ፌደራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ከግንቦት 10 እስከ 12/2017 ዓ.ም በሱሉልታ ከተማ በሚገኘው የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ባካሄደው አገር አቀፍ የተማሪዎች የስነ-ምግባር አምባሳደርነት ውድድር ዩኒቨርሲቲያችንን ወክለው የተወዳደሩት የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ክበብ አባላት ባደረጉት ብርቱ ውድድር ሁሉም ተወዳዳሪ ተማሪዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀትና የመፅሃፍ ሽልማት የተሰጣቸው ሲሆን ዩኒቨርሲቲውም ባደረገው ንቁ ተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል ፡፡ በመሆኑም በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው ውድድር ላይ እንድንሳተፍ በማንኛውም መንገድ እገዛ እና ድጋፍ ላደረጋችሁልን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የስነ-ምግባር መከታተያ ስራ አስፈፃሚ
የስነ-ምግባር መከታተያ ስራ አስፈፃሚ
👍11🎉1