Telegram Web
ኩፋሮች የሚያነሱትን ጥያቄዎች ከበቂ መልስ እና ከበቂ ማብራሪያ ጋር እንዲሁ የእኛን በጨዋ ደንብ ያቀረብነውን ሙግት ይጎብኙት፦
ክፍል አንድ
ክፍል ሁለት
ክፍል ሦስት
ክፍል አራት
ክፍል አምስት
ክፍል ስድስት
ክፍል ሰባት

ለሌሎች ሠበቡል ሂዳያህ ይሆን ዘንድ ኢንሻላህ ሼር አርጉት!
ስም ሰጠው

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥45 መላእክት፡- «መርየም ሆይ! አሏህ ከእርሱ በኾነው ቃል ስሙ አል መሢሕ ዒሣ፣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ፣ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ ያበሥርሻል» ያሉትን አስታውስ!። إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

በመጻሕፍቱ ማመን ከእምነት ማዕዘናት አንዱ ነው፥ መርየም በጌታዋ መጻሕፍት አምናለት። "ሶደቀት" صَدَّقَتْ የሚለው "አመነት" آمَنَتْ በሚል የመጣ ነው፦
66፥12 በጌታዋ ቃላት እና በመጻሕፍቱ አረጋገጠች፥ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡ وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَاتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِ وَكَانَتْ مِنَ الْقَانِتِينَ

መርየም በጌታዋ ቃላት አምናለች፥ የጌታዋ ቃላት "ስሙ አል መሢሕ ዒሣ፣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ፣ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ" የሚል ነው፦
3፥45 መላእክት፡- «መርየም ሆይ! አሏህ ከእርሱ በኾነው ቃል "ስሙ አል መሢሕ ዒሣ፣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ፣ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ" ያበሥርሻል» ያሉትን አስታውስ!። إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

መርየም ከአሏህ በኾነው ቃላት ከተበሠረችበት ቃላት አንዱ ልጇ ስሙ "አል መሢሕ ዒሣ" መባሉ ነው፥ "ዒሣ" عِيسَى የሚለው ስም የልጇ የተጸውዖ ስሙ"Proper Name" ሲሆን "አል መሢሕ" الْمَسِيح ደግሞ የማዕረግ ስሙ"Generic Name" ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ የሚለው ስም "ያህ" יָהּ እና "ሹዋ" יָשַׁע ከሚል ሁለት የዕብራይስጥ ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ያህ" יָהּ የሐሸም ምጻረ ቃል ሲሆን "የሻ" יָשַׁע ማለት ደግሞ "መድኃኒት" ማለት ነው። በጥቅሉ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ ማለት "ያህ መድኃኒት ነው" ማለት ነው፥ "ኤልየሻ" אֱלִישָׁע ማለት "ኤል" אֵל እና "የሻ" יָשַׁע ከሚል ቃል የተዋቀረ ሲሆን "ኤል መድኃኒት ነው" ማለት ነው። በግዕዝ "ኢየሱስ" የተባለው "ያህሹዋ" እና "ኤልሳዕ" የተባለው "ኤልየሻ" የፍጡራን ስም ሲሆኑ "ያህ" እና "ኤል" ለፍጡራን በመነሻ ወይም በመዳረሻ ምጻረ ቃል ሆነው ይገባሉ፥ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ የሚል ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የያዘው የነዌ ልጅ ኢየሱስ ነው፦
ኢያሱ 1፥1 እንዲህም ሆነ የያህዌህ ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ ያህዌህ የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ያህሹዋን እንዲህ ብሎ ተናገረው። וַיְהִ֗י אַחֲרֵ֛י מֹ֥ות מֹשֶׁ֖ה עֶ֣בֶד יְהוָ֑ה וַיֹּ֤אמֶר יְהוָה֙ אֶל־יְהֹושֻׁ֣עַ בִּן־נ֔וּן מְשָׁרֵ֥ת מֹשֶׁ֖ה לֵאמֹֽר׃

የነዌ ልጅን በዐማርኛ ላይ "ኢያሱ" ብለው ስም ያወጡለት "ኢየሱስ" የሚባለው የማርያም ልጅ የፍጡር ስም መሆኑን ለመደበቅ እንጂ ግዕዙ ላይ የመጽሐፉ ስም እራሱ "መጽሐፈ ኢያሱ" ሳይሆን "ኦሪት ዘኢየሱስ" ነው፥ ግዕዙ ላይ "እግዚአብሔር ተናገሮ ለኢየሱስ ወልደ ነዌ" ይለዋል። በ 280 ቅድመ ልደት ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ ኮይኔ የተረጎሙትም ሰባው ሊቃናት ያስቀመጡት "ኤሱስ" Ἰησοῦς ብለው ነው፥ ሉቃስ የነዌ ልጅ ኢየሱስን "ኤሱስ" Ἰησοῦς ብሎ አስቀምጦታል፦
የሐዋርያት ሥራ 7፥45 አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው አምላክ በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ "ከ-"ኤሱስ" ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች። ἣν καὶ εἰσήγαγον διαδεξάμενοι οἱ πατέρες ἡμῶν μετὰ Ἰησοῦ ἐν τῇ κατασχέσει τῶν ἐθνῶν, ὧν ἐξῶσεν ὁ Θεὸς ἀπὸ προσώπου τῶν πατέρων ἡμῶν ἕως τῶν ἡμερῶν Δαυείδ·
ይህንን የፍጡር ስም መልአኩ ገብርኤል ለማርያም በዕብራይስጥ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ ሲላት ሉቃስ በዘገባው ደግሞ "ኤሱስ" Ἰησοῦς ብሎ አስቀምጦታል፦
ሉቃስ 1፥31 እነሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም "ኤሱስ" ትዪዋለሽ። καὶ ἰδοὺ συλλήμψῃ ἐν γαστρὶ καὶ τέξῃ υἱόν, καὶ καλέσεις τὸ ὄνομα αὐτοῦ Ἰησοῦν.

በዕብራይስጥ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ በግሪክ ኮይኔ "ኤሱስ" Ἰησοῦς የተባለው ስም አንዱ አምላክ በመልአኩ ለማርያም ልጅ የሰጠው ስም ነው፦
ፊልጵስዩስ 2፥9 በዚህ ምክንያት ደግሞ አምላክ ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው።

ጥቅሱ "ስሙን ሰጠው" አይልም፥ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን "ኢየሱስ የአብ ሲሆን ለወልድ ሰጠው" ብለው ይህንን ጥቅስ ይጠቅሳሉ።
፨ ሲጀመር "ስም ሰጠው" ስለተባለ የተሰጠው ስም "የሰጪውን ነው" ማለት አይደለም። ለምሳሌ፦
ዳንኤል 2፥37 አንተ ንጉሥ ሆይ! የሰማይ አምላክ መንግሥትን፣ ኃይልን፣ ብርታትን እና ክብርን የሰጠህ የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ።

አምላክ ለናቡከደነጾር "ክብር ሰጠው" ማለት የናቡከደነጾር ክብር "የአምላክ ክብር ነው" ማለት አይደለም፥ ምክንያቱም አምላክ "ክብሬን ለሌላ አልሰጥም" ብሎአልና፦
ኢሳይያስ 42፥8 እኔ ያህዌህ ነኝ፥ ስሜ ይህ ነው። ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።

በተመሳሳይ አንዱ አምላክ ለማርያም ልጅ የሰጠው ስም የራሱን ስም ሳይሆን ፍጡራን ሲጠቀሙበት የነበረውን የሰው ስም እንጂ መለኮታዊ ስሙን ለማንም ፍጡር አይሰጥም።

፨ ሲቀጥል "በዚህ ምክንያት" የሚል አመልካቻዊ ምክንያት እራሱን ዝቅ በማድረጉ ያገኘው ስም ወይም ዝና ነው። ለምሳሌ፦
1ኛ ነገሥት 1፥47 የንጉሡም ባሪያዎች ገብተው፦ "አምላክ የሰሎሞንን ስም ከስምህ ዙፋኑንም ከዙፋንህ የበለጠ ያድርግ" ብለው ጌታችንን ንጉሡን ዳዊትን ባረኩ፤ ንጉሡም በአልጋው ላይ ሆኖ ሰገደ።

የሰሎሞንን ስም ከስም የበለጠ መሆኑን ዝነኛ መሆንን እንጂ በባሕርይ ሰው ከመሆን እንደማያዘልል ሁሉ የኢየሱስ ስም ከስም የበለጠ መሆኑ ዝነኛ መሆንን እንጂ በባሕርይ ሰው ከመሆን አያዘልለውም፦
1ኛ ነገሥት 3፥12 እኔ እንደ ቃል አድርጌልሃለሁ፤ እነሆ፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛ እና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።

ሰሎሞንን የሚመስል ከሰሎሞን በፊት እንደሌለ ከሰሎሞን በኋላ እንደማይነሳ መነገሩ ሰሎሞን በባሕርይ ሰው ከመሆን ዘሎ መልአክ አሊያም አምላክ እንዳማያደርገው ሁሉ አምላክ ኢየሱስን ያለ ልክ ከፍ ከፍ ማድረጉ ኢየሱስን በባሕርይ ሰው ከመሆን ዘሎ መልአክ አሊያም አምላክ አያደርገውም። ከዚህ ይልቅ "ከፍ ከፍ" ለማለት የገባው ሥርወ ቃል "ሁፕሶ" ὑψόω ሲሆን በአምላክ ቀኝ ከፍ ማለቱ ለማሳየት የገባ ቃል ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥33 ስለዚህ በአምላክ ቀኝ "ከፍ ከፍ" አለ። τῇ δεξιᾷ οὖν τοῦ θεοῦ ὑψωθεὶς
የሐዋርያት ሥራ 5፥31 አምላክ ይህን ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ "ከፍ ከፍ" አደረገው። τοῦτον ὁ Θεὸς Ἀρχηγὸν καὶ Σωτῆρα ὕψωσεν τῇ δεξιᾷ αὐτοῦ τοῦ δοῦναι μετάνοιαν τῷ Ἰσραὴλ καὶ ἄφεσιν ἁμαρτιῶν.

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "ከፍ ከፍ" አለ ለሚል የገባው የግሥ መደብ በተመሳሳይ "ሁፕሶ" ὑψόω ነው፥ በእርግጥ ራሱንም የሚያዋርድ አማኝ ሁሉ ከፍ ይላል፦
ማቴዎስ 23፥12 ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።
መዝሙር 37፥34 ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።
ኤፌሶን 2፥7 በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።

ተግባባን አይደል? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እኅቶቼ ሆይ! ሙሥሊም ያልሆኑ አካላትን ወደ ኢሥላም በንጽጽር ለመጣራት "የተደበቀው እውነት" እና "አልገደሉትም አልሰቀሉትም" የተባሉት መጻሕፍት በድጋሚ እንዲታተም በጠየቃችሁን እና በወተወታችሁን መሠረት አንብቡ እና ለክርስቲያኖች አስነብቡ!

መጻሕፍቱን የምትፈልጉ አገር ውስጥ ያላችሁ ሆነ ከአገር ውጪ ያላችሁ በ +251928444408 ዐብዱ መርካቶ ብላችሁ በቀጥታ አሊያም በዋትሳፕ ታገኙታላችሁ፥ እንዲሁ በቴሌ ግራም ይህንን ዩዘር ኔም በመጠቀም http://www.tgoop.com/merkatozon ማግኘት ትችላላችሁ።

እንዲሁ ቤተል ተቅዋ መሥጂድ ሥር ስለሚገኝ ኩብራ ብላችሁ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፦ +251911663699

አየር ጤና አንሷር መሥጂድ ሥር፦ 0963796354

ለብዙዎች ሠበቡል ሂዳያህ ለመሆን ሁሉም ቦታ ሼር አርጉት!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
ኢሥላም እና ሙሥሊም

ክፍል አንድ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አሏህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

"ኢሥላም" إِسْلَام የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ "ኢሥላም" إِسْلَام ማለት ለአንዱ አምላክ በአምልኮ "መታዘዝ" "መገዛት" "እራስን መስጠት" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም "ታዘዝ" ሲለው እርሱም፦ "ታዘዝኩ" አለ፦
2፥131 ጌታው ለእርሱ "ታዘዝ" ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ "ታዘዝኩ" አለ፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዝ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊም" أَسْلِمْ ሲሆን "ታዘዝኩ" ለሚለው ደግሞ "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ ነው፥ "አምላክ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ብሎ ለአንድ አምላክ ብቻ መታዘዝ "ኢሥላም" إِسْلَام ይባላል፦
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ "ታዘዙ"፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲሆን "ኢሥላም" إِسْلَام በግንባር እና በጥሬ ትርጉም ለአንዱ አምላክ በአምልኮ "መታዘዝ" ማለት ነው፦
3፥20 ቢከራከሩህም፡- «ፊቴን ለአሏህ ሰጠው፥ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ሰጡ» በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

"ወጅህ" وَجْه የሚለው ቃል "ወጁሀ" وَجُهَ ማለት "ለየ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መለያ" "ፊት" "ማንነት"Person" ማለት ነው፥ "አካል" የሚለው የግዕዝ ቃል "አካለ" ማለትም "ለየ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መለያ"Person" ማለት ነው። "Person" የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል እራሱ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ከሚል የግሪክ ኮይኔ ቃል የመጣ ሲሆን "ፊት" ማለት ነው፥ ስለዚህ "ፊት" ሲባል "ማንነት" "መለያ" ማለት ከሆነ "ፊቴን ለአሏህ ሰጠው" ማለት "እራሴን ለአሏህ ሰጠው" "አካሌን ለአሏህ ሰጠሁ" ማለት ነው። "ሰጠው" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ ነው፦
2፥112 አይደለም፤ እርሱ በጎ ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአሏህ "የሰጠ" ሰው ለእርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳው አለው፡፡ بَلَىٰ مَنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَلَهُ أَجْرُهُ عِندَ رَبِّهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የሰጠ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ሲሆን "ኢሥላም" إِسْلَام ለሚለው ቃል ሥርወ ቃል ነው፥ እራስን ለአንዱ አምላክ መስጠት የኢብራሂምንም መንገድ ነው፦
4፥125 እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአሏህ "ከሰጠ" እና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነው? አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጐ ያዘው፡፡ وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ከሰጠ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ነው። "ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ፈረደ" "ደነገገ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ፍርድ" "ሕግ" "መርሕ" "ሃይማኖት" ማለት ነው፥ "ሃይማኖት" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሃይማነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሥርወ እምነት" "አንቀጸ እምነት" ማለት ነው። ከአንዱ አምላክ በግልጠተ መለኮት የሚመጣው መርሕ፣ ሥርወ እምነት፣ አንቀጸ እምነት በአምልኮ ለአንዱ አምላክ "መታዘዝ" ብቻ እና ብቻ" ነው፥ በአምልኮ ለአንዱ አምላክ ከመታዘዝ ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም። እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፦
3፥19 አሏህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ
3፥85 ከኢሥላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፥ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ
በባይብል አንድ ሃይማኖት እንዳለ እና ይህም ሃይማኖት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ እንደተገለጠ ይናገራል፦
ኤፌሶን 4፥5 አንድ ጌታ "አንድ ሃይማኖት" አንዲት ጥምቀት።
ይሁዳ 1፥3 ለቅዱሳን "አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት" እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።

ቅዱሳን የተባሉት ቅዱሳን ነቢያት እና ሐዋርያት ናቸው፥ የመጀመሪያው ነቢይ አዳም ነው፦
ኤፌሶን 3፥6 "ለቅዱሳን ሐዋርያት እና ለነቢያት" በመንፈስ አሁን እንደ ተገለጠ በሌሎቹ ትውልዶች ዘንድ ለሰው ልጆች አልታወቀም።
ቀሌምንጦስ 1፥40 በዚህ ጊዜ ንጉሥነትን እና ነቢይነትን ሠጠው በክብር መንበር ላይም አስቀመጠው።
ቀሌምንጦስ 1፥43 በዚህ ጊዜ መላእክት የእግዚአብሔር ቃል፦ "አዳም ሆይ! እነሆ ንጉሥ፣ ካህን እና "ነቢይ" መስፍን ለፍጥረት ሁሉ ገዢ ስላንተ በፈጠርሁት ሁሉ እንድትሆን አደረግሁ...ሲል ሰሙ።

ከ 451 እስከ 521 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ ያዕቆብ ዘሥሩግ"Jacob of Serugh" በእንተ ወላዲተ አምላክ በሚል መጽሐፉ ላይ አዳም ነቢይ እንደነበረ ተናግሯል፦
"አዳም ድንግል ሔዋንን አስገኝቷል፥ "የሕይወት እናት" ብሎ ጠርቷታል። እርሱ ነቢይ ነበረ"።
On the Mother of God (Jacob of Serugh) Homily (I)1 Number 634

ከአዳም ጀምሮ በመገለጥ የተሰጠ አንድ ሃይማኖት አለ፥ ይህንን ሃይማኖት ባይብል በግልጽ ስለማያስቀምጥ አይሁዳውያን ከኪሳቸው "የሁዲ ሃይማኖት" ሲሉ ክርስቲያኖች ከኪሳቸው "የክርስትና ሃይማኖት" ይላሉ። ነገር ግን የሁዱ በይሁዳን ነገር የመጣ "አይሁድ" የሚል ዘር እንጂ ሃይማኖት አይደለም፥ "ክርስትና" የሚለውንም ቃል ኢየሱስ ሆነ ሐዋርያት የማያውቁት ሲሆን "ክርስትና" ብሎ ለመጀመርያ ጊዜ ያሰፈረው አግናጥዮስ ዘአንጾኪያው"Ignatius of Antioch" በ 110 ድኅረ ልደት ነው።
ስለ ኢሥላም ግን በግሥ መደብ ደረጃ በመለኮታዊ ቅሪት ውስጥ ይገኛል፦
መዝሙር 56፥12 አምላክ ሆይ! እኔ የምስጋና ስእለት "የምሰጥህ" ከእኔ ዘንድ ነው። עָלַ֣י אֱלֹהִ֣ים נְדָרֶ֑יךָ אֲשַׁלֵּ֖ם תֹּודֹ֣ת לָֽךְ׃

"የምሰጥ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "አሻሌም" אֲשַׁלֵּ֖ם ሥርወ ቃሉ "ሸለም" שָׁלַם ሲሆን "ታዘዘ" "ተገዛ" የሚል ነው፥ በዐረቢኛ "ዩሥሊም" يُسْلِمْ ሲባል እራስን ለአሏህ መስጠት ነው፦
31፥22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አሏህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አሏህ ነው፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ ۗ وَإِلَى اللَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُورِ

"የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሥሊም" يُسْلِمْ እንደሆነ ልብ አድርግ! አንድ ሰው "ከአንዱ አምላክ ከአሏህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም" ሲል ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ፥ "ስእለት" ማለት "ብፅዓት" "ስጦታ" ማለት ሲሆን ለአምላክ የሚሰጠው ትልቁ ስእለት ውስጥን መስጠት ነው፦
ሉቃስ 11፥40 እናንት ደንቆሮዎች የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን? ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።

"በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ" ሲል ለአምላክ ውስጥን መስጠት ኢሥላም ይባላል። አምላክ ያለውን ሁሉ ማድረግ እና መታዘዝ ኢሥላም ይባላል፦
ዘጸአት 24፥7 የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ አነበበላቸው፤ እነርሱም፦ “አምላክ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም" አሉ።

ለአንዱ አምላክ በአምልኮ መገዛት ኢሥላም ከሆነ በመለኮታዊ ቅሪት ውስጥ ከጥንት ጀምሮ ነፍስን ለአምላክ የማስገዛት እሳቤ አለ፦
መዝሙር 62፥1 ነፍሴ ለአምላክ የምትገዛ አይደለችምን?
መዝሙር 2፥11 ለአምላክ በፍርሃት ተገዙ! በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
መዝሙር 100፥2 በደስታም ለአምላክ ተገዙ! በሐሤትም ወደ ፊቱ ግቡ።
ያዕቆብ 4፥7 እንግዲህ ለአምላክ ተገዙ! ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል።

ኢንሻ አሏህ ክፍል ሁለት ይቀጥላል........

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢሥላም እና ሙሥሊም

ክፍል ሁለት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አሏህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

"ኢሥላም" إِسْلَام ማዕዘናቱ ጦም፣ ሶላት፣ ዘካህ ወዘተ ናቸው፥ ለምሳሌ፦ ጦም ከነቢያችን"ﷺ" በነበሩት ነቢያት እና ሕዝቦቻቸው እንደተደገገ አሏህ ይናገራል። ወደ ነቢያት መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረደ፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጦም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
21፥73 በትእዛዛችንም ወደ በጎ ሥራ የሚመሩ መሪዎች አደረግናቸው፡፡ ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን፡፡ ለእኛ ተገዢዎችም ነበሩ፡፡ وَجَعَلْنَاهُمْ أَئِمَّةً يَهْدُونَ بِأَمْرِنَا وَأَوْحَيْنَا إِلَيْهِمْ فِعْلَ الْخَيْرَاتِ وَإِقَامَ الصَّلَاةِ وَإِيتَاءَ الزَّكَاةِ ۖ وَكَانُوا لَنَا عَابِدِينَ

"በትእዛዛችን" የሚለው ይሰመርበት! ይህም ትእዛዝ ኢሥላም ሲሆን በኢሥላም ማዕቀፍ ጦም፣ ሶላት፣ ዘካህ ወዘተ ከአሏህ የተወረደ ግልጠተ መለኮት ስለሆነ "ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን" ይለናል፥ ይህንን መመሪያ የተከተሉት ለአሏህ ተገዢዎችም ነበሩ። ከሰው ወገን ለመጀመርያ አሏህ ወሕይ ያወረደው ወደ አደም ነው፦
20፥115 ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَآ إِلَىٰٓ ءَادَمَ مِن قَبْلُ

"ከዚህ በፊት" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! "ከዚህ በፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ሚን ቀብሉ” مِنْ قَبْلُ ሲሆን ጊዜን ታሳቢ ያደረገ ነው፥ "ከዚህ በፊት" አሏህ በአደም ጊዜ "ታዛዦች" ብሎ ሰየመ፦
22፥78 "እርሱ "ከዚህ በፊት" "ሙሥሊሞች" ብሎ ሰይሟችኋል፡፡ هُوَ سَمَّاكُمُ الْمُسْلِمِينَ مِن قَبْلُ

"ከዚህ በፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ሚን ቀብሉ” مِنْ قَبْلُ ሲሆን የአደምን ጊዜ ያስታውሰናል። "እርሱ" የተባለው "አሏህ" የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ተውላጠ ስም ነው፥ አሏህ ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን ሲያወርድ "ሙሥሊሞች" ብሎ የጠራን ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት አንዱን አምላክ በአምልኮ "ታዛዥ" ማለት ነው፦
29፥46 በሉም «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፥ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን»። وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ በሰማያት ያሉት መላእክት እራሱ ለአሏህ በአምልኮ የሚታዘዙ ናቸው፦
3፥83 በሰማያት እና በምድር ያሉ በውድም በግድም ለእርሱ "የታዘዙ" ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአሏህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን? أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ነው፥ በሰማያት ያሉት መላእክት ሆነ በምድር ላይ ያሉት ሰዎች በግዴታ አሏህ ላስቀመጠው የተፈጥሮ ሕግ የታዘዙ ሲሆኑ በውዴታ ደግሞ ለሸሪዓው ሕግ ይታዘዛሉ። "ከርህ" كَرْه ማለት "ግዳጅ" ማለት ሲሆን "ጦውዕ" طَوْع ማለት ደግሞ "ፈቃደኝነት" ማለት ነው፥ በሰማያት ያሉት መላእክት ሆነ በምድር ላይ ያሉት ሰዎች ለአሏህ በግዴታ መታዘዛቸው "አል ኢሥላም ከውኒይ" الإِسْلَام كَوْنِيّ ሲባል በውዴታ መታዘዛቸው "አል ኢሥላም ሸርዒይ" الإِسْلَام شَرْعِيّ ይባላል። "ሰው ሲወለድ ሙሥሊም ነው" የሚባለው አል ኢሥላም ከውኒይ ሲሆን አምላካችን አሏህ በሸሪዓህ "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲለን አል ኢሥላም ሸርዒይ ነው፦
5፥44 እነዚያ ትእዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፡፡ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا
እዚህ አንቀጽ ላይ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለሙ" أَسْلَمُوا ሲሆን "የታዘዙ" ማለት ነው። ኢብራሂም ወደ ጌታው በንጹሕ ልብ የመጣ ሰው ነው፦
37፥84 ወደ ጌታው "በ-ንጹሕ ልብ” በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ!፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
26፥89 ወደ አሏህ "በ-ንጹሕ ልብ" የመጣ ሰው ቢኾን እንጂ፡፡ إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ንጹሕ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሠሊም" سَلِيم ነው፥ አንድ በኢሥላም ልቡን ሢያሠልም ልቡ ውስጥ "ሠላም" سَلَام ስላለ ልቡ ሠሊም ስትሆን እርሱ ደግሞ "ሣሊም" سَالِم‎ ይሆናል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 17027
ዐምር ኢብኑ ዐባሣህ እንደተረከው፦ "አንድ ሰው የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ሆይ! ኢሥላም ምንድን ነው? ብሎ ጠየቀ፥ እርሳቸውም"ﷺ"፦ "ልብህን ለአሏህ ዐዘ ወጀል ማሥለም ነው" አሉት"። عَنْ عَمْرِو بْنِ عَبَسَةَ قَالَ قَالَ رَجُلٌ يَا رَسُولَ اللَّهِ مَا الْإِسْلَامُ قَالَ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنْ يُسْلِمَ قَلْبُكَ لِلَّهِ عَزَّ وَجَلَّ

አንድ ሰው ልቡን ለአሏህ ካሠለመ ጀነት ይገባል፥ ልቡን ለአሏህ ያሠለመ ሰው ከጀሀነም ይድናል፦
አል አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 260
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለው፥ እስካልሠለማችሁ ድረስ ጀነት አትገቡም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لاَ تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ حَتَّى تُسْلِمُوا
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 12, ሐዲስ 163
ዐምር ኢብኑ አል ዓስ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሠለመ ዳነ"። عَنْ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ قَدْ أَفْلَحَ مَنْ أَسْلَمَ ‏"‏ ‏.‏

"ሠሊመ" سَلِمَ ማለት "ታዘዘ" "ሰጠ" "ሰላም ሆነ" ሲሆን በዕብራይስጥ "ሸሊመ" שׁ־ל־ם ነው፥ በዕብራይስጥ "ሙሽሊም" משלם ማለት "ታዛዥ" "ሠላማዊ" "እራሱን የሰጠ" ማለት ነው፦
ኢዮብ 22፥21 አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም በጎነት ታገኛለህ። הַסְכֶּן־נָ֣א עִמֹּ֑ו וּשְׁלם בָּ֝הֶ֗ם תְּֽבֹואַתְךָ֥ טֹובָֽה׃

"ሰላምም ይኑርህ" የግሥ መደብ "ዩሻልም" וּשְׁלם ሲሆን ሥርወ ቃል "ሸለም" שָׁלַם ነው፥ ባይብል ሀብ"Bible Hub" ይህንን ቃል ሲያብራራ እንዲህ ይላል፦ "በዐረቢኛ "ሠሊም" سَلِمَ ሲሆን "ደህና መሆን" "አስተማማኝ" "ከጥፋት ነጻ" "የበላይ" "መስጠት" "መስጠት ወይም ራስን ማስረከብ በተለይ ለአምላክ" በሥማዊ ግሥ "ሙሥሊም" እና በግሥ መሠረት "ኢሥላም" በመደበኛ ለአምላክ መታዘዝ ነው"Arabic سَلِمَ be safe, secure, free from fault, make over, resign to, resign or submit oneself, especially to God, whence participle Muslim, and infinitive Islam properly submission to God."

በመለኮታዊ ቅሪት እንዲህ ዓይነት ቃል እና አሳብ ከቀረ ነቢያቱ ከአምላክ በቀጥታ በመጣላቸው በሥርወ መሠረቱ ምን ሊኖር እንደሚችል መገመት አያዳግትም፥ ጥንታዊ ነቢያት የተሰጣቸው ግልጠተ መለኮት የተዋቀረበት አንጓ፣ የተናገሩበት ቋንቋ፣ የመልእክቱ ምጥቀት ሆነ የቃላቱ ልቀት የተላለፈበት ሰነድ በዚህ ዘመን የለም። ጌታዬ ሆይ! ሙሥሊም ሆኜ ውሰደኝ፥ በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ! ሙሥሊሞች ኾነን ውሰደን፦
12፥101 «ጌታዬ ሆይ! ከንግሥና በእርግጥ ሰጠኸኝ፡፡ ከሕልሞችም ፍች አስተማርከኝ፡፡ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ፡፡ ሙሥሊም ሆኜ ውሰደኝ፡፡ በመልካሞቹም አስጠጋኝ» አለ፡፡ رَبِّ قَدْ آتَيْتَنِي مِنَ الْمُلْكِ وَعَلَّمْتَنِي مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ ۚ فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ أَنتَ وَلِيِّي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۖ تَوَفَّنِي مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ
7፥126 «የጌታችንም ተአምራት በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በቀር ከእኛ አትጠላም፡፡ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ! ሙሥሊሞች ኾነን ውሰደን» وَمَا تَنقِمُ مِنَّا إِلَّا أَنْ آمَنَّا بِآيَاتِ رَبِّنَا لَمَّا جَاءَتْنَا ۚ رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَتَوَفَّنَا مُسْلِمِينَ

አምላካችን አሏህ በዲኑል ኢሥላም ሙሥሊም አርጎ ይውሰደን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tgoop.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በቅርብ ቀን ኢንሻ አሏህ!
ማንም ሚሽነሪ ተነስቶ "ኢየሱስ ያድናል" በማለት የኩፍር እና የሺርክ ጎጆ ሠርቶ አይፈለፍላትም።
2025/07/13 00:54:47
Back to Top
HTML Embed Code: