Telegram Web
ጤናወ በእጀወ በቤትወ የጤና በረከት የተለያዩ መፍትሄ ያጡ ችግሮች እናም በሽታወችን እንዴት አባቶች እና እናቶች ባቆዩነን ቅመማቅመም ቅጠል ስር ፍሬ እና ጥበብ መታከም መፈወስ ከችግራችን መውጣት እንዴት እንደምንችል እምንረዳበት የምንችለው  ቻናል ነው ይቀላቀሉ በየቀኑ የምንለቃቸውን ጠቃሚ መረጃ ተካፋይ ይሑኑ ሸር ያድርጉ
    👇
https://vm.tiktok.com/ZMhNYSvDS/       ለበለጠ መረጃ
0912718883
0917040506 በቴሌግራም በውስጥ መስመር የሚፈልጉትን ያስቀምጡ
👉አድራሻችን አዲስ አበባ አየር ጤና ካራቆሬ ወደመድኀኒአለም 200ሜትር ገባ ይበሉ
ቁጥር 2ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በአሮየው 
አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት ያገኙናል ይምጡ
ይፈወሱ
     https://www.tiktok.com/t/ZMhN2XcBE/

በማንኛውም አገልግሎት ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈፅማሉ
በአፋር ክልል፣ ሳጋንቶ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ገንፍለው የውጡት ፍል ውሃዎች

በአፋር ክልል፣ ዱለሳ ወረዳ በተከሰት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየተፈጠሩ ይገኛሉ።

በወረዳው በሳጋንቶ ቀበሌ የደረሰውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በስፍራው በአካል በመገኘት የመስክ ምልከታ ያደረገ የኢቢሲ ሪፖርተር በቀበሌው በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየወጡ መሆኑን መታዘቡን ገልጿል።

በቀበሌው በተለይ በዶፈን ተራራ ላይ የመሬት መንቀጥቀጡ በመጠኑም በድግግሞሹም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን በዚህም ሳቢያ ተራራው እየተናደ እንደሆነ ገልጿል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በፈጠረው ግፊት በቀበሌው እንፋሎት አዘል ፍል ውሃ እና ቅባት አዘል ጥቁር ውሃ ከመሬት እየፈለቀ መሆኑንም ጠቅሷልል።

በቀበሌው የሚኖረው አርብቶ አደር ማህበረሰብ ከሥፍራው ተነስቶ በሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፍር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

በመሬት መንቀጥቀጡ ሳቢያ በፈንታሌ እና በዶፈን ተራራ መካከል የተፈጠረው የመሬት ስንጥቅ ክፍተቱ እየጨመረ መሆኑንም አክሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
ፀደቀ

በኢትዮጵያ የወንድ የዘር ፈሳሽ ልገሳ፣  የሰውነት አካል መለገስ እና በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት እና አስተዳድር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።

አዋጁ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጀምረው የማያውቁ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የጤና አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የሚያደርግ ነው። ለአብነትም መዳን በማይችል እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሀኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደው፣ የሰውነት አካልን ያለ ክፍያ መለገስ፣ የወንድ የዘር ፍሬ እንዲለገስ እና ሌሎችም አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን ይፈቅዳል።

ምክር ቤቱ ላለፉት ወራት የተለያዩ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
የእንጀራ ልጁን ከ10 ዓመቷ ጀምሮ አስገድሮ ሲደፍር የቆየውን ከ10 ዓመት በኋላ እንደገደላት የተረጋገጠበት አቶ ሚካኤል ሽመልስ ጌታሁን የተባለ ግለሰብ ሞት ተፈረደበት፡፡

በአዲስ አበባ አንዲትን ህፃን ከ10 ዓመት እድሜዋ ጀምሮ ለዓመታት በተደጋጋሚ በመድፈርና በመጨረሻም በመግደል ወንጀል የተከሰከው ግለሰብ ሞት ተፈረደበት፡፡

ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ተከሳሹ የሟች እንጀራ አባት ሲሆን ከ10ኛ አመት እድሜዋ ጀምሮ ለማንም እንዳትናገር በማስፈራራት አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት ቆይቷል፡፡

የድርጊቱ ሰለባ የሆነቸው ሟች አዶናዊት ይሄይስ በተከሳሽ የእንጀራ አባቷ እስከተገደለችበት 2015 ዓ.ም ድረስ 2 ጊዜ እንዳስረገዛት እና የመጀመሪያው እድሜዋ 19 አመት እንደሆነ በማስመሰል በሀሰተኛ ማስረጃ ፅንሷን እንድታስወርድ አስገድዷት ነበር ተብሏል፡፡

እንዲሁም በ2015 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ ፖሊሶች ይሄን ወንጀሉን በተመለከተ  በደረሳቸው ጥቆማ ሊይዙት ወደ ቤት በመጡ ጊዜ በመስኮት ወጥቶ ካመለጣቸው በኋላ ተመልሶ በእናቷ ፊት ደጋግሞ በቢላ በመውጋት ሲገድላትም በጊዜው የ25 ዓመት የነበረችው ሟች እርጉዝ እንደነበረች ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው 15 ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተፈፅሟል የተባለውን ይሄንኑ ወንጀል የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ውንብድና ችሎት ክስ ቀርቦበት ሲከራከር ቆይቶ ጥፋተኝነቱም ተረጋግጦበት ችሎቱ ትናንት የሞት ፍርድ እንደፈረደበት ሰምተናል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
በአክሱም የሚገኙ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ችግር በሦስት ቀናት እንዲፈታ ምክር ቤቱ አሳሰበ!

በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርት እንዳይከታተሉ መከልከሉን ተከትሎ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ "ጥያቄያችን በሦስት ቀናት ውስጥ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ከአማኙ ጋር በመመካከር ቀጣይ ሰላማዊ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል" ሲል አስጠነቀቀ።

ምክር ቤቱ ባወጣው ባለ 11 ነጥብ አቋም መግለጫ "የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ አስመልክቶ ያወጣው ህግ እንዲከበር እንጠይቃለን" ብሏል።“ትግራይ ያለችበት ፖለቲካዊ እና ከባቢያዊ ቀውስ በቂ ነው” ያለው መግለጫው “ሌላ ሃይማኖትን መሠረት ላደረገ የቀውስ በር መክፈት ክልሉ ከድጡ ወደ ማጡ መክተት ነው” ሲል አሳስቧል።

Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa
የመሬት መንቀጥቀጡ በከሰም ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ!

በአዋሽ ፈንታሌ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በከሰም ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ።በአፋር ክልል የመንግስት ልማት ድረጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሰን ዳውድ ለጋዜጣ ፕላስ እንዳስታወቁት፣ በአካባቢ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል፣ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችና ተቋማት ላይም ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ ከመጠነኛ ከፍ ወዳለ ደረጃ እየተሸጋገረ መምጣቱን ተከትሎ በአካባቢው በመኖሪያ ቤቶችና መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ያሉት አቶ ሀሰን፤ በተለይ ከትላንት ጀምሮ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳቱን ከፍ እያደረገው እንዳለ ጠቁመዋል፡፡እስካሁን በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው አደጋ ባይኖርም የስኳር ፋብሪካውን ጨምሮ በአካባቢው ባሉ ማህበረሰቦች መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት፡፡ይሁን እንጂ በአካባቢው የከሰም ግድብ እስካሁን ባለው ሁኔታ ጉዳት እንዳልደረሰበት ጠቁመዋል፡፡

ንዝረቱ አሁንም እየቀጠለ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ዜጎችን ከአካባቢው የማስወጣት ሥራ በስፋት እየተሰራ እንዳለ አስታውቀዋል፡፡የከሰም ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞችም ከአካባቢው እየወጡ እንዳለ ተናግረዋል፡፡ትላንት ሌሊት 9:53 ሰዓት ላይ ከሰሞኑ በመጠኑ ከፍ ያለና ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ይተወቃል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

ቤት ውስጥ ፣ አልጋ ላይ፣ ከቤት ውጭ የነበሩ ሰዎች ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል።

ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም በመቀጠሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትዘናጉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህጋዊ መንገዶች የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎችን ለሚከፍቱ ተቋማት ፈቃድ መስጠት ለጊዜውም ማቆሙን አስታውቋል፡፡

በፈረንጆቹ ኦክቶበር 2024 ብሔራዊ ባንክ ለአምስት የሀገር ውስጥ የግል ውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ፈቃድ መስጠቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡በፖሊሲ አውጪ ባንኩ በኩል ይህ ውሳኔ የተላለፈው ደግሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የትይዩ ውጭ ምንዛሬ ገበያውም ወይም በተለምዶ ጥቁር ገበያው ጋር ያለውን የምንዛሬ ዋጋ ልዩነት በማጥበብ ቀስ በቀስም ትይዩ ገበያውን ለማዳከም በማሰብ ነው፡፡

በዚህም መሰረት ዱግዳ ፊደሊቲ ኢንቨስትመንት ፒኤልሲ፣ ኢትዮ ኢንዲፔንደንት፣ ግሎባል ኢንዲፔንደንት፣ ሮበስት ኢንዲፔንደንትና ዮጋ የውጭ ምንዛሬ መገበያያ ቢሮዎች ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ እንደተሰጣቸው ይታወሳል፡፡አሁን ላይ ታዲያ ሌሎች አዳዲስ ተቋማትን ወደዚሁ ገበያ ከማስገባት አስቀድሞ እነዚህ የውጭ ምንዛሬ መመንዘሪያ ቢሮዎች አፈጻጸማቸው ምን ይመስላል? የሚለውን ለመገምገም ሲባል አዲስ ፈቃድ መስጠት መቆሙን ነው ብሔራዊ ባንክ ይፋ ያደረገው፡፡

እነዚህ ተቋማት ከዚህ ቀደም የባንክ ሥራዎችን ሰርተው የማያውቁ በመሆናቸውና ወደገበያው ሲገቡ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ ምክንያት ለገበያው አዲስ አሰራርን ይዘው መምጣታቸውንና ይህም ሁኔታ ባለፉት ጥቂት ወራት ያስመዘገበው ውጤት መገምገም እንዳለበትም ነው በምክንያትነት የቀረበው፡፡የፋይናንስ ዘርፉን የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ ቢሮውን ለመክፈት እያንዳንዱ ተቋም 15 ሚሊዮን ብር ካፒታልና ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ የሚሆን 30 ሚሊዮን ብር በዝግ አካውንት እንዲያስገቡ በመስፈርትነት ማስቀመጡም የሚታወቅ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
🎄የስጦታ በአላችን ለሆነዉ የገና በአል 🎅🏾
🎁የተለያዩ የስጦታ አማራጮችን አዘጋጅተን እየጠበቅናቹ ነው

Call ☎️ 0941573710
Contact @be_liye on Telegram

Telegram ላይ ማግኘት ትችላላቹ 👇

https://www.tgoop.com/simplysellerstore


Tiktok ቤተሰብ ይሁኑ👇

www.tiktok.com/@simply_shoppingb
🔷 የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ
              🔴አንኳን ደስ አላችሁ 🔴

በ 2016 ዓ.ም 45% ትርፍ /Dividend/ አትርፈናል

በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 450 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል

የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2 ሚሊዮን 250 ሺ ብር አትርፈዋል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው

ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ

ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም

40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ

አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ

ለበለጠ መረጃ: በ 0967907669 ይደውሉ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔷 የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ

በ 2015 ዓ.ም 51% ትርፍ /Dividend/ ለባለክሲዮኖች አከፋፍለናል

በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 510 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል

የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.5 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው

ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ

ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም

40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ

አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ

ለበለጠ መረጃ: በ 0967907669 ይደውሉ
ጤናወ በእጀወ በቤትወ የጤና በረከት የተለያዩ መፍትሄ ያጡ ችግሮች እናም በሽታወችን እንዴት አባቶች እና እናቶች ባቆዩነን ቅመማቅመም ቅጠል ስር ፍሬ እና ጥበብ መታከም መፈወስ ከችግራችን መውጣት እንዴት እንደምንችል እምንረዳበት የምንችለው  ቻናል ነው ይቀላቀሉ በየቀኑ የምንለቃቸውን ጠቃሚ መረጃ ተካፋይ ይሑኑ ሸር ያድርጉ
    👇
https://vm.tiktok.com/ZMhNYSvDS/       ለበለጠ መረጃ
0912718883
0917040506 በቴሌግራም በውስጥ መስመር የሚፈልጉትን ያስቀምጡ
👉አድራሻችን አዲስ አበባ አየር ጤና ካራቆሬ ወደመድኀኒአለም 200ሜትር ገባ ይበሉ
ቁጥር 2ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በአሮየው 
አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት ያገኙናል ይምጡ
ይፈወሱ
     https://www.tiktok.com/t/ZMhN2XcBE/

በማንኛውም አገልግሎት ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈፅማሉ
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን መረጃዎች አያይዟል::

♻️የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 /2017 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል። ስለሆነም ምዝገባ ያላጠናቀቃችሁ ከቀነ ገደቡ አስቀድማችሁ እንድታጠናቅቁ ብሏል።

♻️የ2017 የትምህርት ዘመን ፈተናዎች ይዘት የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ሁኔታ ከ9 - 12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7- 8ኛ ክፍሎች የሚሸፍን እንደሚሆን ገልጿል።

♻️ እያንዳንዱ ተማሪ በተማረበት የክፍል ደረጃ የተማረውን የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርጎ ሊዘጋጅ ይገባል። ፈተናዎቹ ተማሪዎቹ የተማሩትን መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ እንደሚሆንም ተመላክቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ!

አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለመ በሞት መለየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ቡልቻ በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ ብለዋል፡፡“እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው፤ ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል ነዳጅ ጭነው ተደብቀው የቆሙ ቦቴዎች መያዛቸውን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ!

አዲስ አበባን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚጓጓዝን ነዳጅ ይዘው በአፋር ክልል ልዩ ቦታው ሰርዶ አድማስ በሚባል ቦታ 'በየጥሻው' የቆሙ ቦቴዎች ተደብቀው በቆሙበት መያዛቸውን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡በአፋር ክልል ንግድ ቢሮ ትብብር የፀጥታ አካል ባደረገው አሰሳ የተያዙት ተሽከርካሪዎቹ የክልሉ ንግድ ቢሮ ለተሸከርካሪዎቹ እጀባ በመስጠት ወደ የመዳረሻቸው እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል ተብሏል፡፡

ባለስልጣኑ ትናንት ባወጣው መግለጫ በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ይሠራል በሚል ያልተጨበጠ ተስፋ ነዳጁን ይዘው የተሸሸጉት እነዚህ ተሸከርካሪዎች ያለአግባባ የሚያገኙትን ትርፍ ከማሰብ ውጪ የጫኑት ነዳጅ በባህሪው በትነት የሚባክን፣ አደጋን የማስከተል አቅም ያለው መሆኑን ለማሰብ አልፈቀዱም ብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈ በየክልል ከተሞች የነዳጅ ማደያዎችን በማድረቅ እጥረት በመፍጠር ህብረተሰቡን የማጉላላት ስራን መስራታቸውን ማመን አይፈልጉም ሲልም ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ተግባሩን በፈጸሙት ላይ መንግስት ለህብረተሰብ ተጠቃሚነት ሲል በድጎማ የከፈለበትን የነዳጅ ወጪ እንዲሸፍኑ የሚደረግ እንደሆነ እና ከምርት መሰውር ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሚደረጉ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በነዳጅ ግብይት ሂደት ውስጥ የሚፈፀሙ ሕገ-ወጥ ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መመጣታቸውን የገለጸው መግለጫው ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች በየቦታው እንዲዘገዩ በማድረግ ተጨማሪ ትርፍ ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ተጠቃሚውን ህብረተሰብ የማጉላላት ተግባር ይፈጽማሉ ሲል ከሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
“ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲዳከም በማድረግ ትግራይን መንግስት አልባ ማድረግ ጥፋት ነው”- ሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረደ

“ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲዳከም በማድረግ ትግራይን መንግስት አልባ ማድረግ ጥፋት ነው” ሲሉ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ አስጠነቀቁ፤ “የግዜያዊ አስተዳደሩን ማጠናከር ለድርድር የሚቀርብ አይደለም” ብለዋል።“ህወሓት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነትን የፈረመ እና 50 አመታት እድሜ ያለው ፖለቲካ ፓርቲ በመሆኑ ቀጣይነት እንዲኖረው እና እንዲጠናከር ማድረግ አስፈላጊ ነው” ሲሉም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሰላምና ጸጥታ ሴክሬተሪያት ሃላፊ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ገልጸዋል።

በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ያለው ውጥረት በፖለቲካዊ መንገድ ብቻ ሊፈታ እንደሚገባ ያሳሰቡት ሌተናል ጀነራል ታደሰ “የተፈጠረው ውጥረት እንዲቆም ከተፈለገ ግን ሁሉም ህብረተሰብ ጫና ማድረግ አለበት ሲሉ አስታውቀዋል።በህወሓት አመራር መካከል ያለው ልዩነት የቅርብ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ዓመታት እየተጠራቀመ የመጣ ነው ሲሉ የጠቆሙት ሌተናል ጀነራል ታደሰ በፓርቲው ውስጥ ያሉ ችግሮች በጊዜው እየተፈቱ ባለመምጣቸው/ተጠራቅመው በመቆየታቸው ነው እዚህ የደረሰው ሲሉ አመላክተዋል።

Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመገንባት ፍላጎት አሳይተዋል ለተባሉ ከ 10 በላይ ባለሃብቶች ፍቃድ ሊሰጣቸዉ ነዉ!

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ እንደገለፀው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ጣቢያ የማልማት ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፀ ሲሆን በዚህ ላይ ለመሰማራት ጥያቄ ያቀረቡ ከ 10 በላይ ባለሃብቶች መኖራቸውን እና በቅርቡ ዉሳኔ እንደሚያገኝ ይጠበቃል ።

የአዲስ አበባት ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ እንደገለፁት በቅርቡ 100 የኤሌክትሪክ አዉቶቢሶች ወደ ከተማዋ እንደሚገቡ የተናገሩ ሲሆን ይህም የትራንስፖርት ዘመናዊነት ከሚታሰበው በላይ ይቀይራል ብለዋል።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ጣቢያ የማልማት ጉዳይ በተመለከተ የ በፌደራል ደረጃ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማ አስተዳደሩ እነዚህን የኃይል መሙያ ጣቢያ የሚተክሉ ባለሀብቶች የመምረጥ እና መሬት የማዘጋጀት ስራ በበላይነት እየተገበረ ይገኛል ።

አቶ ያብባል አዲስ እንደተናገሩት " በዚህ ላይ ለመሰማራት ጥያቄ ያቀረቡ ከ 10 በላይ ባለሀብቶች መኖራቸውን እና በቅርቡ ዉሳኔ አግኝተው በከተማዋ ሰፊ የኤሌትሪክ መኪና የኃይል መሙያ ጣቢያ ይኖራሉ ብለዋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
እ.ኤ.አ. 2025 ከገባ ወዲህ፣ ኖሮቫይረስ፣  ወይንም 'ስቶማክ ፍሉ' በመባል የሚታወቀው፣ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ እየተስፋፋ መሆኑን ሲዲሲ አስታውቋል።

ቫይረሱ እስካሁን ከ21 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለህመም ዳርጓል።

እንደ ሲዲሲ መግለጫ ትውከት እና ተቅማጥ የሚያስከትለው ይህ ተላላፊ ቫይረስ በብዙ ሰዎች ላይ በመከሰት በዚህ አመት ሪከርድ ይዟል።
የኖሮቫረስ ምልክቶች ማስታወክ፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ የሚያስከትል ሲሆን አንዳንዴም ዝቅተኛ ደረጃ ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት፣ ራስ ምታት እና የጡንቻ ህመምን ሊያካትት እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ::  ለቫይረሱ ከተጋለጡ ደግሞ ምልክቶቹ  በሰውነት ላይ ከ 12 እስከ 48 ሰዓታት ሊታዩ ይችላሉ::

መከላከያው እጅን መታጠብ፣ የምግብ ንፅህናን መጠበቅ ፣ የምግብ ማዘጋጃና ሰዎች በጋራ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ አካባቢዎችን በበረኪና ነክ ነገሮች ማፅዳትና በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ራስን ማራቅ መሆኑን ሲዲሲ ይመክራል::

@Yenetube @Fikerassefa
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ የገዥው ሊበራል ፓርቲ መሪነታቸውን መልቀቃቸውን አስታወቁ

አዲስ መሪ እስኪመረጥ ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

Via:- CNN
@Yenetube @FikerAssefa
2025/01/07 04:14:41
Back to Top
HTML Embed Code: