Telegram Web
#ውሰዱን_ቶሎ_አደራ

     ቀን ከሌት ልቤ በፍቅር ሲነድ ይከርማል። ዙልሂጃ ሲመጣ ደግሞ የበለጠ ብሶቱና ናፍቆቱ ይገናል። ከአቅሜ በላይ ይንገበግበኛል። ሻንጣው ከተሰናዳ ሶስት አመታት አለፈው ጠያራው ግን ብቅም አላለም። ከአላህ ተስፋ አይቆረጥምና ከነገ ዛሬ በተስፋ አለን። በአብሬቶች ሀረም አያቴ ወድቆ እንደተንሰቀሰቀ አባቴም ከግቢዎት እንዳነባ እኔም በተራዬ መዲና እንዲወስዱኝ መማፀኔን ታውቃላችሁ። ታድያ ዛሬ የነዚህ ሶስት ትውልዶች ዱኣ በኔ መሳካት የለበት ትላላችሁ? ዱኣቸው ሁሉ መካና መዲና ሳይጠራበት ቀርቶ አያውቅም ታድያ የኔ ነቢ ይሄ አሽከሮት የዘንድሮው ሃጅ ሊያልፈው ይገባል ትላላችሁ? ምኞታችን ውጥናችንም አንድ ነው ላንቱ ኖሮ ላንቱ መሞት። ታድያ ይሄ አሽከሮት ይማፀናል እንደሌላውም ሰው የዘንድሮውን በጠያራ መምጣት። መቼስ የተጠየቁት ትልቁ ሰው ኖት እሺ እንጂ እንቢ አያውቁምና አስደሱን ሰይዲ።

  አያቴ በናፍቆት ልጁንም ተክቷል:
ከአብሬቷች ሀረም እንባቸውም ፈሷል:
የናፍቆት ደብዳቤ ፅፈው አድርሰዋል:
ቶሎ መፈረጅን ፀንተው ጠይቀዋል:
ዘርም ተተካና የልጅልጅ ከአብዱ ደርሷል:
እሱም በተራው የአባቷቹን አደራ አሁን ተረክቧል:
የዘይንዬን ወዳጅ አብሬቶች ጠይቋል:
የንግስናን ሹመት ከአረንጓዴው ቁባ:
ሀጁንም ዚያራ ሊጠራ ከጠይባ:
በእጅጉ ተጎድቷል ቀንሌት እያነባ:
ከዘይነል ውጁድ ጠይቋ መች አለ ያፈረ:
የኛንም ነገር አርጉልን ያማረ:
ዙልሂጃ ሲመጣ መቆዘም መብሰልሰል:
አደራ ዘንድሮ ከመዲና ጎራ ሰሊ እንበል:
በሀይባ ተሞልቷ በረካ አፍርቷ:
ያሰበው ያቀደው ሁሉ ተሞልቷ:
ከሀበሻ ይድረስ በዊላያ በርቷ።

@abduftsemier
@abduftsemier
👍7
8
Live stream started
Live stream finished (8 minutes)
Live stream started
Live stream finished (9 minutes)
#የሸይኽ_ኢብኑ_ተይሚያ_ደረሳ

   ኢማሙ አዝ-ዘሀቢይ (የሸይኽ ኢብኑ ተይሚያ ተማሪ የነበሩ) ሲየር አዕላም አኑበላእ (10/107) (የደጋጎች የህይወት  ታሪክ) በተሰኘው ኪታባቸው ላይ ስለ ሰይደቲ ነፊሳ ሲናገሩ: "ነፊሳ የተከበረችዋ ሷሊሓ የአሚሩል ሙእሚኒን ሀሰን ቢን ዘይድ ቢን ሀሰን ቢን ዐሊይ (ረዐ) ልጅ የሆነችው... #ዱኣ ቀብሯ ጋር ሙስተጃብ ነው እዛም ብቻ ሳይሆን የአንቢያዎችና የሷሊሆች ቀብር ላይም ሙስተጃብ ነው.. መስጂድ ውስጥ እንዲሁም አረፋና ሙዝደሊፋ ላይም...."

@abduftsemier
@abduftsemier
👍6
@YEFKIR_MENGED join በሉ
Live stream started
Live stream finished (15 minutes)
#ዊርድ

ዊርድ ማለት በየዕለቱ የሚደረግ ውዳሴ ዚክር ሲኾን የጥዋትና የማታ፣ የሙጥለቅ ዚክሮች፣ የቁርኣን ዕለታዊ ንባብንና አጠቃላይ ዚክሮችን በተደራጀ መንገድ መፈጸም ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ስለ ዚክር፣ ሰላዋት እንማር ይኾናል፣ እናስተምርም ይኾናል። ግና ዚክሮቹንና ሰለዋቶቹን ከእኛ በፊት የነበሩ ዐሊሞች ባደራጁት መንገድ አናደርግም። ይህ የተደራጀ ዚክርና ወዚፋ ነው ዊርድ ተብሎ የሚጠራው።

ዋሪዳ ማለት ደግሞ ከአላህ የኾነ የሚወርድ ልዩ ነገር እንደማለት ነው። የቃላት፣የሐሳብ፣ሌሎችም መንፈሳዊ ሥጦታዎችን ኹሉ ያካትታል።

ሰይዲ ኢብኑ አጣእ (ቀ.ሲ) በሂከማቸው ላይ እንዲህ ይላሉ: 'ዊርድ የሌለው ሰው ዋሪዳ የለውም።"

መድረሳ ስናስተምር ከምናተኩራባቸው ነገሮች ዋነኛው ዊርድ ነው። ይህንም በየቀኑ ለ20 ደቂቃ ያህል ነው። የሒፍዝ ትምህርት ቤቶች፣ መድረሳዎችና፣ መሳጂዶች ዚክርና ሰለዋት ላይ ሚዛናቸውን ከፍ አድርገው ያለፉ የሐገራችን ኾነ የውጭ ሐገራት ሊቃውንቶችን አውራድ በማስቀጠል ኢማንን ማደስ ዋሪዳ መጠበቅ ግድ ይላል።

@abduftsemier
@abduftsemier
9👍5
Live stream started
Live stream finished (6 minutes)
Live stream started
Live stream finished (2 minutes)
#እማ_ህይወት

የህይወት ስጦታ የነገ ማንነት:
የዛሬ ምርኩዝ የፍቅር አብነት:
መች ይገኛል ፈፅሞ እንደ እናት:
ሻይ ቡና ስታዞር ዳገት ወጥታ ቁልቁል:
ደከመኝ አላለች ቀን ሌት ስትባትል:
ደሞ መች በቃት ልፋቷ አይሎ:
ከፀሀዩ ንዳድ ጋር ስታበስል በቆሎ:
ለሊት ወጥተሽ ማታ እየገባሽ:
አንድ ቀን በምቾት በድሎት ያልተኛሽ:
ሽታዬ እምዬ በምን ቋንቋ ልጥራሽ:
ለኔ ማማር ሲባል የረገፈ ውበትሽ:
ለኔ ደህንነት ነው የጠፋው ወዘናሽ:
ምርቃሽ ደርሶኝ ሰላም ሁኚ እናቴ:
ባንቺ ውስጥ እንደኖርኩ በኔ ትኖሪ ዘንድ ይባረክ ጉልበቴ:
የእናቱ ቀን አውጪ በወዘናው ጣሪ:
አላህ ይፍቀድና ያድርገኝ የእናቴ ጦሪ:
በደስታ በሀሴት ሁሌ እንድትኖሪ።

*ስለ ውዷ ሽቱ ሀሰን ብዙ ቢባል አያልቅም አላህ ረጅም እድሜ ከአፊያ ጋር ያድልሽ እናቴ።
*አላህ ለታመሙ እናቶች ፈውስ ለሞቱ ጀነት ላሉት ረጅም ሀያት ከአፊያ ይስጥልን!

@abduftsemier
@abduftsemier
👍81
😘2
2
የእናትነት_እናት!
==========

 ስሟ ከምግባሯ በአንድ የተጣመረ:
ለራስ ሳይቀንሱ ለሰው የተኖረ፤
ለድሃ ለምስኪን ሩኅሩኅ ደካማ
ከሌላት ለመስጠት ቅንጣት ማታቅማማ:
የሁሉ መመኪያ የእናትነት አርማ:
የሰውነት ልኬት የልጆቿ ግርማ።

ቀን ሌቱን በሃሳብ ለሁሉ መጨነቅ፣
ትጉህ ብርቱነቷ ዘወትር የማያልቅ፤
በችግር ተሻግራ በፈተና ጸንታ
በመውደቅ፣ በመሰበር ቅንጣት ሳትረታ
ጌታዋን አመስጋኝ በቀንም በማታ።

ከፈጣሪ ቁጣ የመጠበቅ ሚስጥር፣
ብቸኛው የእሷ መሐላችን መኖር
ዕድሜ ከጤና ጋር ደስታንም ለግሷት
አላህ ያቆይልን "የእናትነት እናት!"

@abduftsemier
@abduftsemier
Live stream started
2025/07/14 10:53:31
Back to Top
HTML Embed Code: