Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
በርካታ ወንድምና እህቶች መጽሀፉን በመግዛት እንዲሰራጭ ነይተዋል። ወንድሜ ኡስታዝ ወሒድ ዑመር እራሱን ጨምሮ ወንድምና እህቶችን በማስተባበር ባደረገው ጥረትም ከ210 በላይ መጽሀፍትን በመግዛት አርኣያ ሁኗል፣ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈላቸው። ብዙዎቹ በግል የነዩት ስማቸው እንዲጠቀስ የሚፈልጉ ባለመሆናቸው ሁሉኑም በጅምላ ለማመስገን ተገድጃለሁ። የእሳቸውን ክብር ለመከላከል በተሞከረው ጥረት ውስጥ የአቅማቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል። መጽሀፉ ለበርካታ ሰው እንዲዳረስ ከማድረግ በተጨማሪ ከፍ ያሉ ስራዎች እንዲሰሩም ሞራል ሁናችኃልና አላህ መልካም ምንዳችሁን ይክፈላችሁ። በጀነት ከምትወዷቸው ነቢይም ጋር ጎረቤት ያደርጋችሁ ዘንድ አላህን እማጸነዋለሁ። ጀዛኩሙላሁ ኸይራ፣ በአላህ ﷻ ፍቃድ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች መሰራጨት ይጀምራል። የተመረጡ ስራዎችም እዚሁ ለእናንተ ሪፖርት የሚደረጉ ይሆናል።

🔖 በቀሪ መጽሀፍቶች ላይ ለመነያት ግን አሁንም በሩ ክፍት ነው።

1000572021029
Hayat Seid

https://www.tgoop.com/Yahyabook
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
Photo
የኦርቶዶክስ ኢሊቶች ያለወትሯቸው "እፎይ" የተባለውን ግለሰብ መደገፍ እንደ አዋጭ ስትራቴጂ ያዩበት መንገድ ትንሽ ጥያቄ ሁኖብኝ ነበር። መሠል ሰዎች ሲፈጠሩ "አብሮ የኖረውን ህዝብ ለመከፋፈል ነው" በሚል ቀድመው የሚያወግዙ ሰዎች ሳይቀር በዚህኛው ወቅት ግን ከፊት የመሰለፋቸው ሚስጥር ግርታን ይፈጥራል። ከፋፍለውን ለስትራቴጂክ ወዳጅነት የሆነ የሚፈልጉት አካል እንኳን ማስቀረት ሳይፈልጉ ነው በግልጽ ወደ ብልግናው ድጋፍ የገቡት። ሰዎቹን ሳያቸውና የተሳሰሩበትን ገመድ ስመለከተው ግን የሆነ ያልገባን ነገር ያለ ይመስለኛል።

መምህር ዘመድኩን በቀለ፣ መምህር ፈንታሁን ዋቄ፣ መምህር ታሪኩ አበራ ወዘተ ሁሉም በሚባል መልኩ የቀድሞ የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች የዚህ ተግባር ፊትአውራሪዎች ናቸው። ሁሉም በርካታ ልዩነቶች ቢኖሯቸውም የሚያመሳስላቸው ግን አንድ አጀንዳ አለ። ሁሉም ስርኣቱ ጋር የሚደረጉ የጠብመንጃ ትግሎችን የሚደግፉ፣ የሚመሩና የሚያስተባብሩ ናቸው። "ሙስሊሙ በመንግስታዊ ስርኣቱ ተጠቅሟል" በሚል እሳቤም ሙስሊሙን ጠምደው የያዙ ሰዎች ናቸው። በዚህ ሳምንት መምህር ፈንታሁን ዋቄ "እዚህ ሀገር ላይ ነጭ ለብሰህ ዝማሬ ስላካሔድክ ሳይሆን ጥቁር ለብሰህ ጠብመንጃ ካነሳህ ነው መብትህ የሚከብርልህ" ሲል በፌስቡኩ ጽፏል።

ተሳዳቢው ግለሰብ አውቆም ይሁን ሳያውቅ በዚህ ቡድን ፍላጎት ውስጥ ማደሩ ግን በጣም ግልጽ ነው። ክስተቱንም ግለሰቡንም ለአላማቸው የጋራ ሰልፍ/Solidarity/ ህዝቡን ቀስቅሰው ተጠቅመውበታል። ግለሰቡ "ኦሮሚያ ክልል ያለህ ስልጤ ወዮልህ" ሲል የነበረ ከመሆኑ ጋር በዚህ አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ለመሳተፍ ሩቅ ነው ማለትም ይከብዳል። በዚህ በኩል እኔ እና ወንድሜ አብዱረሒም አህመድ ለዚህ ድምዳሜ የዳረጉንን የቪዲዮና የጹሁፍ መረጃዎች በአላህ ፍቃድ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/Yahyanuhe
በትላንትናው እለት በወዳጅነት ፓርክ ለሰለምቴዎች በተዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ "በነብዩ "ﷺ" ዙሪያ" የተሰኘው አዲሱ መጽሀፍ 150 ኮፒ በስጦታ መልክ ተበርክቷል። ከዚህም በተጨማሪ ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ያሳተማቸው ፓምፍሌቶች ለወንድምና እህቶች ተሰጥተዋል። በዝግጅቱ ላይም አንድ እህት እስልምናን ተቀብላለች፥ አልሐምዱሊላህ

➭ ሙሉ ዝግጅቱ በአላህ ﷻ ፍቃድ ሚንበር ቲቪ ላይ በዒድ ቀን ይተላለፋል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/Yahyanuhe
ይህ ዲን በየቀኑ እየተዘለፈና እየተሰደበ እንኳን ህዝብ ግን እንደ ጎርፍ ይሰልማል። በተለይ ረመዳን በዚህ ረገድ ሁሌም ልዩ ወር ነው። ዲኑን የሚጠብቀውም ይፋ የሚያደርገውም አላህ ብቻ ነው።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/Yahyanuhe
መምህር ፈንታሁን ዋቄ በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ከነበሩ ተጽእኗቸው የጎላ ሰዎች መካከል አንዱ ነበር። በጥቅሉ ስሜታዊነት ቢያጠቃውም በማኅበሩና በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ግን ኹነኛ ስትራቴጂስት ነበር። በዘጠናዎቹ በነበረው የተሐድሶ ትግል ውስጥ ማኅበሩ ያሳትማቸው ከነበሩ ጸረ ተሐድሷዊ ጹሁፎች ጀርባ ነበር። ቤተ ክርስቲያኗ ከ50 አመት በፊት ወደነበረው የፖለቲካው የበላይነት መመለስ አለባት ብሎ በጽኑ ከሚሞግቱ ሰዎች መካከል ነበር።

በተለይም ባለፉት ስድስት አመታት ይህንን አቋሙን ሀገር ቤት እያለም ከተሰደደም በኃላ አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ቤተ ክርስቲያኗ ከመንግስት ጋር በነበራት አደገኛ ኮንፍሮንቴሽን ሳቢያ ይህንን ለመፍጠር የሚያስችለው ግራውንድ ሁሉ በመንግስት እንደተዘጋ ሲረዳ በስተመጨረሻም አሁን ላይ እየተካሄደ ያለውን የትጥቅ ትግል መደገፍ ላይ አተኮረ። በተለያዩ የትግሉ ሚዲያዎች በመቅረብ ሀሳቡን ማካፈል፣ ስልጠናዎችን መስጠት፣ አካሔዶችን መጠቆም "ቋሚ አገልግሎቱ" ሆነ። በህግ ቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊትም ከሀገር መሰደድ ችሏል። ይህ ሰው አሁን ላይ ነውረኛ ተግባር እየፈጸመ ለሚገኘው "እፎይ" ለተሰኘው ግለሰብ ይፋዊ ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛል። ግለሰቡን መደገፍ እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ እስልምናን በመስደብ ሳይቀር ከሰሞኑ በተለያዩ የትግል ሚዲያዎች ሀሳቡን ሰጥቷል (ኢንሻአላህ ቀጣይ አቀርባቸዋለሁ)

"መንግስት በጸሎት ሳይሆን በመሳርያ አፈሙዝ ነው የሚወርደውና ታጥቀህ ተዋጋ" ብሎ በይፋ የሚናገረው መምህር ፈንታሁን ዋቄ አንድ እስልምናን በጸያፍ ቃላት በመስደብ ኹከት እንዲፈጠር የሚተጋን ግለሰብ በምን አግባብ ሊደግፈው ይችላል? የሚለው መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው። ተሞክሮ ከከሸፈው የቀድሞ ፕሮጀክት ውስጥ ሌላኛው ክፍል ላለመሆኑ ግን ምንም እርግጠኛ መሆን አይቻልም።


ቪዲዮው፦

https://vm.tiktok.com/ZMBArhptF/
አንድን ሰው (ነብይ) አምላክ ጋር አተካክሎ ከማመን በላይ አምላክን መስደብ አለን?ኃያሉን አምላካችንን "ሰው ነበር" ብሎ ደካማ ከማድረግ በላይ በሱ ክብር ላይ መዘባበት አለን?ስሜት ቢኖራቸው ይህ ንግግር ሰማያትና ምድርን ሳይቀር በድንጋጤ የሚያርገፈግፍ አምላክ ላይ የቀረበ ስድብ ነው። ጭራሽ ተሰደብን ትላላችሁ?
"ንጽጽር መማር ፈልጌ ነበር"

ሰሞኑን በብዛት ከሚመጡልኝ መልዕክቶች መካከል ዋናው ይሄ ነው። ዩንቨርሲቲዎችን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የወጣት ጀመዓዎች ይህንን ጥያቄ በጀመዓም እያቀረቡ አስተውያለሁ። ከረመዳን በኃላ ስልጠና ለመውሰድ አውትላይን ተዘጋጅቶላቸው የሚጠባበቁም አሉ። ይህ ክስተት ፈጥሮት ከሚያልፈው መልካም አጋጣሚ ውስጥ አንዱ ይህ ይመስለኛል። ከጊዜያዊ የእልህ ስሜት በዘለለ በዘላቂነት ልዩነት ለመፍጠር ነይቶ መምጣት ግን ያስፈልጋል።

ካለን የጊዜ፣ የሰው ኃይልና የአቅም ውስንነት አንጻር ሁሉኑም ትምህርት ፈላጊ ማስተናገድ እንኳን ባያስችለንም ቢያንስ ጥቂት አቅም የፈቀደውን መርጦ ለማስተማር ጥሩ መነሳሳት የሚፈጥር ነው። ተሳዳቢዎች ሲሳደቡ በጥላቻ ብቻ ተነድተው ስለሚሰሩት ባክፋየር አድርጎ ነገ ፈተና የሚሆንባቸውን ሜዳ እየፈጠሩ መሆኑን አያቁም።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/Yahyanuhe
ይህ መሠረት የለሽ ክስ ተንቆ ቢተውም በተደጋጋሚ በመነሳቱ ማብራሪያ ማስቀመጡ መልካም ነው።

https://telegra.ph/ነብዩ-ﷺ-የልጅ-ልጆቻቸውን-ብልት-ስመዋልን-03-26
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዘካተል ፊጥርን ድንጋጌ አስመልክቶ የሚነሱ ጥያቄዎችን መሠረት ያደረገ በሸይኽ ዶ/ር ሙሐመድ ሓሚዲን حفظه الله የተሰጠ ፈትዋ ነው። መልዕክቱ ለሰዎች እንዲዳረስ ሼር ማድረግ አይዘንጉ።
ሸይጧን በረመዳን ከታሰረ ኃጥያት እንዴት ከምድር አልጠፋም? የሚለው ጥያቄ በክርስቲያኖች በኩል የሚነሳ ጥያቄ ነው። ይህንን በተመለከተ እንደሚከተለው በአጭሩ ማብራሪያ ተሰጥቷል፣ ያንብቡት፦

https://telegra.ph/በረመዳን-ሸይጧን-ከታሰረ-ኃጥያት-እንዴት-አልጠፋም-03-27
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የገብርኤል ታቦት በሳዑዲ አረብያ ሁጃጆችን ይገድል ነበር ሲሉ ያለምንም ማመንታት በአደባባይ ያስተምራሉ። ገብርኤልን ገዳይ ማድረጋቸው ሳያንስ በመሠል ተረቶች ግን ጥላቻን ለምዕመኑ ይግቱታል። ገብርኤል ሁጃጆችን የሚገድል ከሆነ "ከሊቀ መልዐኩ" ምዕመኑ ምን እንዲማር ፈልገው ነው ተረቱን የፈጠሩት የሚለው ግን የሚረብሽ ጥያቄ ነው።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/Yahyanuhe
የጨረቃ አቆጣጠርን/Lunar Calender/ በተመለከተ ረመዳንና ኢድ አል-ፊጥር በመጣ ቁጥር በክርስቲያን ወገኖቻችን በኩል የሚጠየቅ አለፍ ብሎም ባለማወቅ ሳቢያ ለመሳለቅ የሚሞክሩበት አጀንዳ ነው። ይህንን በተመለከተ መጽሀፍ ቅዱስ ምን ይላል የሚለው በዚህ አጭር ቪዲዮ ተዳሷል።

https://vm.tiktok.com/ZMBf55tFS/
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሰሞኑ አንዳንድ ፖለቲካና ኃይማኖት የተቀላቀለባቸው የኦርቶዶክስ መምህራን እያደረጉት ያለው ቅስቀሳ ከጀርባ በርካታ ጉዳይ እንደተሸረበ የሚጠቁም ነው። መሠል ቅስቀሳ ከሞጣው ቃጠሎ በፊት በተናበበ መልኩ ሲከውኑት ነበር። አሁን ደግሞ ፖለቲካውን ኃይማኖታዊ ካባ ብናላብሰው በሚል "የግራኝ አህመድ መንግስት መጣልህ" አይነት ያረጀ ቅስቀሳቸውን ድጋሚ ጀምረውታል። ሁሉም ሙስሊም በየቤቱ መሳሪያ አዘጋጅቶ እየጠበቀ እንዳለ በህብረት እየቀሰቀሱ ነው። ከልምድ እንዳየነው መሠል ፈጠራ ደጋግመው የሚያራግቡት ያሰቡት ነገር ሲኖር ነው።

የሚመጣውን ዒድ ጨምሮ ሙስሊሙ በጥንቃቄ ጉዳዮችን በመመልከት በወጥመዳቸው ላለመውደቅ ጥረት ያድርግ። የሚያስቆጣንን፣ ስሜታዊ የሚያደርገንን ለሚፈልጉት አላማ የሚወስደንን ጉዳይ ጠንቅቀው ስለሚያውቁት በሚገባ አቅደው ነው የሚመጡት። አደራ ዙሪያችንን በጥንቃቄ እንመልከት።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/Yahyanuhe
እንኳን አደረሳችሁ፣ ዒድ ሙባረክ
"በነብዩ ዙሪያ" የተሰኘው አዲሱ መጽሀፍ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን መነሻ አድርጎ በኒያችሁ መሠረት በነጻ መሠራጨት ጀምሯል። ይህ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የ6 ኪሎ የሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ላይብረሪ ነው። 150 መጽሀፍ ተረክበውን ወደ ላይብረሪያቸው አስገብተዋል። በተመሳሳይ የተለያዩ ዩንቨርሲቲዎችም በተወካዮቻቸው አማካኝነት እየወሰዱ ነው። በአላህ ﷻ ፍቃድ ቀጣይ የሚቀርቡ ይሆናል።

➭ መጽሀፉን ለመውሰድ የምትፈልጉ የተለያዩ የዩንቨርሰቲ ጀመዓዎች፣ የንባብ ማዕከላት ያላችሁ ሙስሊም ማኅበራት፣ ዳዕዋ ላይ የምትንቀሳቀሱ ማናችሁም ሰዎች ልታናግሩንና በነጻ ልትወስዱ ትችላላችሁ።

https://www.tgoop.com/Yahyabook

➭ በዚህ የመጽሀፍ ስርጭት ውስጥ ከአንድ መጽሀፍ ጀምሮ መጽሀፍትን መነያት የምትፈልጉም በተመሳሳይ ልታናግሩን ትችላላችሁ፦

https://www.tgoop.com/Yahyabook
፩/ መብራት ኃይል ኢድ ነገ መሆኑን የሰማ አይመስልም። በተለመደው ሰአት ዛሬም መብራቱን አጥፍቶታል። እዚህ ሀገር ላይ ረመዳንን በተለይም ኢፍጣርን ጠብቆ የሚከናወነውን የመብራት ማጥፋት ተግባር "ሆን ተብሎ" ነው የሚለውን ሀሳብ ለመቀበል ይቸግረኝ ነበር። ምናልባት ተሳስቸ ሊሆን ይችላል የሚለውን የተረዳሁት ግን በተለይ ዘንድሮ ነው። ለኢፍጣር ጉርሻ እንዳነሳን አላርም በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ እንዴት ይጠፋል?ያውም ከረመዳን በፊት ሰላም የነበረ መብራት..?! በዚህ ደረጃ በተመሳሳይ ቀን ሁሌም በሚባል መልኩ መጝሪብ ላይ ማጥፋት ግን "የአጋጣሚ" ነው ሊባል የሚችል አይደለም።

፪/ ከሙስሊም በኣላት ውጭ የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ውሀ ካለወረፋ ለሁሉም ይለቃል። ካለወረፋችን ሲመጣ ተደስተን ምክንያቱን ስንጠይቅ የገና በኣል ወይንም ፋሲካ ስለሆነ ምዕመኑ እንዳይቸገር መሆኑ ተነግሮን እድሉን በጋራ አጣጥመነዋል። ይህ እድል ግን ለሙስሊም በኣላት ወቅት ፍቁድ ያልሆነ የሚመስል ያልተጻፈ ህግ መስሪያ ቤቱ ውስጥ ያለ ይመስላል። ዒድ አል አድሀም ይሁን ዒድ አልፊጥር በኣሉን መሠረት አድርጎ የሚለቀቅ ምንም አይነት ውሀ ግን የለም።

እድሉንም ነፍጋችሁን፣ መብታችንንም አሳጥታችሁን የምትጠቀሙት ነገር ምንድን ነው? በዚህ ተግባራችሁ የምታሳኩትን አላማ አስመልክቶ ግን ሁሌም መልስ የማጣለት ጥያቄ ነው።
የሀረማያ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ለአራቱም ካምፓስ የሚሆን አጠቃላይ 200 መጽሀፍ ከተነያው ላይ ወስደዋል። መጽሀፉን የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ስራ አስኪያጅ ወንድም ሙስጠፋ ለጀመዓው ተወካዮች አስረክቧል። መጽሀፉ ስርጭቱ የቀጠለ ሲሆን ሪፖርቶቹን በአላህ ፍቃድ በተከታታይ ወደ እናንተ የማቀርብ ይሆናል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/Yahyanuhe
2025/03/31 22:09:24
Back to Top
HTML Embed Code: