Telegram Web
Audio
አመስጋኝ እንሁን
ሙላ ናስሩዲን

@Zephilosophy
@Zephilosophy
የዓለም ሰላምን ማረጋገጥ

ኢማኑኤል ካንት  ፤ በ1795 ዓ.ም ባዘጋጀው አነስተኛ በራሪ ወረቀት (Pamphlet) ላይም እንዴት በዓለም ላይ ፍጹማዊ ፍጹማዊ ሰላምን ማስፈን ይቻላል በሚል ደረጃ በደረጃ አስረድቷል፡፡

አገራት ሰላምን ማስፈን ከፈለጉ ሊከተሏቸው የሚገቡ ሶስት መንገዶች ብሎ የጻፋቸውን እንመልከት፡-

1. ሪፐብሊክ መሆን (ህዝባዊ መንግስት መመስረት)-
ካንት ሁሉም የሀገሪቷ ህዝብ በህግ ፊት እኩል መሆን አለባቸው ይለናል፡፡ ህጉም በዜጎች የጋራ ፍቃድ ሊጸድቅ ይገባዋል፡፡ እንዲህ ከሆነ ይለናል ካንት፣ ህዝቦች መንግስታቸው እንዳይዋጋ ያግዱታል፤ ምክንያቱም ወደ ጦርነት ከተገባ ንብረት የሚወድምባቸው እና የሚሰደዱት እነርሱ ናቸውና፡፡ ሃብታሞች እና አምባገነን ባለስልጣናት ብቻ ናቸው ጦርነትን የሚያውጁት፤ በጦርነቱ ከሚያጡትም ይልቅ ትርፋቸው
ይበልጣል፡፡

2. የሪፐብሊኮች ፌዴሬሽን መመስረት  (ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ መንግስታትን በአንድ ማቀናጀት) -
በንግድ ይሁን በሌላም መንገድ በመንግስታት መካከል ግንኙነቶች ሊመሰረቱ ይገባል፡፡ የዚህ ህብረት አካል የሆኑ መንግስታትም ሉአላዊነታቸውን አሳልፈው መስጠት እና በአንድ ንጉስ የመመራት ግዴታ የለባቸውም፤ ይልቁኑ በምክንያት የሚመራ የንግድ ትሥሥርን ይዘረጋሉ፡፡

3. ኮስሞ ፖሊታኒዝምን መቀበል (ሁሉም ሰዎች እኩል ናቸው ብሎ ማመን)
ካንት ሁሉንም ሰው በአንድ መደብ መድቦ እኩል ናቸው አላለም፤ ይልቁኑ ሰዎች በመሃላቸው የጋራ መከባበር ሊኖር ይገባል ይለናል፡፡ ሌላውን ሰው እንደ አውሬ እያየን ወይም ከሰው በታች ዝቅ አድርገን እያንቋሸሽነው ሰላምን ማምጣት አንችልም፡፡

አሁን ላይ የካንትን እሳቤ የሚከተሉ የዓለም አገራት አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል አውሮፓውያን በአውሮፓ ህብረት ስር የጋራ የሆነን የንግድ ትስስር መስርተዋል፡፡ በእነዚህ አገራት መካከልም ጦርነት የመከሰት እድሉ በእጅጉ አናሳ ነው፡፡

@Zephilosophy
"ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። "

የምናደርገው ነገር ትርጉም መስጠት ያቆመበት በሚመስልበት ጊዜ ላይ ነን። እዚህ ሀገር ልጅ እንወልዳለን። የምናወርሰው ሀገር ግን ሲዖል ነው። ምሽቶች ባሎቻቸው ድንገት በወጡበት ይቀራሉ። ይታፈናሉ፥ ይታገታሉ። ልጆች ያልጠገቡትን፥ በውል ያለዩትን አባቶቻቸውን ባልጠበቁት ቅጽበት ይሰናበታሉ። ለሀገራቸው ውለታ የዋሉ ዋርካ ሰዎች በልጅ እግሮች ይገደላሉ። ደም ይፈሳል —በየመንገዱ፥ በየጫካው።  አድባራት አንድ ባንድ ይፈርሳሉ። ማንም ምንም ማምጣት የሚችል አይመስልም። ድንገት ኢምንትነት እንዲሰማህ ትሆናለህ።

ሞት እየጠራህ ትማራለህ? ሞት እያነፈነፈህ ታከማቻለህ? በደጅህ ሞት እያደባ ታገባለህ? ሀገር እየተቃጠለ ትሰርጋለህ? ቆንጆ ቆንጆ ልጆች የጥይት እራት እንዲሆኑ ትወልዳለህ? መሣሪያ የታጠቀ ወንበዴ ቤትህን እየሠረሠረ ታንቀላፋለህ? የዓለም ምጽዓት አንተ ጋር እስከሚደርስ ትተኛለህ?

ሀገሩ የባለጌ ነው። ማን ጌታ እንደሆነ አይታወቅም። በመንገድ ስታልፍ ረግጦህ የገላመጥከው ሰው ዘመደ ብዙ ነው። የጦር መሣሪያ አለው። ባታውቀውም የጎበዝ አለቃ ነው። ትንሽ መንግሥት ነው። ሕይወትህን ከአፈር ይደባልቀዋል። ያየህ እስከማይገኝ ድረስ ድራሽህ ይጠፋል። ወዝህ ያስቀናው ሰው ዳር ሊያስይዝህ ይችላል።

ሀገርህ ከየት እስከየት እንደሆነ አታውቅም። እግርህ ከቤት ወጣ እንዳለ የጠላት ሀገር ነህ። በካርታ ባይከለልም የተበጀ ድምበር አለ። ድንገት  ትጨመደዳለህ፥ እጅ ትሰጣለህ። ብትማረክም ትገደላለህ። ከቀን ውሎህ ተርፈህ፥ በሰላም ወጥተህ ከገባህ እድለኛ ነህ።  ከሄድክበት ስትመለስ ቤትህን በገነባህበት ስፍራ ላታገኘው ትችላለህ። ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። እስከዚያው ያንተ ተራ እስኪደርስ  ታንቀላፋለህ? ወይ የተኛህ ትመስላለህ? ዝም ካልከው በራፍህን አንኳክቶ መምጣቱ አይቀርም
አልነገሩኝም እንዳትል!!

@Zephilosophy
ሌዥዤክ ኮላኮዉስኪ የአለምን ፍፃሜ ሲተነብይ በቲያትር ይመስላታል ። ቅልጥ ያለ ተዉኔት እየታየበት ካለ መድረክ ጀርባ እሳት ይነሳል ። ተዋናዩ ሮጦ መጥቶ ለተመልካቹ እሳት እሳት ሲል ደንገጥ የሚል የለም ። እንደ አንድ የድራማዉ ክፍል እንጂ እንደ እዉነተኛ እሳት ሳያዩት እሳቱ ተዋናዮቹንም ተመልካቾቹንም በልቷቸዉ ያልፋል ።

የእኛ ሀገር አኳኋንም እንደዚህ ነዉ ። ችግር የመጪ ግዜ ብስራትን መጠበቂያ ሀፒ ኢንዲንግ'ን ተስፋ ማድረጊያ መድረካችን ነዉ ። ያለ አዉዱ ሲገባ ሊነጋ ሲል ይጨልማል  እንደሚሉት አባባል በስባሳ ብሂል የለም።

መንግስት ተብሎ የተቀመጠዉም በተስፋ መነሁለልን የሙሉ ግዜ ስራዉ ያደረገ የንቅሎች ስብስብ ነዉ ። እንደ ህዝብም እንደመንግስትም ንቃት ጎድሎን ፥ ከዚያ ማን ማንን ሊታደግ እንደሚችል አላህ ይወቅ

Bicola Nas

@Zephilosophy
ኑሮ አያሻግርም!

እኮ ማነው!
የሰውነት ድልድይ እንዲህ እየፈረሰ፣
የሰውነት መንገድ እንዲህ እየሻከረ፣
መንገዱን በማስዋብ እንዲህ ያሳመረ?
ይልቅ ንገሩልኝ!!
ለእንደኔ ዓይነቱ ሰው፤
በግርግር ደቦ ትልሙ ለፈረሰ፤
የአበባ ዘመኑን በነጠላ መንገድ ሲጓዝ ለጨረሰ፡፡
በቁስ መደራረብ፣
            በዜና ጋጋታ ተስፋ አይሰፈርም፤
“አስፓልት” እግር እንጂ ኑሮ አያሻግርም!

በረከት በላይነህ
የመንፈስ ከፍታ

@Zephilosophy
ሕያውነት
እኚህ ብኩን እጆች፣
እኚህ ጠባብ ሕልሞች፣
በፍርድ ግድግዳ እየተከለሉ፤
ሕያው ታሪኬ ላይ ቆሻሻ ይጥላሉ፤
                         ትቢያ ይከምራሉ፤
                          አሻራ ያጠፋሉ።
ይልቅ ንገሯቸው!
“ቀን ሰርቶ ለሞተ – ለተስፈኛ ጅምር፤
ለስላሳ ወለሉ ነው –የፍርስራሽ ክምር

በረከት በላይነህ
የመንፈስ ከፍታ
አብዮት- ፔን

ተደጋጋሚ እና ለውጥ አልባ በሆነ መንገድ ላይ መጓዝ በራሱ አደገኛ ይሆናል። ለውጥንም ከማምጣት ይልቅ፣ “ሁሌም የምናደርገው በእንደዚህ አይነት መንገድ ነው” ማለት ይቀለናል፡፡ እውነተኛ የአብዮት ሰው ለመሆን ትልቅ ጥረት እና መስዋእትነት ይጠይቃል፤ ራሳችንንም ከማህበረሰቡ ነጥለን በአዲስ እይታ እና መንገድ መጓዝ ይጠበቅብናል፡፡

አሜሪካዊው የፖለቲካ ፈላስፋ የሆነው ቶማስ ፔን፤ “ለረዥም ጊዜ ከማህበረሰቡ ጋር የቆዩ ልማዶች፣ መጥፎ እና ስህተት ቢሆኑ እንኳ ሳንመረምር ልክ እንደሆኑ እንቀበላቸዋለን” ይለናል፡፡ ምን ያህል ኢ-ፍትሃዊነቶችን፣ በደሎችን ... መጥፎ ቢሆኑም እንኳ ልማድ ስለሆኑ ብቻ አሜን ብለን ተቀብለናል?

ለፔን ሰዎች ሰው በመሆናቸው ብቻ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚያገኟቸው መብቶች አሏቸው፡፡ ለምሳሌ በሕይወት የመኖር፣ የነጻነት፣ የመናገር እና የፈለጉትን የማመን መብት አላቸው፡፡
በተጨማሪም እንደየሁኔታው ህግ (መንግስት) የሚሰጠን አልያም የሚነሳን መብቶች አሉን፡፡

ሆኖም ባለስልጣናት ባህል በሚል ካባ የማህበረሰቡን መብቶች መጣስ ቀላል ይሆንላቸዋል። ባህል ወግ ውስጥ ሲደበቁ፣ ልማዶች የማህበረሰቡን አይኖች ይጋርዱታል፤ አምጾም አምባገነን መንግስቱን እንዳይጥል ይሆናል፡፡ እኛ ከመወለዳችን በፊት አያቶቻችን ሲመሩባቸው የነበሩ ወግ እና ልማዶች ዛሬ ላይ ሊያስሩን አይገባም። እያንዳንዱ ትውልድ እንደ ራሱ ነጻ ሁኖ መንቀሳቀስ አለበት... ባህል የአምባገነኖች መጫወቻ ያደርገናል።' አዎ... ከአያቶቻችን የምንወርሰው ጥበብ ይኖራል፤ ሆኖም ግን በእነርሱ ህጎች ዛሬ ላይ መመራት የለብንም፡፡

ፔን መንግስታትን አይወዳቸውም ነበር፤ እንደውም ከስር መሰረታቸው መጥፎ ናቸው ይለናል፡፡

መንግስታት አለቃ እና መሪም
ከመሆን ይልቅ የህዝቡ ባሪያ እና አገልጋይ መሆን አለባቸው፡፡ ይህ  ሃሳብ ነው ፔንን ህዝቦች መንግስታቸው ፍትሃዊ እና መልካም ካልሆነ መገልበጥ አለባቸው ወደሚል ድምዳሜ ያደረሰው፡፡

ኢየሱስ በአይሁድ አለቆች ላይ አመጸ፤ ማርከስ አዲስ የሆነ አብዮታዊ ስርዓት ቀረጸ፤ ጋንዲ እና ማንዴላ በእንግሊዞች ላይ አመጹ... የሁሉም ጥያቄ የነበረው እና ሁሉም ሲሰብኩ የነበረው፣ የሰውን ልጅ ክቡርነት ነው፡፡ ሰው ሰብዓዊ መብቶቹ ሊጠበቁለት የተገባ ነው፡፡
እናም ምንም ያህል ባህል እና ስርዓታችንን የምናከብር ቢሆንም እንኳ የሰውን ክብር የሚነካ ከሆነ ማመጽ ይኖርብናል። ይህን ካላደረግን አምባገነኖች በባህል እና በብሄር ስም ይጨቁኑናል።

አመጽ እና አብዮት ለማስነሳት የሚያስችል ወኔ በውስጣችን አለን? ፔን እንደጻፈው “ዓለምን አፍርሶ እንደ አዲስ መገንባት የሚያስችል ኃይል አለን”

ልማዶች በራሳቸው መጥፎ አይደሉም፤ ሆኖም መጠቃትን እና መጨቆንን በጸጋ እንድንቀበል ምክንያት ይሆኑናል።

አዘጋጅ-ፍሉይ አለም

@Zephilosophy
@Zephilosophy
ስብዕናን የሚያንፁ የስነ ልቦና ምክሮች ለማግኘት ከፈላጋችሁ ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/+Rn0O-d8bj50OUCcP
ማንነት

ልጅ ሳለህ የተነሳኸውን ፎቶ ተመልክተኸው ታውቃላህ ? ምን ትዝ ይልሀል? ምንስ ታስታውሳለህ?  ትንሹ አካልህ በግዙፍ አካል ተቀይሯል። የምታስባቸው ነገሮች ፣የምትመርጣቸው ነገሮች ልጅ ከነበርክበት ጊዜ በእጅጉ ተቀይሯል።ሰለዚህ ማንነትህ ተቀይሯል ማለት እንችላለን ? በእርግጥ ስለባለፈው ማንነትህ ትውስታ ይኖርሀል። ትውሰታህን በሙሉ አትጠተህ  ማንነትህ በሌላ ማንነት ቢቀየርስ አንተ አለህ ማለት እንችላለን?

የፍልሰፍና ማዕድ መፅሀፍ ውስጥ ይሄን ፁሁፍ አገኘሁ
"ፊሊፕ ዲክ የተባለ ደራሲ በጻፈው We can remember it for you wholesale በተሰኘ የአጭር ልቦለድ ታሪክ ውስጥ አርኖልድ ኮነን የተባለ ገጸ ባህሪ እናገኛለን፡፡ ኮነን አንድ ቀን ደስ የማይል ነገርን አገኘ፡፡ ኮነን በጭራሽ አርኖልድ ኮነን አይደለም፡፡ ወይም በሌላ አነጋገር የቀድሞ ማንነቱ ሌላ ነበር። ግራ ተጋባ።

ታሪኩን ሲመረምርም  ስለቀድሞ ማንነቱ ያውቃል። ሲወለድ የተሰጠው ስም አለን ውድ ነበር፡፡ ውድ መልካም ሰው አይደለም። ራስ ወዳድ፣ ጨካኝ እና ምህረት አልባ ነበር፡፡ ከሁለት አመት በፊትም  ከወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር ጥልቅ የሆነ ችግር ውስጥ ገባ። እሱም ሁለት አማራጭ አቀረቡለት፤ ጭንቅላቱ ውስጥ ያሉት መረጃዎች በሙሉ ተደምስሰው በሌላ እና ልቦለዳዊ በሆነ የውሸት ሰው እንዲተኩ አልያም ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግበት እና ስቃይ ባለው እስር ቤት ውስጥ እድሜውን ሙሉ እንዲያሳልፍ፡፡

ትውስታዎቹ እንዲደመሰሱለት መረጠ፡፡ እናም አለን ውድ ጥልቅ የሆነ መደንዘዝ ውስጥ እንዲገባ ተደርጎ ትውስታዎቹ በአዳዲስ እና በውሸት ትውስታዎች ተተኩለት፡፡ ሲነቃም እስከዛሬ የነበሩትን የሕይወት ትውስታዎች ሁሉ ዘንግቷል፡፡ እሱም የሚያውቀው ኮነንን እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

አሁን ላይ ኮነን፣ በቀድሞ ሕይወቱ አለን ውድ'ን እንደነበር አውቋል፡፡ እናም ይህ ሰው ማን ነው? ውድ ወይስ ኮነን?
የኮነን/ውድ የማንነት ቀውስን ለመፍታት ቀላል የሚመስል ችግር ቢሆንም፤ መልሱ ግን እንደምናስበው ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎች የኮነን እውነተኛ ማንነቱ የቀድሞ ማንነቱ እንደሆነ ይደመድማሉ። የአብዛኞቻችን ማንነት ከአዕምሮ እና ከሰውነት እድገታችን ጋር የተቆራኘ ነውና እንዲህም ማሰባችን ተገቢነት ይኖረዋል። እስከ ዛሬ ሁለት አመት ድረስም ይሄ ሰው ወንጀለኛው አለን ውድ ነበር፤ አሁን አለን ውድ የለም የምንል ከሆነ፣ አስክሬኑ የታል፣ የታልስ የሞተው? ማንም የሞተ ሰው የለም፤ እና አለን ውድ የት ሄደ? ይሄ ሰውስ ማን ነው?

አርኖልድ ኮነን (በውሸት የተፈጠረው ማንነት) የአዕምሮ ጤና ሃኪም ነው፡፡ ስለ ልጅነቱም ሆነ ስለ ጉርምስናው የሚያስታውሰው አንዳችም ነገር እውነት አይደለም፡፡ ውድ የእውነት እንደሆነ ሁሉ ኮነን የውሸት ነው፡፡ አሁንስ ላይ ኮነን የውሸት ነው ብለን መደምደም እንችላለን?
ለምሳሌ ኮነን፣ ወንጀለኛው ውድን መሆን ይፈልጋል? ከመልካም ሰውነትስ ጭራቅ የሆነውን ውድ'ን መምረጥ ይፈልጋልን?"

መምረጥ ቢችል የትኛውን ማንነት መምረጥ ይኖርበታል ውድን ወይስ ኮነን?

@zephilosophy
"ከመከራችሁ የሚበዛው ራሳችሁ የመረጣችሁት ነው።"
ደራሲ- ካህሊል ጂብራን

አንዲትም ሴት ተናገረች እንዲህም አለችው። " ስለ ስቃይ ንገርን?"
እሱም አለ ፦

"ስቃያችሁ የማስተዋላችሁ ማቀፊያ ሽፋን (ቅርፊት) መሰበር ነው...
"በፍራፍሬዎች ውስጥ ያለው እንደ ድንጋይ የጠጠረ ፍሬ ልቡ ተከፍቶ በፀሀይ ውስጥ ይቆም ዘንድ የግድ መሰበር እንዳለበት ሁሉ እናንተም ስቃይን ማወቅ ይገባችኋል...

"ልባችሁንስ በህይወታችሁ የእለት ተዕለት ተዐምራት ውስጥ በአስደሳች ሁኔታ ልታቆዩት ይቻለችኋልን? ስቃያችሁስ ከደስታችሁ ያነሰ አስደናቂ ይመስላችኋልን?

"በእርሻ ማሳዎቻችሁ ላይ የሚፈራረቁትን ወቅቶች ሁልጊዜ በፀጋ እንደምትቀበሉዋቸው ሁሉ የልቦቻችሁን ወቅቶችም  ወቅቶች በፀጋ መቀበል ይኖርባችኋል። የሀዘናችሁን የክረምት ወራትም በፀጥታ ትጠብቃላችሁ...

"ከመከራችሁ የሚበዛው ራሳችሁ የመረጣችሁት ነው። በውስጣችሁ ያለው ሀኪምም የራሳችሁን ህመም የሚፈውስበት መድሀኒት አለው። ስለዚህ ሃኪሙን እመኑት እና መራራ መድሃኒቱንም በፀጥታ ተረጋግታችሁ ተጎንጩት...

@zephilosophy
ቡድናዊነት በድናዊነት?
ብርሀን ደርበው

የምንከተለው ፋሽን፣ የሚያስቁን ቀልዶች የምንወዳቸው ሙዚቃዎች ወዘተ ወዘተ... እውን የወደድነው የምንወደውን ነው? የምናደርገው ሁሉ በራሳችን ውሳኔ እና ፍላጎት የተደረገ ወይስ ቀልብያችን የሚለን ሌላ ሆኖ አንዳች ኃይል አስገድዶን?

አንዳንዴ እራሴን እንዲህ ብዬ ጠይቃለሁ የምትከተለው ፋሽን የሚያስቁህ ቀልዶች የምትወዳቸው ሙዚቃዎች ወዘተ ወዘተ... ያንተ ምርጫ ወይስ አንዳች ኃይል አስገድዶህ ምትመርጠው? እውን የወደድከው ሁሉ የምትወደውን ነው? የምታደርጋቸው ውሳኔዎች ባንተ ፍላጎት በቀልብያህ ፍቃድ ወይስ ሌሎች ስለወደዱት ላለመነጠል በዓለም ውስጥ
መናኒ ላለመሆን?

Solomon Asch የተባለ ሳይኮሎጂስት Confirmity Line Experiment የምትባል የሰውን ልጅ ውሳኔ አሰጣጥ የምትገመግም አንዲት የምትገርም ጥናት አለችው። እነሆ ጥናቱ A,B,C ሲል የሰየማቸውን ሦስት የተለያየ ቁመት ያላቸው መስመሮች አዘጋጀ።

ተሳታፊዎች በተዘጋጀላቸው ክፍል ውስጥ ሁሉም በየተራ የትኛው መስመር ረዥም እንደሆነ ጮክ ብለው ይናገራሉ። ታድያ ይሄ ሁሉ ሲሆን ክፍሉ ውስጥ በየዙሩ ከሚገኙት ተሳታፊዎች ከአንዱ ወይ ከሁለቱ በቀር ሁሉም ተዋናያን(ሆን ብለው ስህተት የሆነውን እንዲመርጡ) ይሆኑና በመጨረሻ የተቀረው መልሱን እንዲመልስ ይደረጋል።

ታድያ ውጤቱም ከቅጥረኛ ተዋናያን ጋር ከነበሩት ውስጥ በአማካይ 75% ተሳታፊዎች ቢያንስ አንዴ ስህተት የሆነ መልስ ሰጥተዋል። በአንጻሩ ያላንዳች ተጽእኖ ለብቻቸውን (control group) የመለሱ ተሳታፊዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ትክክለኛውን መልስ መልሰዋል።

በጥቅሉ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው እውነታው ግልጽ እና እርግጥ ሆኖ ሳለ ከሌሎች ላለመነጠል ሲል እያወቀው አልያም ብዙ ሰው ካለውማ ልክ ነው (ሞት ከአገር ጋር እንቅልፍ ነው እንዲሉ አበው) በማለት ካለው እውነት የብዙኃኑን ስህተት ይቀላቀላል።

ግላዊነት በሚንቆለጳጰስበት በዚህ በዘመነ ሉላዊነት ምንበላውን ምግብ ፣የት መብላት እንዳለብን፣ ምንለብሰውን ልብስ፣ ማንን መጥላት፣ ማንን መደገፍ እንዳለብን ሁሉ ባንድም ይሁን በሌላ መንገድ የሚወስንልን ማህበራዊ ሚድያው ሆኗል። ፍቅራችን አድናቆታችን ጥላቻችን የኛ አይደለም። ከየትኛውም ጊዜ በላቀ የመንጋነት ስነልቡና በዓለም ላይ ተንሰራፍቷል። ሌሎችን ቀድሞ መከተል ሌሎችን እንደመምራት የሚቆጠርበት ዘመን ላይ ነን።

ቡድናዊ አስተሳሰብ የተለየ ሃሳብ ማመንጨትን ፣ በተለየ መንገድ ነገሮችን ተረድቶ የተለየ
መፍትሔ መስጠትን ፣ አዲስ እይታን፣ ልዩ ምልከታን በጥቅሉ በራስ መቆምን የሚገድል
ከቡድን ውጭ ያለን ሁሉ በድን የሚል ምልከታ ነው።

Hannah Arendt የተባለች ፖለቲካል ፊሎሶፊስት Adolf Eichman ስለሚባል የናዚ መኮነን የፍርድ ሂደት ላይ በጻፈችው Eichman in Jerusalem በተባለ መጽሐፏ እንዲህ ትለናለች ‘’The sad truth is that most evil is done by people who had never made up their minds to be good or evil. ‘’

የሚያሳዝነው ብዙ ክፋቶችና ጥፋቶች የተሠሩት ክፉና ደጉን ለይተው ክፋትን በሚፈጽሙ ክፉ ሰዎች እና አረመኔዎች ሳይሆን ኢየሱስ “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው።” እንዳለው የሚያደርጉትን ሁሉ አስበውበት ሳይሆን አሳስበዋቸው በፈጸሙ ፤ ስማ በለው በሚመራቸው ጆሯቸው የአእምሮዋቸውን ቦታ በተካባቸው ብኩኖች ነው።

ከሶቅራጥስ ግድያ እስከ ክርስቶስ ስቅላት፣ከጆርዳኖ ቡሩኖ ቃጠሎ እስከ ስልሣዎቹ መረሸን፤ ከናዚ የዘር ፍጅት እስከ አገራችን ፍጅት በፍራቻ በጥላቻ ና በስጋት
ቡድኖች በባህል በፖለቲካ እና በሃይማኖት ስም የመንጋ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ታላቅ ጥፋት
አድርሰዋል እያደረሱም ነው።

ብዙኃንን መከተል ለምን?

የሰው ልጅ ተፈጥሮ(Human natures need to belong) Aristotile(አርስጣጣሊስ) Man is by nature a social animal ሰው በተፈጥሮው ማህበራዊ እንስሣ ነው ይለናል።

በሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ውስጥ ለአደን ለመሄድም ሆነ ከአራዊት ጥቃት እራስን ለማዳን የሰው ልጅ ሕይወቱን ለማስቀጠል የሄደበት መንገድ በቡድን መሆንን ነው። ታድያ በስነ ተረክ እና በባህል ተጠቅሞ ኃይልን ለማንበር ፣ ሰላምን ለማስፈን እና ነውጥን ለመግራት የሚያደርገው ትግል በ DNAያችን እና በ ንቃት ህሊናችን ውስጥ ስለሚታተም ከመንጋው መነጠል ወደ ሞት መጓዝ ነው ብሎ እንዲያስብ እና እንዲደምድም ያደርዋል።

ታድያ እርግጠኛ ባለመሆን ፤ተቀባይነትን ለማግኘት፤ መጣልን/መገለልን ፍራቻ በጥቅሉ ክብርን ለማግዘፍና ህላዌን ለማስቀጠል ሲል ብዙኃኑን ይከተላል።
የማህበራዊ ሚዲያን መስፋፋት ተከትሎ የዲጂታል መንጋነትም ለመቆጣጠር በማያስችል ሁኔታ እየተስፋፋ ነው። ጭብጨባችን እንኳ የራሳችን አይደለም። የገደል ማሚቶዎች ሆነናል ፤ በቀቀናዊ ማንነትን ተላብሰናል። ነገሩን ተረዱትም አልተረዱትም ሃሳብን በሃሳብ ከመሞገት ይልቅ በስድብ፣በዛቻ እና በማስፈራራት የሚመልሱ ከልቡናቸው/በጣታቸው በኩልም ይሁን በአፋቸው/ ከጸያፍ ነገር በቀር የሌለ የሚመስል ባለማእረግ ተራጋሚዎችን እያፈራን ነው።

ዲጂታል መንጋዎች ተከታዮቻቸው እንዲነኩባቸው አስተያየት እንዲሰጥባቸው አንዳች ትችት እንዲደርስባቸው አይፈልጉም። የሚከተሉትን ሰዎች ከፈጣሪያችው እኩል አንዳንዴም በላይ እንከን የለሽ አድርገው ስለሳሏቸው እነሱን ለነካባቸው እንጦሮንጦስ ድረስ ወርደው በቀል የመሰላቸውን ነገር ለማድረግ ሁሌም ዝግጁ ናቸው።

ኒቼ Beyond Good and Evil መጽሐፉ ላይ እንዲህ ይላል “Insanity in individuals is something rare - but in groups, parties, nations and epochs, it is the rule.” ቡድኖች እብደታቸውን ሕግ ያደርጉታል።

በማህበር ሲታበድ፤ በጎራ ሲወፈፍ፣ በወል ሲነሆለል፤ ስሜት ይነግሣል ምክንያት ቦታ ያጣል። መቃወም ያስወግራል ፣ መለየት ያስቀጣል ፣መሞገት ያሠድዳል፣ መመርመር ያስቀስፋል ። ከኛ ወዲያ ክንደብርቱ ከኛ ወድያ ኃያል ርቱዕ ከኛ ወድያ ጎራሽ... ፣ ከኛ ወዲያ ላሳር ከኛ ወድያ... ። የሁሉ ነገር መለኪያ ፣ የሁሉ ነገር መተኪያ፣ እና ሁሉ ነገር በራሱ እኛ ነን የሚል የተደፈነ አስተሳሰብን ያጸናል።

እኛ ደሞ(የመተርጎም ነጻነቱን ላንባቢው ትተን) መኖርን የሚያክል ጥናት የለምና ኖረን ካየነው እንዲህ እንላለን Even a pacifist in a mob could become a warmonger.
ቡድናዊነት/የመንጋ እሳቤ በግለሰቦች ውስጥ ያለን እውነት፣ ለውጥ ፣ሂደትና ፈጠራ ወደ በድንነት በመለወጥ በራስ መቆምን የሚያሽመደምድ ነው። መንጋነት ሲነግሥ ሰውነት ይረክሳል፣ ፍትሕ ትንጋደዳለች፣ ስልጣኔ አፈር ይበላዋል።የወል እሳቤ ማጤን መመርመርን በጥቅሉ ሰው መሆንን የሚገድል ነቀርሳ ነው።

በጅምላ ማሰብ፤ የሰው ልጅ የመጀመርያው ሞቱ ነው። ቆም ብለህ አስብ።ከእሳቱ ከልለው ከጨለማው የዶሉህን ትተህ የራስህን ሻማ ለኩሰህ ብርሃንህን አብራ።ሰው ሆነህ ሳለህ እራስህን ስለምን ታሳንሳለህ? ራስህን ችለህ አስብ! በራስህ ተጠራ! ሰው ሁን!

ብዙኃን በመንጋ ፣በቡድን፣ በጎራ ሲያስቡና ሲወስኑ ብቻቸውን መቆም የቻሉ ምንኛ የታደሉ ናቸው። የሰውነት ምልአት የመሻገር ከፍታ እነርሱ ጋር ናትና።

ቸር ያቆየን!

Credit to ባይራ ዲጂታል መፅሄት

@Bayradigital
@Zephilosophy
"ብዙሀኑን የሚያታልል ጌታቸው ይሆናል ፤ ከዓይናቸው ላይ ቅዠትን ለማጥራት የሚሞክረው መቀጣጫ ይሆናል!።"
ኒቼ
 @zephilosophy
ሐይማኖት- ፍቅር
--
“I belong to no religion. My religion is Love. Every heart is my temple.” ~ Rumi

የእውነትን መንገድ ሊያሳዩን በመሃከላችን በስጋ የተመላለሱ ምርጦች እልፍ ናቸው… ሁሉም ለሁሉ የሚሆን ቅን መልዕክት ትተውልናል… ‘ለእነ እከሌ ብለን መጣን’ ባይሉም “ለእኛ መጡ” ብለን ግን ከፋፍለናቸዋል… ጭራሽ በስማቸው አጥር አበጅተናል - ሐይማኖት!!… እናም ዛሬ ቡድሃ፣ ኢየሱስ፣ መሐመድ፣ ኮንፊሺየስ፣ ክሪሽናና ሌሎች ምርጦች ከአጥሩ ውጭ ላሉ ሰዎች እንዳይደርሱ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል… የሁሉም መልዕክት አንድና ተመሳሳይ ቢሆንም ተከታይ ነን ባዮቹ ውሎ እያደር በፈጠሩት ግንብ ምክንያት መተያየት አልተቻለም… ቢያንስ ከአጥሩ ጫፍ ሰይፍና ጦር እንጂ የፍቅር ቃል አይወረወርም…
እኒያ ምርጦች ግን ምን ነበር ያሉት?...
ኢየሱስ – In everything, do to others as you would have them do to you; for this is the law and the prophets. (Jesus – Matthew 7:12)
ነቢዩ መሐመድ – Not one of you truly believers until you wish for others what you wish for yourself. (The Prophet Mohamed, Hadith)
ቡድሐ - Treat not others in ways that you yourself would find hurtful. (Udana – Varga 5:18)
ሌላውንም እንዲሁ ዘርዝሩ… ይሁዲዎች እንደሚሉት “What is hateful to you, do not do to your neighbor. This is the whole Torah.” - “በአንተ ሊደረግ የማትፈልገውን ነገር በሌላው አታድርግ” ከሚል የፍቅር ቃል ውጭ ምንም አታገኙም… ቢገኝም “… “All the rest is commentary!!!” - (Hillel, Talmud, and Shabbat 31a)
***

@Bridgethoughts
@Zephilosophy
«አብዛኛው የሰው ልጅ የሚከተላቸው እምነቶችና በእምነቱ ውስጥ የሚፈፅማቸው ድርጊቶች መነሻቸው  ልማድ ነው። እምነት በዕውቀት መገለጥን ካልያዘ የሚጠይቀውም ሆነ ምላሽ የሚያገኝለት ጥያቄ ስለማይኖር ሌሎች ስለሚያደርጉት ብቻ የሚደረግ ከንቱ ተግባር ሆኖ ይቀራል።»
ዜኖች

@zephilosophy
ሃልወተ እግዚአብሔር & The problem of evil

አምላክ እንደ ሆንክ አስብ፡፡ አለማትን ሁሉ ፈጠርክ። እናም ፈጥረህ ስትጨርስ የእጅህን አቧራ አራግፈህ ገሸሽ አልክ፤ ሁሉንም ፍትህን ለመመልከት በሚያስችልህም ሰባተኛ ሰማይ ላይ መኖሪያህን አዘጋጀህ። የፈጠርከው ዓለም ውብ ነው፤ እልፍ አእላፍ ከዋክብቶችንም በውስጡ ይዟል፤ ከፈጠርካቸው አለማትም በአንዷ ላይ፣ ላባ እና መንቁር አልባ የሆነ በሁለት እግር የሚጓዝ ፍጡር አለባት... ነገር ሁሉ መልካም እንደሆነም አየህ፡፡

ጎንህን ለማሳረፍም ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገባህ። ሆኖም በመሃል የፈጠርካቸው ፍጡራን በጫጫታቸው ቀሰቀሱህ። አስታወስክ እነዚያ በሁለት እግር ሂያጅ ፍጡራን... እርስ በእርስ እየተገዳደሉ ነው፤ ከፊሎቹም ምግብ እያሉ ወዳንተ ያለቅሳሉ፤ ሌሎች በህመም ይሰቃያሉ...

አሁን ላይ አንተ ምን ታደርግላቸዋለህ? ማንስ ነው ለዚህ ሁሉ መከራ ተጠያቂ የሚሆነው?

ይህ ጥያቄ “problem of evil” ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓለም ሁሉ ስለምን መጥፎ ነገሮች ኖሩ?
ስኮትላንዳዊው ፈላስፋ ዴቪድ ሂዩም
  በአምላኩ ላይ ጥያቄን ያነሳል ፦

አምላክ ሁሉን ቻይ (omnipotent)፣
ሁሉን አዋቂ (omniscient) እና
ፍጹም መልካም(omnibenevolent) ነውን?

ስለምንስ መከራችንን ሳያይ ቀረ፣ ይህ ሁሉ ስቃይስ በእኛ ላይ ሲሆን እርሱ የት ነበር? ሲል ይጠይቃል።

ፍጹም መልካም፣ ሁሉን ወዳጅ የሆነ አምላክ እንዴት አይሁዶች በእሳት እንዲጠበሱ ፈቀደ? ስለምን ህጻናት በርሃብ እንዲሞቱ ሆኑ? ደካማው ሚዳቋ ስለምን ለበረታው አንበሳ ምግብ እንዲሆን ተፈረደበት?

ምናልባት ሁሉን ቻይ ሳይሆን ቀርቶ ይሆን? መርዳት እየፈለገ ሆኖም አቅሙ ስለሌለው ነው እጁን ያልዘረጋው?

ምናልባትም አላወቀም ይሆናል? ሁሉን አዋቂ ካልሆነ ልንፈርድበት አይገባም፡፡
ሆኖም ግን ይህን አምላክ ፍጹም መልካም፣ ሁሉን ቻይ እና ፍጹም አዋቂ ነው ብለን ማለት አንችልም፡፡
በተመሳሳይ ጊዜ ሶስቱንም መሆን አይችልም፡፡ ከሶስቱ ባህርያቱ ቢያንስ አንዱን ልንቀማው ይገባል፡፡

በመከራችን አልረዳንምና ለመከራችን ተጠያቂውም እርሱ ይሆናል። የሚጠብቀን አንቀላፍቶ ይሆን?

ሁለት አይነት ክፋቶች በዓለም ላይ አሉ - ምድራዊ እና ተፈጥሯዊ (ለምሳሌ፤ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ድርቅ፣ ወረርሽኝ እና ወዘተ) እና ሰዋዊ  (መገዳደል፣ ውሸት፣ መስረቅ እና ወዘተ)
ሁለቱም ክፋቶች ጥያቄን ያስነሳሉ፡፡

የመጀመሪያው ማን ነው ዓለምን ከነችግሮቿ የፈጠራት የሚል ጥያቄን ያስነሳል። ሁለተኛው ሰዎች ክፋት እንዲያደርጉ የፈቀደላቸው ማን ነው? የሚል ጥያቄን ያስነሳል፡፡

ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት አስቸጋሪ የሚያደርገው በኃይማኖተኞች ዘንድ የተሳለው አምላክ ሃያል መሆኑ ነው። አምላክ የፈለገውን እንደፈለገው ቢፈጽም የሚጠይቀው አካል መኖር የለበትም ምክንያቱም እርሱ ሃያል ነው።

በኃይማኖተኞች ዘንድ ለ “problem of evil” የተሰጡ ምላሾች አሉ። ምላሾቹም ቲዮዲሲ ተብለው ይጠራሉ።
ሶስት አይነት መልሶችንም ያቀርቡልናል፡፡

⭐️የመጀመሪያው የሰው ልጅ ክፋትን እንዲሰራ ነጻ ፍቃድ አለው የሚል ይሆናል። ሰው እሳት እና ፍትፍት ከፊቱ ቀርቦለታል፤ መልካሙን ወይም መጥፎውን የመምረጥ ድርሻውም የእርሱ ነው ይሉናል፡፡

⭐️ሁለተኛው፤ እኛ ማን ነን ይህ ክፉ ነው፣ ይህ ደግሞ መጥፎ ነው ብለን የምንሰይመው? ለምሳሌ እሳተ ገሞራ በተፈጥሮው መጥፎ ይመስላል፤ የብዙ አራዊቶችንም ሕይወት ሊቀጥፍ ይችላል፤ ሆኖም እሳተ ገሞራ በመኖሩ ምክንያት ነው ተራራዎች የተፈጠሩት ተራሮችም ለደኖች፣ ወንዞች እና ሌሎችም መፈጠር ምክንያት ናቸው፡፡ እናም መልካም እና መጥፎ የሆነውን የሚለይልን አምላካችን እንጂ እኛ አይደለንም፡፡

⭐️ሶስተኛው ሁሉም ነገር የፈጣሪ እቅድ አካል ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ህጻን በርሃብ ሲሞት ምናልባትም ወደ ዘላለማዊ ማር እና ወተት ወደሚፈስባት ዓለም እየተጓዘ ይሆናል። የእርሱንም እቅድ መጨረሻ አናውቅምና ይህ መልካም ነው፣ ይህ መጥፎ ነው ማለት አንችልም፡ በሕይወትህ መጥፎ አጋጣሚዎች ተከስተውብህ የሆኑት ለበጎ ነው እንኳንም ሆኑ ብለህ አታውቅም? ምናልባትም ይህም የእርሱ
እቅድ አካል ይሆናል፡፡

ምንጭ -ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ-ሶቅራጠስ
ፁሁፍ -ፍሉይ አለም

በኃይማኖተኞች ዘንድ ለ “problem of evil” የተሰጡ ምላሾች በቂ ናቸው ብላችሁ ታስባለችሁ ?ከነዚህ ውጪስ ሌሎች ምላሾች የሉም ይሁን?
ግሩፕ ላይ ተወያዩበት
👇👇👇
https://www.tgoop.com/+XgPfefgVVvRhZjk0
የሜታፊዚክስ ፍልስፍና ሙግቶች

የሰው ልጅ ለዘመናት መልስ አልባ እንቆቅልሾችን ለመመለስ ሞክሯል። ገደብ አልባ ስለሆነው ሁለንተና ገደብ ባለው አእምሮ አሰላስሏል። ከጥያቄዎቹም አንዱ የሆነው ማን ፈጠረን? የሚለው ነው፡፡ ይህ ሁሉ ዓለም ከምን ጀምሮ እዚህ ደረሰ? በተለያየ ዘመን ከተለያየ ቦታ የተነሱ የስድስት ፈላስፎች ሙግት እናያለን
ሶስቱ የአምለክን መኖር በአመክንዮ አስረግጠው ሲያስረዱ
ሶስቱ ደግሞ የሰው ልጅ ስነ ልቦናዊ ወይም ፓለቲካዊ በሆነ ምክንያት አምላኩን ፈጠረ ብለው ይሞግታሉ እስቲ አንድ በአንድ እንያቸው።

1.Cosmological argument - አል ኬንዲ

ሁሉም ነገር በሆነ ጊዜ ላይ የሆነ ቦታ ይጀምራል፡፡ ሁሉም ነገሮችም ለመከሰታቸው መንስኤ የሆነ አካል አላቸው፡፡ የምትንከባለል ኳስን በማየት ብቻ መጀመሪያውኑ ከቆመችበት እንድትንቀሳቀስ ያደረጋት እና የጠለዛት ሰው እንዳለ ማወቅ እንችላለን፡፡
ይህ ቀላል የሆነ ለነገሮች ያለን እይታ፣ የእግዚአብሔርን ሃለዎት ወይም የፈጣሪ መኖርን ለማስረዳት ከሚቀርቡ ሃሳቦች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ የሙግቱ ስያሜም Cosmological argument ይሰኛል፡፡ የሙግቱ መነሻ ጥንታዊቷ ግሪክ ብትሆንም፣ የአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ኢስላማዊ ፈላስፋ የሆነው አል ኬንዲ በቀላል ቋንቋ አስቀምጦልናል፡፡ አመክንዮው ቀላል ነው።
A.ነገር ሁሉ ለመከሰት የግድ መነሻ አለው
B.ሁለተንተና ተከስቷል

2.ሰው በአምሳሉ አምላኩን ፈጠረ-ፎየር ባክ

ሰዎች ይታመማሉ፣ ይፈራሉ፣ ይወድቃሉ፣ ይሞታሉ... እናም ከዚህ ሁሉ መከራ የሚያስጥላቸውን መሸሸጊያ ፈጠሩ፡፡ የዓለምን ስቃይ በራሳቸው አቅም ማምለጥ አይችሉምና ከስቃይ የሚያተርፋቸውን ፍጹማዊ አምላክ በአምሳላቸው ሰሩ፡፡ ይህንን አምላክ ልክ እንደ ራሳቸው አካል ይቆጥሩታል፤ ልክ እጃቸው እንደሆነ ሁሉ ያጎርሰናል ብለው ያስባሉ፤ ልክ እግራቸው እንደሆነ ሁሉ ያሻግረናል ይላሉ።
_
“በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል” እንዳለው  መዝሙረኛው ዳዊት፣ አምላክ የሰዎችን ጉድለት ሊሞላ ተፈጠረ  ይለናል ፎየርባክ፡፡

3.የህዝቦች ማደንዘዣ- ማርክስ

ማርክስ ኃይማኖት በገዢዎች (ቡርዥዋ) የተፈጠረ እና ሰራተኛው በእነርሱ ላይ እንዳያምጽ ማድረጊያ መሳሪያ ነው ይለናል፡፡

ኃይማኖት ይህን የሚያደርገው በሁለት አይነት መንገዶች ነው። አንደኛው ለምስኪን፣ ደሃዎች ወይም መልካም ለሆኑ ሰዎች እንደ ሽልማት ዘላለማዊ ገነትን በማቅረብ ሲሆን፣ በአንጻሩ ከህግ ወጥተው ለሚያምጹ እና መጥፎ ለሚያደርጉ ደግሞ ዘላለማዊ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ሁለተኛው ፤ኃይማኖት እንደ እጽ ማደንዘዣ ነው ይለናል ማርክስ ፤ ልክ እንደ ኦፒየም አብዛኛውን የማህበረሰብ ክፍል ያደነዝዘዋል። በችግር ውስጥ እንኳ ቢሆን ደስተኛ እንደሆነ ያስባል፤ ህመሙም አይሰማውም... ደንዝዟልና፡፡ ከልባቸው መዝሙርን ይዘምራሉ፣ በደስታ ውስጥ ሆነው ይጸልያሉ... ይህም ጥያቄ ማንሻ ጊዜ እንዳይኖራቸው ያደርጋል፡፡ የዓለምን ኢ-ፍትሃዊነትንም የአምላካቸው እቅድ አካል አድርገው በደስታ ይቀበሉታል፡፡ ዓለም ምን ብትከፋቸው፣ ፍርዱን ለፈጣሪ ይተዋሉ እንጂ በገዢዎች ላይ አያምጹም፡፡

@zephilosophy
የሜታፊዚክስ ፍልስፍና ሙግቶች
.....የቀጠለ
4.esse est percibi -በርክሌይ

በርክሌ esse est percipi የሚል ፍልስፍናዊ ሀረግ አለው ሃረጉ የተፈጠረው ከላቲን ቃላት ሲሆን፣ ትርጓሜውም “መሆን ማለት ማስተዋል" ነው፡፡ ወንበር በውኑ ዓለም ላይ ያለ ነገር ለመሆን የግድ የሚያስተውለው አካል ያስፈልገዋል፡፡ የሚዳስሰው አልያም የሚመለከተው ሰው ከሌለ ወንበሩ በእውኑ አለም አለ ማለት አንችልም፡፡ በጫካ ውስጥ የወደቀው ዛፍ ሰሚ ከሌለው ድምጽ አያሰማም፣ ጓደኛህም አንተ ካላየኸው ወይም ካልነካኸው በውኑ ዓለም አለ ማለት  አንችልም።

የእውኑ ዓለምም የሚፈልቀው ከአንተ አእምሮ በመነሳት ነው፡፡ ህንጻዎችን  ስትመለከት፣ የአበባ መዓዛን ስትምግ፣ ትኩስ ቡና ምላስህን ሲያቃጥለው እነዚህ ሁሉ በአእምሮህ ያሉ የእውኑ ዓለም መገለጫዎች ናቸው፡፡ የእውኑ ዓለምም የሚያየው (የሚያስተውለው) አካል ሳይኖር ሲቀር መኖሩ ያበቃለታል፡፡

ሆኖም ግን ሰው (ወይም ሌላ አስተዋይ) በማይደርስበት በረሃ ላይም እኮ ዛፎች፣ ተራሮች፣ ድንጋዮች አሉ ይህ ስለምን ሆነ? ለምንስ እነርሱም አልተሰወሩም፡፡
የባርክሌ ምላሽ ቀላል እና አጭር ነው፤

“እግዚአብሔር አለ!” ተመልካች በሌለበት ሁሉ፣ በአጽናፈ አለሙ በሙሉ እግዚአብሔር ተመልካች ነው፡፡  ለዛም ነው የተከልናት አበባ ወደ ቤታችን እስክንመለስ ድረስ ሳትሰወር የምትጠብቀን፤ ለዚህም ነው በጥቅጥቅ ደን መሃል የወደቀ ዛፍ ድምጽ የሚያሰማው፡፡

5.ቅዱሱ አባትችን -ፍሮይድ

እድሜያችን ምንም ያህል ቢሆን እንኳን በውስጣችን ልጅነት አለ፡፡ ሁሌም ቢሆን እንፈራለን፤ ሁሌም ቢሆን ከችግር የሚያወጣን አልያም እጃችንን ይዞ ጨለማውን የሚያሻግረን አባት እንፈልጋለን፡፡ ህግ አልባ በመሰለችን ዓለም ላይ ነጋችን ምን እንደሚሆን አናውቅምና “አይዞህ አትፍራ እኔ አለሁ” የሚለን አባት ከጎናችን እንዲኖር እንፈልጋለን፡፡

በአለማችን ላይ ስሙ የገነነው  ኦስትሪያዊው ኒሮሎጂስት ሲግመንድ ፍሮይድ- ይህ ነው ሰዎች የማይታይ፣ የማይጨበጥ አባት እንዲፈጥሩ ያስገደዳቸው ይለናል፡፡ ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን አድራጊ፣ ደስ ባለን ጊዜ የምንጨቀጭቀው ልክ እንደ አባታችን የሆነ አምላክ - እግዚአብሔር።
ፍሮይድ ሁላችንም በህጻንነታችን ደካማ እና እርዳታ ፈላጊ ነበርን ይለናል፡፡ እርዳታም ባስፈለገን ቁጥር ወደ ወላጅ አባታችን እንሄዳለን፤ ሆኖም እያደግን ስንመጣ አባታችን እንደኛ ከፍጹምነት የጎደለ ፍጡር እንደሆነ እና ሁሉንም ፍላጎቶቻችንን ሊያሟላልን እንደማይችል
እንረዳለን፡፡ ነገር ግን ሁሌም ቢሆን ከአደጋ የሚጠብቀን አካል እንዲኖር እንፈልጋለን፡፡

የሰው ልጅ ተፈጥሮ ሲከፋበት፤ ልክ አባቱን እርዳኝ እንደሚለው ሁሉ ፈጣሪውን ይማጸናል፡፡ ልክ በመኪና መንገድ ላይ እጃችንን ይዞ መንገድ እንደሚያሻግረን ወላጅ አባታችን ሁሉ፣ ይህ ፈጣሪ በጨለማ ጊዜያቶቻችን ላይ እጃችንን ይዞ ያሻግረናል፤ ፈጣሪ ለመልካምነታችንም ከረሜላ (ገነትን) ይሸልመናል፤ ስናጠፋም በቀበቶው ይገርፈናል (ወደ ሲኦል ይዶለናል)

ኃይማኖት ከጥንት ጀምሮ የሰዎችን ምኞት ሲያሳካ ቆይቷል። ደካማነታችን ከምንም፣ ከማንም በላይ ሃያል የሆነ አባትን እንድንፈጥር አደረገን፡፡' ኃይማኖት ለሰው ልጆች የሞት ፍርሃትን አስወገደላቸው፤ ነገውን ለማያውቅ ሰውም ሁሉ ነገሩን በአምላኩ ላይ እንዲጥል አስቻለው፤ መልካም በማድረጉም ይሸለማልና መልካምነትን ወደደ፤ ቢያጠፋም  በዘላለም እሳት ይቃጠላልና ከእኩይነት ሸሸ፡፡ ለራሱም፤ ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል... በታላቁ አባትህ እጅ ነህና! "አለው::

6.Abductive reasoning
ፔሊ

በአስራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ዊልያም ፔሊ የሚባል አንድ ቄስ የእግዚአብሔርን መኖር ወይም ሃልወተ እግዚአብሔርን ሊያረጋግጥልን የሚችል ሙግት አነሳ፡፡ ሙግቱም teleological argument ይሰኛል። በእርሱ ሙግትም በጫካ ውስጥ ሲጓዝ ሰዓት ወድቆ ያገኘ ሰው በእርግጠኛነት ሰዓቱ ሰሪ እንዳለው ያውቃል። ሰዓቱም እንዲሁ በዘፈቀደ ንፋስ በሰበሰባቸው ብረቶች አልተሰራም፡፡ እናስ ለዚህ ተራ ሰዓት እንኳ ፈጣሪ ካለው፣ እንዴት ውስብስብ ተደርጎ የተሰራን ሁለንተና (ዩኒቨርስ) ፈጣሪ የለውም እንላለን?

የስው ልጅ ልብ ሳያቋርጥ በደቂቃ ደም እየመጠነ ይረጫል፤ ሳንባው ለሰከንድ እንኳ ሳያቋርጥ አየር ያስገባል አየር ያስወጣል፤ አይኖቹ በዓለም ላይ ካሉ ካሜራዎች ሁሉ በብዙ እጥፍ ምስልን ይቀርጻሉ እናስ ይህ ከእጅ ሰዓት በላይ የተወሳሰበን ፍጡር የአጋጣሚ ሂደት ፈጠረውን?

ከሰው ጀምረን እስከ ሁለንተና ድረስ ተፈጥሮን እየተነተንናት ብንጓዝ ልክ ገዢ እንዳላት ሁሉ፣ በህግ እና በስርዓት ስትመራ እንመለከታታለን፡፡ ተፈጥሮ ከቅንጣት ጀምሮ እስከ ግዙፍ ከዋክብት ድረስ ያሉ ውስብስብ ሰርዓቶችን ይዛለች።

እናም የፔሊ ጥያቄም ይህ ነው - ሰዓትን ለመፍጠር ሰዓት ሰሪ ካስፈለገ፣ ስለምን ተፈጥሮስ ንድፍ አውጪ የላትም?

ይህ የቴሎሎጂካል ሙግት abductive reasoning ወይም ጠላፊ የምክንያት ሂደት ይባላል፡፡ ይህም የነገሩን መጨረሻ በማየት ብቻ መጀመሪያውን ለመገመት ያስችለናል፡፡ ለምሳሌ በግማሽ ነዶ ያለቀ ሲጋራ በመንገድ ላይ ቢያጋጥመን፣ ሲጋራውን ሲያጨሰው የነበረ ሰው እንዳለ መገመት እንችላለን፡፡

በተመሳሳይ ሂደትም የቴሎሎጂካል ሙግትም- የምናየውን የተወሳሰበ ዓለም የፈጠረ እና ዓለም ሁሉ በህገ ተፈጥሮ እንዲመራ ያደረገ አካል አለ፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው ይለናል።

@zephilosophy
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ስግብግብና ራስ ወዳድ በመሆኑ ቆፍጠን ያለ መሪ ያስፈልገዋል

ምንጭ ፦ ፍልስፍናና ዘላለማዊ ጥያቄዎቹ
ፀሀፊ፦ ቤተልሔም ለገሰ

ፍልስፍና ከሚያነሳቸው አበይት ጉዳዮች አንዱ ፖለቲካ ነው፡፡ ፖለቲካን ስናነሳ ደግሞ አስቀድመን ከምንጠይቃቸው ጥያቄዎች መካከል ‹‹አንድ ሀገር ብሎም መንግስት እንዴት ተመሰረተ? መንግስት ከመኖሩ በፊት ሰዎች እንዴት ይኖሩ ነበር? አኗኗራቸውስ ፍትሀዊ ነበርን? የመንግስት መቋቋም ለማህበረሰቡ ምን ፋይዳ አስው? የሚሉና የመሳሰሉት ይገኙበታሉ፡፡ እኛም የአንደ ሀገር መገለጫ ከሆኑት ውስጥ ዋነኛ ሚና ስለሚጫወተው መንግስት (goverment) የዚህንም ተቋም ምንነትና ስለ አጀማመሩ የተሰነዘሩ ፍልስፍናዊ መከራከሪያ ሀሳቦችን እያየን እንዘልቃለን ...

አንዲት ሀገር በመንግስት እንድትተዳደር መነሻ ሀሳብ የሆነው የማህበራዊ ውል ስምምነት ቀመር (social contract theory) ሲሆን ይህም ውል 'መንግስት ከመፈጠሩ በፊት ሰዎች ይኖሩበት የነበረው የተፈጥሮ ስርዓት አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ ሰላምና መረጋጋትን ማረጋገጥ ስለማይቻል የበላይ አካል መፈጠር አለበት› ከሚል ሀሳብ የመነጨ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ ታዲያ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ ፍልስፍናዊ መከራከሪያ ሀሳቦች ሲያቀርቡ ከነበሩት መካከል ዋነኞቹ ቶማስ ሆብስ (Thomas Hobbes) ጆን ሎክ (john locke) እና ሩሶ (Rousseau) ይገኙበታል። እስኪ የነዚህን ፈላስፎች ሀሳብ በዝርዝር እንመልከት. ..

ቶማስ ሆብስ እ.አ.አ ከ1599-1679 ይኖር የነበረ እንግሊዛዊ ፈላስፋ ሲሆን በእርሱ ዘመን ተከስቶ የነበረው የእንግሊዝ እርስ በርስ ጦርነት በስራዎቹ ላይ ተጽእኖ እንዳሳደረ ይታመናል፡፡ እናም ይህ ጦርነት የቱን ያህል ስጋት ላይ እንደጣለው ለመግለጽ በአንድ ወቅት ‹‹እኔና ፍርሀት መንታ ሆነን ተፈጠርን›› ( I and fear were born twins) ሲል ተናግሯል፡፡

ሆብስ የማህበራዊ ውል ስምምነት ቀመር እንዲፈጠር አስተዋጽኦ ያደረገው 'የሰው ተፈጥሮዊ ባህሪይ' እንደሆነ ይናገራል፡፡ እንደሱ አባባል ‹‹አብዛኛው ሰው የሚመራው ነገሮችን እያሰበና እያገናዘበ ሳይሆን ይልቁንም በስሜትና በራስ ወዳድነት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎችን በፍርሀትና በጦርነት ስጋት ውስጥ እንዲዘፈቁ ያደርጋል፡፡ ስለዚህም ሰዎች አንድ ወጥ የሆነ የማህበራዊ ውል ስምምነት ኖሯቸው ጠንካራ መንግስት ካላቋቋሙ በስተቀር የአበዛኛው ሰው ቅጥ የለሽ ስግብግብ ባህሪይና ዝና ወዳድነት የለት ተዕለት ኑሮውን በአስተማማኝ ሁኔታ መምራት እንዳይችልና ህይወቱም ፍጹም አስቀያሚና ጭካኔ የተሞላ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡››

‹‹መንግስት›› የሚባለው ተቋም የመኖሩ አስፈላጊነትና ፋይዳ ይህ ከሆነ ዘንድ፣ የዚህ መንግስት የሚባል ተቋም ስልጣኑ አስከምን ድረስ ነው? ለሚለው ጥያቄ ሆብስ፤ ሰዎች ለሚመሰርቱት መንግስታዊ ተቋም ተፈጥሮአዊ መብቶቻቸውን ሙሉ በሙሱ አሳልፈው መስጠት እንደሚገባቸውና ይህ የመረጡት አካል ከሁሉም በላይ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ማዘዝ እንደሚገባው ብሎም ስልጣኑ ገደብ የለሽ መሆን እንዳለበት ያስረዳል፡፡ በዚህም እ.አ.አ በ1651 ለህትመት ያበቃውና በባህር እንስሳት ገዢ የተሰየመው 'ዘ ሴቪያታን› የተሰኘው መጽሀፍ ሆብስ ስሰው ልጅ ያለውን ጨለምተኛ አስተሳሰብ ያሳበቀበትና በብዙ ፖለቲካ ተንታኞች ዘንድም ፍጹማዊ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ስርዓት አቀንቃኝ' ተብሎ እንዲታማም አድርጎታል፡፡

በአንጻሩ እ.አ.አ ከ1632-1704 የኖረውና ለዘመናዊ የፖለቲካ ስርዓት መፈጠር ፈር ቀዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት አንግሊዛዊ ፈላስፋ ጆን ሎክ እንደ ሆብስ ለሰው ልጅ ያለው አመለካከት ጨለምተኛ ሳይሆን የሰው ልጅ በተፈጥሮው ደግና ሩህሩህ እንዲሁም በጎና ቅን አሳቢ እንደሆነ ያምናል፡ ፡ እንደሱም አባባል ሰዎች መንግስት ባልነበረበትና በተፈጥሮ ስርዓተ ህግ ስር በሚተዳደሩበት ወቅት በነጻነትና በራሳቸው ፍላጎት የመመራት መብት ስለ ነበራቸው የሌላውን ሰው ህይወትም ሆነ ንብረት አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት ፈጽሞ አያደርጉም፡፡ ‹‹ነገር ግን . . ›› ይላል ሎክ ‹‹ . ነገር ግን ማንም አብዛኛው ሰው ነገሮችን በማመዛዘን የሚኖር ፍጡር ቢሆንም አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ሁኔታዎች ሰውን ወደ ጸብ አጫሪነት ሊያመሩት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም የሰው ልጅ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላሙን ለማረጋገጥ እንዲያስችለው ተፈጥሮ የቸረችውን ነጻነቱን በመስጠት ማህበራዊ ውል ስምምነት እንዲፈጽም ማህበራዊ ተቋም (social institution) እንዲመሰርቱ ይመክራል፡፡

ሎክ ሀሳቡን ሲቀጥልም ‹‹በማህበራዊ ውል ስምምነት የሚመሰረተው ማህበራዊ ተቋም (መንግስት) ውስን የሆነ ስልጣን አንዳለውና ይህም ተቋም በህግ የበላይነት ስር የሚተዳደር እንደሆነ በዜጎች መሰረታዊ መብቶች ውስጥም ጣልቃ መግባት እንደሌለበት ... የዜጎችን መብት የሚሸራርፍ ድርጊቶችን ቢፈጽም ህዝቡ የሰጠውን ስልጣን የመገፈፍ መብት እንዳለው ይናገራል፡፡ ታዲያ የዚህ ታላቅ ስልጣን ባለቤት ሊሆን የሚችለው በህዝቡ ይሁንታ የተመረጡ ሰዎች የሚያቋቁሙት የህገ አዉጪ አካል ሲሆን ተጠሪነቱም በቀጥታ ለህዝቡ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥቶ ይናገራል፡፡

ይቀጥላል

@zephilosophy
@zephilosophy
... ካለፈው የቀጠለ

የጆን ሎክ የማህበራዊ ውል ስምምነት ቀመር ንድፈ ሀሳብ በዘመናችን ውስጥ የዳበረ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን እያራመዱ ለሚገኙት እንደ አሜሪካና ምእራብ አውሮፓ ላሉ ሀገራት ፈር ቀዳጅ ሆኖ የሚጠቀስ ፍልስፍና እንደሆነና የዘመናዊ ሊበራል ዲሞክራሲ ርዕዮተ ዓለም ጠንሳሽ እንደሆነም ተንታኞች ይናገራሉ፡፡

እንደ ታዋቂ የፖለቲካ ተንታኝ ሀሮልድ ላስኪ (Harold Laski) አገላለጽ ‹‹የጆን ሎክ ንድፈ ሀሳብ በእንግሊዝ የፖለቲካ ታሪክ ሙስጥ ቋሚ አሻራ ትቶ ያለፈ በዚህ ላይ ደግሞ በአሜሪካ ፓለቲካ ስርዓት ጠንሳሾች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ከማሳደሩም በላይ የአሜሪካ ህገ መንግስት የተወሰኑ አንቀጾች ቃል በቃል ከእርሱ ስራዎች የተገለበጡ ናቸው›› በማለት ይናገራል፡፡

ቀጥለን የምናየው ከ1712-1778 ድረስ የኖረውን ፈረንሳዊ ፈሳስፋ ጂን ጃኩስ ሩሶ (Jean Jacques Rousseau) ን ሲሆን ይህም ፈስስፋ ከቶማስ ሆብስና ጆን ሎክ ቀጥሎ ከመንግስት ስርዓት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ፍልስፍናዊ የመከራከሪያ ሀሳቦች ከፍተኛ ተጽእኖ ያሳደረ እንደነበርም ይነገርለታል፡፡ ታዲያ ይህ ፈላስፋ በስራዎቹ ታሪክ የማይረሳቸውን የ1789ኙን የፈረንሳይ አብዮት በማነሳሳትና የህዝባዊ ሉአላዊነት ንድፈ ሀሳብ (the theory of popular soveneity ) በማመንጨት ጉልህ ሚና የተጫወተ ሰው ነው፡፡

ጂን ጃኩየስ ሩሶ እንደ ሎክ 'የሰው ልጅ በተፈጥርው ቅንና ሩህሩህ መሆኑን› ቢያምንም ነገር ግን እነዚህ መልካም ባህሪያት በግል ሀብት መፈጠርና በህዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት ሰውን ራስ ወዳድ እንዲሆንና በሌሎች ዘንድም ገዝፎ ለመታየት አንዲጥር ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ አላስፈላጊ ወደ ሆነ የርስ በርስ ፉክክር ውስጥ ተገብቶ ሰላም እንዲደፈርስና መሰረቱም አንዲናጋ ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ እናም የማህበረሰቡን ሰላምና መረጋጋት ለማስከበር ሰዎች በስምምነት ማህበራዊ ውል ስምምነት ቀመር ኖሯቸው አንድ የፖለቲካ ተቋም መመስረት
እንደሚገባቸው ይገልጻል፡፡

የሩሶ የማህበራዊ ውል ስምምነት ንድፈ ሀሳብ ከቶማስ ሆብስ ጋር ተመሳሳይ የሚያደርገው ሰዎች ለሚያቋቁሙት የበላይ አካል ነጻነታቸውን አሳልፈው መስጠት እንደሚገባቸው ማመኑ ሲሆን በአንጻሩ ‹‹ከፍተኛ ስልጣን የሚይዘው ህብረተሰቡ ነው›› የሚለው ሀሳቡ ከጆን ሎክ ጋር ቁርኝት እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡ .

አንዳንዶች የሩሶ የበላይ ተቋም (higher institution) አወቃቀርና አደረጃጀት ወጥነት የጎደለውና ብዥታን የሚፈጥር (para- doxical) ነው ሲሱ ይተቹታል፡፡ ስአብነት ያህል እስቲ the general will የሚለውን ሀሳብ ለመረዳት እንሞክር፡፡

እንደ ሩሶ እምነት በማንኛውም ህብረተሰብ ዘንድ ሁለት ፍላጎቶች ይንጸባረቃሉ፡፡ ከነዚህም አንደኛው በህብረተሰቡ ያለ ልዩነት በጋራ የሚስማሙባቸውና የሚፈቅዱአቸው ፍላጎቶች (the will of all ) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከጋራ ፍላጎቶች ጋር የማይስማሙ የእያንዳንዱ ሰው ግላዊ ፈቃድ ድምር (the general will) የሚባለው ነው፡፡ ታዲያ የአንድ ህብረተሰብ የጋራ ደህንነት (common good) ሊረጋገጥ የሚችለው የእያንዳንዱን ልዩነት በማጥበብ ለጋራ አላማ የሚል ስራ በመስራትና ለውጥ ለማምጣት በመታገል መሆን እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡ ይህም የሚሆነው የሚመሰረተው ተቋም በግለሰቦች ልዩነት ድምር ላይ የተገነባ ስራ ሲሰራ ይሆናል፡፡

የሩሶ የማህበራዊ ውል ስምምነት ቀመር ሁለት አበይት አደረጃጀት ሲኖረው አንደኛው ሰዎች ነጻነታቸውን ሙሉ ለሙሉ አሳልፈው በመስጠት የሚያቋቁሙት ማህበራዊ ተቋም (community based institution) ሲሆን ሁለተኛ ለዚህ ማህበራዊ ተቋም ተጠሪ ሆኖ የሚያገለግለው አካል መንግስት (government) ይሆናል፡፡ በነዚህ አደረጃጀቶች ውስጥ የህዝብ ስልጣን ከፍተኛና ፍጹም ስለሆነ በማንኛውም መልኩ ሊነጣጠስ ሊከፋፈል፣ ሊገረሰስ እንዲሁም ሊወድቅ አይችልም፡፡

የሩሶ የማህበረሰብ ስልጣን ልክ እንደ ሆብስ ምሉዕ በመሆኑ ለግለሰብ ቅሬታዎችና ፍላጎቶች ቦታ የማይሰጥ ነው፡፡ ምክንያቱም እንደ ሩሶ ግንዛቤ ይህ አካል ህብረተሰቡ በጋራ የተስማማበትና የመምራት ነፃነቱንም ሙሉ ለሙሉ የሰው አካል በመሆኑ የሁሉንም ሰው ፍላጎት የማንጸባረቅ ውስጣዊ (በውስጠ ታዋቂነት) ስምምነት እንዳለው ስለሚቆጠር ነው፡፡ የዚህ ማህበረሰባዊ ስልጣን ከፍተኛው አካል ህግ አውጪ (legislative body) ሲሆን እያንዳንዱ የመንግስት ተግባራትና ክንውኖች በህግ የተገደቡ በመሆናቸው ለህዝቡ ሰላምና መረጋጋት በመፍጠር በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ... ይላል ሩሶ

ታዲያ የጆን ሎክ ፖለቲካዊ ፍልስፍና በአሜሪካ ህገ መንግስት (American Constitution) ተጨባጭ መነሻ እንደሆነ ሁሉ የሩሶም ማህበራዊ ዉል ስምምነት ቀመር ደግሞ ለፈረንሳይ ህገ መንግስት መሰረት ከመሆኑም ከላይ ከሩሶ ፍልስፍናዊ እሳቤዎች በቀጥታ የተወሰዱ አንቀጾችም ይገኙበታል፡፡

እኛም መንግስታችን የቱ ይሁን? ብለን እንጠይቅ....

ምላሹን በልባችን እናሳድር!!

@zephilosophy
@zephilosophy
"መሪ አስመሳይና አታላይ መሆን አለበት"
ማኪያቬሊ

ወደ ላይ መውጣት ከፈለግክ የግድ የበታቾችህን መጨፍለቅ ይኖርብሃልን? ስኬት የሚመጣው ሰዎችን በማታለል እና በክፋት ውስጥ ብቻ ነውን? ስለምንድን ነው በአብዛኛው ዘርፍ ላይ ከላይ የሚሆኑ ባለ ስልጣናት ወይም ፖለቲከኞች የእብደት ጠባይ ያላቸው?

የዲፕሎማቱ እና ፈላስፋው ማኪያቬሊ መጽሐፍ የሆነው The Prince ለዚህ መልስ አለው፡፡ ይህ አጭር መጽሐፍ እንዴት አንድ መሪ የራሱን የስልጣን ዘመን ማራዘም እንደሚችል ያሳያል።ምርጥ መሪ ማለት መልካም መሪ የሚል ቀጥተኛ ትርጓሜ የለውም፡፡ ምርጥ መሪ በምንም አይነት መንገድ ስልጣኑን የሚያስጠብቅ መሪ ነው ይለናል። ይህ መሪ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ያጭበረብራል፣ ይሰርቃል፣ ህዝቡን ያታልላል።

በመፅሀፍ ውስጥ እነዚህ ሀሳቦች ይንፀባረቃሉ።

1.መሪ ሥነ - ምግባርን አሽቀንጥሮ መጣል
አለበት፡፡

ህዝቡ በከፋበት ዘመን ከመሪ መልካምነት ሊጠበቅ አይገባም ይላል ማኪያቬሊ ።መሪው በባህሪው መጥፎነት ኖሮበት ሣይሆን መጥፎ ህዝብ መጥፎ መሪን ስለሚያመጣ ነው፡፡ ህዝቡ ሥነ ምግባር የጉደለውና ሥርዓት የሚያውቅ ከሆነ በዚህ ሁኔታ አንድ መሪ የራሱን ደህንነት መጠበቅ ግዴታ ውስጥ ይገባል፡፡ ለዚህ ያለው ብቸኛ አማራጭ ኃይልን በመጠቀም ጨካኝነቱን ማሳየት ነው፡፡ ህዝቡ ገልበጥባጣ በመሆኑ መሪ ህዝቡን ማመን የለበትም፤ ህዝቡን ከማመን ይልቅ የራሱን ማንነት እንደሁኔታው እየቀያየረ መኖር ያስፈልገዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ማካቬሌ ፖለቲካን ከሥነ - ምግባር የሚነጥል ፍልስፍናን አቀረበ፡፡

2.መሪ የሐይማኖተኛና የቅድስና ህይወት ሊኖር አይገባም፡፡

ማኪያቬሊ ሲናገር ሐይማኖትን ህዝብ ይከተለው እንጅ መሪ ሊከተለውና ሊኖርበት አይገባም፡፡ መሪ ሐይማኖተኛ ከሆነ ትሑት ይሆናል፤ ትህትና ደግሞ ደካማ ያደርጋል፡፡ መሪ ደካማ ከሆነ በዙሪያው ያሉት ጠላቶቹ ሰለባ ይሆናል::

3. መሪ ለስልጣኑ ሕጋዊነት መጨነቅ የለበትም፡፡

ለማኪያቪሊ ህጋዊ መንግስት የሚያስፈልገው መረጋጋት ባለበት ሀገር ውስጥ ነው፡፡ መረጋጋት ከሌለ ህግም ቢኖር ተግባራዊ አይሆንም፤ ህግ አልባነትንም በህግ መመለስ አይቻልም፡፡ ህግ በጠፋበት ዘመን ህጋዊ ሥርዓት መፍጠር የሚቻለው ጸጥ - ለጥ አድርጐ በጉልበት መግዛት ሲቻል ነው፡፡ “መልካም ህግ ያለመልካም ክንድ ሊኖር ስለማይችል ከህግ ይልቅ የበረታች ክንድን እመርጣለሁ” ይላል ማኪያቬሊ፡፡

"Since there can not be good laws with out good arms, I will not consider laws but speak of arms.”

መጥፎ ህዝብ የመንግስት ቅጣት ስለሚፈራ ሣይወድ በግድ ሥርዓት ይይዛል፤ ስለዚህ መሪ ለመወደድ ከመጣር ይልቅ ለመፈራት ቢጥር የተሻለ ነው፡፡መሪ ይላል ማኪያቬሊ የመንግስትን ሥልጣን ለመያዝ ህጋዊ መንገድ ከመጠበቅ ይልቅ በራሱ ኃይል መተማመን ይገባዋል፡፡
ማኪያቬሊ በዚህ አመለካከቱ የመንግስት ሥልጣንና ህጋዊ ሥርዓት የተሳሰሩበትን ገመድ በጥሶ ጣለው፡፡

4.መሪ አስመሳይና አታላይ መሆን አለበት

ያልተረጋጋን የፖለቲካ ሁኔታ ማለፍ የሚችሉት ተንኮለኛ ሰዎች ናቸው ብሎ ማኪያቬሊ ያምናል፡፡ ተንኮለኛነቱ ለደህንነቱ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ተንኮለኛነቱ የሚገለፀው ደግሞ ህዝቡን ለማሳሳት አስመሳይ ሁኖ ስለሚቀርብ ነው፡፡ መሪ ጥሩ ሰው ሳይሆን ነገር ግን ጥሩ ሰው መስሎ ህዝቡን መቅረብ አለበት፡፡ በዚህ ጊዜ አስመሳይነቱን ህዝቡ እንዳያውቅበት መጠንቀቅ አለበት፤ ለህዝቡ ሐቀኛ መስሎ ነው መታየት ያለበት፡፡ የህዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ደግ መስሎ መታየት፤ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለሰባዊነት የቆመ መስሎ መታየት አለበት፡፡ ነገር ግን በተግባር ከእነዚህ እሴቶች በተቃራኒ ሁኖ መኖር አለበት፡፡ ተቀናቃኞቹንና ደጋፊ መስለው በዙሪያው እየኖሩ ደባ የሚሠሩበትን ምቹ ሁኔታ ባገኘ ቁጥር ያለምንም ርህራሄ ማጥፋት አለበት፡፡ መሪ እንደ ተኩላ የራሱን እኩይነት በማይነቃ መልኩ ሸፍኖ መያዝ አለበት፡፡ ሊያጠቃቸው የሚፈልጋቸውንም የዋህ፣ ደካማና በእነርሱ ላይ ክፋት የማያስብ መስሎ በመታየት ሊያዘናጋቸውና ባላሰቡት ጊዜ ሊያጠቃቸው ይገባል ይለናል፡፡

___
መሪዎቻችን ይህን የማኪያቬሊን ፍልስፍና አብዝተው የሚጠቀሙት ይመስላል የሚያዋጣቸው ይመስላችኋልን?
ተወያዩቡት💬

@zephilosophy
2025/02/25 02:46:04
Back to Top
HTML Embed Code: