Telegram Web
# ተቻኮልኩ 😍

መገናኘት ላይቀር አብሮ መሳሳቁ
ምነው እንባ እንባ አለኝ  ፈሰዉ የማያልቁ
ተቻኮልኩ አቃተኝ ነገን መጠበቁ
መጨነቄ በዛ ልቤ መሸበሩ
ሀሳቤ ምኞቴ ከአንተ ተሳሰሩ
ምነው ከአንተ ጋራ አሁን በነበሩ
እያለ ዉስጠቴ ብዙ ይሞግተኛል
እንደምትመጣ ሳዉቅ ነገ ይናፍቀኛል

        ፅጌሬዳ አስናቀዉ

@yenagtm
@yenagtm
"ስለሌለሽ አይደል?"

~ ~ ~ ~
ሌሊት ስድስት ሰዓት
የመናፈቅ መዓት
በድቅድቅ ጨለማ
እቅፍሽ የለማ
ቢኖርማ ኖሮ
የማንም ድሪቶ ባልመጣ ከኔ በር
ንፋስ ጌታ ሆኖ ባላዘዘኝ ነበር
ስለሌለሽ አይደል?

እንዲህ ባልነበርኩኝ
የፌስታል ሽወታ ደጄ ድረስ መጥቶ
እንዴት ቤቴ ገባ ውርጭ አቅም አጊንቶ?
ስለሌለሽ አይደል?

ነፍሴን ብቸኝነት አልምዶ ቢያፀናኝ
የሴተኛ አዳሪ ጩኸት ባላስቀናኝ::
ስለሌለሽ አይደል?


ኤልያስ ሽታኹን

@yenagtm
@yenagtm
@yenagtm
የመታሽ ክንፍሽን
የቀማሽ ሳቅሽን
   ማንነው?
እኔን
እኔን የኔ ርግብ
አልችልም ሆኖ ነው ከዓለም ግብግብ
አልችልም ሆኖ እንጂ ባሁኑ ቦታዬ
እኔማ እንድድሮ ባቅፍሽ ነው ደስታዬ
                      (ብስምሽ ደስታዬ)
ልጠይቅሽማ
ተለያየን ማለት ያስብላል ምን ግዴ?
ሰው ትዝታ ሲሆን አቧራ ነው እንዴ?
ተለያየን ማለት ፍቅራችን በነነ
ተለያየን ማለት ፍቅራችን ተነነ
          :
ማለት ይሆን እንዴ?

እኔማ
ተለይቼሽ እንኳ መውደቅሽ ያመኛል
               ማዘንሽ ያመኛል
             ማኩርፍሽ ያመኛል
ሰው ግን ይመጣና
"አልወጣልችልህም" ማለት ነው ይለኛል፡፡
እውነታችውን ነው


ኤልያስ ሽታሁን

@yenagtm
ከ ሄ ድ ሽ  በ ኋ ላ
በሳግ ካለቀሽው
ጮኸሽ ካወራሽው
ቆመሽ  ከዘወርሽው
...
እስከዛሬ ድረስ ከልቤ የቀረው
ዝም ያለ ፈገግታሽ 'ዝም' ብሎኝ የሄደው..

@yenagtm
@yenagtm
ከሁሉም ልብ የሚሰብረው ሐሙስ ምሽት የሆነው ነገር ነው።ጌታችን "ከእራት ተነሳ ልብሱንም አኖረ:ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤በኃላም በመታጠቢያው ውሃ ጨርቅ ጨመረ።የደቀመዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።የእግር ሹራብ በማይደረግበትና ክፍት ጫማ በሚደረግበት በዚያ ዘመን ቀኑን ሙሉ ሲጓዙ የዋሉበትን የሐዋሪያቱን በአቧራ ያደፉ እግሮች ሊያጥብ ተነሳ።በእስራኤል ባህል እግር ማጠብ የሎሌዎች ስራ ቢሆንም የሰማይና የምድር ንጉስ ግን በትህትና እንደ ሎሌ ሆነ።ጌታችን አጎንብሶ የደቀመዛሙርቱን እግር ሲያጥብ ይሁዳም ሊታጠብ ተራውን ይጠብቅ ነበር።ጌታውን ሊሸጥ በተስማማበት ማግስት ጌታችን አጎንብሶ እግሩን አጠበው።

ርዕስ📓ህማማት
ደራሲሄኖክ ሀይሌ


@yenagtm
#ሞት_ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?

ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!

ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!

ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!

ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!

ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!

ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡

(
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)

"ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።"
  - ሉቃስ 24፥5

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችንና ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ
ለመላው የክርስትና መልካም እምነት ተከታዮች
✝️✝️✝️መልካም በአል
✝️✝️✝️

@yenagtm
​​​​​​​​
          
እናቴ  ልውለድሽ

             
ገና ከጅምሩ ስትወልጂኝ አምጠሽ
በስስት አነቡ እኚያ ውብ አይኖችሽ
እጆችሽ አቀፉኝ ከደረትሽ ገባሁ
የልብሽን ፍቅር በትርታሽ ሰማሁ

ጡቶችሽ ደጋጎች ለኔ ተሰዉልኝ
እነሱ እያለቁ እኔን ሙሉ አ'ረጉኝ
ከወተቱ ጋራ ፍቅር አቀመሱኝ
የዋሁ አንደበትሽ ህመምሽን ደብቆ
ልጄ ብሎ ጠራኝ ልጅነቴን አውቆ
.
የትኛው ተነስቶ የትኛውስ ይቅር
እማ ውለታሽን እንዴትስ ልናገር

ብቻ.....

መክፈል ስለማልችል እማ ያንቺን ውለታ
የሁሉ ፈጣሪ የሰማዩ ጌታ
አንዴ ቢፈቅድልኝ
እንደው እሺ ቢለኝ

እኔ እናት ሆኜ አንቺን በወለድኩሽ
ምጥሽን አምጬ ውለታ በዋልኩሽ
ህመምሽን ታምሜ ፍቅሬን ባሳየሁ..

            ካነበብሁት

@yenagtm
@yenagtm
እወዳታለሁ

እንደማታለል በውሸት በቀል
ለጠላኝ ሁሉ እንደ መሰቀል
ስቃይን በሳቅ እንደመከለል
እወዳታለሁ
ብርቱ ነኝ ብሎ እንደመሰበር
አልፍ እንደመሄድ የሞትን ድንበር

ቶማስ አፀደ
@yenagtm
@yenagtm
Forwarded from ÃM€Ñ
የሲኒ ምንጣፍ
350 ብር
ለማዘዝ
@Ye29stotaN ያናግሩን
ፊትህ ያስታውቃል
  እንደድሮ አይደለም
ዝምታ ወሮታል
  ጥርስህም ተከድኖ
ፈገግታ ናፍቆታል
  ልብስህ ደም ነክቶታል
'ሆድህ ቆስሏል' መሰል
  ብላ ስትናገር
የነበረ እኮ ነው እያልኩ
  ልሸሸግ ስሞክር
አድንህ ይሆናል
  እስኪ አንዴ ልይልህ
ብላ አረጋግታ
  እፍፍ እያለችልኝ
ልስፋው ይሆን ብላ
   የከረመ ህመሜን
አባብላ አባብላ
  ነካካችው ቁስሌን
እኔ ሞኙ ደግሞ
  ሰው አገኘው ብዬ
የቱ ጋር ስትለኝ
   ይኸውና ብዬ
ካዳነቺኝ በሚል
  የዋህ የጅል ተስፋ
አይኔ ቢያይም እንኳ
  ሆዷ እየቻለ በኔ ላይ ስትከፋ
ሀዘኔን በሙሉ
  ማጣቴን በሙሉ
ሳወራት ከርሜ
   ድምጿ ከጉያዬ
እያደር ሲጠፋ
   ለምጃታለኋ
ላጣት አልችልማ
  ታዲያ
መዳኒቴ እያልኩ
  ስሞትልሽ እያልኩ
ላቆያት ስለፋ
  ጭራሽ ጥላኝ ሄዳ
እንኳን ልታድነኝ
   ያባሰቺኝ ከፋ

ናኒ

@yenagtm
@yenagtm
www.tgoop.com/Tomarket_ai_bot/app?startapp=r-0000Q2tS

Farm TOMATO with me and secure your token allocation through
Tomarket.ai!

I've prepared a warm welcome meal just for you! 🍅

Use my link to get 50,000 TOMATO! Limited time offer.
www.tgoop.com/Tomarket_ai_bot/app?startapp=r-0000Q2tS

Farm TOMATO with me and secure your token allocation through
Tomarket.ai!

I've prepared a warm welcome meal just for you! 🍅

Use my link to get 2,000 TOMATO! Limited time offer.
2025/01/16 08:43:59
Back to Top
HTML Embed Code: