Telegram Web
" ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው " - ቅዱስ ፓትርያርኩ

ቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን " ራስን በራስ የመሾም " አባዜ መገታት አለባቸው ሲሉ አሳሰቡ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ  ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ በተካሄደው ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ስርዓት ላይ ንግግር አሰምተው ነበር።

በንግግራቸው ላይም ፤ " በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው " ብለዋል።

" ማንኛውም ችግር በውይይትና በምክክር የተበደለውንም በትክክል በመካስ መፈታት ይገባዋል! " ያሉት ቅዱስነታቸው " ከዚህ ውጭ በጥፋት ላይ ጥፋት እየተከሠተ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚፈታተን ድርጊት ማቆም አለብን " ሲሉ አሳስበዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ቀኖና ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ባደረገው ጥረት፣ እንደዚሁም ኦርቶዶክሳዊው ሕዝበ ክርስቲያን ባቀረበው አቤቱታ ከዚህ ቀደም የተፈጸመው የቀኖና ጥሰት ታርሞ በዛሬው ዕለት ትክክለኛውን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ቀኖናዊ ሕግን የጠበቀ ሥርዓተ ሢመት መከናወኑን የገለፁት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህ በመሆኑ " ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን " ብለዋል።

" ለወደፊትም ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን አንድነት በሚጠቅም ጉዳይ ሁሉ ፤ በዚህ ዓይነት በውይይትና በምክክር ብቻ እየፈታን ሕዝባችን በመንፈስና በልማት የሚያድግበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በጋራ እንድንሰራ ጥሪያችንን እያቀረብን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።

(የቅዱስ ፓትርያርኩ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)
👍2215🥰1👏1
💕#ሐምሌ_19_እንኳን_አደረሳችሁ💕

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ኢየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት... የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል
፣ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣ ተራዳኢነት ጸሎት አይለየን።

╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ 👆 ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
👍3928👎1🥰1
👍2019🎉2👏1
Forwarded from ተግሳጽ (💝️ዘ ዑራኤል 💝🌱SEED🐾)
"አንተ በሰማይ፣ ወአንተ በምድር፤ ወአንተ በባሕር ዘታስተጋብኦሙ ለኵሉ ፍጥረት እም አጽናፈ ምድር ወአልቦ ተፍጻሜት ለዕበይከ፡፡"
"ፍጥረታትን ሁሉ ከምድር ዳርቻ የምታሰባስባቸው አንተ በሰማይ አለህ፤ በምድርም አለህ፤ በባሕርም አለህ፤ ለልዕልናህ ፍፃሜ የለውም፡፡"
👍1412😁2
"ሰዎች ማን እንደሆኑ ሲያሳዩህ በመጀመሪያው ቀን እመናቸው" ትላለች ማያ አንጀሎ

ይህንን ጽሑፍ ከትናንት በስቲያ ጽፌው ስሜታዊ ሆኜ እንዳይሆን በሚል ትንሽ ቆይቼ ልመልከተው ብዬ አሳደርኩት:: በቆይታ ሃሳቤ ሊቀየር ስላልቻለ እንደወረደ ለጥፌዋለሁ:: የምናገረው ነገርም እሳቸው ስለ ድንግል ማርያም ከተናገሩት አይከፋም:: ነገረ ሃይማኖታዊ መልስ ከበቂ በአደባባይ ተሰጥቶበታል:: ጉዳዩ ላይ ግን የምለውን ልበል::

ፍኖተ ድድቅ የሚባል እባጭ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከወጣ ጀምሮ አንዴ ዘፈን በሚመስል መዝሙሩ ፣ አንዴ ምንፍቅናን በሚያገሣ ስብከቱ ምእመናንን ሲያወዛግብ ሰንበትበት ብሎ ነበር:: ጌታ በወንጌል "ኀበ ሀሎ ገደላ ህየ ይትጋብዑ አንሥርት" "በድን ባለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ" እንዳለው የፍኖተ ድድቅ ባለቤት ሙዳ ሥጋ ይጥላል ብለው ተስፋ ያደረጉ ሰዎች ዙሪያውን ስለከበቡት ላለፉት ጥቂት ዓመታት ቤተ ክርስቲያን ከነንፍጡ ካልወደደችው ብለው ሲሟገቱ ከርመዋል:: በመሠረቱ ሁኔታው ሰውዬው ደኃ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ተወግዞ ነበር እንድል ያደርገኛል:: ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ማኅበር ለማጥራት ጊዜው አሁን ነው::
"ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ…?" የሚል ኢያሱያዊ ጥያቄ ለመጠየቅ ጊዜው አሁን ነው::

ሰሞኑን ደግሞ በፖለቲካ ቤዛነት የተሾሙ የሆኑ አንድ ጳጳስ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ብለው በፍኖተ ድድቅ አዳራሽ ሲያስጨበጭቡ ሰማን:: ከንዑሰ ክርስቲያን ያነሰ እውቀት ያላቸው እኚህ ጳጳስ ሽልማት እንደሚጠባበቅ አዝማሪ ሰውዬውን ያስደስታል ብለው ያሰቡትን ሁሉ ሲዘባርቁ ነበር::

ከቅርብ ዘመናት ወዲህ እንደ ፓስተር ለማውራት የሚጋጋጡ አባቶች ማየት ከጀመርን ሰነበትን:: አይናቸውን አስሬ የሚጨፍኑ ፣ በግድ እየጨመቁ ዕንባ ለማውጣት የሚታገሉ ፣ ከአሁን አሁን በልሳን ለፈለፉ ብለን በስጋት የምናያቸው ምሁር ለመባል የቤተ ክርስቲያንን ነባር እሴቶች የሚያጣጥሉ የቤተ ክርስቲያን ማድያቶች ብቅ ብቅ ካሉ ሰነበቱ::

ያሁኑ ጳጳስ ትንሽ የሚለዩት ምንም ፈሊጥ የሌለው ያልተለሳለሰ $@&@@ ስለሚናገሩ ብቻ ነው:: የሆነ ቪድዮ ላይ Faith Alone የሚለውን የሉተር ትምህርት የኦርቶዶክስ ቆብ ደፍተው ሲሰብኩ ትንሽ እንኩዋን አላፈሩም:: በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተሹመው ተሸልመው ክህደት እያስተማሩ መቀጠል እንደማይቻል ለማሳየትና አንዴ ከጰጰሱ ምንም አይኮንም ዓይነት አመለካከትን ለማረም ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዕድል ሊጠቀም ይገባዋል:: በ3ኛው ክፍለ ዘመን ጳውሎስ ሳምሰጢ (Paul of Samosata) በአንጾኪያ ሲኖዶስ የተወገዘው ፣ ንስጥሮስ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተወገዘው ጳጳስ ከሆኑ በኋላ ነው:: ቤተ ክርስቲያን መና () —ንን ለመለየት ጵጵስናቸውን ፈርታ አታውቅም::

በወላዲተ አምላክ የነገረ ድኅነት ሱታፌ ላይ በጳጳስ ደረጃ ሲቀለድ አይተን ዝም ልንል አንችልም:: ከቅዱስ ሲኖዶስ ጠንከር ያለ ውሳኔ እንጂ ማስተባበያ አንጠብቅም:: የተነቃነቀ ጥርስ ቀን ይጠብቃል እንጂ መውለቁ አይቀርም:: እንደ ተራ ስኅተት ይቅርታ እንዲጠይቁም አንጠብቅም:: ያስተማሩት የታሰበበት ክህደት ነውና የተብራራ መልስ ከቀኖና ጋር እንጠብቃለን:: "የበራላቸው" ለመባል የብርሃን እናትን ሊጋርዱ የሚጥሩ ሰዎች ማላገጫ ሆነንም አንቀርም::

ሙሴ ቤዛ በተባለበት መጽሐፍ ቅዱስ እያመኑ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ላሉት ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤዛ ሲሆናቸው ማየት አንፈልግም:: ጠንከር ያለ ቀኖናዊ እርምጃ እንጠብቃለን::

ርጉመ ይኩን ዘይረግመኪ
ወቡሩከ ይኩን ዘይባርከኪ
ነገራተ ክልዔ ኢይርሳዕ ልብኪ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ገሊላ ፳ኤል
ሚያዝያ 15 2017 ዓ.ም.

╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ 👆 ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
👍195
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶት የነበረው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው መታገዱ ተገለጸ።

ሚያዝያ ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።

╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ 👆 ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
10👏2
Forwarded from ተግሳጽ (💝️ዘ ዑራኤል 💝)
ተወዳጆች

ወደ እግዚአብሔር ስትመጡ
እንደ እግዚአብሔር በዘመናት የሸመገለ
እንደ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ አዲስ የሆነ ማን ነው ?

እሱ አይደክምም
እሱ አይዝልም

እንኳን እግዚአብሔር
የፈጠራቸው ቅዱሳን እንኳን በባህሪያቸው
ድካም እኮ አይስማማቸውም ትጉሃን ናቸው

ያለ ዕረፍት ሺ ጊዜ ሺ ጊዜ ሲያመስግኑት ይኖራሉ።

ለዚያ ነው በመዝ:- 120 ፡4

እነሆ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋም ይላል።

አይታክትም ይላል ቀጥሎ

መክሮ ለመመለስ እግዚአብሔር አይታክትም
አሰተምሮ ለማሳወቅ እግዚአብሔር አይታክትም
ገስፆ ሰዉ ለማድረግ እግዚአብሔር አይታክትም
ለመባረክ እግዚአብሔር አይታክትም
ፀጋን ለማደላደል እግዚአብሔር አይታክትም ወገኖቼ

ሁልጊዜ ቃሉን የሚያሰማችሁ
ወደ ፀጋው መንገድ ሁልጊዜ የሚስባችሁ
እግዚአብሔር ስለ ማይታክት ነው ።

እግዚአብሔር አምላክ ቸርነቱ ምህረቱ አይለየን ።
🙏229👍3
Forwarded from የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ (💝️ዘ ዑራኤል 💝)
ተወዳጆች

ትአምር ይላችኋል የድንግል ማርያም ማህፀን ነው ።

ሁኖ ማያውቅን ነገር ያመነች ብፅእት
ሄዋን የሌላትን እምነት ይዛ በመገኘት
የሄዋን ጠበቃዋ (ቤዛዋ ) ድንግል ማርያም ናት ።

ሔዋን

በለሱን ስትበላ አምላክነትን ተመኘች
የትዕቢት ሁሉ ዋናውን ተመኘች

ትህትና ዘይት ነው የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ መብራት ነው።
ዘይቱ ሲያልቅ መብራቱ ይጠፋል ።

ትህትና

ከሰው ሰውነት ሲጠፋ መንፈስ ቅዱስ ከሰው ይርቃል ።

አዳምና ሔዋን

👉የትህትናቸው ዘይት ሲያልቅባቸዉ
👉የመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ከነሱ ራቀ
👉ራቁታቸውን ሆኑ
👉በለስን ቅጠል በልተው አገለደሙ

ድንግል ማርያምሳ

ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ ሲላት
እንዲህ ያለ ሰላምታ ለኔ ይገባኛል ? ለፍጡር አለችው
ተመልከቱ ትህትናዋን !!!

በሔዋን

በአለቀው ዘይት ውስጥ
ሞት ወደዚህ አለም ገባ

ነገር ግን

ትህትናን በተሞላቸው እውነተኛይቱ የህይወታችን ማሰሮ
በድንግል ማርያም በኩል መንፈስ ቅዱስ መጣ

ዘይቱ ካለ መብራቱ እንደሚኖር
ትህትና ካለበት መንፈስ ቅዱስ ይኖራልና

ይሄ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው ባለች ጊዜ
ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያሰኛት ይሄ ነው ።

የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን🙏
👍1
Forwarded from የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ (💝️ዘ ዑራኤል 💝)
ተወዳጆች

ሙሉ ናት ድንግል ማርያም
ትህትና የጎደለውን የእናቷን ትህትና ይዛ በመገኘት
የ ሔዋን ቤዛዋ ናት ድንግል ማርያም

በእምነት ማጣት ሞት በ ሔዋን ጆሮ ገባ
በድንግል ማርያም እምነት
ህይወት ቃል ወደ እርሷ ማህፀን ገባ

በሔዋን ትህትና ማጣት ሞት ወደ እኛ ገባ
በድንግል ማርያም ትህትና
ህይወታችን ክርስቶስ ከእርሷ እንዲወለድ ሆነ

የትህትናዋ በር ነው አምላክ ልጇ እንደሆን ያደረገው


ትህትና

የቅድስና ሁሉ መሰረት ነውና

በትህትና በመዋደድ በፍቅር እንኖር ዘንድ
ፈጣሪ ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን🙏

የእመቤታችን አማላጅነትን በረከት አይለየን🙏
4👏1
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
👉ሲያስተምር እንባ ከአይኖቹ ይቀድሙታል ተስፋ የቆረጠውን ወጣት ተስፋ ይሰጠዋል በእግዚአብሔር ቃል ተስፋውን ያለመልማል የመምህር እዮብ ይመኑ ቻናል ይቀላቀሉ 👇👇👇

የመምህር እዮብ ይመኑ ትምህርት
የመምህር እዮብ ይመኑ ትምህርት
የመምህር እዮብ ይመኑ ትምህርት
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
🪀🪀የ1000 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር Live ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
2025/07/08 22:11:55
Back to Top
HTML Embed Code: