥረት ሁሉም ለአዳም ይታዘዝ እና ቃሉንም ይጠብቅ ነበር፦
ቀሌምንጦስ 1፥42"ፍጥረት ሁሉም ለአዳም "ይታዘዝ" እና ቃሉንም ይጠብቅ ነበር።

አምላካችን አሏህ ለመላእክት«ለአደም ስገዱ» ሲል ለኢብሊሥ "ስገድ" አለማለቱን አያሳይም፥ ምክንያቱም አሏህ «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» ብሎታልና፦
7፥12 አላህ፦ «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» አለው፡፡ قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ

“ባዘዝኳችሁ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ" ሳይሆን “ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ" አለው፥ “ባዘዝኩህ” የሚለው ኃይለ ቃል "ለአደም ስገድ" ብሎ አዞት እንደነበር ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳይል። ለምሳሌ፦ ፈጣሪ አዳምን "መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ" ብሎት ነበር፦
ዘፍጥረት 2፥17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ።

ጥቅሱ ላይ "አትብላ" እንጂ "አትብሉ" አላላቸውም፥ ነገር ግን ሔዋን፦ "እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም" ያህዌህ ብሎናል ብላለች፦
ዘፍጥረት 3፥3 ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ ያህዌህ አለ፦ "እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም"።

ለሁለቱም ግን "አትብሉ" ያለበት ትእዛዝ አለመገለጹ ግን "አላላቸውም" እንደማንል በተመሳሳይ "ስገድ" ያለበት ጥቅስ አለመኖሩ "ስገድ አላለውም" አያሰኝም። ሲቀጥል "መላእክት" በሚል ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ "ለ" የሚለውን መስተዋድድ "ብቻ" በሚል መረዳት የለብንም፦
7፥179 ”ለ”እነርሱ ልቦች አሏቸው፥ ግን አይገነዘቡበትም፣ “ለ”እነርሱም ዓይኖች አሉዋቸው፥ ግን ዐያዩበትም፣ “ለ”እነርሱም ጆሮዎች አሉዋቸው ግን አይሰሙበትም፡፡ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا

"እነርሱ" የተባሉት ከሰው እና ከጂኒ ያመጹ ከሓድያን ሲሆኑ "እነርሱ" በሚል ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ "ለ" የሚለውን መስተዋድድ ስላለ "ልቦች" "ዓይኖች" "ጆሮዎች" ያሉአቸው ኩፋሮች ብቻ ናቸው እንደማንል ሁሉ "ለመላእክት" የሚለውም ለኢብሊሥ እንዳልተባለ ማስረጃ አይሆንም፦
2፥34 ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ፥ ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር። "እምቢ" አለ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ፡፡ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ أَبَىٰ وَاسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ

“ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር” በሚለው ኃይለ ቃል ላይ “ሲቀር” የምትለዋን ይዘን "ኢብሊሥ ከመላእክት ነበር" ማለት አሁንም የቁርኣንን ሰዋስው ካለመረዳት የሚመጣ ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ነው፦
26፥77 «እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው፡፡ ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር እርሱ ወዳጄ ነው»፡፡ فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّي إِلَّا رَبَّ الْعَالَمِينَ

ኢብራሂም፦ “ለእኔ ጠላቶች ናቸው። ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር” ማለቱን አስተውል! “ሲቀር” የሚለውን አፍራሽ ቃል ይዘን ከዓለማቱ ጌታ ውጪ ለኢብራሂም ሁሉም ጠላት ነውን? አማንያን፣ ነቢያት፣ መላእክት፣ እንስሳትስ ጠላት ናቸውን? አይ “በቀር” የሚለው በአንጻራዊ ደረጃ የአሏህን ወዳጅ ለመሆን የገባ እንጂ “ሁሉን ጠላት ናቸው ከአሏህ በቀር” ማለቱን አያሳይም ከተባለ እንግዲያውስ “በቀር” የሚለው በአንጻራዊ ደረጃ ኢብሊሥ ብቻ አለመታዘዙን እንጂ መላእክት ውስጥ መካተቱን አያሳይም።

ዲያብሎስ ክሣደ ልቡናውን በማጽናት እና ራሱን በማኩራት ፈጣሪው ለፈጠረው ለአዳም መስገድን "እምቢ" ብሏል፦
2ኛ መቃብያን 9፥3 ክሣደ ልቡናውን በማጽናት እና ራሱን በማኩራት ፈጣሪው ለፈጠረው ለአዳም መስገድን እምቢ ብሏልና።

ዲያብሎስም ከማዕረጉ የወረደው "ለአዳም አልሰግድም" በማለቱ እንደሆነ በጸጸት ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 1፥15 "ለአዳም አልሰግድም በማለቴ እግዚአብሔር ስለ አባታቸው ስለ አዳም ከማዕረጌ አዋርዶኛልና።

አሏህ ለመላእክት«ለአደም ስገዱ» ማለቱን አክብሮቱን ያሳያል እንጂ "አደምን አምልኩ" የሚለውን አያሲዝም። እንደዛማ ቢሆንማ ፈጣሪ በኢየሱስ ለፊላድልፍያ ጉባኤ ኤጲስ ቆጶስ ለሆነው ሰው እንደሚያሰግድ ይናገራል፦
ራእይ 3፥9 እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት "ይሰግዱ" ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።

ፈጣሪ ኤጲስ ቆጶሱን እያስመለከ ነው? "ኸረ በፍጹም" ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን እሳቤ በዚህ መልክ እና ልክ መረዳት ቀላል ነው። ኢየሱስ ወደ ዓለም ሲገባ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር፥ መላእክት ኢየሱስን ያገለገሉት ለመላእክት "ይስገዱ" ስለተባሉ ነው፦
ማቴዎስ 4፥11 እነሆም መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር። καὶ ἰδοὺ ἄγγελοι προσῆλθον καὶ διηκόνουν αὐτῷ.
ዕብራውያን 1፥6 በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ፦ የአምላክ መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ" ይላል።
ዘዳግም 32፥43 ሰማያት ሆይ! ከእርሱ ጋር ደስ ይበላችሁ፥ የአምላክ መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ። εὐφράνθητε, οὐρανοί, ἅμα αὐτῷ, καὶ προσκυνησάτωσαν αὐτῷ πάντες ἄγγελοι Θεοῦ·

የዕብራውያን ጸሐፊ "የአምላክ መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ" የሚለውን ከዘዳግም 32፥43 ግሪክ ሰፕቱጀትን ላይ የጠቀሰ ሲሆን የሙት ባሕር ጥቅል ላይ የተገኘው የዕብራይስጡ ጽሑፍ ላይ በተመሳሳይ ዘዳግም 32፥43 "የአምላክ መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ" የሚል አለ። ዐውዱ ስለ "ሰይፍ" ቢናገርም በውስጠ ወይራ ንግግር "ይስገዱ" ሲል መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበርና "ያገልግሉት" ማለት ነው፥ በኵር ሆኖ የተወለደ የመጀመሪያው ሰው አዳም ሲሆን በጥላነት"typologically" ለሁለተኛ አዳም ለክርስቶስ ይሆናል፦
ኢዮብ 15፥7 በውኑ መጀመሪያ የተወለድህ ሰው አንተ ነህን?

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
2025/02/28 10:11:33
Back to Top
HTML Embed Code: