Telegram Web
መቼ_ነው*
#መቼ ነው* እውነተኛ ክርስቲያኖች የምንሆነው?😭
#መቼ ነው* እግዚአብሔር በፈጠራቸው ነግሮች የምንማረከው?
#መቼ ነው* እግዚአብሔር ለምን እንደፈጠርን የምንረዳው?
#መቼ ነው* እግዚአብሔር እንደሚፈልገው መኖር የምንጀምረው?
#መቼ ነው* ስለ ሀይማኖታችን በሙሉ ልብ እምንናገረው?
#መቼ ነው* እማይጠቅም ንግግር ከመናገር የምንቆጠበው?
#መቼ ነው* ለመልካም ስራ ምሳሌ የምንሆነው?
#መቼ ነው* በስግደታችን በፆማችን የምንጠቀመው?
#መቼ ነው* ፀሎታችን ተሰሚነት የሚያገኝው?
#መቼ ነው* ውሎና አዳራችን በቅዱስ ቃሉ ሚሆነው?
#መቼ ነው* ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ የምንመካው?
#መቼ ነው* የአለምን ትልቅነት ከልባችን የምናወጣው?
#መቼ ነው* ቤታችን ውስጥ ያለው የተበላሸ ሕይወት የሚስተካከለው?
#መቼ ነው* ቤታችን ውስጥ መጸሐፍ ቅዱስ ውዳሴ ማሪያም የሚነበበው?
#መቼ ነው* ውሽት እምናቆመው?
#መቼ ነው* የእግዚያአብሔርን ውሳኔ መቃውም እምናቆመው?
#መቼ ነው* እኔ እኔ ማለት ትተን ወንደሜ እህቴ ማለት እምንጀምረው?
#መቼ ነው* ለሰዎች ከክርስቶስ ውጪ ጌታ እንደሌለ እምንናገረው?
#መቼ ነው* ጥሩና ለጋሽ መልካም ሰው የምንሆነው?
#መቼ ነው። ክርስቲያንነታችንን የምናስተዋውቀው?
#መቼ ነው* ለድሃ እምናዝነው?.
#መቼ ነው* ትዳራችን ሰላም ሚያገኝው?
#መቼ ነው* የጋብቻን ጥቅም ተገንዝበን ለትዳር የምንቻኮለው?
#መቼ ነው* ከሀሜት ሰውን ከመበድል; ከማስቀየምና ከማማት እምንላቀቀው?
#መቼ ነው* ወላጆቻችንን እምናስደስተውና እምንታዝዝው?
#መቼ ነው* ያልተጣራ ውሬ ካማውራት እምንቆጠበው?
#መቼ ነው* እምንዋደደው?
#መቼ ነው* እግዚአብሔር በሰጠን ነገር ደስተኞች የምንሆነው?
#መቼ ነው* ስግደት ፆም ፀሎት የምንላመደው?
#መቼ ነው* የበድለንን ይቅር የምንለው?
#መቼ ነው* ከራስ ወዳድነት እምንላቀቀው?
#መቼ ነው* ከሞት በኃላ ላለው ሕይወት ስንቅ እምናዘጋጀው?
#መቼ ነው* አባቶችን እምናከብረው?
#መቼ ነው* ለእውቅት ጊዜ የምንሰጠው?
#መቼ ነው* የምንሞትበትን ቀን ቀንና ስፍራ ስለማናውቅ ለበጎ ምግባር የምንፍጠነው?በተጠንቀቅ የምንዘጋጀው?
#መቼ ነው*ክርስትናን የምንኖረው?
#መቼ ነው*በእውቀታችን ልክ የምን ስራው?
#መቼ ነው? #መቼ ነው? #መቼ ነው?

ተራራውን ደልድለህ፣ሸለቆውን ሞልተህ፣ጎባጣውን ደልድለህ፣ሸካራውን አለስልሰህ መንገዴን ያቀናህልኝ፤የማለዳ ድምቀቴ፤የቀን ውበቴ የጨለማ ብርሃኔ አምላኬ መድኃኒቴ ቤዛየ ኢየሱስ ክርስቶስ ላንተ እኔስ ምን ልል እችላለሁ?እንዲሁ ተመስገን፣እንዲሁ ክበር፣እንዲሁ ተወደስ፣

በሕይወቴ ስንት አለፈ!፣ሞት ለሚገባኝ አመፀኛ ሕይወት ሰጠኸኝ!፣ዝም ብለህ አፈቀርከኝ! እንዳለፈ ከንቱ ዘመኔ አሁንም በከንቱ ዘመኔ አይፈፀም! በቤትህ በቅፅርህ አልውጣ ፣ፍፃሜየን በሰላምህ ቦታ ከቅድስት ቤተ ክርስትያን አልጉደል!የታመኑ የባሪያዎችህን አይነት ፍፃሜ ለኔም አስተምረኝ!

እንዳመንኩብህ ልሙት፣ፍፃሜየ ለእቅፍህ ብቻ ይሁን፣አንተን አጥቼ በውድ እንቁና አልማዝ ወርቅና ብር ከምዋብ እርቃኔን ከመስቀልህ ስር ልገኝ፣ከስርህ አትጣለኝ፣በአማኑኤል ስምህ፣በተወጋ ጎንህ በፈሰሰ ደምህ ልታተም።በአንተ የሕይወት ተስፍን ላግኝ።እርዳኝም አግዘኝም።

የቅድስት ድንግል ማርያም፣ቅዱሳን መላዕክት፣ነብያት፣ሐዋርያት፣ፃድቃን፣ሰማዕታት፣ቅድስት ቤተ ክርስትያን እና የዕፀ መስቀሉ በረከት አይለየኝ! አይለየን፣አይለያችሁ!
👍1👏1
እንኩዋን ለሊቀ መላእክት "ቅዱስ ሚካኤል" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት

=>ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::

+ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::

+በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል:: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)

+ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::

+"+ ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ +"+

=>ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን እንደ ረዳው ታስተምራለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በመጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 5 ላይ እንደ ተጻፈው ቅዱሱ መልአክ ለኢያሱ ተገልጦለታል:: እሥራኤልን በምድረ በዳ የመራ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ሲያርፍ ታላቅ ሐዘንና ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር::

+እግዚአብሔር ግን ኢያሱን አስነስቶ አረጋግቷቸዋል:: ቅዱስ ሚካኤል 40ውን ዘመን እሥራኤልን ደመና ጋርዶ: መና አውርዶ: ክንፉን ዘርግቶ: ጠላትን መክቶ ከሙሴ ጋ እንደ መራቸው ከኢያሱ ጋርም ይሆን ዘንድ ከሰማይ ወረደ::

+በኢያሪኮ አካባቢም የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በግርማ ለኢያሱ ታየው:: ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ "አንተ ከእኛ ወገን ነህን? ወይስ ከጠላቶቻችን?" ሲል ጠየቀው:: ቅዱስ ሚካኤልም መልሶ "እረዳህ ዘንድ እነሆ የሠራዊት አለቃ ሆኜ ተሹሜ መጥተቻለሁ" አለው::

+ያን ጊዜ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ በግንባሩ ተደፍቶ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰገደለት:: ቅዱሱ መልአክም አክሎ "ፍታሕ ቶታነ አሳዕኒከ እም እገሪከ: እስመ ምድር እንተ ትከይዳ ቅድስት ይዕቲ - የረገጥካት ምድር የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ" አለው::

+ኢያሱም የተባለውን አደረገ:: ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን "ለመላእክት የጸጋ (የአክብሮ) ስግደት ይገባል: በቅዱሳኑ ፊትም ጫማ ተለብሶ አይቆምም" የምትለው:: ያ መሬት ሊቀ መላእክት ቢቆምበት ተቀድሷል:: ዛሬም ቤቱ በታነጸበት: ታቦቱ በተቀረጸበት ቦታ ሁሉ ቅዱሱ መልአክ አለና ጫማን አውልቆ: ባጭሩ ታጥቆ መግባት ይገባል::

+ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከኢያሱ ጋር ሆኖ አማሌቅን ጨምሮ የእሥራኤልን ጠላት አጥፍቷል:: ጥቅመ ኢያሪኮን (ቅጥሩን) አፍርሷል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: በገባኦን ፀሐይን: በቆላተ ኤሎምም ጨረቃን ሲያቆም ከእርሱ ጋር ሆኖ ረድቶታል::

+"+ ዱራታኦስና ቴዎብስታ +"+

=>ቅዱሳኑ ዱራታኦስ (ዶርታኦስ) እና ቴዎብስታ (ቴዎብስትያ) የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ናቸውና በዚህች ዕለት ይታሰባሉ:: በድርሳነ ሚካኤልና በመጽሐፈ ስንክሳር ተጽፎ እንደምናገኘው 2ቱ ቅዱሳን በተቀደሰ ትዳር ተወስነው: ሕጉን ትዕዛዙን ፈጽመው: ለነዳያን ራርተው: ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለው የሚኖሩ ነበሩ::

+ይልቁኑ ግን የጌታችን: የእመቤታችንን እና የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ያለማስታጐል ያደርጉ ነበር:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ሐብት ንብረታቸው አልቆ ተቸገሩ:: ግን የጨነቃቸው መቸገራቸው ሳይሆን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ሊያቆሙ መሆናቸው ነው::

+አማራጭ ሲያጡ ተቀምጠው ተመካከሩ:: የቅዱሱ መልአክ ዝክር ከሚቀር ልብሳቸውን (ያውም የክብር ልብሳቸውን) ሊሸጡ ተስማሙ:: በዚህ መሰረት ቅዱስ ዱራታኦስ ወደ ገበያ ሲሔድ ወዳጁ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወረደለት::

+መንገድ ላይም የጦር መኮንን ሃገረ ገዢ መስሎ ተገናኝቶ አጫወተው:: ችግሩን ጠይቆም መፍትሔውን ነገረው:: "እኔ እዋስሃለሁና ለበዓል የሚያስፈልጉህን ነገሮች ሁሉ ገዝተህ አሰናዳ" አለው::

+"እኔ ወደ ቤትህ መጥቼ ስለምስተናገድ አንድ አሣ አምጥተህ አቆየኝ:: እኔ ሳልመጣ ግን አትረደው" አለው:: ቅዱስ ዱራታኦስ የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ ወደ ቤቱ ሲሔድ ድንቅ ነገርን ተመለከተ:: ሚስቱ ቅድስት ቴዎብስታ በቤቱ መካከል ሁና ቤቱ በበረከት ሞልቷል::

+ማሩ: ቅቤው: እሕሉ ሁሉ በየሥፍራው ሞልቷል:: ባልና ሚስቱ ደስ ብሏቸው:: ነዳያንን ሲያበሉ: እንግዳ ሲቀበሉ ዋሉ:: በሁዋላ ያ መኮንን (ቅዱስ ሚካኤል) በቤታቸው መጥቶ ተስተናገደ::

+በእርሱ ትዕዛዝ የአሣው ራስ (ሆድ) ሲከፈት በውስጡ 300 ዲናር ወርቅ (እንቁ) ተገኘ:: ቅዱሳኑ ይህን ተመልክተው ሲደነግጡ ቅዱስ ሚካኤል ክንፉን ዘርግቶ ራሱን ገለጸላቸው:: ደንግጠው በግንባራቸው ተደፉ::

+እርሱ ግን "በተገኘው ሃብት እዳችሁን ክፈሉ:: ከዚህ በሁዋላ ግን በምድር አትቸገሩም:: በሰማይም ክፍላችሁ ከእኔ ጋር ነው" ብሎ ባርኩዋቸው ወደ ሰማይ ዐረገ:: እነርሱም በሐሴትና በበጐ ምግባር ኖረው ዐርፈዋል:: ለርስቱም በቅተዋል::

+"+ ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ +"+

=>የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ::
*በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ::
*በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ::
*በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ::
*ምጽዋትን ያዘወተረ::
*አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
¤አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::

+"+ አፄ በእደ ማርያም +"+

=>"በዕደ ማርያም" ማለት "በማርያም እጅ" እንደ ማለት ነው:: እኒህ ሰው የኢትዮዽያ ንጉሥ ሲሆኑ የነገሡትም በ1460 ዓ/ም ነው:: ደጉ አባታቸው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሲያርፉ በመንግስቱ ተተክተው ሃገራችንን አስተዳድረዋል:: ድርሰት ደርሰዋል:: አብያተ መቃድስ አንጸዋል::

+በተለይ ለቅኔ ትምሕርት ማበብ ልዩ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ይነገራል:: ልክ በነገሡ በ10 ዓመታቸው ግን መንግስተ ምድር በቃኝ ብለው በምናኔ በርሃ ገብተዋል:: በዙፋናቸውም አፄ እስክንድር ተተክተዋል:: ጻድቁ ንጉሥ ግን ቅዱስ ሚካኤልን ይወዱት ነበርና በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን በክንፈ ሚካኤል ከክፉው ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም አይለየን::

=>ኅዳር 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ
3.ቅዱሳን ዱራታኦስና ቴዎብስታ
4.አፄ በዕደ ማርያም ጻድቅ
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
6.ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ
7.አባ ፊላታዎስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
3.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
4.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
5.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
6.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
7.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ

=>+"+ በሰማይም ሰልፍ ሆነ:: ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ:: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ:: አልቻላቸውምም:: ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም::
1👏1
ሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ:: +"+ (ራዕይ. 12:7)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ
•…ኢትዮጵያን የነካ…

…ኢትዮጵያ ዓሣ ናት፣ ለሰይጣናት ፈቃድ የማትጨበጥ ዓሣ። ኢትዮጵያ ተልባ ናት። ለአፋቃሬ አጋንንቶች ሁሉ የማትጨበጥ ተልባ። ሙልጭልጭ የምትል ተልባ። ኢትዮጵያ የጋለ የብረት የኳስ አሎሎ ናት። ሲያዩዋት የምታምር፣ ሲጨብጧት የምትፋጅ እሳት ናት። ኢትዮጵያን የሚያውቋት የሉሲፈር መንፈስ ርዝራዦች አይደሉም። ኢትዮጵያን የሚያውቋት በስሱም ቢሆን ማንነቷ እንዲገለጥላቸው የተፈቀደላቸው አካላት ብቻ ናቸው። ኢትዮጵያ የሙሴ ጽላት መቀመጫ መንበሩ ናት። ኢትዮጵያ የክርስቶስ ኢየሱስ መስቀሉ ማረፊያ ዙፋኑ ናት። ኢትዮጵያ መካነ ቅዱሳት ናት። ኢትዮጵያ 24/7 ስመ እግዚአብሔር የሚጠራባት የቅዱሳን ምድር ናት። (ይሄ የአውሮጳና የአማሪካ የሃይማኖት ፍልስፍና የወለደውን ዲቃላውን አጭቤ ነጋዴ አይመለከትም) አዎ ኢትዮጵያ በምድር ካሉ ሃገራት ሁሉ የተለየች ናት። በ20 ዓመት የአፍጋኒስታን ቆይታቸው የተባበሩት መንግሥታትን ሁለት ጊዜ ብቻ ለውሳኔ የጠሩት አካላት ለኢትዮጵያ ሲሆን በአንድ ዓመት 12 ጊዜ ስብሰባ ሲቀመጡባት ስታይ የኢትዮጵያ ክብር እና ውድ ዕንቁ የመሆኗ ምስጢር ይገለጥልሃል።

…ይሄን ስንል የሚበሳጩ፣ የሚጎፈሉ፣ የሚናደዱ፣ የሚንበጫበጩ፣ ለሃጫቸው እስኪዝረበረብ ድረስ የሚንተፋተፉ፣ እሷ ኢትዮጵያ ከሶሪያ፣ ከየመን፣ ከኢራቅ ከሊቢያ በምን ትለያለች? የሚሉ የራሳችን ባንዳ የአጋንንት ፈረሶች እንደአሸን ፈልተው እንደሚተራመሱ እናውቃለን። ደግሞም የትየለሌ ናቸው። የእናት ጡት ነካሾች፣ የተረገሙ። አዕምሮአቸው የተደፈነ፣ የጠላት ቅጥረኞች፣ ዘማውያን፣ ነፍሰበላ ሰዶማውያን፣ አረመኔዎቹ ጡት ነካሽ ባንዳዎች ነፍ ናቸው። በኢትዮጵያ ታላቅነት የሚያፍሩ፣ ነጭ ስላልገዛን የሚቆጩ፣ ባርያ የባርያ ልጆች ነፍ ናቸው። "ኢትዮጵያን ሲኦልም ድረስ ገብተን ቢሆን እንበትናታለን" እስከማለት የደረሱ የአጋንንት ፈረሶችን የሚደግፉ የትየለሌ ናቸው። የፈረሱ ጋላቢዎችም፣ ፈረሶቹም ግን ሁላቸውም በአንድነት ይወቃሉ። ይደቅቃሉ። ይደመሰሳሉ። እግዚአብሔር ታላቅ ነው።

…አሜሪካ የጥንታውያን ሃገራት ቀበኛ ናት። ገና ለጋ ጩጬ ስለሆነች በጥንታውያን ሃገራት ትቀናለች። አይኗ ደም ነው የሚለብሰው። አሜሪካ ጥንታዊቷን ሶሪያን አፍርሳለች። ጥንታዊቷን ኢራቅን አፍርሳለች። ጥንታዊቷን ሊቢያን አውድማለች። ጥንታዊቷን የመንን ፍርስርሷን አውጥታለች። አሁን የቀረቻት ጥንታዊቷ ሃገር ኢትዮጵያ ናት። ሶማሌን ገንጥለው፣ ጁቡቲን፣ ኤርትራን ቆራርጠው ገንጥለው። ያለ ወደብ፣ ያለውኃም አስቀርተዋት አልረኩም። ከባህሩ አርቀውን ሊያጠፉን በብርቱ ደክመዋል። አሁን ደግሞ ትግራይን ገንጥለው፣ ኦሮሚያ የምትባል አዲስ ሃገር ፈጥረው፣ ሶማሌን ለብቻው፣ ጋምቤላን ወደ ደቡብ ሱዳን፣ ቤኒሻንጉልን ለሱዳን ሰጥተው ኢትዮጵያን ብትንትኗን ለማውጣት ነበር ድካማቸው። እሱ ግን አይሳካም።

… ኢትዮጵያን በሃለል መሳፈጥ ከጀመረች ወዲህ እሜቴ አሜሪካ አሁን መዋረድ ትጀምራለች። #Nomore ዓለምአቀፋዊ የአማሪካና የተባባሪዎቿ የመውጊያ ብረት ሆኖ ያገለግላል። ዳግማዊ ዓድዋ ዳግም በዚህ ዘመን ይገለጣል። አሜሪካ እና ሸሪኮቿ ሁሉ ነገራቸው " ጓ " ይልባቸዋል። ብኩርናዋም ለሌላ ይሰጣል። መቅኖ ቢስም ትሆናለች። ኢትዮጵያ ዳግም ታሸንፋለች። የኢትዮጵያ ተዋጊዋ እግዚአብሔር ነው። የኢትዮጵያ ተዋጊ ልዑል እግዚአብሔር ነው። እሱ ባይሆንማ ኖሮ እንደ ውስጥ ከሃዲው ብዛት፣ እንደ ውስጥ ሃገር ሻጩ ባንዳ ብዛት ይሄኔ እኮ የለችም ነበር። አንድም ፓስተር አማሪካን ሲቃወም የማታየው ለምን ይመስልሃል? አሜን ነው? አሜን ሃሌሉያ ብቻ ሙያ መስሎሃል። ሂኢ…

… ማርያምን ኢትዮጵያ ግን ትነሣለች !!
👍1
የዘመናችን ቅዱስ ጴጥሮስ !የትውልዱ አቡነ ጴጥሮስ!
ለመንጋው እረኝነትን
ለልጆች አባትነትን
ለቤተ ክርስትያን ክህነትን
ለምድሪቱ ጵጵስናን
ለወንጌሉ ትጉህ ገበሬን
ለአገልግሎት ብፅዕናን የደረቡ ትጉህ ናቸው።
የወሎ መሬት ግን እንደምን ታደለች!
በረክትዎ በኛ ላይ ትሁን!
ኢየሱስ ጌታ ነው።ኢየሱሴ ኬኛ።ተረስቶ ኢየሰስ ዘረኛ ነው አይነት ጨዋታ እነ ፓስተር ከፍያለው ጀምረዋል።ሃይማኖት እንደቲሸርት የሚቀያይር በሃይማኖት ላይ ግልሙትና የተሰማራ ፕሮ-ጠሽ ፓስተር ሁሉ ይህንን ቢል አይደንቅም።የማያውቁትን ኢየሱስ ነውና ካልሰበክናችሁ ካላቀበልናችሁ ብለው ታንቀው ሊሞቱ የደረሰት።
ሰሞኑን ተመስገን ነው።የአደባባይ ላይ አደንቋሪ ስብከታቸውና ወረን የወጣው ትርዒታቸው አዲስ አበባ ላይ ብርድ ስክን ብሏል።ኦዮ ገለታ ዋቃ !
«ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታድያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡»

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
በመላው አለም ያላችሁ የአንዲት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተሰቦች በከበረው የእግዚአብሔር ሰላም እላችኋለሁ እንደ ምታውቁት ዝክረ ቅዱሳን ማህበረ ቅዱስ ዳዊት የህብረት ባንክ የባንክ አካውንት እንደ ተዘጋ በዲ/ዮርዳኖስ አበበ በኩል በyoutubeም በቴሌግራምም በኩል ተነግሯል በመሆኑም አሁን ህጋዊ እና በቤተ ክርስትያኒቱም ሆነ በብፁዓን አባቶች በኩል ይሁንታ አግኝቶ አገልግሎት ላይ የሚውለው የባንክ አካውንት ከስር ያለው ነውና ይህንን አካውንት በመጠቀም ሁላችሁም ገዳማትን አድባራትን እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶችን እንድትረዱ በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጠይቃችኃል።
እንኳን ደስ አለሽ እናታለም ቤተ ክርስትያን ሆሳዕና ጥያቄው ተፈቷል።ህጋዊ ካርታዋን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እምየ ተዋህዶ ተረክባለች። ደስስስስ ሲል!እግዚአብሔር ይመስገን!
2025/07/12 08:05:15
Back to Top
HTML Embed Code: